አራት መቶ ተመላሾች ዛሬ ከሣዑዲ አዲስ አበባ ገቡ፤ ሰማያዊ ለዓርብ ሰልፍ ጠርቷል
በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎቹ ወደሀገራቸው እየተመለሱ መሆኑን የገለፀው የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናቱም ከሳዑዲ አቻዎቻቸው ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸውን አስታውቋል።
በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ አምባሣደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ የተመራ የልዑካን ቡድን ወደ ሪያድ መጓዙ ተገልጿል፡፡
ሰሞኑን መግለጫ እያወጡ ያሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን መንግሥት ለእርምጃው ዘግይቷል፥ የበለጠ ሥራም ይጠብቀዋል ይላሉ።
በጉዳዩ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ለነገ ጥሪ የበተነው መኢአድ የሌሎች አንዳንድ ሃገሮች ዜጎች መብቶች ከኢትዮጵያዊያኑ በተሻለ ሁኔታ እንደሚጠበቅና በኢትዮጵያዊያን ላይ ግፍ ሲደርስ ግን የአሁኑ የመጀመሪያ አለመሆኑን የድርጅቱ ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሃሪ አመልክተዋል፡፡
ዛሬ መግለጫ ያወጣው ሰማያዊ ፓርቲ ደግሞ ነገ ዐርብ፣…