ከፍተኛ የመንግስት ፕሮቶኮል ሹም ከስልጣን ተነሱ(ከኢየሩሳሌም አርአያ)
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት ከፍተኛ የፕሮቶኮል ዋና ሹም ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ በላይ ግርማይ ከስልጣን መነሳታቸውን የቅርብ ምንጮች ገለፁ። የሕወሐት አባል የሆኑትና ከ1990ዓ.ም ጀምሮ የጠ/ሚ/ሩ እንዲሁም የፕሬዝዳንቱ ፕሮቶኮል ሹም ሆነው በአቶ መለስ ዜናዊ ተሾመው ሲያገልግሉ መቆየታቸውን ያስታወቁት ምንጮች የአቶ በላይ ቢሮ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ውስጥ እንደነበረ ጠቁመዋል። የቀድሞ ፕ/ት ነጋሶ ጊዳዳ፣ የጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ እንዲሁም የፕ/ት ግርማ […]
በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ወላይታ ሶዶ 18 ሰዎች ካለፍርድ ቤት ትእዛዝ ጨለማ ቤት ታስረዋል::ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገር ድረስ መጥታችሁ ቅስቀሳ ለማካሄድ መሞከራችሁ በጣም ደፋሮች ናችሁ!
በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ወላይታ ሶዶ 18 ሰዎች ካለፍርድ ቤት ትእዛዝ ጨለማ ቤት ታስረዋል::
“ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገር ድረስ መጥታችሁ ቅስቀሳ ለማካሄድ መሞከራችሁ በጣም ደፋሮች ናችሁ! ከዚህ በኋላም ወላይታ ላይ እንዲህ አይነት ነገር እንዳትሞክሩ!” የወላይታ ሶዶ ፖሊስ ማስፈራሪያ ለሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች
ምንሊክ ሳልሳዊ:- የጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው ሃይለማርያም ደሳለኝ ምንጭ ናት በምትባለው በወላይታ ሶዶ ከከፍተኛ ደረጃ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች እየተፈጸሙ መሆኑን ነዋሪዎች አጋለጡ::ነዋሪዎቹ እንዳሉት ካለምንም ምክንያት የሚያፍኑ የሚያስሩ የሚገርፉ እና ከፍትህ እና ፍርድ ቤት በላይ የሆኑ ትናንሽ ቡድናዊ መንግስታት እና እንዳሻቸው በህዝቡ ላይ የሚፈነጩ ካድሬዎች የወላይታን ህዝብ በስቃይ እና በሰቆቃ ውስጥ እያኖሩት መሆኑን ነዋሪዎቹ አማረው ተናግረዋል::
ባለፈው ሳምንታት ውስጥ እንኳን ከተያዙት የወላይታ ነዋሪዎች መካከል አቶ አየለ ሃሚሶ የሚባል የከተማውን የፍርድ ቤቶች ፕሬዚዳንት እና ዳኛ ደብድባችኋል ተብለው ካለምንም ማስረጃ 18 ሰዎች ተይዘው ላለፉት አስረ አምስት ቀናት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በጨለማ ቤት ታስረው ይገኛሉ::እነዚህ እስረኞች የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ሌሊሼ ኦላ እና ግብረበሮቹ ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመባቸው ሲሆን እንዲሁም ደብዳቢዎቹን ጭናችሁ አድርስቹሃል የተባሉ የባጃጅ ሹፌሮች በቁጥጥር ስር ውለው እየተገረፉ መሆኑን በስቃይ ላይ ያሉት እስረኞች ተናግረዋል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ በህጋዊ መንገድ የተመዘገበውን የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን በሽብርተኛነት እና ህገወጥ የጦር መሳሪያ ይዛቹሃል በማለት እንግልት እና መንግስታዊ ሽብር በከተማው የፖሊስ አዛዥ እና ግብረአበሮቻቸው የተፈጸመባቸው ሲሆን በሻንጣዎቻቸው ላይ ፍተሻ አድርገው ምንም የጦር መሳሪያ እንዳላገኙ እና “ወላይታ ለመግባት ምንም አይነት ፈቃድ ከማንም አንጠብቅም ምክንያቱም አገራችን ነው” በማለት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ቢመልሱም “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገር ድረስ መጥታችሁ ቅስቀሳ ለማካሄድ መሞከራችሁ በጣም ደፋሮች ናችሁ! ከዚህ በኋላም ወላይታ ላይ እንዲህ አይነት ነገር እንዳትሞክሩ!” የሚል ዛቻና ማስፈራሪያ
አድርሰውባቸዋል::
ዛሬ የካቲት 26 2006 “አሁን መሄድ ትችላላችሁ” ብለው ከአዲስ አበባ የሄዱትን ሶስቱን የሰማዊ ፓረቲ አመራሮች 1ኛ/ አቶ ጌታነህ ባልቻ 2ኛ/ አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ 3ኛ/ አቶ ይሁን አለሙ ሲለቁዋቸው ከሀዲያ ጀምረው የሰሯቸውን ስራዎች የያዙበትን ሰነዶች፤ቃለ ጉባኤዎች እና ሁለቱን የወላይታ ተወካዮችን /አስተባባሪዎችን/ እስካሁን ያለቀቋቸው ሲሆን ስለ ንበረታችሁ የምናውቀው ነገር የለም በማለታቸው ንብረቶቻቸውን ሳይረከቡ ወደ አርባምንጭ መንቀሳቀሳቸው ታውቋል::
የታሰሩት የሰማያዊ ፓረቲ የወላይታ አስተባሪዎች ባይፈቱም፤ የተወሰዱባቸው ንብረቶች ባይመለሱላቸወም ሰራው መቀጠል ሰላለበት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ወደ አርባ-ምንጭ ተንቀሳቅሰዋል፡፡
ነገ የአርባ ምንጭ ሰራቸውን እንዳጠናቀቁ ወደ ወላይታ ሶዶ ከትማ ተመልሰው የታሰሩትን የሶዶ ከተማ አስተባባሪዎችን ለማስፈታት ትግሉ የሚቀጥል ሲሆን ንበረታቸውንም የማስመለሰ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ትላንትና የካቲት 25 2006 በሶዶ ከትማ ላይ ያደረጉዋቸው ሰበሰባዎች https://www.facebook.com/blueparty.ethi … =notify_me ይህንን ይመሰል ነበር፡፡ምንሊክ ሳልሳዊ
ኢትዮጵያ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታን የማታቆም ከሆነ እናፈነዳቸዋለን
እስከዛሬ ብዙ ቀልዶችን ሰምቻለው አንደዚህ ግን ያዝናናኝ ቀልድ የለም አንድ የቀድሞ የግብጽ ጀነራል ኢትዮጵያ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታን የማታቆም ከሆነ እናፈነዳቸዋለን አሉ ለአንድ የቴሌቭዥን ጣቢያ በሰጡት ቃለ ምልልስ ኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ እንድታቆም ሶስት አማራጮች አሉ ብለዋል።
የቀድሞው የግብጽ ጀነራል በቀዳሚነት ያስቀመጡት አማራጭ በኢትዮጵያ ፣በሱዳን እና በግብጽ 20 ሚልዮን የሚደርስ የሙዝ እና የዛፍ ችግኝ በመትከል እና የዝናብ ሁኔታው እንዲስተካከል በማድረግ እና አማራጭ በመስጠት ኢትዮጵያ ግድቡን የምታቆምበትን መንገድ ማመቻቸት ነው ብለዋል።
ሁለተኛው አማራጭ የቀድሞ የግብጽ ንጉስ ሱልጣን አብዱል ሃሚድ የኢትዮጵያን አንድ ሶስተኛ መሬት ያስተዳድር ስለነበር ይህን መሬት አንዲሰጠን መጠየቅ ነው ያሉት የቀድሞ ጀነራል የዩጋንዳ አንድ ሶስተኛ መሬትም የግብጽ ንብረት እንደሆነ ተናግረዋል።
ይህንንም ለማድረግ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ እንደተዘጋጁ ነው የሚናገሩት። ሁለቱ አማራጮች የማይሰሩ ከሆነ ግን « በመሬታችን መሞት የለበንም መሞት ካለብንም ግድባቸው ስር ነው መሞት ያለብን ስለዚህ እዛው ሄደን ልንፈነዳቸው ይገባል በመሆኑም ኢትዮጵያ ከሶስቱ አማራጮች አንዱን መምረጥ አለባት» ብለዋል።
እንኳንስ ለሙቅ ለገንፎም አልደነግጥ አለ የሃገሬ ሰው!! አፈነዳለሁ በሎ ፈነድቶ የአሞራ እራት መሆን እንዳለ አያውቁም እንዴ ጀነራል? ቂቂቂ ቂቂቂ ቂቂቂ ቂቂቂ በነገራችን ላይ ጀነራል ሶስቱም የኛ ምርጫ አይደሉም የኛምርጫ ወንዛችንን መገደብ ነው…እኔ የሚገርመኝ ኧረ ግብፅ በጣም አበዛችው
አንድ ሰሞን ክቡር ጠ/ሚር መለስ ዜናዊ እንዲህ ሲሉ ሰምቼ ነበር ” ለሚያስፈራራክ ሰው መፍትሄው አለመፍራት ነው ” ሳስበው ሳስበው ይህ ሰው ጅል እንጂ ጄነራል አይደለም!! ቂቂቂ ቂቂቂ ደስ የሚለው ነገር ጅነራሉም ሆኑ አንዋር ሳዳት አንድ አይነት እምነት አላቸው እዚያው ሄደን እንሙት !! እኛ መግደል መገዳደል ሰልችቶናል ሁላችንም በህይወት እንኑር ነው አቋማችን እግድህ የኛ መሬት ለባዐዳን መቀበርያ ይመች ይመስል የአሁኑ ትውልድም እንደ ድርቡሽ እዚያው እንሙት ቢያንስ እንደ ጣልያኖቹ የገዳዮችና የሟቾች ሃውልት በኢትዮጵያ ምድር ይኑረን አጥንታችን በኢትዮጵያ መሬት ካልተቀበረ የሞትን አይመስለንም ካሉ ባንወደውም ባንፈልገውም ሙትን ለመቅበር ከሟቹ ይልቅ ጉልበትና አቅም ይጠይቃልና ለዚያው መዘጋጀት ነው አንድም ሞት የናፈቃቸው ግብጻውያንን እዚየው ጣሕሪር አደባባይ ላይ ሞታቸው እንድከናወን መጸለይ ነው ካልሆን ግን ምን ይደረግ ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደር ? ይስሙኝ እማ ጀኔራል በአባይ የመጣ እንኳን የኢትዮዻያ ወጣት እማማ አያቴ ትዘምታለች.ቂቂቂ እንዳዉም አረፈዳችሁ ቂቂቂቂቂቂ ቂቂቂ
ጀነራል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ”ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው። ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥” ይላል እግዚአብሔር።
ትንቢተ ኢሳይያስ 19;1-10 ላይ
ስለ ግብጽ የተነገረ ሸክም። እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና እይበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጽም ጣዖታት በፊቱ ይርዳሉ፥ የግብጽም ልብ በውስጥዋ ይቀልጣል።
2፤ ግብጻውያንን በግብጻውያን ላይ አስነሣለሁ፤ ወንድምም ወንድሙን፥ ሰውም ባልንጀራውን፥ ከተማም ከተማን፥ መንግሥትም መንግሥትን ይወጋል።
3፤ የግብጽም መንፈስ በውስጥዋ ባዶ ይሆናል፥ ምክራቸውንም አጠፋለሁ፤ እነርሱም ጣዖቶቻቸውን በድግምት የሚጠነቍሉትንም መናፍስት ጠሪዎቻቸውንም ጠንቋዮቻቸውንም ይጠይቃሉ።
4፤ ግብጻውያንንም በጨካኝ ጌታ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ ጨካኝ ንጉሥም ይገዛቸዋል ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
5፤ ውኆችም ከባሕር ይደርቃሉ፥ ወንዙም ያንሳል ደረቅም ይሆናል።
6፤ ወንዞቹም ይገማሉ፥ የግብጽም መስኖች ያንሳሉ ይደርቃሉም፤ ደንገልና ቄጤማ ይጠወልጋሉ።
7፤ በዓባይ ወንዝ ዳር ያለው መስክ በዓባይም ወንዝ አጠገብ የተዘራ እርሻ ሁሉ ይደርቃል፥ ይበተንማል፥ አይገኝምም።
8፤ ዓሣ አጥማጆቹ ያዝናሉ፥ በዓባይም ወንዝ መቃጥን የሚጥሉት ሁሉ ያለቅሳሉ፥ በውኆችም ላይ መረብ የሚዘረጉት ይዝላሉ።
9፤ የተበጠረውንም የተልባ እግር የሚሠሩ፥ ነጩንም ልብስ የሚሠሩ ሸማኔዎች ያፍራሉ።
10፤ ደገፋዎችዋም ሁሉ ይሰባበራሉ፥ የደመወዘኞችም ነፍስ ትተክዛለች።
ይስሙኝ እማ ጀኔራል በነገራችን ላይ ይኼን ግድብ ማፈንዳት አይደለም መገላመጥ በነፍስ ያወራርዳል፡፡ግድቡ የኢህአዴግ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፡፡ ኢጣሊያንን ያየ በእሳት አይጫወትም” አለች እማማ አያቴ . ቂቂቂ ቂቂቂ ቂቂቂ አይ አቅምን አለማወቅ ያሳዝናል የጦር መሳሪያ እስከ አፍንጫ መታጠቅ እንዲህ የሚያስፈነጭ መስሏቸው ከሆነ ከጣሊያን ይማሩ፡፡ጦርነት ሚጠይቀው ወኔና አላማ ነው ፡፡እንኳን ለግድባችን ….ይሞታል፡፡ታሪክ ጠይቁ የማን ልጆች እንደሆንን የሚኒልክ እና የቴድሮሥ አንፈራም ነገርዬው ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ አይነት ነው ግድቡ ስር ለመሞት መጀመሪያ መድረስ ይጠይቃል፤ ማፈንዳቱ ሳይሻላችሁ አይቀርም? ግን ልታፈነዱ ስትመጡ ልትፈነዱ አንደምችሉ አስባችሁ ግቡ! አገሪቱ ኢትዮጵያ, ህዝቡ ደግሞ የአድዋ ባለ ታሪክ ጀግና አንደሆነ ለአፍታም አንዳትዘነጉ! ቀልደኞች ቂቂቂ!! ጋሸ ጀነራሉ ወግ ከወግነቱ አልፎ አያውቅም ሞያ በልብ ነው ካወራህ ይበቃህል ኢትዮጵያና ህዝቦችዋ ለጠላት የተንበረከኩበት ዘመን የለም የታሪክ አሻራውን ማየት ከፈለክ ሜዳውም ፈረሱም ይህው። ጋሸ ጀነራሉ እንደዚህ አይነት ቀልድ ግብፅም ጀመረች እኛ ማን እንደሆን አታቅም እንዴ? ካላወቀች ጣሊያንን ትጠይቅ! ጀግኖቹ ኢትዮዽያኖችነን!!! ከእሳት እንዴት ችላ ትጠጋለች!! እኛ እኮ ለሚጠሉን እሳት ነን ለሚወዱን ደግሞ ዉሀ ነን.. እ!
ስሙኝማ በነገራችን ላይ አረብ ሲባል የሻገተና የአስተሳሰብ ደኃ ነው፡፡ እንደልማዳችሁ እናፈነዳለን ብልችሁ ስትነሱ እራሳችሁ ላይ አፈንድታችሁ ታልቃላችሁ፡፡ አሁን የጨዋታው ህግ ተቀይሯል፤ እንኳንስ የኃይል እጥረት እያለብን ይቅርና ቢተረፈረፈንም ግድቡ አይቆምም ፡፡ ደግሞ እንዳይገርማችሁ ፤ ይህ ከአራቱ ግዶቦች የመጀመሪያው ነው 3ቱ በቅርብ ጊዜ በቅደም ተከተል ግንባታ ይጀመራል፡፡ ስለሆነም ውኃችን ነዳጃችን ነው ፡፡ ነዳጂ በነፃ አለ እንዴ??? በነገራችን ላይ ጀኔራል ሙዝ እና ችግኙም አሪፍ ሀሳብ ነው። ከግድቡ በኃላ ወደዛም እንዘምታለን ቂቂቂ ቂቂቂ በነገራችን ላይ ጀኔራል ይልቁንም ለብዙ ሺህ አመታት ያለከልካይ የአባይን ውሃ ተጠቅመዋል ስለዚህ ለኢትዮጵያ በርካታ በሊዮን ዶላር ሊከፍሉ ይገባቸዋል!!!!
አሁን ነው መበቀል አረብን እስካሁን በትንሽ ሳንቲም የአበሻን ጉልበት የበዘበዙበት ሳያሳቸው በዚም መጡ ይሄ ግድብ ክብራችንን ከፍ የሚደርግልን ነው በዛውም ልክ ግድቡ ላይ ጥቃት ደርሶ ማለባበስ በቁም እንደመሞት ነው ለአገራችን ክብር መንግስት ራሱን ሊዘጋጅበት እና በማንኛውም እንቅስቃሴ አፀፋዊ መልስ ሊሰጥ ይገባል የስካሁኑ ውርደት በአረቦች ይብቃ ካለበለዚያ ሀገርንም በማስደፈር እስካሁን ከነበሩት መንግስት ቀዳሚው የትውልድ ተወቃሽ መሆኑ ማይቀር ነው እናም መንግስት በሁሉም ነገር አፀፋዊ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆን ይገባል፡
ስሙኝማ ነገርዬው ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ አይነት ነው፡፡ ግብፆች ከድርድር ውጪ የጦርነት አማራጭ ያላቸው አይመስለኝም፡፡ የተያያዙት ተራ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ነው፡፡ ያው ማስፈራራት ነው፡፡ ቢሆንም በደካማ ጎናችን አይጠቀሙም ማለት አይታሰብም፡፡ የግብፅ ግብረሰናይ ድርጅቶችም ሆኑ ማናቸውም የግብፅ መሰረት ያላቸው የኢንቨስትመን ስራዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ካልተደረገ ሊጎዱን ይችላል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ብቻ ሊሰራ የሚችል ወታደራዊም ሲቪል ደህንነት ተቋም ሊመሰረት ይገባል፡፡ መስራት ከባድ ነው፡፡ ማፍረስ ቀላል ነው፡፡ የቁማር ጨዋታው ውጤት ግልጽ ስላይደለ መዘጋጀቱ አይከፋም፡፡ በድንበር አካባቢ ያለንን የፀጥታ አጠባበቅ ማጥበቅም ግድ ይለናል፡፡
ግድቡ ተዓምር ባያመጣልን እንኳ ግብፅ ለዘመናት ያፈራረሰችንን ማካካሻ ስለሚሆን ለእኔ ልዩ ትርጉም አለው፡፡ ለብዙ ላልተገለፁ ነገሮችም መሰረት ይሆናል፡፡ አይደለም 6ሺ 200 ሜጋ ዋትም ካመነጨ በድል አድራጊነት እንዳጠናቀቅን እቆጥራለሁ፡፡የግብፅን የውስጥ መተራመስ ፈጣሪ ለኛ ብሎ ያደረገው እንደሆነስ ማን ያውቃል! ባይሆን ኖሮ የሚተኙልን አይመስለኝም፡፡ በዚህ ምስቅልቅል ጊዜ ይህን ያህል ከተንፈራገጡ ደህና ቢሆኑ ውጤቱን ገምቱ…መንግስትም ለማናቻውም ማስፈራራት ተመጣጣኝ ምላሽ መስጠት ይኖርበታል፡፡ ግድ ነው፡፡
ይስሙኝ እማ ጀኔራል በትምቢቱ ኢሳያስ መዝ67:31 ኢትዮጵያ ላይ ጦርን እንዳታነሱ ትደቃላችሁ ብሏል።በደንብ ይወቁን ይምጡ ሙዝ እንዳሉ የርሳስ ሙዝ በልተው ይሄዳሉ።
ቂቂቂ ቂቂቂ
ህዝብ ሆይ ስማ እንደወርቅ የነጠረ እንደ ብር የነጣ ሀበሻዊ ማንነትህ በሙዝ ተቀይራል እና መሳሪያም ያለህ መሳሪያ ጀገሪያም ያለህ ጀገሪያ አንካሴም ያለህ አንካሴ እነኚህ የሌላችሁ ወኔአችሁን ይዛችሁ ወደ አባይ ውጡ ይህን ማድረግ ያልቻለ ሀበሻ ቢኖር እንጣላለን ማርያምን!!!!!!!
አሁንስ ትግስቴ እያለቀ ነዉ ያአባቴን ak-47 መሳሪያ ይዤ ልሸልል ነዉ ያበጠ ይፈንዳ ምነዉ ሸዋ
አረ ጎራው አረ ጎራው ንቡ ወለደና ቀፎውን ጨነቀው፣
ማር ብቻ መስሎታል መርዙን አላወቀው፣
የማን ዘር ነኝና ከማስ ተወልጄ
ሚኒልክ ያወረሰኝ ዛሬም አለ በጀ።
ዘራፍ ዘራፍ የማንን ሀገር ማን ይነካታል፣
ካለ ሀበሻ ያስከብራታል።
የማን ቤት ጠፍቶ የማን ሊበጅ፣
የአውሬ መውለጃ ይሆናል እንጂ።
ዘራፍ ዘራፍ!!! ዘራፍ!!! ዘራፈ!!
የምኒሊክ ልጅ ነኝ የበላይ የዛ ሳተና
ለጣልያንም ያልተኛ ቆራጡ ጀግና እኔነኝ ያለ ይሞክረኛ !!! ዘራፍ ዘራፍ!!!ተተተተተተተተተ ”ኢትዮጵያ ታበፅእ እደዊሀ ሀበ እግዚአብሄር
እንግዲ እነሱ በሚፈልጉት አማራጭ መሄድ ይችላሉ መብታቸው ነው። እኛ ኢትዮጵያዊያን ያለን አንድ እና አንድ ነው ያለን ያም የኃያላን ኃያል የነገስታት ንጉስ በረዶ የሚያዘንብ ፈርኦንን ከነሰራዊቱ በባህር የጣለ ድንቅ መካር እና ኃያል አምላክ ነው እሱም እጃችንን ዘርግተን ለምነን ከኛ ጋር ነው ስለዚህ ቀድመን አሸንፈናቸዋል
እኛስ እንሙት ችግር ብርቃችን አይደለምና መጪው ትውልድ ግን እኛ ያየነዉን ችግር እኛ ያለፍንበትን የድህነት ህይወት መቅመስ የለበትም ብሔር ሀይማኖት ሳይለየን ሁላችንም በአንድነት ለመጪው ትውልዳችን መስዋት ከፍለን ማለፍ አለብን ስም አይሞትም ታሪክም አይሞትም::እነሱ ያውሩ እኛ እንሰራለን ©2014 ነቆራ እና ሌሎችም ወጎች ከ Love on The way
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ማርች 05, 2014
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
ቢራና ቦርጭ፣
በዓለም ዙሪያ በሃይማኖትና በባህል ሳቢያ ቢራና ሌሎችም የአልኮል መጠጦች ከማይቀመሱባቸው ጥቂት አገሮች በስተቀር ፤ በአብዛኞቹ ፣ እንበል ፣ እዚህ ላይ በተለይ ቢራ፣ በቤት ፣ በባህላዊ ዘዴ ከሚጠመቀው አንስቶ ፣ በዘመናዊ ፋብሪካዎች፣ በገፍ ነው
የደቡብ ሱዳን ድርድር መቋረጥ
በደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች መካከል የሚካሄደዉ የሰላም ድርድር ለጊዜዉ መቋረጡ ተገለጸ።
ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ – አንድነት
የአሜሪካ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት እ.ኤ.አ በ2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ ተፈፀሙ ያላቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሪፖርት ተመልክተነዋል፡፡ በሪፖርቱ የተካተቱት የመብት ጥሰቶች አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ በተደጋጋሚ ያጋለጣቸው እና ከፍተኛ ትግል እያደረግንባቸው የሚገኙ አስከፊ ተግባራት እንደሆኑ ቢታወቅም የቆምንለት ዓላማ እና እየታገልነው ያለው ስርዓት በሌሎች ዘንድም ድርጊቱ የታወቀ መሆኑን ያረጋገጥንበት ነው፡፡ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ በሪፖርቱ […]
የፀረ-ሽብር፣ የፕሬስና የሲቪል ማኅበረሰብ ሕጎቹ ማወዛገባቸውን ቀጥለዋል -ዘሪሁን ሙሉጌታ
“መፈክር በተሰማ ቁጥር መፈክሩን ተከትለን አንነጉድም” አቶ ጌታቸው ረዳ የጠቅላይ ሚኒሰትሩ ቃል አቀባይ የ2013 የስቴት ዲፓርትመንት ሪፖርት መውጣትን ተከትሎ ባለፉት አምስት ዓመታት ሲያወዛግቡ የነበሩት የፀረ-ሽብር፣ የመገናኛ ብዙሃን እና የበጎ አድራጎትና ማኅበራት (የሲቪል ማኅበረሰብ) ሕጎች ማወዛገባቸውን ቀጥለዋል። የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መ/ቤት (ስቴት ዲፓርትመንት) በየዓመቱ በሚያወጣው ሪፖርት ላይ በሕጎቹ የሀገሪቱን ሕዝቦች ስብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ላይ ጫና እንደሚያደርጉ […]
ፓትርያርኩ የቤተ ክርስቲያኒቷን አስተዳደር የማሻሻል አቋሜ ‹‹አልተበረዘም፤ አልተከለሰም›› አሉ
‹‹የፀረ ሙስና አቋማቸው ራሳቸውን ከማስተዋወቅ ያለፈ ውጤት አላመጣም›› /ተቺዎች/ (ሰንደቅ፤ የካቲት ፳፮ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፍትሕ፣ ርትዕና እኩልነት የሞላባት፣ መልካም አስተዳደር የሰፈነባት ለማድረግ በዕለተ ሢመተ ፕትርክናቸው የተናገሩት ቃል ኹሉ እንደጸና መኾኑንና ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ከምእመናን ጋር በመኾን እንደሚያጠናክሩት ፓትርያርኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ተናገሩ፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱ ስድስተኛ …![]()
ነገረ ኢትዮጵያን 2ኛ ዕትም በ PDF

ስለ ወቅቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውህደትና ትብብር በስፋት አትታለች
አድዋን ዘክራለች!
ለሱዳን ተላልፎ ሊሰጥ በታሰበው መሬት ህጋዊና ፖለቲካዊ ትንታኔዎች ተሰጥቶባታል
ኢትዮጵያ ለምን ወደ ኋላ እንደቀረች ተተንትኖባታል
ስለ አገራችን የምርጫ ፖለቲካና ሌሎች አገራዊ ጉዳዮችም አካትታለች
Neger Ethiopia Issue 2 In PDF
‹‹በጠቅላይ ሚኒስትሩ የትውልድ አገር ተቃውሞ ማድረግ አይታሰብም›› የወላይታ ሶዶ ፖሊስ ጣቢያ

በመስክ ጉብኝት፣ አደረጃጀቶቻቸውን በማጠናከር ላይ የነበሩት ከአዲስ አበባ የሄዱት የሰማያዊ ፓርቲ ልዑካን ከአንድ ቀን እስር በኋላ ዛሬ ጠዋት ቢፈቱም የወላይታ ዞን የፓርቲው ተወካዮች ግን አሁንም ድረስ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ የተፈቱት የፓርቲው አመራሮችም ቢሆን ቀጣይ መዳረሻቸው ወደሆነችው አርባ ምንጭ እንዳይንቀሳቀሱ ከመከልከላቸውም በተጨማሪ የስራ ሰነዶቻቸውን ጨምሮ ሌሎች ቁሳቁሶቻቸው በፖሊስ ቁጥጥር ስር በመሆናቸው ከመንቀሳቀስ እንዳገዳቸው በእስር ላይ የነበሩትና የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ብርሃኑ ተክለያሬድ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ ከወላይታ ሶዶ ወደ አርባ ምንጭ በማቅናት ላይ እያለ የከተማው ፖሊስ ‹‹በመሳሪያ ዝውውርና በሽብርተኝነት ጠርጥረናችኋል›› በሚል ከህዝብ ማመላለሻ መኪና አስወርዶ እንዳሰራቸው ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ ከታሰሩ በኋላ እንግልት የደረሰባቸው ሲሆን ‹‹ከምሽቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት የፖሊስ አዛዦች ስራ ላይ ነን በሚል ባዶ ሜዳ ላይ ዝናብ ሲያስመቱን አምሽተዋል›› ብለዋል፡፡ በትናንትናው እለት ምግብና ጠያቂ መከልከላቸውን ነገረ ኢትዮጵያ መዘገቧ ይታወቃል፡፡
አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ የወላይታ ሶዶ ፖሊስ ለእስሩ እንደምክንያት ካነሳቸው ነገሮች መካከል ‹‹በጠቅላይ ሚኒስትሩ የትውልድ አገር ተቃውሞ የማይታሰብ ነው›› የሚል እንደሚገኝበት ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል፡፡ ለከተማው ፖሊስ ጣቢያ ማንነታችን ገልጸን ጉዳዩን ለማጣራት ያደረግነው ጥረት በአግባቡ ሊያነጋግሩን ባለመቻላቸው ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ የወላይታ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ለሊሼ ኦንን በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ማግኘት ብንችልም ጋዜጠኞች መሆናችንን ሲያውቁ ስብሰባ ውስጥ መሆናቸውን በመግለጽ መረጃ እንደማይሰጡን ገልጸውልናል፡፡ ይሁንና ለኢንስፔክተሩ በምንደውልበት ወቅት ኃላፊው ስብሰባ ላይ አለመሆናቸውንና በአቅራቢያቸው እንደሚገኙ የልዑካን ቡድኑ ገልጸውልናል፡፡
አድዋ ለኔ አንዱ ዓለም ተፈራ
እኔ የምኖረው በአሜሪካ ነው። በአሜሪካ ሆኜ የአድዋን በዓል አከበርኩ። የኢትዮጵያዊያን ድረገፆችን እየተመላለስኩ ቃኘኋቸው። ሬዲዮኖችን አዳመጥኳቸው። የስልከ ልውውጦችንና የእንግዶችን ሃሳቦች ተከታተልኩ። ስደሰት፣ ሳዝን፣ በጣም ስደሰትና በጣም ሳዝን ዋልኩ። ሲመሽና የምኝታ ሰዓቴ ቀርቦ ባልጋዬ ላይ ስጋደም፤ እንቅልፍ ቶሎ አልወስድህ አለኝ። መገለባበጡ ለውጥ አላመጣ ሲል በሃሳብ መዋተቱን ተያያዝኩት። አድዋ ለኔ ምንድን ነው? የሚለው ጥያቄ ከዕለቱ ወደላይና ወደታች መዋዠቅ […]
ኢህአዴግ የአንድነት ፓርቲ ኃይሎች በአደረጃጀቴ ሰርገው ገብተዋል በሚል ግምገማ ሊጀምር ነው
ኢህአዴግ የአንድነት ፓርቲ ኃይሎች በአደረጃጀቴ ሰርገው ገብተተዋል በሚል ግምገማ ለጀምር መሆኑ ታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ጽ/ቤት የአንድ-ለ-አምስት የአደረጃጀት አመራሮች በተለያዩ ክፍለ ከተማዎች የሚገኙ የአንድ-ለ-አምስት የአደረጃጀት አመራሮችን በመሰብሰብ “አንድነት ፓርቲ የአንድ-ለ-አምስት አደረጃጀታችን ውስጥ አስርጎ ያስገባቸው ኃይሎች በጊዜ በግምገማ ካልተራገፉ ቀጣዩ ምርጫ ከቁጥጥር ውጪ እንደማይሆን ማንም እርግጠኛ መሆን አይችልም፡፡” ማለታቸውን በስብሰባው ላይ የተሳተፉ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ተናግረዋል፡፡
ምንጮቹ ጨምረው እንደተናገሩት ኢህአዴግ የአንድ-ለ-አምስት አደረጃጀቱን የሚያስተባብሩ ከፍተኛ ካድሬዎችን አንድ-ለ-ሰላሳ ማደራጀት መጀመሩን ተከትሎ አንድነት ፓርቲ አስርጎ ያስገባቸው ኃይሎች አሉ በመባሉ ካድሬዎች እርስ በእርስ መሰላለል እና አለመተማመን ጀምረዋል፡፡ ይህ በካድሬዎቻቸው መካከል የተጠፈጠረው ትርምስ ያሰጋቸው የኢህአዴግ የአዲስ አበባ ጽ/ቤት አመራሮች ለክፍለ ከተማ አመራሮቻቸው አንድነት ሊይዝብን የሚችለው 30 በመቶ የሚሆነውን ህዝብ ነው የተቀረውን በኮንዶሚኒየም ፣ በአነስተኛ ጥቃቅንና በየአንድ-ለ-አምስት አደረጃጀት ይዘነዋል ብለዋቸዋል፡፡ ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ መረጃ የሰጡት የስብሰባው ተሳታፊዎች 750ሺ የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢ፣ 30ሺ የኮንዶሚኒየም እጣ ተጠባባቂዎች ኢህአዴግን ነው የሚመርጡት በሚል ከመድረክ የቀረበው መደምደሚያ እንዳላሳመናቸውም ተናግረዋል፡፡
ጉዳዩን በሚመለከት ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ከአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የደረሰው ዶክሜንት እንደሚያስረዳው ፓርቲው የአዲስ አበባ አደረጃጀቱን ኢህአዴግ በዘረጋው ልክ 138 ያደረሰ ሲሆን በአሁኑ ጊዜም የወረዳ ደረጃና የሴል አደረጃጀቶቹን በኢህአዴግ የአደረጃጀት ቁጥር ልክ የማድረግ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ያመለክታል፡፡
በብኣዴን ካድሬዎች መካከል የተነሳው ፍጥጫ የሕወሓት አመራሮች በሃይል ሊፈቱት ይችላሉ የሚል ስጋት ጨምሯል። ሕወሓት በአማራው ክልል አዲስ የፓርቲ አደረጃጀት ጥርነፋ ሊደርግ ነው።
በብኣዴን ካድሬዎች መካከል የተነሳው ፍጥጫ የሕወሓት አመራሮች በሃይል ሊፈቱት ይችላሉ የሚል ስጋት ጨምሯል።
ሕወሓት በአማራው ክልል አዲስ የፓርቲ አደረጃጀት ጥርነፋ ሊደርግ ነው።
ምንሊክ ሳልሳዊ ፤ የብኣዴን ካድሬዎች ድርጅታቸውን እና አመራራቸው ላይ የሚታየውን ጉዳይ በተመለከተ የፖለቲካ ጥያቄዎች ማንሳታቸውን ተከትሎ ከሕወሓት አሽከር ከሆኑት ጋር በስብሰባ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት ስብሰባው እንደተበተነ ታውቋል:: በሕወሓት እና በብኣዴን መካከል ልዩነቶች የሚፈጥሩ ሁኔታዎች ተከስተው አሁንም በስፋት ቀጥለው ይገኛሉ::የተለያዩ ነባር የብኣዴን ካድረዎችን በሰብብ አስባብ የሚያንጠባጥበው ሕወሓት አሁንም አሽከሮቹን አሰማርቶ በድርጅታቸው ውስጥ ለውጥ እንዲደረግ እና የሕወሓት ደባልነትና ፖለቲካ ጥገኝነት እንዲያበቃ የጠየቁትን ወደ ገደል ለመግፋት አየተሯሯጠ ነው::
ባለፉት ሳምንታት በባህር ዳር እና በአዲስ አበባ የተጠሩ ስብሰባዎች በሕወሓት አሽከሮች እና በለውጥ ጠያቂዎች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ስብሰባው ሲበተን …ለሁለተኛ ጊዜ የተጠራው ስብሰባ በከፊል ካድሬዎቹ ስላልመጡ ለሚመጣው ሳምንት የተላለፈ መሆኑን ታውቋል::በሕወሓት አሽከሮች እና በብኣዴን ለውጥ ፈላጊ ካድሬዎች መካከል የተነሳው ፍጥጫ የሕወሓት አመራሮች በሃይል ሊፈቱት ይችላሉ የሚል ስጋት ጨምሯል::
አዲስ በወጣው እቅድ መሰረት በአማራው ክልል በድጋሚ አዲስ የፓርቲ አደረጃጀት ጥርነፋ እንደሚደርግ እና በዚህ መካከል አስቸጋሪ እና አድመኞች የጸረ ሰላም እና የጸረ ሕዝብ ሃይሎችን የመደምሰስ እንዲሁም በአዲሱ የፓርቲ አደረጃጀት ውስጥ አስፈላጊው ጥቅማጥቅሞችን ለአዳዲስ አባላት መስጠት የሚል ይገኝበታል::ውስጥ ውስጡን እየቀሰቀሱ ችግር በፓርቲው ላይ የሚፈጥሩ ካድሬዎችን በማስወገድ በአዳዲስ ለመተካት ታቅዷል::
የሰማያዊ ፓርቲ የመስክ ጉብኝት የመንግስታዊ ሽብር አሜኬላዎች እየገጠሙት ነው::

ምንሊክ ሳልሳዊ ፦ ሰማያዊ ፓርቲ የጀመረውን ሰላማዊ ትግለ ለማጎልበትና የፓረቲውን መዋቅር የስራ እንቅሰቃሴ ለመገምገምና ለማጠናከር እነዲሁም መዋቅሩ ያለበትን ችግር መፍትሄ ለመስጠት ታስቦ የተዘጋጀ የመስክ ጉብኝት እንዲያደርጉ በሶስት ቡድን የተከፈለ ልኡካን በሃገሪቱ ማሰማራቱ ይታወቃል:: እነዚህ የልኡካን ቡድን አባላት የመስክ ጉበኝት በአጠቃላይ በ14 ዞኖችን የሚያካትት ሲሆን ወደ 200 የሚጠጉ ወረዳዎች ላይ ያሉ የሰማያዊን የፓርቲ እንቅስቃሴ ከሚመሩ አስተባባሪዎች ጋር ውይይት እያደረጉ በተግባራዊ ስራ ላይ ይገኛሉ::
በዚህም መሰረት በሚከተለው የመስክ ጉብኝት ምደባ መሰረት በሃገሪት የተለያዩ መስመሮች የተጓዙ የሰማያዊ ፓርቲ የመስክ ጉብኝት የሚያደርጉ አመራሮች …
ጉዞ መስመር አንድ ፡- ደ/ብርሀን ፤ ሸዋሮቢት ፤ ደሴ ፤ ወልዲያ
1. አቶ ስለሺ ፈይሳ – ም/ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ
2. አቶ ዮናታን ተሰፋዬ – የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ
3. አቶ ሔኖክ መለሰ – በአደረጃጀት ጉዳይ የጥናትና የትግል ስልት ስልጠና ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ
ሸዋ ሮቢት ጨምሮ በደሴ መስመር ላይ ያሉ የሰሜን ሸዋ የፓርቲው የዞን/የቀጠና አመራሮችን በማወያየት ጉዞውን ወደ ወልዲያ እና ደሴ ያቀና ሲሆን ……
ጉዞ መስመር ሁለት – ደብረማርቆስ ፤ ባህርዳር ፤ ወረታ ፤ ጎንደር
1. አቶ በቃሉ አዳነ – አደረጃጀት ጉዳይ ም/ኃላፊ
2. አቶ ይድነቃቸው ከበደ – የህግ ጉዳይ ኃላፊ
3. ወ/ሮ ሃና ዋለልኝ የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ የያዘ የጉዞ መስመር 2 ልዑክ ቡድን የካቲት 24 እና 25 ቀን 2006 ዓ.ም ከምስራቅ ጎጃም የዞን አስተባባሪዎች ጋር በደብር ማርቆስ ከተማ ውይይት አካሄደ፡፡
በምስራቅ ጎጃም ዞን 18 (አስራ ስምንት) ወረዳዎች የሚገኝ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ በ10 (አስሩ) ወረዳዎች ማለትም፡-
1ኛ. አነደድ 2ኛ. ደ/ማርቆስ ከተማ ወረዳ 3ኛ. ጎዛአምን 4ኛ. ማቻከል 5ኛ. ደብረ ኤሊያስ 6ኛ.ባሶ ሊበን
7ኛ. እናርጅ እናውጋ 8ኛ. ጎንቻ ሲሶእነሴ 9ኛ. እነብሴ ሳርምድርጉዞ መስመር ሁለት – ደብረማርቆስ ፤ ባህርዳር ፤ ወረታ ፤ ጎንደር/መርጦ ለማርያም 10ኛ. ሁለት እጁ እነሴ
ከላይ በተገለፁት ወረዳዎች የሰማያዊ ፓርቲ መዋቅር ተዘርግቶ ስራዎች እየተሩ ሲሆን ወደቦታው ያቀናው የልዑክ ቡድን እነዚህን ወረዳዎች ከሚያስተባብረው የዞን አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
በቀጣይ ቀናት በባህር ዳር፣ ወረታ (ደቡብ ጐንደር) እና ጐንደር በተመሳሳይ ሁኔታ የሰሜን ኢትዮጵያ ልዕካን ቡድን የሚንቀሳቀስባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡
ጉዞ መስመር ሶስት – ሆሳዕና ፤ ሶዶ ፤ አርባ ምንጭ ፤ ባድዋቾ ፤ አዋሳ
1. አቶ ጌታነህ ባልቻ – የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ
2. አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ – የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
3. አቶ ይሁን ዓለሙ – የአደረጃጀት ጉዳይ የክትትልና ግምገማ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ የያዘው የመስክ ጉብኝት ቡድን ሶዶ ላይ ካለው መዋቅር ጋር አሰፈለጊውን ስብሰባና ግምገማ ካካሄዱ ቦሀላ ወደ ቀጣይ ከተማ ወደሆነችው አርባ ምንጭ ጉዞ ሲጀምሩ በሰዶ ፖሊሶች ተይዘው በአሁኑ ሰአት በእስር ላይ ይገኛሉ::
ከማንኛውም ሰው ጋር እንዳይገናኙ እና ምግብ እንዳይትገባላቸው የተደረጉት የመስክ ጉብኝት ቡድን ሶስት አባላት የመንግስታዊ ሽብር አሜኬላዎች የሆኑ ያልተማሩ ካድረዎች በበላይ ትእዛዝ በሚል ህገመንግስቱን በረገጠ መልኩ ሰላማዊ ትግልን መርጦ በመንግስት ተመዝግቦ በሚገኝ ፓርቲ እና አመራሮች ላይ የእስር እርምጃ መውሰዳቸው የዲሞክራሲ እሾዎች ማበባቸውን ያመለክታል:: ምንሊክ ሳልሳዊ
አስተያየት በሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ “እኛና አብዮቱ” ላይ ፈቃደ ሸዋቀና
የሻምበል ፍቅረ ስላሴን ባለ 440 ገጽ መጽሐፍ ላነብ ስነሳ ጸሐፊው በሃያ ዓመታት የእስር ቤት ቆይታቸው በስልጣንና የሃላፊነት ዘመናቸው የነበሩትን ብዙ ክንዋኔዎች ፣ ውሳኔዎችና ተዋናዮችን አስመልክቶ የነበራቸውን እይታ እንደገና ለማጤንና ለማሰላሰል እድል አግኝተው የጻፉት ሊሆን ስለሚችል ሚዛናዊ የሆነ ዕውቀት፤ እንዲሁም የመንግስታቸውን የውስጥ ለውስጥ ሥራዎች ከሩቅ እናይ የነበርን ተራ ዜጎች ሳናውቃቸው የቀሩ ነግሮችን የምናገኝበት ይሆናል የሚል ጉጉት […]
የሙዚቃ ቃና ቅንብር – ማርች 05, 2014
ዘወትር ቅዳሜ ማታ ከደሳለኝ መኮንን ጋር፣ምርጥና አዳዲስ የካንትሪ ማለትም የአሜሪካ አገር ሰብእ፣ የሮክ፣ተሶል፣የፖፕ፣የአር-ኤን-ቢ፣ብሉዝ፣የሬጌና የሂፕ-ሃፕ ዜማዎችን እንዲያደምጡ ተጋብዘዋል።
ፍኖት – ኢህአዴግ የአንድነት ፓርቲ ኃይሎች በአደረጃጀቴ ሰርገው ገብተተዋል በሚል ግምገማ ለጀምር መሆኑ ታወቀ
ኢህአዴግ የአንድነት ፓርቲ ኃይሎች በአደረጃጀቴ ሰርገው ገብተተዋል በሚል ግምገማ ለጀምር መሆኑ ታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ጽ/ቤት የአንድ-ለ-አምስት የአደረጃጀት አመራሮች በተለያዩ ክፍለ ከተማዎች የሚገኙ የአንድ-ለ-አምስት የአደረጃጀት አመራሮችን በመሰብሰብ “አንድነት ፓርቲ የአንድ-ለ-አምስት አደረጃጀታችን ውስጥ አስርጎ ያስገባቸው ኃይሎች በጊዜ በግምገማ ካልተራገፉ ቀጣዩ ምርጫ ከቁጥጥር ውጪ እንደማይሆን ማንም እርግጠኛ መሆን አይችልም፡፡” ማለታቸውን በስብሰባው ላይ የተሳተፉ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ተናግረዋል፡፡ […]
የህወሓት ታጋዮች ቅሬታቸው ገለፁ – አብርሃ ደስታ
ባሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል የዉኃና አፈር ጥበቃ (Water and Soil Conservation, ማይን ሓመድን ዕቀባ) ተግባራት የሚከናወኑበት ግዜ ነው። ህዝብ ስራው ትቶ ተገዶ በፕሮግራሙ ይሳተፋል። ለፖለቲካ ሲባል ህዝብ በፍላጎቱ ተሳተፈ ተብሎ ሪፖርት ይቀርባል። እውነታው ግን ሌላ ነው። በየዓመቱ ህዝብ ሳያምንበት ተገዶ ይሰራል። በግዜው ያልሰራ እስከ ሦስት መቶ (300) ብር ተቀጥቶ ይሰራል። በዚሁ ምክንያት ብዙ ሌሎች የግል […]
አቡጊዳ – ግንቦት ሰባት በባህር ዳር የታየዉን ሕዝባዊ ተቃዉሞ ማደራጀትና መምራት ትልቅ ነገር ነው አለ።
የግንቦት ሰባት በድህረ ገጹ ላይ ይፋ ባደረገዉ የሳምንቱ ርእስ አንቀጽ፡ በመኢአድ እና አንድነት ፓርቲ ለተጠራዉ የባህር ዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ ያለዉን አድናቆት ገለጸ። «ፈታኝ ሁኔታዎችን ተቋቁመው የየካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ምን ሕዝባዊ ተቃውሞ ላደራጁና በተቃውሞውም ለተካፈሉ ሁሉ ያለውን አክብሮት ይገልፃል። ሕዝብ ብሶቱን የሚገልጽበት ሕዝባዊ ተቃውሞ ማደራጀትና መምራት መቻል ትልቅ ነገር ነው። ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ወደ ሕዝባዊ እምቢተኝነት […]
የትግራይ ሕዝብ የሥርዓቱ ተጠቃሚ ነዉ በሚለው ላይ የቀረበ አስተያየት – አብርሃ ደስታ
እስቲ በግልፅ እንነጋገር: ለተጋሩ ============== አንዳንድ ተቃዋሚዎች የትግራይን ህዝብ በህወሓት ዘመን የተለየ ጥቅም እንዳገኘ አስመስለው ሲያቀርቡ እንወቅሳቸዋለን። ምክንያቱም የትግራይ ህዝብ በህወሓት ዘመን እንደተጠቀመ ሳይሆን እንደተጎዳ ጠንቅቀን እናውቃለንና። በሌላ በኩል ህወሓት ለፖለቲካ ፍጆታ ሲል የትግራይ ህዝብና ህወሓት አንድ እንደሆኑ ይሰብካል። ህዝብና ገዢ ፓርቲ በምንም ስሌት አንድ ሊሆኑ እንደማይችሉ ግልፅ ነው። ፓርቲና ህዝብ አንድ አድርጎ የማሰብን ያህል […]
መነበብ ያለበት አጭር ጽሁፍ። አያስቅም! አጭር ወግ
አያስቅም! አጭር ወግ ክንፉ አሰፋ ጽሁፉን በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። አያስቅም! አጭር ወግ በብሄራዊ ትያትር አካባቢ አንዲት አነስተኛ ምግብ ቤት ነበረች። «ገሊላ ምግብ ቤት» ትባል ነበር። በአዲስ አበባ «ቁምራ» ከመግባቱ በፊት በአካባቢው ያሉ የመንግስት ሰራተኞች በምሳ ሰዓት ይህችን …
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ማርች 04, 2014
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
የጀርመን አምባሳደር የአፋር ጉብኝት
በአፋር ክልል ወደ አፍዴራ የሚወስደዉን መንገድን ይዞ የአርተአሌ እሳተ ጎመራ ባለበት አካባቢ ፤ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ሊዘሎረ ሲሩስ፤ ባለፈው ሳምንት ጉብኝት አድርገዉ ተመልሰዋል።
ያረጋገጥነው የምግብ ኢዋስትናን (ዋስትና አላልኩም) ነው።
ያረጋገጥነው የምግብ ኢዋስትናን (ዋስትና አላልኩም) ነው። ሠሎሞን ታምሩ ዓየለ ጽሁፉን በ.ፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። የምግብ ኢዋስትና ክፍል 1 ከአጻጻፍ ስልት የአብረሃም ደስታ አጻጻፍ ልቤን ይሰርቀዋል:; የቃላት አመራረጡ፤ የአረፈተ ነገሮቹ አጭር መሆን፤ የቃላት ፍሰቱ አንዳንዴም የአማርኛው ከትግርኛ አነጋገርና አነባብ ጋር …
የዩክሬን ቀውስ፣ የአውሮፓ ህብረትና የሩስያ ግንኙነት
ትናንት ብራሰልስ ቤልጅየም የተሰበሰቡት የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሩስያ ጦሯን ከዩክሬን ካላስወጣች ከሩስያ ጋር የተጀመረው ንግግር እንደሚቋረጥ እንዲሁም ማዕቀቦች እንደሚጣሉባት አስጠንቅቀዋል ።
የጀርመን አምባሳደር ለአፋር ሽምማግሌዎች ምስጋና
በአፋር ክልል ወደ አፍዴራ የሚወስደዉን መንገድ ይዞ ወደ አርተአሌ እሳተ ጎመራ ባለበት አካባቢ ፤ የጀርመንዋ አምባሳደር ሊዘሎረ ሲሩስ፤ በጋዜጠኞች ቡድን በመታጀብ ጉብኝት አድርገዉ ተመልሰዋል።
እዉቅና ያተረፈዉ ጤፍ ምርምር
መካከለኛዉ ምስራቅና የአረቡ ዓለም ስንዴን፤ ጃፓንን ጨምሩ በጥቅሉ እስያ ሩዝን፤ አብዛኛዉ አፍሪቃ በቆሎን ከማዕዳቸዉ አያጡም። አዉሮጳና ሰሜን አሜሪካም ቢሆን ስንዴን በብዛት እንዲሁም ገብስን ማዘዉተሩ ይታወቃል። ጤፍ ደግሞ መገኛዉም ሆነ ምግብነቱ የታወቀዉ ምስራቅ አፍሪቃ ኢትዮጵያ ነዉ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ ሕግ
አየር መንገዱ ወይም ሕጉን ያወጣዉ የኢትዮጵያ የገቢዎችና የጉሙርክ ባለሥልጣን የየሠራተኞቻቸዉን ጤና ለመጠበቅ እስከ ዛሬ የቆዩበት ምክንያትም ግልፅ አይደለም። መስሪያ ቤቶቹ አሁን ለመከልከላቸዉ ሁለተኛ ያሉት ምክንያት ግን አላቸዉ።
የቢን ላደን አማች የክስ ሒደት
የተያዘበት የወንጀል ጭብት ከተረጋገጠ እስክ እድሜ ልክ እስራት ሊፈረድበት ይችላል።የክሱ ጭብት አሜሪካኖችን ለመግደል፥ ለማሸበርና ለማወክ ማሴር፥ ከአሸባሪዎች ጋር መተባበር እያለ ይቀጥላል።የአሜሪካ ፖለቲከኞች በግለሰቡ ላይ ከተያዘዉ የክስ ጭብጥ፥ከሚፈረድበት ቅጣት ምንነት ይልቅ በክሱ ሒደት ላይ እየተከራከሩ ነዉ።
ፓትርያርኩ ከአማሳኞችና ጎሰኞች ጋራ ተዋርደው ከመምከር እንዲታቀቡና በዐደባባይ ቃል የገቡበትን ተቋማዊ ለውጥ በተግባር እንዲያስፈጽሙ ሊቃነ ጳጳሳቱ አሳሰቧቸው
‹‹ቅዱስነትዎ÷ ይህን ታላቅ ሓላፊነት ሲቀበሉ ቅ/ሲኖዶስ አዲስ ዋና ጸሐፊ፣ አዲስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርጎ ሰጥዎታል፤ መምከር ያለብዎ ከእነርሱ ጋራ ነው፤ ከዚያም ካለፈ ከቋሚ ሲኖዶሱ ነው፤ አስፈላጊ ከኾነም ጠቅላላው ጉባኤው ይሰበሰባል፡፡ እርስዎ ግን ወርደው ከማን ጋራ ነው እየተማከሩ ያሉት?›› ‹‹በአገራችን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እና ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በመላው ኢትዮጵያ ሲያገለግሉ ከየት መጣኽ አልተባባሉም፤ …![]()
በኢትዮጵያ የመብቶች ጥሰት ጉዳይ ከብሔራዊ አነታራኪ ፖለቲካዊ አጀንዳነት አልፎ ዓለም አቀፍ አጀንዳ ሆኗል።
ምንሊክ ሳልሳዊ :- ኢትዮጵያ በታሪኳ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ የመብቶች ሕጋዊነት በተጨበጨበለት ሁኔታ እና ይህ በማይባል ደረጃ በወረቀት ላይ ብቻ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ለይስሙላ እና ለማስመሰል የተደነገጉባት አገር ነች፡፡ የቀድሞ መንግስትን ሽንፈት ተከትሎ በኢትዮጵያ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች የፍፃሜ ምዕራፍ ይሆናል ተብሎ ተስፋ ተደርጎ ነበር፡፡ ነገር ግን ጭራሽ ብሶበት ቁጭ አለ፡፡ የሕወሓት ወንበሩን መቆጣጠር ተንተርሶ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በተለይም ሒዩማን ራይት ዎችና አምነስቲ ኢንተርናሽናል የወያኔን ጁንታ በሰብዓዊ መብት ጥሰት በማብጠልጠል ነበር የተቀበሉት፡፡ ባለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት የሰብኣዊ መብት ጥያቄዎች አቤቱታ ማሰማታቸውን አላቆሙም፡፡ ጋዜጠኞችን የሃሳብ ነጻነት ከሚገድብ ጥቃት በመከላከል ላይ የተሰማሩ የመብት አስከባሪ ድርጅቶችም ወያኔ በሚፈጥረው ከባድ የሰብኣዊ መብት ጥሰት በየጊዜው መክሰስ ሥራቸው ሆኗል:: የአሜሪካው ስቴት ዲፓርትመንት በየጊዜው በሚያወጣው ዓመታዊ መግለጫው ወያኔን በሰብዓዊ መብት ጥሰትና የፖለቲካ መብቶችን ማፈን ይከሰዋል፡፡ ባሁን ወቅት የእነኚህን አካላት መግለጫዎች የታወቁ ዓለም አቀፍ መገናኛ ድርጅቶች በመቀባበል ኢትዮጵያ የዜጎቿን መብቶች በመጣስና በማፈን ወደር የሌላት አገር እንደሆነች ዓለም እንዲረዳው እያደረጉ ናቸው፡፡
ታዋቂነታችን በድርቅ በድህነት ብሎም በጭፍጨፋ ደሞ በሰብኣዊ መብት ጥሰት የሕወሓት መራሹ ጁንታ ወደ ስልጣን በጠበንጃ ሃይል ከመጣ ጀምሮ በአለም አቀፍ ደረጃ የተደነገጉ የሰብአዊ መብት ህጎችን ካለምንም ማርቅርቅ እና ድካም ከሌሎች በመገልበጥ በወረቀት ላይ ከማስፈሩም በተጨማሪ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በአለም ላይ የሰው አገር ህግን እና አለማቀፍ ድንጋጌን ከሃገራችን ሁኔታ ጋር ሳይገናዘቡ በስፋት በደመነፍስ ለፍጆታ የተጻፈበት ሃገር ኢትዮጵያ ብቻ ሲሆን በየትኛውም አለም ሃገራት ያልተከሰተ የአለም አቀፍ ህጎችን ግልባጭ በከፊል በህገመንግስት እንዲሁም የገዢ ፓርቲን የፖለቲካ ፕሮግራም በከፊል ደባልቆ በጋራ እንደ አውራ ህግ የወጣባት ሃገር ብትኖር ኢትዮጵያ ብቻ ናት::ኢትዮጵያ በታሪኳ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ የመብቶች ሕጋዊነት በተጨበጨበለት ሁኔታ እና ይህ በማይባል ደረጃ የተደነገጉባት አገር ነች፡፡ እንግዲህ ይህ ሆኖ እያለ ነው በአገሪቱ የመብቶች ጥሰት ጉዳይ ከአገሪቱ ብሔራዊ አነታራኪ ፖለቲካዊ አጀንዳነት አልፎ ዓለም አቀፍ አጀንዳ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ጥላቻ በፈጠረው ፍርሃት ብቻ የሃገሪቱን ህጎች ዜጎች ለመጥለፍ እያዋሉት ነው::
ኢትዮጵያ በአስከፊ ድርቅና ረሃብ ለመታወቅ እንደበቃችው ሁሉ ወያኔ የዜጎችን መብቶች በመጣስና በማፈን እንዲሁም በሰብዓዊነት ላይ በሚፈጽመው ወንጀል በዓለም ላይ ታዋቂነትን እያተረፈ ነው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም;ወያኔ የፖለቲካ ተቀናቃኞችን መብቶች ለመጣስ ስለሚጠቀምባቸው ዘደዎች የሚቀርቡ ማስረጃዎች እና ማብራሪዎች እጅግ ዘግናኝ ናቸው፡፡የወያኔ መሪዎች የፖለቲካ ተቀናቃኖችን ለማዳከም ሲሉ ንፁኃንን ወንጀለኛ የሚያደርግ ዘዴዎችን ሥራ ላይ እንደሚያውሉ በተለያዩ ይፋዊ ሪፖርቶች ላይ ሁሉ ከነማስረጃው እየተነገረ ይገኛል::
ይህ የሰብኣዊ መብጥ ጥሰት እየተባባሰ የሚሄድበት ምክንያት ወያኔ በአብዛኛው ካድሬዎች ዘንድ በስፋት ሰርጾ እንዲገባ ያደረገው የተቃዋሚዎች ጥላቻ እና እንዲሁም የተቃዋሚው ቡድን የትግል አቅጣጫው በተመሳሳይ መልኩ በጥላቻ ላይ የተመረኮዘ መሆኑ ነው::ተቃዋሚዎች የታጠቁ ሃይላት ባለመሆናቸው የመርሃቸው እንቅስቃሴ የተገደበ እና ለፖለቲካ እና ለሚዲያ ፍጆታ የዋለ ተዳፍኖ የሚገኝ ሲሆን የወያኔው ግን በታጠቁ የጸጥታ ሃይሎች እና በፖለቲካ ማጭበርበሮች ላይ ስለተመረኮዘ ካድሬዎቹ በተሰጣቸው የጥላቻ ተግዳሮት እና ወያኔያዊ ስልቶች የፈጠሩትን ጥቅማጥቅሞች ጠብቀው ለማቆየት ሲባል ጥላቻ በፈጠረው ፍርሃት ብቻ የሃገሪቱን ህጎች ዜጎች ለመጥለፍ እያዋሉት ነው::
ይህ ፍርሃት እና ጥላቻ በወያኔ ከትልቅ እስከ ትንሽ ካድሬዎች አናት ውስጥ ስር ለስር በመስደድ የፈጠረው ነገር ቢኖር ማንኛውም ዜጋ ተቃውሞ ካሰማ በወንጀለኛነት በመፈረጅ በማሳደድ በማጥፋት እረፍት ለማግኘት እና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲራወጡ የህዝብን የበላይነት አፈር ከተውታል::ማእከላዊ የወያኔ ጁንታ በዲሞክራሲ ባለመወቀጣቸው የህጎችን የበላይነት ማረጋገጥ ካለመቻሉም በተጨማሪ በህዝብ እና በዲሞክራሲ ላይ በደሎችን የሚያደርሱ ባለስልጣናት የሚጠየቁት በሃገሪቱ የበላይ ህጎች ሳይሆን በወያኔያዊ የፓርቲ መመሪያዎች በመሆኑ በጥቅም መተሳሰር በፈጠርው ዝግ መንገድ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች እየተብራከቱም ከመሆኑ አልፎ የእለት ተእለት ተግባራት አካል ሆነዋል::ምንሊክ ሳልሳዊ
የገዢዎቻችን መጨረሻና የተከተላቸው ሀቅ አንዱ ዓለም ተፈራ
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
የአንድነት ፓርቲ መሪ ኢ/ር ግዛቸው በውጭ ሀገር ያሉ ደጋፊዎች ጋር በስልክ ውይይት አደረጉ
“በዉጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ በአካል ርቆ ቢገኝም ልቡ አገር ቤት ነዉ።” ኢ/ር ግዛቸው
አንድነት ፓርቲ በ450 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ለመወዳደር እቅድ አለው
Ethiopia Zare ሰኞ ካቲት 24 ቀን 2006 ዓ.ም. March 3, 2014)፦ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር፣ በአሜሪካ ካሉ የድጋፍ ማህበራት ጋር ወደ ሁለት ሰዓት የሚጠጋ ሰፊ ዉይይት በቴሌኮንፈራንስ አደረጉ። ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራዉ ፣ የአንድነት ፓርቲ እያደረጋቸው ስላለው ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች ሰፋ ያለ ሃታተ የሰጡ ሲሆን፣ ከስብሰባው ተሳታፊዎች በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጠዋል።
በብሩህ ተስፋና በሰላም የታጀበ በዓለ ሢመት – የጎሰኝነትና የሙስና አሜከላን መንቀል እንጀምር!
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ዓላማ ከምኞትና ከተስፋ አልፎ ፍሬ ሊያፈራ የሚችለው ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ ሊቃውንት፣ ካህናትና ምእመናን ተባብረው ለተግባራዊነቱ መሰለፍ ሲችሉ ብቻ ነው፡፡ ከኹሉ በላይ ግን የብፁዓን አባቶች ሓላፊነት የገዘፈ ኾኖ ሲገኝ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መዳከም የሚጎዳው እኛ አገልጋዮቿንና ምእመኖቿን ብቻ አይደለም፡፡ የቤተ ክርስቲያን መድከም የኢትዮጵያ መዳከም ጭምር ነው፤ የሀገራችን የህልውና መሠረት የተጣለው በዚኽች …![]()
የፈራ ይመለስ!
(ተመስገን ደሳለኝ)
በ2004 ዓ.ም የካቲት 23 ቀን በታተመችው ‹‹ፍትሕ›› ጋዜጣ ላይ፣ ‹‹የፈራ ይመለስ!›› በሚል ተመሳሳይ ርዕስ፣ ከሰላማዊ አብዮት ውጪ አማራጭ ካለመኖሩም ባለፈ፣ ኢህአዴግ ቢያንስ ሕገ-መንግስታዊ ጥበቃ ላላቸው ሕዝባዊ ጥያቄዎች ምላሽ የመስጠት አቅምም ፍላጎትም እንደሌለው ለመሞገት ሞክሬ ነበር፡፡ ግና፣ አገዛዙ ለእንዲህ ያሉ ግዴታዎች የተዘጋጀ ባለመሆኑ ከማድመጥ-መዳ–መጥን፤ ከመመከር-መከራን፤ ከማሰብ-ቃሊቲ መሰብሰብን፤ ከመሻሻል-ከሀገር ማሸሽን፤ ከማመን-መርገጥን… በመምረጡ፤ ዛሬም ድረስ ነፃነት ናፋቂው ዘመነኛ ትውልድ፣ በፀጥታ አርምሞ ወደተዋጡት አደባባዮች ከማማተር ያለፈ አማራጭ እንዳያገኝ ገፊ-ምክንያት ሆኖ ቀጥሏል፡፡
የዋሽንግተንና የአዲስ አበባ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እየተተቸ ነዉ
“በሙስና በእምነት ማጉደል በማታለልና በአመለካከት የሚለዩን ዝም በማሰኘት ሐይልን የያዛችሁ በተሳሳተ የታሪክ ገጽታ ላይ ነው ያላችሁት! ቡጢያቹን የምትፈቱ ከሆነ እጅ እንዘረጋላችሗለን” ያሉት ኦባማ አንባገነናዊ ቡጢያቸዉን ካልፈቱ…አንባገነናዉያን ጋር እጃቸዉን ዘርግተዉ ሲጨባበጡ መታየታቸዉ ትዝብት ላይ እየጣላቸዉ ነዉ!
ዋሽንግተን ዲሲ፤ የካቲት 24/2006 (ቢቢኤን) ፦ የዩናይትድ እስቴትስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉን ገደብየለሽ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለማመላከት ያደረጋቸዉን ጥናቶች ዋቢ በማድረግ በየካቲት 20/2006 ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል።መሰረቱን አርሊንግተን ቨርጂኒያ ያደረገዉ ፖለቲኮ የሚባለዉ ጋዜጣ/መጽሔት የኦባማ አስተዳደር የኢትዮጵያ መንግስትን ከመሰሉ ለነጻነት ምቹ ካልሆኑ አገራት ጋር ያለዉ ምጸታዊ የዲፕሎማሲ ቁርኝትንም ይተቻል።
ከቀዝቃዛዉ ጦርነት ጀምሮ የዩናይትድ እስቴትስ መንግስታት ዜጎቻቸዉን ከሚጨቁኑ አገራት ጋር ግንኙነት ለመመስረት እምብዛም እንደማይጥሩ ፖለቲኮ እየገለጸ፤ለሚዛናዊነቱ ተስፋ የተጣለበት የኦባማ ካቢኔ ከሌሎቹ የዩናይትድ እስቴትስ ፕሬዝዳንቶች በባሰ መልኩ ለዜጎቻቸዉ ደህነነት ምቹ ካልሆኑ 25 አገራት ጋር ግንኙነት አለዉ ሲል የኦባማን የብሐራዊ ደህነነትና ጥበቃ አማካሪ የሆኑትን ሱዛን ራይስ ንግግርን በዋቢነት ያቀርባል። ራይስ “ግልፅ እንሁን አንዳንዴ እኛ አጥብቀን የምንይዛቸዉን ዉድ የሆኑ መብቶችን ከማያከብሩ መንግስታት ጋር የስራ ግንኙነት አለን” በማለት በባለፈዉ የነሐሴ ወር መናገራቸዉን ፖለቲኮ ይገልጻል።
ፖለቲኮ ለነጻነት የማይመቹ ብሎ ከጠራቸዉ 25 አገራት ዉስጥ ኢትዮጵያን በቁጥር 11 ላይ ያስቀመጠ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማሪያም ደሳለኝ ይመሯታል የምትባለዋ ኢትዮጵያ የጸረ-ሽብር ህጓን ፖለቲከኞችን፣አክቲቪስቶችን፣መንግስትን ተጠያቂ የሚያደርጉ አካላትን ለማሰር እንደ ማህተም ትጠቀምበታለች ሲል ተጠያቂ ያደርጋል።ፖለቲኮ አክሎም የመለስ ዜናዊ አስተዳደር በ1999 ሶማሊያን በመዉረር እራሱን ለዩናይትድ እስቴትስ ግልጋሎት ማቅረቡንያስረዳል። ይህንንኑ አጋጣሚ በመጠቀም በአሜሪካ የሰለጠኑ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከብሔር ብሔረሰቦች የተነሱ አማጺያንን ለማስቆም የጦርነት ወንጀል መፈጸማቸዉ በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ክስ ቢቀርብበትም ዋሽንግተን አዲስ አበባን በዲፕሎማሲ “እቅፍ-እቅፍቅፍ” እያደረገች መቀጠሏን ገልጿል።
ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብትን ይጥሳሉ ከሚባሉት ጭቋኝ አገራት ጎራ ብትመደብም ፤እንደ አዉሮፒኣይኑ ቀመር በ2008 ብቻ ከዩናይትድ እስቴትስ 969 ሚሊዮን ዶላር በእርዳታ ተቀብላለች!
በኢትዮጵያ ዉስጥ ቀጣይ የሆነ የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ግድያ፣እስር፣የሐይማኖትነጻነትን መነፈግ፣የፕሬስ ነጻነት መመንመን፣የመማርና ማስተማር ሒደት ነጻነት በመንግስት መዳፍ ዉስጥ መግባት፣የመደራጀት-የመሰባሰብ-ሐሳብን በነጻ የመግለጽ ሁለንተናዊ መብት፣ የፍርድ ቤት አሰራር መበላሽትና በስልጣን መባለግን በመተንተን የዩናይትድ እስቴትስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በየካቲት 20/2006 አመታዊ ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል። የኦባማ አስተዳደር አካል የሆነዉ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አሳቃቂ የሆነ የመብት ረገጣ ኢትዮጵያ ዉስጥ መኖሩን እያወጀ የኦባማዉ ቤተ-መንግስት ኢትዮጵያን ከመሰሉ በአንባገነናዉያን ከሚመሩ አገራት ጋር “መለስ-ቀለስ” ማለቱ እያስተቸዉ ነው። የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱን የሚመሩት ጃን ኬሪ አገራቸዉ ከስህተት የጠራች አለመሆኗን ያስረዳሉ።
“ዛሬ ስለ ሌሎች አገራት ያለዉ ሪፖርት ይፋ ለማድረግ ብንመጣም፤ እዚሁ አገራችን ላይ እራሳችንን በከፍተኛ መልኩ ተጠያቂ እናደርጋለን! እንከን የለሽ አለመሆናችንን እናዉቃለን” ጃን ኬሪ።
ጃን ኬሪ መስሪያቤታቸዉ ይፋ ያደረገዉ የሰብዓዊ መብት ሪፖርት ዋሽንግተን ዲሲ ባሉ የመስሪያ ቤቱ አባላት ጥናት ብቻ የተዘጋጀ ሳይሆን በእያንዱ አገራት ያሉ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤቶች ተሳታፊ መሆናቸውን ሲያስረዱ “በመላዉ አለም ያሉ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤቶች በጥናት እንደዚሁም እነዚህን ጽሁፎችን በመጻፍ አክቲቪስቶችን በመቅረብ መንግስታትን በማናገር የኤንጂኦና የሚዲያ ሪፖርቶችን በመተንተን አያሌ ሰአታትን አባክነዋል”ሲሉም ገልጸዋል።
ኬሪ ለነጻነትና ለመብት በሚደረግ ጥረት ዉስጥ ግለሰባዊ ሚና የጎላ መሆኑን መሆኑንም ይገልፃሉ።ከተለያዩ አገራት የለዉጥ ተምሳሊት የሚሏቸዉን ግለሰቦችን ስም በማንሳት የኢትዮጲያዉን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ሚናን አድንቀዋል “እስክንድር ነጋ ሐሳብን በነጻ ስለመግለጽ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚጽፍ ነው” ብለዋል።
በሚያዚያ 4/2004 የፔን አሜሪካን ሽልማትን ያገኘዉ እስክንድር ነጋ አለም አቀፋዊ ትኩረትን ያገኘ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ነዉ። የኢትዮጵያ መንግስት በሽብር ፈጠራ ወንጅሎት ከመስከረም 3/2003 ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛል።
የዩናይትድ እስቴስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ነጻነትን ከሚነጥቁ ጥቂቶች ጋር ሳይሆን ነጻነትን ከተነፈጉ ብዙሗን አጋር በመሆን አብሮ እንደሚቆም ኬሪ ቃላቸዉን እያደሱ ይናገራሉ “ዛሬ ቃላችንን በድጋሚ ለማረጋገጥ እንወዳለን! ክብርን ከሚነፍጉ ጥቂቶች ጋር ሳይሆን ክብርን ከሚሹ ብዙሗን ጋር አብረን ለመቆም ዝግጁ መሆናችንንም ለመግለጽ እንወዳለን!”በማለት ቢያስረዱም መንግስታቸዉ ከጨቋኝ አንባገነናዊያን ጋር በሚያደርገዉ ዲፕሎማሲያዊ ቅርርብ ተጠያቂ እየሆነ ነው።
በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ብዙ ቃልኪዳን የገቡት በራክ ኦባማ ቃሊኪዳናቸዉ አለተፈጸመም። በተመሳሳይ መልኩ ያሁኑ የዉጭ ጉዳይ መስራያ ቤት ሐላፊ ጃን ኬሪም ሆኑ የቀድሞዋ ሒላሪ ክሊንተን ከአንባገነናዊያን ጋር ያለዉን ግንኙነት ሲያደረጁ እንጂ ሲያመነምኑ አልተስተዋለም በማለት በርካታ ምሁራን፣ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ ተንታኞች ወቀሳ ያቀርቡባቸዋል።
በጥር 12/2001 ቃለመሃላ የፈጸሙት ፕሬዝዳንት ኦባማ ሰላምና ክብርን ለሚሹ የአለማችን ዜጎች የርሳቸዉ መመረጥ ብስራት እንደሆነ አመላክተዉ ነበር። ከትላላቅ የአለማችን መዲናዎች ጀምሮ ወላጅ አባታቸዉ እስከመጡበት የኬኒያ መንደር የተስፋ ቃል ነበራቸዉ! እንዲም በማለት ስሜትን በሚነካ መልኩ ተናግረዉ ነበር…
“ከትላልቆቹ መዲናዎች እስከ አባቴ የተወለደባት መንደር ዛሬ ለሚመለከቱን ህዝቦችና መንግስታት፤ አሁን አሜሪካ የእያንዳንዱ አገር የእያንዳንዱ ግለሰብ ወዳጅ ናት! ሰላምና ክብርን ለሚፈልጉ ሴቶችና ህጻናት ዳግም ለመምራት ዝግጁ ነን” ፕሬዝዳንት በራክ ኦባማ።
ኦባማ ምንጫቸዉ ለሆነችዋ አፍሪካ ፕሬዝዳንታዊ ሐይላቸዉን በመጠቅም ያበረከቱት አስተዋፅኦ አናሳ ነዉ።ፕሬዝዳንቱ ቃለመሃላቸዉን ሲፈጽሙ ስልጣንን በማጭበርበር-በሙስናና የሐሳብ ልዩነትን በማፈን በሚቆናጠጡ አንባገነናዉያን ላይ ጣታቸዉን ቢቀስሩም ከነዚህ ምቹ ያልሆኑ አሳፍሪ መንግስታት ጋር እርሳቸዉም ይሁን ካቢኔአቸዉ ዲፕሎማሲያዊ ገደብን አለማበጀቱ አጠያያቂ እየሆነ ነዉ።
በአሜሪካዋ መዲና በዋሽንግተን ዲሲ ጥር 12/ 2001 ቀዝቃዉ አየር በጭብጨባ እየሞቀ ብዙዎች እያለቀሱ ኦባማ ለአንባገነናዊያን መልእክት አስተላልፈዋል…
“በሙስና በእምነት ማጉደል በማታለልና በአመለካከት የሚለዩን ዝም በማሰኘት ሐይልን የያዛችሁ በተሳሳተ የታሪክ ገጽታ ላይ ነው ያላችሁት! ቡጢያቹን የምትፈቱ ከሆነ እጅ እንዘረጋላችሗለን” ያሉት ኦባማ አንባገነናዊ ቡጢያቸዉን ካልፈቱ…አንባገነናዉያን ጋር
እጃቸዉን ዘርግተዉ ሲጨባበጡ መታየታቸዉ ትዝብት ላይ እየጣላቸዉ ነዉ።
ብዙ የተገቡ ቃልኪዳስኖች ተግባራዊ ሳይሆኑ በየካቲት 20/2006 ከዩናይትድ እስቴትስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአመቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲታወጅ “ከነጻነት ፈላጊዎች ጋር እንቆማለን!” የሚል ቃልኪዳን ተገብቷል።የዩናይትድ እስቴትስ መንግስት ባወጣዉ የሰብዓዊ መብት ሪፖርት የኢትዮጵያን መንግስት “ጨቋኝ-አፋኝ-አሳሪ-ገዳይ-ኢዲሞክራሲያዊ” መሆኑን ይፋ አድርጓል። ፖለቲኮ ጋዜጣ/መጽሔት ይህ ሪፖርት በወጣበት ማግስት የኦባማ አስተዳደር ኢትዮጵያን ከመሰሉ ለዜጎቻቸዉ ምቹ ካልሆኑ አገራት ጋር ይወዳጃል ሲል ይተቻል።
የዲሞክራሲ ተምሳሊት ነን የሚሉ የምእራቡ አገራት ለአንባገነናዊያን ዲፖሎማሲያዊ ከለላ መስጠታቸው የጥቅም ትስስር ወይስ ምጸታዊ የሆነ የዲፕሎማሲ ጨወታ? የሚለዉ ጥያቄ ቢነሳም …ትችቱእንደቀጠለ ነዉ።
ሳዲቅ አህመድ
የሙዚቃ ቃና ቅንብር – ማርች 04, 2014
ዘወትር ቅዳሜ ማታ ከደሳለኝ መኮንን ጋር፣ምርጥና አዳዲስ የካንትሪ ማለትም የአሜሪካ አገር ሰብእ፣ የሮክ፣ተሶል፣የፖፕ፣የአር-ኤን-ቢ፣ብሉዝ፣የሬጌና የሂፕ-ሃፕ ዜማዎችን እንዲያደምጡ ተጋብዘዋል።
የአፍሪቃ ኅብረትና የእንፋሎት ኃይል
የአፍሪቃ ኅብረት በታዳሽ ኃይል ምንጭ ረገድ ፤ በከርሰ ምድር የሚገኝ የተፈጥሮ እንፋሎትን ለማስፋፋት ባለው አቅድ ፣ ከእርዳታ ተባባሪ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ውል መፈራረሙ ተገለጠ። ውሉ ፣ በምሥራቅ አፍሪቃ የሚገኘውን የአንፋሎት ኃይል የሚመለከት
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ማርች 03, 2014
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
የኢትዮጵያውያን ስሞታ ከሳዉዲ እሥር ቤት
በስዑዲ ዐረቢያ በተለያዩ አሠሪዎች ተቀጥረው ይሠሩ የነበሩ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ፤ ባለፈው ኅዳርና ታኅሣሥ፣ በሕጋዊ የሥራና የመኖሪያ ፈቃድ ሰበብ ፤ በፖሊስና በጋጠ ወጥ ወጣቶች ፤ ማዋከብ ፤ ግድያና ድብደባ ፤ አስገድዶ መድፈርና የመሳሰሉ
የሰማያዊ አመራር አባላት በሶስት መስመር ወደ ተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች ተጓዙ
ዛሬ ጠዋት ልክ12 ሰዓት ላይ የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን የያዘ ሶስት ልኡካን ቡድን ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ጉዞ ጀምሯል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ የጀመረውን ሰላማዊ ትግል በመላው የሀገሪቷ ክፍል ለማንቀሳቀስና ለማጎልበት ከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች የሚመራ የልዑካን ቡድን በሶስት አቅጣጫዎች ዛሬ ጠዋት 12 ሰዓት ላይ ጉዞ ጀምሯል፡፡ የልዑካን ቡድኑ በመስክ ጉብኝቱ ወቅት የፓረቲውን መዋቅር የስራ እንቅሰቃሴ መገምገምና ለማጠናከር […]
የደሴ ሕዝብ በኢሕኣዴግ የግዳጅ መዋጮ ተማሯል::በደሴ ወንጀል በመበርከቱ የሰአት እላፊ ገደብ ተጥሏል:: በከተማዋ ፌዴራል ፖሊሶች በምሽት ወታደራዊ ልምምድ ያደርጋሉ::
የደሴ ሕዝብ ከመለስ ፋውንዴሽን ጋር በተያያዘ ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ ይፈለግበታል::
ምንሊክ ሳልሳዊ :- ከደሴ የሚደርሱኝ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት በሕወሓት አዛዥነት በብኣዴን ሰብሳቢነት የመለስ ዜናዊን አመራር አካዳሚ ሕንጻን ለመገንባት የመለስ ፋውንዴሽን ከህዝቡ ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚጠበቅበት እና ለግንባታው የግዴታ አስታውጾ እንዲያደርግ እያስገደዱት መሆኑን እና ሕዝቡም ከኑሮ ውድነት ጎን ለጎን ከአፉ ላይ ሊጎርሰውን ያዘጋጀውን በጉልበተኞች እየተነጠቀ መሆኑን በማማረር አቤቱታውን ማሰማቱን የደሴ የለውጥ ሃዋርያ ወጣቶች አንድነት ለምንሊክ ሳልሳዊ በላከው መረጃ ገልጽዋል::
መረጃዎቹ እንደጠቆሙት የገንዘብ አሰባሰቡ ሂደት በሁሉም ክፍለከተሞች ባሉ የወያኔ ካቢኔዎች ሲሆን እያንዳንዱ የካቢኔ አባል በግል እንዲሰበስብ የገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ የተሰጠው ሲሆን ከፍተኛ ገንዘብ ለሰበሰበ ሽልማት ስለሚሰጠው የሚል ቅል ስለተገባላቸው የስልታን እና የደሞዝ እድገት ለማግኘት እና ታማኝነታቸውን ለማረጋገጥ በሽፍን ድጋፍ ሕዝቡን በግዳጅ እና በማስፈራራት በዛቻ ገንዘብ እንዲያዋጣ እያደረጉት ሲሆን ይህንን በተመለከተ ሕዝቡ በቤቱ አሊያም በስብሰባ ካልተገኘ በቅጣት ሁሉ መልክ ተጨማሪ እንዲከፍል ይደረጋል የሉት የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ሕዝቡ በሚሄድበት መስሪያቤት አሊያም ስብሰባ ቀደም ብሎ የከፈለ ሰው ደረሰኙን ካልያዘ ጉዳዩን ለማስፈጸም በድጋሚ እንዲከፍል የሚደረግ ሲሆን እረስቸዋለሁ ሄጄ ላምጣ የሚል ነገር ተቀባይነት የለውም::
እንዲሁም በደሴ የብኣዴን ጽ/ቤት ሃላፊነት ተጨማሪ ለመለስ ፋውንዴሽን በሚል በግዳጅ ገንዘብ እየተሰበሰበ ሲሆን የጽ/ቤቱ ሃላፊ የሆኑት አቶ ጌታዊ ይርጋ (የቀድሞ የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ) ከዚህ ቀደም በሙስና ታስረው የነበሩ እና ከህግ ውጪ ለፖለቲካው አስፈላጊ ሆነው በመገኘታቸው በትእዛዝ ከተፈቱ በኋላ ሲቭል ሰርቭስ ኮሌጅ ተልከው ሰልጥነው በደሴ የብኣዲን ጽ/ቤት ሃላፊ ሆነው ከተመደቡ ጀምሮ በግዳጅ ከእጅ ወደ አፍ የሚኖረውን በኑሮ ውድነት የተማረረውን ህዝብ እያስገደዱ የመንግስት ሰራተኛውን ከደሞዙ ላይ 30% እንዲቆረጥ ውሳኔ በመስጠት እንዲሁም በየቤቱ የብኣዴን ካድሬዎች እየዞሩ ከቀበሌ ሰዎች ጋር በመሆን ሕዝቡ 100 ብር እንዲከፍል በበደል ላይ በደል እየፈጸሙበት ይገኛል:: እንዲሁም ባለሃብቱን እያስገደዱት ያሌለን ገንዘብ እንዲተፋ ወጥረው ይዘውታል ሲሉ ለምንሊክ ሳልሳዊ መረጃውን ልከዋል::
=================ምንሊክ ሳልሳዊ====================
በሌላ ዜና በደዜ ከተማ ዙሪያ ጨለማን ተገን አድርገው የሰዎች ግድያ እና ዝርፊያ ወንጀሎች ከበፊቱ በበለጠ በመበርከቱ የከተማው ፖሊስ መምሪያ ማንኛውም የከተማው ነዋሪ ከምሽቱ አራት ሰአት በኋላ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርግ የሰአት እላፊ ገደብ መጣሉን የከተማው ነዋሪዎች ለምንሊክ ሳልሳዊ በስልክ ገልጸውለታል::
ባለፉት ሁለት ቀናት በመላው አገሪቱ የተካሄዱትን ፍተሻዎች በተመሳሰለ መልኩ የሞባይል ቤቶች እና የኢንተርኔት ካፌዎችን እንዲሁም የመረጣቸውን ብሎም የጠረጠራቸውን ግለሰቦች በድንገት ፍተሻ በማካሄድ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሞባይሎች ላፕቶፖች ዲስክቶፖች ኮምፒተሮች እና የሚሞሪ ካርዶች ሰብስቦ የወሰደው የደሴ ፖሊስ ሰአት እላፊውን ጥሶ የተገኘ ነዋሪ በጸጥታ ሃይሎች ለሚወሰድበት ማንኛውም እርምጃ መንግስት ተጠያቂ እንደማይሆን ገልጿል::
ከዚሁ ጋር በተያያዘ መረጃ የደሴ ከተማ በፌዴራል ፖሊስ ወታደራዊ ልምምድ ተወጥራ እንደምታመሽ ታውቋል:; ቁጥራቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ የፌዴራል ፖሊሶች ከምሽቱ 3 30 ጀምሮ ወታደራዊ ልምምድ ለማድረግ በዋናው የከተማዋ መንገዶች በመጠቀም ላይ ሲሆኑ በህዝቡ ላይ ሽብር እየነዙ መሆኑን ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ነግረውታል::ይህንን እያደረጉ ያሉት የከተማውን ነዋሪ ለማስፈራራት እና ለማሸበር እየጣሩ እና በሃርቡ አከባቢ የሚንቀሳቀሱ የፌዴራል ፖሊሶች ለሊቱን በወታደራዊ ልምምድቸው ጊዜ ስለሚጮሁ ህዝቡን ከስራ ቤቱ ገብቶ እንዳያርፍ እንቅልፍ እየነሱት ሲሆን ምን ያክል መንግስት ጭንቀት ላይ እንዳለ ያሳያል ሲሉ መረጃውን የላኩት ነዋሪዎች ገልጸዋል::መረጃውን ላቀበላችሁኝ የደሴ ወጣቶች አመሰግናለሁ ምንሊክ ሳልሳዊ::

ክሬሚያ ድሮና ዘንድሮ
ክሬሚያ። ዛሬ የዩክሬን ግዛት ናት።ዩክሬን ዳግም ከምዕራባዉያኑ ደጋፊዎች እጅ ከወደቀች ቅዳሜ-ሳምንት ሆናት።ፕሬዝዳት ቭላድሚር ፑቲን ግርማዊ ቀዳማዊ ንጉስ ኒኮላዉስ አይደለም።ዳግማዊ አሌክሳንደር፥ ሌኒን ወይም ስታሊኒንም አይደሉም።በክሬሚያ ሲመጣ ግን እንደሁሉም ሁሉ እጃችንን አጣጥፈን አንቀመጥም አሉ።
03.03.2014ዜና 16:00 UTC
የዓለም ዜና