ይሄይስ አእምሮ

በሀገራችን የስም አወጣጥ ወግና ልማድ እልም ያለችዋ ጥሩራ ባሪያ “አልማዝ” ወይም “ፀሐይ”፣ በነጭናጫነቷና በምግባረ ብልሹነቷ መንደርተኛው ሁሉ የሚያውቃት ሴት ወይዘሮ “ዐመለወርቅ” ወይም “አበቅየለሽ”፣ እልም ያለው ቦቅቧቃ “ደም መላሽ” ወይም “ሺመክት”፣ ቤሣቤስቲን የሌለው የኔቢጤው መናጢ ድሃ “ሀብታሙ” ወይም “አዱኛ”፣ እንዴት ያለው ንፉግና ክፉ ሰው “ቸሩ” ወይም “ደጉ”፣ … ተብሎ ሲጠራ እናውቃለን።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በዩናይትድ ስቴትስ የመንግሥት በጀት ሳይፀድቅ ሣምንታት መቆጠሩ በሀገሪቱ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያስከትለው ተፅዕኖ ምን ይመስላል? የዛሬው የኢኮኖሚው ዓለም መሰናዶዋችን የሚያተኩርበት ርዕስ ነው።

«እዉቀት ለነገ» በሚል መርህ ከስድሳ የሚበልጡ ከሰሃራ በታች የሚገኙ አፍሪቃዉያት ሀገራት ምሁራንን ጭምር ያሳተፈ የሁለት ቀን ጉባዔ ጀርመን ሃኖቨር ከተማ በሚገኘዉ የፎልክስቫገን ተቋም ተካሂዶአል። ጉባዔው በአፍሪቃ በማህበራዊ፤ በሳይንስ፤ በህክምና፤ እንዲሁም በሃይማኖት ረገዶች በሚደረገዉ ሳይንሳዊ ምርምር ሥራ ላይ ተወያይቶአል፤

ዚምባቡዌ ላይ የአደንዛዥ እፅ ዝዉዉርና አጠቃቀምን አስመልክቶ የሚካሄደዉ ጉባኤ፤ መሪዎቹ ወሳኝ ርምጃ ካልወሰዱ የአህጉሩን መረጋጋት ሊጎዳ እንደሚችል አመለከተ። የምዕራብ አፍሪቃ የኤኮኖሚ ማኅበረሰብና በተመድ የእፅ ተከታታይ ጽ/ቤት አፍሪቃ ዉስጥ ሕገ ወጥ የአደንዛዥ እፅ ዝዉዉርን ለመግታት የሚያስችል አዲስ ርምጃ ላይ እየመከሩ ነዉ።

የዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት በዓለማችን ከስምንት መቶ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ እየተራበ የሚታየዉ የምግብ ብክነት ተቀባይነት እንደሌለዉ አመለከተ። ድርጅቱ ዛሬ ይፋ ባደረገዉ ዘገባዉ የምግብ ማጣት ብቻ ሳይሆን የተመጣጠነና በቂ ምግብ አለማግኘት አካላዊ እድገታቸዉ ለእድሜያቸዉ የማይመጥን ልጆች ቁጥርም 165 ሚሊዮን መድረሱንም አስታዉቋል።

ከጉጂ ቦረናና ሊበን ዞኖች ሀገረ ስብከትና ሌሎች አብያተ ክርስቲያን በዘረፉት ገንዘብ ‹‹ሺበሺ›› በሚለው አስከፊ የሙስና ስያሜ የሚታወቁትና በነፍስ ግድያ ወንጀሎች የሚጠረጠሩት አቡነ ሳዊሮስ የሚያስተባብሯቸው የግብር አምሳሎቻቸው፣ መልአከ ገነት አባ አፈ ወርቅ ዮሐንስ እና መልአከ ገነት አባ ዮናስ ታደሰ ዋነኛ ተጠያቂዎች ይኾናሉ ተብሏል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንን ‹‹የዐፄ ምኒልክ ሥርዐት እንዲመለስና የዐፄ ምኒልክ ባንዴራ እንዲሰቀል የሚፈልጉ ናቸው›› ብለው …

ጥቅምት ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በወጣት አብዱላሂ ሁሴን አማካኝነት በኢትዮጵያ የኦጋዴን ክፍል የተፈጸመውን የጦር ወንጀልና የሰብአዊ መብት ጥሰት ፊልም የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም በስዊድን ቁጥር አንድ ቴሌቪዥን በትናንትናው እለት መቅረቡን ተከትሎ አለማቀፉ ጠበቆች ጉዳዩን ወደ አለማቀፍ ፍርድ ቤት ለመውሰድ እንቅስቃሴ ጀመረዋል። ወጣት አብዱላሂ ለኢሳት እንደገለጸው ፊልሙ ከተላለፈ በሁዋላ ሚዲያዎች ሸፊ ሽፋን የሰጡት ሲሆን፣ ስቴላም የተባሉ …

ጥቅምት ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእየአመቱ የሚከበረው የኢድ-አል አድሃ ( አረፋ) በአል ኢብራሂም ልጁን ለመስዋት ያቀረቡበትን እለት ለመዘከር ነው። በአዲስ አበባ በተካሄደው የበአል አከባበር ስነስርአት ከዚህ ቀደም ያልታዩ ክስተቶች ታይተዋል። ዘወትር እንደሚደረገው የመጅሊስና አዲስ አበባ መስተዳድር ባለስልጣናት ንግግር አላደረጉም። ድምጻችን ይሰማ ትናንት ባወጣው መግለጫ የመንግስት ባለስልጣናት ወይም የመጅሊስ አመራሮች መልእክቶችን ለማስተላለፍ ንግግር ማድረግ ከጀመሩ …

ጥቅምት ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመስተዳድሩ ውስጥ የሚሰሩ የኢሳት ወኪሎች እንደገለጹት ከዚህ ቀደም በመስተዳድሩ ውስጥ የሚፈጸመውን ሙስና ማጋለቱን ተከትሎ መንግስት ተጠርጣሪ ግለሰቦችን ከቦታቸው በማንሳት ወደ ሌሎች መስሪያ ቤቶች በማዛወር የህዝቡን ቅሬታ ለመመለስ ጥረት ቢያደርግም፣ አሁንም በአስተዳደሩ ኢንዱስትሪ ልማትና ከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት ስር በሚገኙት የከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንት ፣ የመሬትና መሬት ነክ ቋሚ ንብረት ምዝገባ …

ጥቅምት ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአለማቀፍ የወንጅል ፍርድ ቤት 50 አመታት የተፈረደባቸው ቻልረስ ቴለር  በዛሬው እለት ለእንግሊዝ ፍርድ ቤት ተላልፈው የተሰጡ ሲሆን፣ በሩዋንዳ እንዲታሰሩ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተድርጎባቸዋል። ፕሬዞዳንቱ በሴራሊዮን ለተፈጸመው የጦር ወንጀል እጃቸው አለበት በሚል ዘሄግ የሚገኘው የወንጀል ፍርድ ቤት አምና የ50 አመታት እስር እንደፈረደባቸው ይታወቃል።  

በምዕራብ ትግሪይ በአዲ ሃርሽ እና አዲ ዐይኒ መጠለያ ሠፈሮች ውስጥ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ይደርስብናል የሚሏቸውን በደሎች ያሰሙበትን፣ መብቶቻቸው እንዲከበሩ የጠየቁበትን ሰልፍ በቅርቡ አድርገዋል፡፡ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በተፈጠረ ግጭት ሕይወት ጠፍቷል፤ ሰው ተጎድቷል፡፡

ዘንድሮ በተካሄደው የጀርመን ምክር ቤት አባላት ምርጫ ከሻነፉት ተወዳዳሪዎች መካከል አንድ አፍሪቃዊ ጀርመናዊ ይገኙበታል ። በዘንድሮው ምርጫ የምክር ቤት መቀመጫ ለማግኘት የበቁትን አፍሪቃዊ ጀርመናዊ የህዝብ እንደራሴን ጨምሮ የውጭ ዝርያ ያላቸው የጀርመን ምክር ቤት አባላት ቁጥር ከፍ እያለ ነው ።

የወባ በሽታን ለመከላከል የሚረዳ ክትባት የመገኘቱ ዜና በተለይ በበሽታዉ ክፉኛ ለሚጠቁ ሀገራሃት ታላቅ የምስራች ነዉ። የወባ በሽታን ጨርሶ ለማጥፋት ግን ዘመናትን የሚጠይቅ እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

 

 ከፕሮፌሰር መስፍን /ማርያም

እንደ ኢትዮጵያ ባለ ኋላቀር አገር አገር ውስጥ መሠልጠን ብዙ ችግር አለበት፤ እኔ ራሴ በኮምፒዩተር መጻፍ ከጀመርሁ ሠላሳ ዓመት ሊሆነኝ ነው፤ ታዲያ መብራት ጠፋና የምሠራው ባጣ የቆዩ ወረቀቶችን ሳገላብጥ አንድ እአአ በዲሴምበር 26 1965 ከዱሮ ተማሪዬ የተጻፈልኝን ደብዳቤ አገኘሁ፤ በዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በነበረ ከአንድ በጣም ጎበዝ ወጣት የተላከልኝ ነበረ፤ ከተመረቀ በኋላ በአንድ ኩባንያ ውስጥ ተቀጥሮ ለጥቂት ዓመታት ሠርቶ ትምህርቱን ለመቀጠል ወደ አሜሪካ ሄዶ በሎዝ አንጄለስ አካባቢ ከሚገኝ ትምህርት ቤት ገብቶ ነበር፤ ደብዳቤውን የጻፈልኝ ከዚያ ነው፤ ደብዳቤው ሰባት ገጾች አሉት፤ ከሰባቱ ገጾች አምስቱ ስለኢትዮጵያ ያለውን ስጋት የሚገልጽ ነው፤ በሎዝ አንጀለስ አካባቢ ካሉ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት በሚያደርግበት ጊዜ ሁሉ ብዙዎቹ የሚያሳዩት የመንደረኛነት ስሜት እያበሳጨው የተማሩት ሰዎች በእንደዚህ ያለ ማኅበረሰባዊ ኋላቀርነት ውስጥ ሆነው ኢትዮጵያ የምትባለው አገር እንዴት መራመድ ትችላለች? እያለ ይሰጋ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጥቅምት ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለወራት ተቋርጦ የነበረው የድምጻችን ይሰማ ተቃውሞ ነገ በመንግስት ባለስልጣናትና በመጅሊስ መሪዎች ንግግር ላይ ተግባራዊ እንደሚሆን ከወጣው መርሀግብር ለማወቅ ተችሎአል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚካሄደው ዝግጅት የመንግስት ባለስልጣናትም ሆኑ የመጅሊስ አመራሮች ንግግር የሚያደርጉ ከሆነ ንግግሩ እስኪቆም ድረስ ተቃውሞው ይቀጥላል። ተቃውሞው በመላ አገሪቱ እንደሚከናወን ድምጻችን ይሰማ ያወጣው መረጃ ያመለክታል። ፖሊስ ጸጥታ ለማስከበር …

ጥቅምት ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲሱን የትምህርት አመት ለመጀመር ምዝገባ ያጠናቀቁት ተማሪዎች ፣ ከአለባበስ ጋር በተያያዘ ባነሱት ተቃውሞ የግቢው መስታውቶችና አንዳንድ አገልግሎት መስጪያ እቃዎች መሰባበራቸው ታውቋል፡፤ ይህንንም ተከትሎ ፖሊስ ግቢውን መቆጣጠሩን ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ተማሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። የተቃውሞው መነሻ የዩነቨርስቲው ባለስልጣናት ከቤተከርስቲያን መልስ ነጠላ ለብሰው ወደ መመገቢያ ክፍል የገቡትን ተማሪዎች ፣ ነጠላ ለብሳችሁ መግባት …

ጥቅምት ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሕአዴግ ካድሬዎችን ለማሰልጠን የተገነባውን የፖለቲካ ማሠልጠኛ ተቋም በሚኒስትር ማዕረግ ሲመሩ የነበሩት አቶ አዲሱ ለገሰ ከኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የተውጣጡ ምክትሎች ተሹመውላቸዋል፡ ፡ ከብአዴን አቶ ለገሰ ቱሉ፣ ከደሕዴን አቶ ወንድሙ ገዛኸኝ፣ ከሕወሓት አቶ ነጋ በርሄ ሲሆኑ፣ ከኦሕዴድ የተወከለው አመራር እስካሁን አለመታወቁን ሪፖርተር ዘግቧል። ማሠልጠኛ ማዕከሉ  በስድስት ዙሮች በርካታ ካድሬዎችን ያሰለጠነ መሆኑን …

ጥቅምት ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክረምቱን መውጣት ተከትሎ ወባ በሚያጠቃቸው ወረዳዎች ወረርሺኙ መከሰቱን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በገዳይነቱ  ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃ  የሚይዘው የወባ በሺታ በአሁኑ ስዓት በአርሶ አደሩ ህይዎት ውስጥ ፈታኝ መሆኑን ከሁሉም ክልሎች ለፌድራል ጤና ጥበቃ ሚኒስትር የተላለፈው መረጃ ያመለክታል፡፡ በበሺታው ፈውስ አጥተናል የሚሉት ኗሪዎች ከገበያ እንደ ሸቀጥ እቃ የሚገዙዋቸው መዳህኒቶች የማዳን አቅም …

ጥቅምት ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሱዳናዊው ቱጃር ሞ ኢብራሂም የተቋቋመው የሞ ፋውንዴሽን መልካም አስተዳደርን ያሰፈረ፣ ስልጣኑን በሰላም ለለቀቀ የአፍሪካ መሪ 5 ሚሊዮን ዶላር በሽልማት መልክ ይሰጣል። በዚህ አመትም ለ4ኛ ጊዜ አሸናፊ የሚሆን የአፍሪካ መሪ አልተገኘም። እስካሁን ድረስ ሽልማቱን ያሸነፉት የኬፕ ቨርዴው ፔድሮ ቬሮና ፓይሬስ፣ የቦትስዋናው ፌስተስ ሞጋኤና የሞዛምቢኩ ጆአኪም ቺሳኖ ናቸው።

ጥቅምት ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ ባወጣው ዘገባ እንደገለጸው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በናይጀሪያ ቡድን መሸነፉ ያበሳጫቸው  ደጋፊዎች የናይጀሪያን ቡድን አሳፍሮ ሲጓዝ በነበረው አውቶቡስ ላይ ድንጋይ በመወርወር አንድ ተጫዋች አቁስለዋል። ኖሳ ኢግቦር የተባለው ተጫዋች መዳፉ አካባቢ መመታቱን የዘገበው ቢቢሲ፣ የናይጀሪያ ቡድን ባለስልጣናት ክስተቱን ለአለማቀፉ እግር ኳስ ፌደሬሽን ማሳወቃቸውንም ገልጿል። ድርጊቱን ተከትሎ ምናልባትም ፊፋ በኢትዮጵያ ላይ …

ኑር ከሰው ኑር ከሃገር ይል ነበር፡ የሃገሬ ሰው፤ ሰው ለሰው መፈጠሩን የሚገልጽ አባባል ነው። በአጠገብህ ካለው መሰልህ ሰው አብረህ መኖር ከቻልክ በመላው ሃገርህ ካለው ሰው መኖር አያቅትህም ለማለት ነው። የሰው ልጅ ለራሱ መልካሙን እንደሚያስብና እንደሚሰራ ሁሉ ራሱን ለማጥፋትም የዛኑ ያህል ይሠራል። ጥያቄው ባብላጫው ለየትኛው ይሠራል ነው? ሕዝብ እንደ አንድ የሃገር ዜጋ ተሰባስቦ ሲኖር ማሟላት ያለበት […]

SHARE:

ታስረው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ከ2 ቀን ቆይታ በኋላ ተለቀቁ
አባላቱ በዛሬው እለት ከቀኑ 8 ሰአት በአራዳ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ፖሊስም ለፍርድ ቤቱ በፌደራል ፖሊስ ካምፕ አካባቢ የፓርቲ አርማ ይዞ ማለፍና ባልተፈቀደ ቦታና ሰአት ቅስቀሳ ማድረግ የሚል አስቂኝና የፈጠራ ክስ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ግን ቅዳሜና እሁድ ወጣቶቹ ያለአግባብ እንደተንገላቱ ለፖሊስ በመግለፅ በአስቸኳይ በመታወቂያ ዋስ እንዲወጡ በማዘዙ ሁሉም አባላት ሊፈቱ ችለዋል፡፡

በዘር ማጥፋት፥በሰብአዊ ፍጡር ላይ በተፈፀመ ወንጀል እና በጦር ወንጀል የሚጠረጠሩ ፖለቲከኞችን እንዲመረርምር፥ በተረጋገጠባቸዉ ላይ እንዲፈርድ የተቋቋመዉ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ግን እስካሁን ክስ የመሠረተዉ በስምት የወንጀል ጭብጦች ነዉ።በስምንቱም ጉዳዮች የከሰሳቸዉ፥ ወይም የፈረደባቸዉ ፖለቲከኞች በሙሉ ግን አፍሪቃዉያን ናቸዉ።

‹ይህቺ ኢትዮጵያ የምትባለውን ሀገር የሚጠብቅና የሚታደግ አንዳች ኃይል አለ› የሚባለውን ነገር እንድናምን የሚያደርጉ ብዙ አጋጣሚዎች አሉ፡፡ ሕዝቧ ብትን፣ ቅዝቅዝ፣ ድብዝዝ ሲል ከየት እንደሚመጣ ሳይታወቅ ብቅ የሚል፣ እንደ አውሎ አጥለቅልቋት፣ እንደ እቶን አንድዷት፣ እንደ ሐረግ አስተሣስሯት፣ እንደ ደመና ከልሏት፣ እንደ አደይ አበባ አስውቧት፤ እንደ ቀስተ ደመና ቃል ኪዳኗን አድሶ፣ እንደ ጠል አረስርሶ፣ እንደ ሸማ ፍቅር አላብሶ፣ እንደ ደመራ የሀገር ፍቀር ስሜት ለኩሶ፣ እንደ ጨረቃ አድምቆ፣ እንደ ፀሐይ አሙቆ፣ እንደ ሰም አጣብቆ፣ የሚጎበኝ መንፈስ አላት፡፡

እውን ኳስ ነው ያስለቀሰን? እውን ግብ ነው የናፈቀን? እውን የጨዋታ ጥበብ ነው የጠማን? እውን ለዓለም ዋንጫ መድረሳችን ነው እንዲያ ፍቅርን እንደ ሸማ ያላበሰን? እኔ ግን ያየሁት ከዚህ ሁሉ በላይ የሆነውን ነው፡፡ አንዳች ያጣነው ነገር፣ አንዳች የጠማን ነገር፣ አንዳች የተነጠቅነው ነገር፣ አንዳች ቁጭት ውስጥ የከተተን ነገር፣ አንዳች እንደ ዋልታ የሚይዘን፣ እንደ ማገር የሚያስተሣስረን፣ እንደ ተራዳ የሚደግፈን፣ እንደ ደመራ የሚሰበስበን፣ እንደ ችቦ አንድ የሚያደርገን፣ አንዳች ነገር የጠማን ይመስለኛል፡፡

ትናንት የኳስ ደጋፊዎችን አልነበረም ያየሁት፣ የኢትዮጵያን ደጋፊዎች እንጂ፡፡ አንድነቷን፣ ኅብሯን፣ ልዕልናዋን፣ ታላቅነቷን የሚደግፉ፤ መለያየትን፣ መከፋፈልን፣ መገፋፋትን፣ መጠፋፋትን፣ የሚቃወሙ ኢትዮጵያውያንን ነው ያየሁት፡፡ ሰንደቋን ከንሥር በላይ ከፍ ያደረጉት፣ መዝሙሯን በባዶ ሆዳቸው ሰማይ እስኪገረም ድረስ የዘመሩት፣ ከተማዋን በአረንጓዴ፣ ቢጫ ቀይ ያጥለቀለቁት ለኳሱ ብቻ አይመስለኝም፡፡ ዓላማቸው ከኳስ በላይ ነበር፡፡ ፍላጎታቸው የኳስ ቡድኑ ሦስት ነጥብ እንዲያመጣ ብቻ አልነበረም፡፡ ፍላጎታቸው አንድነት፣ ሉዓላዊነት፣ ሕዝባዊነት፣ ጀግንነት፣ ኢትዮጵያዊነት ሦስት ነጥብ እንዲያመጣ ነበር – አምጣቷልም፡፡

ትናንት ናይጄርያ ቡድናችንን፣ እኛ ታሪካችንን አሸንፈናል፡፡

የሰሜኑ ዋልያ ከወጣበት የዳሽን ተራራ ይልቅ፣ ዋልያዎቹ የወጡበት የኢትዮጵያዊነት ተራራ ይበልጥ ነበር፡፡ ከዋልያው ብርቅዬነት የዋልያዎቹ ብርቅዬነት በልጧል፤ እንዲህ አንድ አድርጎ የሚያስደስተን፣ አንድ አድርጎ የሚያስለብሰን፣ አንድ አድርጎ በቁጭት የሚያስለቅሰን አጥተን ነበር፡፡ ልቅሷችን የበደል፣ ደስታችን የግላዊ ጥቅም፣ መሰባሰቢያችን ብሔረሰብ፣ መገናኛችን የወንዝ ቋንቋ፣ መነጋገሪያችን አካባቢያዊ ጉዳይ፣ ንግግራችን ጨቋኝና ተጨቋኝ ሆኖብን ነበር፡፡ ዋልያዎች ሆይ ክብር ይስጣችሁና ከዚያ ከፍ አድርጋችሁናል፡፡ አልተሸነፋችሁም አሸንፋችኋል፡፡ መለያየትን፣ መከፋፈልን፣ መገፋፋትን፣ ወንዝ ለወንዝ መሄድን፣ በሰፋ ግብ አሸንፋችኋል፡፡ ባንዲራ አስለብሳችሁ፣ ለባንዲራ አስዘምራችሁ፣ ለባንዲራ አስለቅሳችሁናል፡፡

ልጆቻችን አንድ፣ ከፍ ያለ፣ አድማስ ላይ ብቻ የሚታይ፣ ከሁላችንም ድምር በላይ የሆነ ሀገራዊ ስሜት እንዲሰማቸው አድርጋችኋል፡፡ በየተወሰነ ዘመን ራሱን እንደሚያድሰው የከራድዮን ወፍ የኢትዮጵያዊነትን መንፈስ እንደገና አደሳችሁት፡፡ በየትኛው ሕግና መመሪያ፣ በየትኛው አሠራርና ቅጣት፣ በየትኛው መዋቅርና አደረጃጀት ይህንን የሰንደቅ ዓላማ ፍቅርና ክብር፣ ይህን የሀገር ፍቅርና ክብር፣ ይህን የአንድነት ስሜትና መንፈስ ልናመጣው እንችል ነበር? እንኳን ኖራችሁ፡፡

እናንተ አላዘዛችሁንም፣ ግን አደረግነው፤ አልነገራችሁንም፣ ግን ፈጸምነው፤ ዐዋጅ አላወጣችሁም፣ ግን ተገበርነው፤ መዋቅር አልዘረጋችሁም፣ ግን ልባችን ውስጥ ገባችሁ፤ አልቀጣችሁም፣ ግን ታዘዝናችሁ፤ ጥሪ አላስተላለፋችሁም፣ ግን ሆ ብለን ወጣን፤ አልመዘገባችሁንም፣ ግን አባላችሁ ሆንን፤ ደወል አልደወላችሁም፣ ግን ሌሊት በስታድዮም ሰዓታት አደርን፤ አበል አልከፈላችሁንም፣ ግን ሳይደክመን ተሰለፍን፤ ወደ ከፍታው መራችሁን፣ እኛም  በደስታ ተከተልናችሁ፡፡

በኳስ ሜዳማ ብራዚልም ይሸነፋል፤ ስፔንም ይሸነፋል፤ የኳስ ወላጅ እናቱ እንግሊዝም ትሸነፋለች፡፡ የአኩስምና የላሊበላ፣ የጀጎልና የጎንደር ግንብ ጥበብ የተሞላበት ያንን የመሰለ ኳስ፣ የጠጅ አጣጣላችን፣ የጠላ አጠማመቃችን፣ የቅመም አቀማመማችን፣ የወጥ አሠራራችን፣ የክትፎና የቆጮ፣ የገንፎና የአምባሻ ጥበባችን በእናንተ ጨዋታ ታየ፡፡ ኳስን ገረማት፡፡ እንግሊዝ አፍ ያዘች፣ ስፔንን ገረማት፣ ብራዚል ልትቀሩ ነው ብላ ቅር አላት፣ ፈረንሳይ አጀብ አለች፣ ጀርመን ተደነቀች፤ ጣልያን ተደመመች፡፡

አሁን ስለ እናንተ ስንናገር በኩራት ነው፤ አሁን ልጆቻችን የሚጨዋወቱት በቁጭት ነው፡፡ ‹ዋልያው ንሥሩን ጋልቦታል› እንላለን፡፡ ይህንን ድሮ በ ‹ዜና እስክንድር› ብቻ ነበር የምንሰማው፡፡ እስክንድር ጠቢቡ ወደ ገነት ለመሄድ ብሎ ንሥሩን ከፈረስ ጋር አዳቅሎ ጋለበው አሉ፡፡ እናንተም እንዲሁ ንሥሩን ጋልባችሁ ወደ ልዕልናው ገነት፣ ወደ ኢትዮጵያዊነት ገነት፣ ወደ አንድነት ኤደን ወሰዳችሁን፡፡

ይህቺን ቀን እንደ አድዋ ድል፣ እንደ ዶጋሊ ድል፣ እንደ ሚያዝያ ሃያ ሰባት፣ ስናከብራት ትኖራለች፡፡ የድል ቀን ናትና፡፡ አንድነት መለያየትን፣ ኅብረ ብሔርነት ጠባብነትን፣ ኢትዮጵያዊነት ጎጠኛነትን፣ ሉዓላዊነት ተዋራጅነትን ድል ያደረጉበት ቀን ናት፡፡ 

    የቃለ ዐዋዲው ድንጋጌ በፍርድ ቤቶች ያለው ተቀባይነት ማነስ ያስከተለው ችግር፣ ልዩ እምነት ያላቸው አንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣናት በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚያደርሱት ሕገ መንግሥቱን የጣሰ ተጽዕኖ፣ ወደ ዐረብ አገሮች እየሔዱ እምነታቸውን ወደ እስልምና የሚለውጡ ኦርቶዶክሳውያን ቁጥር መበራከትና ከእኒህም የካህናት ሚስቶች መኖራቸው፤ የአብነት ት/ቤቶች ህልውና ቀጣይነትና በተለይም የመጻሕፍተ ሊቃውንት ጉባኤያት በብዛት መታጠፍ፤ የመንፈሳዊ ኮሌጆች አስተዳደር፣ የደቀ …

SHARE:

ቅዳሜ ዕለት የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ዛሬ ከሰአት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡
ቅዳሜ እለት በጃንሜዳ ፖሊስ ማዘዣ ጣቢያ ታስረው የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ችሎት አካባቢ ወደሚገኘው ወረዳ 9 ፖሊሰ ጣቢያ ተወስደው 2 ቀን እንዲያድሩ ከተደረጉ በኋላ ዛሬ ጠዋት ወደ ጃንሜዳ ፖሊስ ጣበያ ተመልሰው የተወሰዱ ሲሆን አሁንም በጃንሜዳ ፖሊስ ጣቢያ ይገኛሉ፡፡ በወረዳ 9 የ2 ቀን ቆይታቸውም የፖሊስ አባላት በግዴታ የወንዶቹን ፀጉር የቆረጧቸው መሆኑ ተረጋግጧል፡፡አባላቱ ዛሬ በ8 ሰአት ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ የተነገራቸው ሲሆን በጃንሜዳ ፖሊስ ጣቢያ የፓርቲው አባላትና ከፍተኛ አመራሮች እየጠየቋቸው ይገኛሉ፡፡

አሌክስ አብረሃም

እናት አገርን የሚያሳምረው ህንፃ ይመስለኝ ነበርአገርን የሚያሳምረው መንገድ ይመስለኝ ነበር አገርን የሚያሳምረው ዛፍና ቅጠል ይመስለኝ ነበር ….አገርን የሚያሳምረው ለካ ለአንድ አላማ የተሰለፈ በአንድነትና በአብሮነት ስሜት ፈገግታና እልሁ ፊቱ ላይ የሚንቀለቀል ህዝብ ነው !! አገሬ ቆንጆ ናት ድህነት ብስቁልና መገፋት የጋረደው ፈገግታችን እንዲህ እንደ ዛሬ ከችግራችን በላይ ፈክቶ ሲታይ አልኩ …… ኢትዮጲያ እች ናት፤ አገሬ እችናት !!

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተመስገንደሳለኝ

‹‹ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም
እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም›› ማን ነበር ያቀነቀነው? …ብቻ ማንም ይሁን ማን፤ እኔም እደግመዋለሁ፡- ሀገሬን የደፈረ ይውደም!! …እነሆ ከፉከራው ወደ አጀንዳችን እንለፍ፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን፣ በሚቀጥለው ዓመት በብራዚል በሚካሄደው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ለመሳተፍ፣ ከናይጄሪያ ጋር የደርሶ መልስ ግጥሚያ ብቻ ቀርቶታል፡፡ በነገው ዕለትም የመጀመሪያውን ጨዋታ በአዲስ አበባ ያደርጋል፡፡ በዚህ ፅሁፍ የማነሳው ሃሳብም፣ ስለጨዋታው ሳይሆን፣ ጨዋታውን
የሚያደምቀው ሰንደቅ-ዓላማን (ባንዲራን) በተመለከተ ይሆናል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …