ትንሽ ስላቅ፤ የፍትህ ሳምንት በኢትዮጵያ ሊከበር ነው
ያው እንደሚታወቀው ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ፍቅር ከወደቅሁኝ ቆይቻለሁ። ስለዚህ ነጋ ጠባ ኢቲቪን ብጠቅስብዎ አየሰልቹ። ዛሬም “ቸር ያሳደርከኝ ቸር አውለኝ፣ ከተናግሮ አናጋሪ አገናኘኝ” ብዬ ፀሎት ካደረስኩ በኋላ መጀመሪያ ያገኘሁትት የኢቲቪ ዜና አንባቢን ነበር። ባትሰማኝም “ደህና አደርሽ እግዚአብሄር ይመስገን” ብዬ ተቀበልኳት። እርሷም ዜናዋን ቀጠለች። “የፍትህ ሳምንት በኢትዮጵያ ሊከበር መሆኑ ተገለጠ…” አለችኝ። እውነትሽን ነው? ፍትህ …ፍትህ… ፍትህ የቱ…? ብላት …![]()