ምዕራባውያን ፖለቲከኞች አንዳርጋቸው ጽጌ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቁ

ኢሳት ዜና (ነሐሴ 4፥ 2007)

የአሜሪካ ፤ የብሪታኒያ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት የፖለቲካ አመራሮች አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር እንዲፈቱ ለጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ደብዳቤ መላካቸውን አልጀዚራ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘገበ።

የፖለቲካ አመራሮች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፉት ደብዳቤ አቶ አንዳርጋቸው ለብቻቸው 24 ሰአት የተፈጥሮ ብርሀን በማያገኙበት

ሁኔታ እስር ላይ መሆናቸውን እንደጠቀሱ አልጀዚራ በብቸኝነት ማግኘት ችያለሁ ያለውን መረጃ ዋቢ በማድረግ አስነብቧል።

ለኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄያቸው ያቀረቡት እነዚህ አካላት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የያዙበት ሁኔታ አሳሳቢ እና በሀገሪቱን ከአለም አቀፍ ማህበረሰብ የሚነጥል እንደሆነ ገልጸዋል።

በአሜሪካ የውጪ ጉዳዮች ኮሚቴ አባል እና የካሊፎርኒያ የሪፕብሊካን የምክር ቤት አባል በሆኑት ዳና-ሮህራባቸር  ስም የተፈረመው ይኸው ደብዳቤ የኢትዮጵያ መንግስት በሰብአዊ መብት ላይ የያዘውን አካሄድ በጽኑ መተቸቱን አል-ጀዚራ በሪፖርቱ አትቷል።

የብሪታኒያ ምክር ቤት አባላት ጀርሚ ኮርቢንና ኤሚሊ ቶርቤሪ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት አና ጎሜስ፥ ሪቻርድ ሆዊትና ሌሎች ታዋቂ የፖለቲካ አመራሮች ደብዳቤውን በጋራ መጻፋቸውን ታውቋል ።

ያሉበት ሁኔታና ቦታ የማይታወቀው አቶ አንዳርጋቸው በቤተሰቦቻቸው እንዳይጎበኙ ተደርጎ የሚገኝ ሲሆን በኢትዮጵያ የሚገኘው

የብሪታኒያ ኢምባሲ ተወካዮች እስካሁን ሶስት ጊዜ ብቻ መጎብኘት ችለዋል።

የብሪታኒያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርና የተለያዩ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አቶ አንዳርጋቸው በቤተሰቦቻቸው

እንዲጎበኙና የህግ ምክር አገልግሎት የሚያገኙበት ሁኔታ እንዲመቻች ጥያቄ ቢያቀርቡም በኢትዮጵያ መንግስት በኩል የተወሰደ እርምጃ አለመኖሩን አልጀዚራ በዘገባው አመልክቷል።

1 Comment on “ምዕራባውያን ፖለቲከኞች አንዳርጋቸው ጽጌ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቁ”

  1. You see, these ferenjis are asmesayoch.

    Just two weeks ago obama was in Ethiopia, an insult to Ethiopians, to legitimize the same TPLF that is holding and torturing Andargachew.

    The USA and co. are perpetuating oppression, misery and violence in Ethiopia, and these same ferenjis picked TPLF and brought it to power so that it could commit all those crimes against Ethiopians.

    Those ferenjis are as responsible as TPLF and should be held accountable.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*