በቼክ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሚፈጸመውን ጥቃት ተቃወሙ
ታህሳስ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያኑ ለኢሳት በላኩት መረጃ ሰኞ እለት ፕራግ በሚገኘው የሳውዲ ኢምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት በጩኸትና የተለያዩ መፈክሮችን በመጠቀም አውግዘዋል።
ያዘጋጁትን የተቃውሞ ደብዳቤ ለኢምባሲው ተወካይ ማስረከባቸውንም አክለው ገልጸዋል።