ፀረ አደንዛዥ/ሱስ አስያዥ ዕፅ ንግድ ምክክር DW Amharic October 13, 2014 Tagged with Amharic, amharic news, Ethiopia, ethiopian news in amharic, Ethiopians, News in Amharic የአፍሪቃውያት ሀገራት ሚንስትሮች አደንዛዥ እና ሱስ አስያዥ ዕፅ ስለደቀነው ስጋት ሰሞኑን መከሩ። አፍሪቃ ብዙ አደንዛዥ እና ሱስ አስያዥ ዕፅ ባይመረትባትም፣ ለሕገ ወጡ ዓለም አቀፍ የአደንዛዥ እና ሱስ አስያዥ ዕፅ ንግድ መሸጋገሪያ መሆኗ የአህጉሩን መንግሥታት በማሳሰቡ፣ ይህንኑ ሕገ ወጥ ንግድ መቆጣጠር ስለሚቻልበት ሁኔታ በስፋት ተወያይተዋል።