ሁሉም ወደ “ሀገሩ” ከተባለ እኔም ልምጣ፤ አቶ መለስም ይውጣ (ብልስ?)
አቤ ቶኪቻው
መጀመሪያ ቆይ ርዕሱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩን አንቱ ያላልኩት በትህትና ጉድለት ሳይሆን ርዕሴ ቤት እንዲመታልኝ ፈልጌ ነው።
ዛሬ እና ትላንት ከደቡብ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎችን አስመልክቶ ሀሳቤን ላካፍላችሁ ሙከራ አድርጌያለሁ። እውነቱን ለመናገር እየተፈጠረ ያለው ነገር በጣም የሚያስጨንቅ ነው። ለዚህም ነው ደጋግሜ ነገሩን ማንሳቴ ወደፊትም ደግሜ አነሳዋለሁ።
ታድያ በእናት ድርጅታችን ኢህአዴግ ውስጥ “የብሎግ እና ፌስ ቡክ ጨዋታዎች አደናቃፊ ዋና የስራ ሂደት ባለቤቶች” በሰጡት አስተያየት ተነስቼ ትንሽ ጭማሪ ይዤ መጥቻለሁ። በርግጥ በርካታ ወዳጆቼ መልስ ሰጥተዋቸዋል እኔም ብጨምርላቸው ግን ክፋት የለውም።
በተለይ ዮሴፍ የተባለ ወዳጃችን ይህንን ነገር በተደጋጋሚ መጠየቄ አልተዋጠለትም መሰለኝ በፃፈልኝ አስተያየት፤
“…የሆነ የትግርኛ ምስሌያዊ አነጋገር አስታወስከኝ ”ዐሻስ’ያ ሐደ ደርፉ”ልተርጉምልህ አይደል የሞኝ ዘፈን ሁሉ ግዜ አንድ አይነት ነው እንደ ማለት ነው ነገሮችን እየደጋገምክ ስትጽፍ እንደፊትህ ( ይቅርታ የሞኝ የሚመስል ፊት ስላለህ ነው) አንተም ሞኝ እየመሰለከኝ መጣህ!”
በማለት ወርፎኛል። ይህ ወዳጄ የኢህአዴግ ቀንደኛ ደጋፊ መሆኑን በተለያዩ ሰላማዊ ሰልፎች እና ሰላም ባላቸው አበሎች ያረጋገጠ ይመስለኛል። ጎበዝ እንዲህ ነው እንጂ “እየበሉ እየጠጡ ዝም የጋን ወንድም” ከመባል ድነሃል። እናም ወዳጄ ዮሴፍ ለሚከፈለው አበል ጥሩ አገልግሎት እየሰጠ ስለሆነ ለትጋቱ ላመሰግነው እወዳለሁ።
ምን መሰለህ ዮሴፍ እንግዲህ ሞኝ ከመሰልኩህ አይቀር አሁንም ልጠይቅህ ነው። ቀጥሎም ነገሩ ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ እኔም ሌሎች ደጋግመን መጠየቃችንን እንቀጥላለን! በሌላ አባባል መነዛነዛችን አይቀርም። በቅንፍ (የግድቡን ዜና እና ዜማ ያኽል ግን ሰዉ “ኤጭ አሁንስ…” እስኪለን ድረስ አይደለም)
በነገራችን ላይ የደቡቡ ፕረዘዳንት አቶ ሽፈረው ሽጉጤ የወሰዱት ርምጃ ምን ማለት እንደሆነ ገብቶሃል? ከገባህስ ትክክል ናቸው ብለህ ታስባለህ? እውነቱን ለመናገር ወዳጄ ርምጃው ገብቶህ ቢሆን፤ ቢያንስ ቢያንስ ለአቶ መለስ ህልውና ስትል ነገሩን ትቃወመው ነበር።
ከአማራ ክልል የመጡ ዜጎችን “ወደ ሀገራችሁ ሂዱ!” ብሎ ማባረር ትክክል ነው ብለህ ካሰብክ እደነቃለሁ። (አንቅሃለሁ አላልኩም። ማነቅ ከኛ ወገን አይደለችም)
“ብሄር ብሄረሰብ እጅ ለእጅ ተያይዞ አባይን ይገነባል ህዳሴን ያበስራል ወዘተ ይወዝታል…” የሚባለው ታድያ እንዴት ነው? አንዱ ብሄር አንዱ ዘንድ ሄዶ መኖር ካለቻለ እጅ ለእጅ የሚያያዙት “በብሉቱዝ” ነው? እረ እርሱም ቢሆን ተቀራርቦ መቀመጥን ይጠይቃል!
እንደኔ እምነት አቶ መለስ ዜናዊም ቢሆኑ በአቶ ሽፈራው ሽጉጤ ውሳኔ ይስማማሉ ብዬ አላምንም። ነገር ግን ተስማምተው፤ እሳቸውም “በደቡብ ክልል የሚኖሩ የሌላ ክልል ተወላጆች ወደ ሀገራቸው መዛወራቸው አግባብ ነው!” ብለው ውሳኔውን በይፋ ካደነቁ፤ ያኔ በሰፊው እፅፋለሁ። ምን ብለህ አትለኝም? አቶ መለስም ወደ እናት ሀገራቸው ኤርትራ ይሂዱ! እኔም ወደ እናት ሀገሬ አዲሳባ እመጣለሁ!
ዮሴፍ ለምን ግን ክፉ ታናግረኛለህ?
ለማንኛውም በብሎጋችን ቆይታህ ይቀጥል!
ኣቤ አበጀህ: ውቭ በበላበት ይጮሀል ነው ነገሩ::
ኢትዮጵያዊ የትም ሂዶ የመኖርና የመስራት መብቱ ነው:: የመለስ መንግስት ግን እርስ በርሳችን እንድንተላለቅ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም:: ደግነቱ የኢትዮጵያ ጠላቶችና ተላላኪያቸው መለስ እንዳማራቸው ይቅር እንጂ አሁን የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላቱ ወያኔና አጫፋሪዎቹ ብቻ መሆናቸው ገብቶታል. ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር::
ከመቕለ
ዮሴፍ የሚስማማ አይመስለኝም:: ለምን አትልም….አማራ ከደቡብ ይውጣ…አማራ ከኦሮሚያ ይውጣ…ከተባለ..ደቡቡ ከአማራ ይውጣ..ኦሮሞው ከአማራ ይውጣ…..እያለ እያለ ትግሬውም ይውጣ ይባላል, በዚያን ጊዚ ማ ይጎዳል? አዲሳባ እኮ የኦሮሚያ ነች:: ናዝሬት የኦሮሚያ ናት:: አዋሳ የደቡብ ናት:: ባህር ዳርና ጎንደር ያማራ ናቸው:: በጠቀስኩዋቸው ከተሞች ያሉትን ግብዳ ህንጻዎች የትግሬ መሆናቸዉን ከረሳው ይዉጡ ሊል ይችላል:: በዚህ ጉዳይ ቀዳሚ ተቃዋሚ ትግሬዎች ይሆናሉ ብዬ ነበር:: ጉዳቱ በነሱ ስለሚብስ:: መለስ ይሞታል (ቢበዛ ጃጅቶም ቢሆን), ይህ የተበደለ አማራ ግን አራስ ነብር ሆኖ እንደሚኖር አትጠራጠር:: ታሪክን ማጥፋት አይቻልም:: በቀል ስንወራረስ መኖራችን ብቻ ነው የሚያሳዝነው:: መለስም ኢሃዲግም ይጠፋሉ ኢትዮጵያ ግን ትኖራለች:: ትግራይ ብትገነጥል እንኩውን ቅሚ የሚረሳ አይመስለኝም:: ወደ ልቦናችሁ ተመለሱ::
thank Abea we also back to our land ETHIOPIAN and WEYANA and its fellows go to Tigray
ወይኔ ወያኔ ጎትቶ ወደ ዘር ፖለቲካ ከተተን?! ግድ የለም ወንድሞች እህቶች: መጨረሻ ላይ እኛ እናሽንፋለን::
ቶኪቻው አቦ ይመችህ ሁሉም ወደ እናት ሃገሩ መለስንም ወደ ኧርትራ ይመችው ይሆን?
አቤ ቶክቻው ሆይ እንደምን ሰነበትክሳ፡፡
ፅኁፎችን በተወሰነ አልፎ አልፎ አነባቸዋለሁኝ፡፡በእርግጥም አንዳንዶቹ ያስቁኛልም፡፡ቁምነገርን በቀልድ ብጤ እያዋዛህ ማቅረብህ አንባቢ እንዳይሰለችብህ ለማድረግ ችለሃል ጥሩ ነው፡፡ቁምነገርን በቀልድ እያዋዛህ አርትስቲክ በሆነ መንገድ ማቅረብህ እንዳለ ጥሩ ሆኖ ግን ፅሁፍህ አንዳድንድ ጊዜ ግን ጥልቀት ያለው እውቀት የጎደለው የሚሆንበት ጊዜ አለ፡፡ለምሳሌ አንድ ወቅት ቴሌ-ቪዥን የሚለውን ቃል ቴሌ እና ቪዥን ብለህ ነጣጥለህ ካቀረብከው በኋላ ቴሌ የሚለውን እንደተለመደው የቴሌኮሙኒኬሽን የስልክ አገልግሎት የድምጽ ማስተላለፍ እንደሆነ በተሳሳተ መንገድ ተረጎምከው፡፡በእርግጥ ቴሌ(Tele) ማለት ከርቀት ወይንም እርቀት ማለት ሲሆን አጠቃቀሙም በርቀት የመገናኘት ቴክኖሎጂን ለማመላከት የታሰበ ቃል ነው፡፡ስለዚህም Tele-Communication ሲባል የርቀት ግንኙነት ማለት ነው፡፡ይህንን እንኳን እንዲያው ለማት ያህል እንጂ እንደትልቅ ስህተት በመቁጥር አይደለም፡፡ይልቁንስ በዚህ ፅሁፍህ ላይ ስለተሳሳትከው ነገር ጥቂት የተሰማኝን አንድ ሁለት ልበል፡፡
1ኛ)ኢህአዲግ የሚባል ነገር በስም ካልሆነ በስተቀር በተግባር ትርጉም ባለው መንገድ የለም፡፡ያለው ወያኔና የወያኔ ቀንደኛ ዋና አለቃ መለስ ዜናዊ ነው፡፡ስለዚህም የሌለን ነገር እንዳለ በማስመሰል ህዝብን አታሳስት፡፡ለምሳሌ ኢህአዲግ የሚባለውን ጥቅል ሽፋን ስትከፍተው በውስጡ የምታገኘው ኢህአዲግን አንድ ላይ ሆነው ግንባር የፈጠሩ ሌሎች ፓርቲዎችን ጭምር ሳይሆን እራሱን ወያኔን ብቻ ነው፡፡ለምሳሌ ባሁኑ ፓርላማ ውስጥ ስንት የተቃዋሚ ፓርቲ አባል አለ?አንድ ነው ያለው፡፡ኢህአዲግ 99.6 ፐርሰንት ካሸነፈ ኢትዮጵያ ውስጥ በስም ካልሆነ በስተቀር በተግባር የመድብለ-ፓርቲ ስርዓት አለ ለማለት አይቻልም፡፡ልክ እንደዚሁ ኢህአዲግ የሚባል ነገር የለም ያለው ወያኔና ወያኔ ብቻ ነው፡፡ኢህአዲግ የሚባለው ስም የተፈጠረው ኢትዮጵያ ወያኔ በሚባል ከአንድ ዘር በወጣ ትግሬዎች ነው የምትገዛው እንዳይባል ወያኔ ማስክ አድርጎ ህዝብንና አለምን የሚያሳስትበት ጭንብል ነው፡፡
2ኛ) “እንደኔ እምነት አቶ መለስ ዜናዊም ቢሆኑ በአቶ ሽፈራው ሽጉጤ ውሳኔ ይስማማሉ ብዬ አላምንም።”በማለት የፃፍከው እጅግ ሲበዛ አሳሳች ነገር ነው፡፡ይህንን እርምጃ እንዲወሰድ አስቀድሞውኑ ማን ሃሳቡን አቀርቦ ለክልል መስተዳድር ትእዛዝ ሰጠና ነው መለስን የምትሸፋፍነው እረ? ነው ወይንስ እንደዚህ አይነት ከባድ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ኢትዮጵያ ውስጥ ክልሎች የራሳቸው ሙሉ ስልጣን አላቸው ብለህ ልትሰብከን ነው?እውን አንተ ስታስበው ሽፈራው ሽጉጤ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ዜጎችን ከግብርና ቀያቸው በዚህ አይነት ሁኔታ ለማፈናቀል ይህንን ያህል ስልጣን አላቸው ብለህ ታስባለህን?አቤ ቶክቻው በዚህ አይነት አስተሳሰብህ እራስህ ተጃጅለህማ እኛንም መልሰህ አታጃጅለን እንጂ፡፡እርምጃው በአቶ መለስ ቀጥተኛ ውሳኔና ትእዛዝ የተወሰደ ነገር ነው፡፡ይህ አይነት የተለመደ የፖለቲካ ቁማርና ጨዋታ የፊደል ሀሁ ካልገባህማ መጣጥፍህን ብታቆም ይሻልሃል፡፡
በስተመጨረሻም የምመክርህ ነገር ሀገራዊና አለም አቀፍ የሆኑ ሳይንሳዊ ቴክኖሎጂያዊ ኢኮኖሚያዊና የፖለቲካዊ ነገሮችን ከመፃፍህ በፊት ከአስተማማኝ የመረጃ ምንጮች መረጃ አሰባስብ፡፡አስተማማኝ ሲባል ደግሞ የተለመዱ Mainstream ጋዜጦችና ሚዲያዎችን የተለመደ ያልበሰለ ጥራዝ-ነጠቅ ወሬ ብቻ ሳይሆን ሌሎች አማራጭ(Alternative)ሚዲያዎችን ጭምር ማለቴ ነው፡፡ያለበለዚያ እያዋዙ በቀልድ አርትስቲካዊ በሆነ መንገድ የምታቀርባቸው መጣጥፎችህ ቁምነገር የሚያስጨብጡትን ያህል በቅጡ ካልታሰበባቸው ደግሞ እንደዚሁ በተቃራኒው እያዋዙ ህዝብን ሊያሳስቱ ይችላሉ የሚል ፍርሃት አለብኝ፡፡በእርግጥ አንድ ፅሁፍ ሲቀርብ በአንተ አይነት አካሄድ ባለ አርትስቲክ አቀራረብ ሲኖረው አንባቢን እንዳይሰለች ያደርጋልና ጥሩ ነው፡፡ነገር ግን የሚያብለጨልጭ ነገር ሁሉ ወርቅ አይደለምና ፅሁፉ ባማሩ ቃላት ተከሽኖ መቅረቡና ከውጪ ሲያዩት ማማሩ ብቻ በራሱ የውስጡን ወሳኝ የሆነውን ይዘትና ቁምነገር ትክክል ያደርገዋል ማለት አይደለም፡፡ለማንኛውም አድናቂህ ነኝ በርታ፡፡የሰጠሁህንም ገንቢ አስተያየት አስብበት፡፡