ከመፃፍ በፊት ራስን መገምገም
ስሜነህ ታምራት (ስዊድን)
የቀድሞው ባለሥልጣን ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ “እኛና አብዮቱ” በሚል ርዕስ አንድ መጽሐፍ ለንባብ አብቅተዋል። ይህንኑ መጽሐፍ መነሻ አድርገው፤ ወይም የቆየ የፖለቲካ መስመር ልዩነት አነሳስቷቸው ይሁን ብቻ አቶ ሰለሞን ገ/የስ በኢትዮ-ሚዲያ ድረ-ገጽ ላይ “የመጽሐፍ ግምገማ” በሚል ርዕስ የጻፉትን አንብቤ እንደጨረስኩ ሁለት ሀሳቦች መጡብኝ።