ዋ! አንቺ ሳውዲ ምድር!!
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
አይኖቼ በደም ቀሉ። ልቤ ተሰበረ። ከሳዉዲ አረቢያ፣ ከባህር ማዶ፣ የወገኖቼ ጩኸትና ሮሮ፣ ከጣራዬ በታች የመነጨ ይመስል፣ በጆሮዬ በቅርበት ያቃጭላል። በርግጥ እንደ አገር፣ እንደ ሕዝብ ፣ እንደ ኢትዮጵያዊ መዋረዳችንን አየሁ። በተለይም ደግሞ በአሁኗ ሰዓት፣ እንደ ወገን ምንም ማድረግ ባለመቻሌ ዉስጤ ደበነ። የማድርገዉን ሳጣ መሬት ተንበረከኩ። አይኖቼን ወደ ላይ አንስቼ፣ እጆቼን ዘረጋሁ። «ሄሮድስ ሊገድልህ ፈልጎ በነበረ ጊዜ፣ […]
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በሥራ አስኪያጁ ላይ የተላለፈውን የስንብት ርምጃ ውድቅ በማድረግ ወደ ሓላፊነታቸው እንዲመለሱ ለሊቀ ጳጳሱ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡ ይኹንና ትእዛዙ በ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ዘንድ ተቀባይነት አግኝቶ ተፈጻሚ ባለመኾኑ በአሜሪካ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጋራ በሐዋርያዊ ጉብኝት ላይ የሚገኙት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ እየተጠበቁ ነው፡፡ ራሳቸውን ‹‹የሊቀ ጳጳሱ የግል አማካሪ›› ብለው …![]()
ESAT Radio Nov 17
News, Radio Magazine or Mestawot
የኢትዮጵያ መንግሥት የሶማሊያዉ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አሸባብ እና አሸባሪዎች ያላቸዉ ሌሎች ቡድናት ኢትዮጵያ ዉስጥ አደጋ ለመጣል መዘጋጀታቸዉን የሚጠቁም መረጃ ደርሶኛል በማለት ሕዝቡን አስጠንቅቋል።
የራሱዋ አሮባት የሰው ታማስላለች አሉ:: መረበ መራሽ ትግሬዎች are shedding crocodile tears for Ethiopians in Saudi Arabia while their citizens are dying in the Mediterranean sea. ጉድ ነው
ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen
News, Call-in show or special interviews and Ye Musica Qana
የኬንያ እና የሶማልያ መንግሥታት በኬንያ ከለላ ያገኙ ከ500,000 የሚበልጡ የሶማልያ ስደተኞችን ወደ ትውልድ ሀገራቸው ለመመለስ ከተመድ የስደተኞች ጉዳይ ተመልካች መሥሪያ ቤት፣ በምሕፃሩ «ዩ ኤን ኤች ሲ አር» ጋ አንድ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል።
የዓለም ዜና

በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርሰው መከራ መስማት ህሊና መሸከም ከሚችለው በላይ ሆኗል። ኢትዮጵያዊን እህቶቻችን ወንድሞቻችን በአሰቃቂ ሁኔታ እየተገደሉ፤ አካሎቻቸው በስለት እየተቆራረጠ፤ እየተደበደቡና እየተደፈሩ ነው።
ይህ ሁሉ የሚፈፀው በሪያድ፣ ጂዳና አዲስ አበባ የሚገኙ የወያኔ ዲፕሎማቶች መልካም ፈቃድና ሙሉ ተባባሪነት መሆኑ ደግሞ ይበልጥ የሚያንገበግብ ነው። ወያኔ ለአረብ ሀብታም ሸሪኮቹ ለም መሬቶቻችንን ሰጥቶ ኢትዮጵያዊ በአገሩ ሠርቶ የእለት ጉርሱን መሸፈን የማይችልበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ አደረገው። ቀጥሎ ደግሞ በሺዎች የሚቆጠሩ ልጃገረዶችና ወጣት ኢትዮጵያንን እየደለለ ከባርነት ላልተሻለ ግርድና አሳልፎ ሰጣቸው። ይህ ሁሉ ግፍ አልበቃ ብሎ “በሏቸው፤ ቀጥቅጧቸው፤ ህገወጦች ናቸው” እያለ በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ በአጋፋሪነት እያስተናገደ ነው።
በኩየት በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ላይ ተመሳሳይ ሰቆቃ ሊደርስ የሚችል መሆኑ ምልክቶች እየታዩ ነው። በኩዌት ያለአንዳች ምክንያት ቁጥራቸው በአንድ ሺህ በላይ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን በድንገት ከሥራ ተባረዋል። እዚህም የወያኔ እኩይ እጆች እንዳሉት መረጃዎች አሉ። በሌሎች የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንም ሕይወታቸው በዘወትር ስጋት ላይ ወድቋል።
የኢትዮጵያዊያን እጣ ፈንታ በአገር ውስጥም ከአገር ውጭም ሰቆቃና እንግልት መሆኑ የሚያሳዝን ብቻ ሳይሆን የሚያስቆጭ፤ ለመራራ ትግል የሚያነሳሳም ነው። ለአገሩ ሕዝብ የሚቆረቆር መንግሥት ኑሮን ቢሆን ኖሮ ሕይታችን እንዲህ የተመሰቃቀሰ ባልሆነም ነበር።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የሳውዲ አረቢያ እና ሌሎችም የመካከለኛ ምሥራቅ አገራት መንግሥታት ለኢትዮጵያዊያን እህቶቻንና ወንድሞቻችን ሰብዓዊ ክብር እንዲሰጡ አበክረን እናሳስባለን። ሰብዓዊ መብቶችን መድፈር ዓለም ዓቀፍ ወንጀል መሆኑን ልንነግራቸው እንፈልጋለን። በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ አሁኑኑ ይቁም!!! ሰቆቃ ፈፃሚዎች ለፍርድ ይቅረቡ!!!
በተቻለው ፍጥነትና ባገኘነው እድል ሁሉ ተጠቅመን ሕይወታቸው አደጋ ላይ ላሉት ወገኖቻችን እንድንደርስ ግንቦት 7 ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሪ ያደርጋል።
በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ በዘላቂነት የሚወገደው ወያኔ ከሥልጣን ተባሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ የመረጠው መንግሥት ሲያስተዳድር በመሆኑ ለዚህ ታላቅ ግብ በኅብረት እንነሳ።
በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ ይቁም!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
Ethiopian national soccer team – ready for away match with Nigeria’s counter part
Ethiopia, terrorism charges, ginbot 7
Semayawi Party, Medrek,Saudi, Ethiopians, demonstrations
ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz
ህዳር ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሳውድ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ ተባብሶ በቀጠለበት በዚህ ወቅት፣ የሳውዲን መንግስት ለመቃወም በሳውድ አረቢያ ኢምባሲ ፊት ለፊት ተቃውሞዋቸውን ለመግለጽ የወጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በፌደራል ፖሊሶች ተደብድበዋል። ከ100 በላይ ሰዎች ታስረው የነበረ ሲሆን እስከ ምሽት ድረስ 40 የሚሆኑት ተለቀዋል። ሰልፉን ያዘጋጀው የሰማያዊ ፓርቲ 15 የአመራር አካላትም በእስር ላይ …
ላለፉት ሰባት ዓመታት በዐረብ ሀገር የኖረችና ከአራት ወራት በፊት ነዋሪነቷን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገች ወጣት ኢትዮጵያዊት፣ ከኢትዮቲዩብ ጋር ባደረገችው ቃለምልልስ በዐረብ ሀገር የነበራትን ቆይታ፣ በሀገር ቤትም ያለውን ችግር፣ የኢትዮጵያን ኤምባሲ በተመለከተ በግሏ የደረሰባትን ስትገልጽ ልብ ትሰብራለች። ትናንት ኅዳር 5 ቀን 2006 ዓ.ም. (ኖቨምበር 14፣ 2013 እ.ኤ.አ.) ዋሽንግተን ዲሲ በሳዑዲ ዐረቢያ ኤምባሲ በርካታ ኢትዮጵያውያኖች የተቃውሞ ሰልፍ ባደረጉበት ወቅት ነበር ኢትዮቲዩብ ያናገራት።
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት መድረክ ሣዑዲ አረቢያ ውስጥ በኢትዮጵያዊያን ላይ “ተፈፅሟል፣ እየተፈፀመም ነው” ያለውን ግፍ በመቃወም ዕሁድ፤ ኅዳር 8/2006 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል፡፡
የሰልፍ ዕውቅና የሚሰጠው ክፍል ግን በቃል አሉታዊ መልስ እንደሰጠው አስታውቋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ሰማያዊ ፓርቲ ሳዑዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ላይ እየደረሰ ያለውን ችግር በመቃወም የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ፡፡
አዲስ አበባ በሚገኘው የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ አቅራቢያ በተሰባሰቡት ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ “ከፍተኛ ድብደባ፣ እንግልትና እሥር ተፈፅሟል” ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ድርጊቱን አውግዟል፡፡
የአዲስ አበባ አስተዳደር በበኩሉ ለቪኦኤ በሰጠው ቃል ሰልፉ “ሕገወጥ ነው” ብሏል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ አዘጋጆቹ “ከሚመለከተው ክፍል ፍቃድ…
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከፍበኛ መሻሻል ማድረጉ ይታወቃል፡፡ ፈባጠን አካሄድ አፍሪካን አልፎ በቀሪውም ዓለም መድረክ ሊያሣትፈው የተቃረበ ይመስላል፡፡
ነገ፣ ቅዳሜ ኅዳር 7/2006 ዓ.ም ከናይጀሪያ አቻው ጋር በሚያደርገው የመልስ ግጥሚያ አስፈላጊውን ሁሉ አሟልቶ ካሸነፈ በመጭው ሰኔ ብራዚል በምታስተናግደው የዓለም ዋንጫ ውድድር ላይ አህጉሪቱን ከሚወክሉ አምስት የአፍሪካ ብሔራዊ ቡድኖች አንዱ ይሆናል ማለት ነው፡፡
ለዚህ ወሣኝ ፍልሚያ ቡድኑ “ብቃት ያለው ዝግጅት አድርጌአለሁ” ይላል፡፡
ሰሎሞን ክፍሌ የነገው የመልስ ጨዋታ ወደሚካሄድባት የናይጀሪያ ከተማ ካላባ ደውሎ የቡድኑን ዋና አሠልሐኝ ሰውነት ቢሻውንና ሌሎችም የቡድኑን አባላት አነጋግሯል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
ፌደራል አቃቢ ሕግ “የግንቦት ሰባት አባል በመሆን” ና “የሽብር ወንጀል ፈፅመዋል” ሲል በሃያ ሰዎች ላይ ክሥ መሥርቷል፡፡
ሰዎቹ መቼ እንደታሠሩ ግን አልገለፀም፡፡
ጉዳዩ እየታየ ያለው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ሲሆን ተከላካይ ጠበቃ ያቀረበው የክሥ መቃወሚያ በፍርድ ቤቱ ውድቅ ሆኗል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የአንዳንድ ተከሣሾች ጉዳይ በሌሉበት መታየት ጀምሯል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የመለስካቸው አምኃ ዘገባ ያዳምጡ፡፡
News, Community Heroes or Call-in, Crossfire and African Topics
ሐኪሞቹና ረዳቶቻቸዉ አዲስ አበባና ደብደረ ብርሐን ከተሞች በሚገኙት ሆስፒታሎች ዉስጥ በማሕፀን፥ በኩላሊትና በአይን ሕመም ይሰቃዩ ለነበሩ በሺሕ ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን የቀዶ ሕክምና ርዳታ አድርገዋል
አዲስ አበባ ላይ በሳዑድ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ ሊካሄድ የነበረ የተቃዉሞ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ። አሶሲየትድ ፕረስ እንደዘገበዉ ፖሊስ በመቶዎች የሚቆጠሩን ሰልፈኞች ለመበታተን ኃይል ተጠቅሟል።
የዓለም ዜና
ያለንን ችሎታ ማካፈል እንፈልጋለን ይላሉ። ችሎታቸውም እግር ኳስ መጫወት ነው።
ማምሻውን በደረሰን መረጃ
ሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ዜጎቻችን ላይ የደረሰውን በድል እና ስቃይ ለመቃወም አዲስ አበባ በተጠራው ሠላማዊ ሠልፍ የኢትዮጵያ መንግስት ፖሊሶች አሰቃቂ ድብደባና እሰር መፈፀማቸው ቀደም ተብሎ መገለፁ የሚታወቅ ነው፡፡ አሁን በደረሰን መረጃ ቁጥራቸው ወደ 100 የሚጠጉ እስረኞች የተለቀቁ ሲሆን ፤ከነዚህም መካከል ጋዜጠኞች እንደሚገኙበት ለማወቅ የተቻለ ሲሆን የተቀሩት ማለትም፡-
1ኛ. ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የፓርቲው ሊቀ/መ
2ኛ. አቶ ስለሺ ፈይሳ የፓርቲው ም/ት ሊቀ/መ
3ኛ. አቶ ወረታው ዋሴ የፓርቲው የፋይናስ ጉዳይ አላፊ
4ኛ. አቶ ጌታነህ ባልቻ የፓርቲው የአደረጃጀት ጉዳይ አላፊ
5ኛ. አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት አላፊ
6ኛ. አቶ ዮናታን ተስፋዬ የፓርቲው የወጣቶች ጉዳይ አላፊ
7ኛ. አቶ አብታሙ ደመቀ የብሔራዊ ም/ቤት አባል
8ኛ. አቶ ዮናስ ከድር የብሔራዊ ም/ቤት አባል
9ኛ. ዮሴፍ ተሻገር የብሔራዊ ም/ቤት አባል
10ኛ. ወጣት አቤል ኤፍሬም አባል
11ኛ. ሰለሞን ወዳጄ አባል
12ኛ. ፋሲካ ቦንገር አባል
13ኛ. መርከብ ሀይሌ አባል
14ኛ እመቤት ግርማ አባል
15ኛ. አስራት አብርሃም ደራሲና ጻአፊ (በግል)
16ኛ. ዳዊት ፀጋዬ ደራሲና ጻአፊ (በግል)
17ኛ. እየሩስ ተስፋ አባል
18ኛ. ንግስት ወንድኢፍራው አባል
ከላይ በስም ዝርዝ የተገለፁ እስካሁን መስቀል ፍላወርና ፒያሳ ማዘጋጃ አካባቢ በሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙ ሲሆን ከፍተኛ ደብደባ እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ለማወቅ ተችሎአል፡፡ እንዲ አይነቱን ድርጊት ፓርቲው ያስቆጣው መሆኑን እየገለፀ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ እንጠይቃለን፡፡
በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው በደል እና ስቃይ መጠኑ ከመጨመር አልፎ ሕይወትን እስከማሳጣት መድረሱ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህን በደል እና ስቃይ ለመቃወም እና ሀዘናችንን ለመግለፅ በዛሬው ዕለት ማለትም ህድር 6 ቀን 2006 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው በሳውዲ አረቢያ ኢምባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ የተጠራ ቢሆንም በመንግሥት ታጣቂዎች በተወሰደ በአሰቃቂ እርምጃ ሰልፉ ሊካሄድ አልቻለም፡፡
እኛ ኢትዮጵያን በውጭ በሚገኙ ዜጐቻችን ላይ የሚደርሰው በደልና ግፍ እንዲቆም፣ ይህንንም ድርጊት የፈፀሙት ለሕግ እንዲቀርቡና የተጐዱ ዜጐች ተገቢውን ካሳ እንዲያገኙ፤ የኢትዮጵያ መንግሥትም በዜጐቹ ላይ ያሳየውን ቸልተኝነት በአስቸኳይ በማቆም ተገቢ የሆነውን የመንግሥት ኃላፊነት እንዲወጣ ቢጠየቅም፤ ሰልፉ በተቃራኒው በመንግሥት ታጣቂዎች በተወሰደ አሰቃቂ እርምጃ ተጠናቋል፡፡
በሳውዲ እየተፈፀመ ያለውን በደል በመቃወም በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያዊያን ድምፃቸውን በማሰማት ላይ ቢሆኑም እኛ ኢትዮጵያዊያን ግን በገዛ ሀገራችን ድምፃችንን እንኳን እንዳናሰማ ታፍነናል፡፡ በዚህም እንቅስቃሴ ላይ የተሳተፉ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎችና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ከፍተኛ ድብደባ፣ እንግልትና እስር ተፈፅሞባቸዋል፡፡

የመንግሥት ፖሊሶች የራሳቸውን ዜጋ በመደብደብና በማሰቃየት ብሎም በማሰር በሳውዲ በሚገኙ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን በደል ሀገር ውስጥ በሚገኙ ንፁሐን ወገኖቻቸው ላይ ደግመውታል፡፡
ይህ በውሸት ዲሞክራሲ ስም የተደበቀው አምባገነን መንግሥት ሕዝብን ለማሸማቀቅ የወሰደውን እርምጃ ወደ ጐን በመተው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቅድም አያቶቹን በማስታወስ ያስረከቡትን ክብር ከማስመለስ ወደ ኋላ እንደማይል እርግጠኛ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡
ፓርቲያችን እንዲህ አይነቱን የለየለት የመንግሥት ሕገ ወጥ ተግባር ትኩረት ሰጥቶ የሚመለከተው መሆኑን እየገለፅን፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጐናችን እንዲቆም በአፅንኦት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
ህዳር 6 ቀን 2006 ዓ.ም

በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው በደል እና ስቃይ መጠኑ ከመጨመር አልፎ ሕይወትን እስከማሳጣት መድረሱ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህን በደል እና ስቃይ ለመቃወም እና ሀዘናችንን ለመግለፅ በዛሬው ዕለት ማለትም ህድር 6 ቀን 2006 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው በሳውዲ አረቢያ ኢምባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ የተጠራ ቢሆንም በመንግሥት ታጣቂዎች በተወሰደ በአሰቃቂ እርምጃ ሰልፉ ሊካሄድ አልቻለም፡፡
እኛ ኢትዮጵያን በውጭ በሚገኙ ዜጐቻችን ላይ የሚደርሰው በደልና ግፍ እንዲቆም፣ ይህንንም ድርጊት የፈፀሙት ለሕግ እንዲቀርቡና የተጐዱ ዜጐች ተገቢውን ካሳ እንዲያገኙ፤ የኢትዮጵያ መንግሥትም በዜጐቹ ላይ ያሳየውን ቸልተኝነት በአስቸኳይ በማቆም ተገቢ የሆነውን የመንግሥት ኃላፊነት እንዲወጣ ቢጠየቅም፤ ሰልፉ በተቃራኒው በመንግሥት ታጣቂዎች በተወሰደ አሰቃቂ እርምጃ ተጠናቋል፡፡
በሳውዲ እየተፈፀመ ያለውን በደል በመቃወም በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያዊያን ድምፃቸውን በማሰማት ላይ ቢሆኑም እኛ ኢትዮጵያዊያን ግን በገዛ ሀገራችን ድምፃችንን እንኳን እንዳናሰማ ታፍነናል፡፡ በዚህም እንቅስቃሴ ላይ የተሳተፉ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎችና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ከፍተኛ ድብደባ፣ እንግልትና እስር ተፈፅሞባቸዋል፡፡
የመንግሥት ፖሊሶች የራሳቸውን ዜጋ በመደብደብና በማሰቃየት ብሎም በማሰር በሳውዲ በሚገኙ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን በደል ሀገር ውስጥ በሚገኙ ንፁሐን ወገኖቻቸው ላይ ደግመውታል፡፡
ይህ በውሸት ዲሞክራሲ ስም የተደበቀው አምባገነን መንግሥት ሕዝብን ለማሸማቀቅ የወሰደውን እርምጃ ወደ ጐን በመተው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቅድም አያቶቹን በማስታወስ ያስረከቡትን ክብር ከማስመለስ ወደ ኋላ እንደማይል እርግጠኛ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡
ፓርቲያችን እንዲህ አይነቱን የለየለት የመንግሥት ሕገ ወጥ ተግባር ትኩረት ሰጥቶ የሚመለከተው መሆኑን እየገለፅን፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጐናችን እንዲቆም በአፅንኦት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
ህዳር 6 ቀን 2006 ዓ.ም

Getachew=Shiferaw-
በጧቱ ነበር ወደ ወሎ ሰፈር ለማቅናት መንገድ የጀመርኩት፡፡ መሃል ላይ አንድ ስልክ ደረሰኝ፡፡ ‹‹የሰማያዊ ፓር አመራሮችና አባላት ታግተዋል›› የሚል፡፡ ለማረጋገጥ ወደ ቢሮ መሄድ ነበረብኝ፡፡ ቢሮ ስደርስ የአካባቢው ሰዎች ሰብሰብ ሰብሰብ ብለው ስለ ታሳሪዎቹ፣ ሳውዲ ውስጥ ስለሚሰቃዩት ኢትዮጵያውያን፣ ስለሰላማዊ ሰልፉ ያወራሉ፡፡
በርካታ ፖሊሶች በቢሮው አካባቢ ተሰባስበዋል፡፡ ግቢው ውስጥ ግን ማንም የለም፡፡ ቢሮው በር ላይ ሳውዲ ውስጥ ለሚሰቃዩት ወገኖች በምልክትነት የተሰቀለው ጥቁር ምልክት እንዳልተነሳ ስመለከት ፖሊሶቹ ስለ ጉዳዩ እውቀት እንደሌላቸው ገባኝ፡፡ አመራቹን በአንዳች ነገር ከሰው ብቻ እርምጃ እንዲወስዱ ተነግሯቸዋል ማለት ነው፡፡
ከሰዎች መረጃ እያሰባሰብኩ እያለ ሌላ ስልክ ደረሰኝ፡፡ ‹‹ወደ ጃን ሜዳ ፖሊስ ጣቢያ ወስደዋቸዋል›› የሚል ነው፡፡ ወደዛው መሄድ አለብኝ፡፡ አንድ ጓደኛየን አግኝቸው ከእሱ ጋር አመራሁ፡፡ ኤምባሲው ጋር የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ ለመቀላቀል እየረፈደብን ቢሆን ስለ ታሳሪዎቹ መረጃ ማግኘት ነበረብን፡፡
ጃን ሜዳ ፖሊስ ጣቢያ ስንደርስ ኢንጅነሩንና ሌሎች ጥቂት አመራሮችን ከርቀት አየናቸው፡፡ ሌሎቹን አስገብተው እየደበደቧቸውም ይሁን ለሌላ ጉዳይ ውስጥ ገብተው አይታዩም፡፡ ፖሊሶቹ ወደ እኛ ሲመጡ ሳውዲ ኤምባሲ ያለውን ጉዳይ ከመታሰር ብለን ታሳሪዎቹን ከእርቀት ሰላም ብለን ወደ ኤምባሲው እየተቻኮልን አቀናን፡፡
ሰዓቱ እየሄደ በመሆኑ ላንደርስ እንችላለን ብለን ሰግተናል፡፡ በእርግጥ የኢህአዴግ አንዱ ስልትም እንዲህ በተለያዩ ጉዳዮች በመወጠር ዋናውን ነገር ማሳት ነው፡፡ ወሎ ሰፈር አካባቢ ወደ 6 ሰዓት አካባ ስንደርስ ጥቁር የለበሱ ሰዎች ከኤምባሲው አቅጣጫ እየተመለሱ ነው፡፡ ሌላው ህዝብ ደግሞ በየ መንገዱ ዳር ቆሞ ይመለከታል፡፡
ይበልጥ እየቀረብን ስንሄድ የምናውቃቸውን ሰዎች አገኘን፡፡ እስካሁን አልተደበደብኩም የሚል ሰው አላጋጠመንም፡፡ አንዲት ምን አልባትም ሳውዲ ውስጥ የምታውቀው ሰው ጥቃት የደረሰበት ዘመድ ያላት የምትመስል ሴት ስቅስቀስ ብላ ታለቅሳለች፡፡ ሙሉ ጥቁር ልብስ ለብሳለች፡፡ ይህች ሴት እንዲህ የምታለቅሰው ከድብደባው ይልቅ ለዜቾቻችን ክብር ያልተሰጣቸው መሆኑ ነው፡፡
ሌላኛዋ ደግሞ የምታለቅሰው በጣም በመደብደቧ ነው፡፡ አንድ ሌላ ወጣት (ጓደኛየ ጋር ይተዋወቃሉ) ሰላም ካለን በኋላ በየ ቦታው ይቀመጣል፡፡ ምኑን እንደመቱት ስንጠይቀው ኩላሊቱ አካባቢ የተገመደለ አዲስ ቁስል አሳየን፡፡ ልጁ በንዴት ይቁነጠነጣል፡፡
በርካቶች መታሰራቸውን ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የነበሩት ነግረውናል፡፡ አብዛኛው የተበተነው ወጣት እያማረረ ነው፡፡ አንደኛው ‹‹ሰላማዊ ትግል አያስፈልግም›› ይላል፡፡ ለጎኑ ካሉት ክርክር ይገጥመዋል፡፡ ሌላኛው ‹‹ ነገ ኳስ ላይም ቢሆን ይህን ጮከታችን እናሰማለን››፣ ሌላኛው ‹‹እኔ የተደበደብኩት አገሬ ውስጥ ነው ወገኖቹ ሳውዲ ውስጥ እየሞቱ ነው፡፡››፣ ሌላኛዋ ‹‹እሁድም መጥተን መደብደብ አለብ›› ……
እኔም ቢሆን ኢህአዴግ ይፈቅዳል የሚል ተስፋ አልነበረኝም፡፡ ሰማያዊዮች ሲታሰሩም ማረጋገጥ የቻልኩት ይህን ነው፡፡ ግን መታሰርም ሆነ መደብደብ አንድ ነገር ነው፡፡ ይህ ለዜጎቻችንም ሆነ ለራሳችን ያለንን ክብር የምናሳይበት ነው፡፡ ኢህአዴግ ዳግመኛ ከገዳዮቻችን፣ ከጠላቶቻችን ጎን ቆሞ፡፡ ጸረ ህዝብነቱንም አስመሰከረ፡፡
አንዳንዴ ስትደበደብ ወይንም ስትሰታሰር ይወጣልሃል፡፡ እኔ እየዞርኩ ሳይ የዋልኩት የዜጎችን ሰቆቃ ብቻ ነው፡፡ እናም ቅጥል ብያለሁ፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ለመሳተፍ የወጡ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ታሰሩ፡፡ ከጽ/ቤታቸው ተነስተው ወደ ሰላማዊ ሰልፉ ቦታ ሲሄዱ 4 ኪሎ የኦሮሚያ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ጎን በሚገኘው ወታደራዊ ገራዥ መታሰራቸውን ዘጋቢያችን ከቦታው አድርሶናል፡፡ ከመታሰራው ቀደም ብሎ ከፖሊስ ጋር እንሂድ አትሄዱም በሚል ጭቅጭቅ ላይ እንደነበሩ ሰምተናል፡፡ ሌሎች የፓርቲው አባላትና አመራሮች ተበታትነው ወደ ሳውዲ አረቢያ […]
ጥላቻው እያደገ ሔዷል ፣ ሳውዲ አሰሪዎች ኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኞቻቸውን ድሮ ድሮ በአረቦች ዘንድ የተከበርን ፣ የታፈርን የእኛን የሃበሻ ልጆች “ጨካኞች ፣ የማይታመኑ !” እያሉ ጥላቻቸውን መገልጽ ጀምረዋል። November 14,2013 የወጣው አረብ ኑውስ Recent clashes make Saudis wary of Ethiopian maids በሚል ርዕስ ስር ሳውዲ አሰሪዎች ኢትዮጵያን ሰራተኞችን ለማባረር እየዛቱ ነው ! ይህ የአረብ ኒውስ ዘገባ […]
የህግ ባለሙያው ዶ/ር ሸክስፒር ፈይሳ ንግግር ያደርጋል
አሁንም የኢትዮጵያዊያኖች የድረሱልኝ ጥሪ እየተሰማ ነው(ቪድዮዎችን ይመልከቱ)
Ethiopia Zare (ሐሙስ ኅዳር 6 ቀን 2006 ዓ.ም. November 30, 2013)፦ በካናዳ የንግድ መናገሻ በሆነችው ቶሮንቶ ከተማ በሳኡዲት አረቢያ በኢትዮጵያዊያኖች ላይ የሚፈጸመውን ግፍ በመቃወምና በአሰቃቂ ሁናቴ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የሻማ ማብራት ስነስርአት ነገ አርብ እንደሚካሄድ ይፋ ተደረገ።
Ethiopians demonstrate outside Saudi Embassy in Washington, D.C.
Qootcha people in Ethiopia and arrests
Ethiopians returning from Saudi Arabia
ህዳር ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአውሮፓና አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮያውያን በሰልፍ ተቃውሟቸውን ሲገልፁ ውለዋል። በሳዑዲ ዐረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈፀመ ያለው ግፍ ተባብሶ መቀጠሉን ተጠቂዎቹ ለኢሳት ገለፁ። በሪያድ ወደማጎሪያ ካምፕ ውስጥ የተወሰዱ ኢትዮጵያውያን ካሉበት ስፍራ ሆነው ለ ኢሳት በስልክ እንደገለፁት፤ በትናንትናው ዕለት ብቻ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በከባድ መኪናዎች እየተጫኑ ወዳልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል። ስደተኞቹ-ለሳዑዲ ፖሊሶች፦” ወደ …
ህዳር ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህዳር እና የታህሳስ ወራትን በሙሉ በጾም በጾሎት ምእመኑ እግዚኦታ እንዲያሰማ ቄስ አለሙ ሺጣ የኢትዩጵያውያን ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ዋና ጽሓፊ በአምላክ ስም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በኢትዩጵያ በአሁኑ ስዓት እየተሰተዋለ ላለው ችግር ፣በምስራቅ አፍሪካ እና በአፍሪካ ሐገራት እንዲሁም በአለም ለሚታየውና ለሚሰማው በደል- ሀይማኖቱ በሚጠይቀው ስርዓት እጆችን ወደ አምለክ እንድናነሳ እና እንድናለቅስ …
ህዳር ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሸንጎው ከፍተኛ የአመራር ምክርቤትቅዳሜ ጥቅምት 29፣ 2006 ባደረገው ስብሰባ በሳዑዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ በሀገሪቱመንግስት የጸጥታ ሀይሎችእየደረሰ ያለውን ህገወጥ እስራት፣ድብደባና ስቃይ በታላቅ ሀዘንና አንክሮ እንዳጤነው ገል ል። ሸንጎው ለዚህ ግፍ ሰለባዎችና ለቤተሰቦቻቸው የተሰማውን ሀዘን በመግለጽ ከጎናቸው እንደሚቆምምአረጋግጧል። በተመሣሳይ የ ኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ ( ኢህአፓ) ሳውዲ አረብያ በዜጎቻችን ላይ …
በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎቹ ወደሀገራቸው እየተመለሱ መሆኑን የገለፀው የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናቱም ከሳዑዲ አቻዎቻቸው ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸውን አስታውቋል።
በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ አምባሣደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ የተመራ የልዑካን ቡድን ወደ ሪያድ መጓዙ ተገልጿል፡፡
ሰሞኑን መግለጫ እያወጡ ያሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን መንግሥት ለእርምጃው ዘግይቷል፥ የበለጠ ሥራም ይጠብቀዋል ይላሉ።
በጉዳዩ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ለነገ ጥሪ የበተነው መኢአድ የሌሎች አንዳንድ ሃገሮች ዜጎች መብቶች ከኢትዮጵያዊያኑ በተሻለ ሁኔታ እንደሚጠበቅና በኢትዮጵያዊያን ላይ ግፍ ሲደርስ ግን የአሁኑ የመጀመሪያ አለመሆኑን የድርጅቱ ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሃሪ አመልክተዋል፡፡
ዛሬ መግለጫ ያወጣው ሰማያዊ ፓርቲ ደግሞ ነገ ዐርብ፣…
“የወገን ደራሽ ወገን ነው” በሚል መሪ ቃል የተጠራ የኢትዮጵያዊያን ሰልፍ ዛሬ፣ ኅዳር 5 / 2006 ዓ.ም ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የሣዑዲ አረቢያ ኤምባሲ ደጃፍ ላይ ተካሂዷል፡፡
በሰልፉ ላይ በርካታ ኢትዮጵያዊያን የተገኙ ሲሆን ሣዑዲ አረቢያ ለሚገኙ ወገኖቻቸው ጥበቃ እንዲደረግ፣ ሰብዓዊ መብቶቻቸው እንዲከበሩ፣ በአፋጣኝ ወደ ሃገራቸው የሚመለሱበት ሁኔታ እንዲመቻች ጠይቀዋል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በቁጫ ወረዳ፥ ከ 20 በላይ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል። ከ 100 በላይ ተማሪዎች፥ መምህራንና አርሶ አደሮች መታሠራቸውም ይነገራል።
ከወረዳው ባለሥልጣናት ጉዳዩን ለማጣራት ባባለፉት ሁለት ቀናት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
መለስካቻው አምሃ ተከታዩን ከአዲስ አበባ ልኳል።
በሐረሪ ክልል ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሰብል ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ። የአካባቢዉ ገበሬዎችና ኗሪዎች ለዶይቼ ቬለ እንደገለፁት በማሳ ላይ ያለ የስንዴና ገብስ ሰብል እየረገፈ፤ አንዳንዱ ሰብልም ማሳላ እያለ መልሶ በቅሏል።
በሌሎች ሐገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች እየተበደልን ነዉ ይሉ ይዘዋል።ስደተኞቹ እንደሚሉት የየሐገሩ ባለሥልጣናት ያስሯቸዋል፥ ያንገላቷቸዋል፥ ያስፈራሯቸዋል፥ ቀለል ሲል ደግሞ ጉቦ ይጠይቋቸዋል።በየሥፍራዉ ለሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ለዓለም አቀፍ የርዳታ ድርጅቶች በየጊዜዉ አቤት ቢሉም እስካሁን የረዳቸዉ የለም
ኮብለር የሌሎች አማፂ ቡድናት አባላትም ትጥቃቸዉን እንዲፈቱ ጠይቀዋል።ትጥቅ ካልፈቱ ግን ዓለም አቀፉ ጦር በሐይል እንደሚያስፈታቸዉ ዝተዋል።ይሁንና የኪንሻሳና የካምፓላ ባለሥልጣናት አዲስ እሰጥ አገባ መግጠማቸዉ ምሥራቃዊ ኮንጎ «ዘላቂ ሠላም» ለማስፈን የተለፋዉን ሁሉ መና እንዳያስቀረዉ እያሰጋ ነዉ።
የዕለቱ ዜና
For me, the people of Kingdom of Saudi Arabia and #Ethiopia are two people with the same behavior. Especially, until the former have gotten the oil to become rich. Both are religious people who lived under series of regimes that used religion as a t…