የተቃዋሚዎች አዳዲስ የትግል ስትራቴጂ የኢሕአዴግ ስጋት…በደቡብ ሱዳን አሶሳን አስታኮ እየተፈጠረ ያለ ችግር …. በአሶሳ የኦነግ ሰራዊት ነኝ ያለ ቡድን ካለቶክስ እጁን ሰቷል…….
የተቃዋሚዎች አዳዲስ የትግል ስትራቴጂ የኢሕአዴግ ስጋት ሆኗል::
– ዲያስፖራውን በድሪቶ ወሬዎች መጥለፍ ስራችን ሊሆን ይገባል::ብለዋል – በደቡብ ሱዳን አሶሳን አስታኮ እየተፈጠረ ያለ ችግር መኖሩን አንስተው ተወያይተዋል:: – በአሶሳ የኦነግ ሰራዊት ነኝ ያለ ቡድን ካለቶክስ እጁን ሰቷል ሲሉ ተደምጠዋል:: – በድርጅታችን ቢዝነሶች ላይ የሚጠሩ ባይኮቶችን የሚያደናቅፉ የተቃዋሚ ዲያስፖራዎችን ከበፊቱ በበለጠ መልኩ መተባበር እና አስፈላጊውን እርዳታ ማድረግ እንዳለባቸው ተወያይተዋል::
Minilik Salsawi
ከፍተኛ የወያኔው ቱባ ባለስልጣናት እና የደህንነት ሃላፊዎች በመጪው የአገዛዝ ሂደታቸው ላይ ተገናኝተው መወያየታቸው ከውስጥ አዋቂ ምንጮች የተገኘ ዘገባ ጠቁሟል:: በአፍሪካ ጎዳና ቦሌ መስመር ከሚገኝ ለባለስልጣናት ብቻ ክፍት ከሆነ የጎልፍ መጫወቻ ክለብ ውስጥ ተጠራርተው የተሰበሰቡት ባለስልጣናቱ የተቃዋሚዎች አዳዲስ እና ስልታዊ ስትራቴጂ እንዳሳሰባቸው እና የትግል ስልቱ ስጋት እንደሆናቸው በውይይታቸው አስቀምጠዋል::
በኤርትራ በኩል ያለውን እንቅስቃሴ መምታት ያስፈልጋል አያስፈልግም በሚለው ዙሪያ የተነጋገሩ ቢሆንም ለጊዜው እሱ ይቆይ እና በአሁን ሰአት ስጋት የሆነው የተቃዋሚዎች አዳዲስ የትግል ስልት እና የዲያስፖራው ከስልቱ ጋር መቀናጀት ስለሆነ ይህንን በፍጥነት በፕሮፓጋዳ እና በተግባር እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል::በድርጅታን ውስጥ የተሰገሰጉትን ተመሳስለው መረጃ የሚያቀብሉ እና የተቃዋሚውን እንቅስቃሴ የሚያበረታቱት የሚተረጠሩ ሁሉ ክትትል እየተደረገባቸው እንዲያዙ በሚለው የተስማሙ ሲሆን ከምርጫው በፊት እንደሁኔታው ታይቶ በሙስና እና የሃገርን ሰነድ በማባከን እንዲከሰሱ እንዲሁም አሸባሪ እየተባሉ የሚከሰሱ ሰዎች እንዲቀንሱ እና በሌላ የወንጀል ህግ አንቀጽ እንዲከሰሱ ያሉ ሲሆን አሸባሪ እያሉ መክሰስ ተቃውሞ እንዳበረከተ እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ብቻ የአሸባሪነት ክስ እንዲቀርብ ተነጋግረዋል::የሃገሪት ፖሊስ በተለይ ፌዴራል ፖሊስ ከበፊቱ በተሻለ መልኩ ጥቅማጥቅም እና መብቶች እንዲሰጡት በሚወስዳቸው እርምጃዎች ላይ እንዳይላላ ያደርገዋል ሲሉ ተደምጠዋል::
በደቡብ ሱዳን በኩል አንዳንድ ሃይሎች እየተፈጠሩ ስለሆነ ከመበራከታቸው እና ከመጠናከራቸው በፊት በአከባቢው ጥብቅ ቁጥጥር መደረግ እንዳለበት እና ባለፉት ወራቶች በቆረጣ እና በመረጃ ስብስብ የታገዘ እርምጃ በኦነግ ታጣቂዎች ላይ እንደተወሰደ ሳይጠቅሱ አላለፉም::የኤርትራ ፓስፖርት ይዘው በኡጋንዳ በማድርግ ወደ ደቡብ ሱዳን ዘልቀው በመግባት አሶሳ መስመር ላይ ስለላ ሲያካሂዱ የነበሩ ግለሰቦች የተያዙ ሲሆን ወርቁ የተባለ የኦነግ አባል የሆነ እና የዐኦ ዳውድ የቀድሞ ሹፌር ሊያመልጥ እንደቻለ ታውቋል::እጁን የሰጠው ቡድን ከኤርትራ ተደራጅቶ ይምጣ አሊያም እዛው ደቡብ ሱዳን ውስጥ ይደራጅ ጉዳዩ እየተጣራ መሆኑን የደህንነት ሃላፊዎቹ አስረድተዋል::
ዲያስፖራው አሁንም የኢሕአዴግ የእግር እሳት እንደሆነ በሚያስታውቅ ሁኔታ ጥልቅ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ዲያስፖራው በብዛት የድህረገጽ ተጠዋሚ ስለሆነ በድሪቶ ወሬዎች መጥለፍ ዋና ስራ እንዲሁም በውጪ የሚገኙ የተቃዋሚ አባላትን በተለያየ ጥቅማ ጥቅም በመደለል አስፈላጊ መረጃ ማሰባሰብ ሲሉ ውጪ አግር በሚገኙ የድርጅታችን የንግድ ስራዎች ላይ እንከን እንዳይፈጠር ባይኮት እንዳይጠራ አስታውጾ እያደረጉ እና ለሚተባበሩን የተቃዋሚ ዲያስፖራዎች አስፈላጊውን ትብብር እና ድጋፍ ማድረግ አለብን ሲሉ ተደምጠዋል::በማለት የውስጥ አዋቂ ምንጮች መረጃቸውን አድርሰውኛል::