አዲስ አበባ ዛሬ – የተሰበሰበው ሁሉ በድንጋይም በቡጢም ቻይናዎቹ ላይ ሲረባረብ ጉዳዩ አስፈሪ መልክ ያዘ …. ሁለት ጥይቶች ወደሰማይ ተተኮሱ…

ኢትዮ-ቻይና በቻይና -አፍሪካ አደባባይ

ኢትዮ ቻይና በቻይና አፍሪካ አደባባይ

ዛሬ ጠዋት 2፡45 ላይ ቦሌ…ከድልድይ ወደ ሚሊኒየም አዳራሽየሚወስደው መንገድ መጠምዘዣ ላይ ከአስፓልቱ ጠርዞች በአንዱ ጥግ አንድ ቻይናዊ (ቻይና መሰለኝ) ከአንድ ፖሊስ ጋር ሞቅ ያለ ክርክርነገር ገጥሟል….እጁን እያወናጨፈ ያወራል…መቼም “ቻይና”ዊው አማርኛ አጥንቶ ይሆናል እንጂ በዚህ ፍጥነት የሚያወራው ነገር (ቻይንኛ/ማንዳሪንከሆነ) ፖሊሱ የሚገባው አልመሰለኝም…”ቻይና”ው የፖሊሱን ነው መሰለኝ የዱላ ቆመጥ በእጁ ይዟል…አጠገባቸው ስደርስ ቻይናው “temper is come” ሲል ሰማሁት… በእንግሊዝኛ ሊያስረዳውእየሞከረ ነው ማለት ነው….ሰይጣኑን ያመጣው ምን ይሆን ብዬ እያሰብኩ ሳለ ሴት ፖሊስ መጣችና ቻይናው በእጁ የያዘውን ቆመጥ እያየች‹‹ማነው የሰጠው;›› ስትል ሰማሁዋት …”ቻይና”ው በሆነ ብልሃት ከፖሊሱ እጅ እያሳሳቀ የወሰደው ነው የሚመስለው…ወንዱ ፖሊስ ቆመጡንተቀበለ….አንድ አስር እርምጃዎች ወደፊት ስሄድ በርከት ያሉና ሻንጣዎች የያዙ ቻይናዎች ከአካባቢው ሰው ጋር ውዝግብ የገቡ ይመስላል….ሌባ ተተናኩሎዋቸው ይሆናል አልኩ (ያው ሌቦቹ እኛ አይደለን?!) ግን በሚታዩኝ አንድ ሁለት የፌዴራል ልብስ የለበሱ ወታደሮች የታጀበአንድ ጥቁር እንደ ሌባ ተይዞ ስላላየሁ፣ እንዲሁም ከግርግሩ መሃል አንድ ቻይናዊና አንድ ኢትዮጵያዊ ወጣት አንገት ላንገት ሲተናነቁማየቴ ጉዳዩ ሌላ አንደሆነ ጠረጠርኩ….ይሄኔ ሌሎቹ ቻይናዎች ድብድቡ ወደእነሱ እንዳይመጣ ለመከላል ይሁን ወይ የወንድማቸው መመታትደማቸውን አፍልቶት እንጃ ብቻ አጠገባቸው የሚገኘውን ሰው ባለ በሌለ ሃይል መማታት ያዙ…አሁን ተሞኙ አልኩ…እጁን አጣጥፎ የእነሱንዱላ እንደአሻንጉሊት ወይም እንደ ጌም ገፀባህሪት የሚቀበል ሰው ያለ መስሏቸው ይሆን? (ይቺ ናት ጨዋታ አለ ጥልዬ) እዚያየተሰበሰበው ሁሉ በድንጋይም በቡጢም ቻይናዎቹ ላይ ሲረባረብ ጉዳዩ አስፈሪ መልክ ያዘ …. ሁለት ጥይቶች ወደሰማይ ተተኮሱ…አንድ "ቻይና" ፊቱ በደም ተለውሶ ከግርግሩ ውስጥ ሲወጣና "ቻይና"ዎቹ ቁጥሩ በጣም እየበዛ የመጣው ህዝብ እደማይለቃቸው ሲገባቸው (ጥይቶቹምፀቡ የዋዛ እንዳልሆነ ሲገልፁ)….ገለል ገለል አሉ…ጉዳዩ በ”ቁጥጥር” ስር ሲውልና “ቻይና”ዎቹ መሃል አስፓልት ላይ እንዲቀመጡታዘው ደምና አቧራቸውን (“ለሀገሬ የከፈልኩት ነው” ይሉ ይሆናል) እየጠራረጉ ከነሻንጣዎቻቸው ሲቀመጡ….. እኔም ወደጉዳዬ ሄድኩ….

“Made in China” የሚል ጫማ ስንገዛ አንዳንዶቻችን “መቼም እግሬን አይወስዱብኝም”ብለን ነበር…መንገድ ሲሰሩ ስናይ ያገሬ መሀንዲስ ዛሬ እዚህች ጋ…ነገ ደግሞ እዚያች ጋ እየቆፈረ የሆነች ኪሎ ሜትር ላይ አመትመተኛት አቁሞ ትንሽ መፍጠን ሲችል ቻይና ሀገሯ ትገባለች ብለን ነበር… እርግጥ ነው ከአዲስ አበባ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ወጣ ስንልየተተከሉና ግብራቸውን ለመረዳት ስንሞክር አማርኛ እያማረን ቀርቶ በተበደርነው እንግሊዝኛ እንኳ እንዳይገባን የራሳቸው ቋንቋ ብቻየተለጠፈባቸው ግዙፍ ኩባንያዎች ስናይ ፍርሃት ቢጤ የሚሰማን ጥቂቶች አይደለንም (የሀገራችንን መልክ እየቀሙን እንደሆነ ደመ ነፍሳችንእየነገረን)….(ጎበዝ፣ ቻይንኛ መማር አይከፋም…ቢያንስ ምን እያሉ እደሚያሻሽጡን ይግባን እንጂ).…
Image

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በተለምዶ OCR (OldClass Rooms) በሚባለውና የኢትዮጵያና የውጪ ቋንቋዎችና ስነፅፍ እንዲሁም የፎክሎር ትምህርቶቸ በሚሰጡበት ህንፃ ውስጥ የቋንቋዎችጥናት ተቋም ቤተመፃህፍት ነበር (“ነበር” እንበል) የእነዚህ ትምህርቶችን የተመለከቱ መፃህፍት…ጥናቶችና ጆርናሎች የሚገኙበት…የህንፃው አንደኛ ፎቅ ላይ የተሰየመ….ባለፈው ሰሞን በአጋጣሚ ወደዚያ ህንፃ ሳቀና መልኩ ተቀይሮ አገኘሁት….ቤተመፃኅፍቱ ዕድሳትየተደረገለት መስሎኝ ነበር መጀመሪያ… ጠጋ ስል የተስፋፋ የቻይና ግዛት ሆኗል ….የቻይና ኢምፓየር ህንፃው ውስጥ ተገንብቷል…“ConfuciusInstitute” በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ…ግርግዳው ላይ የቻይናን ባህል የሚያስጎበኙ በፍሬም የታሸጉ ፎቶ ግራፎች ተሰቅለዋል……ቤተመፃህፍቱየለም (ነፍስ ይማር ብለናል) …. ወዳጆቼ፣ ፈቅደን ስንሰጣቸው የትድረስ እንደሆነ ካላወቅን (እናውቃለን ማለት ይከብዳል-ማወቅም የምንፈልግ አንመስልም) ንቀት ብትነግስብን በማን ይፈረዳል?
Elizabeth Mengistu