ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

Image

መጀመርያ በዚህ የዓመቱ ምርጥ ብየ በምጠቅሰው ጥቅስ ልጀምር፦”የመሬት ላራሹ” ጩኸት ውጤቱ “መሬት ለነጋሹ” ሆኗል፤ ለገበሬው የታሰበውን መሬት ወያኔ ወሰደው። የዱሮ ንጉሣዊ ገዢዎቿ ቤተ ሰቦች ስለነበሩ በቊጥራቸው ማነስ ምክንያት እነሱን በማር ግብር ለማጥገብና በሰላም ለመኖር ቀላል ነበረ። የዛሬዎቹ ገዢዎች ብሔረ ሰቦች ስለሆኑ እነሱን ሁሉ በሚሊዮን ዶላር ማጥገብ መራቆትን አስከትሏል።” ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ (‘ዕርቅና ሰላም፤ የሕይወት ቅመም’ የካቲት 2006 ዓ.ም)
ወየኔዎች ወደ ሥልጣን ከመጡ በሗላ የአገሪቱን ሃብት ባገኙት አቅም እና ዘዴ ሁሉ በማራቆት ብቻ የተወሰኑ ሳይሆኑ የትግራይ ሕብረተሰብ በታሪክ ላይ የሚኖሮው ግንዛቤ የተጣመመ እንዲሆን አድረገውታል። በርከት ያሉ እንሰሳዎች በተለያዩ ምክንያቶች ሆን መጀመርያ በዚህ የአመቱ ምርጥ ብየ በምጠቅሰው ጥቅስ ልጀምር፦”የመሬት ላራሹ” ጩኸት ውጤቱ “መሬት ለነጋሹ” ሆኗል፤ ለገበሬውየታሰበውን መሬት ወያኔ ወሰደው። የዱሮ ንጉሣዊ ገዢዎቿ ቤተ ሰቦች ስለነበሩ በቊጥራቸው ማነስ ምክንያት እነሱን በማር ግብር ለማጥገብና በሰላም ለመኖር ቀላል ነበረ። የዛሬዎቹ ገዢዎች ብሔረ ሰቦች ስለሆኑ እነሱን ሁሉ በሚሊዮን ዶላር ማጥገብ መራቆትን አስከትሏል።” ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ (‘ዕርቅና ሰላም፤ የሕይወት ቅመም’ የካቲት 2006 ዓ.ም)

ወየኔዎች ወደ ሥልጣን ከመጡ በሗላ የአገሪቱን ሃብት ባገኙት አቅም እና ዘዴ ሁሉ በማራቆት ብቻ የተወሰኑ ሳይሆኑ የትግራይ ሕብረተሰብ በታሪክ ላይ የሚኖሮው ግንዛቤ የተጣመመ እንዲሆን አድረገውታል። በርከት ያሉ እንሰሳዎች በተለያዩ ምክንያቶች ሆን ብለው አጥቂዎቻቸውን ወይንም መሰሎቻቸውን ያታልላሉ። እንሰሳዎቹ በማታለል ዘዴ የሚኖሩበት ምክንያት የተለያዩ ምክንያቶች አሉዋቸው። ለምግብ፤ ወይንም እራሳቸው ከጥቃት ለመከላከል ሊሆን ይችላል።ይሁን እንጂ በተፈጥሮ እራሳቸውን እና ሌሎችን ሆን ብለው ለማታተለል/ለመዋሸት “የተሰሩ ፍጡሮች” ሰዎች ብቻ እንደሆኑ ያነበብኳቸው አንዳንድ የስነ ልቦና መጻሕፍቶች ይገልጻሉ።

የተለያየ ውሸት የተለያ ምክንያት ቢኖሮውም፡ ዋሾች አድማጭ ፈላጊዎች ናቸው። አታላዮች/ዋሾዎች እንደ እንደተሰጥዎአቸው የማጭበርበር፤ የመዋሸት ወይንም ማራኪ የንግግር ችሎታቸው ይለያያሉ። የተከታዮቻቸው ብዛትም አንደሚጠቀሙበት የማጭበርበር ስልት ይለያያል። ተራ ዋሾዎች ካደጉበት የውሸት ባሕሪ በመነሳት ሕዝብን የመምራት ፍላጎት እያዳበሩ በሄዱ ቁጥር፤ በመንግሥት፤ በፖለቲካ፤ በሃይማኖት ግብተው መሪነቱን ከያዙ፤ አደገኛ የውሸት ባሕሪያቸው በመጠቀም ሕዝቡን በውሸት ጐዳና በመምራት፤ “ዋሾ ማሕበረሰብን” ይገነባሉ።

እራሱን ያታለለ ማሕበረሰብ “የሕሊና ጎዶሎ/ሃንዲካፕ” ነው። ሌላ ቀርቶ በየጽሑፎቻችን ላይ የሚታዩ ግድፈቶች/ የቃላት ስህተቶች ልብ ሳንላቸው አልፈን ከታተሙ በሗላ ነው ስህተቶቹ ግልጽ ሆነው የሚታዩን። የዋህ ሕሊናም በአታላዮች አስተሳሰብ ሲጠለፍ እራሱን መፈተሽ ስለሚያቅተው፤ ከመሪዎቹ የሚነገሩት ሁሉ እውነት ስለሚመስለው፤ እሱም በውሸቱ ዘመቻ እየተካፈለ በሄደ ቁጥር እየዋሸ እንደሆነ አይታወቀውም። በመጠጥ ከሰከረ ይልቅ፤በውሸት የሰከረ ማህበረሰብ አስቸጋሪ ስለሚሆን (ዲናያል/ክሕደት) እውነታውን ለማስጨበጥ ጊዜ ስለሚፈጅ፤ የእውነት አስተማሪዎች ከዚህ ማሕበረሰብ ጋር ከፍተኛ ግብግብ ይገጥማቸዋል።

ይህ አሳዛኝ ባሕሪ ኢትዮጵያ ውስጥ በባሰ ደረጃ በወያኔዎች ዘመን ተከስቷል። የ ‘ወያኔ ትግሬ’ የውሸት ባሕሪ በታሪካችን፤በባሕላችን፤ በአርበኞቻችን እና በሉዓላዊነታችን ክብር ላይ ጥቃት አድርሷል። ጉዳቱ በጣም ከፍተኛ ነው።

ለዚህ ጹሑፍ መነሻ የሆነኝ፤ ሶሞኑን ‘ትግራይ ኦን ላይን’ በተባለው “ፍሎሪዳ” መሰረቱ ያደረገ የወያኔዎች ድረገጽ “Woyane Tigray: 39 Years and Still Standing” በሚል ያስነበበውን መነሻ በማድረግ ነው። (ጸሐፊው ሞቡቱ ሴሰ ሴኰም ሆነ ጋዳፊ ከወያኔ ዕድሜ በላይ እንደገዙ አላወቀም።

“እንደ ጋዳፊ
መለስን በጥፊ ፤
ሳንፈልጋቸው
ሃያ አመታቸው!”

ተብሎ የተጨፈረለትን የወያኔ ስርዓት አልሰማም መሰለኝ።) ርዕሱን በዚሁ ልምልስ እና ጸሓፊው በበላይ ዘለቀ እና በአሉላ መካካል ያለው ልዩነት ያነጻጸረበትን የውሸት ክስ እንመለከት።ከብርሃነ ካሕሳይ በሚል የተጠቀሰው ርዕሰ የጻፈው ጸሐፊ የዓይጋ ድረገጽ አዘጋጅ ወይንም የትግራይ ኦንላይን አባል አዘጋጅ እንደሆነ ይገመታል።ቢሆንም ባይሆንም ቁም ነገሩን ብቻ እንመልከት።

“…The warrior of Dogali, Gundet and Gura, is not receiving the accolade he rightly deserves simply because he happens to be a Tigrayan. Reverence for Belay Zeleke, who fought the Italians in Gojjam for a brief period, appears to be far greater than the hero of Africa. Unfortunately, the courageous Belay Zeleke was subsequently hanged by Emperor Hailesellaise upon his return from Bath, England, where he had resided after fleeing the country, leaving the people at the mercy of the Italian occupiers.” http://www.tigraionline.com/articles/wo … years.html (By Berhane Kahsay
Tigrai Onlne – February 09, 2014)

ይህ ውሸት ተደጋግሞ በወያኔ ትግሬ መሪዎች እና ተኮልኳሊዎቻቸው ተነግሯል። ባለፈው ወር የዶጋሊ በዓል ማክበር ሲገባ፤ ወያኔዎች ሳያከብሩት በዝምታ አልፈውታል። በዚህ የተነሳ ወዳጄ አቶ ብርሃኑ ሰፋ ያለ ቅሬታው ኢ ኢ ዲ ኤን በተባለ ማሕበራዊ መድረክ ለተቃዋሚውም ሆነ ለወያኔዎች ለምን አንዳልተከበረ ቅሬታው ገልጿል። ቅጁም ለእኔ አስተላልፎልኛል። ድሮ ደርግ ምፅዋ ላይ /ዶጋሊ ላይ ስለ አሉላ ያዘጋጀው የሲምፖዚየም ንግግር በመጽሐፍ ተጠርዞ አንዳነብበው ልኮልኝ አንብቤ አንድ ነገር አንዳዘጋጅ ተማጽኖኝ ነበር። ንባቡ ገና ሳልጀምር ወያኔዎች ከላይ የተመለከተው ሚዛን ያልጠበቀ የክስ እሮሮ በራሳቸው ከማድረግ ይልቅ በሌለው ላይ ክስ ሲያወርዱ አንብቤ ነው ይህ ድንገተኛ መልስ ለመጻፍ የተነሳሳሁ።

ወየኔዎች የውሸት ክስ፤ስም ማጥፋት፤ ክሕደት የድርጅታቸው ባሕርያዊ ቋሚ መለያቸው ነው። በጣም በርከት ያሉ መጽሐፍቶች የአጼ ዮሐንስም ሆነ የራስ አሉላ ታርክ እና ሞገስ ‘አማራ ታሪክ ጸሐፊዎች”’ ብለው ወያኔዎች በሚጠሯቸው የኢትዮጵያ ታሪክ ጻሀፊዎች የጻፏቸው እያንኳሰሱ፤ ዛሬ ወያኔዎች ከ22 አመት ንግሥና በሗላ ገንዘቡ፤ሕትመቱ፤ሳነሱሩ፤ውሸቱ ፤ብዕሩ፤መዛግብቱ፤ዩኒቨርሲቲው እና ምርምር ተቋማቱ በእጃቸው ቁጥጥ ባለበት ዘመን ምንም ሳይጽፉ በሃያ ሁለት አመት ውስጥ ስለ ዮሐንስ አንድ መጽሐፍ (በትዕቢት የተቆለለ ፤በውሸት የተበረዘ) የገብረኪዳን መጽሐፍ ብቻ ነው። ወደ ሃውልት ስንገባም፤ ወየኔዎች በአገሪቱ ስም ከውጭ አገር ዕዳ እየተበደሩ ወደ ኪሳቸው ከማግበስበስ እና ልጆቻቸው ወደ ውጭ አገር እየላኩ ከማስተማር እና እራሳቸውም በውድ ገንዘብ እየገዙ ዲግሪ ከማግኘት በስተቀር ለንጉሡም ሆነ ለራስ አሉላ ሃውልት ማሰራት ሲችሉ ወይንም ሕዝቡን አሰባስበው (እርዳታ እንኳ ካስፈለገ) ከማስሰራት ይልቅ እስካሁን ደቂቃ ድረስ ምንም የሰሩላቸው ሃውልት ወይንም መታሰቢያ የለም።

ስለ አሉላ ተሰራ የተባለው ሃውልት “የተቀመጡበት ፈረስ የአህያ ምስል በመያዙ፤ሕዝቡ ተቃውሞውን በማሰማት ሌላ የፈረስ ምስል የያዘ ሃውልት እስኪሰራ ድረስ በአቡጀዲ ሸፍነውት አንደነበረ ይታወቃል።

አንዳንዶቹ የሚሉት ያህያ ምስል አንዲቀመጡ የተደረገው ሆን ተብሎ በሻዕብያ አፍቃሬ ኤርትራዊያን ወያኔዎች ሴራ ምክክር እንዲቀረጽ አንደተደረገ በሃሜታ መልክ ይሰማል።

በሃያ ሁለት አመት ለአጼ ዮሐንሰም ሆነ ለአሉላ ይህ ነው የሚባል አጥጋቢ መታሰቢያ አንዳልሰሩላቸው የምከራከረው በመረጃ ነው። አማራ አንዲህ አደረገ ፤ያለፉት ጸሐፊዎች የንጉሳችን ታሪክ አልጻፉም፤ ሃውልት አልተሰራላቸውም… እያሉ በውሸት እስካሁን ድረስ የወያኔ ትግሬዎች የትግራይን ሕዝብ ሲያታልሉ 22 አመት አልፏቸው ስለ አሉላም ሆነ ስለ ዮሐንስ የሰሩት አንደም መታሰቢያ አይገኝም። ይልቁንስ ወያኔዎች “ለአሉላ ወይንም ለዮሐንስ” ሃውልት ነፍገው ኤርትራ ምድር ድረስ ሄዶ፤ ምፅዋ እና ሳሕል የኢትዮጵያን ሰራዊት የወጋ በክሕደቱ ዘመን ከጠላት (ሻዕቢያ) ጋር ተሰልፎ የወጋን የራሳቸው ታጋይ ለሆነው “ሓየሎም አርአያ “ (ሐዱሽ አርአያ) ሽሬ አውራጃ ውስጥ ሃውልት አቁመውለታል። ታዲያ

“…The warrior of Dogali, Gundet and Gura, is not receiving the accolade he rightly deserves simply because he happens to be a Tigrayan. Reverence for Belay Zeleke, who fought the Italians in Gojjam for a brief period, appears to be far greater than the hero of Africa.”

በማለት የወያኔ ቱልቱላዎች በታሪክ ጻሀፊዎች እና ባለፉት ገዢዎች ላይ የትግሬ እና የአማራ አርበኞችን እያነጻጸሩ የሚከስሱት ዘረኛ ክስ ከመክሰስ በፊት ሁሉም ነገር በእጃቸው ባለበት ሃያ ሁለት አመት እራሳቸው ያልሰሩትን ሌሎች አንዲሰሩላቸው መጠበቅ እና መክስስ አስገራሚ ክሰ ነው?

ለመታሰቢያ የቆሙ ከጣሊያን ወራሪዎች ጋር ተዋግተው በክብር የተሰውት የነ ደጃዝማች አፈወርቅ ፤የነ አቡነ ጴጥሮስ ፤የነ አሉላ፤ የእነ ምኒሊክ ወዘተ መታሰቢያ ሃውልቶች እያፈራረሰ እና እንዲፈርስ ዘመቻ እያካሄደ ያለው የሃያ ሁለት አመት አሳፋሪ ታሪክ የታቀፈው ማን ሆኖ እና ነው ማቆሚያ የሌለው ሃያ ሁለት አመት “የሕፃናት ልቅሶ እና ክስ” እየተለቀሰ ሌላውን ወገን ተወቃሽ የሚሆነው? ወያኔዎች ትንሽ የአደብ ሓፈረት የሚባል የሕሊና ገዢ እንዴት አንደተለያቸው ይገርመኛል? በሃይለስላሴም ሆነ በደርግ ዘመን ስለ አሉላም ሆነ ስለ ዮሐንሰ ጀብዱ አንዳንጽፍ ተከለከልን ካላችሁ፤ ውጭ አገር ሲኖሩ የነበሩ በርካታ የትግሬ ምሁራን የማን ጎፈሬ ሲያበጥሩ ኖሮው ነው (ከዘውዴ ገ/ስላሴ በቀር) አማራው እንዲጽፍላቸው የጠበቁት እና ተከሳሽ የሚያደርጉት? ያስ ተከድኖ ይብሰል፡ – ሃውልት አልቆመላቸውም፤ ታሪካቸው አልተጻፈም .. ወዘተ… የምትሉት አሰልቺ ልቅሶ ‘ሃያ ሁለት አመት’ ሙሉ ከማልቀስ እና ከመክሰስ ያለፈ ስራ ምን ሰራችሁ? እስኪ ንገሩን? ምን ሃውልት ሰራችሁ? የሐለፎም ሓውልት? የወያኔ ተጋዮች ሃውልት? ለነሱ ከማቆም ይልቅ ለክሳችሁ መነሻ የሆነው የወላጆቻችን ጀግንነት እና ንግሥና አማራዎች ነጠቁን ብላችሁ በረሃ ለመሄድ ከገፋፋችሁ ምክንያት አንዱ ከሆነ የአሉላም ሆነ የዮሃንስ ሃውልት ቅድሚያ ለምን አልሰጣችሁትም? የአሉላ እና የዮሐንስ ገድል ይበልጣል ወይስ አሉላ እና ዮሐንስ ያስከበሩትን ድምበር እና ባሕር ያስደፈሩ እና የዘጉ የወያኔ ታጋዮች ገድል? የአሉላም ሆነ የዮሐንስ ገድል የቀበረ እና በባንዳ ተልዕኮ የተሳተፉትን የጎሳ ታጋዮች ገድል ጎልቶ በበላይነት አንዲታይ እያደረገ ያለው ማን ነው? ኢትዮጵያዊያኖቹ ዮሐንስ እና አሉላ መታሰቢያ ሳይቆምላቸው፤ ለጎሳ ታጋዮች ለምን ቅድሚያ ተሰጣቸው?
የወያኔ ውሸት ታሪክን የመበረዝ እና የማጣመም ባሕሪ በምን ዓይነት የአጻጻፍ ዘዴ ቢጻፍ የውሸታቸው ክምር አንዴት መግለጥ እንደሚቻል ሳስበው ይጨንቀኛል። በዶጋሊ፤ጉንደት፤ጉራዕ፤ዓድዋ፤ባድመ፤ዓድዋ… የተደረጉ ጦርነቶች የትግሬዎች የመከላከል ታሪክ እና ጀግንነት ብቻ ነው እያሉ ያለ ምንም ሐፍረት ወይንም ዩልኝታ የሚገልጹት ባሕሪያቸው ሳስበው ለሕሊና ይከብዳል። የዚህ ውሸት ማቆሚያው መቸ እና የት ይሆን?

የዶጋሊ፤የሳሐቲ፤ወዘተ …. ወዘተ… ብዙ ኢትዮጵያዊያን የተቀላቀሉበት አንዳንዱም በመሪነት የመሩዋቸው ታላላቅ ውግያዎች ውጤት እንጂ የትግሬዎች ብቻ አይደለም። ድሉ እና ሱታፌው የትግሬዎች አንጂ የተቀሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ሱታፉ አልነበረም፡ የሚሉት ተዳጋገሚ ውሸታቸው በመጽሐፍም በንግግራቸውም በየስብሰባውም እስኪሰለቸን ድረስ ደጋግመውታል። ሃቁ ግን እነሱ እንደሚሉት ሳይሆን በተጠቀሱት ጦርነቶች የተሳተፉት ትግሬዎች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም የተሳተፉበት ውጊያ እና ድል ነበር። መረጃውም ቆየት ብየ አቀርባለሁ። ይህ መረጃ ላንዴ እና ለመጨረሻ ውሸታቸውን የሚያቆም በመሆኑ መረጃውን እንድትጠቀሙበት በጥንቃቄ አስቀምጡት።

መረጃውን ከመጥቀሴ በፊት ማለት የምፈልገው ነገር፤ መረጃው ካነበቡት በሗላ አንዳንድ ወያኔዎች፤ “ምንም እንኳ ከሌሎች አካባቢዎች የመጡ ሰራዊቶች በዶጋሊ፤ በጉራዕ…ወዘተ ይኑሩ እንጂ አብዛኛው ተዋጊ የትግሬ ሰራዊት ስለነበር፤ ድሉ የትግሬ ሰራዊት ነው፡ የሚሉ የወያኔ ጐሰኞች ሊኖሩ ይችላሉ።ለነዚህ የምሰጠው መልስ “ዓድዋ ላይ የተሳተፈው ተዋጊ ሠራዊት፤ አብዛኛው ትግሬዎች ሳይሆኑ የሸዋ የንጉሥ ምኒሊክ ሠራዊቶች ናቸው። ሌላ ቀርቶ የወያኔ ወዳጅ የሆነው አይሁዳዊው ‘ኤሪክ ሓጋይ’ “አሉላ” በተባለው መጽሐፉም የትግሬ ሰራዊት እጅግ ጥቂት ስለነበረ አሉላ የሰራው የውግያ አስተዋጽኦ ጎልቶ የሚታይ አልነበረም። ኢሚንት ነው። በማለት መስክሯል። በዚህ ክርክር ከገባን “ከራስ መንገሻ (አሉላ) ሸራዊቶች” ይልቅ ከሌሎች ኢትዮጵያ መንደሮች የመጣ በተለይም ከሸዋ በብዛት የተሳተፈ ሠራዊት ስለነበር፤ የዓድዋ ድል ‘የሸዋ ሠራት ድል’ መሆን አለበት ሊባል ነው ማለት ነው?” ዋናው የውሸት ቀፎ የሆነው የ ‘ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ’ ድርጅት፤ በድርጅቱ ሁለተኛ ጉባኤ (1975) ያጸደቀው ውሳኔ አንዲህ ይላል “በአገራችን የሰሜን ጦርነቶች በዶጋሊ፤ጉንደት፤ጉራዕ… የተካሄዱ ጦረነቶችና ድሎች የኤርትራ ሕዝቦች እና የትግራይ ሕዝቦች ድል ነው”። ሲል በ13ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በእነ አምደጽዮን (ከሸዋ እየገሰገሱ) እና በመሳሰሉት የድሮ ነገሥታት ከሩቅ ያገሪቱ ግዛቶች እየተወረወሩ ወደ “ሓማሴን ምድር ወይንም ወደ ባሕረ ምድር” (ኤርትራ) በመሄድ ከቱርኮች እና ከመሳሰሉ ወራሪዎች ተዋግተው ጠላት ድል የመቱትን ሁሉ በመደበቅ፤በአካባቢው የተደረጉ ጦርነቶች የትግሬ ጀግኖች ውጤት እያሉ ሚዛን ያጣ ትምክሕት በማሰራጨት አዲሱን የትግራይ ትውልድም ያንን ውሸት እየተቀበለ በዛው ትምክሕት እየተወጠረ መራመድ ጀምሯል።
አሁን ወደ መረጃዬ ልሂድ።

«—-ዘመናዊ የካራቢነር ጠመንጃና መድፍ የጨበጠው የግብፅ ጦር ወደትግራይ አምርቶ የመረብን ወንዝ ተሻገረ።በኅዳር 7 ቀን 1875 ከዚህ ወንዝ አጠገብ ጉንደት ከተባለች ሥፍራ ላይ በንጉሠነገሥት ዮሐንስ 4ኛ የተመራ የኢትዮጵያ ሠራዊት መንገድ ዘጋበት።ንጉሡ ሠራዊቱን በሁለት ከፍሎ ፤ አንዱን ክፍል ራሱ፤ ሁለተኛውን ክፍል በዚያን ጊዜ የተመሰከረለት ጀግና የነበረው ራስ አሉላ እንዲመራው አደረገ። ሁለቱም የኢትዮጵያ ክፍለ ጦር ከተለያየ አቅጣጫ ደወ ግብፁ ምሽግ ተንቀሳቀሱ። የጉንደት ጦርነት ሙሉ ቀን ፈጀ። ከምሽቱ ላይ ድሉ ለኢትዮጵያውያን ማድላቱ እየለየ መጣ። አብዛኛቹ በጀግንነት የተዋጉ ግብፃውያን ከትግሉ አውድማ ላይ የወደቁ ሲሆን፣ ከነዚህም ውስጥ አራኪል ቤይ እና ሻምበል አረንድሩፕ ያገኛሉ። ከፊሉ ተማረከ፣ አምልጦ ምፅዋ ሊገባ የቻለው በጣም ጥቂት ነው።

« ከዚህ ውድቀትም በኋላ ከዲቭ እስማኤል በኢትዮጵያ ላይ ቀጣዩን ዘመቻ ለመክፈት ዝግጅት ማድረግ ጀመረ። ለቀጣዩ ጦርነት ካሁኑ የበለጠና የተሻለ ትጥቅ ያለው ሠራዊት ለማዝመት ወሰነ። ላሁኑ ዘመቻ 20,000 ወታደር አዘጋጅቶ በእጁ የሚገኘውን የተሻለ መሣሪያ ሁሉ አስታጠቀው። እስማኤል ለአዲሱ ዘመቻ በጀርመን አገር በወታደራዊ ሥልጠና የተመረቀውን መኮንን ሙላይ ሐሰን ፓሻን አዛዥ አድርጎ ሾመው። ከሱም ጋር ሌሎች የግብፅ የጦር መሪዎች አብረውት የዘመቱ ሲሆን፣ ከነዚህም አንዱ ዝነኛው ራቲብ ፓሻ ነበር።

በታኅሣሥ ወር 1875 የከዲቩ ጦር ምፅዋ ላይ አርፎ በዝግታ ወደ ማህል ኢትዮጵያ መንቀሳቀስ ጀመረ። በየካቲት 1876 ከመረብ ወንዝ ተጠጋ።
« ለዚህ የግብፅ ወረራ ምላሽ ዮሐንስ 4ኛ በሞሐመዳውያን ላይ “የመስቀል ዘመቻ“ አዋጅ አስነገረ። ንጉሡ ከጎጃምና ከሸዋ የማጠናከሪያ ኃይል እንዲመጣ አድርጎ ፣ጠቅላላው የሠራዊቱ ቁጥር 60,000 ደርሶ ነበር። ሁለቱ ሠራዊቶች በመጋቢት ወር 1876 ጉራዕ ላይ ተጋጠሙ። ግብፆች ምሽጋቸውን ዙሪያውን በጉድብ ሰንሰለት ስላጠሩት የኢትዮጵያውያኑን ጥቃት ለመከላከል አመችቷቸው ነበር። ከግጥሚያው መጀመሪያ ላይ ስለቀናው ተደፋፍሮ ሙላይ ሐሰን በልምድ የበሰለውና ሽማግሌው ወታደር ራቲቭ ፓሻ ተው እያለው ጠላቱን በግላጭ ገጥሞ እደመስሳለሁ ብሎ ከምሽጉ ወጣ። ይህ ውሳኔ ለግብፆች መጥፊያቸው ሆነ። የኢትዮጵያ ወታደር በቁጥሩ ከወራሪው ጦር እጅግ ከፍ ያለ ነበርና የውጊያውን ሰልፍ ጥሶ እየተወረወረ ከጠላቱ ምሽግ ውስጥ ገባ። በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጊያው ወደ መተላለቅ ተለውጦ የግብፅ ጦር በድንጋጤ ተውጦ ፈረጠጠ። ሙላይ ሐሰን ፓሻ ሩጦ ለማምለጥ ሲሞክር ተይዞ ከንጉሡ ፊት ቀረበ። ንጉሡም ድል የሆነበትን ቀን እንዳይረሳው ሲል ከክንዱ ላይ ሁለት መስቀል እንዲተኮስበት አደረገ። በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል የሰላም ውል ከተደረገ በኋላ ከዲቭ እስማኤል ፣ ሙላይ ሐሰን ፓሻና ሌሎችም በጉራይ ጦርነት ላይ ከሱ ጋር የተማረኩትን ከፍተኛ መኮንኖች ማስለቀቂያ ከፍሎ አስፈታቸው።»(ገጽ 289 እስከ 299፣“የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመሪያው እስካሁኑ ዘመን፣ጸሐፊዎች፦ አንድርዜይ ባርትኒስኪ እና ዮዓና ምንቴል-ኒየችኮ” ተርጓሚ፦ ዓለማየሁ አበበ 2003)

ስለሆነም በጉራዕ፤በጉንደት፤በስዋኪን፤በዶጋሊ፤በዓድዋ፤በማይጨው፤መመሳሰሉት ጦርነቶች እና በቅርቡም የትግሬው ወያኔ እና የኤርትራው ሻዕቢያ በጫሩት 70,000 የሚገመት ተጠያቂ የሌለው ሕይወት የበላ የጥላቻ ጦርነት ከሁሉም ወይንም ከከፊል የኢትዮጵያ ግዛቶች የሚኖር ሕዝብ የተካፈለበት ጦርነት ነበር። ወያኔዎች በሁለተኛ ጉባኤያቸው የኛ የትግሬዎች ገድል ብቻ ነው ብለው ያሉት በውሸት የተመሰረተ “የትግራይ ጦር ብቻ” የተሳተፈበት ጀግንነት ያሉትን ውሸትም ሆነ፤ የወያኔ ታሪክ ጸሐፊዎች ነን የሚሉን ትምክሕተኞቹ የትግሬ ብሔረተኞች በመጽሐፍቶቻቸው የሚዋሹት እና የሚመኩባቸው የተጠቀሱት የትግሬ ጦር ውሎ ጀብዱ ሁሉ የትግሬ ብቻ ሳይሆን ጦሩ በዚያን ዘመን ኢትዮጵያ ተብላ በምትታወቀው አገር ይኖሩ የነበሩ ዜጎች በጦርነቱ ተካፋይ እንደነበሩ ከላይ ለመከራከሪያ ያቀረብኩት የመረጃ ሰነድ ማለትም “የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመሪያው እስካሁኑ ዘመን፣ጸሐፊዎች፦ አንድርዜይ ባርትኒስኪ እና ዮዓና ምንቴል-ኒየችኮ” ተርጓሚ፦ ዓለማየሁ አበበ 2003 ያስረዳል።

የትግሬዎች እና የተጠቀሱት የአካባቢ ተሳታፊዎች የቁጥር ልዩነት ይችላል ወይ? አዎ ምናልባት ሊኖረው ይችላል። ያም በእርግጠኝነት ይህ ነው ማለት ባይቻልም ካራት ወይንም ከሦሰት ክ/ሃገራት የተውጣጡ ተዋጊዎች በቁጥር አነስተኛ ማሕበረሰብ ከነበረው ከትግራይ ጦር ሲነጻጻር ሊበዛ ወይንም እኩል ሊሆንም ይችልም ይሆናል። የጉራዕ/ጉንደት ጦርነት ግን ከጎጃምና ከሸዋ በብዛት የዘመተ መኖሩን በግልጽ ያሳያል። ጎንደርና ወሎ ያልተጠቀሱበት ምክንያት ሁለቱም በንጉሡ ቀጥተኛ ቁጥጥር ሥር የነበሩ በመሆኑ ተሳትፎአቸው ግልጽ ስለሆነ ነው።

አሁን መረጃው ሰጥቻለሁ። የወያኔ ትግሬ ጸሐፍት ጉረኞች በየመጽሕፍቶቻችሁ እና በየቃለ መጠይቃችሁ የምትነዙት አጉል ጉራ እና ታሪክ አደፍራሽነታችሁ ረገብ አንድትሉ በግራ ቀኝ የተጻፉ የታሪክ ሰነዶች አንብቡ። ለዚህም ነበር አፄ ዮሐንስ ‘የትግሬ ልጅ ሆይ” ሳይሆን ሲሉ የነበሩት ለጦርነት ሲዘጋጁ “የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ” ነበር እያሉ መላውን ግዛታቸው ያለው ሕዝብ ለጦርነት ጥሪ ሲያደርጉ የነበሩት። ለዚህም ነበር “የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ ልብ አድርገህ ተመልከት። ኢትዮጵያ የተባለች አንደኛ እናትህ ናት፣ ሁለተኛ ዘውድህ ናት፣ ሦስተኛ ሚስትህ ናት፣ አራተኛ ልጅህ ናት፣ አምስተኛ መቃብርህ ናት። እንግዲህ የእናት ፍቅር፣ የዘውድ ክብር፣ የሚስት ደግነት፣ የልጅ ደስታ፣ የመቃብር ከባቲነት እንደዚህ መሆኑን አውቀህ ተነሣ።“(አፄ ዮሐንስ ፬ኛ) ሲሉ የነበሩት።

ወያኔዎች የትግራይ ወያኔ ብሄረተኞች ከንጉሥ ዮሐንስ “የኢትዮጵያዊነት” ትርጉም ምን ማለት አንደሆነ ሊማሩት አልፈቀዱም። አለማፈራቸው ዛሬ ደግሞ ይባስ ብለው “ማንነት” ትግራዋይነት አንጂ “ኢትዮጵያ” የሚባል ማንነት የለንም መላት ጀምረዋል። ንጉሥ ዮሐንስ እያሉን ያሉት ግን “ኢትዮጵያ ማንነትህ ናት” -ኢትዮጵያ የተባለች አንደኛ እናትህ ናት፣ ሁለተኛ ዘውድህ ናት፣ ሦስተኛ ሚስትህ ናት፣ አራተኛ ልጅህ ናት፣ አምስተኛ መቃብርህ ናት። እንግዲህ የእናት ፍቅር፣ የዘውድ ክብር፣ የሚስት ደግነት፣ የልጅ ደስታ፣ የመቃብር ከባቲነት እንደዚህ መሆኑን አውቀህ ተነሣ።” ሲሉ በወርቃማው ‘ኢትጵያዊ ማነንት’ ትርጉማቸው ተርጉመውልን ቢሄዱም “የወያኔ ባንዳዎች” ወደ ቁልቁል ወደ መንደራቸው በመሸማቀቅ “ትግራዋይነት” አንጂ ኢትዮጵያዊ የሚባል ማንንት የለም፤ በማለት ወደ “ትግሬነት” ወደ “ኤርትራዊነት” ማንነት ወደ እሚሉት ደደቢታዊ እና ናቕፋዊ የግንጠላ አዝማሚያ እና መንደርተኛነትን አጥብቀው ማማንዠክ ይዘዋል።

የትግራይ ኦን ላይን ውሸታሞች በአማራ ሕብረተሰብ እና አርበኞች ላይ ያላቸው የጥላቻ መንፈስ ከኤርትራዊያኖቹ የባሰ ጥልቅ እንደሆነ ልብ ያለው በበሰለ ሕሊና የተከታተላቸው ታዛቢ የሚመሰክረው ቢሆንም ዛሬም ከሃያ ሁለት አመት በሓላም ጥላቸው እና ትንኰሳው ስላልበረደላቸው፤ በትግሬው አሉላ እና በአማራው በላይ ዘለቀ (አማራ እና ትግሬ የሚለው በሽታቸው ሲያወዳድሩ) መካከል ልዩነት ፈጥረው “አማራዎች” የአሉላን ክብር እንድያንስ አድርገዋል፡ እያሉ የአማራ ጸሐፊዎችን የሚከስሱት ውሸት እራሳቸው በራስ አሉላ ላይ እያደረጉት ያሉት ደባ እንዳይጋለጥ የሚያደርጉት ተንኰል ነው። የሚከተለውን ጉድ አንብቡ፤

“Tigrai Rep. officially disowns the indomitable lion of Dogali, Ras Alula” በሚል ርዕስ ወንድማችን ጌታሁን በቀለ የዘገበውን እንመልከት።

The Horn Times Newsletter, Dec 2, 2012
By Getahune Bekele

“ The great Abyssinian chief Ras Alula is at present a person of much interest to the Italians, and the Reforma is publishing a sketch of his life, in the course of which it is stated

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በቅረቡ ወደ ሚዲያ የመጡት የኤርትራው ወዲ ኢሳያስ አፈወርቂ በሚዲያ ቀርበው አንድ አንድ ነገር በማለታቸው፤ ከማን እናንሳለን በሚል ነው የሚሉ ሰዎች ጋር መስማማት የለብንም፡፡ አጋጣሚ ነው ብለን ማለፍ ካልፈለግን አጋጣሚ ባይሆንም አጋጣሚውን ለእኛም እንድ አንድ “እውቀት” የሚጨምር ነገር ልናገኝበት የምንችል አጋጣሚ አድርጎ መውስድ ግድ ይለናል፡፡ እውቀት የሚለውን ነገር ግን ልብ ልንለው የሚገባ ነው፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ምላሽ ተከትሎ ብዙ አስተያየት የተሰጠ ቢሆንም፣ የግል ዕይታዬን ማካፈል የተደጋገመ ቢሆን ጥሩ ነው ብዬ አመንኩ፡፡ ምክንያቱም በመሬት ላይ ካለና ከምናየው እውነትና እውቀት ጋር የተጋጨ ስለመሰለኝ፡፡
የቡድን አመራርን በተመለከተ የቡድን አመራር ነው ለሃያ ዓመት በፓርቲያችን ያለው ማለት አቶ መለስ እያሉም አመራር ላይ ነበርን ሊሉን ከሆነ ተሳስተዋል፡፡ ከህወሃት ክፍፍል በፊት (እነ ሰዬ፣ ገብሩ፣ ተወልድ፣ ወዘተ) በሚመክሩበት አጀንዳ እኛም ነበርን ሊሉን አይችሉም፡፡ በዚያን ጊዜ የቡድን አመራር በህወሃት ውስጥ እንደ ነበር እናውቃለን፣ ይህ በኢህዴግ ውስጥም ዘልቆ ገብቶ ነበር ማለት አይቻልም፡፡ ይልቁንም አንድ አንድ የህወሃት ሰዎች በየክልሉ ተቀምጠው የህወሃት ውሳኔ ያስፈፅሙ ነበር፡፡ ከህወሃት ክፍፍል በኋላ ነገሮች እንደተቀየሩ እሙን ነው፡፡ ከህወሃት የቡድን አገዛዝነት ወደ አቶ መለስ ዜናው እጅ ስልጣን ተጠቃሎ ነው የገባው፡፡ ለዚህም ነው አቶ መለስ ዜናዊን “ጠቅላይ” የሚባሉት፡፡ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ቦታውን ከያዙት በኋላ በጠቅላይነት የሚያማቸው የለም፡፡ እንደ እኔ ዓይነቱ ወደ ቡድን አሰራር ገብተዋል የሚል ግምት የያዝን አለን፡፡ ሌሎች ደግሞ ወደቀድሞ ቦታ ተመልስው ህወሃት ነው ከጀርባ ሆኖ ማርሽ የሚቀይረው ብለው ይጠራጠራሉ፡፡ እንዲህ ያለህ የተምታታ ግምት ስለአለ ነው በዘዴ በእርግጥ ጠቅላይ ሚኒስትር ነዎት?የሚል ሽንቋጭ ጥያቄ ያስነሳው፡፡
ኢህአዴግ በግልፅ እንደሚናገረው ተግባራዊ ነገር አድርጊያለሁ ብሎ የሚያምነው ከተሃድሶ በኋላ እንደሆነ የሚታወቅ ነው፡፡ ከተሃድሶ በኋላ ደግሞ አቶ መለስ ጠቅላይ የነበሩበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ ወቅት አቶ ኃይለማሪያምም ሆኑ ሌሎች ሰዎች ሹመት እንጂ ስልጣን አልነበራችሁም፡፡ ለምሳሌ አቶ ኃይለማሪያም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነበሩ፡፡ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ ጠቅላዩ የነበራቸው መረጃ በሙሉ ነበረኝ ምክንያቱም የቡድን አመራር ስለምንከትል ብለው አይዋሹኑም፡፡ ቢሉም በፍፁም አናምኖትም፡፡ በዚያ ደረጃ ተተኪ ልሆን እችላለሁ ብለው ዝግጅት እንዳልነበሮት የሚያሳብቀው እውነት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ድንገተኛ ሞት ቦታውን ሲይዙ ከሚሰጡት መግለጫ ለመረዳት የሚቻል ነበር፡፡ ለማነኛውም በቅጡ የኢህአዴግ የቡድን አመራር እንዲኖር ማድረግ ተገቢ ቢሆንም ወሳኝ ስብዕና ደግሞ ከጠቅላይ ሚኒስትር የሚጠበቅ መሆኑን ተረድተው የቡድንም የግለሰብም ወሳኝነት ተመጣጥነው የሚሄዱበት መስመር የግድ እንደሚል ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ በነገራችን ላይ የአሜሪካው ፕሬዝደንት በግላቸው እንደፈለጋቸው አይወስኑም፡፡ ይህን ለመረዳት ቢንላደንን ለመያዝ የተደረገውን ዘመቻ እንዴት በቡድን እና እንዴት በግል ኃላፊነት ወስደው እንደወሰኑ የሚያሳየውን ፊልም ይመልከቱት፡፡
ቴሌ እና የሚታለብ ላም
ይህን በተመለከት ዶክትር ካሱ ኢላላ ብለውት እስከ ዛሬ ድረስ ካደረጉት ስህተት እንደ አንዱ የሚቆጠር የነበረ ነው፡፡ ኢህአዴግ አፍ እንጂ ጆሮ የለውም የሚለውን በሚያጠናክር ሁኔታ ቃል በቃል ሲደግሙት በግሌ አዝኛለሁ፡፡ ምንም ጥርጥር የሌለው ነገር ቴሌ “በመንግሰት እጅም” ሆኖ አትራፊ ነው፡፡ ቴሌ አሁን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በነገሩን መረጃ መሰረት በመንግሰት እጅ ሆኖ 6 ቢሊዮን ብር ትርፍ ለልማት ያውላል ብለውናል፡፡ ያልገባቸው ነገር ግን ቴሌ በግል ይዞታ ቢሆንም ከዚህ ሶሰት እጥፍ የሚሆን ትርፍ ሊያተርፍ እንደሚችል ነው፡፡ ከዚህ ትርፍም መንግሰት ድርሻውን ያገኛል፡፡ በኢህአዴግ ሰፈር ያለው ችግር የልማት ባለቤት ህዝብ ይሁን ወይስ መንግሰት የሚለው ነው፡፡ የግል ባለይዞታዎች ከቴሌ ትርፍ ካተረፉ የብር ኖት አይበሉም መልሰው አዋጭ ነው ብለው ባሉት መስመር ኢንቨስት ያደርጉታል፡፡ ምን አልባትም ከመንግሰት በተሻለ አዋጭ መስመር ነው ስራ ላይ የሚያውሉት፡፡ ለዚህ ጉልዕ ምሰሌ በመንግሰት እጅ የሚገኙ የነበሩትን የቢራ ፋብሪካዎች አሁን ለመንግሰት እየከፈሉ ያሉትን ታክስና በኢኮኖሚ ውስጥ እየፈጠሩ ያሉትን መነቃቃት ነው፡፡ እነዚህ ተቋሞች በመንግሰት እጅም እያሉ አትራፊ ነበሩ፤ አሁን ግን የበለጠ አትራፊ ናቸው፡፡
በዋነኝነት የቴሌ በመንግሰት እጅ መቆየት የሚፈለገው ለልማት ካለው ፋይዳ እንዳልሆነ ይገባናል፡፡ በስልጣን ለመቆየት ግን እንዲህ ያለን ህዝቦችን የሚያስተሳሰር ቴክኖሎጂ በግለሰብ እጅ አስገብቶ የነፃነት በር ሆኖ እንዲያገለግል አይፈለግም፡፡ ለሃምሳ ዓመት መግዛት የሚፈልግ ፓርቲ በዚህ ደረጃ ወርዶ ለማፈን ቢሞክር ባህሪው ነው ብሎ መውሰድ ነው፡፡ በልማት ስም በተለይ ለገጠሩ ህዝብ ለማስፋፋት ብለው ሰበብ ከሰጡ በኋላ ግን የቴሌ ገንዘብ ለባቡር መስመር ዝርጋታ እየዋለ ነው ብለው የገጠሩን ህዝብ ለመጠቀሚያ ብቻ እንደሆነ ይፋ አድርገዋል፡፡ የቴሌው የህዝብ ግንኙነት በቅርቡ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አሁን በተያዘው ማስፋፊያ 85 ከመቶ የሚሆነው የሀገሪቱ ክፍል በኔትወርክ ይሸፈናል ብለዋል፡፡ ይህ ማለት ጠቅላላ ሀገሪቱን ለመሸፈን የቀረው ጥቂት ነው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ አገልግሎቱን
ግርማ ሠይፉ ማሩ
ከመንግሰት በተሸለ ጥራት ለሚሰጡ የግል ድርጅት አስተላልፉ፣ መንግሰት የመሰረተ ልማት ማስፋፊያና ቁጥጥር ላይ ለምን አይገባም
የሚለው መከራከሪያ አሁንም ለፊት ለፊት ጉንጭ አልፋ ጭቅጭቅ እንጂ ይህ ሊሆን የሚችለው በአብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ
መቃብር ላይ መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡ ይዘገይ ይሆናል እንጂ ይህ እንደሚሆን ግን ጥርጥር የለውም፡፡ ማለትም አብዮታዊ ዲሞክራሲ
አስተሳሰብ ወደ መቃብር ይወርዳል፡፡
እዚህ ጋ ሊሰመርበት የሚገባው ነገር የግል ባለሀብቱን ስብሰባ እየጠሩ የግሉ ዘርፍ ምትክ የሌለው እንደሆነ እናምናለን፤ ከግል ዘርፉ ጋር ጠብ የለንም የሚል መንግሰት ጠቅላይ ሚኒስትር “መንግሰት ብቻ ነው ይህን ትርፍ ለልማት የሚያውለው” ማለት እንዴት ያለ ተቃርኖ እንደሆነ ነው፡፡ በግለሰቦች (ሲደመሩ ህዝብ የሚሆኑት) እምነት የሌለው መንግሰት፤ የህዝብ ወኪል የሚሆን አይደለም፡፡ በህዝብ ስም ግን ይነግዳል፡፡ መንግሰት ብቻ ነው የሚያለማው የሚለውን ከወሰድን የአሜሪካ መንግሰት ከመከላከያ እና ከተወሰኑ ፓርኮች በስተቀር የመንግሰት የሚባል ነገር የለውም፡፡ በአሜሪካ ልማት የለም በቻይና ነው ያለው እንደማይሉ ተሰፋ አደርጋለሁ፡፡ ብዙ ሰው ቻይና ከአሜሪካ ቀጥሎ ግዙፉ ኢኮኖሚ እያሉ ሲሳሳቱ አሜሪካ ቻይናን 10 ዕጥፍ እንደምትበልጣት የምናውቅ አይመስላቸውም፡፡ ቻይና ከጃፓን በለጠች እንጂ አሜሪካ ጋር አልደረሰችም፡፡ ይህችን እንደ እግረ መንገድ ያዙልኝ፡፡ እርግጥ ነው የቻይና መንግሰት ሀብታም ነው፣ ህዝቡ ግን ድሃ፡፡ ምክንያቱም ፍልስፍናው መንግሰት ብቻ ነው የሚያለማው የሚል እና የኛዎቹም ቅጂያቸው እንደዚያ ስለሆነ ነው፡፡ ሰትራቴጂው ገጠሩን እዚያው ገጠር ለማሰቀረት እቅድ ከሌለ በስተቀር የገጠሩ ህዝብ አሁን የሚፈልገው ስልክ እና መብራት ይዛችሁለት በጫካ ስር መኖር ሳይሆን ከተሜነት ነው፡፡ ወደ ስልኩ እና መሰረተ ልማቱ መምጣት ይኖርበታል፡፡
የታክስ ምጣኔ እና የታክስ መሰረት ማሰፋት
ግብር በማይከፈልበት የቦርድ ክፍያ እና ሌሎች ገቢዎች ለሚደጎም ባለስልጣን ብዙ ግልፅ ያልሆነ ግን ደሞዝተኛውን በከፍተኛ ደረጃ እየጎዳ ያለው ከፍተኛ ታክስ የሚከፈልበት የደሞዝ ጣሪያ አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ አለመሆኑ ነው፡፡ በጋዜጠኞች የቀረበውም ጥያቄ ይህን የሚመለከት እንጂ አጠቃላይ የታክስ ሪፎርም እየተባለ ለረዥም ጊዜ የተያዘ የተሰፋ ፕሮጀክት ምንደረሰ የሚል አይደለም፡፡ ደሞዝተኛውን ደሞዝ ጨመርንልህ ብሎ በግብር ከመቀማት በተግባር የታክስ ምጣኔውን ማስተካከል የዘገየ ብቻ ሳይሆን የዜጎችን የስራ ተነሳሸነት እየገደለ ያለ በምድር ላይ ያለ ሀቅ ነው፡፡ የነዳጅ ዋጋ በዓለም አቀፍ ገበያ ጨመረ ብሎ በየጊዜው የነዳጅ ዋጋ የሚጨምር ፣ ይህንንም ተከትሎ የትራንስፖርት ዋጋ ላይ ጭማሪ የሚያደርግ መንግስት በቀጥታ ከደሞዝተኛ ላይ የደሞዝ መቀነስ እንደሆነ መረዳት አዳጋች አይደለም፡፡ ለኢትዮጵያ ሲቪል ሰራተኞች የመነሻ ደሞዝ ከፍ ማድረግ (ዝቅተኛ የደሞዝ መጠን መወሰን) እና የግብር ማሰከፈያውን የገቢ መጠን ከፍ ማድረግ አፋጣኝ ምላሽ የሚሻ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ዜጎች የሚያገኙትን ገቢ እየተከታተለ የሚቀማቸውን አይፈልጉም፡፡ መንግሰትም ቢሆን፡፡ በታክሰና ግብር ስም እየቀሙ እኔ ለልማት አውለዋለሁ ማለት ከስድብ አይተናነሰም፤ ዜጎችም ሰርተው የሚያገኙትን ገንዘብ ለልማት ለዚያውም ለዘላቂ ልማት ነው የሚያውልቱ፡፡ ከዜጎቹ እየቀማ ዜጎችን በማደኽየት የሚበለፅግ መንግሰት ልማታዊ ነኝ ሊል አይችልም፡፡
ሊስትሮም ሁን ብባል ወረዳም ሂድ ከተባልኩ አደርጋዋለሁ፤
ሊስትሮም ሁን ብባል ወረዳም ሂድ ከተባልኩ የምሄድ ወታደር ነኝ፡፡ ይህ አባባል በኢህአዴግ ሰፈር የግል ነፃነት ስለሌለ ምን ያህል እውቀት እንደሚባክን ነው የሚያሳየው፡፡ ልክ ነው በሚቀጥለው ዙር ወደ ክልል ቢባሉ ሊሄዱ ይችላሉ፡፡ አሁኑ በምክትል ጠቅላይ ሚኒሰትር ማዕረግ የሚያገለግሉት ቱባ ባለስልጣን ወደ ክልል ብሎም ወደ ዞን ሲላኩ እሺ ብለው መሄዳቸው የዚሁ ማሳያ ነው፡፡ ከክልል ፕሬዝደንትነት ወደ ጠቅላይ ሚኒሰትረ አማካሪነት ተመሳሳይ የምደባ ዝውውር ነው፡፡ ይህ ግን በምንም ምክንያት ተገቢ ነው ብሎ መውሰድ አይቻልም፡፡ ቅዱስ መፅሐፍ ምሳሌ 4፡18 “የጻድቃን መንገድ እንደ ንጋት ብርሃን ነው፤ ሙሉ ቀን እሲከሆን ድረሰም እየጨመረ ይበራል” ይላል፡፡ ምን ነው የኛ መሪዎች ቁልቁል ማየት ፈለጋችሁ፡፡ የሌሎች ሀገር መሪዎች ከመሪነት ሲለቁ ተከታይ ቦታቸው ሊሰትሮ መሆን ወይም የእርሱ ተመጣጣኝ አይደለም፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ አማካሪነት ነው፡፡ ዛሬ ክሊንተን አንድ ሰዓት ንግግር አድርገው የሚያገኙት ገንዘብ ከወረዳ በጀት በስንት እጥፍ እንደሚልቅ ነጋሪ የሚፈልግ አይመስለኝም፡፡ ይህን ብቃት አረጋግጫለሁ ያለ ሰው ወረዳ ለመሄድ አያስብም፡፡ በምደባ የተገኘ ስልጣን ግን በምደባ ሊነሳ ይሚችል ነው፡፡ በምደባ ከሚገኝ ስልጣን ያድነን፡፡ እኔ ግን ከዚህም በላይ የገባኝ፣ የጋራ አመራር አለ ብሎ ከግል ተጠያቂነት ለመሽሽ እንዳይሆን የሚል ፍርሃትም አለኝ፡፡ ሌላው ግን አብዛኛው ሹመኛ ነገ ወረዳ ልወረወር እቻላለሁ በሚል ስጋት ተግቶ በዘረፋ ይሰማራል፡፡ የብቃት ከግምት መውጣትና የምደባ ሹመት የሚያመጣው ጣጣ እጅግ ብዙ ነው፡፡ ለዛሬ ይብቃን ቸር ይግጠመን፡፡
ኢትዮሚድያ – Ethiomedia.com

የብልሹ አሠራርና ሙስናን ችግር በዐደባባይ የተናገሩ የመጀመሪያው ፓትርያርክ ናቸው ጽኑ አቋም ስለሚጎድላቸው ለጣልቃ ገብነት የተመቹ ኾነዋል ጣልቃ ገብነቶችን መቋቋምና የቅ/ሲኖዶሱን ልዕልና ማስከበር ይጠበቅባቸዋል የተጠጓቸውን ‹አማካሪዎች› ማንነት መለየትና ዙሪያቸውን መፈተሽ አለባቸው የተሟላና ብቃት ያለው የአማካሪ መዋቅር ያስፈልጋቸዋል (አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፫ ቁጥር ፯፻፴፯፤ የካቲት ፳፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.) የካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም.፤ ለስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ …

የሃገራቸው ነገር ሲነሳ የሚከነክናቸው ወገኖቻችን ኢትዮጵያ ላለባት ችግር መፍት ሄው ምንድነው? እያሉ ኣጥብቀው ሲጠይቁ ይደመጣል። መፍትሄውም ብቻ ሳይሆን ችግሩ ማለትም እውነተኛው ችግር የት ላይ ነው ያለው? ብለውም ኣጥብቀው ሲደመሙ ይታያል። በዛሬዋ ኣጭር ጽህፌ በነዚህ መራራ ጥያቄዎች ዙሪያ ቁንጥል ኣሳብ ለማቀበል ኣስቢያለሁ። በርግጥም ሁላችን ኢትዮጵያዊያን የሆንን ችግሩ ምንድነው? ብለን ከጠየቅን ኣንዳንዶች ሊገረሙብን ይችላሉ። የችግሩ ተካፋይ ሆነን […]

Image

ብርሃኑ ሃይለስላሴ ይባላል። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ እያለ ጥናቱን ትቶ በካድሬነት ተግባር የተሰማራ እንደነበር አውቃለሁ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የምንማር የትግራይ ልጆችን እየሰለለ ነበር የሚውለው።

ተመረቀና በህወሓት አባልነቱ መሰረት የትምህርት ዉጤቱ ግምት ዉስጥ ሳይገባ፣ ሳይወዳደር (ሌሎች ብቁ ሰዎች እያሉ) በእምባ አለጀ ወረዳ የጤና ጥበቃ ሐላፊ ተደርጎ በፓርቲ በመሾሙ ዓዲሽሁ ከተማ ገባ። በዓዲሽሁ ከተማ ብዙ ሴቶችን ደፈረ። ህዝብ ጮሆ። ሰሚ የለም። ምክንያቱም ሐላፊ ነው።

ሴቶችን በመድፈር ወንጀል ከመክሰስ ይልቅ ሌሎች ሰራተኞች ያላገኙት የማስተርስ ትምህርት ዕድል ተሰጠው። ሴቶች ስለደፈረ ተሸለመ ማለት ነው። በጦላይ ለስልጠና ተልኮ እዛም ሌላ ሴት ደፈረ። የተደፈረች ሴት የሕግ ከለላ አጥታ ከሱ ጋር እንድትታረቅና ክስ ላትመሰርት ተገደደች።

ከስልጠና በኋላ ህወሓቶች የማይጨው ለምለም ካርል ሆስፒታል CEO አድርገው ሾሙት። እነሱ ምን ይሳናቸዋል!? በማይጨው ከአንድ ዓመት ባልበለጠ ግዜ ዉስጥ አስራ አራት ሴቶችን ደፈረ፤ ስልጣኑን ተገን በማድረግ። ሴቶች አቤት ይላሉ። ግን ሰሚ የለም። በማይጨው ሰው በመኪና ገጨ። ራሱ ሰው ገጭቶ ሽፌሩ እንደገጨ ለማስመሰልና ከቅጣት ለመዳን ከሽፌሩ ጋር ተዋዋለ። ክስ ተመስርቶበት፣ በፖሊስ ተይዞ በስድስት ሺ ብር ዋስ ተለቀቀ።

ይህን ሁሉ ግፍ ሲፈፅም የማይጨው ኗሪዎችና የሆስፒታሉ ሰራተኞች ቅሬታ አሰሙ። ረበሹ። ተሰበሰቡ። የሆስፒታሉ ሰራተኞች ተሰብሰበው ከፓርቲ አባልነቱ እንዲወገድ ጠየቁ (ምክንያቱም የገዢው ፓርቲ አባል በመሆኑ ስልጣኑ ተገን አድርጎ ነው ግፍ እየፈፀመ ያለው ከሚል እሳቤ)። ከስራ (ከሐላፊነቱ) ታግዶ በፖሊስ እንዲያዝ ወሰኑ። ቢሮው ታሽጎ ሁለቴ ቁልፍ ሰብሮ መግባቱ ተረጋገጠ። ማንም አልጠየቀውም።

አቶ ብርሃኑ ሃይለስላሴ በሰራተኞቹ ስብሰባ ቀርቦ ሁሉም የተጠቀሱት ወንጀሎች መፈፀሙ አምኖ ይቅርታ ጠየቀ። በተበዳዮቹና ሰራተኞቹ ግፊት በፖሊስ እንዲታሰር ተደረገ። ህዝቡ ተረጋጋ። እኛም “ኮርማው ታሰረ!” ብለን በፌስቡክ ፃፍን። ህወሓቶች ለምን አስራ ስምንት ሴት እስኪደፍር ድረስ ዝም አሉት? ሕግ ለካድሬዎችስ አይሰራም ወይ? ብለን ጠየቅን። የህወሓቶች አድሎአዊ አሰራር ወቀስን። መታሰሩ ግን ጥሩ መሆኑ ጠቆምን።

አቶ ብርሃኑ በፖሊስ ከታሰረ ከሁለት ቀናት በኋላ መለቀቁ ሰማሁ። መለቀቁን አስመልክቼ በፌስቡክ ፃፍኩ። መለቀቁ ግን በሌላ አካል አልተረጋገጠም ነበር።

አሁን ከአስራ ስምንት ሴቶች በላይ የደፈረ ባለስልጣን ምን ቢቀጣ ጥሩ ነው!? አሁን በደረሰኝ መረጃ መሰረት አቶ ብርሃኑ አልታሰረም። ወደ ሌላ የስራ ቦታ ተዛወረ እንጂ። ህወሓቶች አንድ ባለስልጣን ወንጀል ከሰራ ባለስልጣኑ ከመቅጣት ይልቅ ወደ ሌላ የስራ ሐላፊነት ይቀይሩታል። ቅጣት ግን የለም። ሽልማት እንጂ።

አሁን አቶ ብርሃኑ ከዞን (ከማይጨው) ወደ ክልል (መቐለ) የስልጣን እርከን አድጎ በመቐለ የትግራይ ክልል የጤና ቢሮ የHMIS ዲፓርትመንት expert ሁኖ በሙሉ ደሞዝና የተሻለ የሐላፊነት ደረጃ እየሰራ ይገኛል። ይህን ጉዳይ የማይጨው ለምለም ካርል ሆስፒታል ሐላፊዎች አረጋግጠውታል። ለምን የሚል ጥያቄም አስነስተዋል። አሁን በማይጨው ሆስፒታል ሰራተኞች ጥሩ ስሜት የለም።

አሁን እንደሰማነው ግን ከእሰር የተፈታው በህወሓቶች ነው። በክልል ጤና ቢሮ እንዲሰራ ትእዛዝ ያስተላለፈውም አቶ ሃይሉ አስፈሃ የተባለ የደቡባዊ ዞን ዋና አስተዳድሪና የማይጨው ለምለም ካርል ሆስፒታል የቦርድ ሰብሳቢ ነው። የሆስፒታሉ ሰራተኞች ይሁኑ የቦርዱ አባላት ሳይሰበሰቡና ምንም መረጃ ሳይኖራቸው አቶ ሃይሉ አስፈሃ (የቦርዱ ሰብሳቢ) ግን የቦርዱ ዉሳኔ እንደሆነ አድርጎ ደብዳቤ በመፃፍ በክልል ጤና ቢሮ እንዲቀጠር ማድረጉ ለማረጋገጥ ተችሏል።

ባሁኑ ሰዓት በማይጨው ከተማ ኗሪዎችና ለምለም ካርል ሆስፒታል ሰራተኞች በከባድ ቀውስ ዉስጥ እንደሚገኙ ለማወቅ ችያለሁ። የማይጨው ህዝብ በዋና አስተዳዳሪው አቶ ሃይሉ አስፈሃ ከፍተኛ ቅሬታ እያነሳ ሲሆን ህወሓቶች ለህዝብ ያላቸው ንቀት እያሳዩን ነው በሚል የተቃውሞ መንፈስ እንዳለ ከማይጨው ኗሪዎች የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል።

አይ ህወሓቶች መቼ ነው ለህዝብ ደህንነት የምትቆሙ? በትግራይ የሚፈፀሙ አስተዳደራዊ በደሎች ቢጋለጡኮ ስንት ጉድ በሰማን ነበር! ይህን ጉዳይ እስከመቼ እንችለዋለን?!

በህወሓት እምነት የለኝም። ከዚህ በላይ ምን ሊያደርገን ይችላል!? እናንተስ?

It is so!!! ABRHA DESTA

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ሽብርተኛ ነህ በሚል መስረት የሌለዉ ክስ ተከሶ የ18 አመት እስራት ፣ በፖለቲካ ዉሳኔ እንደተፈረደበት ይታወቃል። የአሜሪካው የዊጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይሄን ይቃወማሉ። ጋዜጠኛ እስክንደር ነጋን፣ ለነጻነቱ የጻፈ ሲሉ፣ ከሌሎች አንጋፋ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እኩል አስቀምተዉታል። የጆን ኬሪ ይፋዊ ዘለፋ፣ የጋዜጠኛ እስክንደር ሆነ የሌሎች በርካታ ጋዜጠኞችና የሰላማዊ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች መታሰር፣ ኢሕአዴግ በአገሩ ካሉ […]

የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር፣ በአሜሪካ ካሉ የድጋፍ ማህበራት ጋር ወደ ሁለት ሰዓት የሚጠጋ ሰፊ ዉይይት በቴሌኮንፈራንስ አደረጉ። ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራዉ ፣ የአንድነት ፓርቲ እያደረጋቸው ስላለው ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች ሰፋ ያለ ሃታተ የሰጡ ሲሆን፣ ከስብሰባው ተሳታፊዎች በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጠዋል። «በዉጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ በአካል ርቆ ቢገኝም ልቡ አገር ቤት ነዉ። ኢትዮጵያን በልቡ ይዞ የሚኖር […]

በብሄራዊ ትያትር አካባቢ አንዲት አነስተኛ ምግብ ቤት ነበረች። «ገሊላ ምግብ ቤት» ትባል ነበር። በአዲስ አበባ «ቁምራ» ከመግባቱ በፊት በአካባቢው ያሉ የመንግስት ሰራተኞች በምሳ ሰዓት ይህችን ምግብ ቤት ያጨናንቋት ነበር። ቁምራን የማታውቁ ካላችሁ፤ ለጽድቅ የሚደረግ መንፈሳዊ ጾም እንዳይመስላችሁ። እድገትና ትራንስፎርሜሽኑ ያመጣው አዲስ ክስተት ነው – ቁርስ ምሳና ራት በአንድ ጊዜ የመመገብ ዘዴ። «ኑሮ በዘዴ፣ ጾም በኩዳዴ» […]

ጀርመን በአፍሪቃ ብዙም የቅኝ አገዛዝ ታሪክ የሌላት ልትመስል ትችል ይሆናል። የታሪክ መዛግብት የሚያሳዩት ግን ሌላ ነው። ጀርመን እአአ በ1884 ምዕራባውያን ኃይላት አፍሪቃን በመካከላቸው የተከፋፈሉበት ጉባዔ የተካሄደው በርሊን ውስጥ ነበር።

Coalition for Equitable Land Acquisitions and Development in Africa በምህጻረ ቃል CELADA በመባል የሚታወቀው በካናዳ ኦታዋ ውስጥ የተቋቋመ ድርጅት በአፍሪካ እየተኪያሄደ ያለውን የመሬት ቅርምት አስመልክቶ በርካታ የፓርላማ አባላት፣ የተራድኦ ድርጅት ሃላፊዎች የዩኒቨርሲቲ መምህራን በተገኙበት በአፍሪካ በኢንቨስትመንት ስም የሚደረገውን የመሬት ቅርምትና ካናዳ ልትይዘው የሚገባትን ፖሊሲ በተመለከተ በኦታዋ ፌብሩዋሪ 25 ቀን 2014 ዓም የተሳካ ስብሰባ አድርገዋል። በሚሊየን […]

የአድዋ ድል ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የማንነታችን መሰረትና የህልውናችንም መገለጫ ብቻ ነው አልልም ። ዓድዋ ለመላው የጥቁር ህዝብ የነፃነት ተምሳሌትና የአርነት ምንጭ ስለመሆኑ የታሪክ መዛግብትም ሆኑ ባእዳን የታሪክ ልሂቃን ሳይቀር የሚመሰክሩት ሃቅ ነውና ። በዓድዋ የጥቁር ዘር አትንኩኝ ባይበት ሲረጋገጥ የጥቁር ዘር ለነጻነቱ ቀናኢ መሆኑን ለአለም የታየበት መሆኑም የሚታበል አይደለም ! የዚህ ታላቅ ድል ባለቤቶች ደግሞ ኢትዮጵያውያን […]

ኢቲቪ የሕዝብ ሜዲያ ነው። በሕገ መንግስቱ መሰረት ለኢሕአዴግ ሳያደላ ገለልተኛ በሆነ መንገድ እዉነትን መዘገብ ነበረበት። ነገር ግን ከሰባ እስከ ሰማኒያ የሚጠጋዉ ሕዝብ የተገኘበትን ታሪካዊ የባህር ዳሩን ሰልፍ አሳንሶ ለማቅረብ፣ ሰልፉ ከተበተነ በኋላ፣ ሁሉም ወደ የሰፈሩ በሚሄድበት ጊዜ የተነሱ ፊልሞችን በማሳየት፣ ወደ ሰማኒያ ሺህ የሚጠጋዉን ሕዝብ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ብቻ እንደሆነ ለማስመሰል የተሞከረበት ሁኔታ ነዉ፣ በኢቲቪ የታየው። […]

(ሐመር፤ ፳፩ኛ ቁጥር ፲፤ የካቲት ፳፻፮) ዳዊት አብርሃም የካቲት ፮ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የተቋማዊ ለውጥ አመራር የአደረጃጀትና አሠራር ጥናት ተጠናቅቆ ርክክብ ተካሒዷል፡፡ የጥናቱን አጠቃላይ ሒደትና ወደፊት ሊገጥመው የሚችለውን ተግዳሮት ከትንታኔ ጋራ ይዘን ቀርበናል፡፡ *                        *                       * የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር የሠለጠነ ሊኾን ይገባዋል፡፡ በቤተ ክርስቲያን የተንሰራፋው ሙስናና ብልሹ አሠራር እንዲሁም የሥነ ምግባር …

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ……….. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይድነቃቸው ከበደ ‹‹ የኢትዮጵያ ሃየር መንግድ ለአፍሪካ ኩራት ነው ›› ሲባል ከቃላት መፈክርነት ባለፈ የአውነትም ኩራት ስለመሆኑ ጥርጣሪ  የሚያድርባቸው ዜጎች እንደሚኖሮ እገምታለው፡፡ ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ አየር መንግድ በረዥም ታሪኩ ውስጥ ከሌሎች የአፍሪካ …

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ……….. Read more »

ጉባኤዉ በጋራ ያዘጋጁት የአሜሪካ የዓለም ተራድኦ ድርጅት USAID  የአሜሪካ የመከላከያ ስጋት ቅነሳ ኤጄንሲ የአሜሪካ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና የቅርብ ምስራቅና ደቡብ ኢስያ እስትራቴጂክ ጥናት ማእከል ናቸዉ። 

ከየካቲት 16  እስከ 20 በአዲስ አበባ የተካሄደዉ አዉደ ጥናት ጽንፈኛ መልክቶችን መግታት ላይ ያተኮረ መሆኑ ታዉቋል። በተለይ በአፍሪቃ ቀንድ አልሸባብና አልቃይዳ ጽንፈኛ የአመጽ መልክቶችን በማስተላለፍ በስም የተጠቀሱት ድርጅቶች ናቸዉ።

በአፍሪቃ እስትራቴጂክ ጥናት ማእከል፣ የተሻጋሪ ስጋቶችና ጸረ ሽብር ኤክስፕርት Benjamin P. Nickels  በአፍሪቃ ቀንድና በሌሎች አካባቢዎች ለጽንፈኝነት አመጽ መፈጠር የተለያዩ ምክንያቶች እንዳሉ ገልጸዋል። ከእነዚህም መካከል ከአስተዳደር ጋ በተያያዘ የሚፈጠሩ ችግሮች፣ ድህነት እና…

ዩጋንዳ በቅርቡ ያፀደቀችው ግብረ ሰዶማዊነትን የሚቃወም ህግ ዓለም ዓቀፍ ትችት አስከትሏል ። አንዳንድ ምዕራባውያን ሃገራት ለዩጋንዳ የሚሰጡትን እርዳታ እያገዱ ነው ። የጀርመን የልማት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በበኩሉ የበርሊን መንግሥት ፣ የልማት እርዳታ ቅነሳ ከማድረጉ በፊት ጥንቃቄ የተሞላበት ክትትል እንደሚያደርግ አስታውቋል ።

በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል በተደረገው የድንበር ጉዳይ ስምምነት መሰረት ኢትዮጵያ ወደግዛቷ 62.6 ኪሎ ሜትር ዘልቆ የሚገባ እና በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የሚያፈናቅለውን የመሬት ርክክብ በምስጢር መፈጸሟን ተከትሎ በዚሁ ሱዳን በምትረከበው ድንበር አከባቢ የመሬት ጥያቄ የሚይነሱ የሚያምጹ እና የሚሸፍቱ ሊኖሩ ይችላሉ በሚል ወያኔ የሱዳን ሰራዊት እና የራሱ ምልምል የሆኑ ትውልዳቸው ሱዳን የሆነ ኢትዮጵይውያንን አሰልጥኖ ህገወጦችን መቆጣጠር በሚል ሽፋን የድንበር አከባቢ ተወላጆችን ለማስመታት በዝግጅት ላይ መሆኑ ታውቋል::

ይህ ይቋቋማል የተባለው የጋራ የጦር ሰራዊት ህገወጥ ብሎ የፈረጃቸውን እና የመሬት ጥያቄ ሊያነሱ ይችላሉ ተብለው የሚገመቱትን የአማራ ገበሬዎች ለመምታት የታቀደ እና እንዲሁም ይህንን ተከትሎ የተቃዋሚ ድርጅቶች አማጺያን ሰርገው ይገባሉ በሚል ስጋት የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳን ወያኔ ወደ ካርቱም ልኮ ሚኒስትሩ ሳምንት ካርቱም ሰንብተው ወደ ሃገር ቤት መጥተዋል::

በሰሜን ጎንደር በምእራብ ጎጃም በቤንሻንጉል እና በጋምቤላ አከባቢዎች ወያኔ ፋታ የማይሰጡ የለውጥ ጥያቄ ያላቸው ታጣቂ አማጽያን ጦር ወድረው እየተኮሱበት መሆኑን ያማረረው ኢሕኣዴግ የሱዳንን መንግስት በመማጸን የጋራ የጦር ሰራዊት በማቋቋም በጀቱን ኢሕኣዴግ ከህዝብ ቀረጥ ከሚከፍልበት ገንዘብ የሚሸፍን መሆኑ ተረጋግጧል::ምንሊክ ሳልሳዊ

እስቲ የተወሰኑ አመታት መለስ ብለን እናስብ፤ የኢንተርኔት አገልግሎት ባልነበረበት ጊዜ። ማንኛውንም መልዕክት ይሁን መረጃ ለማግኘት ከባድ እና ጊዜን የሚወስድ ነበር። የኢንተርኔት አገልግሎት ለትምህርት፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር ለመገናኘትም ይሁን ዜና እና መረጃን ለማግኘት ምን ያህል ጠቅሞናል? ጉዳቱስ እንዴት ይገለፃል?

ዩጋንዳ በቅርቡ ያፀደቀችው ግብረ ሰዶማዊነትን የሚቃወም ህግ ዓለም ዓቀፍ ትችት አስከትሏል ። አንዳንድ ምዕራባውያን ሃገራት ለዩጋንዳ የሚሰጡትን እርዳታ እያገዱ ነው ። የጀርመን የልማት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በበኩሉ የበርሊን መንግሥት ፣ የልማት እርዳታ ቅነሳ ከማድረጉ በፊት ጥንቃቄ የተሞላበት ክትትል እንደሚያደርግ አስታውቋል ።

ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት (HRW) ደቡብ ሱዳን ውስጥ ሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች የጦር ወንጀል በመፈጸም ላይ ናቸው ሲል አጋለጠ። በፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በሚመራው የደቡብ ሱዳን መንግሥት ወታደሮችና ፣ የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ሪኤክ

ትላንት የጥላቻ ንግግርን የተመለከተ ጥናት ማሟያ ውይይት ላይ ተሳትፌ ነበር። በርዕሰ ጉዳዩ ላይ በሰፊው የምመለስበት ቢሆንም፥ ቀብዱን ግን እነሆ፦

ርዕሱ በኢሕአዴግ እና በደጋፊዎቹ አተረጓጎም “የጥላቻ ንግግር” ተብሎ ሊመደብ ይችላል። አንድ የዴሞክራሲ ሕልመኛ ርዕሱ ላይ የተጠቀሰውን ዓ/ነገር ቢናገር ኢ-ዴሞክራሲያዊም ሆነ ጥላቻ ሰባኪ አያሰኘውም ባይ ነኝ እኔ ግን። እኔ ራሴ ርዕሱ ላይ የተጻፈውን ያለምንም ጥላቻ ከውስጥ ፍላጎቴ ነው ያፈለቅኩት።

ከዴሞክራሲ ዐብይ ባሕርያት አንዱ ገዢ ፓርቲዎች ወርደው የሕዝብ ምርጫ በሆኑ ተቃዋሚዎች መተካት የሚችሉበት እና ገዢ የነበሩ ተቃዋሚ ሆነው የሚሮጡበት ስርዓት ማመቻቸት ነው። ስለዚህ ለኔ ኢትዮጵያ ለዴሞክራሲያዊነት መፍጨርጨሯ ሐቀኛ ነው ልል የምችለው ኢሕአዴግ ወርዶ ተቃዋሚ ሆኖ ሳየው ነው።

የጥላቻ እና የፍቅር ንግግሮች የሉም ማለት አልችልም። ነገር ግን የጥላቻም ይሁን የፍቅር ንግግሮች ዋጋቸው ከአንድ ክበብ አያልፍም። ለምሳሌ ኢትዮጵያ ነክ የአገር ውስጥ እና የውጭ ሚዲያዎች በባሕሪያቸው መድባቸው ብባል በሦስት እመድባቸዋለሁ፦
1ኛ) አፍቃሬ-ኢሕአዴግ፣
2ኛ) ኢሕአዴግን-አያሳየኝ እና
3ኛ) I-don’t-know-what-to-doዎች በማለት።

የመጀመሪያዎቹ [አፍቃሬ-ኢሕአዴግ]ዎቹ ዋነኛ ሥራቸው በማንኛውም መንገድ ኢሕአዴግን ማንቆለጳጰስ እና ከተቃዋሚዎች ክፉ ዓይን መጠበቅ ናቸው። አዳም ሲፈጠር ጀምሮ “በስም መስጠት ነው (naming)” ነው ሥራውን የጀመረው እንዲሉ እኔም በዚህ ምድብ የምፈርጃቸውን ጥቂቶች ልዘርዝር፤ ኢቴቪ፣ ዛሚ ኤፍኤም፣ ኢትዮ-ቻናል፣ ትግራይ ኦንላይን እና ወዘተ ናቸው።

ሁለተኛው ምድብ ውስጥ የሚገኙት [ኢሕአዴግን-አያሳየኝ]ዎች ደግሞ የሚደግፉት (የሚያፈቅሩት) የተለየ የተቃዋሚ ቡድን የላቸውም፣ የሚራሩለት እንጂ። ነገር ግን ያለምንም ጥርጥር ኢሕአዴግን አይወዱም። ስለዚህ ሥራቸው ኢሕአዴግን መተቸት ነው። እነዚህ ውስጥ ኢሳት፣ ፋክት፣ ኢትዮጵያን ሪቪው እና ወዘተ ይገኛሉ።

ሦስተኛው ምድብ [I-don’t-know-what-to-do]ዎች ውስጥ ያሉት ደግሞ በመሐል ቤት ይዋልላሉ። ለዚህ ቡድን አሪፍ ምሳሌ የሚሆኑት ደግሞ አዲስ አድማስ ጋዜጣ እና ሸገር ኤፍ ኤም ናቸው። በተረፈ ጥቂቶች ብቻ ለመፈረጅ የማይመች የሚዲያ ሥራ እና ሊረዱት የሚከብድ የአቋምና አቀራረብ ልዩነት ያሳያሉ።

ለምን እነዚህን ፍረጃዎች እና ስየማዎች ማድረግ አስፈለገኝ? ምክንያቱም የጥላቻ ንግግሮች በማን፣ እንዴት እንደሚተረጎም ቀላል ማስረጃ ስለሚሆነኝ ነው። ምድብ አንድ ውስጥ ለሚገኙ ማንኛውንም ዓይነት ኢሕአዴግ ላይ የተሰነዘረ ትችት የጥላቻ ንግግር ነው።
ምድብ ሁለት ውስጥ ለሚገኙትም ከኢሕአዴግ አፍ የሚወጣ ሁሉ ክፉ ነገር ነው። ሦስተኛው ምድብ ከቻለ ሁሉንም ለማስደሰት ካልቻለ ሁሉንም ላለማስከፋት ይፈጨረጨራል። በመሐል ቤት እውነት ማደሪያ ታጣለች። ሁሉም ለዓላማው እጇን ይጠመዝዛታል።

በአገራችን የጥላቻ ንግግር የሚባሉት ሁሌም ከጥላቻ የመነጩ ላይሆኑ ይችላሉ። በባሕላችን የሰውን ስህተት ፊት ለፊቱ መንገርን እንደአለመከባበር የሚያስቆጥር ስህተት ነው። ስለዚህ የአንድን ሰው ጉልህ እንከን እንዲህ ነህ ብሎ መንገር በጣም አስደንጋጭ ነው የሚሆነው። እንዲያውም በጠብ ወቅት ብቻ የሚከሰት ነገር ነው። ስለዚህ በትልቁ (በፓርቲና በፖለቲካዊ አመለካከት ላይ) ሲሰነዘር የእርምት አስተያየት መሆን ቀርቶ የትችት ማዕረግ እንኳን አያገኝም። የጥላቻ ይመስላል (ይባላል)።

ነገር ግን፤ ድክመትን እየሸሸጉ ብርታትን እንደመንገር ያለ አደገኛ ንግግር (dangerous speech) አይቼም ሰምቼም አላውቅም። ለግለሰብም ይሁን ለቡድን ግብዝነት ይዳርጋል። ድክመት ሲነገረው እልል ብሎ በፈገግታ ተጉመጥምጦ የሚውጥ ግለሰብም ይሁን ቡድን ገጥሞኝ አያውቅም፤ ከትችቱ አለመማር ግን እየሰሙ አይቻልም፤ ከስህተት ላለመማር መፍትሔው እንደኢሕአዴግ ተቺውን ማፈን ብቻ ነው። ትችት ካደመጡት ግን ምናልባት ለመዋጥ ጊዜ ይወስድ ይሆናል እንጂ ዘልቆ መቆጥቆጡ አይቀሬ ነው።

ይሄ ሁሉ ግን ስለጠሉ ብቻ የሚተቹ፣ ስለወደዱ ብቻ የማይሞገሰውን የሚያወድሱ የሉም ማለት አይደለም። ጥላቻና ፍቅርም ምክንያታዊ አይሆኑም ማለት ይከብዳል። ነገር ግን ክርር ያሉት የሥነ ልቦና ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል።

የጥላቻ ንግግርን መብት ከሐሳብን የመግለጽ መብት ለይቶ ለማስቀረት ሁነኛው መፍትሔ የማንፈልገውን ብቻ ሳይሆን የምንፈልገውንም ጭምር ማወቅ አለብን፤ አራማጅ ተራማጅነታችንም በመርሕ እንዲመራ ማድረግ መድኃኒቱ ነው።

  ሰሞነኛ ጉዳዮችን በወፍ በረር አንቀጾች ስንቃኛቸው ጽሁፉን በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።  ሰሞነኛ ጉዳዮችን በወፍ በረር አንቀጾች ስንቃኛቸው ይሄይስ አእምሮ ([email protected])  መግቢያ “እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች አሉ፤ እንዲያውም እርሱ የሚጸየፋቸው ሰባት ናቸው፤ እነርሱም፡- ‹በንቀት የሚመለከት ዐይን፤ ሐሰት የሚናገር ምላስ፤ …

ሰሞነኛ ጉዳዮችን በወፍ በረር አንቀጾች ስንቃኛቸው Read more »

                    ከተዘጋ ውሸታሙ ኢትቪ ይዘጋ ተድላ ጌትነት ጽሁፉን በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ከተዘጋ ውሸታሙ ኢትቪ ይዘጋ አርብ የካቲት 14ቀን 2006ዓ/ም በተላለፈው የ ኢትዩጵያ ህዝብ አይንና ጀሮ የሆነው ኢሳት እዲዘጋ ወያኔወች ፈረንሳይ ለሚገኘው …

ከተዘጋ ውሸታሙ ኢትቪ ይዘጋ Read more »

ቦይንግ 767 – እገታ እና እንድምታው ጽሁፉን በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።  ቦይንግ 767 እገታ ክንፉ አሰፋ           አንድ የኢህአዴግ ካድሬ፣  ቤት ለመከራየት ወደ አንዲት ወይዘሮ መኖርያ ይሄዳል።  ስፍራው እንደደረሰ ሌላ ተከራይም ከወይዘሮዋ ቤት ብቅ እንዳለ አስተዋለ። ሌላኛው ተከራይ ሰይጣን …

ቦይንግ 767 እገታና እንድምታው Read more »

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል 34 አምቡላንሶችን ለክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች አስረከበ። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር 34  24.7 ሚሊዮን ብር ያወጣባቸው 34 አምቡላንሶችን ለክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አስረከበ። ከ300 ሺህ በላይለሚሆኑ ዜጎች አገልግሎት እየሰጠ ያለው ማኅበር፣ አሁን ደግሞ አቅሙ ከፍ ሊል እንደሚችል አስታውቋል። 

በአዲስ አበባ የሚያስገነባው የገቢ ማስገኛ ሥራም መጀመሩን፣ ዋና ጸሓፊው ገልጸዋል። ዝርዝሩን መለስካቸው አምኃ ከላከዉ ዘገባ ያድምጡ።

የምስራቅ አፍሪቃ የልማት በየነ መንግስታት ድርጅት ኢጋድ የደቡብ ሱዳን መንግስትና ተቃዋሚዎቹን የማደራደር ጥረት ቀጥሏል። ኢትዮጵያ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ከደቡብሱዳን የሰላም ድርድር ጋር የተያያዘና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ሃይለማራምደሳለኘ የተላከ ልዩ መልዕክት ለፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር አድርሰው ተመልሰዋል።
ልዩ የተባለው መልዕክት ይዘት ግን አልተብራራም። የቀሪዎቹ አራት የሱዳን መንግስት ተቃዋሚ ባለሥልጣናት ከእስር አለመፈታት ፣ ለሰላም ድርድሩ  መሳካት እንቅፋት ከሆኑ ነጥቦች አንደኛው እንደሆነ ይነገራል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቶ ዲና ሙፍቲ ለአገር ዉስጥ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የህዳሴ ግድብ ግንባታጋር በተያዘ የግብጽ መንግስት ላይ ሂስ ሰንዝረዋል። አቶ ዲና የግብጽባለስልጣናት የግድቡን ግንባታ…

© Masresha Mammo
የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሞራል መሠረት እና ብቃት በሌላቸው ፖለቲከኞች እጅ ከወደቀ ሰንብቷል። ይህ የሰነበተ እውነታ በአሁን ሰዓት ከዝቅጠትም በታች እየኾነ ነው። ለኢትዮጵያ የሚያዋጣት ብሔርን መሠረት ያደረገ ፖለቲካዊ ርዕዮት ነው የሚለው የፖሊቲካል ኢኮኖሚ ስትራቴጂ ሁሉን አቀፍ ፍትህ የተንሰራፋበት ቢኾን ምናልባት አዋጪ ሊኾን ይችላል የሚል ግምት ማስቀመጥ ይቻል ነበር። ነገር ገን ስትራቴጂው ወረቀት ላይ ሌላ መልክ የያዘ፤ ምድር ላይ ደሞ ሌላ ትርክት የዋጠው ነው። ከጅምሩ ፍትሃዊነቱ አጠራጣሪ ስለኾነ ስትራቴጂው ለማፋጀት ያለመና እርስ በርስ በጥርጣሬ ከመተያየት የማያመልጡ የብሄር ፖለቲከኞችን እየፈለፈለ ይገኛል። ለዚህም ነው ከሁለት ዐሥርተ ዓመታት በፊት “በትምክህት” ፍረጃ የተጸነሰው ሕዝብን የማቃለል ጅምር ወደ ለሃጭ ተዋስዖ ያደገው።

የብአዴን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አለምነው መኮንን ይህን የለሃጭ ተዋስዖ ከየት አመጡት? የሚለው ጥያቄ በእኔ እምነት ወሳኝ ጥያቄ ነው። ብዙዎች እንደሚያምኑት ብአዴን እንደ ፓርቲ የራሱ የኾነ ነጻነት እና እምነት ያለው ፓርቲ አይደለም፤ አሻንጉሊት እና አስፈጻሚ፤ ከሕወሃት የሚወርድለትን ትዕዛዝ እና ፖለቲካዊ ትንተና ለማስተላለፍ የሚያገልግል “ትቦ/ቧንቧ ፓርቲ” ነው። ከአራቱ የኢሕአዴግ ፓርቲዎች ውስጥ ራሱን ሥልጣን እንደሚጋራና 22 ሚልዮን ሕዝብ እንደሚወክል ድርጅት ፖለቲካዊ ስሌት ውስጥ አስገብቶ የሚንቀሳቀስ ፓርቲም አይደለም። “የአማራውን” ሕዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚያስችል ምንም ዐይነት ተነሳሽነትም የለውም። ይህን እውነታ በግልጽ ለመረዳት የፓርቲውን ቁልፍ ሰዎች ማንነት ማየት ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ። አንድ የብሔር ፓርቲ የአባልነት መመዘኛ መስፈርቱ ምንድነው? የሚለውን ጥያቄ ቀድመን እናንሳ። በደም እና በዘር ከዚያ ብሔር የተገኘ ሰው ብቻ ነው የፓርቲው አባል መኾን ያለበት? ወይስ በምርጫም የዚያ ብሔር አባል ነኝ ማለትን ያካትታል?

የሚያካትት ከኾነ በብሔር የመደራጀት ትርጉም ለምን ያስፈልጋል የሚለውን ጥያቄ ማንሳታችን አይቀርም። ይህን ጉዳይ ማንሳት የፈለግኹት የመንግሥት ቁልፍ ሰው ናቸው ተብለው የሚነግርላቸውን አቶ በረከትን እንደምሳሌ ለመመልከት ነው። አቶ በረከት በደም ከአማራው ጋራ የሚያስተሳስራቸው አንዳችም ነገር የለም። ነገር ግን የአማራው ጉዳይ የእኔ ነው ብሎ በተቀመጠው ፓርቲ ላይ ቁልፍ ቦታ አላቸው። የብአዴን አመራሮችም ኾኑ አባላት አቶ በረከት ከዚህ ፓርቲ ራሳቸውን እንዲያወጡ መጠየቅ አለባቸው፤ ቡግና ውስጥ ተወልዶ ማደግ አማራነትን ያቀዳጃልና እኔም አማራ ነኝ የሚል አቋም ካላቸው፤ ቀድመህ ለተገኘህበት የብሔር ማንነት ቅድሚያ ስጥ ከሚለው የራሳቸውና የተከታይ ካድሬዎቻቸው ትንተና ጋራ ስለሚጋጭ የሚያዋጣ አካሄድ አይኾንም። እንደ በረከት ዐይነት “የአማራነት ልብስን ቀደው ያሰፉ” ሰዎች ለአማራው ሕዝብ ቆመናል ብለው ከሚያስቡ ሰዎች ጋራ በአንድ ጠረጴዛ ላይ መቀመጣቸው መዘዙ ብዙ ነው። በዋነኛነት ሌሎችን ነጻነት ያሳጣቸዋል። ነጻነት የሌለው ሰው ደግሞ ከራሱ የሚናገረው ነገር የለውም።

አቶ በረከት ከጫካ ጀምረው የሕወሓት ዋነኛ ሐሳብ አስተግባሪ ናቸው። አማራ ትምክህተኛ እና ነፍጠኛ ነው የሚል የፖለቲካ መሣርያ ይዘው መሥራት የጀመሩት ዛሬ አይደለም። አማራው እንደ ሕዝብ ትምክህት አለበት ወይ የሚለው ሐሳብ በራሱ ሕዝብን በአንድ ቅርጫት ውስጥ አስገብቶ እንደመፍረድ ስለሚቆጠር ሐልዮቱ በራሱ ወኃ የሚያነሳ ጭብጥ የለውም። የአማራውን ልሂቅ ስህተት እና ተግባር ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋራ ጭቆናን ሲካፈል ለኖረ ሕዝብ ማሸከምም የወጣለት ኢ-ፍትሃዊነት ነው። የትኛውም አማራ፤ የትኛውም ትግሬ፣ የትኛውም ኦሮሞ፣ የትኛውም ጉራጌ፣ የትኛውም ወላይታ . . .እና ሌሎችም ብሔሮች የጨቋኝ አገዛዝ ሰለባዎች ነበሩ፤ እንደ ሕዝብ። አሁንም ናቸው። አማራ እንደ ሕዝብ የተለየ ያገኘው ጥቅም አለ ብዬ አላስብም። ስለዚህ አማራውም እንደ ሕዝብ በብሔር መብቱን ያስጠብቅ የሚል መነሻ ይዘን ከመጣን ስድብን ተሸክሞ የሚዘልቅበት ምንም ዐይነት ምድራዊ ምክንያት ሊኖር አይችልም።

የህወሓት ከፍተኛ ባለሥልጣናት አማራውን ወክለናል ብለው በሚንቀሳቀሱ አመራሮች ላይ ለምን “ትምክህተኛ”፣ “ነፍጠኛ” እና “ለሃጫም” የሚሉ ቃላቶችን በአፋቸው ላይ ማስቀመጥ መረጡ? በኦሮሞው ላይ “ጠባብ” እና “ሁሉም ሲፋቅ ኦነግ ነው” የሚለውን ፍረጃ እና ስድብ ማሸከምስ ፈለጉ? ይህን ፍረጃ እና ስድብ የመረጡበት ምክንያት አንድና አንድ ብቻ ነው። የሁለቱ ብሔሮች ጥንካሬ የሥልጣን መሠረታቸውን ስለሚያናጋ ነው። ራሳቸው ቀይደው ባመጡት የብሔር ፖለቲካ አደረጃጀት ኦሮሞው እና አማራው ባላቸው የሕዝብ ብዛት ብቻ የሥልጣን ተቀናቃኝ በመኾን ወደፊት የሥልጣን ርካብ ላይ እንደ ሕወሓት ያለው ድርጅት እንዳይወጣ እንደሚያደርገው ጠንቅቀው ያውቃሉ። ስለዚህም “እኔ ትምክህተኛም፤ ጠባብም አይደለሁም” የሚለውን ፍረጃ መልስ እስኪሰጡበት ድረስ ሥልጣናቸውን ማራዘም ይፈልጋሉ። ሕወሃት ለሌሎቹ የኢትዮጵያ ብሔሮች ቀርቶ ሕዝባዊ መሠረት አለኝ ለሚለው የትግራይ ማኅበረሰብም የማይገደው መኾኑን በተደጋጋሚ አሳይቷል። (ለዚህ የአብርሃ ደስታን ሪፖርቶች መከታተል ብቻ በቂ ነው)።

ብዙ የነቁ የትግራይ ልጆች እና ራሳቸውን ከአረና ጎን አሰልፈው የሕወሃትን አምባገነናዊ አስተዳደር ለሚታገሉ ሰዎች የሚያወጣላቸው ስም አማራውን እና ኦሮሞውን ከፈረጁበት ጋራ ተመሳሳይ ነው። አሁንም አዲሱ “የትምክህት ለሃጭ” ተዋስዖ በገዛ ልጁ አባቱን ማሰደብ ዐይነት ነው። ይህ አዲስ ነገር አይደለም። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ ይህንኑ ተመሳሳይ ድርጊት ፈጽመዋል። ይህ ሕዝብን የማቃለል እና በእሳት ላይ ቤንዚን የማርከፍከፍ ተግባር ተጸንሶ የሚያድገው በሕውሓት ሴል ውስጥ አይደለም ብሎ ማንም አይጠረጥርም።

በ97 ምርጫ ገዢው ፓርቲ ከተቃዋሚ ፓርቲ በኩል ያለው ጫና እየበረታበት ሲመጣ እና በፖሊሲ ክርክሮች ላይ ሕዝቡ የበለጠ ድምጹን ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ሊሰጥ ወደሚችልበት ኹኔታ ባዘነበለበት ወቀት “ኢንተርሃምዌይ” የምትለዋን ቃል ከአለቃቸው ተቀብለው በቴሌቪዥን መስኮት መጥተው የነገሩን አማራውን እወክላለሁ ብለው የተቀመጡት አቶ አዲሱ ለገሰ ነበሩ። ከራሱ አፍልቆ ያመነበትን ነገር በራሱ ቋንቋ የሚናገር አንድም ባለሥልጣን እንደሌለን እናውቃለን። አቶ መለስ ቃላቶችን ይፈበርካሉ፤ እነዚያን የተፈበረኩ ቃላት በዙሪያቸው ኅሊና እና ሆዳቸውን የሸጡ ባለሥልጣናት እንደ ዐየር ባየር ነጋዴ አውጥተው እንደ በቀቀን ሲጮኹብን ይውላሉ።

እጅግ በጣም አስገራሚው ነገር ኢሕአዴግ ውስጥ ካሉት አራት ድርጅቶች መካከል በአመራር ደረጃ ለወከሉት ሕዝብ ባለመቆርቆር ብአዴኖችን የሚተካከላቸው አለመገኘቱ ነው። በታምራት ላይኔ ተጀምሮ፣ በአዲሱ ለገሰ ተባብሶ፣ በአለምነው መኮንን የዝቅጠት ደረጃ ላይ ደርሷል። ምንም እንኳ “የዘር ምርጥ፤ ወይም ንጹህ ዘር” የሚባል ጽንሰ ሐሳብ በዚህ ዓለም ላይ ባይኖርም፤ (አለ ብለው የሚያስቡ ካሉ፤ እንደ ሂትለር ዐይነት በሽታ የተጠናወጣቸው ይመስለኛል) አንዳንዶች የእነሱን ዘር ከሌላው ዘር የተለየ እና የተሻለ አድርገው ለማሳየት ሲታትሩ እየተመለከትን ነው። እያንዳንዱ የሰው ልጅ ሲፈጠር እኩል ነው የሚለውን ዋናና መሠረታዊ ጉዳይ ኾነ ብለው ለመሸሽ ፖለቲካዊ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ “ማንነት እንዲህ ነው፤ እንዲያ ነው” በሚል ጉንጭ አልፋ ክርክር ውስጥ የሚገቡ ሰዎችም ሞልተዋል። እነዚህ በፖሊቲካ መጫዎች ሜዳው ታስቦ እና ተሰልቶ ከተቀመጠላቸው ተዋስዖ ውጪ አዲስ ተዋስዖ መፍጠር ያቃታቸው ናቸው። ቀጣይቱ ኢትዮጵያ አዲስ ተዋስዖ ያስፈልጋታል። ሁሉም የሰው ልጆች በመጀመርያ እኩል ናቸው በሚል መሠረታዊ ኀልዮት ላይ የሚያጠነጥን ተዋስዖ።

የለሃጭ ተዋስዖው በሁለት ወገን ራሳቸውን የቀየዱ ልጋጋም ተፋላሚዎችን እያሳየን ነው። “ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል” ወደሚል መፈክረኛነት መሻገር አርቆ አሳቢነትን የሚያሳይ እንዳልኾነ ግልጽ ነው። ምክንያታዊ ከኾኑ ምልከታዎች ወጥተን የስድብ ጅራፍ የምናጮህ ትውልዶች መኾናችንም አሳዛኝ እውነታችን ኾኗል። አማራው እንደ ሕዝብ እየተሰደበ ነው የሚለው ነገር የሚያስቆጣን እና የሚያንገበግበን ከአማራ ስለተወለድን ብቻ ከኾነ ፍትሃዊ የመኾን ዕድላችን ይመነምናል። ይህ ማለት ግን መሰደብን አሜን ብላችሁ ተቀበሉ እና እለፉት ከሚል እሳቤ ጋራ ፈጽሞ አይገናኝም። ግለሰቦችም ኾኑ ብሔሮች በማንኛውም ኹኔታ መሰደባቸውን መቃወም እና መታገል ነው ዋናው እና ትልቁ ቁም ነገር።
በሌላ በኩል ሌላው ብሔር ሲሰደብ ወገባቸውን ታጥቀው የሚመጡ ሰዎች አማራውም እንደ ሕዝብ ሊሰደብ አይገባውም ብለው ከጎኑ ካልቆሙ፤ ለብሔር እንቆረቆራለን የሚሉት ጊዜያዊ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ትርፋቸውን ለማስጠበቅ ብቻ እንደኾነ ያሳብቅባቸዋል። ይህ ደግሞ እንደ አገርም ኾነ እንደ ማሕበረሰብ ዘላቂ የኾን ትርፍ የምናካብትበት ጉዳይ አይኾንም።

ለብሔር/ለጎሳ ፖለቲካ ቅድሚያ ሰጥተው የክርክር ሰይፋቸውን የሚመዙ ሰዎች አሁን አማራ በሚባለው ብሔር ላይ የተቃጣውን ስድብ ሲቃወሙት ካላየን፤ የሚከተሉት ፖለቲካዊ ርዕዮት ሚዛን የሚደፋ ነው ብለን እንድናስብ አያደርጉንም።

በእኔ እምነት አቶ አለምነው መኮንን የፈጸሙት ነገር ወንጀል ነው። ያውም ትልቅ ወንጀል። ጉዳዩ በግምገማ ወይም ከሥራ ኀላፊነታቸው ዝቅ በማድረግ ብቻ የሚታለፍም አይደለም። የሚመራውን ሕዝብ በዚህ ደረጃ አሳንሶ እና አዋርዶ የሚመለከት መሪ ፓርቲውንም ኾነ አገሩን አይጠቅምም። የፌዴራል መንግሥቱ የክልል መንግሥታት እና ባለ ሥልጣናት የህዝብን ክብር እና ስም የሚያጎድፍ ተግባር ሲፈጽሙ ነገሩን የሚዳኝበት የራሱ የኾነ ሕገ መንግሥታዊ ማዕቀፍ አለው። በዚህ ጉዳይ ላይ መንግሥት ርምጃ የመውሰድ የሞራል ብቃትም ኾነ መሠረት የለውም የሚል መከራከርያ ሊነሳ እንደሚችል እገምታለሁ። ይህ መከራከርያ እና ግምት ትክክል ነው ብዬም አምናለሁ። ይህ ዐይነቱ በሕዝብ ላይ ቁጣ ሊያስነሳ የሚችል ድርጊት ከወዲሁ በራሱ በፌዴራል መንግሥቱ መልስ የማያገኝ ከኾነ፤ ራሱን በጊዜ ሂደት ከስሩ መንግሎ ሊጥለው እንደማይችል ምንም ማረጋገጫ አይሰጠንም። ይህ ሐሳብ ራሳቸውን በተቃዋሚ ጎራ ላሰለፉ ዜጎች ‘የዋህና የኢትዮጵያን መንግሥት ተፈጥሯዊ ማንነት ካለማወቅ የመነጨ’ ሊመስላቸው ይችላል። ለጊዜው መልሴ ይምሰላችው ግድ የለም የሚል ይኾናል። ነገር ግን በበሰበሰ አሠራሩም ቢኾን ይህን ጉዳይ ችላ ማለት አያዋጣውም ባይ ነኝ። ባለሥልጣናቴ ሙስና ሲሠሩ አገኘኋቸው ብሎ ዘብጥያ ካወረደ፤ አቶ አለምነህን የማያወርድበት ምንም ምክንያት ሊኖር አይችልም ከሚል መነሻም ነው።

በመጨረሻ፦ የአቶ አለምነው ንግግር ማንንም ሰው የኾነ ሰው ሁሉ ምን ያህል ሊያስቆጣ እንደሚችል ለማሳየት ንግግሩን በሌሎች ብሔሮች ገልብጬ ማየት ፈለግሁ። ይህን ማድረግ የፈለግኹት ለብሔር ማንነት ቅድሚያ የሚሰጡ ሰዎች ዝምታ ምን ያህል አግባብ እንዳልነበረ ለማሳየት ነው።

አቶ አለምነው እንዲህ ነበር ያሉት። “አማራው በባዶ እግሩ እየሄደ፤ ነገሩ መርዝ ነው፤ ይህንን የትምክህት ለሃጩን ካላራገፈ በአንድነት አብሮ መኖር አይችልም!”

ይህንኑ ንግግር የሕወሃት ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲህ ብለው አቀረቡት ብለን እናስብ “ትግሬ በሰቆጣ እየሄደ፤ ነገሩ መርዝ ነው፤ የእብሪት ለሃጩን ካላራገፈ በአንድነት አብሮ መኖር አይችልም!”

እንደገና ይህንኑ ንግግር የኦህዴዱ ምክትል ፕሬዝዳንት ሲያቀርቡት “ኦሮሞ በቦት ጫማ እየሄደ ነገሩ መርዝ ነው፤ የመገንጠል ለሃጩን ካላራገፈ በአንድነት አብሮ መኖር አይችልም!” ቢሉ ምላሾቻችን ምንድን ነው የሚኾኑት? የለሃጭ ተዋስዖ ምናልባትም ልጋግ ኾኖ ሁላችንንም ጠራርጎ እንዳያጠፋን ያሰጋል። ሁላችንም ከጊዜያዊ ጥቅማችን በላይ ለሰው ልጆች እኩልነት እኩል እንቁም።

Image

ሶማሊያ ዋና ከተማ መቅዲሾ ውስጥ ዛሬ በደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃት ከ10 የሚበልጡ ሰዎች ህይወት ጠፋ ። ሰባት ሰዎች ደግሞ ቆሰሉ ። በሶማሊያ ብሔራዊ የፀጥታ ዋና መስሪያ ቤት አቅራቢያ በደረሰው በዚሁ ጥቃት ከተገደሉት መካከል ሰላማዊ ሰዎችና የደህንነት ኃይሎችም ይገኙበታል ። ለጥቃቱ አሸባብ ሃላፊነቱን ወስዷል ።

በጀርመን በየካቲት ወር አጋማሽ ላይ ለሳምንት የሚዘልቀዉ የካርኔቫል ድግስ ዛሪ በድምቀት ተጀምሮአል። ጀርመናዉያን የሚያከብሩት ብዙ ባህላዊና ልማዳዊ በዓላት አልዋቸዉ። ትልቅና ተወዳጅ ከሆኑት በዓላት መካከል ፤ የገና፣ የዘመን መለወጫ እንዲሁም የፋሲካ በዓል ሲሆን፤ ከሃይማኖት ጋር ግንኙነት የሌለዉ የካርኔቫል ድግስም

የባሮሶ እና የአቻዎቻቸዉ ንግግር ከአቡጃ ሲንቆረቆር የሰሜን ምሥራቅ ናጄሪያ ግዛት የአዳማዋ መንደሮች ጥይትና ቦምብ ይዘንብባቸዉ ነበር።አስራ-ሰወስት ሰዎች ተገደሉ።አንድ የክርስቲያን መንፈሳዊ ትምሕርት ቤት ጋየናይጄሪያ የዛሬዉ ሰሜናዊና ደቡባዊ ግዛትዋ

………………..ቴወድሮስ ከጎንደርና ከአሁኑ አማራ ይልቅ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ከዚያም አልፎ እየሩሳሌም ነጻ ለማውጣት እቅድ እንደነበረው ይነገራል፡፡አጼ ዮሃንስም እራሱን የትግራይ ሳይሆን የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ነበር፡፡ አሉላ አባነጋ ቀይ ባህር ድረስ ይዋትት የነበረው ለተንቤን አሊያም ለትግራይ አልነበረም፡፡

አጤ ምኒልክ የአንኮበር ወይንም የሸዋ ንጉስ ብቻ አልነበሩም፡፡ ምኒልክና ጀኔራሎቹ አድዋ ድረስ የዘመቱት የአሁኑ ዘመን መሪዎች እንደሚሉት ‹‹ነፍጠኛውን›› ብቻ ወክለው አልነበረም፡፡ ንጉስ ጦና እና ሌሎችም የትግራይን ተራራዎች የወጡ የወረዱት ለእናት ሃገራቸው ኢትዮጵያ ነው።

እንደ በላይ ዘለቀ ያሉ ጀግና የኢትዮጵያ አርበኞች በአምስት አመቱ የትግል ወቅት የጣሊያን ፋሺስትን የተዋጉት ተጋድሎ ያደረጉት ለኢትዮጵያ ሃገራቸው ነው ። በደርግ ዘመን በሶማሊያ እና በኤርትራ ተራሮች ወንበደዎችን የተዋጉት ወታደሮች የእናት ሃገራቸው አንድነት …. በባድመ የተሰዉት ወጣት ወገኖቻችን የእናት አገራቸው አንድነት አነሳስቷቸው ነው። ምንሊክ ሳልሳዊ

አንድነት/መኢአድ እና ትብብር፣ በጋራ የአድዋ ድልን ለማክበር ከአንድነት ጽ/ቤት ጀመሮ እስከ ጊዮርጊስ የእግር ጉዞ እንደሚያደርጉ፣ በሚኒሊክ ሃዉልት ሥርም አበባ እንደሚያስቀምጡ በመግለጽ ፣ በሕጉ መሰረት ፖሊስ አስፈላጊዉን ትብብር እንዲያደርግ ቢያሳዉቁም፣ ኢሕአዴግ በሚቆጣጠረዉ የአዲስ አበበ አስተዳደር አማካኝነት «በዓሉ በብሄራዊ ደረጃ ስለሚከበር ማስተናገድ አንችልም» የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ሕዝቡን ባሳተፈ መልኩ በብሄራዊ ደረጃ የአድዋ በዓል፣ በኢሕአዴግ ዘመን፣ ከዚህ በፊት […]

የአንድነት ፓርቲ ከሰባ እስከ ሰማኒያ የሚሆን ሕዝብ ድምጹን ለማሰማት መዉጣቱ ገልጾ፣ ለባህር ዳር ሕዝብ ያለዉን አክብሮኢትና አድናቆት የካቲት 20 ቀን 2006 ባወጣዉ መግለጫ ገለጸ። ፓርቲ የባህር ዳሩ አይነት እንቅስቅሴ በሌሎች የአገሪቷ ክፍሎችን እንደሚደረጉ ያሳወቀ ሲሆን በአገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ሁሉ ከጎኑ እንዲቆሙ፣ ድጋፍ እንዲሰጡና ትግሉን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል። UDJ Press release on Bahir […]