አማኑኤል ዘሰላም

በምርጫ ዘጠና ሰባት ወቅት የነበረውን ሁላችንም የምናስታወሰው ነው። ያኔ የኢትዮጵያ ሕዝብ ድምፁን ለቅንጅት ቢሰጥም፣ ህወሓት/ኢሕአዴግ የሕዝቡን ድምፅ ነጥቆ እስከአሁን ድረስ በኃይልና በጡንቻ እየገዛ ነው። በሥልጣን ላይ ለመቆየት በቀዳሚነት አገዛዙ የወሰዳቸው አምስት እርምጃዎች ነበሩ። እነርሱም …

ሙሉውን አስነብበኝ …

ነፃነት ዘለቀ – ከአዲስ አበባ

የግርማ ካሣን ጽሑፎች አልፎ አልፎ አነባቸዋለሁ። ሀገር ወዳድ መሆኑን ይጠቁማሉ – ጽሑፎቹ። ታታሪ ሰው ይመስለኛል፤ በጥረቱና በሀገር ፍቅር ስሜቱ እወደዋለሁ። ሁልጊዜ ሳይታክት ይጽፋል። ሳይታክቱ የሚጽፉ ብፁዓንነት የሚበዛባቸው ቢሆን ዕድለኞች ግን ናቸው። ብዙዎቻችን እየደከመን መጻፍ ቀርቶ ማንበባችንንም እያቆምን በምንገኝበት ሰዓት አዘውትሮ መጻፍ መታደል ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ዘለቀ ረዲ

የተከበራችሁ አንባቢያን በተለመደው ግንኙነተችን መሰረት ዛሬ ከእዲስ አበባ ተነስቼ ገላን፣ ዱከም፣ ደብረዘይት፣ ቢዮዲማ፣ ሞጆ፣ ሙዳ፣ ኤጀርሳ፣ ቆቃ፣ ዐለምጤና፣ መቂ ዝዋይ አድርጌ ጉዳየን ጨርሼ ወደአዲስ አበባ ለመመለስ ያቀድኩ ቢሆንም በመንገዱ መጨናነቅ ሳቢያ በመጣሁበት መንገድ ተመልሼ አዲስ አበበ መግባት ከባድ እንደሆነ ስለገመትኩ በዚያ መመለስ ሰዓቴን እንደሚጨርስ ስለተረዳሁ በዝዋይ ቡታ ጅራ እዲስ አበባ መመለስን መረጥኩ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ታህሳስ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተለያዩ ዞንና ወረዳዎች አማራ ናችሁ ተብለው በተባረሩ በሺዎች በሚቆጠሩ ዜጎች  ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና አካላዊ ጉዳት እንደተፈፀመ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ባካሄደው ጥናት አረጋግጧል ፡፡ በክልል በተለያዩ ዞንና ወረዳዎች ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ቁጥራቸው ከ10 ሺህ  በላይ የሚገመቱ ዜጐች ለረዥም አመታት ይኖሩበት ከነበረው አካባቢያቸው የዚህ ክልል “ተወላጆች አይደላችሁም” …

ታህሳስ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ብሉምበርግ እንደዘገበው  ከአራቱም አገራት የተውጣጣ ኮሚቴ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከተቋቋመ በሁዋላ፣ በግድቡ ላይ ጥናት የሚካሂዱ ምሁራንንና ይመርጣል። ይህ ቡድን ጥናቱን ሲያጠቃልል ለሶስቱም መንግስታት የጥናት ውጤቱን ያቀርባል። ከዚህ ቀደም የተቋቋመው አንድ አለማቀፍ ቡድን በግድቡ ፕሮጀክት ላይ ተጨማሪ ጥናት እንዲካሄድ ጠይቆ ነበር። ባለፈው ወር በሚቋቋመው ኮሚቴ ላይ አለማቀፍ ተወካዮች እንዲገኙ …

ታህሳስ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የፕሬስ ታሪክ ውስጥ ለ18 ኣመታት በሕትመት ላይ የቆየው የሪፖርተር አማርኛ እና እንግሊዝኛ ጋዜጦች አሳታሚ የሆነው ሚዲያ ኤንድ ኮምኒኬሽን ሴንተር ባለቤትና የቀድሞው የህወሃት ታጋይ አቶ አማረ አረጋዊ በጠና ታመው በአዲስ አበባ በኮሪያ ሆስፒታል ሕክምናቸውን እየተከታተሉ መሆኑን የቅርብ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ አቶ አማረ ባደረባቸው ድንገተኛ ሕመም በኮሪያ ሆስፒታል ሲረዱ 10 ቀናት …

ታህሳስ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያኑ ለኢሳት በላኩት መረጃ ሰኞ እለት ፕራግ በሚገኘው የሳውዲ ኢምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት በጩኸትና የተለያዩ መፈክሮችን በመጠቀም አውግዘዋል። ያዘጋጁትን የተቃውሞ ደብዳቤ ለኢምባሲው ተወካይ ማስረከባቸውንም አክለው ገልጸዋል።

ታህሳስ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-የአለማችን ታላላቅ መሪዎች፣ እና ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት በዚህ ዝግጅት የማንዴላ የትግል ጉዜ ተዘክሯል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ይህን ታላቅ የታሪክ ሰው ለመግለጽ አስቸጋሪ ነው ብለዋል፡፤ እስረኞችን ብቻ ሳይሆን አሳሪዎችንም ነጻ ያወጣ፣ሀሳብን ወደ ተግባር የለወጠ  ሲሉ ማንዴላን ገልጸዋቸዋል። ከእንግዲህ እንደማንዴላ አይነት ሰው አናገኝም ያሉት ኦባማ፣ከማንዴላ ባንስም ማንዴላ ግን የተሻልኩ ሰው …

ማክሰኞ፣ ታኅሣስ 1/2006 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ በብዙ አሥር ሺሆች የተቆጠረ ህዝብ ዕኩልነትን ዕውን ለማድረግ አስቸጋሪ የሆነ የረጅም ጊዜ ትግል ያካሄዱትን የፀረ-አፓርታይድ ትግል መሪውን ኔልሰን ማንዴላን ተሰናብቷል።

በጆሐንስበርግ ሶከር ሲቲ ስታዲየም የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማንና የቀደሙ የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶችን ጨምሮ በርካታ ታላላቅ ዕንግዶች፣ ታዋቂ ሰዎች እና ደቡብ አፍሪካዊያን መጥፎ የአየር ሁኔታ ሳይበግራቸው እኒህን ሁሉ ሰው ”ታታ” እያለ በፍቅር የሚጠራቸውን ሰው በአክብሮት ለመሰናበት ተገኝተዋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ1962 ዓ.ም ኢትዮጵያ ለኔልሰን ማንዴላ ወታደራዊ ሥልጠና ስትፈቅድ የማሠልጠኑን ኃላፊነት የተወጡት ኮሎኔል ፈቃዱ ዋኬኔ ትውስታቸውን ለቪኦኤ አካፍለዋል።

ሥልጠናው “እጅግ ምሥጢራዊ ነበር” ይላሉ የ77 ዓመቱ ጡረተኛ ኮሎኔል።

ኮሎኔል ፈቃዱ ዋኬኔን በአዲስ አበባ መኖርያ ቤታቸው ያነጋገራቸው እስክንድር ፍሬው ያዘጋጀው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል፤ ያዳምጡት፡፡

ግንቦት ሰባት Ginbot-7ግርማ ካሳ

በቅድሚያ ሰላምታዬ ይድረሳችሁ። ከአምስት ዓመታት በፊት ከአንዳንዶቻችሁ ጋር፣ በቅርበት፣ በቅንጅት ድጋፍ ማኅበራት ውስጥ አብረን ሰርተናል። አብረን ለሰላም ለዲሞክራሲ፣ ለሕግ የበላይነት መስፈን፣ ለዜጎች ሰብዓዊ መብት መከበር፣ ለሕሊና እስረኞች መፈታት ስንጮህ፣ ስንሰራ፣ ስንደክም፣ ስንመክር ነበር። መሃከል መንገድ ላይ የፖለቲካ ስትራቴጂ ልዩነቶች ተፈጠሩ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ባለፈው ሐሙስ ምሽት በ95 ዓመታቸው ያረፉትን የቀድሞው የደቡብ ኣፍሪካ ፕሬዝዳንት ኔልሰን ማንዴላን በይፋ ለመሰናበት ዛሬ በጆሃንስበርግ ከተማ ደማቅ የመታሰቢያ ስነስርዓት ተካህዷል።

የUS አሜሪካ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማን ጨምሮ ከ70 በላይ የመንግስታት መሪዎች በስነድርዓቱ ላይ ተገኝቷል።

የዩክሬን መንግስት ከአውሮፓ ህብረት ጋር ከዚህ ቀደም የተስማማበትን ልዩ የንግድና የፖለቲካ ውል ለጊዜው አልፈርምም ማለቱን የሚቃወሙ ኃይላት የጠሩት የአደባባይ ሠልፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል ። ሃገሪቱ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ግንኙነቷ እንዲጠብቅ የሚፈልጉ ተቃዋሚዎችና ደጋፊዎቻቸውና የአውሮፓ መንግስታት የመንግስትን እርምጃ እያወገዙ ነው ።

ፕሬዚደንት ቪክቶር ያኑኮቪች የሚመሩት የዩክሬይን መንግሥት ከአውሮጳ ህብረት ጋ የፖለቲካ እና የንግድ ትብብር ስምምነት ለመፈረም ዝግጁ ባለመሆኑ በሀገሪቱ ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ ግዙፍ ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው።

በአዲስ አበባ የታሪክ እና የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ከመፍረስ የተረፉ የጥንት ቤቶች በታሪክነታቸው ተመዝግበው ለሕዝብ እና ለሀገር ጎብኚዎች አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ ላይ መሆኑ ተነገረ።

በኢንዶኔሽያ የባሊ ደሴት ዋና ከተማ ኑሳ ዱዎ የዓለም ሀገራት የንግድ ሚንስትሮች የዓለም የንግድ ድርጅት በዓለም አቀፍ ንግድ ላይ ያቀረበውን ሰነድ ባለፈው ቅዳሜ ያፀደቁበት ስምምነት የሀገራቱን የኤኮኖሚ ዕድገት

ይድነቃቸው ከበደ Yedenekachew Kebedeይድነቃቸው ከበደ
ህዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም ሕገ-መንግሥቱ የፀደቀበት ቀን ነው። ይህንንም ተከትሎ በመንግሥት አሳሳቢነት እልፍ ሲልም አስገዳጅነት ህዳር 29 በየዓመቱ ከተለያዩ ጎሳ የተወጣጡ ሰዎች ተሰባስበው በመንግሰት ሹማምንቶች ፊት በአደባባይ ከበሮ የሚደለቅበት ቀን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በፎቶሾፕ የተሠራው ከቨር
ባለፈው ሰሞን  tigraionline.com የባሕር ማዶ ዜጎቻችን የሳዑዲ አረቢያውን መጥፎ አጋጣሚ ተቃውመው በኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት የወጡትን ሠላማዊ ሰልፍ ፎቶ ለፖለቲካ ግብዓቱ በማሰብ ለኢሳያስ አፈወርቂ ቱፈዛ የተወጣ ሰልፍ አስመስሎ በፎቶሾፕ በመቀየር ዜና ሠራበት፡፡ አሁን ደግሞ ትላንት ያየሁት በፌስቡክና በትዊተር ላይ የተለቀቀ ‹‹የዕንቁ›› መጽሔትን ከቨር የቀየረ ፎቶ ተመሳሳይ ማጭበርበር ሞክሯል፤ ይህንን ማን እንደሠራው ባይታወቅም ችግሩ ስር እየሰደደ መሆኑን ማሳበቁ ነው እንግዲህ፡፡

በፌስቡክና ትዊተር ላይ የታየው ፎቶ ላይ ቴዲ አፍሮ ‹‹ምኒልክ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ ያደረጉት ጦርነት ለእኔ ቅዱስ ጦርነት ነው›› ብሎ እንደተናገረ ተደርጎ ቀርቧል፡፡ እውነተኛው ላይ ደግሞ ‹‹አመጣጡን ያየ አካሔዱን ያውቃል›› ይላል፡፡ ገርሞኝ የውስጠኛውን ቃለምልልሱን አገላበጥኩ፡፡ ከውስጥ ያለው ስለጦርነቱ የቀረበለት ጥያቄ ላይም ‹‹ቅዱስ ጦርነት›› የሚል ፈልጌ አጣሁ፡፡

እውነተኛው የመጽሔቱ ከቨር

 

የቃለ ምልልሱ ቅንጫቢ

መንግሥት ድህነትን ለመቅረፍ የሚያስችል መንገድ ካልዘረጋ ሰብኣዊ መብት እንደጣሰ መቆጠር አለበት፡፡

ዓለምአቀፉ የሰብኣዊ መብቶች ድንጋጌ(Universal Declaration of Human Rights) የመጀመሪያው አንቀጽ የመጀመሪያው ዓረፍተነገር‹‹All human beings are born free and equal in dignity and rights (ሁሉም ሰዎች ነጻ እና በክብርና መብት ዕኩል ሆነው ይወለዳሉ)›› ይላል፡፡ በግል ሕይወቴ የድህነትን ያህል የሰውን ልጅ ብር የሚያዋርድ ነገር አይቼ አላውቅም፡፡ አሁንም ድረስ፣ በዚህ 21 በምንለው ክፍለዘመን ሰዎች በዘራቸው፣ በጾታቸው፣ በሃይማኖታዊ አመለካከታቸው እና ሌሎችም ክብራቸው ይዋረዳሉ፡፡ ነገር ግን የትኛውም ጉዳይ ሰዎች በድህነታቸው የሚዋረዱትን ያክል በግልጽ እየታየ አይደለም፡፡ በዛሬ ጊዜ ሆቴል በር ላይ በዘሩ፣ ሃይማኖቱ ወይም ጾታውአትገባምየሚባል ሰው የለም፤ በድህነቱ ግን ከበር የሚመለስ አለ፡፡ ሰዎች ምንም ይሁኑ ምን፣ ምንም ይመኑ ምን ድሃ ከሆኑ የሰው ንዑስ ተደርገው የመቆጠር ዕድላቸው ሰፊ ነው፡፡

ብዙ ምሁራንድህነት የሰብኣዊ መብት ጉዳይ አይደለም፤ ድህነትን መቅረፍም እንደየመንግሥታቱ አቅም የሚወሰን እንጂ ሊጠየቁበት የሚገባ ግዴታቸው አይደለምይላሉ፡፡ ምናልባትም ከዓለምአቀፍ ተቋማት መካከል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ብቻ ነውድህነት የሰብኣዊ መብት ጉዳይ ነውእያለ በመከራከር ላይ ያለው፡፡ በሁለትዮሽ ክርክሮቹ መሐል ጥቂት ለመዋኘት ብሞክርም ድህነትን ከሰብኣዊ መብት ጉዳይ አሳንሼ እንዳየው ያሳመነኝ የለም፡፡

አዎ፣ ድህነት የማኅበራዊ ፍትሕ ጉዳይ ነው፤ የኢኮኖሚያዊ መብት ጉዳይ ነው፡፡ ግን የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሰብኣዊ መብቶችም ጉዳይ ነው፡፡ አንዳንዶች የድህነት መቀረፍ ለሰብኣዊ መብት መከበር መንገድ ይጠርጋል ብለው ያስባሉ፤ እኔ ግን ድህነትን መቅረፍ በራሱ አንድ ሰብኣዊ መብት ማክበር ነው ባይ ነኝ፡፡

ተፈጥሮ ለሰው ልጅ የሚበቃ ሀብት አላት፤ ይህንን ማብቃቃት የሚሳናቸውና ሰዎች በድህነት አረንቋ ውስጥ እንዲማቅቁ የሚያደርጉት ስርዓት አልበኞቹ ‹‹ስርዓት ለማስያዝ›› የሚሾሙ መንግሥታት ናቸው፡፡ ሕዝብን ከድህነት አረንቋ ውስጥ ማውጣት ግዴታቸው እንጂ ውለታቸው አይደለም፤ ምክንያቱም ከድህነት መውጣት (በፀጋ መኖር) የዜጎች ሰብኣዊ መብት ነው፡

በቅድሚያ ሰላምታዬ ይድረሳችሁ። ከአምስት አመታት በፊት ከአንዳንዶቻችሁ ጋር፣ በቅርበት፣ በቅንጅት ድጋፍ ማህበራት ዉስጥ አብረን ሰርተናል። አብረን ለሰላም ለዲሞክራሲ፣ ለሕግ የበላይነት መስፈን፣ ለዜጎች ሰብዓዊ መብት መከበር፣ ለሕሊና እስረኞች መፍታት ስንጮህ፣ ስንሰራ፣ ስንደክም፣ ስንመክር ነበር። መሃከል መንገድ ላይ የፖለቲካ ስትራቴጂ ልዩነቶች ተፈጠሩ። «ሁለ ገብ» የሚል የትግል ስልት መርጣችሁ የተለየ መስመር ያዛችሁ። እኛ ደግሞ በዚያ በሰላሙ መንገድ ቀጠልን። […]

ህዳር ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በጅጅጋ ከፍተኛ መስሪያ ቤቶች ውስጥ የሚሰሩ የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የህወሀት  ከፍተኛ የመከላከያ አዛዦች ወደ ሶማሊ ክልል ሲመዱ  ከክልሉ መንግስት ጋር በመተባበር ከፍተኛ ሀብት አጋብሰው እንደሚመለሱ ተናግረዋል። በአሁኑ ጊዜ ተቀማጭነታቸው ጅጅጋ የሆኑት እና በክልሉ ቁጥር አንድ ሀብታም የሚባሉት /ወ/ት ሀዋ የሌተናንት ጄኔራል ዮሀንስ ገ/መስቀል ሁለተኛ ሚስትና የልጅ እናት ሲሆኑ፣ ግለሰቧ …

ህዳር ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በከፍተኛው ፍርድ ቤት ታስረው ከተለቀቁ በሁዋላ ተመልሰው እንዲታሰሩ የተደረጉት የቁጫ ወረዳ የአገር ሽማግሌዎች፣ የዋስትና መብታቸው ተነስቶ ተመልሰው በአርባምንጭ እስር ቤት እንዲታሰሩ መደረጉን ከሽማግሌዎች አንዱ ገልጸዋል። ችግሩን ለፌደራል መንግስት አቤት ለማለት እስከዛሬ ሲመላለሱ የቆዩት የአገር ሽማግሌዎች አንድም ባለስልጣን ሳያገኙ በመቅረት ነገ ወደ አካባቢያቸው ተመልሰው ፍርድ ቤት እንደሚቆሙና እንደ ጓደኞቻቸው የዋስትና …

ህዳር ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል ያለፈቃዳቸው የአንድ ወር ደሞዛቸው የተቆረጠባቸው የቦንጋ መምህራን፣ የስራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ ካስታወቁ በሁዋላ፣ ዋና አስተዳዳሪው ማከስኞ ከመምህራን ጋር ለመነጋገር ቀጠሮ መያዛቸው ታውቛል። ከመምህራን ተወካዮች ጋር የተነጋገሩት ባለስልጣኑ፣ ስምምነት ለመድረስ ባለመቻላቸው ከመላው መምህራን ጋር ለመነጋገር ወስነዋል። መምህራን የተቆረጠባቸው ደሞዝ መልሶ የማይሰጣቸው ከሆነ በአድማው ለመቀጠል እየተናገሩ ነው።

ባለፈዉ ዓመት ደግሞ ሳይንቲስቶች አንድ ግንደ ቆርቁር መሰል የጥንት ወፍ ዝርያ አገኙ። «ኔልሰንማንዴላ» ብለዉ ሰየሙት።ማንዴላ ጀርመናዊዉ ፖለቲከኛ እንዳሉት ታሪክን የዘወሩ ታላቅ ሰዉ ነበሩ።በዚያ ዘመን ግን ሰዉ መሆናቸዉን እንኳ ያወቁት ካንዲት የጥቁሮች ነፃ ሐገር ሲደርሱ ነበር።1962።

የደቡብ አፍሪቃ ብሔራዊ ኮንግረስ ታዋቂ አባልና በተጨማሪ የትጥቁ ትግል ክንፍ፣ «የህዝብ ጦር » (Umkhonto we Sizwe)የተሰኘው ኀይል መሪ የነበሩት፤ 27 ዓመታት በእሥራት የማቀቁትና ዘረኛውን ሥርዓት አፓርታይድን ድል አድርገው ፣ በዴሞክራሲ ለመመረጥ

ወደ ሰሜን አሜሪካ ከማለፋቸው በፊት የምዕራብ አውሮፓ የሥራ ጉብኝታቸውን ትናንት በበርሊን ያጠቃለሉት ፤ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ፣ ኢንጂኔር ይልቃል ጌትነት፤ ስለድርጅታቸው የትግል ስልት፤ ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ይዞታ፤ እንዲሁም፤

የደቡብ አፍሪቃ ብሔራዊ ኮንግረስ ታዋቂ አባልና በተጨማሪ የትጥቁ ትግል ክንፍ፣ «የህዝብ ጦር » (Umkhonto we Sizwe)የተሰኘው ኀይል መሪ የነበሩት፤ 27 ዓመታት በእሥራት የማቀቁትና ዘረኛውን ሥርዓት አፓርታይድን ድል አድርገው ፣ በዴሞክራሲ ለመመረጥ

የዛሬይቱ ቀን በህይወቴ አዲስ ምዕራፍ የጀመርኩባት ዕለት ናት።እናት ሐገሬ ኢትዮጵያን ለቅቄ የሞያሌን ኬላ ተሻግሬ የኬንያን ምድር የረገጥኩባት ታሪካዊ እለት ።ኅዳር ሠላሣ ቀን አስራ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ስምንት ዓመተ ምሕረት ዕለተ ዐርብ ከቀትር በፊት።ከደቡብ ኢትዮጵያ ወደ ሰሜን ኬንያ ጋንቦ ቀበሌ የገባሁበት ቀን ስምንተኛ ዓመት መታሠቢያ።
የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ አስር ቁጥር ሃያ ሦሥትን ይመልከቱ። ባላሠቡትና ባልጠበቁት ጊዜና ሰዓት ከትውልድ ቀዬዎ ሊሠደዱ ይችላሉ።ዛሬ ምስራቅ አፍሪቃ ምድር ወገብ አቅራቢያ ቪክቶርያ ሐይቅ ዳርቻ ላይ ሆኜ የተሠደድኩበትን ምክንያት ሣሠላስል መሠደዴ አግባብነት ነበረው ወይስ እንደ ኮነሬል መንግስቱ ፍርጠጣ ነው ለማለት ህሊናዬ ዘወትር እንደጠየቀኝ አለ።
ሟቹ የወያኔ ጠቅላይ ሚንስትር የግንቦት ሠባቱን የምርጫ ውጤት በአጋዚ ጥይት ከቀለበሡትና ሕገ መንግስቱ በሕገ አራዊት ከተለወጠ በኋላ የሐገር ቤት ሠላማዊ ትግልና የፕሬስ ነፃነት ጥቅምት ሃያ ሁለት ቀን አክትሟል።
ጋዜጠኞች፣የሠብዓዊ መብት ተሟጋቾች ተለቅመው ሲታሠሩ፣ወጣቱ ያለ ሀጥያቱ በየጦር ካምፑ ሲታጎር የኔ ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል ለማንም ግልፅ ነበር። ጥቅምት ሃያ ሁለት አመሻሽ ላይ ሱፍና ከረባት፣መነፅርና ፕሮቶኮል ቀርተው አልባሌ በመልበስና በመምሠል ከቦታ ቦታ ስሽሎኮለክ ብቆይም ነገሮች ከመሻሻል ይልቅ እየተበላሹ በመምጣታቸው ወደ ኬንያ ለመጓዝ ህዳር ሃያ ሁለት አካባቢ የወሰንኩ ይመስለኛል።
ጠቅላይ ሚንስትር ለገሠ ዜናዊ በኛ ላይ ጦር ሲያውጁ ያቀረቧቸው አማራጮች ት<ዝ ይሉኛል።
፩ አርፎ መቀመጥ ፪መሠደድ ፫ጫካ መግባት ፬ቃሊቲ ።
ለነፃነት የሚደረገውን ትግል ለማገዝ በወቅቱ የኔ ምርጫ መሠደድ ነበር።ሠላማዊ ትግል አላዋጣ ሲል ጠመንጃ ማንሣት የግድና ተገቢ መሆኑን ከነማንዴላ ኤኤንሲ ፓርቲ ውሣኔ መማር ይቻላል።
አማርኛ ቃለ መጠይቅ ለቪኦኤ ለመስጠት የሚጠየፉት የብአዴኑ በረከት ስምዖን የማስታወቅያ ሚንስትር በነበሩበት ፩፱፱፪ የፓርላማ ምርጫ ወቅት በአፍሪቃ አዳራሽ የክርክር መድረክ ላይ ወያኔ ስልጣን በጠመንጃ እንደያዘና በምርጫ ቢሸነፍ ስልጣን ለመልቀቅ ዝግጁ ነወይ ስል ላቀረብኩላቸው ጥያቄ ደርግ መብታችንን በመርገጡ ጠመንጃ አንስተናል ሲሉ መናገራቸውን አስታውሣለሁ።መብቱ የተረገጠ ሕዝብ ጠመንጃ ሊያነሣ እንደሚገባ በረከት የተገነዘቡ ይመስላል።
የኔ ድርሻ እንደጋዜጠኛና የሠብዓዊ መብት ተሟጋች ከሐገር ከተሠደዱ ቦኋላ የፈረንጅ ሐገር ኑሮ ለምዶ ሆዳም ዲያስጶራ መሆን ሣይሆን የተሠደዱበትን ዓላማ ባለመዘንጋት ሐገራዊና ህሊናዊ ግዴታን መወጣት ነው።
የፓለቲካ ስደተኛ ነኝ ብሎ የኬዝ ደራሲ መሆንና የስደተኛ መታወቅያ ታቅፎ ከንቱ የተስፈኛ ህይወት መምራትን ልንጠየፈው ይገባል።ሁለት ሺ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሆኖ ወያኔን ወያኔ ብሎ መጥራት የሚፈራ ማንነት ይዞ መንከላወስ በታሪክና በትውልድ እንደሚያስወቅስም መረዳት ያስፈልጋል።
ሁለት ልብ ሆኖ ሁለት ማልያ እየለበሡ በአንድ ሜዳ ላይ መጫወት አይገባም።እኔ የፓለቲካ ስደተኛ ነኝ።የየትኛውም የፓለቲካ ድርጅት አባል አይደለሁም።መሆንም አልፈልግም።ያ ማለት ግን የሐገሬ ጉዳይ አያገባኝም፣ካናዳ ገብቼ የስደት ኑሮ ለመኖር የመጣሁ የኤኮኖሚ ስደተኛ ነኝ፣ኬዜ ተቀባይነት እንዲያገኝ ምርጥ የኬዝ ደራሲዎች የፃፉልኝን ገፀ ባህሪ በተገቢው መድረክ የምተውን ተወናይ።ካልሆነም ፍራሼ ስር የደበቅኩትን ፓስፓርት አድሼ ምሣዬን ካምፓላ በልቼ ለራቴ አዲስ አበባ የምበር ዋቴ።ዛሬ ይህን ሁሉ ያስቀባጠረኝ እንደዋዛ ከሐገር፣ከቤተሠብ፣ከጓደኛ ተለይቼ ሁለት ሺ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሁለት ቀናት በስደት መቆየቴን በመዘከር ነው።
ህይወት ይቀጥላል።አዲስ አበባ ላይ መፃፍና መኖር ብከለከልም ካምፓላ ላይ እየፃፍኩ እኖራለሁ።ብዕሬ ዝም አትልም።እውነትን፣ነፃነትን፣ፍትህን በሐገሬ ሠማይ ላይ እስክመለከት ድረስ እፅፋለሁ።ሕገመንግስቱ ከወሬና ከመነበብ ባሻገር በተግባር እስኪፈፀም፣ሕዝቤ በነፃና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ሕዝብ የሚመርጣቸው ፓርቲዎች ስልጣን እስኪረከቡ ድረስ እፅፋለሁ ፣እናገራለሁ።
ማንዴላን የታራክ ሠገነት ላይ የሠቀላቸው ለነፃነት የከፈሉት ክቡር ዋጋ ነው።ሞት እንደሆነ አይቀሬ ነው ።እየሞቱ ከመኖር ለትውልድ ነፃነት በየመስኩ የአቅማችንን እናበርክት መልክቴ ነው።
እስክንድር፣ውብሸት፣ርዕዬት፣አንዱዓለምና በርካቶች……..የኛ ማንዴሎች ናቸው።
እንደአንዳቸውም ባለመሆኔ ባዝንም ባለሁበትም ቢሆን ስለነሡና ስለሐገሬ ልጮህ እወዳለሁ።አምላኬም ይረዳኛል።ዛሬ አዲስ የልደት ቀኔ ናት።ዕድሜዬም ስምንት ነው።አዲስ ህይወት ከኬንያ ጋንቦ ጀምሬ አሁን ካባላጋላ ላይ ነኝ።የነፃነት ትግሌ ግን እስከመቃብሬ በብዕሬ ይቀጥላል።ትግልእስከመቃብር።
ደረጀ በጋሻው<pen Ethiopian>


   ጎንደር ላይ በታኅሣሥ 20 ለሚኖረን የ‹‹አራቱ ኃያላን›› መጽሐፍ መርሐ ግብር የተመረጠው 
ታየ በላይ ሆቴል አዳራሽ ነበር፡፡ 
ነገር ግን ከጎንደር ከተማና አካባቢው (ከደብረ ማርቆስ፣ ባሕርዳር፣ ደብረ ታቦር፣ አዲስ ዘመን፣ እስቴና ሌሎችም) በመርሐ ግሩ ላይ ለመሳተፍ የተመዘገቡት ታዳሚዎች ቁጥር ከአዳራሹ ዐቅም በላይ በመሆኑ አዳራሽ ለመቀየር ተገደናል፡፡
በዚህም መሠረት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ባደረገልን ድጋፍ መርሐ ግብሩ የሚካሄደው በጎንደር ከተማ ሲኒማ ቤት መሆኑን እንገልጣለን፡፡ በዚሁ አጋጣሚም አስቀድሞ ትብብሩን ላደረገልን ታየ በላይ ሆቴል ላቅ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

ጎንደር ላይ እንገናኝ፡፡

Image

ባለፈው ሐሙስ ምሽት ላይ ዓለማችን ታላቅ ሰው አጥታለች፡፡

የደቡብ አፍሪካ አባትና በዓለማችን ላይ የራሳቸውን አሻራ አስቀምጠው ያለፉት የነፃነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ በተወለዱ በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ተለይተዋል፡፡ የእኝህ ታላቅ መሪ ሕልፈት የዓለማችን ዓይንና ጆሮ በአንድ ቦታ እንዲያርፍ አድርጓል፡፡ በአራቱም የዓለማችን ማዕዘናት ከልጅ እስከ አዋቂ በማዲባ የተሰማውን ሐዘን እየገለጸ ይገኛል፡፡ በተለይ ደቡብ አፍሪካዊያን በማዲባ ሕልፈት የተሰማቸው ጥልቅ ሐዘን እየገለጹ ነው፡፡ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ደቡብ አፍሪካ ታላቅ ልጇን አጣች ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የማንዴላ ሕልፈት ግን ከአገሪቱ አልፎ የዓለማችንን ትኩረት መሳብ ችሏል፡፡ ማንዴላ አፓርታይድን ለማስወገድ ያደረጉት የትግል ጉዞ ወደ ፖለቲካው ዓለም እንዲቀላቀሉ ምክንያት የሆነላቸው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፣ ምድራችን ታላቅ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰብ ማጣቷን ተናግረዋል፡፡ በርካታ የዓለማችን ፖለቲከኞችና ታዋቂ ግለሰቦች አርዓያ የነበሩት ኔልሰን ማንዴላ ቢያልፉም፣ ስማቸው ግን አሁንም ከመቃብር በላይ ውይላል እያሉ ናቸው፡፡

ማንዴላ እንዲህ የዓለማችንን ትኩረት ሊስቡ የቻሉበት ምክንያት በሕይወት ዘመናቸው የሠሯቸው በርካታ ሥራዎች ናቸው፡፡ ማንዴላ የደቡብ አፍሪካን ፀረ አፓርታይድ እንቅስቃሴ በመምራት አገሪቱ ከቅኝ ግዛት ከወጣች በኋላ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚዳንት በመሆን አገልግለዋል፡፡ ማንዴላ የሰው ልጆችን በቆዳቸው ቀለም በመከፋፈል አሰቃቂ ግፍ በሰብዓዊ ፍጡራን ላይ የሚፈጽመውን የአፓርታይድ ሥርዓት ለመገርሰስ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍለዋል፡፡ ማንዴላም ይህንን በማድረጉ ሒደቱ ውስጥ የዘመናቸውን 27 ዓመታት በእስር ቤት እንዲያሳልፉ ተገደዋል፡፡ ማንዴላ ይህን ያህል ጊዜ በእስራት እንዲያሳልፉ የተፈረደባቸው በነጮች የተመሠረተውን የአፓርታይድ መንግሥት ሊያስወግዱ ተነስተዋል በሚል ውንጀላ ነው፡፡

ባለፈው ሐሙስ በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ማንዴላ ግን በዓለማችን ጭቆናን ለሚታገሉ እንደ ምልክት የሚታዩ አርዓያ ግለሰብ ናቸው፡፡ ማንዴላ 27 ዓመታትን በእስራት በማሳለፍ ለነፃነት ያላቸውን ቁርጠኛ አቋም ለዓለም አሳይተዋል፡፡ በ71 ዓመታቸው ከእስር ቤት የተለቀቁት ማንዴላ በደቡብ አፍሪካ ተንሰራፍቶ የነበረውን የአፓርታይድ ሥርዓት ለማስወገድ ያከናወኑት ትግል ግን ሰላማዊ መንገድን የተከተለ ነበር፡፡ ለዚህም ነው በርካቶች ማንዴላን የደቡብ አፍሪካው ማህተመ ጋንዲ የሚሏቸው፡፡

ማንዴላ ምንም እንኳን አሰቃቂና ዘግናኝ የሆኑ 27 ዓመታትን በእስር ቢያሳልፉም፣ ከተቀናቃኞቻቸው ጋር እርቅ በማውረድ የዓለምን ትኩረት መሳብ የቻሉ ታላቅ መሪ ናቸው፡፡ ከባላንጣዎቻቸውም ጋር የእርቅን መንገድ በመከተላቸው የኖቤል የሰላም ሽልማትን መቀዳጀት ችለዋል፡፡

ኔልሰን ማንዴላ የደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚዳንት ከሆኑ በኋላ በአገሪቱ ለሁሉም ዜጎች እኩልነትን በማምጣት ለብዙዎች አርዓያ መሆን ችለዋል፡፡ ይህንንም በማድረጉ ሒደት ማንዴላ የአገሪቱ አንገብጋቢ ችግር የነበረውን ድህነት በዋነኝነት ተዋግተዋል፡፡ ማንዴላ ከፍተኛ መስዋዕትነት በመክፈልና ከራሳቸው በፊት አገራቸውንና ሕዝቡን በማስቀደም በሁሉም ሕሊና የሚታወስ ሥራ ሠርተዋል፡፡

ማንዴላ ‹‹የቀስተ ዳመና›› አገር የተባለችውን ደቡብ አፍሪካ መገንባት የቻሉት በፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው የመጀመሪያ ሥራቸው የሆነውን የብሔራዊ እርቅ ፕሮግራም ይፋ በማድረጋቸው ነው፡፡ በቆዳ ቀለም ልዩነት ምክንያት ክፉኛ የተጐዳው የአገሪቷ ኢኮኖሚም ሊያገግም የቻለው ማንዴላ ቅድሚያ እርቅንና መቻቻልን ማምጣት በመቻላቸው ነው፡፡

ኔልሰን ማንዴላ ከኢትዮጵያ ጋርም ቅርብ ግንኙነት አላቸው፡፡ ማንዴላ በአገራቸው ነፃነትንና ፍትሕን ለማምጣት በሚያደርጉት ትግል ውስጥ የተወሰነ ጊዜ በአገራችን አሳልፈዋል፡፡ ማንዴላ ወደ ኢትዮጵያ የመጡበት ዋናው ምክንያት ወታደራዊ ሥልጠና ለማግኘት ነበር፡፡ ማንዴላ ኢትዮጵያ ሁሌም ቢሆን ከልቤ የማትጠፋ አገር ናት ማለታቸው ይታወሳል፡፡ ኢትዮጵያም ቢሆን ለማንዴላም ሆነ ለደቡብ አፍሪካ ባለውለታ መሆኗ ይታወቃል፡፡ የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መሥራች ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ደቡብ አፍሪካም ሆነች መላው የአፍሪካ አገሮች ከቅኝ አገዛዝ እንዲወጡ ያደረጉት ትግል በታሪክ ሁሌም ይወሳል፡፡

ማንዴላ ከዚህ ዓለም በሞት ቢለዩንም ሥራቸው ግን አሁንም ከመቃብር በላይ ነው፡፡ እኛም ከማንዴላ የሕይወት ጉዞ በርካታ ልንማረው የሚገባ ነገር አለ፡፡ እኝህን የዓለማችን ታላቅ ሰው ልንዘክራቸው ይገባል እንላለን፡፡

reporter amharic

Dawit Solomon
ለባቡሩ የተሰራው ሲፈርስ ምን ይባላል?
——————
የአዲስ አበባ የቀላል ባቡር መስመር ዝርጋታ ያላመሰቃቀለው ህይወት የለም፡፡ያልፈረሰ መንገድ ቤት አይጠየቅም፡፡ታይተው ያልተጠገቡ መኪና የናፈቃቸው መንገዶች ፈርሰዋል ባቡሩ ሊመጣ ነው ተብለው፡፡ንግድ ቤቶች የስንት ቤተሰብ ማገር የነበሩ ከቦታቸው ተነቅለዋል፡፡ስለ ባቡሩ እንጂ ባቡሩ ስላፈናቀላቸው ቤተሰቦች ህይወት ማውራት‹‹ጸረ ልማትነት›› በመሆኑም ንግድ ቤቱ ሲፈርስ ህይወቱ እየፈረሰ እንደሆነ ተንታኝ የማያሻው አባወራ የሆዱን በሆዱ አድርጎ‹‹የልማቱ ደጋፊ ነኝ››ይለናል፡፡
ባቡሩ ያፈረሳቸውን ተሻግረን ስንመጣ ከላይ ለመጥቀስ ከሞከርኳቸው መፍረሶች ጋር የማይገናኝ የመንገድ መፍረስ እናገኛለን፡፡የባበሩ ሃዲድ መዘርጋት የጀመረበት ቦታ ነው፡፡እዚሁ ሸገር ጉምሩክ ፊት ለፊት የባቡር መንገዱን ከመኪና መንገድ የሚለይ ግድግዳ ሳትመለከቱ እንዳልቀራችሁ እገምታለሁ፡፡መከለያው ከሰው ቁመት አይተናነስም የጎን ርዝመቱም የት የሌለ ነው፡፡በሲሚንቶ የተሰራው መከለያ ጠንከር ብሎ የመኪና ግጭትን ተቋቁሞ የታለመለትን አገልግሎት ይሰጥ ዘንድ ብዙ የህዝብ ገንዘብ ፈሶበታል፡፡
ቻይናዊው ኮንትራክተር አበሻውን ቡልዶዘር አሽከርካሪ በእጆቹ እየጠቆመ ቡልዶዘሩ የሲሚንቶው ክምር ላይ ወጣ፡፡በጠራራ ጸሐይ ግድግዳው ተደረመሰ፣ሹፌሩ አንዱን እየናደ ወደ ሌላኛው አመራ፡፡ምን ጥፋት እንደተገኘበት ባላውቅም ግድግዳው እንዲፈራርስ ተደረገ፡፡ሌሎቹ የፈረሱት ለባቡር ተብለው ነበር፡፡ይህ ግን ለባቡሩ ተብሎ የተሰራ በመሆኑ ለምን እንዲፈርስ እንደተደረገ ሊገባኝ አይችልም፡፡አስፈላጊ ሆኖ ባለመገኘቱ፣ግድግዳው በመጣመሙ፣ግድግዳው ሲሰራ የመንገዱ ውበት በመቀነሱ፣መንገዱ በመጥበቡ፣ብቻ እንዲፈርስ የተደረገው በሌላም ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡
እንዴት ነው ነገሩ ግን መቼ ነው ሳንጀምር የምናስበው፣መቼ ነው ህዝብ ማክበር የምንጀምረው፣ምናልባት ይህ የኮንትራክተሮች ጉዳይ ነው ሊባል ይችላል፡፡ቢሆንስ እየሰሩ የሚያፈርሱ ከሆነ ጨረስን ያሉንን እንደማያፈርሱት አልያም ስህተት እንደማናገኝበት በምን ልናምናቸው ነው?

እነሆ ባለ ስልጣናት፣ ‹‹ልማታዊ›› አርቲስቶችና የፓርቲው የኪነት አባላት ሲጨፍሩ ሰነበቱ፡፡ ራሳቸውን ‹‹ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች›› ብለው ጠርተው፣ ኢትዮጵያንም ወክለው፡፡ በእርግጥ እነዚህ ሰዎች አብረው መጨፈር መቻላቸው ራሱ አንድ ነገር ነው፡፡ ባለፉት 23 አመታት የተነዛው ጥላቻ በገንዘብና በሆድ አደርነት የሚሸፈንም አልነበረም፡፡ እንደ ቅስቀሳው ብዛት ካድሬዎች፣ የኪነት ቡድኑ አባላትና ‹‹ልማታዊ›› አርቲስቶች እርስ በእርሳቸው አለመተራረዳቸውም አንድ ነገር ነው፡፡ ችግሩ ከጭፈራ ያለፈ አለመሆኑ ነው፡፡ ጭፈራ ችግር ቢፈታ ኖሮ በአንድ ስታዲየም ውስጥ የተገኙት ፖለቲከኞች፣ የኪነት ቡድንና ‹‹የጥበብ›› ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን 90 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን አሸሸ ገዳሜ ከማለት ወደኋላ አይሉም ነበር፡፡ ጭፈራ ችግራችን ቢቀርፍልን ኖሮ!

ይህ የአንድ ቀን ‹‹የብሄር ብሄረሰቦች›› ጭፈራ ዳቦ መሆን ቢችል ኖሮ የባለስልጣን መኪናዎች በክረምት ጭቃ፣ በበጋ አባራ አልብሰዋቸው የሚያልፉት የጎዳና ተዳዳሪዎች በባዶ ሆዳቸው፣ በጎስቋላው አካላቸውም ቢሆን ለአንድ ቀን ይቅርና አመቱን ዳሌያቸውን መወዝወዝ ባልከበዳቸው፡፡

እውን ጭፈራ ለኢትዮጵያውያን ችግር መፍትሄ መስጠት ቢችል ሳውዲ፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ዚምባብዌ፣ ኢትዮጵያም፣ ማዕከላዊ፣ ቂሊንጦ፣ ጉራፈርዳ፣ ኦጋዴን…… ውስጥ ከመሰቃየት ልክ እንደ ስፖርት ጧት ጧት፣ ልክ እንደ ምግብ ወይንም ክኒን በቀን ሁለት ወይንም ሶስት ጊዜ ቅስቀሳ፣ ዝግጅት፣ ወጭ……ሳያስፈልገን ሚሊዮን ሆነን ከመጨፈር ባልሰነፍን!

ጭፈራ ውሃ ቢሆን ህጻናትና አዛውንቶች አሁን ጀሪካን የሚያጎብጠውን ወገባቸውን ‹‹ለብሄር ብሄረሰቦች ቀን›› ባልለገሙ፡፡ ጭፈራ የመብራት፣ የስራ፣ የትምህርት፣ የቤት…ችግርን ቢፈታ… የህዝቡስ የህዝብ ነው፡፡ ብሄርን፣ ብሄረሰብንና ህዝብን ወክለናል የሚሉትን ተለጣፊ ፓርቲዎች ጭፈራ ከህወሓት ተመጣጣኝ ስልጣን የሚሰጣቸው ቢሆን ኖሮ ባለፈው 23 አመታት የጨፈሩት የትራንስፖርትና የሴቶች ጉዳይን እንደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሲቆጥሩ ባልቆዩ ነበር፡፡ አሁንም ቢሆን ከደብረጽዮን ስድብ፣ ከስብሃት ነጋ ቅብጠት፣ ከአባይ ጸሃዬ ግልምጫ፣ ከመለስ የሙት መንፈስ.. ቢገላግላቸው ምንም ፈቀቅ ሳይል ከነጎደው የእድገቱና… ይልቅ በጭፈራ ትራንስፎርሜሽን ወገባቸውን መቆራረጣቸው ባልከፋ፡፡

እውን ጭፈራ ለህዝብ ስልጣን መፍትሄ ቢሆን ኖሮ እነ ታማኝ በየነም በባዕዳ አገር ከመንከራተት ይልቅ ጅጅጋ ይቀርባቸው ነበር፡፡ ታማኝ እንኳ ወጣት ነው፡፡ አርጅተውም ስለ ህዝብ ስልጣን፣ ስለ ፖለቲከኞች ችግር መናገር ያላቆሙት እነ ዶክተር ሀይሉ፣ እነ ፕሮፌሰር መስፍን፣ አስግደ፣……. ሰሚ ካጣ ጩኸት የአንድና ሁለት ቀን ሆታ፣ ጭፈራና ፌሽታ ሊከብዳቸው አይችልም፡፡ ግን ምን ያደርጋል? ጭፈራ ጭፈራ ነው፡፡ የሞቅታ፣ የስካር፣ የማወናበጃ፣……

መምህሩ ናቸው፤ የእነዚህን ባለሀብቶች የሕይወት ታሪክ ሥሩ ብለው የሰጡን፡፡ ስምንት ባለ ሀብቶች፡፡ እነዚህን ሰዎች የምናውቃቸው በቴሌቭዥን እየቀረቡ ስለ ልማት ሲናገሩ ነው፡፡ አንዳንዶቹ እንዲያውም ተሸልመዋል፡፡ እኛ መምህራችንን ጠየቅናቸው፡፡ እነዚህን ለምን መረጧቸው? ስንል፡፡ እርሳቸውም ‹‹እነዚህን በሦስት መመዘኛ መረጥኳቸው›› አሉ፡፡ ‹‹አንደኛ ልማታውያን ናቸው፣ ሁለተኛ ተሸላሚ ናቸው፣ ሦስተኛ ደግሞ ዛሬ ቢጠሯቸው የማይሰሙ የናጠጡ ባለጠጎች ናቸው፡፡›› አሉ መምህራችን፡፡ ‹‹ስለዚህም ወጣቱ ትውልድ ከእነርሱ ትምህርት መቅሰም አለበት፡፡ ሀብት እንዲሁ አይገኝም፡፡ ተለፍቶ ነው፤ ተደክሞ ነው፡፡ ደም ተተፍቶ ነው፡፡ ‹ፐ› ላይ ለመድረስ ከ‹ሀ› መጀመር ያስፈልጋል፡፡ ከዕንቁላል ንግድ ተነሥተው ሚሊየነር የሆኑ አሉ፡፡ ከሱቅ በደረቴ ተነሥተው ሚሊየነር የሆኑ አሉ፡፡ ከአንዲት ሱቅ ተነሥተው ሚሊየነር የሆኑ አሉ፡፡ ከጉልት ተነሥተው ሚሊየነር የሆኑ አሉ፡፡ እነዚህ ለትውልዱ አርአያ ናቸው›› አሉን መምህሩ፡፡

ስምንት ቡድን ተቋቋመ፡፡ ስምንቱ ቡድኖች አንዳንድ ሚሊየነር ያዙ፡፡ ታሪካቸውን የምንሠራበት ቅጽ ተሰጠን፡፡ የመጀመሪያዋን ብር እንዴት አገኟት?ወደ ሚሊየነርነት በየት መንገድ ተጓዙ? ምን ዓይነት ውጣ ውረዶችን አለፉ? እያንዳንዷን ሀብት እንዴት አጠራቀሟት? የሚሉ ጥያቄዎች ተሰጡን፡፡ እኛም የደረሱንን ባለሀብቶች እያነሣን ‹የኛ ባለሀብት ምርጥ ታሪክ ሳይኖራቸው አይቀርም፡፡ እንዲህ እና እንዲያ ሰምተናል እያልን እንፎካከር ጀመር፡፡ በቡድን የተሰጠኑንን ባለሀብቶች ታሪክ ሠርተን ከሁለት ሳምንት በኋላ ለመገናኘትና የደረስንበትን ለመወያየት ተቀጣጥረን ተለያየን፡፡

ከሁለት ሳምንት በኋላ በመወያያ ክፍላችን ስንገናኝ ሁላችንም ፈገግታችንን ለባለሀብቶቹ ሽጠንላቸው የመጣን ይመስል እንዳኮረፍን ነበርን፡፡ ሁሉም እንደ ነፋስ አቅጣጫ መጠቆሚያ ራሱን ይወዘውዛል፡፡ መምህራችን እስኪመጡ ድረስ የረባሽ ስም ይጻፋል የተባልን ይመስል ዝም እንዳልን ነበር፡፡

መምህሩ መጡና ‹በሉ የደረሳችሁበትን አቅርቡ› አሉን፡፡ ሁሉም ዝም አለ፡፡ ‹‹የቤት ሥራችሁን አልሠራችሁም ማለት ነው?›› አሉን፡፡ ዝም፡፡

የመጀመሪያውን ቡድን ጠሩ፡፡ ልጀቹ ወጡ፡፡

‹‹እኛ ያገኘናቸው ባለሀብት ምንም ነገር አልነበራቸውም፡፡ የሀብት ማግኛ መንገዳቸውም ‹ማመቻቸት› ይባላል፡፡ድንገት አንድ ዘመዳቸው ከአንድ ድርጅት በርካሽ የግንባታ ማሽነሪዎችን እንዲገዙ አመቻቸላቸው፡፡ ማሽነሪዎቹንም ለመግዛት ከባንክ ብድር ተመቻቸላቸው፡፡ ብድሩንም ለመውሰድ ኳላተራል ተመቻቸላቸው፡፡ በዚህም የተነሣ በአንድ ጊዜ በሁለት እጅ የማይነሡ ባለሀብት ሆኑ፡፡››

‹‹እሺ ከድህነት እንዴት ነው ወደ ባለሀብትነት የተለወጡት፣ ሂደቱ ምን ይመስል ነበር››

‹‹ምንም ሂደት የላቸውም፡፡ በድንገት ተነሡ፤ በድንገት አደጉ፤ በድንገት ተመነደጉ››

እሺ እናንተስ› አሉ ወደ ሁለተኛው ቡድን ዞረው፡፡ ልጆቹ ተነሡ፡፡

‹‹የኛ ባለሀብት ምንም ነበሩ፡፡ የሀብት መንገዳቸውም ‹ማስገባት› ይባላል፡፡ ድንገት አንድ ባለ ዘጠኝ ፎቅ ሕንጻ ሲሠሩ ታዩ፡፡ ምንድነው ተብሎ ሲጣራ ሚስታቸው የእነ እንትና ዘመድ ናቸው አሉ፡፡ እንዴው አንድ ቀን ነው አሉ፡፡ መኪና ሙሉ ሞባይል ጭነው ከሐርቲሼክ አዲስ አበባ የገቡት፡፡ ፈታሾቹም ምን አፍዝ አደንግዝ እንደተደገመባቸው አይታወቅም እንደ ኤድስ ማስታወቂያ አላየንም አልሰማንም ብለው አሳለፏቸው፡፡ ይሄው ሚሊየነር ሆኑ››

‹እናንተስ›› አሉ ገርሟቸው ሦስተኛዎቹን ቡድኖች

‹‹የኛ ባለሀብት ደግሞ ንክኪ ናቸው ይባላል፡፡ ሳይነካኩ በፊት ግንበኛ ነበሩ፡፡ ከተነካኩ በኋላ ግን በሞቱ ሰዎች ስም ሳይቀር መሬት እየወሰዱ ቸበቸቡት፡፡ አሁን ስለ መሬት ፍትሐዊ አጠቃቀም ትምህርት የሚሰጡ የሪል ስቴት ባለሀብት ሆነዋል፡፡ ከቀበሌ ቤት ወጥተው ቀበሌ የሚያህል መሬት ወስደው ለቀበሌ ደንብ ማስከበር የሚያስቸግር የሀብታም ቀበሌ የሚሆን ሪል ስቴት እየገነቡ ነው፡፡ ይኼው ነው›› አለ የቡድኑ መሪ፡፡

አራተኛው ቡድን ተነሣ፡፡

‹‹የኛው ለየት ይላሉ፡፡ የሀብት ማግኛ መንገዳቸውም ‹መጠጋት› ይባላል፡፡ ከአንድ ሀብታም ሰው ጋር አንድ ወዳጃቸው ያገናኛቸዋል፡፡ የእርሳቸው ሥራ ሀብታሙ ሲያዝን እርሳቸው ማልቀስ፣ ሀብታሙ ሲስቅ እርሳቸው መንከትከት፣ ሀብታሙ ሲያመው እርሳቸው መርፌ መወጋት፣ ሀብታሙ ሲሸተው እርሳቸው ማነጠስ፣ ሀብታሙ ሲናደድ እርሳቸው መደባደብ ብቻ ሆነ፡፡ ከዚያም እርሳቸውም ሳያስቡት፣ ኧረ እንዲያውም ሳያውቁት ሚሊየነር ሆነው ተገኙ፡፡

አምስተኛው ቡድን ቀጠለ፡፡

‹‹እኒህኛው ባለሀብት ‹መሰጠት› በተባለው መንገድ ነው ሀብት ያገኙት፡፡ ምን ነገር አልነበራቸውም፡፡ ነገር ግን በአንድ ባለ ሥልጣን አማካኝነት እኔ ነኝ ያሉ ፕሮጀክቶች ሁሉ ይሰጧቸው ጀመር፡፡ ቢወዳደሩም ያልፋሉ፤ ባይወዳደሩም ያልፋሉ፡፡ እንኳን የመንግሥት የኤን ጂ ኦ ፕሮጀክቶችም ይሰጧቸዋል፡፡ እነሆ በዚህ መንገድ ዛሬ የሀገሪቱ ወሳኝ ባለሀብት ሆነዋል››

ስድስተኛው ቡድን ተከተለ፡፡

‹‹የኛ ባለሀብት የሀብት መንገድ ‹ብቻ› ይባላል፡፡ አንድን ዕቃ ለማስገባት የሚፈቀድላቸው ‹እነ እገሌ ብቻ› ናቸው፡፡ ስለዚህም በፈለጉት መንገድ የፈለጉትን ዓይነት ዕቃ ያስገባሉ፡፡ በፈለጉት ዋጋም ይሸጣሉ፡፡ መመሪያቸው ብትፈልግ ግዛ ባትፈልግ ተወው ነው፡፡ እኒህ ባለ ሀብት ከዐሥር ዓመታ በፊት አንዲት የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቅ ብቻ ነበረቻቸው፡፡ በአንድ እርሳቸውም በማያስታውሱት ቀን ግን የሆነ ዕቃ ‹ብቸኛ አስመጭ› እንዲሆኑ ተሾሙ፡፡ ተሾመውም አልቀሩ ይኼው ሚሊየነር ሆኑ፡፡

‹ሰባተኛውስ ቡድን› አሉ መምህሩ

‹‹የኛው ሰው የሀብት መንገድ ‹ትብብር› ይባላል፡፡ እርሳቸው መርካቶ ሱቅ ከፍተው ከዱባይ ዕቃ ያመጡ ነበር፡፡ እንድ ባለ ሥልጣን ግን ‹ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ ረዳት እንፍጠርልዎ› አላቸው፡፡ እርሳቸውም ተስማሙ፡፡ ረዳት የመንግሥት ባለ ሥልጣንም ተፈጠረላቸው፡፡ ከእርሱም ጋር ሸሪክ ሆኑ፡፡ እነሆም መንገዱን እርሱ ሲጠርግ ሥራውን እርሳቸው እየሠሩ ባለሀብት ተባሉ፡፡

ጉድ ነው ዘንድሮ አሉ መምህሩ፡፡ ስምንተኛው ቡድን ቀጠለ፡፡

‹‹የዚህኛው መንገድ ‹ቀንዶ› ይባላል፡፡ ባለ ሀብቱ ከብት እያረዱ በመሸጥ ይታወቃሉ፡፡ አንድ ሰው ግን ከብት እዚህ ከምትሸጥ ለምን ድንበር ሄደህ አትሸጥም አላቸውና፡፡ ወሰዳቸው፡፡ የሀገሪቱንም የቀንድ ከብቶች ድንበር እያሻገሩ ሶማሌና ሱዳን መላክ ጀመሩ፡፡ ሰውም ቀንዶ ይላቸዋል፡፡ እርሳቸውም ቀንዳም ባለሀብት ሆነዋል፡፡

መምህሩ ተነሡና አፈጠጡብን፡፡

‹እና ታሪካቸው ይኼ ነው ማለት ነው፡፡ በዚህ አልፈው፣ እንዲህ ሆነው፣ ይህን ተፈትነው፣ ይህንን ውጣ ውረድ አልፈው፣ ይህን ልምድ ቀስመው የሚባል ታሪክ የላቸውም ማለት ነው?›› አሉ መምህሩ፡፡

አንዱ ጓደኛችን ተነሣና ‹‹አዎ፤ ሀብት እንጂ ታሪክ የላቸውም፡፡ ሀብታቸው ድንገቴ ነው፡፡ በቃ ድንገት ተነሥተው እንደ ሮኬት ተተኮሱ፡፡ በቃ፡፡ ከአንድ ቀጥለው ሚሊየን ነው የቆጠሩት፡፡››

‹‹ታድያ እንዴት ነው ለእናንተ አርአያ የሚሆኑት›› አሉ መምህሩም ተናደው፡፡

‹‹አርአያ ባለ መሆን ነዋ› አልናቸው፡፡

© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት የወጣ ነው 

በዳዊትከበደወየሳ

ተጨማሪ ማስታወሻዎችና ከኢትዮጵያ የወሰዱት ሽጉጥ መጨረሻ

የነጻነት ታጋዩ ኔልሰን ማንዴላ በ95 አመታቸው ከዚህ አለም ሲለዩ፤ የተለያዩ አገሮች እንደየራሳቸው ግንኙነት የራሳቸውን ታሪክ ሲያወሩ ነበር። የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ሃዘናቸውን ሲገልጹ ከማንዴላ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት በመግለጽ ነበር። እኔ በምኖርበት አትላንታ ከተማ ዜናው ሲቀርብ፤ ኔልሰን ማንዴላ አትላንታ በመጡበት ወቅት፣ ከነአንድርው ያንግ ጋር ሆነው የማርቲን ሉተር ኪንግ ማዕከልን ስለመጎብኘታቸው ነበር – ዋናው ዜና። ሁሉም አገር ስለማንዴላ የየራሱ ትዝታ አለው። ኢትዮጵያውያንም ስለኔልሰን ማንዴላ የራሳችን ታሪክ እና ትዝታ አለን። እናም ማንዴላ የዛሬ 51 አመት ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ስለነበረው ጉዳይ በማውጋት ታሪካችንን እንጀምራለን።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ዓለም አቀፍ የስደት ድርጅት ከሳዑዲ ዓረቢያ ለተመለሱ ቁጥራቸውም 120 ሺሕ እንደሚደርስ ለሚገመቱ ተመላሽ ኢትዮጵያውያን 13.1 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንዲደረግ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጥያቄ አቀረበ፡፡ ድርጅቱ እንደሚለው ከስደት ተመላሾቹ ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ በመሆኑ የ24 ሰዓት አጣዳፊ ዕርዳታ ያስፈልጋል፡፡ እስካለፈው ሐሙስ ኅዳር 26 ቀን 2006 ዓ.ም. ድረስ ከ100 ሺሕ በላይ ተመላሾችን መቀበሉን ያስታወቀው አይኦኤም፣ ከእነዚህ ውስጥ ከ90 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ የስደት ተመላሾች የቀጥታ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ በየቀኑም ከሰባት ሺሕ በላይ ስደተኞች እየተመለሱ ናቸው ብሏል፡፡ አይኦኤም ለትራንስፖርት፣ ለሕክምና፣ ለምግብና ለተዛማጅ አገልግሎቶች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስታውቆ፣ ቤተሰብ ለሌላቸው 167 ልጆች ዕርዳታ ማድረጉን ገልጿል፡፡

ሃምሳ ስምንት ሕፃናትን ወደ ቤተሰቦቻቸው መሸኘቱን አስታውቋል፡፡ አይኦኤም 2.5 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ቢያገኝም፣ የ13.1 ሚሊዮን ዶላር ክፍተት ስላለ፣ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው አስታውቋል፡፡ ለእያንዳንዱ ተመላሽ በነፍስ ወከፍ 130 ዶላር እንደሚያስፈልገው ገልጿል፡፡ እስካሁን ዩኒሴፍ፣ ዩኤንኤችሲአር፣ የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር፣ የዓለም ቀይ መስቀል ኮሚቴና ሌሎች አካላት የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጋቸውን አስታውቋል፡፡

Image