የዐማራ ተጋድሎ የነሃሴ 3 ቀን 2008 ዓ.ም (ከኹመራ እስከ ሸበል በረንታ) ዘገባ

በባሕር ዳር የዐማራ ፖሊስ በንዴት አምስት ፌደራሎችን ገድሎ ራሱን አጠፋ
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎AmharaResistance‬, ‪#‎የአማራ_ተጋድሎ‬ ‪#‎MulukenTesfaw‬ ‪#‎Miniliksalsawi‬

• (የገዱ አንዳርጋቸው መነሳት የዐማራን ተጋድሎ ወደፊት ያስፈነጥረዋል!!)
• የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር የነበረው ድርድር ያለስምምነት ተበትኗል
• በባሕር ዳር የዐማራ ፖሊስ በንዴት አምስት ፌደራሎችን ገድሎ ራሱን አጠፋ
• ‹‹አታልቅሱ፤ ልጄ ለተቀደሰ ዓላማ ተሰውቷል›› በባሕር ዳር ልጃቸውን ያጡ እናት
• ወረታ ከተማ የመጠጥ ውኃ ውስጥ መርዝ ሊጨምር የነበረው ግለሰብ እብድ ነኝ በማለት እያጭበረበረ ነው የዐማራ ተጋድሎ የነሃሴ 3 ቀን 2008 ዓ.ም (ከኹመራ እስከ ሸበል በረንታ) ዘገባ

Muluken Tesfaw – ኹመራ፤ በአሸባሪነት ስም የማንነት ጥያቄያቸውን ሊያደፋፍኑት ቢጥሩም እንደማይሳከ የወልቃይት ጠገዴ ዐማሮች ተናግረዋል፤
ዛሬ በኹመራ፣ በዳንሻና በአዲረመጥ ከተማ ያነጋገርናቸው የወልቃይት ጠገዴ ዐማሮች እንደሚናገሩት የማንነት ጥያቄያችን ለማዳፈን የአሸባሪነት ስም እየሰጡ በየሰአቱ ይፈትሹናል፡፡ አማርኛ የሚናገር ሰው ሁሉ እንዲሸማቀቅ ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል ብለዋል፡፡ ከኹመራ ያገኘነው ግለሰብ ‹‹አሁን የማወራህ ከፎቅ ላይ ወጥቼ ነው፤ በየቦታው እኛን የሚከታተል የትግራይ ሰው በየቦታው ነው፡፡ ያለንበትም ሁኔታ ያስጠላል›› ሲል የሚደርስበትን ጫና ገልጧል፡፡
የወያኔ ሰዎች አንዳንድ ዐማሮችን በገንዘብ በመግዛት መሣሪያ አስታጥቀው ወደ በርሃ በመላክ ከተወሰ ቀን በኋላ ‹‹ምሕረት ጠይቀናል›› ብለው ይመለሳሉ፡፡ በኋላም የወልቃይት ጠገዴ ዐማሮች እንዳስታጠቋው በመግለጽ ድራማ እንደሚሠሩ ገልጸዋል፡፡ በዚሁ አያይዘውም አንዳንድ መገናኛ ብዙሃንና የተቃዋሚ ድርጅቶች የወልቃይት ጠገዴን ዐማራ የማንነት ጥያቄ ዘገባ ሲሠሩ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ብሎም በእውነት ላይ የተመሠረተ እንዲሆን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
አርማጭሆ፤ በታችና በምዕራብ የአርማጭሆ እንዲሁም በጠገዴ አካባቢዎች ውጥረት እንዳለ ከቅራቅር ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸዋል፡፡ ባለፉት ሦስት ቀናት ኩርቢ አካባቢ ከ30 በላይ የመከላከያ ሠራዊትና ሦስት መኪኖች ሙሉ በሙሉ በሕዝቡ መደምሰሳቸው ታውቋል፡፡ ከሦስት መኪና ውስጥ ከነበሩ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ውስጥ ቁጥራቸው አምስት የሚሆኑ ብቻ በከፍተኛ ቁስል መትረፋቸው ነው የተነገረው፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ የቅራቅር ከተማ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ መውጣታቸው ይታወቃል፡፡ ትናንት ደግሞ ‹‹ኢትዮጵያ ሰላም እንድትሆን ካስፈለገ የአርማጭሆ ሕዝብ መሣሪያ ማውረድ አለበት›› በማለት ስብሰባ ላይ የተናገረ የሕወሓት ካድሬ በምዕራብ አርማጭሆ አብርሃጂራ ከተማ ተገድሏል፡፡

ጎንደር፤ በከፍተኛ ባለሥልጣናት የተካሔደው ስብሰባ ያለ ምንም ውጤት ተበትኗል
በጎንደር ዛሬ ነሐሴ 3 ቀን 2008 ዓ.ም. በአቶ አዲሱ ለገሠ እና በአቶ በረከት ስምዖን የተመራው የከፍተኛ ባለሥልጣናት ስብሰባ ያለ ምንም ውጤት ተበትኗል፡፡ የጎንደር ከተማ እና የሰሜን ጎንደር ዞን የካቢኔ አባላት ‹‹ከዚህ በኋላ ከሕዝባችን ጎን እንቆማለን›› ብለው ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል፡፡ በስብሰባው የተነሱ አጀንዳዎች ‹‹የተገደሉ ሰዎችን ኃላፊነት አገዛዙ ይውሰድ፤ የወልቃይት የዐማራ ማንነት ጥያቄ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈታ›› የሚሉ ሲሆኑ ከፍተኛዎች ባለሥልጣኖች ከሕወሓት በኩል የተሰጣቸውን ተልእኮ ለማስፈጸም ሙሉ በሙሉ ቢንቀሳቀሱም ተሳታፊዎች ትተዋቸው ወጥተዋል፡፡ በሽምግልና ለመፍታት የተደረገው ሴራም አልተሳካም፡፡ የካቢኔ አባላቱ ስብሰባውን ረግጠው ሲወጡ ችግር ይፈጠራል ተብሎ ቢሰጋም ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ምንም ዓይነት ነገር እንዳልነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ የሕዝቡ የእለት ተለት እንቅስቃሴም የተገደበ እንደሆነ ከቦታው የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ነገ ነሐሴ 4 ቀን 2008 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በጎንደር የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችን በአውሮፕላን የማስወጣት ሥራ እስከዛሬም ድረስ እየተከናወነ እንደሆነ ተገልጧል፡፡
ወረታ፤ በወረታ ከተማ የመጠጥ ውኃ ውስጥ መርዝ ሊጨመር ሲል የተያዘው ሰው እብድ ነኝ በማለት ለማታለል እየሞከረ እንደሆነ ዛሬ ከቦታው በስልክ ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸውልናል፡፡ ግለሰቡ ትግሬ ከመሆኑም በላይ ብዙም አማርኛ የማይችል ሲሆን የአእምሮ ጤነኝነት እንደሌለው ለማሳየት እየሞከረ ነው ብለዋል፡፡ አስተያየት ሰጪዎቹ ‹‹የአእምሮ ጤነኛ ያልሆነ ከሆነ እንዴት በድብቅ ያን ያክል ሰው ጨራሽ የሆነ ኬሚካል ለመጨመር ፈለገ? ምን ሊሠራና ማን ወረታ አመጣው?›› በማለት መገረማቸውን ገልጸዋል፡፡
ከወረታ ከተማ 25 ኪሎ ሜትር ያክል የሚገኙት የአዲስ ዘመንና የይፋግ ከተሞች እሁድ ለት የተጋድሎ ሰልፍ ከወጡ ወዲህ እስካሁን ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንደሌለ ነው የተገለጸው፡፡ በአዲስ ዘመንና በይፋግ በተጋድሎ የተሰው ሰዎች ብዛት ሦስት ነው ተብሏል፡፡
ደብረ ታቦር/ ነፋስ መውጫ፤ በደብረ ታቦር አንድ የኦሮሞን ሾፌር ሕዝቡ ጥበቃ አድርጎ ሸኝቶታል
በደብረ ታቦርና ነፋስ መውጫ ከተሞች እስካሁን ድረስ ውጥረት እንዳለ ነው፡፡ አንዳንድ ቅጥረኞች የተጋድሎ መሪ ናቸው ያሏውን ሰዎች በሌሊት እያሳፈኑ መሆኑን የታወቀ ሲሆን እነዚህ ግለሰቦች በቤተሰቦቻቸው እንዲመከሩ ተደጋጋሚ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ከነፋስ መውጫ ትንሽ ራቅ ብላ ባለችው የጨጭሆ መንደር ያሉ ዐማሮች እስካሁን ድረስ ተጋድሏቸውን አላቆሙም፡፡
በደብረ ታቦር ከተማ ቅዳሜ ለት በነበረው ተጋድሎ አንድ የተሳቢ መኪና የያዘ ሰው በተጋድሎው መካከል ሲመጣ ሕዝቡ መኪናውን ሊያወድም ሲል ‹‹እባካችሁ እኔ እንደናንተ የተገፋሁ ወገን ነኝ እንጅ ወያኔ አይደለሁም›› በማለት መታወቂያውን ሲያሳይ የኦሮሞ ተወላጅ ሆኖ ተገኘ፡፡ በዚህም ሕዝቡ ‹‹አንተማ የእኛው ወንድም ነህ›› በማለት ከሎሚ ዱር እስከ መሎ ድረስ ሰው ተመድቦ በሰላም እንዲሸኝ ተደርጓል፡፡
ባሕር ዳር፤ የባሕር ዳር ዐማሮች እስካሁን ትግል ላይ ናቸው፡፡ እሁድ በነበረው ተጋድሎ የዐማራ ክልል ፖሊሶች ከዱላ በቀር ምንም ዓይነት መሣሪያ እንዲይዙ አልተፈቀደላቸውም ነበር፡፡ የወያኔ ወታደሮችንና የፌደራል ፖሊሶች በዐማሮች ላይ የሚያደርጉትን ጭፍጨፋ የተመለከተ የዐማራ ክልል ፖሊስ ትናንት በንዴት አምስቱን የፌደራል ፖሊሶች ካጋደመ በኋላ ራሱን ማጥፋቱን ከቦታው በስልክ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ይህ ጀግና ለሌሎች የክልሉ ፖሊሶች ያሳየው አርአያነትን የሚያደንቁት የባሕር ዳር ወጣቶች ‹‹ራሱን ባያጠፋ ኖሮ በምንም መልኩ አሳልፈን አንሰጠውም ነበር›› ሲሉ በቁጭት ገልጸዋል፡፡
በጎጃም ሌላም የሰማነው አስገራሚ ታሪክ አለ፤ እሁድ በነበረው ተጋድሎ ልጃቸው የተሰዋባቸው እናት ለሀዘን የሚሔዱትን ዐማሮች ‹‹አታልቅሱ! የእኔ ልጅ የተሰዋው ለተቀደሰ ዓላማ ነው!! አባቶቻችን ለሕዝባቸውና ለአገራቸው ያደረጉትን መስዋትነት ስለከፈለ ደስተኛ ነኝ›› በማለት ሀዘንተኞችን ሲያጽናኑ በቦታው የነበሩ ዐማሮች በንዴትና በሚታያቸው ተስፋ የበለጠ ያነቡ እንደነበር የመረጃ ምንጫችን ከባሕር ዳር ተናግሯል፡፡
ባሕር ዳር ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ የማይታይባት ከተማ እንደሆነች የተናገሩት የመረጃ ምንጮቻችን በጢስ ዓባይና በዘጌ በኩል ያሉ ገበሬዎች ከመከላከያ በሚደርስባቸው ጥቃት ልክ አጸፋ እየሰጡ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል፡፡ በባሕር ዳር የሞቱት ሰዎች ከ70 በላይ ደርሷል፡፡ አንድ የዐይን ምስክር ‹‹ከ12 በላይ አስከሬን ሲነሳ ተመልክቻለሁ›› ብሏል፡፡
ደብረ ማርቆስ፤ ደብረ ማርቆስ ከተማ ቀጣይ ቅዳሜ የተጋድሎ ሰለፍ ለማካሔድ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል፡፡ የደብረ ማርቆስ ዐማሮች በቀጣይ ቅዳሜ በንጉሥ ተክለ ሃይማኖት አደባባይ ይወጣሉ፡፡
ሸበል በረንታ፤ የሸበል በረንታ ጀግኖች በወረዳው የነበረውን የጥይት መካዘን ተከፋፍለዋል፡፡ እሁድ ለት ለተጋድሎ የወጡት የሸበል በረንታ ዐማሮች በወረዳው አስተዳደር (ፖሊስ) ጽ/ቤት የነበረውን የመሣሪያ መካዘን ውስጥ የነበረውን የተለያየ መሣሪያ ዐማሮች ተከፋፍለዋል፡፡
የዐማራ ሕዝብ ትግል ያሸንፋል!!

12 Comments on “የዐማራ ተጋድሎ የነሃሴ 3 ቀን 2008 ዓ.ም (ከኹመራ እስከ ሸበል በረንታ) ዘገባ”

  1. እራሳችንን ከኢትዮጵያዊነት ጋር እናዋህድ አማራ ዘርን ይዳስሳል ኢትዮጵያዊነት ግን ሁላችንንም ያዋህዳል። አመሰግናለሁ

  2. ጀግና የሀገሬ ህዝብ የምታደርገው ጀግንነት ያኮራል፡፡እሰር ቤቶችን የወረዳው ፖሊስ ጣቢያዎችን፡ የወያኔ የንግድ ተቆማትና የወያኔ ተላላኪ የሆኑ ግለሰቈቦች እስከዛሬ ድረስ የመዘበሩህ ያንተው ገንዘብና ሀብት ነውና ለደሀው ወገንህ አከፋፋል፡፡አነስፈላጊ ሲሆንም ቀንደኞችን ለመያዣነት አፍናቸው፣፤ ሞት ለወያኔና ባሪያወቺ፡ኦህዴድና ብሀዴን

  3. You have to armed your self otherwise The crule agazi(agazen) hayenas will come to your door and will kill you just like animals.

  4. I am so happy to hear that woyanes are exposed in every corner of Ethiopia that they are the true enemies of our people. Those agazies has to be eliminated from our land, every Ethiopian has to watch his neighborhood who is living next to him and never trust any tegreans. Please Please never never trust tegreans, Remember “Leebe Tegray”

  5. Antil we have the true military who stands for our country not for some individuals, Amharas and Oromo has to armed themselves to defend their right from enemies like Tegreans woyanes.

  6. Only takes a village sir! Don’t we all be One.

    Kaldeferese Ayteram!

    Every where in the world there is no freedom without some kind of sacrifice!
    We may be killed, we have enough time to kill!

    There is no any human blood that ever been drained with out draining back! time is the only witness!

    For those youngsters in Ethiopia, please know that kill the Tigre that is most close to you! They declared already it is Amhara and oromo killing time!

    Killing them back will reduce the number of most key Tigre that help their time to kill longer.

    Trust me do it

  7. የባቢሎን ግንብ፤
    ተደማምጦና ተግባብቶ ቁም ነገር መስራት የተሳነው ሁኔታ ሲያጋጥም ብዙ ግዜ፣ ምነው የባቢሎን ግንብ ተገነባባችሁ እንዴ ይባላል።
    አሁንም በእኛ ኢትዮጵያውያን መካከል የዚያን ዓይነት ግንብ የተፈጠረ መስሎ ይሰማኛል።
    ተማርን የተባልነው ሳንቀር እርስ በርሳችን መናናቅ እንጅ ተከባብረን መስራት አልቻልንም። ልዩነት ባሕሪያዊ የሰው ልጅ ተፈጥሮ ነው፣ ቢሆንም አንዱ ያቀረበዉን ሃሳብ በጥሞና ማዳመጥ እና ለዚያ የሚሆን ምላሽ በሰከነና በሰለጠነ፣ በመከባበርና በመተሳሰብ ወዘተ መረዳት ሲቻል በተቃራኒው ይኬዳል።
    አንዱ የእኛ ኢትዮጵያውያን አደገኛ ባህርይ ደግሞ፣ በነገሩ ላይ የተስማማን መስለን ይሁን እንጂ ዉስጥ ዉስጡን አሸምቀን ሌላውን ለመጣል የቆየና እስካሁን ድረስ አብሮን የዘለቀ መጥፎ ዓመላችን ነው።
    ነገሮችን በግልጽ ማቅረብ ሳይሆን፣ ከበስተጀርባ ሃሜትና ሴራ በማውጠንጠን መስራት ነው የሚቀናን።
    ታዲያ እንደዚህ እየተሆነ ነው ኢትዮጵያን የምንገነባው፧ አንድን ብሔር እንደ ህዝብ ጠልተን በግርግር ወደ ስልጣን ለመዉጣት የሚደረግ ሩጫ፣ ያንን ህዝብ ድምጽ እወክላለሁ ብሎ የተነሳው ኤሊት፣ ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ ወክየዋለሁ ለሚለው ህዝብ ጥቅም መቆሙ አጠራጣሪነቱ ብዙ ግዜ የታየ ነው።
    ስለዚህ ረጋ ተብሎ ኃላፊነት በተሞላበት ስሜት ተግባብቶ መስራት ነው የሚሻለው እንጅ በብልጣብልጥነት እና በግርግር ሁኔታዎችን ለመቀየር መሞከር ሕገ ወጥ ከመሆኑ ባሻገር፣ የፈለገ የማይሰማ መንግስት ቢሆንም ቅሉ ህግ የማስከበር ኃላፊነት አለበት።
    ደርግ በዚያን ቀዉጢ የግርግር ወቅት እነ ኢህአፓ ህጻናት ልጆችን ድንጋይ አስይዞ መሳሪያ ከያዘ ኃይል ጋር እንዲጋጭ ባደረጉበት ጊዜ፣ ደርግ ከገጠመው ሁለንተናዊ ችግር ለመዉጣት ሁለት አማራጮች ብቻ ነበሩት።
    አንድ፤ አገሪቱን ኃላፊነት በሌለው ሁኔታ ለስርዓት አልበኞቹ ማስረከብና፣ ያገሪቱን ዕጣ ፈንታ እጁን አጣምሮ መመልከት፤
    ሁለት፣ አመጻዉን ቀልብሶ ስርዓት ማስያዝ።
    አሁንም ታዲያ ያጋጠመው የዚያን ዓይነት ክስተት ነው። ያሁኑ አስተዳደርን ጨምሮ ሌሎቻችንም ብንሆን ወጣቶቹን በዚያ ዘግናኝ መልክ ባረደበት ጊዜ የየራሳችን ፍርደ ገምድል አስተያየት ስንሰጥ ቆይተናል። ከበሮ ሲያዩት ያምር ዓይነት መሆኑ ነው። አሁንም ታዲያ ልክ እንደያኔው በግርግር በህጻናት እና ወጣቶች ሞት ሲነግዱ እንደነበሩት፣ በሞቀ ስፍራቸው ሆነው ያዝ በለው ግደለው፣ ወዘተ የዘረኝነት ቅርሻት ታጅቦ፣ ሌላ አገሩን ሊገነባና ከችግሯ ሊያላቅቅ የሚችልን ትውልድ ለማስጨረስ ላይ ታች መባሉ በጣም ያሳዝናል።

    እኔ የሚታዬኝን የመፍትሔ ሃሳብ እንደሚከተለው አቀርባለሁ፤
    ፩ኛ)በስልጣን ላይ ያለው የኢህአዲግ መንግስት የዘጋቸውን መድረኮች፣ ዜጎች ሃሳባቸውን በነጻ የመግለጽ መብቶች፣ የመሰብሰብ ወዘተ… ባስቸኳይ ክፍት ያድርግ፤
    ፪)ከህገ መንግስቱ በተጻረረ መልኩ ያወጣቸውን ጸረ ሽብር ህጎችን የመሳሰሉ ይሻር፤
    ፫)በፖለቲካና ዕምነታቸውና በነጻ ኅሊናቸው ምክንያት እስር ቤት ያጎራቸውን ዜጎች ይፍታ፤
    ፬)የዕርቅና የሰላም መድረክ በመፍጠር ያሉንን ቅሬታዎች በመግባባትና ይቅር ባይነት መፍታት፤
    ፭)ተቃዋሚ ፓርቲዎች ነን የምንልም ኃላፊነትና ድፍረት በተሞላበት ሁኔታ፣ በሰከነ መልኩ የህዝቡን ጥያቄ በግልጽ በመምራት ወጣት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ከመንግስት ጸጥታ ኃይሎች አላስፈላጊ ግጭትና ጉዳት እንዳይደርስ በግንባር ቀደምትነት የመምራት ኃላፊነት አለባችሁ፤
    ወጣት ምንጊዜም ትኩስ ነውና በአግባቡ ካልተመራና ካልተያዘ፣ ብዙ ጥፋት ያስከትላል። ይህንን ዝም ብለን እየተመለከትን ቆይተን ኋላ እገሌ ነው ያጠፋው ብለን ጣት መጠቋቆሙ ዕርባና አይኖረውም።
    ያለፈው አንድ ትውልድ ምሁር ያጣነዉም በእንደዚህ መልክ ነበር። አዎ ላንዳንድ ባለ አጀንዳዎች ታጋይ ቢሞት ትግል አይሞትም እያሉ የሚያደናግሩባት ቃል አለቻቸው።

    ወጣቶች ሆይ፤ የጡረታ መውጫ የደረሰባቸው አጀንዳ ትታችሁ ወደፊት ለናንተ የምትሆን አገራችሁን የስርዓት ባለቤትና ተምሳሌት እንድትሆን ተግታችሁ ስሩ።

    ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኖራለች።

  8. Very poor የሽወዳ ሙከራ።ትዮጵያ ታፍራና ተከብራ••••••••ወዘተ። ንጹሃን ዜጎችን በሰላም የወጡትን ወጣቶች በአጋዚ ትግሬ የጨረሰው ወያኔ ሁኖ ሳለ ሕዝቡን ተጠያቂ ማድረግ ምን ለማት ይሆን ? ? ? መንግስት እያልክስ የምትጠራው የትኛውን መንግስት ነው ? ? ? ? አይ የደደቢት ሊቃውንቶች ! ! ! ዕውነትም ደደብ። ሕገመንግስቱስ ያልከው የቱ ነው ? ? ? የደደቢቱ አይሰራም ሕገመንግስቱ ! ! ! ! ወያኔ በራሱ ሕገመንግስት ተጠልፎ ውድቋል እኮ።አይ የደደቢት ልቅ ! !

  9. amharawe must stand for you right.fight tigra. kill tigra wayne.this revolt not for ethiopawent . this stragle is for amharawent

  10. የአማራ ህዝብ ኮራንባችሁ፡ ይህን ደንቆሮና የመሀይም ክምችት የሆነውን ዘራፊ ወንበዴ ጠራርጋችሁ ውሻ መቅበሪያ ዉስጥ ሳትጨምሩ እንዳትመለሱ አደራ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*