ሕመም፡- አንድም ለትምህርት፤ አንድም ለሞት! —- ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
ጥንታውያን የአብነት ሊቃውንት፤ ‹ሕመም አንድም ለትምህርት፤ አንድም ለሞት ነው› ይላሉ። መታመሙን ላወቀ፣ መድኃኒቱን ለፈለገ፣ መድኃኒቱንም በትክክል ለወሰደ፣ ወስዶም ለዳነ ሰው ሕመም ለትምህርት ይሆነዋል፡፡ ሦስት ነገር ይማርበታልና፡፡ አንድም ዳግመኛ እንዳይዘው ጥንቃቄን፣ አንድም ቢይዘው ሊተርፍ የሚችልበትን መፍትሔ፣ አንድም ደግሞ ለሌላው የሚመክረው ልምድን …