የምርጫ ቦርድ ቧልት !

የምርጫ ቦርድ ቧልት ! YIDNEKACHEW KEBEDE

—————–
ከምንም በላይ ለነጻ፣ፍትሃዊ፣ ተኣማኒና አሳታፊ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ፣ የምርጫ ሜዳውን እንዲያስተካክል ትኩርት በመስጠት ሰማያዊ ፓርቲ ለቦርዱ ጥያቄ አቅርቧአል፡፡ ፓርቲያችን ለሚያቀርባቸው ተደጋጋሚ ጥያቂዎች አዎንታዊ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ምርጫ ቦርድ ሲንደፋደፍ ማየት የተለመደ ክስተት ነው፡፡
————————
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በታሕሣሥ 28/2007 ዓ.ም ባደረግው ስብሰባ፣ሰማያዊ ፓርቲ እስከ ጥር 4/2007 ዓ.ም ፣ምርጫ ቦርድን ይቅርታ በመጠየቅ የይቅርታ ደብዳቤ እንዲያስገባ ውሳኔ ማሳለፉን በ EBC የዜና እወጃው፤ የምርጫ ቦርድ የህዝብ ግንኝነት ኃላፊ ቀርበው ተናግረዋል፡፡ ፓርቲያችን በጉዳዩ ዙሪያ የሚሰጠው ውሳኔ እንደተጠበቀ ሆኖ፣እኔ በግሌ እንዲኸ ዓይነቱ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር የማይሞከር ፍፁም ድፍረት የተሞላበት የሞኝ አሞኝ ጨዋታ ምርጫ ቦርድ ባይሞክረው የተሻለ ነበር፤የሚል እምነት አለኝ !
ሰማያዊ ፓርቲ በመልመልመጥ ወይም በልመና ላይ የተመሠረት የፓለቲካ ውሳኔ እንደማያሳልፍ ዛሬ ብቻ ሣይሆን ከምስረታው ጀምሮ የሚታወቅበት የፀና አቋሙ ነው፡፡ለዚህም ፓርቲያችን ገና ከምስረታው ጅምሮ ከምርጫ ቦርድ የገጠመው ውጣ-ውረድ እጅግ በሚያስደንቅ ሁኔታ፣ከተለመደው ከቦርዱ ጋር የመተሸሸት አካሄድ እራሱን በማራቅ በህግ እና በሞራል የበላይነቱን በማረጋገጥ፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ አዋጅ መሠረት ሕጋዊነቱን ያረጋገጠ ፓርቲ ነው፡፡ምርጫ ቦርድ በወቅቱ የፓርቲያችን ውሳኔ በመቃዎም ደፋ ቀና ማላቱ የሚታወስ ቢሆንም ፣ ምንም ዓይነት የሕግም ሆኖ የሞራል ድጋፍ ስለሌለው የፓርቲያችን ውሳኔ በመቀበል፣ እውቅና ሰጥቻለው በማለት ሊያሳውቀን ችሎአል፡፡
ይህ ከሆነ ከ3 ዓመታ በኋላ “ሰማያዊ ፓርቲ ከምስራታው ጀምሮ በቦርዱ ተመዝግቦ እውቅና ሳይሰጠው ፣እንደተቋቋመ በማስመሰል መግለጫዎችን ሲሰጥ ቆይቷል”በማለት ቁጭት አዘል ማስጠንቀቂ ለመስጠት መቻሉን ለማመልከት ቦርዱ እንደመነሻ የተጠቀመበት አንዱ ክስ ነው፡፡ክሱ ግን ፍፁም መሠረት ቢስ ከመሆኑ ባለፈ ፣ትልቅ ተቋም ነኝ ብሎ የሚያስበው ምርጫ ቦርድ “እንደ-ነገረኛ ሰው” ቂም በመያዝ አሁን ላይ ላሰበው መጥፍ ዓላማ ማስፈፀሚያ ለማድረግ ሲጥር መታየቱ ትዝብት ውስጥ የሚጥል አካሄድ ነው፡፡
ሌላው ደግሞ ምርጫ ቦርድ በተለያየ ወቅት የመወያያ ዕርስ በማዘጋጀት ለፓርቲያችን የእንወያይ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ፣ፓርቲያችን ለቀረበለት ጥሪ አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት በቦታው ተገኝቷል፡፡ ይሁን እንጂ ከምርጫ ቦርድ ጋር በተደረገው የፓርቲዎች ውይይት፣ሕጋዊ እና መሰረታዊ ጥያቄ በመጠየቅ እንዲሁም ጠንካራ አቋም በመያዝ ከመርጫ ቦርድ ጋር አለምግባባቶች ተፈጥሯአል፡፡ ፓርቲያችን ለሚያቀርባቸው ጥያቄ እንዲሁም ገንቢ ለሆኑ አሰተያየት ቦርዱ እሱ እንደሚለው “ሆደ ሰፊነቱ”ቀርቶ በአግባቡ የፓርቲያችን አቋም የመረዳት አቅም ቢኖረው የት በተደረሰ ነበር፡፡
በተለይ ምርጫ ቦርድ ሰማያዊ ፓርቲ ይቅርታ እንዲጠይቅ ያስገደደበት ዋና ዋና ምክንያቶች “በምርጫ አልመግባባት እና የግጭት አፈታት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዝግጀት” ታህሳስ 3/ 2006 ዓ.ም፣ “የ2007 አገር አቀፍ ምርጫ አስመልክቶ የአፈጻፀም የጊዜ ሠሌዳ” ታህሳስ 7/2007 ዓ.ም እና “የ2007 አገር አቀፍ ምርጫ አስመልክቶ መንግስት ለሚያድርገው የፋይናስ ድልድል” ታህሳስ 22/2007 ዓ.ም በተካሄደው የፓርቲዎች ምክክር ላይ ሰማያዊ ፓርቲ የያዘው አቋም ነው፡፡
ከላይ በተጠቀሱት ዕርስ ዙሪያ በተደረጉ ውይይቶች ሰማያዊ ፓርቲ ፣ገዥው ፓርቲ በጉዳይ ፈጻሚው የምርጫ ቦርድ በኩል በተለመደው መንገድ በምርጫ ሥም ለመሥራት የተያያዘውን እኩይ ተግባር ራቁቱን የሚያስቀር፣ ምክንታዊ የመወያያ አጀንድ በማቅርብ፣ ሰማያዊ ላቀረበው ጥሪ ቦርዱ ለመቀበል ፍቃዳኛ አለመሆኑ ለማረጋገጥ ተችሎአል፡፡ከምንም በላይ ደግሞ ለነጻ፣ፍትሃዊ፣ ተኣማኒና አሳታፊ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ፣ የምርጫ ሜዳውን እንዲያስተካክል ትኩርት በመስጠት ለቦርዱ ጥያቄ አቅርቧአል፡፡ ፓርቲያችን ለሚያቀርባቸው ተደጋጋሚ ጥያቂዎች አዎንታዊ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ምርጫ ቦርድ ሲንደፋደፍ ማየት የተለመደ ክስተት ነው፡፡
ቦርዱ ከመንደፋደፍ ተግባሩ ተላቆ ወደ-እውነተኛ መንገዱ እንዲገባ የተደረገው ተደጋጋሚ ጥርተ ባለመሣካቱ፣ በሰለጠነ መንግድ ምርጫ ቦርድ የሚያዘጋጃጀቸው የውይይት መድረኮች ፓርቲያችን የተጣለበት የህዝብ አደራ ለመወጣት ስብሰባዎችን እረግጦ ውጥቷአል፡፡ይህ ደግሞ የተለመደ የተቃዎሞ መግለጫ ዘዴ ከሆኑት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ላይ የያዘው አቋም ተገቢ ብቻ ሣይሆን ሕጋዊም ጭምር ነው፡፡ይልቁንስ መሆን ካለበት ፓርቲያችን ለጠየቃቸው ጥያቄ እና ለሰጠው ገንቢ አሰተያየት ፈጣን ምላሽ ባለማግኘቱ ምርጫ ቦርድ ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል፡፡
የምርጫ በርድ ለገዥው መንግስት የማድላት አደገኛ ሱስ መጠመዱን የሚያሳብቅ ደርጊቶች ሲፈፅም ማየት ለኢትዮጵያዊያን አዲስ ነገር አይደለም ፡፡ ይልቁንም እንዲህ አይነቱ አስመሣይ አካሄድ የሚፀየፍ ፣እውነተኛ እና ገለልተኛ የምርጫ ቦርድ ተቋቁሞ ኃላፊነቱን ሲወጣ ማየት የአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ምኞት ነው፡፡ ሕዝብን የማስተባበር እና የመምራት ኃላፊነት ያለባቸው ፓርቲዎች ሰማያዊ ጭምር ለዚህ ተግተው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ይህን ለማለት የበለጠ ድፍርተ የሚሰጠኝ፣ሰማያዊ ፓርቲ ከሌሎች 8 ፓርቲዎች ጋር በመተባበር በመጪው ምርጫ ሂደት ላይ እና በምርጫ ቦርድ ላይ ያለው አቋም ነው፡፡
የ2007 አገር አቀፍ ምርጫ አስመልክቶ “ነፃነት ለፍትሓዊ ምርጫ “በሚል መርዕ በሁለት ዙር የተከፈለ ሕዝባዊ ንቅናቂ በመፍጠር በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ፡፡ ዘጠኙ የትብብር ፓርተሪዎች የመጪው ምርጫ ነጻ፣ፍትሃዊ፣ ተኣማኒና አሳታፊ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲካሄድ የምርጫ ሜዳውን እንዲያስተካክል ትኩርት በመስጠት እስከ ሕይወት መሰዋትነት በመክፈል የህዝብ የስልጣን ባለቤትነትን ለማረጋገጥ ቆርጠው ተንስተዋል፡፡ ይህ አይነቱ አካሄድ ያልተዋጠለት ገዥው መንግስት በጉዳይ ፈፃሚው በምርጫ ቦርድ አማካኝነት የትብብሩን እንቅስቃሴ ለመግታት በመጣር ላይ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጄ የዘጠኙ ትብብር ፓርቲዎች ተስማምተው ለማስፈፀም የተነሱለትን ዓላማ፣ በኽንዲ ዓይነቱ ተልካሻ ምክንያት ወደኋላ የሚሉበት አንዳችም ምክንት እንደማይኖራቸው ከመነሻቸው የያዙት አቋም የሚያመላክት ነው፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !

Image