ጎሹም ሄደላችሁ!
ከተስፋዬ ገ/አብ
የኮሎኔል መንግስቱን መፅሃፍ ሳነብ ከገረሙኝ ነገሮች አንዱ የኮሎኔል ጎሹ ወልዴን ስም አለመጥቀሱ ነበር። ቢያንስ፣ “የታጠቅ ጦር ሰፈር አመሰራረት” በሚለው ምእራፍ ስር እንኳ ስሙን ሊያነሳው በተገባ።
በቂ ምክንያት ማቅረብ ባልችልም ስለ ኮሎኔል ጎሹ በጎ ስሜት አለኝ። ምናልባት የመንግስቱን ስርአት ተቃውሞ ስለኮበለለ እንደ ውለታ ቆጥሬለት ሊሆን ይችላል። ጊዜው አይረሳኝም። ጎሹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ለቆ ሲኮበልል እኔ ደብረዘይት ነበርኩ።
በአየር ሃይልና በአየር ወለዶች የብረት ጫማ ቁጥጥር ስር የነበረችው ደብረዘይት በጎሹ ወልዴ የመኮብለል ወሬ ታምሳ እንደነበር አስታውሳለሁ። “የቡርቃ ዝምታ” ላይ እንደጠቀስኩት፣ ደብረዘይት ላይ የፖለቲካ ወሬ የሚከካው ከአየርሃይል ሆቴል ባንኮኒ ላይ ነበር። እዚያ የማይመጣ የለም። በተለይም ሁሉን አዋቂና አስፈፃሚ የሆኑት መስመራዊ መኮንኖች የሆቴሉ ቋሚ ደንበኞች ናቸው። ለሃሜቱና ለብልግናው ደብረዘይት ምቹ ናት። ዋዝጂፕ እያንኳኩ፣ ከጠመንጃና ከጥይት ፋብሪካ፣ ከአየር መቃወሚያና ከታንክ መገጣጠሚያው ወደ አየር ሃይል ሆቴል ይጎርፋሉ።
ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ አገር ለቆ በኮበለለ ሰሞን ከሆቴሉ ባንኮኒ አካባቢ የሰማሁዋት ግጥም ዛሬም ድረስ ትታወሰኛለች፣
አትመንጥሩ፣ አትመንጥሩ – ደኑን ስንላችሁ፣
ነብሩም አንበሳውም – ጎሹም ሄደላችሁ…
ፖለቲካና ስነጥበብ ሲቀላቀሉ ያሳብዳል። እነዚህ ሁለት ስንኞች ለጎሹ ወልዴ ወገናዊነት እንዲሰማኝ ሳያደርጉኝ አልቀሩም። በዚያው ሰሞን ደግሞ ሌላ ወሬ ወደ አየር ሃይል ሆቴል ብቅ አለ። “ደቡብ ከሚገኘው እዝ 10 ሺህ ወታደሮች ከነትጥቃቸው ከድተው ኬንያ ገቡ” የሚል ነበር። ጎሹ ወልዴ ከአሜሪካ ወደ ናይሮቢ ተመልሶ፣ እነዚያን የከዱ የጦርሰራዊት አባላት እየመራ፣ በሞያሌ በኩል ወደ አዲስአበባ እየገሰገሰ ነው” ተባለ። በወቅቱ በጎረምሳነት መንፈስ፣ “እየገሰገሰ ነው!”፣ “በከበባ”፣ “በማጥለቅለቅ” የሚሉ ቃላት ይስቡኝ ነበር። ምናልባት፣ በ18ኛው ክፍለዘመን ገበሬ አደራጅቶ፣ ፒተርስቡርግን ከብቦ ንግስቲቷን ስላንቀጠቀጣት አመፀኛ ያነበብኩት በዚያው ሰሞን ስለነበር ሊሆንም ይችላል።
ምን ያደርጋል?
የጎሹ ወልዴ ሰራዊት “ከዛሬ ነገ አዋሳ ደረሰ” እያልን ብንጠብቅም ወሬው “የቆሪጥ ፉገራ” ሆኖ ቀረ። በግልባጩ እንዴት እንደሆነ እስከዛሬ ምስጢሩ ባልተነገረ ፍጥነት፣ እኔ ወያኔ ሆኜ፣ እኔ ባቀረብኩት ሃሳብ መሰረት፣ ወያኔ 25 አመታት መንገስ እንዲችል፣ ለቢሾፍቱ ቆሪጥ ነጭ ላም አርደንለት፣ ቆሪጥ “ለ25 አመት ንገሱ! አዲሳባ ግቡ!” ብሎ ስለፈቀደ እንደ ፓሎኒ ኳስ እየነጠርን አዲሳባ ገባን።
ከዚያም እንደገና የጎሹ ወልዴ ስም ተነሳ።
“መድህን የተባለ ፓርቲ መስርቶአል። ጎሹና ቢል ክሊንተን የትምህርት ቤት ጓደኛሞች ነበሩ። ወያኔ አለቀላት!” የሚል የወሬ ምላጭ ጆሮአችንን ሸረካከተው።
በዚህች አለም የህይወት መንገድ ላይ ህይወት ተገላቢጦሽ ስትሆን ብዙ ጊዜ አይቻታለሁ። ዛሬ ጎሹም ክሊንተንም የሉም። የነበረው ሁሉ እንዳልነበር ሟች ሆኖአል። ሟች መሆን ደባሪ ነው። ጎሹ “መድህን” የተባለ ድርጅቱን ለልደቱ በነፃ ሸጦለት ሲያበቃ፣ “ጴንጤ ሆኛለሁ ተውኝ!” ማለቱን ሰማሁ።
“ያ! ቆፍጣና ወታደር ምን ቢገጥመው ይሆን እንዲህ ባንዴ ፊቱ የጨለመ?” ብዬ ጠየቅሁ።
እምነት ላይ ጠበቅ ያሉ ጓደኞቼ፣
“…ተሳስተሃል! ጎሹ ዘላለማዊ የህይወት መንገድ አጊኝቷል። ለራስህ እወቅበት።” አሉኝ።
ፖለቲከኞቹ ጓደኞቼ ደግሞ፣
“…ጎሹን በነገር አሳብደው ከፖለቲካ የጨዋታ ሜዳ ያባረሩት ኢህአፓዎች ናቸው” ሲሉ ‘ምስጢር’ ነገሩኝ። ሁለቱም ምክንያቶች አልተዋጡልኝም። “ጎሹ ከራሱ እየሸሸ ነው” አልኩ።
ርግጥ ነው፣ ጎሹ ከተሰናበተ በሁዋላ ሌሎች ነብርና አንበሳዎች ተተክተው ነበር። ብዙዎች እየመጡ ሄደዋል። ያልቻሉ ተሰናብተዋል። የቻሉ ቀጥለዋል። ስድቡንም፣ ውግዘቱንም፣ ሃሜቱንም ችለው የነፃነትን ብርሃን በሩቅ እያዩ የሚጓዙ አሉ። ህዝብ ምንጊዜም ተስፋ አይቆርጥም። የደከሙትን እየሸኘ አዳዲሶችን ይወልዳል። ቢሆንም ግን …ቢሆንም ግን…እንዲህ ባለው ጊዜ ቢያንስ አሳብን መሰንዘር በጎ በሆነ ነበር…
Ezih Lay Ensmamalen
Tesfaye, you are one of the FINEST writer I have ever read, by any standard. keep writing …..DF from washington DC.
This man has a lot of potential.His pen remind us all the forgotten histories so that we can learn from them.Can we call him a history library? The Ethiopian diaspora primitives can claim they are experts in all and easily intimidate intellectuals from being involved in national issues. I hope you continue to contribute your enormous knowledge without being intimidated by traditionals.
አትመንጥሩ አትመንጥሩ -ደኑን ስንላችሁ፣
ነብሩም አንበሳዉም -ጎሹም ሄደላችሁ… ተስፍሽ በኮፒ ራይት ካልተጠየቅኩ እኛ ደግሞ የዚህ ዘመን ሰዎች ስለሚያሳስበን ነገር ነውና መግጠም ያለብን ግጥሙን በዚህ መልክ ቀይረነዋል /ለነገሩ እገሌም ሄደላችሁ ብለን ለመግጠም ብናስብ እንኩአን ማን ሄደላችሁ ልንል ነው/ አትመኑ አትመኑ -መለስን ስንላችሁ ፣
አሰብን ጋምቤላን-ቤንችን ሸጠላችሁ… የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን ደስ ይለው የነበረው ” የኢትዮጵያ ህዝቦች እንኩአን ደስ አላችሁ
ክንፈና ሃየሎም ሞቱ ስንላችሁ ይሄው ዛሬ ደግሞ
መለስ ሞተላችሁ ”
Tesfish I really tried to get what your message is all about but to no avail if you have any doubts about col. Goshu woldes military and academic biography I can provide you ,nonetheless Goshu being half Oromo and half Amhara with immense knowledge of politics and diplomacy would have been the golden choice to lead the near to disintegration Ethiopia
እውነቱን ብሎአል_ኮለኔል ጎሹ እባክዎን ሃገራችን አጣብቂኝ ውስጥ ገብታለች ያለዉን የወረወረ ፈሪ አይባልም..ተቃዋሚው ጎራ ነገር አለሙ ተጭበርብሮበታል እርሶም
ካሎት እውቀት ቢያካፍሉአቸው የተፈጠሩባትን አገር ተሃደጉአት ማለት ነበረ..እትዮፕያ በአሁኑ ሰአት ከምንግዝየም የበለጠ መሪ ትፈልጋለች እርሶ ልምዱም እውቀቱም አሎት እና እባክዎ አንድ ይበሉን
I admire your potentials on every subject you write. Don’t listen to those who accuse you for their own secret interest to be exposed. When I read news on ethiopian review, I am interested only in Tesfaye¨s article which is informative, educational and truth. Go on Tes!
Colonel Goshu is one of the best well educated, talented person with an outstanding oratory capacity. He is an Ethiopian patriot. He did a great job in his best capacity to bring about democracy in Ethiopia. By the way, Colonel Goshu was a member of the protestant church even when he was in Ethiopia. I would like to appreciate a lot Colonel Goshu for his tireless effort to defend the wellbeing of our beloved country Ethiopia. I do not want to speculate why Colonel Goshu had abadoned politics, because he is the one who knows all the reasons behind it. God bless you and your family Colonel Goshu Wolde!
Correction to Tesfaye’s poem. It was on the walls of some buildings at the Addis Ababa University that was written AS :
Denun ena Zafun chaka Mentrachihu
Anbessa, Kechine, Goshum hedelachihu
Zinjerona Tota bicha Kerulachihu.
But now we have got even the pests.
Elias, this guy Tesfaye admitted to having been literally crazy in Debre Zeit. In his book ” yegazeTegnaw Mastawesha ” he graphically describes how he danced on the streets of down town debre zeit in broad day light having totally lost his mind. In this article, at the beginning of the third paragraph, he writes, ” poletika ena sinetibeb siqelaqelu yasabidal. ” I couldn’t agree more. As you know, today,Tesfaye’s full-time job and obsession is ” poletika ena sinetibeb. ” This guy disrespects anybody that loves Ethiopia and respects any body that hates our country. Why does he want to hear from Col. Goshu who he just accused of selling MEDHIN PARTY to Lidetu? His purpose in writing this article is obvious : It is to vilify and insult yet one more great Ethiopian of Oromo origin because Tesfaye hates Oromos with out separatist agenda. Recently, in an interview in ” Current Affairs” paltalk room, he said he doesn’t think ” Bulcha Demeksa is an Oromo because he loves emperor Haile Sellase too much. ” This mad man hates everything Ethiopian. Try Tsebel !!!
courage Tesfae gebreab
አቶ ተስፋየ
ኮሎኔል ጎሹ ከድሮም ፕሮቴስታንት ነበሩ ስህተት ቁ. 1
የኢህፓን ሰራ እና ሰርጎ ገብ ታግለው አቸንፈዋል ስህተት ቁ 2
ኮሎኔል ጎሹ በስነምግባራቸው በአገልግሎታቸው እና እድሜያቸው አንቱ እንጂ አንተ ሊባሉ አይገባቸውም
ለአገራቸው በአገር ውስጥና በውጭ አገር በጨዋነትና በታማኝነት ሰርተዋል ደክመዋል ታግለው አታግለዋል ምርጫ 97 ምስክር ነው::
ኮሎኔል ጎሹን በኢሳት ብናገኛቸው በጣም ደስ ይለናል::
በአማርኛ እስከጻፍክ ኢትዪጵያዊ ጨዋነትን ብትከተል መልካም ነው
ለሃገራችው የደከሙ ኢትዮጵያውያንን ማክበር ጉዳቱ ምን ላይ ነው? ተስፋየ እንደዎረደ የሰዎችን ታሪክ በስማ በለው ጥላት መቀባት ማቆም ዓለበት:: ተስፋየ በመንደር አማርጝኣ እንደፈለገ መዘባረቁ ለመሆኑ የጤና ነው ትላላችሁ? ተስፋየ ያችን የምትዎዳትን እስታሊችናያ ስትይዝ “Think twice, trice before you pick your pen to write a piece”; that is my sisterly advise. I hope ESAT will interview Colonel Goshu Wolde. God bless our beloved Ethiopia!!!
ስድ አደጉ ተስፋዬ ገብረአብ ኢትዮጵያን በቅን ያገለገሉ ዶ/ር ኮሎኔል ጎሹ ወልዴን አንተ ብሎ ስለጻፈ ትልቅ የሆነ ከመሰለው ተሳስቷል:: ተስፋዬ ከመጽሃፎቹ በአንደኛው ስራ በመፈለግ ላይ እንደነበረና እንዳልቀናው ገልጾ ወዲያው ወያኔን እንደተቀላቀለ ነው የነገረን:: ከሶስትና ከአራት አመት ላልበለጠ ለወያኔ አድሮ አጅቦ አዲስ አበባ እንደገባ መግለጹን ሁሉም የሚያውቀው ነገር ሆኖ ኮሎኔል ጎሹ በ1986 በአሜሪካ ጥገኝነትን ይጠይቃሉ:: ወያኔን ከመቀላቀሉ በፊት ስራ ያጣው ወጣት ተስፋዬ “በአየር ሃይልና በአየር ወለድ የብረት ጫማ ቁጥጥር ስር በነበረችው ደብረ ዘይት” ሁሉን አዋቂና አስፈጻሚ ከሆኑት መስመራዊ መኮንኖች ጋር በአየር ሃይል ሆቴል ባንኮኒ ላይ ወሬ ሲከካ ስለ ኮሎኔል ጎሹ ከሀገር መውጣት ግጥም እንደሰማ ይቀደዳል:: አንባቢ ይፍረድና አንድ ሃይ ስኩል በቅጡ ያልጨረሰ እዚህ ግባ የማይባል ስራ ፈላጊ ተማሪ አየር ሃይል ሆቴል ያውም በብረት ጫማ ቁጥጥር ካለችው ደብረ ዘይት ከተማ ከሚገኝ የአየር ሃይል ሆቴል ከመስመራዊ መኮንኖች ጋር ባንኮኒ ላይ ሲውል:: ተስፋዬ የራሱን የውስጥ ስሜት ለማታለል የተጎዳበትን ጠባሳ ለማሻር በምኞት ፈረስ ወደኋላ ገስግሶ እውነት ያልሆነ ወሬ ነዛብን:: ተስፋዬ በደርግ የመጨረሻዎች አመታት የሚከፈለው የሻእቢያ ኢንተለጀንስ ሰራተኛ ወይ የወያኔ ጆሮ ጠቢ ወይ ቅልጥጥ ያለ ብሩን የሚረጭ የነጋዴ ልጅ ካልሆነ ስራ ፈላጊ ተማሪ ሆኖ ከመሰመራዊ መኮንኖች ጋር በአየር ሃይል ሆቴል ባንኮኒ ላይ ሲያውካካ ይታያችሁ:: ወሬ ቻልኩ አሳመርኩ ብሎ ቀደዳና መውሻከት ተገቢ አይመስለኝም ለዚህም ጉዳይ ተስፋዬ እውነቱን እንደሚነግረን እንጠብቃለን እንደ ባሎኒ ኳስ እየነጠረ አዲሳባ እንደገባ ቆሪጥ ለሃያ አምስት አመት ወያኔን እንዲነግስ እንደፈቀደ አደረገው ወሬውን ሁሉ:: ቸር ያሰማን!