ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጉባኤ ላይ የተሳተፉ አንድ የሀይማኖቱ አስተማሪ ፣ የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ  ጉባኤ በ፴፪ኛው ዓመታዊ ስብሰባው ያወጣው መግለጫ ፣ በስብሰባው ላይ የተነሱትን ነጥቦች ዘርዝሮ አቀረበ ነው ብለዋል። ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሀይማኖት አባቶች በድፍረት መናገራቸው ከምን የመጣ ይመስለውታል ተብለው የተጠየቁት መምህሩ፣ ምናልባትም ለውጡ ከፓትርያርኩ ጋር የተያያዘ ሳይሆን …

ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነባር የህወሀት ተጋይ የነበሩትና በአሁኑ ጊዜ በገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው የሚገኙት ታዋቂው ታጋይ አቶ አስገደ ገብረስላሴ ፣ ልጆቻቸው በከፍተኛ ስቃይ ላይ እንደሚገኙ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ገልጸዋል። የማነ  የተባለው ልጃቸው፣ በእስር ቤት ላይ በደረሰበት ግፍ ምክንያት አካል ጉዳተኛ ሆኗል። አህፎም ደግሞ ከስራ ገበታው ላይ ታፍኖ ከተወሰደ በሁዋላ፣ …

ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ መድረክ በስዊድን የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኒታን በተመለከተ በተለይም በቅርቡ በስዊድን ቴሌቪዥን  የኦጋዴን ህዝብ ጭፍጨፋ አስመልክቶ ያሳየውን ዶክመንትሪ ፊልም የተመለከቱ የስዊዲን የህግ ጠበቃና የአለም አቀፍ የህግ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጁሪስት ስቴላ ያርዴት የመንግስት ባለስልጣናትን በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ለመክሰስ እንደተዘጋጁ በማስታወቃቸው እሳቸውንና ሌሎችን እንግዶች በመጋበዝ ኖቬምበር 2 ቀን 2013 …

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም Prof. Mesfin Woldemariamፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

በአሥራ አምስተኛው ምዕተ-ዓመት ግድም ሆላንድ የታወቀ የባሕር ኃይል ሆኖ ከደቡብ አፍሪካ እስከደቡብ አሜሪካ፣ የኔዘርላንድ የቆዳ ስፋት 41 526 ኪ.ሜ. ካሬ ወይም የትግራይ ግማሽ ነው፤ የሕዝቡም ቁጥር አሥራ ስድስት ሚልዮን ተኩል አይሞላም። የትግራይን ግማሽ በሚሆን መሬት ላይ የትግራይን ሦስት እጥፍ ግድም የሚያህሉ ሰዎች ይኖሩበታል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ በሀገራችን ላይ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲሰፍንና ፍትሃዊነት እንዲኖር በቁርጠኝነት እየታገለ ይገኛል፡፡ በትግሉ ውስጥም ፓርቲያችን የተጋረጡበትን ፈተናዎች እየተወጣና የሚከፈለውን ዋጋ እየከፈለ ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ በመቀጠል ለህዝቡ ያለውን ታማኝነት እያረጋገጠም ነው፡፡ ፓርቲያችን በመላ ኢትዮጵያ ያለውን አደረጃጀት በመጠቀምና ሕዝቡን በማሳተፍ ለሶስት ወራት የሚቆይ ህዝባዊ ንቅናቄ በማካሄድ የመጀመሪያ ዙር የሆነውን ሰላማዊ […]

በሙሥና የተጠረጠሩ ክሥ ተመሠረተባቸው
የኢትዮጵያ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አቃቢ ሕግ በሙስና የተጠረጠሩ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ዕውቅ ነጋዴዎች ላይ ትናንት ክሥ መሥርቷል።

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አሥራ አምስተኛ የወንጀል ችሎት ትናንትና ዛሬ በዋለው ችሎት የቀድሞ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታና ምክትላቸው የነበሩት የአቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ፣ የሃገር ውስጥ ደኅንነት ኃላፊ የነበሩት አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፣ እንዲሁም አንዳንድ ከፍተኛ ነጋዴዎች በሃገሪቱ ላይ በመቶዎች ሚሊዮን ብር የሚገመት ጉዳት በማድረስ ተከስሰዋል።

የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሦስት የተለያዩ መዝገቦች፤ ባጠቃላይ በአርባ ሁለት ተጠርጣሪዎች ላይ ከመቶ በላይ ክሦችን መመሥረቱ ታውቋል።

ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና …

የኢትዮጵያ መንግስት ቢያንስ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት ስራ ፈላጊዎችን ወደ ሳውዲ አረቢያ እንዳይገቡ ማገዱን ኣስታወቀ።
በዚሁ መሰረት 40 ሺሽ ያህል ቀደም ሲል የተፈቀዱ ቢዛዎችም ተሰርዘዋል።

የጀርመን መከላከያ ሚኒስቴር የጀርመን የአፍጋኒስታን ኩንዱዝ ተልዕኮ ማብቃቱን ባለፈው ቅዳሜ አስታውቋል። የጀርመን ጦር ኩንዱዝን ሙሉ ለሙሉ ለቆ መውጣት የአካባቢውን ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆን ለጦሩ የተለያየ አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ አፍጋናውያንን አስግቷል ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ለአሥር ቀናት በመላ ሀገሪቱ እና ከሀገር ዉጪ የሚገኙ አብያተክርስቲያናት ተወካዮች በተገኙበት የሀገረ ስብከቱን ጳጳሳት ጠርታ በውስጧ ስላሉ ችግሮች አወያይታለች።

በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የካንሰር ታማሚዎች ቁጥር እየጨመረ በመሄድ ላይ መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት ይገልጻል። ድርጅቱ አያይዞም በጎርጎሪዮሳዊዉ 2020ዓ,ም 65 በመቶ የሚሆኑ የካንሰር ታማሚ በአዳጊና በማደግ ላይ በሚገኙ ሃገራት እንደሚገኝ ከወዲሁ ጠቁሟል።

በጀርመን ባለፈው መስከረም ወር በተካሄደው ምክር ቤታዊ ምርጫ የብዙኃኑን ድምፅ ያገኙት የክርስትያን ዴሞክራቶች እና የክርስትያን ሶሻል ህብረት፣ ከሶሻል ዴሞክራቶቹ ፓርቲዎች ጋ በቅርቡ የጥምር መንግሥት ያቋቁማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

33 ፓርቲዎች እየተባሉ የሚጠሩት በ15/02/ 05 የአዳማ ፔቲሽን ተብሎ የሚጠራውን የፈረሙ ናቸው፡፡ የጋራ ስምምነት ሰነድ የፈረሙት 24 ፓርቲዎች ሲሆኑ ጥቅምት 10 ቀን በዋለው ስብሰባቸው ወደ ቅንጅት አድገዋል፡፡ እሁድ በተደረገው ስብሰባቸው የመተዳደሪያ ደንብ፣ የመመስረቻ ፅሁፍና መለስተኛ የድርጊት ፕሮግራም በመፈረም “ትብብር ለዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ/ ትብብር/ በሚል ተሰይመዋል፡፡ በዚህ ውስጥ የተካተቱት 10 ፓርቲዎች ብቻ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ያልተካተቱበት ምክንያት ተብራርቷል፡፡ […]

ወ/ሮ አዜብ መስፍን Azeb Mesfinኢዮብ ይስኃቅ

ከዕለታት አንድ ቀን ባልተለመደ ድፍረት የሙስና ኮሚሽን ሰይፉን ትላልቅ የወያኔ ባለሥልጣናት ላይ አሳረፈ። እንደመድኃኒት ብልቃጥ እዚህም እዚያም ተወሽቆ የነበረ ብርና ንብረት እያስቆጠረ ወንጀለኞቹን ዋስ እየከለከለ ወደ ወህኒ ወረወረ። ሚኒስትሮች ከቦታቸው ተፈናቀሉ፤ የሙስና እናት የሚለውን ሜዳሊያ ያጠለቀችው ወ/ሮ አዜብ ከኤፈርት ተባረረች። ያዲሳባ ከንቲባነትም ሱሚ ነው ተባለች። ከሁለት ብቻ ሳይሆን ከብዙ ያጣች ሆነች። ህዝቡ እልል ለማለት ቢፈልግም ወያኔን ስላላመነ መጨረሻውን ለማየት መጠባበቅ ያዘ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በመጀመሪያው ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባው ስለሚያተኩርባቸው ጉዳዮች ዛሬ፣ ጥቅምት 13 ቀን 2006 ዓ.ም. ጥዋት በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በቅዱስነታቸው መግለጫ መሠረት ምልአተ ጉባኤው÷ ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት ምእመናንን ስለ መጠበቅና ማብዛት፣ የቤተ ክርስቲያንን የትምህርት ተቋሞች በጥራትና አደረጃጀት በመለወጥ ከመማርና መሠልጠን አልፎ መከራን ለመቀበል የተዘጋጁ ላእካነ ወንጌልን …

የአየር ንብረት ለውጥና ልማት በአፍሪካ ​​
የአየር ንብረት ለውጥና ልማት በአፍሪካ
የአየር ንብረት እየተለወጠ የመሆኑ ነገር እውነት መሆኑንና ለውጡ ለሚያስከትለው አደጋም የአፍሪካ መጋለጥ ምን ያህል የሰፋ እንደሆነ ለአህጉሪቱ ተጠራጣሪዎች ማስረዳትና እነርሱን ማሳመን የመጀመሪያው ተግባር መሆን እንደሚገባው ተገለፀ፡፡

አፍሪካ የልማት ጎዳናዋን ከበለፀጉ ሃገሮች መቅዳት አለባት የሚባለውም ስህተት ነው ሲሉም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ ካርሎስ ሎፔዝ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በተከፈተው “የአየር ንብረት ለውጥና ልማት በአፍሪካ” ሦስተኛው ጉባዔ መክፈቻ ላይ ተናግረዋል፡፡

ዋና ፀሐፊው የአፍሪካን የዛሬ የአየር ንብረት ለውጥ ይዞታ አውሮፓን ከስድስት መቶ ዓመታት በፊት አጋጠሟት ከነበረውና ቁጥሩ እጅግ የበዛ ሰው ከፈጀው አጥፊ ወርርሽኝ ጋር …

ጥቅምት ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት በም/ጠ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሚመራው የልኡካን ቡድን ላይ ጥቃት ፈጽሞ በርካታ ወታደሮችን መግደሉን የግንባሩ ቃል አቀባይ ለኢሳት ገለጹ። አቶ ሀሰን አብዱላሂ እንደገለጹት ጥቃቱ የተፈጸመው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ9 የክልል መሪዎችንና ባለሀብቶችን አስከትለው በአካባቢው ጉብኝት ለማድረግ ቀብሪደሀር አየር ማረፊያ ባረፉበት ወቅት ነው። ባለስልጣኖቹ ጉበኝት እንደሚያደርጉ አስቀድሞ …

ጥቅምት ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ልሳን የሆነው ፍኖተ-ነፃነት እንደዘገበው፦አብረሃ ጅራ እና አብደራጊ የተባሉ ሁለት ወረዳዎች ከዚህ በፊት በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን ስር የነበሩ ቢሆንም፤  መሬቱ  ግን ባብዛኛው በቅርብ ጊዜ ከትግራይ ክልል በመጡ ገበሬዎች ተይዟል፡፡ ቦታዎቹ በብዛትና በስፋት የሰፈሩት ገበሬዎቹች አስተዳደራዊ የበላይነትን በመጠቀም ወረዳዎቹን ወደ ትግራይ ለማካለል እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተጠቁሟል፡፡ …

ጥቅምት ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ራሱ  የ 40 በ 60 መኖሪያ ቤት ሠርቶ  ለመስጠት የሰጠውን መግለጫ አምነው ከ81 ሺህ ሰዎች በላይ ሙሉ ክፍያ ከፈፀሙ በሁዋላ፤  ሀሳቡን በመቀየር ከፋዮቹ በማህበር ተደራጅተው ቤቱን ራሳቸው እንዲሠሩ መወሰኑ ተመዝጋቢዎችን አሳዝኗል። እንደ ሪፖርተር ዘገባ በአሁኑ ጊዜ  መቶ በመቶ  የከፈሉ የ40/60 ተመዝጋቢዎች በመኖርያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበር ወደ ተነደፈው …

ጥቅምት ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ(ህወሀት) ውስጥ የተካረረ አለመግባባት እንደተፈጠረ በስፋት በሚነገርበት በዚህ ወቅት አቶ ስብሀት ነጋ ፣ የኢህአዴግ እንጂ የመለስ የሚባል ራእይ የለም ብለዋል። የህወሀት መስራች የሆኑት አቶ ስብሀት ነጋ ይህን ያሉት ከጋዜጠኛ ደረጀ ደስታ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ነው። አቶ ስብሀት ፦” መለስ የ ኢህአዴግን ራዕይ ለማስፈፀም ከፊት ሆኖ ብዙ …

‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ የአንድነት ምልክት የኾነች ሐዋርያዊት፣ ጥንታዊት፣ ብሔራዊትና ሉዓላዊት ናት፡፡ ትላንት የነበረችው ቅድስት ተዋሕዶ ሃይማኖት ዛሬም አትለወጥም፡፡ ቤተ ክርስቲያን አንዲት ናት፡፡ በመንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቷ ሕዝቡን አንድ አድርጋ ትቀጥላለች፡፡›› ‹‹ከፍተኛው የቤተ ክርስቲያን ባለሥልጣን ቅዱስ ሲኖዶስ ነው፡፡ በካህናትና ምእመናን ላይ ሁሉ ሥልጣኑ ይሠራል፡፡ ውሳኔው ይግባኝ የለውም፡፡›› ‹‹የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ ለእምነታችንና ለቤተ ክርስቲያናችን ዋስትና የሚሰጥ …

የእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ፣ የጀርመን ቡንደስ ሊጋ፣ የስፔን ላሊጋ እና የጣሊያን ሴሪ አ የእግር ኳስ ግጥሚያ በዛሬው የስፖርት ጥንቅራችን ሰፋ ያለ ቦታ ተሰጥቷቸዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድንን በተመለከተ ከአድማጮች የደረሱን አስተያየቶችን አካተናል። የአትሌቲክስ ውድድር ውጤትም የዝግጅቱ አካል ነው።

ዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሚዋጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዎች ባለፈው ዓርብ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ያተኮረ በተለይም አዲስ ኣበባ በሚገኘው እና ማዕከላዊ ተብሎ በሚታወቀው የፌደራሉ የምርመራ ማዕከል በእስረኞች ላይ ይፈጸማሉ ባላቸው ሰብዓዊ ሰቆቃዎች ላይ ያነጣጠረ አዲስ ሪፓርት ይፋ ኣድርገዋል።

በጀርመን መዲና በርሊን እንብርት ላይ በሚገኘው በብራንድን ቡርገር ቶር አደባባይ ላይ፤ አፍሪቃን ጨምሮ ከሌሎች አህጉራት የተሰባሰቡ ስደተኞች ለአስር ቀናት ሲያካሂዱ የቆዩትን የርሃብ አድማ ትናንት እሁድ ማቆማቸዉ ተነግሮአል።

አብረሃ ጅራ እና አብደራጊ የተባሉ ሁለት ወረዳዎች ከዚህ በፊት በአማራ ክልል ስር ነበሩ፡፡ ነገር ግን መሬቱ ባብዛኛው በቅርብ ጊዜ ከትግራይ ክልል በመጡ ገበሬዎች ተይዟል፡፡ ገበሬዎቹም አስተዳደራዊ የበላይነትን በመጠቀም ወረዳዎቹን ወደ ትግራይ ለማካለል እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተጠቁሟል፡፡ ጥቅምት 5 ቀን 2005 ዓ.ም በዋለው ስብሰባ የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብ የጀመሩ ሲሆን ከ500 ሺህ ብር በላይም ለጉዳዩ ማስፈፀሚያ ማዋጣታቸው ተጠቁሟል፡፡ […]

እንደ መንደርደሪያ የሁለት ሺህ ስድስት ዓመተ-ምህረት የመጀመሪያ ወር ተጠናቅቋል፤ አዳዲስ ክስተቶችም ታይተዋል፤ ያለፉት አስራ ሁለት ዓመታትንበጃንሆይ ቤተ-መንግስት ያሳለፉት ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ፣ በኦህዴዱ ሙላቱ ተሾመ መተካታቸው አንዱ ነው፡፡ አባይ ፀሀዬና ዶ/ር ካሱ ኢላላም ከበረከት ስምዖንና ኩማ ደመቅሳ በተጨማሪ በሚኒስትር ማዕረግ የኃ/ማሪያም ደሳለኝ ‹‹የፖሊሲና ጥናት ምርምር›› አማካሪ ሆነው መሾማቸው ሌላው ነው (በነገራችን ላይ ሹመቱን እንደተለመደው አይቶ ችላ […]

ባለፈው ሣምንት የሆነ ነገር ጽፌ በአንዳንድ የዘመኑ የዴሞክራሲ ነፋስ በገባቸው ድረ-ገፆች ማስነበቤ ይታወሳል፡፡ ያ ጦማሬ በተቃውሞው ጎራ ተሰልፈው እየታገሉ ለሚገኙ የተወሰኑ አካላትና ለላንቲካውና ለመናጆነትም ቢሆን ለአንድ አካሄዱ ‹ያስፈራኝ› ግለሰብ የተላከ ነበር፡፡ መልስ ስጠብቅ አንድ ሣምንት ሆነኝ፡፡ ነገር ግን በድጋፍም በነቀፌታም በስድብም ጭምር ጥቂት ከማይባሉ ግለሰቦች በኢሜል ከተላከልኝ መልእክት በስተቀር ከጠየቅኋቸው አካላት ጭንቀቴን ተረድተው በተዛዋሪም ቢሆን […]

አቶ አብርሃም ያየህ Abraham Yayehውይይት ከግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ
ክፍል ሁለት፣ ምዕራፍ ሁለት
አብርሃም ያየህ

“አቶ ኢሳያስ አፈወርቂና ሌሎች የህዝባዊ ግንባር ለፍትህና ለዲሞክራሲ መሪዎች በሁለቱ ሀገሮች [ኢትዮጵያና ኤርትራ] መካከል ያለው ወሰን ትርጉም የሌለው በመሆን ላይ ነው እስከማለት ደርሰው ነበር። ጥቂት የግንባሩ ከፍተኛ ካድሬዎች በመጨረሻ ኤርትራና ኢትዮጵያ በፌደሬሽን መሰረት ላይ የሚተባበሩበት [የሚተሳሰሩበት] ሁኔታ እስከሚፈጠር ድረስ የውህደትና የኮንፌደሬሽን መዋቅሮች እየተጠናከሩ መራመድ እንደሚኖራቸው ሃሳብ ሰጥተዋል”

ሙሉውን አስነብበኝ …

“ህወሓት መለስ ከነበረበት በጣም የጠነከረ ድርጅት ይሆናል”አቶ ስብሃት ነጋ
አቶ ስብሃት ነጋ Sibhat Nega

Ethiopia Zare (እሁድ ጥቅምት 10 ቀን 2006 ዓ.ም. Nov. 20, 2013)፦ ሰሞኑን በአሜሪካ ለሚገኙት የህወሓት መስራችና የቀድሞ ሊቀመንበር ለአቶ ስብሃት ነጋ የዘኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ደረጀ ደስታ እስከዛሬ ተጠይቀው የማያውቋቸውን ጥያቄዎች አቅርቦላቸዋል። ቃለምልልሱን ጋዜጣው ላይ በቅርብ ይዞት የሚወጣ ሲሆን፣ ይኸንኑ ቃለምልልስ ለኢትዮጵያ ዛሬ በድምፅ ልኮልናል። ከተጠየቋቸው ጥያቄዎ ውስጥ ከህወሓት ማዕከላዊ አባልነት እንዴት ወደ ተራ አባልነት እንደተሻገሩ፣ ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር ያላቸውን ጠብ፣ ከአቶ መለስ ጋር የነበራቸውን አለመግባባት፣ የአቶ መለስ ደካማ ጎን፣ ሙስኝነትን፣ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ላይ ያላቸውን ውግዘት፣ ስለፕሬሱ፣ … ይገኙበታል። (ለማዳመጥ የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!)

{play}images/doc/audio/2013/131020-sibehat-nega-interview-with-zethiopia.mp3{/play}

የአፍሪቃ ህብረት በሥልጣን ላይ ያለ መሪ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መቅጫ ፍርድ ቤት መከሰስ የለበትም በሚል አሁን ለፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ጥያቄ ለማቅረብ ሰሞኑን ወስኖዋል።

ከ29 ሚልዮን ብር በላይ የበጀት ጥያቄ ለቅ/ሲኖዶስ ቀርቧል የ49 አህጉረ ስብከትን 800 ወረዳዎች ይሸፍናል ከ21,680 በላይ የሰው ኃይል ይሳተፍበታል አጽንዖት ተሰጥቶ እንዲሠራበት አጠቃላይ ጉባኤው በጥብቅ አሳስቧል የአህጉረ ስብከት የስታቲስቲካዊ መረጃዎች አያያዝ ጥራት አሳሳቢ ኾኗል ‹‹የምእመናን ምዝገባ ለቤተ ክርስቲያን ያለው ጠቀሜታ ከመለካት በላይ የኾነ ወሳኝ ተግባር እንደኾነ የጉባኤው አባላት ተረድተናል፡፡ ያለንን አቅም በማቀናጀት በቀጣዩ ጊዜ በጥራት …

በዚህች ኣጭር ጽሁፍ ውስጥ ኤርትራን ለነጻነት ትግሉ በመጠቀሙ ዙሪያ በሚነሱ ክርክሮች ላይ የግል ኣስተያየት ለማከል እፈልጋለሁ። እንደሚታወቀው ኣመጸኛው ህወሃት ያስመረራቸው እና ለለውጥ የሚታገሉ ሃይሎች በሰላማዊ መንገድ በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ማምጣት ዘበት ነው ብለው ኣምርረው በማመናቸው ነፍጥ ማንገባቸው ከታወቀ ውሎ ኣድሯል። እነዚህ ሃይሎች ኤርትራን እንጠቀማለን ኤርትራ የኢትዮጵያን ህዝብ ትግል ለማገዝ ከፍተኛ ፍላጎት ኣሳይታለች እያሉ ነው። ታዲያ […]

አብርሃም ያየህ (ክፍል ሁለት)
ላንዳንድ ሰዎች፣ ወይንም ለበርካታ ሰዎች ማለት ይቻላል፣ ሀገር ማለት ጮማ የሚቆርጡበት፣ ጠጅ የሚጋቱበት፣ ለሽርሽር የሚሄዱበት፣ ወንዙን ተራራውን እየጠሩ በግጥምና በስድንባብ የሚመፃደቁበት፣ የሚጨፍሩበትና የሚዘሉበት፣ ወዘተ ብቻ ይመስላቸዋል። በጣም የሚገርመውና የሚያሳዝነው ደግሞ፤ ሌላው የፖለቲካ ሱስ ያለበት ይመስል፣ ከፖለቲካ ገለልተኛ ነኝ፣ ፖለቲካ አልወድም፣ ኃይማኖተኛ ነኝ፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዋጋ የለውም ወዘተ. የሚሉ ጉዶች አሉ። አንዳንዶቹማ፣ መታገሉንና ላገር መቆርቆሩ ቀርቶ፤ ነብሳቸውን ሽጠው ከሚታገሉ ሰዎች ጋር ላለመታየት እንኳ ሲንጰረጰሩ ማየት ትውልዱ ምን ያህል እንደከሰረ የሚያመለክት ነው። ይቺን አጋጣሚ ተጠቅሜ፣ ባለፈው ዓመት እዚህ ከምኖርበት ዴንማርክ ያጋጠምኝን አብነታዊ ክስተት ላካፍል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አብርሃም ያየህ (ክፍል አንድ)

የኤርትራን ነፃነት በተመለከተ የወያነ መሪዎችና ቲፎዞዎቻቸው ሁሌም ሊያስረዱን የሚፈልጉት፣ ኤርትራ ነፃነቷን ያገኘችው በነሱ ፍላጎት ሳይሆን፤ ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በጦርነት አሸንፎ ኤርትራን ስለተቆጣጠረ ምንም ማድረግ የሚቻል ነገር ያለመኖሩን ነው። ይሁን እንጂ ይህ ትክክለኛ መግለጫ አይደለም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አረንጓዴ – የሮማ ደንብን ስምምነት ፈርመው በፓርላማዎቻቸው ያፀደቁ፤ ቢጫ – የሮማን ደንብ የፈረሙ ግን በፓርላማዎቻቸው ያላፀደቁ፤ ቀይ – የሮማን ደንብ ያልፈረሙና የአይሲሲ አባል ያልሆኑ ​​
አፍሪካ ከአይሲሲ ጋር ያላት ግንኙነት

ሥራ ላይ ያሉ የሃገሮች መሪዎች እንዳይከሰሱ የሚያደርግ ከለላ ዓለምአቀፉ የወንጀል ችሎት – አይሲሲ እንዲሰጣቸውና በኬንያ መሪዎች ላይ የተከፈተው ክስም ላልተወሰነ ጊዜ እንዲዘገይ እንዲደረግም የአፍሪካ ሕብረት ሰሞኑን ጠይቋል፡፡

መሪዎቹ ባለፈው ቅዳሜ፣ ጥቅምት 2/2006 ዓ.ም አዲስ አበባ ላይ ባደረጉት ስብሰባ ጉዳዩን ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚያቀርብና የሚከታተለ ኮሚቴ አቋቁመዋል፡፡

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም /ፎቶ ፋይል/ በሌላ በኩል ደግሞ ይህ የመሪዎቹ ጥያቄ አግባብነት የሌለው ነው ሲሉ የፖለቲካ ሣይንስ ምሁር እና የሕግ …