አርማጮ ያለው የወያኔ ጦር በአማራ ንቅናቄው ጦር አሁንም ተሰንጎ ተይዟል::- ሻእቢያ መረጃ ያሾልካሉ ባላቸው የነጻነት ታጋዮች ላይ ማስጠንቀቂያ አወረደ:: – የውህደቱ ጉባዬ ይካሄዳል ተብሎ እየተጠበቀ ነው:: ቅድመ ምክክሮች እየተካሄዱ ነው::
አርማጮ ያለው የወያኔ ጦር በአማራ ንቅናቄው ጦር አሁንም ተሰንጎ ተይዟል::
– ሻእቢያ መረጃ ያሾልካሉ ባላቸው የነጻነት ታጋዮች ላይ ማስጠንቀቂያ አወረደ::
– የውህደቱ ጉባዬ ይካሄዳል ተብሎ እየተጠበቀ ነው:: ቅድመ ምክክሮች እየተካሄዱ ነው::
– የሕወሓት ጄኔራሎች እና የደህንነት ሃላፊዎች ጎንደር እየተመላለሱ ነው::
Minilik Salsawi
ከአስመራ የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ከውህደቱ ቀድመው የሚወጡ የስብሰባው መረጃዎች እና ሻእቢያን የሚመለከቱ ግፎችን በዝርዝር መረጃ ሰጥተዋል የተባሉ የነጻነት ተዋጊ ኢትዮጵያውያን በግምገማ እየታመሱ መሆኑን የሻእቢያ ምንጮች ጠቁመዋል:: አመራሮቻቸውን በግንባር አስቀምጦ ለነጻነት በረሃ የገቡትን ታጋዮች ሰብስቦ በሱዳን ሲም ካርዶች እየተጠቀማቹ መረጃዎችን በኤስኤሜስ ቴክስት እና በኢንተርኔት ታቀብላላቹ የመረጃ መውጣት ፍንጮች እየታዩ ነው ሳይስፋፉ ራሳችሁን አጋልጡ እየተባሉ ሲተራመሱ መክረማቸው ታውቋል::
ስለ አስመራው ትግል ዝርዝር መረጃዎች አሉን የሚሉ የድህረገጽ ሚዲያዎች በርክተዋል በሚል ዙሪያ ከፍተኛ ግምግማ የተካሄደ ሲሆን ሁኔታው መጣራት አለበት በሚል መተራመሱ ሲቀጥል በኤርትራ የኢንተርነት አክሰስ የሚጠቀሙ እንዲታገድባቸው እና ለፕሮፓጋንዳ ሰራተኞች በክትትል እንዲፈቀድላቸው የተደረገ ሲሆን የሱዳን ሲም ካርድ የሚጠቀሙ የበረሃ ልጆች በጠቅላላ ከነስልካቸው እንዲነጠቁ እና ምንም አይነት አክሰስ እንዳይፈቀድላቸው ሻእቢያ ከባድ ማስጠንቀቂያ አውርዷል::መረጃውን የሰጡን የሻእቢያ ምንጮቻችን ከአፋኝ መንግስት ወደ ሌላ አፋኝ መንግስት በሽያጭ ይሁን በተውሶ በማይታወቅ መልኩ ዝውውር አድርገናል ሲሉ የነጻነት ታጋዮቹ ውስጥ ውስጡን ያጉረመረሙ መሆኑን ገልጸዋል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ የውህደቱ ጉባዬ ይጀመራል ተብሎ እየተጠበቀ ሲሆን ቅድመ ምክክሮች መካሄዳቸውን በስብሰባው ለመሳተፍ የሄዱ ቡድኖች የገለጹ ሲሆን ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል::
በአርማጮና በአከባቢው የሚገኘው የአማራ ንቅናቄ ጦር የወያኔን ሰራዊት ሰንጎ በመያዝ እየተዋጋ መሆኑን የድርጅቱ ምንጮች ገልጸዋል::ይወያኔው መንግስት ባከባቢው የተነሳውን ጦርነት መቆጣጠር ባለመቻሉ ከኢታማጆር ሹሙ ጀምሮ የደህንነት ምክትሉ አቶ ኢሳያስ እና የጠ/ሚ የደህንነት አማካሪ አለቃ ጸጋይ ድረስ የአከባቢውን ወታደራዊ እና የደህንነት ባለስልጣናትን ጨምሮ እየተረባረቡ መሆኑን የቅርብ ምንጮች አስታውቀዋል::የአማራ ክልል የደህንነት ሃላፊዎች አቶ ተሾመ እና አቶ አያኖ መቀመጫቸውን ጎንደር በማድረግ ከፍተኛ መረጃ በመሰብሰብ ከወታደራዊ ደህንነቶች ጋር በመቀዳጀት ለፌዴራሉ መንግስት በማስተላለፍ ላይ ይገኛሉ::እንዲሁም ይህንን እንቅስቃሴ በበላይነት ለመምራት የመከላከያ ዘመቻ የበላይ መኮንን የሆነው ጄኔራል ገብረዝጌር መብራትኡ ከአዲስ አበባ ጎንደር በመሄድ ሂደቱን እያስተባበረ ያለ ሲሆን ወደ ሱዳን መንግስትም የደህንነት ምክትል ሹም አቶ ኢሳያስ የተባለ የሚመራው ቡድን መላኩ ታውቋል::
በትላንትናው እላት በከባድ መሳሪያዎች እና ታንኮች ታጅቦ ወደ አርማጮ የገባው የወያኔው ሰራዊት በሽምቅ ውጊያ የሰለጠነ ልዩ ጦር ሲሆን ተጨማሪ ጦር አስቸኳይ ስምሪት ..9 ..9 ..እያደረገ በአከባቢው በመዟዟር ተቃዋሚዎች ይኖሩብታል ያለውን ቦታ ሁሉ በማጽዳት ላይ ሲሆን የሃገር ቤት በወያኔ ህግ ተመዝግበው ያሉ የፖለቲካ ድርጅት አባላት የዚህ ጽዳት ዘመቻ ተጠቂ እንዳይሆኑ ሲያስፈራ ሁኔታውን በአጭር ጊዜ ሳይስፋፋ ሙሉ ሰሜን ጎንደርን እና በከፈል ደቡብ ጎንደርን ለማጽዳት ዘመቻው በደህንነቶች እና በወያኔ ጦር የተጀመረ መሆኑን ምንጮች ከአከባቢው ተናግረዋል::