ኣፈናና ዛቻ ያልበገራቸው የወሎ ወጣቶች ተጠናክረዋል።ባነሮችና ባንዲራዎች ተዘጋጅተው በመሰራጨት ላይ ይገኛሉ።

ኣፈናና ዛቻ ያልበገራቸው የወሎ ወጣቶች ተጠናክረዋል። በደሴና ዙሪያዋ ያሉ ወጣቶችን የማፈኑ ሂደት ተጠናክሮ ቀጥሏል። የደሴ ዙሪያ ወጣቶች በተጠናከረ መልኩ ለሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉት ዝግጅት የተጠናከረ ሲሆን ኣስፈላጊ የሆኑ ባነሮችና ባንዲራዎች ተዘጋጅተው በመሰራጨት ላይ ይገኛሉ።

ዛሬ ጠዋት ኮምቦልቻ ከተማ የታፈኑ ወጣቶች
1. ዘሪሁን ገሠሠ
2. ጀማል ኡመር
3. ተማም እና ሌሎችም ሥማቸው ያልታወቀ ወጣቶች በገፍ ታፍሠው ተወሥደዋል:: ዘሪሁን ገሠሠ የኮንቦልቻ ነዋሪ ሲሆን የወያኔ መንግሥት በአካባቢው ህዝብ ላይ የሚያደርሠውን ግፍ በተደጋጋሚ በማጋለጥ ይታወቃል! በዚህ የተነሣ ከዚህ በፊት ታፍኖ ከሁለት ወራት እሥር በኋላ የተለቀቀ ነበር። ዘሪሁን ገሠሠ በደሴና በኮምቦልቻ ከተሞች የሚደረገውን ሠልፍ ያሥተባብራል በሚል ከፍተኛ ማሥፈራራትና ዛቻ ሲደርሥበት እንደቆየ ይታወቃል!

የዘሪሁን ገሠሠ የፍርድ ቤት ማዘዣ ይህን ይመሥላል። የተጠረጠረበት ወንጀል ግን ግልጽ አይደለም!! ያው እንደተለመደው ፍርድ ቤት ቀርቦ ወንጀል ይጋገርለታል ማለት ነው።የደሴ ዙሪያ ወጣቶች በተጠናከረ መልኩ ለሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉት ዝግጅት የተጠናከረ ሲሆን ኣስፈላጊ የሆኑ ባነሮችና ባንዲራዎች ተዘጋጅተው በመሰራጨት ላይ ይገኛሉ።

Gashaw Mersha's photo.
Gashaw Mersha's photo.

ወያኔ በወሎ ከተሞች የሚደረገውን ሠልፍ ለማደናቀፍ የዘመቻ እሥር ከጀመረ ሠነባብቷል። አሁን ከመሸ በደቡብ ወሎ ቃሉ ወረዳ ሐርቡ ከተማ ውሥጥ ብዛት ያላቸው ወጣቶች እየታፈሡ ነው። በዚህ ሠዓት አብደላ ሙሃመድ የተባለን ወጣት ከቤቱ ይዘውት ሂደዋል!!የደሴ ዙሪያ ወጣቶች በተጠናከረ መልኩ ለሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉት ዝግጅት የተጠናከረ ሲሆን ኣስፈላጊ የሆኑ ባነሮችና ባንዲራዎች ተዘጋጅተው በመሰራጨት ላይ ይገኛሉ። እንግዲህ ሁላችንም ታሥረን እሥክናልቅ ድረሥ ትግሉ ይቀጥላል!