ሰማያዊ ቀለም በኢህአዴግ ላይ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል

• ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ለቀለም አብዮት ከቻይና 20 ሺህ ቲሸርቶችን አስገብቷል›› ምክትል ሳጅን መላኩ
• ‹‹አብዮት እየጠራ ያለው ኢህአዴግ ነው›› አቶ ዮናታን ተስፋዬ
Image
በትናንትናው ዕለት ፖሊስ የጥምቀትን በዓል ለማስተባበር በቀጨኔ መድሃኒያለም የተሰበሰቡ የበዓሉ አስተባባሪዎችን ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ለቀለም አብዮት ከቻይና 20 ሺህ ቲሸርቶችን ስላስገባ ሰማያዊ ቲሸርት እንዳትለብሱ›› ሲል ማስጠንቀቁን ተወካዮቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ሰማያዊ ቲሸርት እንዳይለበስ ያስጠነቀቁት የቀጨኔ ማዘዣ የወረዳ 4 ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ሳጅን መላኩ የጥምቀት በዓልን ለማስተባበር በቀጨኔ መድሃኒያለም የተሰበሰቡትን 150 ያህል ወጣቶች ‹‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ለቀለም አብዮት ከቻይና 20 ሺህ ቲሸርቶችን አስገብቷል፣ ቲሸርቶቹ አዲሱ ገበያ አካባቢ እንደሚገኙ መረጃ አግኝተናል፡፡ ማንም ሰው ሰማያዊ ቲሸርት እንዳይለብስ፡፡ ትዕዛዙ ከበላይ አካል የመጣ ነው›› ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ ተወካዮቹ ለጥምቀት ያዘጋጁዋቸው ቲሸርቶች ከፖለቲካ ጋር ግንኙነት እንደሌላቸውና ከመልበስም እንደማይቆጠቡ በመግለጻቸው ጉዳዩ ባለመግባባት ተቋጭቷል፡፡

የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ መላከ ሰላም ቆሞስ አባ ፍቅረማሪያም ፖሊሶቹንና የበዓሉን አስተባባሪዎች ለማስታረቅ ጥረት ቢያደርጉም ፖሊሶቹ ‹‹ከበላይ አካል የመጣ ትዕዛዝ በመሆኑ እኛ የምንወስነው ነገር የለም፡፡›› በማለታቸው ባለመግባባት ተጠናቅቋል፡፡ ከቲሸርት በተጨማሪ ሰማያዊ ዣንጥላም እንዳይያዝ ፖሊሶቹ መከልከላቸውን የበዓሉ አስተባባሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ስለ ሁኔታው ያነጋገርናቸው የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ‹‹ኢህአዴግ ህዝቡን ስለማያምነው የማያስደነግጠው ነገር የለም፡፡ በደነገጠ ቁጥር ህዝብን የሚከለክለው ለዚህ ነው፡፡ አብዮት እየጠራ ያለው ራሱ ኢህአዴግ ነው፡፡ ምን ያህል ለመድብለ ፓርቲ ስርዓት ግንባታ በሩ ዝግ እንደሆነ፣ ይህንም ሰብሮ ለመውጣት የተዘጋጀ ኃይል እንዳለ፣ ከዛ ውስጥ ሰማያዊ አንዱ መሆኑን ያውቀዋል፡፡›› ሲሉ የኢህአዴግን የስጋት ምንጭ ከምን እንደመነጨ ገልጸውልናል፡፡ ኢህአዴግ ህዝቡን በሆነ ባልሆነው ለማሸማቀቅና ለመከልከል ቢሞክርም ለውጡ እንደማይቀር፣ ፓርቲያቸው ይህንን ለውጥ ለመምራት የተዘጋጀ መሆኑንም ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ ኢህአዴግ እንዲህ ከሰጋም ‹‹አዲሱ ገበያን እንዳያቃጥለው እሰጋለሁ›› ብለዋል አቶ ዮናታን፡፡

በሌላ ዜና የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ንግድና ኢንዱስትሪ ሰራተኞች ሰማያዊ ቲሸርት (የደንብ ልብስ) ተሰርቶ መጥቶላቸው የነበር ቢሆንም በቀለሙ ምክንያት እንዳይለበስ በመከልከሉ ቢጫ ቀለም ያለው ሌላ ቲሸርት እንደተሰራላቸው ሰራተኞቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ ‹‹የመለስ ፋውንዴሽን›› ካሰራቸው ቲሸርቶች መካከል ሰማያዊ ቀለም ያላቸው እንዳይለበሱ መከልከሉን ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

Image

ክርስቲያኖች ለሀገር መሪዎችና ለሰላም እንድንጸልይ ታዘናል።እርቅን፥መግባባትን ማወጅ ሃላፊነታችን ነው፤የሚያስተራርቁ ብጹአን ናቸው ተብሎ ተጽፏልና::

በቅርቡ በሀገራችን ምርጫ ይካሄዳል።ከዚሁ ጋር ተያይዞ ፉክክር፥ክርክር፥ውድድር ይኖራሉ።አንዳንዴም በሌላውም ዓለም እንደሚታየው መረር ያሉና መስመር ሊያስለቅቁ የሚችሉ ሽኩቻ ስድብና በጥላቻ ላይ የተመሰረታ ዘመቻ ይታያል።ከዚህም በፊት በሀገራችን ብዙ ሰዎች የሞቱበት አሳዛኝ ሁኔታ ተከስቶ ነበር።ያ እንዲደገም አንፈልግም።ለሰላምና ለመግባባት እንጸልያለን።

ገዢው ፓርቲ የፖለቲካ ውድድር ማድረግ እንዲችሉ ሜዳውን ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ማመቻቸት ይጠበቅበታል። ምርጫ ቦርድ፥ፍርድ ቤትና ሚዲያው ሁሉንም እኩል የሚያስተናግዱ ሊሆን ይገባል።ኢትዮጵያ የምታድገው የተለያዩ ሃሳቦች ተፋጭተው ከውድድር በሚገኝ የነጠረ አስተሳሰብ ነው።ተቃዋሚ ሲኖር ለገዢው ፓርቲ መስተዋት ይሆናሉ፤ቁጥጥርና ክትትል ያደርጋሉ፤ሙስናን ሌሎች ህገወጥነትን ያጋልጣሉ።ተወዳድረው ከተመረጡ ደግሞ ሀገር የመምራት እድል ያገኛሉ።

የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች እንግልትና እስራት በተለያዩ ባለስልጣኖች ይደርስባቸዋል።እነዚህ በአግባቡ ታይተው መፍትሄ ሊበጅላቸው ይገባል።ወንጀል የሰሩና ያልሰሩ መለየት አለባቸው።ባልተጣራ ሁኔታና በግል ቂም በቀል ንጹህ ሰው በፍጹም መንገላታት የለበትም።

መንግስት ምንም አላደረገም ማለት አይቻልም።ሀገሪቷ ከቀደሙት መንግስታት የተሻለ የዲሞክራሲ ብልጭታ ታይቶባታል።ሆኖም ግን ብዙ የሰብአዊ መብት ጥሰት በባለስልጣኖች ይፈጸማል። ሳይውል ሳያድር በዜጎች ላይ በደል የሚያደርሱት ላይ እርምጃ መወሰድ አለበት።የሰብአዊ መብት ጥሰት ከባድ ወንጀልና ሃጢያትም ነውና።

ሰሞኑን በአንዳንድ ፓርቲዎችና በምርጫ ቦርድ መካከል ያለው መቃቃር በሰላምና በመግባባት እንዲያልቅ እንጸልያለን።
እነዚህ ፓርቲዎች ክፍተኛ ዝግጅት አድርገው ለመወዳደር ተነስተዋል፤አንዳንድ ግድፈቶች አሉ ከተባለ በማለፍ በተቻለ መጠን ምርጫውን እንዲካፈሉ መንግስት መጣር አለበት።

ተፎካካሪ ፓርቲዎች በመካከላቸው የሚነሱትን ልዩነቶች ብስለት በተሞላበት መንገድ በውይይት መፍታትና አንድነት መፍጠር ሀገራዊ ግዴታቸው መሆኑን በውሉ ሊያጤኑት ይገባል። በአንዳንዶች የምናየው ስር የሰደደ ጥላቻ፥ስድብ፥የሰውን ስብእና ማዋረድና ዘረኝነት መግባባትንና እርቅን ይጎዳልና በአስቸኳይ መቆም አለበት።

በሀገራችን የዲሞክራሲ ግንባታ ትልቅ ሚና የሚጫወቱና ባሁን ሰአት ካሉት ፓርቲዎች ሁሉ በተሻለ ደረጃ ላይ ካሉት ከአንድነትና መኢአድ ጋር ያለው ችግር ተወግዶ ወደ ምርጫው እንዲገቡ ያስፈልጋል። ምርጫ ቦርድም ነገሩን በቅንነት በማየት ጥቃቅን ግድፈቶችን ቸል በማለት ወደ ምርጫው እንዲገቡ ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል ብለን እናምናለን።ይህ ካልሆነ ግን ለሚገነባው የመድብለ ፓርቲ( multi-party) ሲስተምና ለሃገሪቷም ትልቅ ውድቀት ይሆናል።እነዚህም ፓርቲዎች በሰላማዊ ትግል ላይ ተስፋ ይቆርጣሉ።እነርሱ ወደ ህዝባዊ እምቢተኝነት(Civil Disobedience) እንገባለን እያሉ ነው፤በዚህም ሀገሪቷ ወደ አላስፈላጊ ውጥረት ውስጥ የምትገባ ሲሆን ይህ ደግሞ የሚካሄዱትን የልማት ስራዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሊያዳክም ይችላል።

ዛሬ በኢትዮጵያ አንዱ የጎደለው ነገር ቅንነት ነው።ቅንነት ከሌለ መጨቃጨቅ፥መካሰስ፥ፍርድ ቤት መንከራተት ብቻ ይሆናል።አንዱ አንዱን ለማጥቃት ሰበብና ምክንያት ብቻ ነው የሚፈልገው፤አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱትም አይነሳምና። ስለሆነም ችግሮች ሁሉ የሚፈቱት በመነጋገርና በመከባበር ነው።ያለፈውን በደል ይቅርታ በመጠያየቅ ህዝባችን ከድህነት የሚወጣበትን መንገድ ማፋጠን እንጂ እኛ ለስማችንና ለክብራችን ስንከራከር ህዝብ ማለቅ የለበትም።

እግዚአብሔርም ይሄን አይወድም፤ይቅር ተባባሉ፥ተከባበሩ፥ክፉን በመልካም አሸንፉ እንጂ በክፉ አትሸነፉ ነው ያለው።ሌላ አማራጭ የለም። “እርስ በርስ መግባባት፥ሀገርን መገንባት” መርሃችን ይሁን።

አብያተ ክርስቲያናትና የሃይማኖት ተቋማት እውነትን በፍቅር የመናገር ሃላፊነትና ግዴታ አለባቸው። ቅንነት ለኢትዮጵያ!
ፍቅርና ፍትህ ለኢትዮጵያ!

ዳንኤል ጣሰው

ከኢትዮጵያ ተነሺ አብሪ

“አንድነትና መኢአድ ጋር ያለው ችግር ተወግዶ ወደ ምርጫው እንዲገቡ ያስፈልጋል። ምርጫ ቦርድም ነገሩን በቅንነት በማየት ጥቃቅን ግድፈቶችን ቸል በማለት ወደ ምርጫው እንዲገቡ ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል ብለን እናምናለን:: …. እናምናለን።ይህ ካልሆነ ግን ለሚገነባው የመድብለ ፓርቲ( multi-party) ሲስተምና ለሃገሪቷም ትልቅ ውድቀት ይሆናል።” “ብዙ የሰብአዊ መብት ጥሰት በባለስልጣኖች ይፈጸማል። ሳይውል ሳያድር በዜጎች ላይ በደል የሚያደርሱት ላይ እርምጃ መወሰድ […]

የሰማያዊ ፓርቲ ለምርጫ የሚያደርገዉን እንቅስቃሴ በስፋት እንደቀጠለበት የደረሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ። ፓርቲው የምርጫ ምልክት ከሌሎች ቀድሞ በማመልከቱ፣ ምልክት የሰጠው ሲሆን፣ በተናጥል ተወዳዳሪዎችን አዘጋጅቶ እያሰመዘገ እንደሚገኝም የአመራር አባላቱ ይናገራሉ። የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ሃላፊ አቶ ጌታነህ ባልቻ ሰማያዊ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመስራት ፍላጎት እንዳለውና የምርጫዉን ዘምቻ በጋራ ማቀናጀቱ አስፈላጊ እንደሆነ ፣ ለሚሊዮኖች ድምጽ ጋዜጣ ገልጸው […]

ታሪኩ ዝዋይ እሥር ቤት ወንድሙን ለማየት ይገባል። እዚያም፣ “ተመስገንን ጥሩልኝ ” ሲል ፖሊሶችን ይጠይቃል። በዚህ ግዜ የመቶ ዓለቃ ማዕረግ ያለው ወታደር (ፖሊስ) ተመስገንን መጠየቅ እንደማይችል ይነግረዋል። ታሪኩም “ምን ተፈጠረ ወንድሜን እንዳልጠይቀው የተከለከልኩት ?” በማለት ለፖሊሱ ጥያቄ ያቀርባል። ፖሊሱም በማመናጨቅ “ውጣ” ይለዋል። ነገሩ ያላማረው ታሪኩ ለወንድሙ ያመጣውን ስንቅ እንደያዘ ወደ በሩ ያመራል። ነገር ግን” ውጣ” ያለው […]

The post ሰበር ዜና የጋዜጠኛ ተመስገን ወንድም ታሪኩ ድብደባ እና ዘረፋ በዝዋይ እስር ቤት ፖሊሶች ተፈጸመበት appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

ከአንድነት  ድጋፍ ማህበር በሰሜን አሜሪካ  የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ   ጉዳዩ፡  ፡ በቅርቡ  በኢትዮጵያ  ምርጫ  ቦርድና  በአንድነት ፓርቲ መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ በተመለከተ፡፡   እንደሚታወቀው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ /አንድነት/ ፓርቲ ባለፈው ሣምንት ከምርጫ ቦርድ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ጠቅላላ ጉባዔ በ4 ቀን ውስጥ እንዲጠራና የፓርቲውን  መሪ በድምፅ አሠጣጥ መመሪያው መሠረት እንዲመርጥ ስለተገደደ አንድነት ፓርቲም በሆደ ሰፊነት በምርጫ ቦርድ ትዕዛዝ […]

ከአንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማህበር የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ጉዳዩ፥ በቅርቡ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድና በአንድነት ፓርቲ መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ በተመለከተ፡፡ እንደሚታወቀው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ /አንድነት/ ፓርቲ ባለፈው ሣምንት ከምርጫ ቦርድ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ጠቅላላ ጉባዔ በ 4 ቀን ውስጥ እንዲጠራና የፓርቲውን መሪ በድምፅ አሠጣጥ መመሪያው መሠረት እንዲመርጥ ስለተገደደ አንድነት ፓርቲም በሆደ ሰፊነት በምርጫ ቦርድ ትዕዛዝ […]

ጥር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፖሊሶቹ በበኩላቸው – <<እኛን ህዝብ ጋር አታጣሉን>> ሲሉ ለአዛዦቻቸው ትእዛዝ ምላሽ ሰጥተዋል። የክልሎ ፖሊሶች  ከመቼውም በላይ ለእርምጃ እረንዲዘጋጁ  የተነገራቸው፤የማረሚያ ቤቶችንና የትራፊክ ፖሊሶችን ጨምሮ ላለፉት ስድስት ቀናት በአማራ ክልል ለሚገኙ ፖሊሶች በሚሉ ሲሰጥ በነበረው ስልጠና  ላይ ነው። እስከ ትናንት ሐሙስ  ድረስ በቆየው በዚሁ ስልጠና ላይ ከምርጫው  እና ከጥምቀት በዓል …

ጥር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዝዋይ ወህኒ ቤት የሚገኘውን ወንድሙን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ለመጠየቅ ትናንት ማለዳ ወህኒ ቤቱ በራፍ ላይ የደረሰው ታሪኩ ደሳለኝ በወህኒ ቤቱ ሀላፊና ስምንት በሚደርሱ ወታደሮች ድብደባ እንደደረሰበት በፌስ ቡክ ገጹ ታሪኩ አስታውቋል፡፡ለተመስገን ይዞ የመጣውን ምግብ ወታደሮቹ መሬት ላይ ከመድፋታቸውም በላይ በኪሱ የያዘውን ገንዘብ ወስደውበታል፡፡ታሪኩ ከደረሰበት ድብደባ በላይ ወንድሙን ሳይጠይቅና …

ጥር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ፣የደሴ፣ የሀዋሳ፣የአርባምንጪ፣ የሀረር፣ የሚዛን ተፈሪ፣የሰበታ፣ የባህርዳር፣ የወልቂጤና የሌሎችም ከተሞች ነዋሪዎች  ለኢሳት እንደገለጹት፣በካድሬዎች አማካይነት ህዝቡ የምርጫ ካርድ በግዳጅ እንዲወስድ እና ድምጹን ለኢህአዴግ እንዲሰጥ እየተደረገበት ያለው ግፊት ከመቼውም ጊዜ በላይ እየከፋ መጥቷል። ከካድሬዎቹ ማስፈራሪያዎች መካከል፦<<የምርጫ ካርድ ካልወሰዳችሁ የቀበሌ መታወቂያና ሌሎችንም አስተዳደራዊ አገልግሎቶች አታገኙም፣ በምርጫው ኢህአዴግን ካልመረጣችሁ ሁዋላ ላይ ተጣርቶ …

ጥር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ኦሞ ዞን አመር ወረዳ- ላላ ቀበሌ ነዋሪ በሆኑ አርብቶ አደሮችና- በፖሊስ መካከል ግጭት ተቀስቅሶ የሰው ነፍስ መጥፋቱን ነገረ ኢትዮጰያ ዘገበ፡፡ ጋዜጣው ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ትናንት ጥር 7/2007 ዓ.ም  <<አርብቶ አደሮች ማጎ ፓርክ ገብተው አውሬ ገድለዋል>> በማለት  ፖሊስ- አርብቶ አደሮቹ ገዳዩን አሳልፈው እንዲሰጡት በጠየቀበት ወቅት ነው ግጭቱ የተነሳው። …

የፕሮግራም መግለጫ

ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡

የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡

ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡

ሰዎች በሚገለገሉበትና በሚያዘወትሩት አካባቢ ትምባሆ ማጨስ በበርካታ ሃገራት መከልከል ከተጀመረ ከታራረመ። በኢትዮጵያም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ይህን መሰል ዉሳኔ ማሳለፉ ተሰምቷል ተግባራዊነቱ ቢዘገይም።

ከአራት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ በናይጀሪያ የምክር ቤት አባላትና ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ይካሄዳል ። በአሁኑ ጊዜ በሽብር ማዕበል በምትናወጠው በናይጀሪያ ምርጫ እንዴት ሊካሄድ ይችላል የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል ።በምርጫው ዋዜማ በናይጀሪያ አሳሳቢው የፀጥታ ችግር ብቻ አለመሆኑን የዶቼቬለዋ ሽቴፋኒ ዱክሽታይን ዘገባ ያስረዳል ።

የአንድንታ ፓርቲ በኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት እንዲፈጠር በምንም መለኪያ በገለልተኝነት የማንጠብቃቸውን የዲሞክራሲ ተቋማት በተግባር ለመፈተን እንዲቻል የሁለት ሺ ሰባት ምርጫን በሁሉም ሂደቶች ህዝቡን በማሳተፍ እንደሚወዳደር እና ህዝብን የስልጣን ባለቤት ለማድረግ እና የኢህአዴግ አገዛዝ የመጨረሻ እንዲሆን በቁርጠኝነት እንደሚሰራ መወሰኑ ይታወቃል፡፡ ይህን ስንወስን እነዚህ ተቋማት ገለልተኝነታቸውን አረጋግጠው ታሪክ የሚሰሩበት እድልም ያገኛሉ የሚል ተሰፋ ነበር፡፡
ይሁን እንጂ ምርጫ ቦርድ ይህን እድል ከመጠቀም እና በህግ የተሰጠውን ኃላፊነት በብቃት ከመወጣት ይልቅ ለገዢው ፓርቲ ያለውን ወገንተኝነት በምርጫው ሂደት ዋዜማ በይፋ እያረጋገጠ ይገኛል፡፡ አሁንም ቦርዱ ወሰነ ተብሎ በሚዲያ የተገለፀው እንዲሁም ለፓርቲያችን በፅሁፍ የተሰጠው “በአስራ አምስት ቀን ውስጥ በጋራ ጉባዔ አድርጉ” የሚል ትዕዛዝ፤ ቦርዱ በተደጋጋሚ ፓርቲያችንን ደንብ እንዲያከብር እየጠየኩ ነው በማለት ከደንብ ውጭ እንድንሰራ የአዛኝ ቂብ አንጓች ሆኖዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ የመጥራት ኃላፊትን ያለበት የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ወይም ደግሞ በአባላት ጥያቄ የጠቀላላ ጉባዔ አባላትን አንድ ሶስተኛ ፊርማ አስባስበው በኦዲትና ኢንስፔክሽን ትዕዛዝ መሆኑ በግልፅ እየታወቀ ከፓርቲያችን መተዳደሪያ ደንብ ውጭ በ15 ቀን ውስጥ ጉባዔ ጥሩ የሚል ትዕዛዝ፤ ቦርዱ ከገዢው ፓርቲ ጎን ተሰልፉ እየተጫወተ አንድነትን ከጫወታ ለማስወጣት ካለሆነ ሌላ ምንም ትርጉም ልንሰጠው አንችልም፡፡ ይህ ደግሞ ቦርዱ እየሰራ ያለውን ታሪካዊ ወንጀል ይፋ የሚያደርግ ነው፡፡
ይህ በማን አለብኝ ሰሜት የተሰጠ ውሳኔ ሳይታረም ቢቀርና ገዢው ፓርቲ ያለምንም ጠንካራ ተቀናቃኝ ብቻውን ሮጦ ብቻውን እንዲያሻንፍ የሚያደረግ ተቋማዊ ሴራ ቦርዱን በታሪክ ተጠያቂ ማድረግ ብቻ ሳይሆን በዚህች ሀገር ዘላቂ ሰላም ላይ ለሚፈጠረው አደጋ ቦርዱ ከተጠያቂነት እንደማይድን ለማስታወስ እንወዳለን፡፡
በዚህ አጋጣሚ አንድነት ፓርቲ የሰላማዊ ትግሉን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ለማድረግ እና ህዝቡን የስልጣን ባለቤት የማድረግ እንቅስቃሴውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልና በቀጣይ ሳምንታትም በመንግሰትና በቦርዱ ላይ ጫና ማሳደሩን እንደሚቀጥልበት እያረጋገጥን አንድነት ፓርቲ ወደ ህገወጥነት የሚወሰደውን “የጋራ ጉባዔ” አካሂዱ የሚለው የምርጫ ቦርድ ውሳኔ የማንቀበለው መሆኑን ለመላው አባላትና ደጋፊውች ማረጋገጥ እንወዳለን፡፡
ጥር 8/2007
ድል የህዝብ ነው!!!
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ/አንድነት/

Image
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም በወታደሮች ተደበደበ
በዝዋይ ወህኒ ቤት የሚገኘውን ወንድሙን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ለመጠየቅ ትናንት ማለዳ ወህኒ ቤቱ በራፍ ላይ የደረሰው ታሪኩ ደሳለኝ በወህኒ ቤቱ ሀላፊና ስምንት በሚደርሱ ወታደሮች ድብደባ እንደደረሰበት በፌስ ቡክ ገጹ ታሪኩ አስታውቋል፡፡ለተመስገን ይዞ የመጣውን ምግብ ወታደሮቹ መሬት ላይ ከመድፋታቸውም በላይ በኪሱ የያዘውን ገንዘብ ወስደውበታል፡፡ታሪኩ ከደረሰበት ድብደባ በላይ ወንድሙን ሳይጠይቅና የሚገኝበትን ሁኔታ ሳያጣራ መመለሱ ህመም እንደፈጠረበት አስታውቋል፡፡የታሪኩ ስለ ሁኔታው የገለጸው እንዲህ በማለት ነበር፡፡
ስምንት አንድን ሰው በደም እስኪታጠብ ድረስ በርግጫ፣ በጥፊና በሰደፍ መደብደብ፣ በእጁ ላይ የሚገኝውን ብርና መፃሀፍ መንጠቅ፣ ስልኩን መስበር…. ይህ ድርጊት በሌሊት አንድ ሰው ላይ በሌቦች የተፈፀመ ሳይሆን ትላንት ከረፋዱ በ 5 ሰዓት ላይ በዝዋይ እስር ቤት ግቢ ውስጥ በኔ ላይ የተፈፀመ ነው፤
ነገሩ እነዲህ ነው የሆነው፣ እንደልማዴ ዝዋይ የደረስኩት በማለዳ ነው፡፡ የያዝኩትን ስንቅ አስፈትሼ እንደጨረስኩ የሬዲዬ መገናኛ የያዘ መቶ አለቃ እንደሆነ የሚገልፅ ማዕረግ ያለው ወታደር እየገላመጠኝ “ለምን መጣህ?” አለኝ፤ “እዚህ የታሰረ ወንድም አለኝ እሱን ለመጠየቅ ነው” ስል መለስኩ፡፡ ቀጥ ብለህ ወጣ ተከተለ “አንተ ወንድምህን መጠየቅ አትችለም” ሲለኝ “ምክኒያቱ ይነገረኝ” ብዬ ብናገር ከጉዳይም አልቆጠረኝም “እሺ እኔ ባልገባ እንኳን ያመጣሁት ምግብን አድርሱልኝ” ብል ስሚ አጣሁ፡፡ አንገቴን ደፍቼ ልወጣ ስል መቶ አለቃው በሬዲዬ እያወራ አንድቆም በእጁ ምልክት ሲሰጠኝ ልገባ ነው ብዬ ደሰ አለኝ፡፡ መቶ አለቃው በፍጥነት ወደኔ በመምጣት ያዙት አለ፡፡ በዙሬያዬ ወደ ስምንት የሚጠጉ ወታደሮች ከበቡኝ፡፡ የመቶ አለቃው “የተመስገን ታናሽ ወንድም ታሪኩ ነህ?” አለኝ፡፡ የተመስገን ወንድም መሆኔን በአንገቴም በአፌም “አዎ ነኝ” ከማለቴ ጥፊ ጆሮዬ ላይ ጮኽ፡፡ ከዛም አንደኛው በከስክስ ጫማ ሌላኛው በሰደፍ ተቀባበሉኝ፡፡ ደምቼ መሬት እስክወድቅ ድረስ ደበደቡኝ….ደበደቡኝ፤ ወደኩኝ፡፡ ከነደሜ አነሱኝ የያዝኩትን ብርና መጽሐፍ ነጠቁኝ ያመጣሁትን ምግብ መሬት ላይ ደፉተው እየገፈታተሩ ከግቢው አስወጡኝ፡፡ እስር ቤቱ ፊት ለፊት አቧራው ላይ ተቀመጥኩኝ፡፡ ተሜን በዓይን ርቀት ያህል ብቀርበውም መጠየቅ ባለመቻሌ አለቀስኩኝ፤ ደሜን አፍስሼ ወንድሜን ሳላይ ተመልሻለሁ … ተሜ ለኔ አንተን አለማየት የማይቻል ሽክም ነው፡፡ ይሄንንስ እነዴት ልንገርህ?!

የአንድንት ፓርቲ በኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት እንዲፈጠር በምንም መለኪያ በገለልተኝነት የማንጠብቃቸውን የዲሞክራሲ ተቋማት በተግባር ለመፈተን እንዲቻል የሁለት ሺ ሰባት ምርጫን በሁሉም ሂደቶች ህዝቡን በማሳተፍ እንደሚወዳደር እና ህዝብን የስልጣን ባለቤት ለማድረግ እና የኢህአዴግ አገዛዝ የመጨረሻ እንዲሆን በቁርጠኝነት እንደሚሰራ መወሰኑ ይታወቃል፡፡ ይህን ስንወስን እነዚህ ተቋማት ገለልተኝነታቸውን አረጋግጠው ታሪክ የሚሰሩበት እድልም ያገኛሉ የሚል ተሰፋ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ምርጫ […]

ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ/አንድነት/ የተሰጠ መግለጫ የአንድንታ ፓርቲ በኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት እንዲፈጠር በምንም መለኪያ በገለልተኝነት የማንጠብቃቸውን የዲሞክራሲ ተቋማት በተግባር ለመፈተን እንዲቻል የሁለት ሺ ሰባት ምርጫን በሁሉም ሂደቶች ህዝቡን በማሳተፍ እንደሚወዳደር እና ህዝብን የስልጣን ባለቤት ለማድረግ እና የኢህአዴግ አገዛዝ የመጨረሻ እንዲሆን በቁርጠኝነት እንደሚሰራ መወሰኑ ይታወቃል፡፡ ይህን ስንወስን እነዚህ ተቋማት ገለልተኝነታቸውን አረጋግጠው ታሪክ የሚሰሩበት እድልም ያገኛሉ […]

የመጻፍ ፍላጎት በጭራሽ አልነበረኝም፡፡ ይሁን’ይ ዛሬ እንደወትሮው አላስችልህ አለኝ፡፡ መጻፍ የማልፈልገው መጻፍን በመጥላት ሣይሆን የሀገራችን ችግር ከመጻፍም፣ ከማንበብም፣ ከመመልከትና እጅን አጣምሮ በመቀመጥ በቁጪት ከመብከንከንም በእጅጉ ያለፈ በመሆኑ ነው፡፡ አዎ፣ ጊዜው የወሬና የሀተታ ሣይሆን የተግባር መሆን ይገባዋል – ልብ ላለው(2)፡፡ ብዙዎች – እኔንም ጨምሮ – ላለፉት ሃያ ምናምን ዓመታት በከንቱ ኃይላችንን መጨረሳችንን ሳስበው ይገርመኛል፡፡ እነሱ ላይሰሙ […]

ከመከላከያ እስታፍ አፈትልኮ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በከፍተኛው የመከላከያ ሰራዊት እርከን ሲሰሩ የቆዩ ከፍተኛ መኮነኖች ሌተናል ጀኔራል አበባው ታደሰ፥ ሌተናል ጀኔራል ሰዓረ መኮነን፥ ሜጀር ጀኔራል ሞላ ሃይለማሪያም፥ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በላያቸው ላይ እየፈፀመው ያለውን ተግባር ትክክል አይደለም በማለት በዚህ ሳምንት ወደ ጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማሪያም ደሳለኝ የቅሬታ ደብዳቤ እንደፃፉ ለማወቅ ተችሏል፣ በግላቸው ከፃፏቸው ደብዳቤዎች የተወሰኑትን ለመጥቀስ […]

ጥር ፫ ቀን ፳፻፯ January 11, 2007 ህወሓት/ኢህአዴግ  አሁንም  እንደገና  በሀገሪቱ  ምርጫ ሂደት ብቻውን ሮጦ  ብቻውን ለማሸነፍ እንዲችል አስከፊ አፈናውንና እመቃውን  አጠናክሮ ቀጥሏል።  ተፎካካሪ የሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶችን ከፖለቲካው በተለይም ከምርጫው ሂደት ተገፍትረው እንዲወጡ ለማድረግ ሳይታክት እየሰራ ነው። በሰሞኑም በአንድነት፣ በመኢአድና በሰማያዊ ፓርቲ ላይ የምርጫ ቦርድ ተብየውን በመጠቀም የሚደረገው ማዋከብ ህወሓት/ኢህአዴግ በምርጫው ሂደት ውስጥ ብቻውን ከራሱ […]

በቃል የቀረበው አቤቱታ ከድምጽ ክምችት ክፍል ጠፍቷል ተብሏል በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች እና ሌሎች በተመሳሳይ መዝገብ ያሉ የሽብር ተከሳሾች በቂሊንጦ እስር ቤት አስተዳደር መካከል ያለው አቤቱታ እስካሁን እልባት ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ዛሬ ጥር 7 ቀን 2007 ዓ.ም ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰማያዊ፣ […]


ሰሚ ካጡ የሶማሌ ተረቶች አንዱ እንዲህ ይላል፡፡
አንድ ሰው የጠፋች የአካባቢው ግመል ፍለጋ ጫካ ይገባል፡፡ ከብዙ መከራ በኋላ ያቺን ግመል አግኝቶ ከተማ ገባና ግመሏን ለባለቤቱ ሳይመልስ ሐሳቡን ቀይሮ ራሱ ያልባትና ይጋልባት ጀመር፡፡ ግመሏን ከአውሬ ለማዳን ጫካ ገብቶ የነበረው ሰውዬ እርሱ ራሱ ግመሏን መውሰዱ ብዙዎችን አስገረማቸው፡፡ ትንሽ ቆየና ከዚያች ከአንዷ ግመል ወተት እያለበ በግመሏ ላይ ተቀምጦ እየዞረ ለአካባቢው ሰው ወተት መሸጥ ጀመረ፡፡ ነገር ግን የግመሏ ወተት በአንድ ጊዜ ሀብታም ሊያደርገው አልቻለምና ሌላ ነገር አሰበ፡፡ በወተቱ ውስጥ ውኃ እየጨመረ ቀላቅሎ መሸጥ፡፡ ‹‹ሰውም ምነው የሰውየው አመሉም ወተቱም ተቀየረሳ›› እያለ ዝም ብሎ ይገዛ ጀመር፡፡ (ይገዛ የሚለው ቃል ጠብቆ እንዳይነበብ አሳስባለሁ) 

ሰውዬውም በግመል ወተቱ ላይ ውኃን እያበዛው፤ የግመሉም ቁጥር እየጨመረ ሄደ፡፡ እየቆየም በግመልና በግመል ወተት ከሚታወቁት የሀገሩ ነጋዎች በላይ እኔ ነኝ ያለ፣ ቢጠሩት የማይሰማ ሀብታም ሆነ፡፡ የአካባቢው ሰዎችም ‹‹ይኼ ሰው ትናንት ምንም አልነበረውም፡፡ የጠፋ ግመል ሊፈልግ ጫካ ገባ፤ ተመልሶ መጣ፤ ከተማ ገባ፤ በአንድ ጊዜ ተመነደገ›› እያሉ ይገረሙ ነበር፡፡ ወተት ብቻ ተሽጦ እንዴት በሁለት ዓመት ሦስት መቶ ግመል ሊገዛ ቻለ፡፡ የሚለው የሕዝቡ ሁሉ ወሬ ሆነ፡፡ 
 
ሰውዬው ግን ምንም አልመሰለው፤ በወተቱ ውስጥ ውኃውን እየጨመረ ቀጠለ፤ እንዲያውም እበላ ባይ ቱልቱላዎችን ቀጠረና የእርሱ ወተት ሰው ጠጥቶት የማያውቅ መሆኑን እንዲለፍፉ አደረ፡፡  አንዳንድ ጊዜ እንዲያውም ወተቱን ለመልኩ ብቻ ይጨምርበትና የቀረው ውኃ ያደርገው ነበር፡፡ ‹‹ኧረ ሕዝቡ እያማረረ ነው፤ በአንድ በኩል በድንገት ተነሥህ፤ ከተማ ገብተህ ቢጠሩህ የማትሰማ ሀብታም ሆንክ፤ ይኼንን ስንታገሥህ ደግሞ ወተቱን ቀንሰህ ውኃውን እያበዛህ መሸጥ ጀመርክ፡፡›› ሲሉት ‹‹ተውት ባካችሁ፣ ለመሆኑ የእኔን ወተት ከመግዛት ውጭ ሕዝቡ ምን አማራጭ አለው፤›› ይል ነበር፡፡
 
በወተቱ ውስጥ የሚጨመረው ውኃም እየበዛ፣ ግመሎቹም እየበዙ ሄዱ፡፡ ግመሎቹም ሀገሩን ሞሉት፡፡ የሚያድሩበትና የሚግጡበት ልዩ የከተማ መሬት ተሰጣቸው፡፡ ወንዝ ዳር የሚገኝ ለም መሬት፡፡    
 
አንድ ቀን ሸበሌ ወንዝ አጠገብ ግመሎቹን አሠማርቶ እርሱ አንድ ዛፍ ጥላ ሥር ሻሂ ከልጁ ጋር ይጠጣ ነበር፡፡ በዚህ መሐል ከደጋ የዘነበ ዝናብ ወንዙን ሞላውና በግራ በቀኝ ሲግጡ የነበሩትን ግመሎች ጠራርጎ ወሰዳቸው፡፡ የጎርፉን ድምጽ ሰምተው አባትና ልጅ ከጥሻው ሲወጡ ግመሎቻቸው ሁሉም ተወስደዋል፡፡ እሪታውን ሰምተው የተሰበሰቡ የሀገሩ ሰዎችም በአግራሞት የሆነውን ነገር ይመለከቱ ነበር፡፡ 
 
‹‹አየህ›› አሉት አንድ አዛውንት ‹‹ያ በወተቱ ላይ እየጨመርክ የሸጥከው ውኃ ተጠራቅሞ፣ ተጠራቅሞ ጎርፍ ሆኖ ግመሎቹን ወሰዳቸው፡፡ ግፍ እንደዚህ ነው፡፡ ሲሠራ ቀላል ይመስላል የተጠራቀመ ዕለት ግን ጎርፍ ሆኖ ይወስዳል፡፡ ተው ብንልህ አልሰማ ብለህ ነበር፤ አንተ በግፍ ግመል ስትሰበስብ የግፉ ውኃ ሌላ ቦታ እየተሰበሰበ መሆኑን ረስተህዋል፡፡ ቀን ጠብቆ ግን ይሄው ጎርፍ ሆኖ መጣ›› አሉት፡፡
 
ግፍና ጎርፍ፡፡

ነገረ ኢትዮጵያ በኢቦላ ስጋት የታገቱት 21 ቀን ሊቆዩ ይችላሉ ተባለ በኢቦላ በሽታ ስጋት ከቤታቸው እንዳይወጡና እንዳይገቡ በፖሊስ እየተጠበቁ ያሉት የፈረንሳይ ሌጋሲዮን ነዋሪዎች በሽታው እንዳለባቸውና እንደሌለባቸው እስኪታወቅ ድረስ 21 ቀን ቤታቸው ውስጥ ሊቆዩ እንደሚችሉ ከጤና ጥበቃ ባለስልጣናት እንደተነገራቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ዛሬ ከቀኑ 12 ሰዓት አካባቢ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣናት መጥተው የጎበኟቸው […]

ይህን ፅሁፍ ሪፖርተር ያወጣው ባለፈው ዓመት ቢሆንም አዲስ  ፎርቹን ሕጋዊ ሰንድ መስጠት መጀመሩን የዘገበው በዚህ ሳምንት ነው Read in English
15 MAY 2013 ተጻፈ በ  

የአዜብ መስፍንና የመለስ ዜናዊ ልጅ የሆነችው ሰመሃል መለስ በየቀኑ ከልክ በላይ አልኮል እንደምትጐነጭ የቅርብ ታማኝ ምንጮች አስታውቀዋል። የ27 አመት ወጣቷ ሰመሃል አቅሏን እስክትስት ከጠጣች በኋላ እየተነፋረቀች እንደምታለቅስ ታውቋል። ቦሌ በሚገኘውና የቀድሞ ስዩም መስፍን መኖሪያ ቤት ውስጥ ከወላጅ እናትዋ ጋር የምትኖረው ሰመሃል የሚያስለቅሳት ነገር አስገራሚ ሆኖዋል። ሰመሃል በአባትዋ ሞት አሊያም በእናትዋ መታመምና በደረሰባት የፖለቲካ ኪሳራ እንዲሁም […]

ሕወሃት የጥቂቶችን ጥቅም የሚያስጠበቅና የተቀረነውን በባርነት አንቆ እየገዛ ያለ አምባገነን ስርዓት ነው። ስርዓቱ የሕዝብን ሕዝቡን ለማፈን እና ለመግዛት በየጊዜው መልምሎ ለእኩይ ተግባራቱ የሚጠቅምባቸው፣ ለሆዳቸው ያደሩ በርካታ ደካማ ሰዎች አሉ። እነዚህ ሰዎች ከሕወሃት ጋር ሆነው ሕዝቡን የሚጎዱት “ህዝቡ የት ይደርሳል ? ሕዝቡ ምን ያደርገናል ? ወያኔን አገልግለን ብንጠቀም ይሻላል” ከሚል የአጭር ርቀት አሳፋሪ አሰተሳሰብ ነው። የአንድነት […]

ጥር ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ንቅናቄው  በግንቦት 7 እና በ አርበኞች ግንባር መካከል የተደረገውን ውህደት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ << እኛ መዋሃድ መወሰናችንን  ስንገልጽ፤ በተናጠል ከሚደረጉት – በጋራ የሚደረጉ የትግል ጥረቶች ውጤታማ ይሆናሉ በሚል ብቻ ሳይሆን፣፡”የተቃዋሚ ድርጅቶች፣ በምንም ዓይነት ሁኔታ በሀገርና በሕዝብ ደረጃ ትርጉም ያለው ሥራ በጋራ መስራት አይቻሉም’ የሚለውን፣ አስከፊ ተመክሮና አመለካካት ለመስበርም …

ጥር ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ ጥር 7/2007 ዓ.ም የዓመቱን የሥላሴ በዓል ለማክበር አራት ኪሎ የሚገኘው ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን የተገኙ ወጣቶች ሰማያዊ ቲሸርት በመልበሳቸው በፖሊስ መባረራቸውን ነገረ- ኢትዮጰያ ዘግቧል፡፡ ፖሊስ፤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅስ የተጻፈበት  ሰማያዊ ቲሸርት የለበሱትን ወጣቶች ቲሸርቱን እንዲያወልቁ ሲጠይቅ ወጣቶቹ አናወልቅም በማለታቸው ከበዓሉ እንዳባረራቸው የዐይን እማኞች ገልጸዋል፡፡  ከተባረሩት ወጣቶች መካከል …

ጥር ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ልኳንዳ  ተብሎ በሚጠራው አካባቢ  የሚገኘውንና ከጥንት ጀምሮ  የአባት ጦረኞችና የአርበኞች መኖሪያ የሆነውን የወታደር ካምፕ  ቦታው ተከልሎላቸው የሰሩት  ራሳቸው   አርበኞቹ  መሆናቸው ተመልክቷል። ፈጽሞ ባላሰቡበትና ባልተዘጋጁበት ሁኔታ መኖሪያ ካምፓቸው ያለ ምንም ተለዋጪ ማረፊያ  መሳሪያ በታጠቁ ወታደሮች እንዲፈርስ መደረጉ እንዳስደነገጣቸው የሚናገሩት ነዋሪዎቹ፤ ውሳኔውን በመቃወም እስከ ፍትህ ሚኒስቴር ድረስ አቤት ቢሉም ሰሚ …

ጥር ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከትግራይ ሕዝብ ዲሚክራሲያዊ ድርጅት ‹‹ደሚህት››  ጋር ግንኙነት  ተብሎ የሽብርተኝነት ክስ የተመሰረተበት የአንድነት የመቀሌ ዞን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ፤ ወጣት ሺሻይ አዛናው በትናንትናው ፍርድ ቤት ቀርቦ ተጨማሪ ቀጠሮ ተጠየቀበት። ወጣት ሲሳይ  ቀደም ሲል በተጠየቀበት የሃያ ስምንት ቀናት ቀነ-ቀጠሮ መሰረት ትናንት በአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት   ቢቀርብም፣ ፖሊስ ማስረጃዬን ሰብስቤ አልጨረስኩም …

ፍኖተ ነፃነት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ሬድዩ ፋና እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ/ኢቲቪ) በአንድነት ፓርቲ ላይ የጠነሰሱት ሴራ ተጋለጠ፡፡ አንድነት፣ ‹‹ኢትዮጵያውያን ካልሆኑ ሰዎች ገንዘብ ያሰባስባል›› የሚል ውንጀላ እየቀረበበት እንደሚገኝ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ለፍኖተ-ነፃነት ገልፀዋል፡፡ በተለይ ራዲዮ ፋና ‹‹አንድነት ከግንቦት ሰባት ገንዘብ ይቀበላል፣ በውጪ ሀገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ካልሆኑ ሰዎች ገንዘብ ይሰበስባል›› የሚል ውንጀላ እያቀረበ መሆኑን የፓርቲው […]

Image
ሬዲዩ ፋና፣ ‹‹አንድነት ከአሸባሪ ቡድኖች ገንዘብ ይቀበላል›› በማለት ወነጀለ ::አንድነት፣ ‹‹ኢትዮጵያውያን ካልሆኑ ሰዎች ገንዘብ ያሰባስባል›› የሚል ውንጀላ እየቀረበበት እንደሚገኝ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ለፍኖተ-ነፃነት ገልፀዋል፡፡ በተለይ ራዲዮ ፋና ‹‹አንድነት ከግንቦት ሰባት ገንዘብ ይቀበላል፣ በውጪ ሀገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ካልሆኑ ሰዎች ገንዘብ ይሰበስባል›› የሚል ውንጀላ እያቀረበ መሆኑን የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች አያይዘው ገልፀዋል፡፡

አንድነት እየቀረበበት የሚገኘው ውንጀላ መሰረተ-ቢስ መሆኑን የገለፁት አመራሮቹ፣ ፓርቲው አሜሪካን ሀገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ብቻ ገንዘብ እንደሚያሰባስብ እና ለዚህም በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሆኑ የአንድነት ደጋፊዎች፣ በፓርቲው እውቅና ተሰጥቷቸው የድጋፍ ሰጪ ቻፕተር ማቋቋማቸውን ገልፀዋል፡፡ ‹‹አዋጁ በሚፈቅደው መሰረት ብቻ ዜግነታቸው ኢትዮጵያዊ ከሆኑ ሰዎች ብቻ ገንዘብ እንደሚያሰባስቡ›› የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ስዩም መንገሻ አስታውቀዋል፡፡ የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ግርማ ሰይፉ፣ በበኩላቸው የፓርቲው የፋይናንስ አሰራር ግልፅነትን መሰረት ያደረገ እንደሆነ ገልፀው፣ በየዓመቱም ኦዲት እንደሚደረግና ምርጫ ቦርድም ለተከታታይ ዓመታት የፓርቲውን የፋይናንስ አሰራር ግልፅነት የሚታይበት እንደሆነ ጠቅሶ ለፓርቲው ሰርተፍኬት መስጠቱን› አቶ ግርማ አውስተዋል፡፡ የራዲዮ ፋና ውንጀላም ከዚህ አንፃር ተገቢነት እንደሌለው አስታውቀዋል፡፡ ይህን መሰሉን ውንጀላ የአንድነት አባል ነን የሚሉ ሰዎች ባሳለፍነው ሳምንት በሬዲዮ ፋና ላይ ቀርበው ያሰሙ ሲሆን የሬዲዮ ፋና ጋዜጠኛ ነኝ የሚል ብሩክ ከበደ፣ የተባለ ግለሰብም ይህን መሰሉን ውንጀላ እንዳቀረበ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የአንድነት ፓርቲ ም/ፕሬዘደንት አቶ ግርማ ሰይፉ እና የፓርቲው ዋና ጸሀፊ አቶ ስዩም መንገሻ በሬዲዮ ፋና “ሞጋች” በተባለ ፕሮግራም ላይ ዛሬ ጥር 7 ቀን 2007 ዓ.ም በቀረቡበት ወቅት የገዢው ቡድን ተጠሪ የሆነው ብሩክ ከበደ ፣ “አንድነት ፓርቲ በሽብር ከተፈረጁ ቡድኖች ገንዘብ ይሰበስባል” የሚል ውንጀላ ሲያቀርብ እንደነበር የፓርቲው አመራሮች ለፍኖተ-ነፃነት አስረድተዋል፡፡

ገዢው ፓርቲ አሰርጎ ባስገባቸው ሰዎች “የደንብ ጥሰት አለ” የሚል ውንጀላ ሲቀርብበት የነበረው አንድነት ዛሬ ላይ ደግሞ ውንጀላው በህዝብ ስም በተቋቋሙት ሚዲያዎች አማካኝነት “በአሸባሪነት ከተፈረጁ ቡድኖች ገንዘብ ይቀበላል” በሚል ሌላ ውንጀላ እየቀረበበት ይገኛል፡፡
በቅርቡ በማህበራዊ ሚዲያዎች ገዢው ቡድን “አንድነት ፓርቲ ከግንቦት ሰባት 1 ሚሊዮን ብር ተቀብሏል፡፡” የሚል ክስ በተላላኪዎቹ በኩል ሊያቀርብ መዘጋጀቱን የሚያጋልጥ መረጃ መውጣቱ አይዘነጋም፡፡

የፕሮግራም መግለጫ

ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡

የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡

ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ሬድዩ ፋና እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ/ኢቲቪ) በአንድነት ፓርቲ ላይ የጠነሰሱት ሴራ ተጋለጠ፡፡ አንድነት፣ ‹‹ኢትዮጵያውያን ካልሆኑ ሰዎች ገንዘብ ያሰባስባል›› የሚል ውንጀላ እየቀረበበት እንደሚገኝ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ለፍኖተ-ነፃነት ገልፀዋል፡፡ በተለይ ራዲዮ ፋና ‹‹አንድነት ከግንቦት ሰባት ገንዘብ ይቀበላል፣ በውጪ ሀገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ካልሆኑ ሰዎች ገንዘብ ይሰበስባል›› የሚል ውንጀላ እያቀረበ መሆኑን የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች […]

ከተመሰረተ ከ10 ዓመት በላይ የሆነዉ የ«ኢትዮ ኮለኝ የስፖርትና የባህል ማሕበር» ዓመታዊዉን ባህላዊ መድረክ ሲያዘጋጅ ይህ ለሁለተኛ ግዜ መሆኑ ነዉ። በኖርዝ ራይን ዊስት ፋልያ እንዲሁም አቅራቢያ ግዛቶች ዉስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የተሰባሰቡበትን ባህላዊ መድረክ ቃኝተን በዕለቱ ዝግጅታችን ይዘን ቀርበናል።