ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ወጣቶች ንቅናቄ ምስረታ መግለጫ
ሕያው የሆነው የኢትዮጽያ ታሪክ በተገቢው መንገድ እንዳስቀመጠው የአማራው ሕብረተሰብ ለአያሌ ሺህ ዘመናት የኢትዮጽያን ሉዓላዊነት ከውጭ ተስፋፊዎች በመከላከል ሃገራችን ክብሯን እንደጠበቀች በነጻነት ደምቃ በአንድነቷ ኮርታ ከጥቁርዓለም ውስጥ ብቸኛ ልዋላዊ የግዛት አንድነት ያላት የራሷ ቋንቋና ፊደላት ባለቤት የሆነች ታላቅ ሃገር ትሆን ዘንድ የአማራው ተወላጅ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር በመሆን መስፈሪያ የሌለው ዋጋ ከፍሎ ሃገሩን በነጻነት ቢያኖርም በየጊዜው አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ ያባረራቸው ቅኝ ገዠ ወራሪዎችና የአድህሮት ሃይላት ሃገር በቀል የእናት ጡት ነካሽ ባንዳ ተላላኪዎችን በማደራጀትና በማስታጠቅ ታፍሮና ተከብሮ የኖረውን ሉዓላዊ ነፃነቷን ሊፈነጩበትና ነባር
አንድነቷን አላልተው ሕልውናዋን ሙሉ በሙሉ በደላሎቻቸው ቁጥጥር ስር ለማድረግና ነባር ሆኖ የቆየውን ሃገራዊ ማንንነት ለመበረዝና ለማውደም የሚያደርጉትን የተቀነባበረ ሴራ በአስተማማኝ መንገድ ለማሳካት ኢትዮጽያዊነትን አንቆ አሻፈረኝ ያለውን የአማራውን ሕዝብ ስልታዊ በሆነ መንገድ አዳክሞ ለማጥፋት ላለፉት 100 አመታት ሲደረግ የነበረው ሴራ በዘመነ ወያኔ ተሳክቶ አማራው ከስልጣንና ከወታደራዊ አመራር ሙሉ በሙሉ በማግለል ከምሁር እስከ ቀን ሰራተኛው ከነጋዴ እስከ ገበሬው ሁሉን ባደረሰ መልኩ የበቀል ሰይፍ ተመዞበት በጅምላ ኢኮኖሚያዊ ሃይሉም ተመቶ ጥገኛና ስደተኛ የማድረጉ ወያኔያዊ ስልት ተግባራዊ ከሆነበት ባለፉት 22 አመታት ውስጥ በአማራው ህዝብ ላይ የተካሄደው ጥቃት ከማንም የተሰወረ አይደለም። የህወሐት ወያኔ የጥቃት ሠይፍ ከተመዘዘበት ከደደቢት እስከ ምንሊክ ቤተ መንግስት የተቀላው የአማራው ተወላጅ አንገት ቤቱ ይቁጠረው። በጥላቻ ተወልዶ በበቀል ያደገው ይህው እኩይ የዘረኛ መንጋ ከመነሻው ይዞ የተነሳውን የጸረ አማራነት ፖሊሲ ለማሳካት በቀጥታና በተዘዋዋሪ ሲያካሂድ የኖረውን የዘር ማጽዳት ተግባር ስልታዊና ዝግመታዊ በሆነ መልኩ በመለወጥ በአማራው ህዝብ ላይ ፈረንጆች (Systematic Genocide) እንደሚሉት የአማራውን ሕዝብ ከሚኖርበት የተለያዩ ክልሎች በማፈናቀል ሐብትና ንብረቱን በማሳጣት ቤተሰቡን በትኖ በረሀብ እርዛት በድንቁርና በጎዳና አዳሪነት ኑሮው እንዲገፋ በማድረግ ከማንነቱ እስከ ወዲያኛው ተቆራርጦ እንዲኖር ለማድረግ በቅርቡ በደቡብ ክልል ጉራፈርዳና በቤኒሻንጉል እንዲሁም ሰሞኑን በምዕራብ ሸዋ በሚኖሩ የአማራ ተወላጅ አርሶ አደሮች ላይ የተፈጸመውን አሳዛኝ ድርጊት እንዲገታ በአማራነታችን ተሰባስበን ትግሉን ለማገዝ ቁርጠኛ አቋም ላይ ለመድረስ እንድንችል አብይ ምክንያት በመሆኑ ይህን ንቅናቄ ለመመስረት ሳንወድ በግድ ተገፍተን በማንነታችን ዙሪያ ለመሰባሰብ አስገድዶናል።
ይህ በአማራው ሕዝብ ላይ በተከታታይ በመፈጸም ላይ ያለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ በአንድ ቦታ መግታትና መቆም ካልቻለ አሁን በያዘው የበቀል ፍጥነት ከቀጠለ ውጤቱ አስከፊና ሊገመት ከሚችለው በላይ ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል፤ ስለሆነም ሕወሐት/ወያኔ የአማራውን ሕዝብ ለማጥፋት የመዘዘው የጥፋት ሰይፍ ያለ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በተዓምር ወደ አፎቱ ስለማይመለስ በዐማራው ትግዕስትና ሆደ mሰፊነት ወያኔ ያቀደው የዘር ማጥፋት ሊገታ እንደማይችል በመረዳት የአማራው ነገድ ወጣቶች በመሰባሰብ በማንነታችንና በእናት ሃገራችን ላይ የተቃጣውን አደጋ ባለን አቅም ለመከላከል ባለብን ትውልዳዊና ሃገራዊ ግዴታ በንቅናቄያችን ዙሪያ ወጣቱ በመሰባሰብ ትግሉን በማገዝ ታሪካዊ ሃለፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ እናቀርባለን።
የአማራ ወጣቶች ንቅናቄ የትኩረት አቅጣጫው በሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ፕሮግራም የሠፈረውን በግፍ ሀብት ንብረታቸውን ተነጥቀው ለተፈናቀሉ የዐማራ ነገድ ተወላጆች ዕርዳታ ማሰባሰብ፣ድምፅ አልባ እና ባገሩ ባይተዋር ለሆነው የዐማራ ነገድ ድምፅ መሆን የዐማራውን ሁለንተናዊ ዐቅም በመገንባት ዐማራው በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሕይዎት ውስጥ ተገቢ ቦታውን እንዲይዝ ለማድርግ ሞረሽ ወገኔ የዐማራው ድርጅት በሚያደርገው ሁሉአቀፍ እንቅስቃሴ የዐማራው ወጣት ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የበኩሉን ድርሻ ከመወጣት ባሻገር የዐማራውን ወጣት በዘመኑ የብዙኃን መገናኛዎች በመድረስ ትውልድና አገር አድን ሚናውን እንዲወጣ የማደራጀትና የማንቃት
ሥራዎችን መሥራት ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ለመላው የዐማራ ነገድ ተወላጆች የምናስተላልፈው መልዕክት፣ አባቶቻችን ያቆዩንን ነፃነት፣አንድነትና
ሰላም ማረጋገጥ የሚቻለው ዐማራው ተደራጅቶ በአውራ ጠላትነት ፈርጀው ፣ፈጽሞ ሊያጠፉት ከተሰለፉት ኃይሎች በአቻነት ሲቆም ብቻ ነው፡፡ ድር ሲያብር አንበሣ እንደሚያስር ሁሉ፣ የእኛም መደራጀት በማንነታችን ላይ የተከፈተውን የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ተግባር ፈጽሞ በማስቆም የኢትዮጵያን ትንሣዔ የሚያረጋግጥ ስለሆነ የዐማራው ወጣት ይህን ንቅናቄ በመቀላቀል ትውልዳዊ ኃላፊነታችን በክብር እንድንወጣ የድረሱልን ጥሪ በሚያሰማው የዐማራ ነገድ ስም ጥሪአችን እናቀርባለን፡፡ እኛም እንደ አባቶቻችን ታሪክ ሠሪ እንሁን!
አማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደግ!
ሞረሽ የአማራ ወጣቶች ንቅናቄ ግንቦት ፳፰፤ ፪ሺ፭ ዓ/ም