የኢሕአዴግ መንግሥት አሳምሮ ይፈራል!
===========
በኃይሉ አርአያ (ዶ/ር) – የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት አባል

ሰሞኑን የኢሕአዴግ መንግሥት ይፈራል አይፈራም የሚል ጉዳይ ከፓርላማ ተነስቶ ወደ መገናኛ ብዙኃንም ደርሷል። ጉዳዩ የተነሳው የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ አዲሱ ፕሬዚዳንታችን በፓርላማ ያደረጉትን ንግግር አስመልክቶ

ባቀረቧቸው የማማሻሻያ ሐሳቦችና ጠቅላይ ሚኒስትራችን በሰጡት ምላሽ ዙሪያ ነው። ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዝ ሪፖርተር ጋዜጣ ጥቅምት 13 ቀን 2006 ዓም በአወጣው ዕትሙ ‹‹’ፈሪ’ መንግሥት?›› በሚል ርዕስ ጋዜጠኛ የማነ ናግሽ ጥሩ ትንተና አቅርቧል። የፍርኃት ነገር ከተነሳ ጋዜጠኛው ያነሳውን ለማዳበር በእኔም በኩል የምለው አለኝ። የኢሕአዴግ መንግሥት አሳምሮ ይፈራል። የኢሕአዴግ መንግሥት አሳምሮ ይፈራል ስል ግን በደፈናው አይደለም። በርካታ የማይፈራቸው ነገሮች አሉ። ለምሳሌ ጦርነትን አይፈራም። በተለይ ሕወሓት/ኢሕአዴግ ጥርሱን ነቅሎ ያደገበት ጉዳይ ነው። ሕግ መጣስን አይፈራም። ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን መጣስን አይፈራም። መዋሸትን አይፈራም።

የኢሕአዴግ መንግሥት ይፈራል ስል በተለይ የማተኩረው በአንድ ጉዳይ ላይ ነው። እውነት ላይ። የኢሕአዴግ መንግሥት እውነትን ይፈራል። እውነትን ስለሚፈራ እሱ ራሱ በሚፈልገው መንገድ እንዲታወቅ ከሚፈልገው ውጪ ሕዝቡ እውነቱን እንዲያውቅ አይፈልግም። ይህ ደግሞ የአምባገነን አውራ ፓርቲዎች መንግሥታት አንዱና ዋናው የደባቂነትና የሸማቂነት መገለጫ ባህሪ ነው። የኢሕአዴግ መንግሥት እውነትን ለመፍራቱ በርካታ ማስረጃዎችን መጥቀስ ይቻላል። ለጊዜው ግን አራቱን ብቻ በምሳሌነት እንደሚከተለው ልጥቀስ።

1. ከቅርቡ የሶማሊያ ጦርነት ጋር በተያያዘ የእውነት መረጃን ከሕዝብ መደበቁ

እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጎረቤት ሶማሊያ ውስጥ ገብቶ ከአክራሪና ከሽብር ኃይሎች ጋር ተዋግቷል። እኔ እስከሚገባኝ ድረስ አሁንም እየተዋጋ ነው። ከማን ጋር ነው የተዋጋውም ሆነ የሚዋጋው? ለምንድን ነው የተዋጋው/የሚዋጋው? ጣልቃ ገብነቱ ሕጋዊ ነው አይደለም? ወደሚሉት ውስብስብ ጥያቄዎች አልገባም። እኔ የምገባው ወደ እውነት መረጃ አስፈላጊነት ነው። ጦርነት ነውና ወታደሮች ሞተዋል፣ ቆስለዋል። ገንዘብ ወጪ ሆኗል። የሞቱት የሕዝብ ልጆች ናቸው። ወጪ የሆነው የሕዝብ ገንዘብ ነው። ጦርነቱ የተካሄደው በውጭ ዕርዳታ ገንዘብ ነው እንዳልል፣ ነፍሳቸውን ይማርና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትራችን አቶ መለስ ዜናዊ ጦርነቱን በተመለከተ ፓርላማ ፊት በመቅረብ የአውራ ጣታቸውንና የሌባ ጣታቸውን ጫፎች አነካክተው ዜሮን በማሳየት ‹‹ሳንቲም ዕርዳታ አላገኘንም›› ማለታቸውን አስታውሳለሁ።

የሞቱት የሕዝብ ልጆች ናቸውና የኢትዮጵያ ሕዝብ ስንት ልጆቹ እንደሞቱ እውነቱን ለማወቅ ይፈልጋል። እውነቱን የማወቅ መብትም አለው። የወጣው የሕዝብ ገንዘብ ነውና ሕዝቡ ያወጣውን ለማወቅ ይፈልጋል። እውነቱን የማወቅ መብትም አለው። እኔ እስከማውቀው ድረስ በተለይ በእነዚህ ሁለት ጉዳዮች ላይ የኢሕአዴግ መንግሥት የጉዳዩ ባለቤት ለሆነው ሕዝብ በይፋ የሰጠው መረጃ የለም። ምናልባት ለአሜሪካ፣ ለአፍሪካ ኅብረትና ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ‹‹እኔ እንደ መንግሥት እየከፈልኩ ያለሁትን መስዋዕትነት ዕወቁልኝ›› በሚልና የባለውለተኛ ወሮታ ለማግኘት በሚስጥር አሳውቆ ሊሆን ይችላል። ይህ መደረጉ አይከፋም። መጀመሪያ መስማት ያለበት ግን ባለጉዳዩ ሕዝብ ነው። ለምንድን ነው ባለፈው እውነታውን ለሕዝብ ያላሳወቀውና አሁንም ቢሆን የማያሳውቀው? እውነትን ስለሚፈራ ነው። መደበቅና መሸመቅ ዓይነተኛ ባህሪው ስለሆነ ነው። ለሕዝብ የማወቅ መብት አክብሮት ስለሌለው ነው።

ጦርነቱን በበጎ ጎኑ አይተነው፣ ሠራዊታችን ሶማሊያ የገባው ሉዓላዊነታችንን ላለማስደፈር፣ ድንበራችንን ለማስከበር፣ የአገራችንንና የአካባቢያችንን ሰላም ለመጠበቅና ከዚያም ባለፈ የዓለማችንን ሰላም ለማስከበር ለሚደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማድረግ ነው እንበል። ታዲያ እንደዚህ ላለ ‹‹የተቀደሰ›› ዓላማ የተከፈለን መስዋዕትነት የኢትዮጵያ ሕዝብ ቀርቶ ዓለም እንዲያውቀው ይደረጋል እንጂ ይደበቃል?

ይህን አጭር ጽሑፍ ለማዘጋጀት ሳስብ እስቲ አሜሪካ በቪየትናም ጦርነት የሞቱባትን ወታደሮች ለሕዝብ በይፋ አሳውቃ እንደሆነ ልይ ብዬ ኢንተርኔት ውስጥ ገባሁ። “Us Soldiers Killed in Vietnam” በሚል ‹‹ጉግል›› ሳደርግ ያገኘሁት መረጃ ብዛትና ዝርዝር የሚገርም ነው። በአጭሩ ግን 58,220 ወታደሮች እንደሞቱ፣ የሟቾቹ ቁጥርም በዘር፣ በፆታ፣ በሃይማኖት፣ በመጡበት ‹‹ስቴት››፣ በሠራዊት ምድባቸው (አየር ኃይል፣ ምድር ጦር፣ መርከበኛ፣ ወዘተ.)፣ በአሟሟታቸው ሁኔታ (በውጊያ፣ በድንገተኛ አደጋ፣ በሕመም፣ እርስ በርስ መገዳደል፣ ወዘተ.)፣ በጦርነቱ መጀመሪያ የሞተ ወታደር ስም፣ ጦርነቱ ሊፈጸም ሲል በመጨረሻ የሞተ ወታደር ስም፣ ወዘተ፣ ተዘርዝሮ ተቀምጧል። በተመሳሳይ ሁኔታ የኢራቅንና የአፍጋኒስታንንም አየሁ። መረጃው ከሞላ ጎደል በታመሳሳይ ሁኔታ ተቀምጧል። ወጪ የሆነው የገንዘብ መጠን ሁሉ ተቀምጧል። ከዚያ በኋላ እስቲ መንግሥታችንም ምናልባት ሳናውቀው መረጃ አስቀምጦ እንደሆን ብዬ ለማየት ሞከርኩ። የውጭ ጋዜጦችና ሌሎች የዜና ምንጮች በዜና መልክ ካስቀመጧቸው ጥቂት ተባራሪ መረጃዎች በስተቀር ምንም ነገር የለም።

ለምንድን ነው የአሜሪካ መንግሥት ከላይ የተጠቀሱትን ጦርነቶች በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ለሕዝቡና ለተቀረው ዓለም ሲሰጥ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በሶማሊያ ያካሄደውን ጦርነት በተመለከተ መረጃ ትንፍሽ ያላለው? ይህን ጥያቄ በአግባቡ ለመመለስ ብዙ ማለት ይቻላል። በአጭሩ ግን የአሜሪካ መንግሥት መረጃ የሰጠው እውነትን ስለማይፈራ ነው። በራሱ ስለሚተማመንና ሕዝቡንም ስለሚያምን ነው። የሕዝቡን መረጃ የማግኘት መብት ስለሚያከብር ነው። የኢሕአዴግ መንግሥት መረጃ ያልሰጠው በእኔ እምነት እውነትን ስለሚፈራ፣ በራሱ ስለማይተማመንና ሕዝቡንም ስለማያምንና መረጃ የማግኘት መብቱንም ስለማያከብር ነው።

በዲሞክራሲ የዳበሩ መንግሥታት ምንጊዜም እውነትን አይፈሩም፣ አይደብቁም፣ አይሸምቁም ማለቴ አይደለም። አልፎ አልፎ እውነትን ይፈራሉ፣ ይደብቃሉ፣ ይሸምቃሉ። ሆኖም እውነትን መፍራት፣ መደበቅና መሸመቅ እንደ አምባገነን መንግሥታት ዓይነተኛና መገለጫ ባህሪያቸው አይደለም። ከሁሉም በላይ ደግሞ በእነዚህ አገሮች ውስጥ ጠንካራ ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ ነፃና ጠንካራ ፕሬስ፣ ነፃና ጠንካራ ሲቪክ ማኅበራትና ንቃተ ህሊናው የዳበረና ለመብቱ ቀናዒ የሆነ ሕዝብ ስላሉ እውነትን የሚፈራ፣ የሚደብቅና የሚሸምቅ መንግሥት ይዋል ይደር እንጂ ይጋለጣል። የአሜሪካው የዋተርጌትና የቢል ክሊንተን-ሞኒካ ለዊንስኪ ቅሌት እንዲሁም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጁሊያን አሳንጅና በኤድዋርድ ስኖውደን እንዲሁም በሌሎች ንቁና ተቆርቋሪ ዜጎች አማካይነት እየጎላ የመጣው የመረጃ ፍልፈላና ፍትለካ የዚህ አንድ ማስረጃ ነው። በዚህም ምክንያት ዲሞክራሲያዊ መንግሥታት እውነትን ከመፍራት፣ ከመሸመቅና ከመደበቅ ድርጊት በተቻላቸው መጠን ይቆጠባሉ። በአምባገነን ሥርዓት ግን የመንግሥት ፕሬስ አድር ባይ በመሆኑ፣ ነፃው ፕሬስ፣ ተቃዋሚዎችና ሲቪክ ማኅበራት ደካሞች በመሆናቸው፣ ሕዝቡም የታፈነና በፍርኃት ድባብ ውስጥ የሚኖር በመሆኑ መረጃ የመፈልፈልና እንዲያፈተልክ የማድረግ አቅም ያንሳቸዋል። ስለዚህ መንግሥት በእነዚህ ኃይሎች ድክመት ምክንያት በማናለብኝነት እንደፈለገው ይሆናል፣ እንደፈለገው ያደርጋል።

2. የመንግሥት መገናኛ ብዙኃንን በሞኖፖል መያዙ

የኢሕአዴግ መንግሥት እውነትን የሚፈራ ለመሆኑ ሌላው ዋና ማስረጃ በሕዝብ ገንዘብ የሚሠሩ መገናኛ ብዙኃንን (ጋዜጣ፣ ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን) በሞኖፖል መያዙ ነው። በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 29 ንዑስ አንቀጽ 4 ላይ ‹‹ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች፣ ሐሳቦችና አመለካከቶች በነፃ መንሸራሸራቸውን ለማረጋገጥ ሲባል ፕሬስ በተቋምነቱ የአሠራር ነፃነትና የተለያዩ አስተያየቶች የማስተናገድ ችሎታ እንዲኖረው የሕግ ጥበቃ ይደረግለታል፤›› ይላል። በተጨማሪ በዚሁ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ 5 ‹‹በመንግሥት ገንዘብ የሚካሄድ ወይም በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያለ መገናኛ ብዙኃን የተለያዩ አመለካከቶችን ለማስተናገድ በሚያስችል ሁኔታ እንዲመራ ይደረጋል፤›› ይላል። የኢሕአዴግ መንግሥት እውነትን ከመፍራቱ የተነሳ በእነዚህ ንዑሳን አንቀጾች ውስጥ የተካተቱ መሠረታዊ መብቶች ፍርክስክሳቸውን አውጥቶታል። ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች፣ ሐሳቦችና አመለካከቶች በነፃ መንሸራሸራቸውን ይፈራል። እውነትን ይፈራል። ለዲሞክራሲ ሥርዓት መልካም አሠራር ሲባል የተለያዩና ጥርስ ያላቸው አስተያተቶች ማስተናገድን ይፈራል። ከመፍራቱ የተነሳ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃንን ዘግቶ ይዟል።

አልፎ አልፎ የተለያዩ አስተሳሰቦችን ያቀረበ ለማስመሰል በቤት ልጆች እዚያው ተፈጭተው፣ እዚያው ተቦክተው፣ እዚያው ተጋግግረው የሚቀርቡ ፕሮግራሞችን ያይራል (Air) ያደርጋል። በምርጫ ሰሞንም ነፃነት ያለ ለማስመሰል የሚዲያ በሩን ለስሙ ገርበብ አድርጎ በመክፈት የተለያዩ ሐሳቦች ይቀርባሉ ለማስባል ይሞክራል። በዚህም ቢሆን የቀረቡ ሐሳቦችን በቅድሚያ ቀርፆ የሚፈራቸውን ሐሳቦች ቆርጦ (ሳንሱር አድርጎ) ነው የሚያቀርበው። በጋዜጣና በሬዲዮ የሚቀርቡ ሐሳቦችን ደግሞ ‹‹ይህን ካላስወጣችሁ››፣ ‹‹ይህን ካላስተካከላችሁ›› እያለ በቅድሚያ ሳንሱር የማያላውስ እንቅፋት ይፈጥራል። እንደ እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት አካሄድ ከሆነ፣ እንዲሁም በጎረቤትና በሩቅ አገሮችም እንደሚታየው ከሆነ ብዙ የግልና ነፃ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ጣቢያዎች እንዲሁም ጋዜጦች መኖር ነበረባቸው። የመንግሥት የሚባል ቴሌቪዥንም ሆነ ሬዲዮ መኖር አልነበረበትም። ትላልቅ የሚባሉ፣ በዲሞክራሲ የዳበሩና በራሳቸው የሚተማመኑ አገሮች የቴሌቪዥንም ሆነ የሬዲዮ ጣቢያዎች የሏቸውም። (ያሏቸው የሉም ማለት ግን አይደለም)። የእኛ መንግሥት ግን ሲጀመርም እውነተኛ ዲሞክራሲ የሚባል ነገር ስላልተዋሀደው፣ እንዲሁም በግል ቴሌቪዥና በግል ሬዲዮ ጣቢያዎች ሊንሸራሸሩ የሚችሉ እውነታዎችን ስለሚፈራና እውነትን በእውነት ለመጋጠም ችሎታውም፣ ድፍረቱም ስለሌው እነዚህ ተቋማት እንዳይኖሩ ከልክሏል። ተረጋግተው፣ በነፃነታቸው ተማምነው የሚሠሩ ነፃ ጋዜጦችም የሉም ማለት ይቻላል። ስለዚህ ሥራዬ ብሎ የመረጠው መንገድ የመንግሥት የመገናኛ ብዙኃንን የሕዝብን የተለያየ መረጃ የማግኘት መብትን በሚፃረር ሁኔታ በሞኖፖል በመያዝ እሱ የመረጠውን እውነታ ብቻ፣ እሱ በመረጠው ጊዜና መንገድ ለሕዝብ ማንቆርቆር ነው። የዚህ ዓይነት መንገድ የፍርኃት አካሄድ ነው።

ጽጌረዳና ዲሞክራሲ አንድ ናቸው። ጽጌረዳ አበባዋ ውብ ነው። ከውብ አበባዋ ጋር ግን እሾህ አላት። እሾሁ የተፈጠረው ለክፉ ነገር አይደለም። የአበባዋን ውበት ከጉዳት የሚጠብቅ የተፈጥሮ መከላከያ ነው። እሾሁም የውበቷ አካል ነው። ስለዚህ ጽጌረዳን ስንወድ የተፈጥሮዋ አካል ከሆነው ከእሾህዋ ጋር ነው። ዲሞክራሲም ‹‹እሾህ›› አለው። የዲሞክራሲ ‹‹እሾህ›› ነፃነቱ፣ ሙያዊ ብቃቱና ትጋቱ ካለው ፕሬስ፣ ብቃቱና ቁርጠኝነቱ ካላቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ነፃነቱና ጥንካሬው ካላቸው ሲቪክ ማኅበራት፣ ንቃቱ ካላቸው ዜጎች የሚሰነዘሩ ገንቢና ሂሳዊ እውነታዎች ናቸው። የኢሕአዴግ መንግሥት ከእነዚህ አቅጣጫዎች የሚመጣውን እሾህ ስለሚፈራ እውነተኛ ዲሞክራሲን በሩቁ ብሏል።

3. ኢትዮ ተሌኮምን በሞኖፖል መያዝ

ቴሌኮሙዩኒኬሽን በዘመናዊ መልኩ ቴክኖሎጂ የወለደው የእውነት መረጃ መንሸራሸሪያ ጎዳና ነው። በሌላው ዓለም እንደ ፀጋና እንደ ልማት መሣሪያ ሲወሰድ በአምባገነን ሥርዓቶች ግን እንደ አደገኛ መሣሪያ ይወሰዳል። በዚህ ምክንያትም በአገራችንም ይህን ‹‹አደገኛ›› መሣሪያ ለመቆጣጠር ሲባል መንግሥት በሞኖፖል ይዞታል። መንግሥት እንደሚለው ኢትዮ ቴሌኮምን በሞኖፖል የያዘው ለልማት የሚውል ከፍተኛ የገንዘብ ምንጭ (‹‹የምትታለብ ላም››) ስለሆነ ብቻ አይደለም። የመረጃ መንሸራሸሪያ ጎዳናና የእውነት ምንጭ ስለሆነ ነው። እንዲያውም የኢሕአዴግ መንግሥት ኢትዮ ቴሌኮምን በሞኖፖል ለመያዙ ዋናው ምክንያት የከፍተኛ ገንዘብ ምንጭ ከመሆኑ ይልቅ የመረጃ መንሸራሸሪያ፣ የሕዝብ መገናኛና የእውነት ምንጭ የመሆኑ ፍራቻ ነው ብዬ አምናለሁ። የኢሕአዴግ ምንግሥት መረጃ ኃይል የመሆኑን እውነታ ጠንቅቆ ያውቃል። ይህንን እውነታ ይፈራል።

4. በአሳሪና አስፈሪ ሕጎች ራሱን ማጠሩ

የኢሕአዴግ መንግሥት ዙሪያውን በአስፈሪና አሳሪ ሕጎች በማጠር የእውነት ፍርኃቱን ለመቀነስ ይሞክራል። የእውነት መምጫ መንገዱ ብዙ ነው። ለምሳሌ በነፃ ፕሬስ አማካይነት ይመጣል። በጠንካራ ሲቪክ ማኅበራት አማካይነት ይመጣል። የጠያቂነትና የለምን ባይነት መንፈስ ባላቸው ዜጎች አማካይነት ይመጣል። እውነትን የሚፈራው የኢሕአዴግ መንግሥት አንዱ ዋነኛ ሥራው ሆኖ የተገኘው የእውነት መንገዶችን የሚዘጉ አስፈሪና አሳሪ አዋጆችን ማውጣት ነው። ነፃው ፕሬስ የእውነት መምጫ መንገድ እንዳይሆን በአሳሪና አስፈሪ የፕሬስ አዋጅ ታጥሯል። ሲቪክ ማኅበራት የእውነት መምጫ መንገዶች እንዳይሆኑ በሲቪክ ማኅበራት አዋጅ ታስረው እንዲሽመደመዱ ተደርገዋል። የጠያቂነትና የለምን ባይነት መንፈስ ያላቸው ዜጎች የእውነት መንገድን እንዳያሳዩ በሽብር ሽፋን በፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ እንዲሸማቀቁ ተደርገዋል። ከዚያም ባለፈ ወደ ወህኒ እንዲወርዱ የተደረጉም አሉ።

ኢትዮጵያ የሽብርተኝነት ሥጋት የለባትም ማለት አይደለም። የፀረ ሽብርተኝነት ሕግ ስታወጣም የመጀመሪያ አገር አይደለችም። ሌሎች አገሮችም አውጥተዋል፣ በተለይ በዲሞክራሲ የዳበሩ አገሮች። ትልቁ ጥያቄ ‹‹የወጣው ፀረ ሽብር አዋጅ በማን እጅ ነው? በምን ዓይነት መንግሥት እጅ ነው?›› የሚለው ነው። በዲሞክራሲ በዳበሩ አገሮችና በእኛ አገር ያለው ሁኔታ የሰማይና የምድር ያህል ይራራቃል። በዲሞክራሲ የዳበሩ መንግሥታት ራሳቸው የዜጎቻቸው መብቶች እንዳይነኩ በከፍተኛ ደረጃ የሚጨነቁ፣ የሚጠበቡና የሚጠነቀቁ ናቸው። አርባ ዓመት ለመግዛት ዕቅድ በማውጣት ቸክለው የተቀመጡና ሥልጣናቸውን ለመከላከል ከፀሐይ በታች ባለ በማንኛውም ዓይነት ስልት ከመጠቀም ወደ ኋላ የማይሉ አይደሉም። የፍትሕ ተቋሞቻቸው ነፃ ናቸው፣ የአስፈጻሚ አካላት ትእዛዝ ፈጻሚዎች አይደሉም። ፖሊሶቻቸውና የደኅንነት ሰዎቻቸው በከፍተኛ ደረጃ የሠለጠኑ፣ የዜጎችን ሰብዓዊ መብቶች የሚያከብሩ፣ ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ሕግን በሚገባ የሚያውቁና የሚያከብሩ ናቸው። ስንዝር ሥልጣን ሲሰጣቸው ክንድ የሚወስዱ አይደሉም። ፀረ ሽብር አዋጆቻቸውም በአመዛኙ የሚያተኩሩት ከውጭ በሚመጡ አደጋዎች ላይ ነው። በእኛ አገር በአሁኑ ጊዜ የአዋጁ ዋና ሰለባ የሆኑት በአመዛኙ የአገሪቱ ዜጎች ናቸው። ስለዚህ የኢሕአዴግ መንግሥት በፀረ ሸብር ሽፋን አዋጁን ተቃዋሚዎችንና የጠያቂነትና የለምን ባይነት መንፈስ ያላቸውን ዜጎች ለማጥቃትና በአጠቃላይ ሕዝቡን ለማሸማቀቅና ለማሸበር በመሣሪያነት ይጠቀምበታል የሚል ከፍተኛ ሥጋት አለ።

የኢሕአዴግ መንግሥት አፈ ቀላጤዎች ‹‹የፀረ ሸብር ሕጉን የሚፈሩት ሕገወጦች ብቻ ናቸው›› ይሉናል። አዎ፣ እውነት ነፃ በምታወጣበት አገር አባባሉ ያስኬዳል። በእኛ አገር ግን እውነት ነፃ ታወጣለች ብሎ መተማመን አይቻልም። በዚህ ምክንያት ንፁኃን ዜጎችም ፀረ ሽብር ሕጉን ይፈራሉ፣ ሽብርተኞች ሆነው ግን አይደለም። ዜጎች ሽብርተኝነትን ያወግዛሉ። የሚፈሩት የኢሕአዴግ መንግሥት አዋጁን እንደሚፈልገውና እንደሚያመቸው በመለጠጥ ያለ ኃጥያታችን ሊወነጅለንና ሊጎዳን ይችላል ከሚል ሥጋት በመነሳት ነው። ሥጋታቸው ደግሞ ያለመሠረት አይደለም። እንግዲህ የኢሕአዴግ መንግሥት ከነፃው ፕሬስ፣ ከነፃና ጠንካራ ሲቪክ ማኅበራት እንዲሁም የጠያቂነትና የለምን ባይነት ባህሪ ካላቸው ዜጎች የሚመጣ እውነትን ለመከላከል በተደራራቢ አዋጆች ዙሪያውን አጥሯል። ይህ ደግሞ እውነትን ለመፍራቱ ግልጽ ማሳያ ነው። ለመሆኑ የኢሕአዴግ መንግሥት እውነትን መፍራትና መበርገግ የጀመረው ከመቼ ጀምሮ ነው? መፍራት የጀመረው እውነትን ፊት ለፊት ያየ ዕለት ነው። ያ ዕለት ደግሞ ሚያዝያ 30 ቀን 1997 ዓ.ም. ነበር። በዚያን ዕለት ያየውን እውነት በሳምንቱ ግንቦት 7 ቀን 1997 ደግሞ አየው። ይህ ዕለት ደግሞ በምርጫ ቦርድ ውሳኔ ሳይሆን በሕዝብ ድምፅ መሸነፉን የተረዳበትና ይበልጥ የበረገገበት ዕለት ነበር። የአቶ መለስ ዜናዊ የግንቦት 7 ምሽት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም የዚህ መበርገግ ዓይነተኛ ምልክት ነበር። ከእነዚህ የእውነት ቀናት ጀምሮ እስካሁን ድረስ የኢሕአዴግ መንግሥት እንደበረገገ አለ። የእነዚያን ቀናት የሽንፈት እውነታ ዳግም ላለማየት የማይፈነቅለው ድንጋይ፣ የማይወስደው ዕርምጃ፣ የማያወጣው ግልጽም ሆነ ስውር መመርያ፣ የማይቀይሰው ስትራቴጂ፣ የማይደነቅረው መሰናክል፣ የማያወጣው ወጪ፣ የማይጥሰው እሴት የለም። በምርጫ የመሸነፍ እውነታን ሲያስበው ስለሚያስበረግገው፣ ለ2007 ምርጫ ዝግጅት የጀመረው በ2002 ምርጫ ማግሥት ነው። የ2002 ምርጫ ዝግጅት የጀመረው በ1997 ምርጫ ማግሥት ነው። (ይህ አካሄድ በእንድ ጎኑ ሲታይ የሚደነቅ ነው። ምርጫ ወራት ብቻ ሲቀረው የሚንደፋደፉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከዚህ ብዙ ትምህርት ሊቀስሙ ይችላሉ፣ እስካሁን አላደረጉትም እንጂ)።

ለማጠቃለል የኢሕአዴግ መንግሥት አሳምሮ ይፈራል። አልፈራም ካለ አለመፍራቱን በድርጊቶቹ ያሳይ። በሶማሊያ ጦርነት የኢትዮጵያ ሕዝብ የከፈለውን መስዋዕትነት በተመለከተ ትክክለኛና ይፋዊ መረጃ በመስጠት የሕዝብ መረጃ የማግኘት መብቱን ያክብር። የመንግሥት መገናኛ ብዙኃንን ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች (እውነተኛ ተቃዋሚዎችን ጨምሮ) ለሚመጡ ሐሳቦች መንሸራሸር በአምስት ዓመት አንድ ጊዜ ሳይሆን ዓመቱን በሙሉ ክፍት ያድርግ። በተጨማሪ የመገናኛ ብዙኃን ዘርፉንና ኢትዮ ቴሌኮምንም ለግሉ የንግድ ዘርፍ ክፍት ያድርግ። አሳሪና አስፈሪ ሕጎችን በመሰረዝ ወይም በማሻሻል እንደ ምሽግና እንደ ማጥቂያ መሣሪያ መጠቀምን ያቁም። የኢሕአዴግ መንግሥት በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ተጨባጭ ለውጥ ካላመጣ አሥር ጊዜ በቃል ‹‹አልፈራም!›› ቢልም እውነትን ለመፍራቱ በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ተጽፈው የሚታዩ ጉልህና ተጨባጭ ማስረጃዎች ሆነው ይቀጥላሉ።
Image

Image
Getachew Shiferaw VIA Minilik Salsawi
ከጓደኞቼ ጋር በጠየቅነው ወቅት እንድናስተላልፍ አደራ ብሎናል፡፡ ድምጻችን ይሰማዎች ሆይ! እስክንድር አድንቋችኋል፡፡ ከሁለትና ሶስቱ ውጭ ቢሮ ውስጥ ተቀምጠው የሚውሉት ከ70 በላይ ፓርቲዎች ጉዳያችን አይደለም ቢሉትም እስክንድር ግን ቃሊት ሆኖ እያንዳንዱን እንቅስቃሴያችሁን ይከታተላል፡፡

መልዕክቱንም እንዲህ አስተላልፏል፡፡ ‹‹ድምጻችን ይሰማ ብለው የተነሱት ወጣቶቻችን ለፖለቲካው እንቅስቃሴም ትልቅ ተምሳሌት ናቸው፡፡ ሌላው ማህበረሰብም ሊደግፋቸው ይገባል፡፡ ወጣቶቹ ኢትዮጵያ ውስጥም አምባገነንን ሊያስጨንቅ የሚችል ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንደሚቻል በቀላሉ አስመስክረዋል፡፡ መብቱን በቀላሉ አሳልፎ የማሰጥ ወጣት እንዳለው አሳይተዋል፡፡ እስኪ አስቡት ይህ የወጣት እንቅስቃሴ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ቢሆን ምን ታዕምር ሊፈጥር እንደሚችል? እውነቴን ነው የምላችሁ ፓርቲዎችን ጨምሮ በፖለቲካው ዘርፍ እንቀሳቀሳለሁ የሚል አካል ድምጻችን ይሰማን ሞዴል ማድረግ ይኖርበታል››፡፡

እስክንድር እውነት አለው፡፡ እኔ በበኩሌ የማይዋዥቅ እንቅስቃሴ ያየሁት ድምጻችን ይሰማን ነው፡፡ ለሌላኛው የፖለቲካ እንቅስቃሴም ቢሆን ቀላል የማይባል ድምቀት ሰጥቶታል፡፡ በፖለቲካው ዘርፍ ብቻ ያተኮረው እንቅስቃሴን በተለይ በፌስ ቡክ በቅርብ አመታት ጠንከር እያለ ቢሆንም አጀንዳ ቀረጻው፣ አደረጃጀቱና እንቅስቃሴው አዝጋሚ ነው፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ ሲኖር፣ ባለሰልጣናት ሲመረጡ፣ ሲሻሩ፣ ሙስና ተከሰተ፣ መሬት ተሸጠ ሲባል ዜና ማስተላለፍ፣ ወቅታዊ ጉዳይን ማስተላለፍ ላይ የተጠመደ ነው፡፡ በእርግጥ ይህም አንድ በጎ ጅምር ነው፡፡

ሆኖም ትኩስ ጉዳይ ካላገኘ እንደገና ይቀዘቅዛል፡፡ አንዱን አጀንዳ ጥሎ ሌላ ከማንሳት ያለፈ ዳር የማድረስ ችግር ይታይበታል፡፡ ቀደም ብሎ የያዘው ጉዳይ (እስራት፣ የዜጎች መፈናቀል፣ ሙስና……) ዳር ሳይደርስ ሌላ አዲስ ወሬ ከመጣ ዋና አስመስሎት የነበረውን አጀንዳ በትኖ አዲሱን ይቀበላል፡፡ ያው ዋና አጀንዳው አልነበረውም ማለት ነው፡፡ አሊያም አጀንዳ ለመያዝ አቅም አልነበረውም፡፡ በዚህ ረገድ ድምጻችን ይሰማ የተለየ ነው፡፡ ኳስም ይኑር ሩጫ፣ ሙስናም ይሁር ሹምሽር በድምጻችን ይሰማ ሰፈር የሙስሊሙ ጉዳይ፣ የኮሚቴዎቼ ዜና አይደበዝዝም፡፡ በፖለቲካው ጉዳይ ግን በወረት አጀንዳዎች ዳር ሳይደርሱ ሌላኛውን ማንሳት የተለመደ ነው፡፡ አዲስ ዜና ያጠቃናል፡፡ በአሁኑ ወቅት ለጭቆና ራሱን መስዕዋት ያደረገውን የኔሰው ገብሬን እያስታወስነው አይደለም፡፡ ውብሸት ታዬን እኛ እረስተነው ያስተወሱት ፈረንጆቹ ናቸው፡፡ ከክልል የሚባረሩት ኢትዮጵያውያን የአንድ ሰሞን ጉዳይ ነው፡፡ ታሰረ፣ ተፈታ፣ ተገደለ፣ ሙስና…….ዜና ሆነው ያልፋሉ፡፡ ከሳምንት በኋላ በሳውዲ የሚሰቃዩትን ዜጎቻችንን ጉዳይ ረስተን ሌላ ጉዳይ እናነሳለን፡፡ ከዋናው ጉዳያችን ልቅ የኢህአዴግ ካድሬዎች የሚያነሷቸው ማስቀየሻዎች ላይ በርካታ ጊዜያችን እንገድላለን፡፡ እንደገና ሌላ ዜና ይመጣል፡፡

እኔ እንደሚመስለኝ ዋናው ችግራችን የተበታተንን በመሆናችን ነው፡፡ ፌስ ቡኩንም ሆነ ሌላውን እንቅስቃሴ በተደራጀ መለኩ፣ በሙያ፣ በስነ ምግባር የሚመራው አልተገኘም፡፡ ዲያስፖራውና አንዳንድ ፓርቲዎች አካባቢ የሚገኙ በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦች (በግል) ብቻ እንቅስቃሴ የትም ሊያደርሰው አይችልም፡፡ ማህበራዊ ድህረ ገጹ፣ ፖለቲካ እንቅስቃሴው የመሪ ያለህ እያለ ነው፡፡

በ1960ና 70ዎቹ ትውልድ በብጫቂ ወረቀት፣ በመልዕክተኛ፣ አልፎ አልፎም በቤት ስልክ ተገናኝተው ለራሳቸው ሳይሆን ለሰፊው ህዝብ ታግለዋል፡፡ በዛን ወቅት ፌስ ቡክ ቢኖር በየ ካፌና ጠባብ ቤቶች ተሰብስቦ የራሱን አገራዊ ፖሊሲ መቅረጽ የቻለው ያ ትውልዱ ምን ያህል ሊጠቀምበት ይችል እንደነበር መገመት አያዳግትም፡፡

ይህ ግን የአሁኑ ትውልድ በአጠቃላይ ችግር እንዳለበት የሚያሳይ አይደለም፡፡ ጥቂቶችም ቢሆኑ የአሁኑ ትውልድ በሙሉ የባከነ እንዳልሆነ እያሳዩን ነው፡፡ ድምጻችን ይሰማን በዚህ በፈዘዝነው መካከል ሆኖ መደራጀት፣ መጠየቅ፣ አጀንዳና ማንሳትና ዳር ማድረስ፣ አምባገነንን ማስጨነቅ ችሏል፡፡ ስለሆነም ድምጻችን ይሰማን መመልከቱ አዋጭ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ድምጻችን ይሰማ ሆይ! የኢትዮጵያውያን ድምጽ ጮህ ብሎ ይሰማ ዘንድ እናንተም አርዕያነታችሁን ተወጡ፡፡

የድሮው ትውልድ ፍልስጤም ድረስ ተጉዞ ሰልጥኗል፡፡ የሌሎች አገር ዜጎች እንኳን ስል አብዮት ብለው ኢትዮጵያ ድረስ መጥተው አሰልጥነዋል፡፡ አሁን ፌስ ቡክ የሚባል አውላላ ሜዳ ትልቅ ማሰልጠኛ ጣቢያ ሆኗል፡፡ እናም የዳሌ ምስል እየተከተለ ‹‹like›› የሚያደርገውን ወጣት፣ አንዱን ዜና ይዞ ሌላኛውን የሚያነሳውን፣ በአገር ጉዳይ አያገባኝም ብሎ ራሱን የሚሸነግለውን ስለ ትግል ስልት፣ ስል መደራጀት፣ ስለ አጀንዳ ቀረጻ ስልጠና ብትሰጡት፣ ‹‹ዱብ ዱብ›› እንዲል ብታደርጉት ምን ይመስላችኋል? —

እንደ ሰው አንድ የሚያደርገን ባሕርይ፣ እንደ ኢትዮጵያዊነትም ሁላችንንም የሚመለከተንና የፖለቲካም ሆነ የሃይማኖት ልዩነት የማይነጣጥለው በደል በሳዑዲ አረብያ ግዛት እየተፈጸመ ነው። የጥቃት ዒላማዎቹ ኢትዮጵያውያን ናቸው። የጥቃቱ ልክ የለሽነትና አሰቃቂነት ደግሞ ይበልጥ የጎላው በሴት እህቶቻችን ላይ ነው። ይህ ዛሬ በሳዑዲ አረብያ የሚደረገው ጥቃትን ማስቆምና ቁጣችን መቆምያ እንደማይኖረው ማሳየት ለነርሱ ብቻ ሳይሆን ለራሳችን ደህንነትም ጭምር የምናደርገው ነው። ምክንያቱም […]

በግንቦት 7 አና በአርበኞች መካከል ያለው ልዩነት እየጎላ መጥቷል:: ጀነራል ፍፁም አርበኞች ወደ ገንቦት 7 እንዲቀላቀል ግዳጅ ቢሰጥም ከአረበኞት ተቀባይነት አላገኘም:: በትናቸው(አንዳርጋቸው) ጥጌ በወያኔ የግድያ ሙከራ ተፈፅሞብኝ ነበር የሚለው ከሃቅ የራቀ አውነቱን ለመሸፈን የተደረገ ፕሮፓጋንዳ ነው:: ዋናው ቁምነገሩ አርበኞች በጉራጌና “በጋላ” (አንዳርጋቸው) አንመራም እያሉ ነው:: አርበኞች በብዛት ከጎንደር የመጡ ሲሆን ከመቶ አይበዙም:: ግንቦት 7 በአሁኑ ሰዓት ምላስ እንጂ ምንም ጡንቻ የለውም:: የአንዳርጋቸው ጥጌ የአስመራ ጉዞ ስኬታማ አልነበረም:: በአስመራ ያሉት የተለያዩ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች በጎሪጥ ነው የሚተያዩት:: አይተማመኑም::

መጽሐፍ ወሬ ነጋሪ ደራሲ መሐመድ ይማም ግምገማ በልጅግ ዓሊ በሚያዚያ ወር የሰሜን አሜሪካ ክረምት ገና ሙሉ በሙሉ ሳይለቅ በፊላደልፊያ ከተማ ውስጥ በማይታወቅ ሰው ኢትዮጵያዊቷ ጀግና ተገደለች። በምሳ ሰዓት አካባቢ ወደ ቤት የተመለሰችው እህቷ ጠዋት በሰላም የተለየቻትን በደም አበላ ውስጥ ተዘፍቃ አገኘቻት። ፖሊስም ጠራች። የፍላደልፊያ ፖሊስ ይህንን የተቀነባበረ ግድያ የፈጸመውን ወንጀለኛ መያዝ ስላቃተው እንቆቅልሹ ያልተፈታ በሚል […]

በሪያድ መንፉሃ በተከሰተው ሁከት ግራም ነፈሰ ቀኝ ተጎጅዎች እኛ ነን ! እንኳንስ ሰው ተደብድቦ ፣ ሞቶባቸው ፣ እንኳንስ መኪና ተሰብሮባቸው እንዲያውም እንዲው ናቸው ። ከማለዳ እስከ ሌሊት የዘለቀውን ሁከት መቆጣጠር ይቻል ዘንድ ገና ሲጀመር አቅጣጫውን አይተው የመንግስት ተወካዮችን የመከሩ በርካታ ነበሩ። የሰማ አካል ግን የለም ! ስልክ ተደውሎ የማይነሳበት ፣ አልፎ አልፎ መስመሩ ሲነሳ ሃላፊዎችን […]

ዛሬ ረፋድ ላይ … በሳውዲ ዋና ከተማ ዛሬ ከረፋዱ ጀምረው እስከ እኩለቀን በሪያድ መንፉሃ ወደ ሃገራችን ስደዱን በሚል መንፉሃ ባንክ አልራጅህ አካባቢ በርካታ ኢትዮጵያውያን መንግስት የወሰደውን እርምጃ ተቃውመው ወጡ! ቤተሰቦቻቸውን እና ሻንጣቸውን ይዘው አውራ መንገድ የወጡት ኢትዮጵያውያን ህጋዊ መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ግማሾቹ ወደ ሪያድ ኢንባሲና ኮሚኒቱ መስሪያ ቤት በእግራቸው ያመሩ ሲሆን መንፉሃ አካባቢ የቀሩት ከፖሊስ […]

(ፋክት መጽሔት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፲፱ ጥቅምት ፳፻፮ ዓ.ም.) ተመስገን ደሳለኝ … ኢሠፓ መራሹ መንግሥት በኢሕአዴግ ከተተካ ጥቂት ወራት ቢያልፈውም፣ የተራዘመው የእርስ በርስ ጦርነት ያልደረሰባቸው በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙ አንዳንድ ከተሞችን ገና በቅጡ አልተቆጣጠራቸውም፤ በአናቱም በኢሠፓ መንግሥት ሽንፈት ሳቢያ እንዲበተን ከተገደደው የአገሪቱ መደበኛ ወታደር አብዛኛው ከእነትጥቁ የትውልድ መንደሩንና ቤተሰቡን መቀላቀሉ በአገሪቱ ላይ ከባድ ፍርሃት አንብሯል፡፡ በሰላም …

እ.አ.አ በ፲፱፻፵፯ ዓ.ም. በአሥመራ ከተማ ተወልደው የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአሥመራ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጅማ ተከታትለዋል፡፡ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ከአሥመራ ዩኒቨርሲቲ በሕግ አግኝተዋል፡፡ ከ፲፱፻፸፪ – ፲፱፻፸፬ ዓ.ም በአሥመራ ዩኒቨርሲቲ ያስተማሩት ፕሮፌሰር ተከሥተ በሎንዶን ዩኒቨርሲቲ ከ‹‹ስኩል ኦቭ ኦሪየንታል ኤንድ አፍሪካን ስተዲስ›› ሁለተኛ ዲግሪ ያገኙ ሲኾን የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከስዊድን ኡፕሳላ ዩኒቨርስቲ በታሪክ ትምህርት ሠርተዋል፡፡ ፕሮፌሰሩ ዛሬ ታትሞ ከወጣው አዲስ …

ምዕራብ አፍሪቃዊቱ ሀገር ማሊ እአአ የፊታችን ህዳር 24 አዲስ ምክር ቤት ትመርጣለች። የምርጫው ዘመቻ በሳምንቱ መጀመሪያ የተጀመረ ሲሆን፣ ለ147 የብሔራዊ ምክር ቤት መንበሮች 1141 ዕጩዎች በተወዳዳሪነት ቀርበዋል።

ጥቅምት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ዋና ሃለፊ በአቶ ጌታቸው አሰፋ እና በጠቅላይ ሚኒስትሩ የብራዊ ደህንነት አማካሪ በአቶ ጸጋየ በርሄ ቁጥጥር የተመራና በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌና በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል መሪዎች ላይ የተቀነባበረው የግድያ ሙከራ ከሸፈ። ከግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው ለግድያ የተላከው ሙሉቀን መስፍን የተባለው ግለሰብ በትናንትናው እለት በቁጥጥር …

ጥቅምት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምክር ቤቱ ነገ በሚያደርገው ስብሰባ ለመንግስት ስልጣን አስጊ ሆኗል ባለው የሽብርተኝነት አደጋ ላይ እንደሚመክር ለማወቅ ተችሎአል። ምክር ቤቱ ከፍተኛ ስጋት ደቅነዋል ባላቸው ግንቦት7 እና የኤርትራ መንግስት ላይ ተነጋግሮ የመፍትሄ እርምጃ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል። ምክር ቤቱ በሳውዲ አረቢያ በካምፕ ውስጥ ስላሉ ኢትዮጵያም ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። የውጭ ጉዳይ መስሪያ …

ጥቅምት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮምሽን በመካሄድ ላይ ባለው 6ኛው የአፍሪካ ሚዲያ አመራሮች ፎረም ላይ ኢህአዴግ የሚያቀነቅነው  የልማታዊ ጋዜጠኝነት ጽንሰ-ሀሳብ በአፍሪካ ጋዜጠኞች ተተችቶአል። ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች ችግሮቻቸውን ፊትለፊት አውጥተው መናገር ባለመቻላቸውም ወቀሳ ደርሶባቸዋል። ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ በዚሁ ጉባዔ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር የፕሬስ ነጻነት በኢትዮጽያ መረጋገጡን በማውሳት ፕሬሱ ግን በውስጡ …

ጥቅምት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በሶማሊ ክልል ዋና ከተማ ጅጅጋ የሚታየው ሁኔታ እስከ ዛሬ ከታዩት ሁሉ የተለየ ነው ይላሉ ነዋሪዎች። ከሌሎች አካባቢዎች በመሄድ ወደ ከተማው መግባት ወይም ከከተማው በመውጣት ወደ ሌሎች አካባቢዎች መሄድ  የተከለከለ ነው ይላሉ። የመከላከያ ሰራዊት አባላት በከተማው በብዛት በመገኘት ቤት ለቤት የሚያካሂዱት ፍተሻ ለነዋሪዎች ጭንቀትን ፈጥሮባቸዋል። በክልሉ ፕሬዚዳንት ትእዛዝ …

ጥቅምት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየካ ክፍለ ከተማ በቀድሞ አጠራሩ ከፍተኛ 12 ቀበሌ 18 ለህዝብ አገልግሎት በሚል የተሰራው ጤና ጣቢያ ካለፉት 6 ወራት ጀምሮ የእስረኞች ማጎሪያ ፖሊስ ጣቢያ እንዲሆን መደረጉን ነዋሪዎች ገልጸዋል። የአካባቢው ነዋሪ በቂ የህክምና ቦታ አጥቶ በሚቸገርበት ጊዜ ፣ መንግስት ጤና ጣቢያውን ፖሊስ ጣቢያ ማድረጉ በእጅጉ እንዳሳዘናቸው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። በጉዳዩ …

የሳውዲ አረቢያ መንግስት ህገወጥ ነዋሪዎችን በዚህ ሳምንት ተከታትሎ መያዝ ከጀመረ ወዲህ ታዳጊ ወጣት ኢትዮጵያውያን የሚማሩበት የጂዳው ትምህርት ቤት ሥራ መሰናከሉ በርካታ ወላጆችን ስጋት ላይ ጥሏል።

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ) ከጥቅምት 27 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ትቅምት 29 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስድስተኛው የአፍሪካ ሚዲያ መሪዎች ፎረም እየተካሄደ ነው፡፡ ፓርቲያችንም ይህንን ጉባዔ በአንክሮ እየተከታተለው ሲሆን በርካታ የአፍሪካ ሚዲያ ባለሙያዎች የፕሬስ ነፃነት ባልተረጋገጠበት፣ የግል ጋዜጦችና መፅሄቶች ተልካሻ ሰበብ እየተፈለገ በሚዘጉበት፣ ጋዜጠኞች ሀገር […]

ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በቁጫ ወረዳ የሚማሩ ተማሪዎች ከማንነት እና መብት መከበር ጋር በተያያዘ ያነሱትን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ የአንደኛ እና መለስተኛ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ትምህርት ማቆማቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ተማሪዎቹ በቋንቋችን እንማር፣ በአካባቢያችን የሚታየው የመብት ረገጣ ይቁም የሚሉ ጥያቄዎችን ማንሳታቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ የፌደራል ፖሊስ አካባቢውን ከተቆጣጠረው በሁዋላ ቁጥራቸው ከ25 …

ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመሬት፣  ከኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ጋር በተያያዘ በመላ አገሪቱ ለቀረቡ 990 ሺ 627 አቤቱታዎች  መንግስት መልስ ለመስጠት እንደተሳነው መረጃዎች አመልክተዋል። የመልካም አስተዳደር ኮማንድ ፖስት ሴክሬታርያት ፅ/ቤት የ2005 የ6 ወራት የመልካም አስተዳደር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እንደሚያሳየው ከመሬት፣  ከኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ጋር በተያያዘ በመላ አገሪቱ ለቀረቡ 990 ሺ 627 አቤቱታዎች …

ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ወሎ ዞን በእያንዳንዱ ቀበሌ  10 ሰዎች እየተመለመሉ አሸባሪዎችን ነቅተው እንዲጠብቁ ስልጠና እየተሰጣቸው መሆኑን አርሶ አደሮች ተናግረዋል። በስልጠናው የተነሳ አዝመራችንን እንኳ በወቅቱ ለመሰብሰብ አልቻልንም የሚሉት አርሶደአሮች፣ በአካባቢያቸው ጸረ ሰላም ሀይሎች ሲንቀሳቀሱ ከተመለከቱ ወይም ጸጉረ ልውጦችን ከተመለከቱ ለመንግስት አካላት ሪፖርት እንዲያደርጉ ተነግሮአቸዋል። ለሁለት ሳምንት በሚቆየው በዚህ ስልጠና አርሶአደሮቹ …

ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጉራጌ ዞን የእንድብር ከተማ  ነዋሪዎች እንደተናገሩት በከተማቸው ካለፉት 5 ቀናት ጀምሮ መብራት በመጥፋቱ እናቶች እህል አስፈጭተው ልጆቻቸውን መመገብ የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል። አቅሙ ያላቸው 30 ኪሎ ሜትሮችን ተጉዘው ወልቂጤ ከተማ በመሄድ እህል ለማስፈጨት መቻላቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ አቅሙ የሌላቸው ግለሰቦች ግን ይህን ማድረግ ባለመቻላቸው ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል ብለዋል። …

ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የስዊዝ ሳይንቲስቶችን የምርመራ ውጤት በመጥቀስ አልጀዚራ  እንደዘገበው፤ በያሲር አራፋት ሰውነት ውስጥ ከመጠን ያለፈ ፖሎኒየም የተሰኘ የራዲዮ አክቲቭ ንጥረ ነገር ክምችት ተገኝቷል። ይሁንና እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2004 ለሞት የተዳረጉት ያሲር አራፋት በፖሎኒየም የተመረዙት መቼ እንደሆነ የሳይንቲስቶቹ ጥናት አያመለክትም። የምርመራ ጥናቱ ውጤት በያሲር አራፋት አስከሬን ውስጥ ከትክክለኛው መጠን   የ …

የስደተኛው ማስታወሻ በተስፋዬ ገብረአብ Yesedetegnaw Mestawesha by Tesfaye Gebreabበይምርሐነ ክርስቶስ ጣራ ላይ የሚገኘው የዳዊት ኮከብዳንኤል ክብረት

ባለፈው ሳምንት ተስፋዬ ገብረ አብ አቡነ ተክለኃይማኖትን በተመለከተ ያነሣቸውን ነጥቦች ማየት ጀምረን ‘የሦስቱን ተክለ ሃይማኖቶች’ ጉዳይ ለዛሬ አቆይተነው ነበር። እንቀጥል።

1) የሰባተኛው መክዘ ተክለኃይማኖት
ተስፋዬ የጠቀሳቸው የሰባተኛው መክዘ ተክለኃይማኖት የሉም። እስካሁንም እንደርሱ ፈጠራቸውን የሚናገሩ እንጂ ማስረጃ ያመጡ አልተገኙም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ኢትዮጵያ ውስጥ የሽብር ጥቃቶች ሊደርሱ ይችላሉ በሚል የጸጥታ ኃይሎች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ በታዘዙበት በኣሁኑ ወቅት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኣንድ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ በፈነዳ ቦምብ አራት ሰዎች መሞታቸው ተዘገበ።

የጀርመን ባለሃብቶች በልዩ ልዩ ቀውሶች ና በሙስና ስሟ በሚነሳው በአፍሪቃ በአመዛኙ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ አይደፍሩም ። ይኽው ጉዳይ ከትናንት በስተያ ቦን ውስጥ በተካሄደው አፍሪቃ ውስጥ የሚሰሩ የጀርመን ባለሃብቶች የምጣኔ ሃብት ማህበር ጉባኤ ላይ ትኩረት ተስጥቶት ነበር ።

አንዳድ የመብት ተሟጋቾች ከሰወስት መቶ ሐምሳ በላይ ኤርትራዉያን ስደተኞች ወደ አዉሮጳ ለመሻገር ሲሞክሩ ላፑዱዛ አጠገብ በደረሰዉ የጀልባ አደጋ ሰምጠዉ ለመሞታቸዉ የአዉሮጳ ሕብረትን የስደተኞች መርሕ ተጠያቂ ያደርጋሉ

ክፍል 1 ሰሞነኛ አዲሱን አመት ተቀብለን ሁለት ወራት ሳንሻገር ጥቅምት 11 ቀን የኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ እና ሥራ አሥኪያጁ ጋዜጠኛ ሚሊዮን ደግነው ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድ ቤት ቀረቡ፤ በዳግም ቀጠሮ ዕረቡ ጥቅምት 20 ቀን በሐዋሳ ከተማ ጋዜጠኞቹ ለፍርድ ቤት ቀጠሮ ሄደው በስልት የተቀናበረ በሚመስል ሆኔታ ለመኪና አደጋ ተዳርገው ጋዜጠኛ ኤፍሬም የከፋ አደጋ […]

በእኛ አገር መንግስትና ፓርቲን መነጠል አይቻልም፡፡ህገ መንግስቱ ሳይቀር በብዙ አንቀጾቹ የገዢው ፓርቲ ፕሮግራም ግልባጭ መሆኑ ትስስሩን ላቅ ያደርገዋል፡፡ስለዚህ መንግስት ሲለወጥ ባንዲራ፣ህገ መንግስት፣ብሄራዊ መዝሙር እንቀይራለን፡፡የመንግስት ስርዓት መዘርጋት አለመቻላችን ያመጣብን ጣጣ ልንለው እንችላለን፡፡
ህዝቡ በፓርቲው እምነቱን አጣ ማለት መንግስትንም አያምነውም ተብሎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ኢህአዴግ በኢትዮጵያ የመንገስታት ታሪክ አመኔታ በማጣት ረገድ ግምባር ቀደሙ ይመስለኛል፡፡እምነት የጠፋበት አጋጣሚም ከኢህአዴግ የትጥቅ ትግል ቆይታ ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ደርግ የያኔዎቹን አማጺያን ወንበዴ፣አገር አስገንጣይ በማለት ይፈርጃቸው ነበር፡፡ከተሜው የደርግን ፕሮፓጋንዳ ሲጋት በመቆየቱ ተጋዳላዮቹ ወደ ከተማ ሲገቡ የተቀበላቸው በፍርሃት ድባብ ታስሮ ነበር፡፡
ትግራይን ነጻ ለማውጣት በረሃ የገቡት የትግራይ ልጆች የህዝቡን አመኔታ ለማግኘት የሐውዜንን ድብደባ ለደርግ የተሳሳተ መረጃ በመስጠት የቪዲዮ ካሜራ በማዘጋጀት የተዋጣለት ፊልም መቅረጻቸውና ለጊዜውም ቢሆን በዚህ ምክንያት የትግራይ ህዝብን ድጋፍ ለማግኘት ቢበቁም እያደር ግን የሐውዜን ምስጢር አፈትልኮ መውጣቱ ተአማኒነታቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ፈጥሯል፡፡በግሌ እምነት የሰጧቸው ዋና ዋና ተግባሮቻቸው የሚከተሉት ናቸው
—- በትግራይ መንግስት የወረሳቸውን ቤቶች በመመለስ ለሌሎቹም ይህንን እንደሚያደርጉ ቃል ቢገቡም ቃላቸውን መጠበቅ አለመቻላቸው
—- የአልባንያን ሶሻሊዝም ተጋዳላዮቹን ይግት የነበረው ኢህአዴግ አዲስ አበባን ለመቆጣጠር ከጫፍ በደረሰበት ወቅት የምዕራባዊያንን ድጋፍ ለማግኘት ራሱን ነጭ ካፒታሊስት በማድረግ መጥራት መጀመሩ ርዕዮት አልባ አድርጎታል፡፡ይህም በሚከተለው የፖለቲካ ፍልስፍና አቋመ ቢስ ስላደረገው የገዛ ታጋዮቹን እምነት አሳጥቶታል፡፡
—–በበደኖ፣በአርባጉጉና በአሰቦት በተፈጸሙ አንድ ብሄር ላይ ያነጣጠሩ ጭፍጨፋዎች ኦህዴድና/ኦነግ ሃላፊነት በመውሰድ መጠየቅ ይገባቸው የነበረ ቢሆንም ኢህአዴግ የኦህዴድን እጅ እንደ ጲላጦስ በማጠብ የደሙን ዋጋ ኦነግ ላይ መጣሉ በኦሮሚያ አማኝ አሳጥቶታል፡፡
—– የመምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት የነበሩትን መምህር ዶክተር ታዬ ወ/ሰማያትን የ17 ዓመት እስራት ሲያከናንብ በዜና ያስደመጠው ‹‹ታጣቂ ቡድን እያደራጁ ነው››ብሎ የነበረ ቢሆንም በፍርድ ቤት ይህንን ማስመስከር አልቻለም፡፡
—–እነ ርዕዮት አለሙ በታሰረበት ቅጽበት ምሽቱን በኢቴቪ የተደመጠው ዜና ‹‹በመንግስት መሰረተ ልማቶች ላይ አደጋ ለማድረስ ሲያሴሩ ተገኝተዋል፡፡››ተብሏል፡፡ፍርድ ቤት ጋዜጠኞቹ በቀረቡበት ወቅት ግን በኢቴቪ የቀረበው በክሳቸው ውስጥ አልተካተተም፡፡ይህም አመኔታን የሚያሳጣ ድርጊት ሆኖበታል፡፡
—-የ1997 ምርጫን ነጻና ፍትሃዊ አደርጋለሁ በማለት ቃል የገባው ኢህአዴግ ለ200 ሰዎች ዕልቂት መንስኤ የሆነን ኮሮጆ ግልበጣ ፈጽሟል፡፡
—-የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቢሮን ለአመታት ተቆጣጥረውት የነበሩት አቶ ስዮም መስፍን የኢትዮ ኤርትራ የድንበር ኮሚሽን ፍርድን ለኢትዮጵያ ህዝብ ባስደመጡበት ወቅት ‹‹እንኳን ደስ አለን ብዙ ሺህ የህይወት ዋጋ የከፈልንባት ባድመ ለእኛ ተፈረደች››በማለት ህዝቡ ደስታውን በሰላማዊ ሰልፍ እንዲገልጽ ቢያደርጉም እውነታው ግን ባድመ ለኤርትራ መወሰኗ ነበር፡፡
—- በተለያዮ ቦታዎች ስለተፈጸሙ የቦንብ ፍንዳታዎች መንግስት ተቃዋሚዎችን ተጠያቂ ቢያደርግበትም ዊኪሊክስ በቅርቡ በለቀቀው መረጃ መንግስት ሆን ብሎ እንዲህ አይነት ድራማዎችን እነደሚሰራ አጋልጧል፡፡እስከ እናንተ ለምን መንግስትን እንደማታምኑ ምክንያታችሁን አካፍሉን፡፡

ምንጭ :- START – UNIVERSITY OF MARYLAND – የአሸባሪዎች አጥኚ ቡድን

የአሸባሪ ድርጅቶች መዝገብ
በሃገሩ ቋንቛ መጠሪያው .. አልተገለጸም

የድርጅቱ ስም …..የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (TPLF)

የሚንቀሳቀስበት አከባቢ … ኢትዮጵያ

የተቋቋመበት ጊዜ ….. አልተገለጸም

የአባላቶቹ ቁጥር/ጥንካሬው … አይታወቅም

መለያው ….. ኮሚኒስት/ሶሻሊስት/ብሄርተኛ/ተገንጣይ

የገንዘብ ምንጩ …. አይታወቅም

የተነሳበት የፖለቲካ ፍልስፍና
ራሱን የትግራይ ንቅናቄ ወይንም ወያኔ በማለት በ1970ዎቹ መጀመሪያ በመንግስቱ ሃይለማርያም አገዛዝ ላይ የተጀመረ ተቃውሞ
በ1975 አከባቢ የትግራይ ነጻ አውጪ በማለት ተመስርቶ በኤርትራ ነጻ አውጪ ስር እየተዳደረ ውጊያ የከፈተ ድርጅት ነው::አላማቸው የአልቤንያን ሞዴል የተከተለ የኮሚኒስት ስርኣት በማስፈን የታለመ…የትግራይን ህዝብ ከደርግ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት የተነሳ ነበር::በሜይ 1989 የደርግን ሰራዊት በማሸነፍ ሙሉ ትግራይን መቆጣጠር ችሎ ነበር::በተለያየ ጊዜ ከሻእቢያ ጋር እና በተናጠል በተለያዩ አከባቢዎች የአሸባሪነት ድርጊት ፈጽሟል::
ዝርዝር መረጃውን ከዚህ ድህረገጽ ያገኙታል:- http://www.start.umd.edu/start/data_col … sp?id=4287

በእኛ አገር መንግስትና ፓርቲን መነጠል አይቻልም፡፡ህገ መንግስቱ ሳይቀር በብዙ አንቀጾቹ የገዢው ፓርቲ ፕሮግራም ግልባጭ መሆኑ ትስስሩን ላቅ ያደርገዋል፡፡ ስለዚህ መንግስት ሲለወጥ ባንዲራ፣ህገ መንግስት፣ብሄራዊ መዝሙር እንቀይራለን፡፡የመንግስት ስርዓት መዘርጋት አለመቻላችን ያመጣብን ጣጣ ልንለው እንችላለን፡፡ ህዝቡ በፓርቲው እምነቱን አጣ ማለት መንግስትንም አያምነውም ተብሎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ኢህአዴግ በኢትዮጵያ የመንገስታት ታሪክ አመኔታ በማጣት ረገድ ግምባር ቀደሙ ይመስለኛል፡፡እምነት የጠፋበት አጋጣሚም ከኢህአዴግ የትጥቅ […]

ይድረስ ያልኩት በቀጥታ ባይደርሶትም መስማትዎ እንደማይቀር እገምታለሁ፡፡ ሰላም የምሎት ሰላምታ የእግዚአብሄር በመሆኑ ነው፡፡ እንጂ ጫንቃችን ላይ ተጎብራችሁ የዜግነት ክብንርን አውርዳችሁ የዜግነት ክብር የምታዘምሩ በሆናችሁ፣ በብሄር ፣በጎሳ ከፋፍላችሁ…ሰብዓዊ መብታችንን ገፋችሁ..ኑሮን መቋቋም እንዳንችል አድርጋችሁ ለስደት ስለዳረጋችሁን ሰላምስ ማለት አይገባም ነበር፡፡ ለስምም ሆነ አልሆነ በአሁኑ ሰዓት ለሀገሪቷ ጠ/ሚኒስትር በመሆንዎ ነው ይድረስ ያልኩት ለእርሶ ይሁን እንጂ ለሚመለከታቸው ባለስልጣኖች ሁሉ […]

ለሸገር ልጆች፦፦፦
የድሮ አራዶች እነ ድንጋይ ኳሱ
ቦርቸሌን ከርቸሌን በደንብ ያዳረሱ።
ለወሬ ነጋሪ ካሉ የተረፉ፧
ምን አለ ቢያወጉን፧ምን አለ ቢጽፉ፧
ያዲሳባ ልጆች አብሮ አደጎቼ፣
በናፍቆት ባዘኑ እያነቡ አይኖቼ።
ድንገት ሣናስበው እንደተለያየን፣
በሞያሌ ሾልከን በቦሌ እንገባለን፣
አይቀርም አንድ ቀን፦እናወራዋለን፣
በአመቺው ዘዴ እንተርከዋለን፣
ዕድሜና ጤናውን አምላክ ካልነፈገን።፧
ሁል ግዜ ድሪሜ፣
የዘወትር ህልሜ፣
እንዳይነፍገን ዕድሜ።
እስከምንገናኝ በአካል በዐይነ ስጋ፣
ፌስ ቡክ ያገናኘን እርሱም እስኪዘጋ።
*ድንገት ለተለያየነው አብሮ አደጎቼና ወዳጆቼ ሁሉ መታሠቢያ ተፃፈ።
ተዱ ዘአራዳ ከዩጋንዳ

እለተ ሰኞ – ጥቅምት ሊሸኝ ህዳር ሊገባ የቀሩት ጥቂት ቀናት ብቻ ናቸው። በሳውዲ አረቢያ በህጋዊ መንገድ ገብተው ከአሰሪዎቻቸው ጋር ባለመግባባትና ፈርጀ ብዙ በሆነ ምክንያት መኖሪያ ፍቃድ የተበላሸባቸው ማደስ እንዲችሉ ፣ ከአሰሪዎቻቸው ጠፍተው ያለ ህጋዊ ሰነድ በግል ሲሰሩ ለነበሩ ፣ ከአምስት አመታት በፊት በህጋዊ መንገድ በሃጅ በኡምራ ገብተው ወደ ሃገራቸው ሳይመለሱ በህገ ወጥ መንገድ ያለ መኖሪያ […]

በለገጣፉ ፖሊስ ከቢሮው ቅዳሜ ዕለት የተወሰደው ጋዜጠኛ ሚልዮን ደግነውና ሰኞ ማለዳ የስራ አጋሩን የተቀላቀለው ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ በእስር ከቆዮ በኋላ ትናንት አመሻሽ እያንዳንዳቸው 600 ብር ዋስ በማስያዝ መለቀቃቸው ታውቋል፡፡ ጋዜጠኞቹ ለእስር የተዳረጉት በኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ በለገጣፉ የተፈጸመን የመሬት ሙስና የሚያትት ዜና እና ዘገባ በመስራታቸው መሆኑም ታውቋል፡፡ፖሊስ ቅዳሜ የያዘውን ሚልዮንን በማረፊያ ቤት በማቆየት ቃሉን የተቀበለው ሰኞ […]

ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከማንነት ጋር በተያያዘ አንዴ ሲሞቅ ሌላ ጊዜ ሲቀዘቅዝ የነበረው የቁጫ ተቃውሞ በዛሬው እለት በሰላም በር ከተማ ተጠናክሮ መካሄዱን ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ ያመልክታል። ዛሬ ተቃውሞውን ያካሄዱት ተማሪዎች ሲሆኑ ፣ ተማሪዎችም ላቀረብነው ጥያቄ መልስ የማይሰጠን ከሆነ ትምህርት አንማርም ብለዋል። ተቃውሞውን አስተባብረዋል የተባሉ መምህራንም በአስቸኳይ ስብሰባ ተጠርተው ተቃውሞን የመሩትን እንዲያጋልጡ …

ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጸረ ሽብር ግብረሀይል  ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላላፈው መልእክት አልሸባብና በኤርትራ የሚደገፉ ሀይሎች በመላው አገሪቱ ጥቃት ለመፈጸም እየተዘጋጁ መሆኑን አስተማማኝ መረጃ ደርሶኛል ብሎአል። ዜጎች እራሳቸውን ለመከላከል አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸውም ገልጿል። ሰሞኑን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ፍተሻዎች ሲደረጉ የሰነበቱ ሲሆን፣ የትናንቱ ማስጠንቀቂያም ይህን ተከትሎ የተሰጠ ነው። መንግስት በኤርትራ የሚደገፉ የሽብር …

ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሚኒስትሮች ምክር ቤትን ደንብ ቁጥር 250/2003 ሽሮ እንደገና ለማቋቋም የተዘጋጀ ፤ ተጠሪነቱ ለጠ/ሚኒስትሩ የሆነ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲን ለማቋቋሚያ የወጣው አዋጅ ሀሙስ ይጸድቃል።በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ተዘጋጅቶ በካቢኔ ፀድቆ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ኮምፒዩተርን መሰረት ያደረጉ የትራንሰፖርት እና የኢንዱስትሪ የቁጥጥር ስርዓቶች ደህንነት ኮምፒዩተርን መሰረት …

ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰንደቅ እንደዘገበው በ2004 በጀት ዓመት ባልተሟላ ሰነድ ከ3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ባላይ ወጪ በማድረጉ በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ጠንካራ ትችት የቀረበበት የመከላከያ ሚኒስቴር የሒሳብ መዛግብቱን ዋናው ኦዲተርን ጨምሮ ለማንኛውም አካል ሚስጢር ማድረግ የሚያስችለውን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል። አዲሱ የመከላከያ ሠራዊት ረቂቅ አዋጅ ሰነድ በአንቀጽ 72 ንዑስ አንቀጽ …

ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወጣት እስከ አዋቂ ያለው ከግማሽ በላይ የሚሆነው ኢትዮጵያ በልጅነቱ  በቂ ምግብ ሳያገኝ ተጎድቶ እንደሚያድግ የተመለከተው በኢትዮጵያ ይፋ በሆነው the cost of hunger in Ethiopia ጥናት ውስጥ ነው። 67 ከመቶ የሚሆነውና ከ15 አስከ 64 የእድሜ ክልል ውስጥ ያለው ኢትዮጵያዊ ጠንካራ ሰራተኛ ቢመስልም በልጅነቱ ያጣው የተመጣጠነ ምግብ አቀንጭሮትና አቀጭጮት …

ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሾፈሮቹ ለኢሳት እንደገለጹት ከኢትዮጵያ ወደ ጅቡቲ የሚሄዱና   ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ እቃዎችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ተፈትሸው ለማለፍ ረጅም ጊዜ እንደሚወስዱባቸው ተናግረዋል። ከ10 እስከ 15 ኪሎ ሜትር የሚደርስ የመኪኖች ሰልፍ መኖሩን የሚናገሩት ሾፌሮች፣ በጸሀይ ላይ በሚያደርጉት ጥበቃ በርካታ ሾፌሮች እየተጎዱ መሆኑንም ይገልጻሉ። ፍተሻው የተጀመረው ዛሬ አራት አመት ገደማ ቢሆንም፣ …