ሰበር ዜና፣ የኢትዮጵያዊያን ሰላማዊ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ
በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ ነዋሪዎች ወይዘሮ ዌንዲ ሸርማን የተባሉ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ረዳት ሚኒስቴር በቅርቡ ኢትዮጵያው ውስጥ ያደረጉትን ጉብኝት ባጠናቀቁበት ጊዜ አገራችን ውስጥ በተጨባጭ ካለው ነባራዊ ሁኔታ በተጣረሰ ሁኔታ የተናገሩን እንዲያብራሩ ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ጠይቀዋል። በተለየም በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ውስጥ በወያኔ በተጫነው አፋኝ ሥርዓት እየተማረሩ የሚወዷትን አገራቸው እየለቀቁ እራሳቸውን ለከፍተኛ አደጋ አጋልጠው የሚሰደዱት ዜጎቻችን ስፍር ቁጥር የሌላቸው መሆናቸውንና እነዚሁም ወገኖቻችን በሄዱበት አገሮችም ውስጥ ለግድያ፣ለስቃይ፣ ለእስርና ለተለያዩ ችግሮች የሚዳረጉት አገራቸው ውስጥ ካለው እጅግ አስከፊ አገዛዝ ለመላቀቅ መሆኑ ግንዛቤ ማግኘት እንዳለበት ሰልፈኞቹ አበክረው ጠይቀዋል። በተለይም በየዓመቱ የስቴት ዲፓርትመት የሰብዓዊ መብትሪፖርት ላይ ኢትዮጵያን አስመልክቶ የዲሞክራሲ አለመኖርና የሰብዓዊ መብት መጣስ እንደሚደረግ በዝርዝር ከሚዘገበው በተጻራሪ ሴትየዋ የተናገሩት እርምት እንዲደርግበት ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል።
ኢትዮጵያን አስመልክቶ አሜሪካን የምትከተለውን ፖሊሲ በመቃወም ዋሽንግተን ከተማ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ያካሄዱት ሰልፍ ፍቶግራፎች።








