ዜጎችን መታደግ የማይችሉ የሃይማኖት መሪዎች ቆባቸውን ያውልቁ::በዜጎች ላይ የሚደርሱ በደሎች የማይቆረቁራቸው የሃይማኖት አባቶች ሊወገዱ ይገባል። (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ለሶስተኛ ጊዜ
ዜጎችን መታደግ የማይችሉ የሃይማኖት መሪዎች ቆባቸውን ያውልቁ::በዜጎች ላይ የሚደርሱ በደሎች የማይቆረቁራቸው የሃይማኖት አባቶች ሊወገዱ ይገባል። (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ለሶስተኛ ጊዜ
Minilik Salsawi – mereja.com – በኢትዮጵያ በሃይማኖታዊ የመንፈስ ጥኡም ሰበካና ዜማ ጋር በማጣፈጥ የጨቋኞችን የበላይነት በመስበክ ሕዝብን ማስፈራራት እና ማሸማቀቅ የጳጳሳት እና የሼህዎች አብይ ተግባር ነው።ዜጎችን መታደግ የማይችሉ በአስቸኳይ ቆባቸውን አውልቀው ከተራው ሕዝብ የመቀላቀል ግዴታ አለባቸው።ቤተክርስቲያን እና መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ እጅና ጓንት ሆነው በኢትዮጵያውያን ላይ የማያባራ ጭቆና ማካሄድ ከጀመሩ ረዥም ዘመናት ተቆጥረዋል። ይብልጡኑ የመንግስቶች ጎህ ከቀደደ ጀምሮ በተለይ የተዋህዶ ሃይማኖት መሪዎች አስፈሪ እና አስደንጋጭ እንዲሁም አሳዛኝ ደግሞም አሳፋሪ ቃላቶችን በመጠቀም ስጋዊ እና ምድራዊ ስልጣኖችን ለገዢዎች ለማደላደል ይህ ነው የማይባል ግፍ በምእመናኖቻቸው እና በሌሎች አማኞች ላይ ፈጽመዋል አስፈጽመዋል፤ እየፈጸሙ ነው፤ እያስፈጸሙ ነው። ይህ የማይዋጥለት አሊያም የሚክድ ካለ እውነት የማይደላው ብቻ ነው።

የኢትዮጵያ ጨቋኝ መንግስታት የሆኑ ከጥንት እስከ ዛሬ የተንሰራፉ በህዝብ ላይ የሚያደርጉት ጭቆና እና በደል ታሪክ የማይሽረው ጠባሳ በሰው ልጆች የትውልድ ሂደት ላይ መፍጠሩ እንደተጠበቀ ሆኖ የሃይማኖቶች ሚና ግን እጅግ በሚያሳዝን መልኩ ዜጎች በግፍ በጨቋኝ መንግስቶች ሲታረዱ በመባረክ የመንግስታቱን እድሜ አስረዝመዋል አሁንም እያስረዘሙ ነው። የመንግስት እና የሃይማኖት ቁርኝት የሚፈለገው ስልጣንን አደላድሎ ለመያዝ እና ህዝብን ረግጦ ለመግዛት ካለ ምኞት እንጅ ለዜጎች ከመቆርቆር የመነጨ አይደለም።ምንሊክሳልሳዊ የሃይማኖት አባቶች በሃይማኖታዊ የመንፈስ ጥኡም ሰበካና ዜማ ጋር በማጣፈጥ የጨቋኞችን የበላይነት በመስበክ ማስፈራራት እና ማሸማቀቅ የጳጳሳት እና የሼህዎች አብይ ተግባር ነው።በኢትዮጵያ ውስጥ ተገዝተው አሊያም አድርባይ ሆነው በመስራት ላይ ያሉ የሁሉም ሃይማኖት መሪዎች እጅግ ጥንቃቄ በጎደለው ሁኔታ በዜጎች ላይ የሚደርሱ ግድያዎች ድብደባዎች እስሮች እና መንገላታቶችን እንደ አንድ መንፈሳዊ የሃይማኖት መሪ እንደ ሰብአዊ ተፈጥሮ አሊያም መጽሃፋቸው እንደሚያዛቸው ለዚጎች ሲደራደሩ ሲከራከሩ ሲያወያዩ ሲሆንም አንተም ተው አንተም ተው ሲሉ ሲያስታርቁ ሲያቻችሉ አልታዩም ከዚህ በከፋ መልኩ በልማታዊ ዲሞክራሲ የፖለቲካ ፉጨት ስር ተደብቀው በመንፈሳዊ ካባ ስር በለው በሚል አብዮታዊ ዜማ ዜጎችን እያስፈጁ ይገኛሉ።
አንድ የሃይማኖት አባት የታመመ ሲጠይቅ፤ የሞተ ሲቀብር ፤የተቸገር ሲረዳ ፤የታሰረ ዞሮ በመጎብኘት ሲያጽናና እንጂ ሲፖተልክ አሊያም ሲወሸክት ማየት ያማል። በሃገራችን ምእመናንን እንምራለን የሚሉ ሕዝብን መንፈስ እንመግባለን የሚሉ የለሊት ወፍ የሆኑ የክርስትና እና እስልምና የሃይማኖት መሪዎች ዜጎችን መታደግ የማይችሉ ከሆነ በአስቸኳይ ቆባቸውን አውልቀው ከተራው ሕዝብ መቀላቀል ግዴታ አለባቸው። ይህ ጉዳ
ይ የብዙሃኑ የዜጎች ጉዳይ ስለሆነ ክርስቲያን እስላም የሚባልበት ሳይሆን የኢትዮጵያውያን የጋራ ጉዳይ ነው።በሃገሪቱ ዜጎች በአለም ላይ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በነጻነት በመጻፋቸው የእኩልነት እና የነጻነት ጥይቄ በማንሳታቸው ብቻ አሸባሪ ተብለው እስር ቤት በታጎሩባት ኢትዮጵያ ጉዳዩን እስኪ ላስጠናው ላጥናው ያለ የሃይማኖት መሪም ይሁን የሃይማኖት ሃራጥቃ የለም። እንዲሁም በታሰሩ ሰዎች እና በአሳሪዎች መካከል እርቀ ሰላም እንዲወርድ ለወደፊቱ ስህተቶች ካሉ እንዳይደገሙ ነገሮችን ለማግባባት እና ለማቻቻል የፈቀደ አንድም የሃይማኖት መሪ የለም። ይብስኑ የሃይማኖት መሪዎቹ በየስብሰባው እና በየጭብጨባው ዜጎች የመንግስታዊ ሽብር ዱላ ሰለባ እንዲሆኑ እያበረታቱ ይገኛሉ ።ምንሊክ ሳልሳዊ
የዜጎች ሁኔታ ያሳሰባቸው የሃይማኖት መሪዎች በከፍተኛ ዛቻ እና ማስፈራራት እንዲሁም በጥቅም በማሰር እንዳይንቀሳቀሱ አሊያም በተዘዋዋሪ ባልሰሩት ወንጀል ለማጥመድ ሴራ በመጎንጎን እያስፈራሩ የህዝቦችን የሰብ አዊ መብት ጥያቄዎች እንዳያነሱ በማስደንገጥ እንዲሁም በጥቅማ ጥቅም እና በገንዘብ በመደለል አባትነታቸውን ለስጋዊ ባለስልጣናት እንዲሸጡ እና የፖለቲካ ምንዝር እንዲፍጽሙ እየተደረገ ሲገኝ ይህንን የምንዝር ጌጥ ከመለማመዳቸው የመጣ የሃይማኖት አባቶች ከጨቋኞች ብሰው በሕዝብ ላይ ከፍተኛ በደል እንዲፈጸም ከባዱን ሚና እየተጫውቱ ይገኛሉ ።
የሃይማኖት አባቶች ሰጥ ለጥ ብለው ስለልማት ብቻ እንዲሰብኩ የእስላሙንም ሆነ የክርስቲያኑን ጥያቄዎች በተገኙበት እንዳያስተጋቡ ማስጠንቀቂያ ለቄሶች እና ጳጳሳት እንዲሁም የወያኔ መንግስት በቅርቡ ለሾማቸው የእስልምና ምክር ቢት ሼሆችን ከፍተኛ የሆነ ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል። እኔ ስጨፈጭፍ እናንተ አጨብጭቡ የሚለው አሸባሪው የወያኔ መንግስት ሃይማኖቶችን በራሱ አይዲኦሎጂ በመቀረጽ ቀሚሳቸውን ያንዥረገጉ ሰላዮችን እና የሃይማኖት ነቀዞችን በመመደብ ዜጎችን በተመለከተ የሚደርሱ በደሎች እና ገፈፋዎች ጠያቂ እንዳያገኙ አስታራቂ እንዳይሹ አድርጓል።ዜጎቹን የማይታደግ የሃይማኖት መሪ ቆቡን አውልቆ ከፖለቲካው ጎላ ሊቀላቀል አሊያም ገለልተኛ ሰው ሆኖ እንዲቀመጥ ለመምከር እንፈልጋለን ። ምንሊክሳልሳዊበኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሃይምኖቶች ለመንግስታዊ ሽብር ተገዢ እና ታዛዥ እንዲሁም የሽብር ሰባኪ ሆነው ዜጎችን በአደባባይ እያስግደሉ ዜጎች ከሞቱ በኋላ በሃይማኖታቸው ስርአት እና ደንብ እንዳይቀበሩ ተጽእኖ በማድረግ ለምድራዊው የጨቋኝ ምደብ ተባባሪ እና አስተባባሪ በመሆን ከባድ ወንጀል እየፈጸሙ ይገኛሉ። ስለዚህ በዜጎች ላይ የሚደርሱ በደሎች የማይቆረቁራቸው የሃይማኖት አባቶች ሊወገዱ ይገባል። #ምንሊክሳልሳዊ
የሃይማኖት ኣበቶቻችን ከዝ ነገረ እራሰቸውን ቆጥቡ ¡
The so called Patriarch judged the public to be wrong and implicitly hold them accountable for the deaths, etc.
But I say this to Mr. Mathias: Mathias, you are the father of lies, not me but the holy book declares:
‘You are of your father the devil (TPLF), and your will is to do your father’s desires. He was a murderer from the beginning, and has nothing to do with the truth, because there is no truth in him. When he lies, he speaks out of his own character, for he is a liar and the father of lies.’ [John 8:44]
Mathias, you don’t qualify to be a patriarch. Nor you are a believer that is why I prefer to refer you Mr.
Leaders or believers of the faith are commended this: ‘Let what you say be simply ‘Yes’ or ‘No’; anything more than this comes from evil’ ,(Matthew 5:37).
Thus, you and your subordinates are like the pharisees who charged Lord Jesus Christ. Charging (judging) the public is charging God (Jesus Christ)!
Hallelujah, alike the Lord, the public will win and you the evil will go to grave for ever
የሃይማኖት አባቶች ተባሉ እንደት በምን መስፈረት ሕዝብ ሲያልቅ የት ነበሩ አብረው ዶልተው በሉዋቸው አልተፈራረሙም ይሆን በጎሳ የተሰበሰቡ ሃይማኖት የሌላቸው ሊኖራቸው የማይችሉ ገንዘብ አፍቃሪዎች በወያኔ ቅኝት የተቃኙ በእምነት ሰበብ የሃይማኖትን ዋጋ የሚያሳቱ የ666 ጥርቅሞች!
የሃይማኖት አባቶች ተባሉ እንደት በምን መስፈረት ሕዝብ ሲያልቅ የት ነበሩ አብረው ዶልተው በሉዋቸው አልተፈራረሙም ይሆን በጎሳ የተሰበሰቡ ሃይማኖት የሌላቸው ሊኖራቸው የማይችሉ ገንዘብ አፍቃሪዎች በወያኔ ቅኝት የተቃኙ በእምነት ሰበብ የሃይማኖትን ዋጋ የሚያሳጡ የ666 ጥርቅሞች!
( the so called “OLF and patriots g7 non-sense members & supporters” ) እናንተ
ጠጅ ና አረቄ ቤት ማቅራራትና ተረት መተረት እንጅ ሌላ ምን ክህሎት አላችሁ.
ስራ መስራት አትወዱ፣ ሌላዉን አታሰሩ፣
በባዶ መኮፈስ፣ መጀነን፣ መንጠራራት ብቻ!
አንድነት ትርጉሙ የማይገባችሁ፣ ሃይማኖት ትርጉሙ የማይገባችሁ
ምኞታችሁ እንደ ሳኡዲ ወሃቢ ንጉሳዊ ቤተሰቦች ቤተ መንግስት ግቢ ተኝቶ ህዝብ መግዛት
ለማንም ከሰማይ ተቆርሶ የተሰጠ መሬት የለም
ምድር የፈጣሪ ናት
በሰላም ና በህግ መኖር ብቻ ነው የሚጠበቀው
የመርገምት ልጆች ናችሁ፣ ፈጣሪ እናንተን ረግሙዋል
Ye Hayimanot Tirgumunima Bitawkut Noro Yhe Hula Hizib Ayalikim Neber Beteley Ye Ethiopia Ortodox Tewahido Bebizat Yemenigisit Adrewoch Nachu Malet Yichalal Anidim Ken Le Hlinachu Seritachu Atakum Geziw Parti Memeriya Sisetachu Bicha Erik Eyalachu Sew Tasifejalachu Esikezarem Be Egziabher Hayil New Yenorinew Wedefitim Esun Yizen Eninoralen Erik Eyalachu Atasifejun Bemejemeriya Wisitachihun Atsidu Bebado Meda Mekofes Waga Yelewim
DIL LE ETHIOPIA HIZIB
ETHIOPIA LEZELALEM TINUT
Ginbot 7 be Orthodox haiymanot lay
ketnsa qoytoal gebe haile tebyewum
bête kerstian lemafrs gedag hulu tesxtxot
neber . Yihiem betqnbabre NETSANT LE ETHIOPIA
bemibal Radio ke Demtsachin Yisema yemibal
Akrari terrorist buden gar bemetbabr.
altesakam sewochum tawqwal .
Alemeye , Asteraye , Amare , Philipos yemibalut
wangnochu nachew .
ሰላም ለሀገራችን
Ginbot 7 ina Demtsachin Yesema be ORTHODOX
HAYMANOT LAY MEZMET KEJEMERU SENEBABTOAL.
INDIYAWUM KE AKRARIWOCHU GAR “ALLAH AL KEBER”
YEMILU KERIATIAN NEN BAYOCH MELMELWAL .
kENEZIHM ASTERAYE , AMARE KASSAYE , PHILIPOS
WANGNA YE PROPAGANDA MEDIACHW ” NETSANET LE ETHIOPIA”
YEMIBAL YETAWKE YE SHABIA TELALAKI ALEMEYE YEMIBAL
HODAM SHEMAGLE NEAW .
This are Woyanes under the Cover of Religion. We know that.
All relgion leaders are woyana. They are not speaking for last 25 years when 130,000 is dying or 1500000 peoples in jail.
You guys are devil no one hear you now!
No trust on you LABOCH!
Yehaymanot abat minamin inatachu tibeda. shermuxa. ansemachum. tebedu. igna minfeligew weyane kesiltanu endiwerd bichanew.