ሳሚ ቺቺሮቮ ከ አልጄሪያ ነኝ የሚለው ይህ ግለሰብ የኢትዮቴሌኮም ዋና ድረገፅ ሙሉ ለሙሉ በመቆጣጠር የድርጅቱን መልዕክት በራሱ መቀየሩን ድሬቲዩብ ከድረገፅ ተመልክቷል. ኢትዮቴሌኮም በዚህ ጉዳይ ላይ የሰጠው መግለጫ የለም, በደንበኞች ላይ ሊያደርስ የሚችለው ጉዳት ወይም እያደረሰ ያለውን ጥቃት ለማወቅ አልተቻለም. ኢትዮቴሌኮም በአፋጣኝ ድረገፁን በቁጥጥር ውስጥ አድርጎ የደረሰውን ጉዳት ሊያሳውቅ ይገባል. ይህ ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ኢትዮ […]

በኢትዮጵያ የሚገኘው የፍትህ ስርዓት ራሱን እንደ ካሮት ቁልቁል ማሳደግ ከጀመረ ዘመናት ተቆጥረዋል በተለይ ከቅርብ አመታት ወዲህ የፍትህ ስርዓቱ ዋነኛ መገለጫ በሆኑ ፍርድ ቤቶች ዳኞች ውሳኔ የሚሰጡባቸው ጉዳዩች << ፍትህ >> መሳቂያ መሳለቂያ መሆኗን በገሃድ እያሳዩን ይገኛሉ በእነ ኤልያስ ክፍሌ የክስ መዝገብ ስሟ ሰፍሮ በ 2004 በቁጥጥር ስር የዋለችው ወይዘሮ ሂሩት ክፍሌ የፍትህ ስርዓቱ ወደለየለት ውርደት […]

በቅርቡ ክሳቸው ተቋርጦ በነጻ የተሰናበቱት ጋዜጠኞች ወደ ቀድሞ ሞያቸው ለመመለስ ፍራቻ አድሮባቸው እንደሚገኝ ገለጡ። ከአንድ አመት በላይ ከስድስት ጦማሪያን ጋር በሽብርተኛ ወንጀል ክስ ቀርቦባቸው የነበሩት ጋዜጠኛ ዘላለም ክብረት እና ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ ወደ ጋዜጠኝነት ላመመለስ ፍራቻ አድሮባቸው እንደሚገኝ ከCBS ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ መልልስ ገልጸዋል። ይሁንና የእስር ጊዜዋን አጠናቅቃ በቅርቡ የተፈታችው ጋዜጠኛ ሙያዋን እንደምትቀጥልና […]

በማለዳ ከእንቅልፌ በመንቃት ጉዞዬን ልደታ ወደሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት አደረኩ፡፡ ጉዞዬን ወደ የልደታው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያደረኩት ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት፣ በዛሬው ዕለት ‹‹በእነሶልያና ሽመልስ›› የክስ መዝገብ ስር ለሚገኙትና ከእስር ያልተለቀቁት ጦማሪያን አጥናፍ ብርሃኔ፣ በፍቃዱ ሀይሉና ናትናኤል ፈለቀ ላይ ፍርድ ቤቱ ብይን ለመስጠት መዝገቡን ለሐምሌ 22 ቀን 2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቶበት ስለነበረ ነው፡፡ […]

ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ከትላንት በስቲያ ከኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር ባደረጉት አዲስ አበባ ዉስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ ጉባኤ ለጋዜጠኛ ጥያቄ በሰጡት መልስ የዚያችን አገር መንግስት በዴሞክራሲያዊ መንገድ እንደተመረጠ አድርጎ መግለጻቸዉ ከብዙ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች ትችት አስከትሏል። Freedom House  የተባለዉ መሰረቱ እዚህ United States  የሆነዉ ድርጅት ኢትዮጵያ ተገቢ ያልሆነ ሙገሳ ከUnited States  ተትሮአታል ሲል መግለጫ […]

የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ድርጊቱ የተፈጸመው ንብረትነቱ የቱርክ የሆነና በጥጥ ማምረት ስራ ላይ የተሰማራውን የቶረን የእርሻ ኩባንያ ገንዘብ ጭኖ በመጓዝ ላይ ባለ መኪና ላይ ነው። የኩባንያው ሃላፊዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአሜሪካ ዶላርና ብር ይዘው በ7 የልዩ ሃይል ፖሊስ አባላት ታጅበው ወደ ወንዶ ጎጊ ወረዳ በሚጓዝበት ወቅት፣ አንደኛው ወታደር ለመጸዳዳት በሚል መንገድ ላይ ከወረደ በሁዋላ፣ ጥይቱን አቀባብሎ […]

በረከት በህይወት የሉም ! በጅዳ የሚገኘው« ብግሻን» ሆስፒታል የምርመራ ውጤት። ኢትዮጵያ ሃገሬ ጅዳ በዋዲ ጅዳ ሳውዲ አረቢያ ለህክምና በድብቅ ገብተው የልብ በሽታ ህክምና የተደረገላቸው የመንግስት ከፍተኛ ሹም በህይወት መኖራቸውን እንደ ሚጠራጠሩ ከሆስፒታሉ የሚወጡ ምስጢራዊ ምንጮች አረጋገጡ፡፤ በልብ በሽታ የሚሰቃዩት አቶ በረከት ለህክምና ጅዳ ሳውዲ አረቢያ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል ህክምናቸውን ተከታትለው ወደ ሃገር ከተመለሱ ወዲህ የጤንነታቸው […]

ኦባማ በአፍሪካ ኅብረት ያደረገው ንግግር ብዙ ጥያቄዎችን መልሷል፤ የኦባማ ጉብኝት ያስከተለው ጫጫታ ሁሉ መልስ አገኘ፤ የሰው ልጆች በመሀከላቸው ምንም ዓይነት የአድልዎ ልዩነት ሳይደረግባቸው በሰውነታቸው ብቻ በተፈጥሮ ያገኙትን ክብራቸውንና መገሣቸውን አስከብረው መኖር እንዳለባቸው በአጽንኦት ተናገረ፤ ዛሬ የአሜሪካኑ ፕሬዚደንት ያደረገው ንግግር ከፕሬዚደንትና …

ኦባማ የአፍሪካን ገዢዎች እያዋዛ ደቆሳቸው! ፕ/ሮ መስፍን ወልደ ማርያም Read more »

በደቡብ ኢትዮጵያ ሸካ ዞን የሚገኙ የቴፒ ወጣቶች በህወሓት አገዛዝ የሚደርስባቸው በደል አንገሽግሿቸው ራሳቸውን አደራጅተው በአገዛዙ ላይ እርምጃ መውሰድ ከጀመሩ በርካታ ወራት ተቆጥረዋል። እነዚህ ወጣቶች ግንቦት 27 ቀን 2007 ዓ.ም. በአካባቢያቸው የሚገኝን አንድ የፓሊስ ጣቢያ ወረው እስረኞችን ማስፈታታቸው በመላው ኢትዮጵያ እንዲታወቁ ምክንያት ሆኗል፤ የአገዛዙ ሚዲያም ድርጊቱ መፈፀሙ በተዘዋዋሪም ቢሆን አምኗል። ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለዲሞክራሲ፣ ለእኩልነት እና ለአገር […]

ከአክሱም ወደ አዲስ አበባ 63 መንገደኞች አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ኮድ 3 የሰሌዳ ቁጥሩ 51672 ኢትዮጵያ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ነጋሽ በተባለ ቀበሌ አቅጣጫ ስቶ 300 ሜትር ጥልቀት ባለው ገደል በመግባቱ መሆኑን በክልሉ የትራፊክ ደህንነትና ቁጥጥር የግንዛቤ ማሳደጊያ አስተባባሪ ምክትል ኢንስፔክተር አበበ ሙላው ገልጸዋል። በአደጋው 15 መንገደኞች ወዲያው ስድስቱ ደግሞ ወደ ህክምና በመሄድ ላይ እያሉ ህይወታቸው ማለፉን […]

ኦባማ “ዴሞክራሲ ማለት ፎርማል ምርጫ ማለት ብቻ አይደለም” ሲል አዳራሹ በአንድ እግሩ ቆመ ጭብጨባው ቀለጠ ፉጨቱ አስተጋባ ሁሉም በዚህች ሰበብ ምርጫ እያጭበረበሩ እዴሜ ያራዝሙ ስለነበር እውቅና ያገኙ መሰላቸው። የኦባማ ንግግር ግን ባላሰቡት መንገድ ነበር የቀጠለው። “ጋዜጠኞች ስራቸውን በመስራታቸው የሚታሰሩ ከሆነ፣ …

የኢትዮጵያ መንግስት በዲሞክራሲያዊ ምርጫ የመጣ ነው በማለት እጅጉን አስቀይሞን የነበረው ኦባማ ዛሬ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ልዩ ሆኖ ቀረበ። Read more »

ዊክሊክስ ባወጣው መረጃ ላይ የኢትዮያና የኬንያ ገዢዎች ሶማሊያን ለአራት ቦታ በመክፈል ለመቀራመት በሚስጥር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስነብቧል። ሶማሊያ ለም እና በማዕድን የበለጸገ ምድር ባለቤት በመሆንዋ የብዙ ሀገራትን ፍላጎትን ትስባለች።ዊክሊክስ ጅቡቲ ከሚገኘው የሳዑዲ አረቢያ ኤንባሲ መረጃውን እንዳገኘው ገልጿል።በአሁኑ ወቅት ብዙ አገራት በሶማሊያ ውስጥ ይገኛሉ፤የተወሰኑት በግፊት እንዲወጡ ተደርገዋል ብሎአል። ሶማሊያ ለአራት ክልል ትከፈላለች ሁለቱን ኢትዮጵያ ስትወስድ ቀሪውን […]

በህብረት ለመብታችን በሁለት እግራችን በትክክል ስንቆም ማንም ከስራችን አይጠፋም!!! እንደ ወያኔ አይነት መንግስት አለም ላይ ቢዞር ሃይማኖተኞችን፡ጋዜጠኞችን፡ተቃዋሚዎችን፡እንዲሁም ማንኛውም የነሱን አመለካከት የማይደግፉ ዜጎችን አሸባሪ ብሎ ካለጥፋታቸው የወነጀለ አንድም መንግስት የለም። 100% አሸናፊ አምባገነኖቹ ምኞታቸው የገዛ የሃገራቸውን ነጻነት ናፋቂ ዜጋ አለም አቀፍ አሸባሪ ማሰኘት ነበር። እነሱ ይበሉን እንጂ በአሸባሪነት የሚያስፈርጀንን ማስረጃ ልክ እንደለመዱት ካንጋሮ ፍርድ አጭበርብረው ማቅረብ […]

‹‹ኦባማ ኢህአዴግን በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የተመረጠ ነው ማለታቸው የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ግንባታ ላይ ውሃ የሚቸልስ ነው›› • ‹‹ኢህአዴግ የጠራው የቅንጦት ግብዣ ላይ መገኘት የህዝቡን ሰቆቃ እንደመርሳት እቆጥረዋለሁ›› የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የኢትዮጵያ መንግስት ዛሬ ሀምሌ 20/2007 ዓ.ም ምሽት 1፡00 ሰዓት ላይ ቤተ መንግስት ውስጥ ለአሜሪካው ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ የሚያደረገው የእራት ግብዣ ላይ እንደማይገኙ ለነገረ ኢትየጵያ […]

ፕሬዚዳንት ኦባማ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ከመጀመራቸው በፊት የብሔራዊ ጸጥታ አማካሪ የሆኑት ሱዛን ራይስ ወደኬኒያ እና ኢትዮጵያ ስለሚደረገው ጉብኝት መግለጫና ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሸ ሰጥተው ነበር፡፡ የጉብኝት ዝርዝር መርሃ ግብር በማስረዳት ንግግር የጀመሩት ራይስ ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከኢህአዴ ሹማምንትና ከአፍሪካ ኅብረት ኃላፊዎች …

የሱዛን ሳቅ – ምርጫ መቶ በመቶ ማሸነፍ ምን ያስቃል? Read more »

በታህታይ አድያቦ ወረዳ አካባቢ የሚገኙ የገዢው የኢህአዴግ ስርዓት ወታደሮች እርሰ በራሳቸው እየተገዳደሉ እንደሚገኙ ተገለፀ። በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ታህታይ አድያቦ ወረዳ ተሰማርተው የሚገኙ የኢህአዴግ መከላከያ ሰራዊት በመካከላቸው አንድነትና ፍቅር እንደሌላቸው የገለፀው መረጃው በተለይ ደግሞ በአባላትና በአዛዦች መሃል በተከሰተው ያለመስማማት ምክንያት ወታደር ታዘዘ ደበበ የተባለ ግለሰብ መቶ አለቃ አስራት ባዩና አምሳ አለቃ ካሳ አለሙ የተባሉን በጥይት […]

መቼም የአሜሪካን ፕሬስደንት ባራክ ኦባማን ለመቀበል ምስራቅ አፍሪካ ሺር ጉድ ስትል ከርማለች በተለይ አገራቺን ኢትዮጵያ የህነን ጉብኝት ያማረና የተሳካ እንዲሆን ከአቅሟ በላይ ስትጥር ስታፀዳ ከርማለች በተለይም በ100% ሙሉ በሙሉ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመርጠዉ(እረ ጎበዝ ሳቄ አመለጠኝ ) ገዢዉ ኢህአዴግ ለከሰረ ፖለቲካው ግባአት ለማድረግ እላይ ታች ሲል መከረሙ ይታወሳል፡፡ በርግጥ ባራክ ኦባማ ይህ ጉብኝት ተኩረቱና ዋና አላማዉ […]

የወያኔ ቅጥር ሰራዊት የሽምቅ ሐይል ስምሪት ክፍል በሶስት አቅጣጫዎች በተለይም በትግራይ ጠረፍ በአብረሐ ጅራ፣ በጎንደር ወልቃይት ጠገዴ በባሌ በኩል ከባድ ዉግያ እንደገጠመዉ የሚጠቁሙ መረጃዎች ትናንት ማምሻዉን በአስቸኳይ መልዕክት ለበላይ አካላት የተላለፉ ሲሆን፥ እንዲሁም በአርማጭሆ ህዝብ እና በሰራዊቱ መካከል እየተጧጧፈ የሚገኘዉ አለመግባባት ከአሳሳቢነቱ በመዝለል በየትኛዉም አቅጣጫ በሽምቅ ዉጊያ ቀላል ጉዳት የደረሰባቸዉ ወታደሮቻችን ወደ ኋላቸዉ በመሸሽ ላይ […]

የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት ‪#‎ህዝባዊ‬ ወያኔ ሓርነት ትግራይ በሚቆጣጠረው መከላከያ ሰራዊት ውስጥ እርስበርስ አለመተማመንና ጥርጣሬ አይሏል፡፡ ‪#‎የህወሓት‬ አገዛዝ ከሱዳን ጋር የተፈጠረውን ወታደራዊ ግጭት የህዝቡን ትኩረት ሊያስቀይርበት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ #የህወሓት አገልጋይ የሆኑ “የአማራ ክልል” ባለስልጣናት ወደ ወልቃይት ሄደው በአካል ህዝቡን እንዲያነጋግሩ ከህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት ቀጭን ትዕዛዝ መተላለፉ ታወቀ፡፡ ================================================== ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ በሚቆጣጠረው […]

የአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች የህወሓት ፀረ ሽምቅ የተባለ ታጣቂ ሀይል ላይ ጥቃት ማድረሱን አስታወቀ ባሳለፍነው ሳምንት ነበር አርበኞች ግንቦት 7 የሱር ኮንስትራክሽንን ንብረት ማውደሙ የተነገረው አልሸባብ 80 ኢትዮጵያዊያን ወታደሮች መግደሉ ተነገረ ህወሓት መራሹ ጦርና የሱዳን መከላከያ ሀይል ድንበር ላይ ተፋጠው እንደሚገኙ ተዘገበ፡፡ የአሜሪካዊው የራፕ ሙዚቀኛ 50 ሴንት የክስረት ገመና በፍርድ ቤት ይፋ ሆነ     የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ […]

”…ፍትሕ ሚኒስቴር በቅርቡ ‹‹በሥነምግባር ችግር›› በሚል የተማምን የጥብቅና ፍቃድ በመሰረዝ ለአንድ ዓመት ከሰባት ወራት እንዳገደው የሚታወቅ ነው፡፡….ተማም ብዙ ጊዜውን በቤቱ በማንበብ ነበር ጊዜውን የሚያሳልፈው፡፡ በጨዋታ መካከል ስለባልደረባችን ጋዜጠኛ ሀብታሙ ምናለ መታሰር ነገርኩት፡፡ ደነገጠ፡፡ ‹‹አጃኢብ›› አለና ‹‹በምን?›› አለኝ በጣም አዝኖ፡፡ ‹‹የአልሸባብ ህዋስ ነህ፤ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በሚገኙበት ስብሰባ ላይ የሽብር ድርጊት ለመፈጸም አሲረሃል›› ተብሎ ተጠርጥሮ መያዙን […]

የ1997 ምርጫ በኢህአዴግ ኮሮጆ ገልባጭነት ወደ ሁከት ከተቀየረ በኋላ አገሪቱ ወደ ወህኒ ማዕከልነት ተለወጠች፡፡እፍርታሙ ኢህአዴግ ከቅንጅት አመራሮች አንስቶ ጋዜጠኞችን፣የሲቪክ ተቋማት አመራሮችንና ተራውን የህብረተሰብ ክፍል ጭምር በጊዜያዊነት ወዳዘጋጃቸው ማጎሪያቸው ወሰደ፡፡ መች በዚህ ብቻ በቃቸው፡፡አልያዝናቸውም ያሏቸውን ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ፎቶግራፍ በሚቆጣጠሩት ቴሌቭዥን አማካኝነት በመለጠፍ ‹‹እጅ ስጡ››ማለቱን ተያያዙት፡፡እንፈልጋቸዋለን ካሏቸው ጋዜጠኞች አንዱ እስክንድር ነጋ ነበር፡፡ በዚያው ሰሞን አንድ የኢትዮጵያ አየር […]

ሐምሌ 2 /2004 ለሊት ሰባት ሰዓት ማዕከላዊ የደረሰው ጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸው ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት የደረሰበትን አሰቃቂ ድርጊት አስረድቷል፡፡ በዚህ የተበሳጩት የማዕከላዊ ቢሮ ቁጥር 49 መርማሪዎች ኢንስፔክተር አለማየሁ፣ዘመድኩንና ጸጋዬ የተባሉ የሱፍን ከፍርድ ቤት መልስ ቢሯቸው ድረስ በማስመጣት ‹‹ፍርድ ቤት ሄደህ መጥሪያ ይዘህልን መጣህ አሉ ባክህ?›› ‹‹የደረሰብኝን ከመናገር ውጪ ምን አጠፋሁ?›› ባገኙት ነገር ሁሉ ወረዱበት ጾሙን […]

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጥቃት ቀጥሏል ከወለጋ ቄለም 160 ኪ/ሜትር እርቀት ላይ በኢትዮጵያና በሱዳን አዋሳኝ ልዩ ስሙ ቢልበል ተብሎ በሚጠራዉ ስፍራ በትናንትናዉ እለት ከምሽቱ 6፡45 ጀምሮ ከባድ ዉጊያ በማድረግ ከ 60 በላይ የወያኔ ሰራዊት አባላትን በመደምሰስ 18 ወታደሮችን ማቁሰሉ ተረጋገጠ። በቦንሳ ሰባ ፣ በዶ/ ኑሮ ደደፎ ፣ በአቶ ድሪባ ወርዶፋ ፣ እንዲሁም በብደታ ሹኬ ተነጣጥሎ የነበረዉ […]

ታፍኖ የታሰረው መምህር የት እንዳለ አልታወቀም ሀምሌ 1/2007 ዓ.ም ጎንደር ከተማ ውስጥ በፖሊስና ደህንነቶች ታፍኖ የታሰረው የሰማያዊ ፓርቲ አባል መምህር አለላቸው አታለለ የት እንደሚገኝ ለማወቅ እንዳልቻሉ ቤተሰቦቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ በጎንደር መምህራን ኮሌጅ የአይ ሲቲ መምህርና የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ የሆነው መምህር አለላቸው አታለለ ሀምሌ 1/2007 ዓ.ም ወደ ደብረታቦር ተወስዶ በደብረታቦር ከተማ አንደኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ […]

ኦባማ ለአፍሪካ መሪዎች ግብረሰዶምን ሊያስተዋውቅ ኬንያ ገባ በተለይ በዲስ አበባ በሚደረገው የአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ላይ ግብረሰዶም በአፍሪካ ተግባራዊ እንዲሆን መልክቱን የሚያስተላልፍ ሲሆን ወያኔዎች አሜሪካ ገንዘብ ከሰጠችን እና አርበኞች ግንቦት 7 እኛ አሸባሪ ያልነውን እሷም አሸባሪ ነቱን አጽድቃ በአለም መሀብረሰብ እንዲወገዝና እየመጣብን ካለው የስልጣን ማፈናቀል ካዳነችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተግባራዊ እንደርጋለን ብለው እንደሚደራደሩ አትጠራጠሩ። ምክንያቱም እነሱ […]

የናዚ ወያኔ ስልጣን ላይ ከተቆናጠጠ ጊዜ ጀምሮ በርካታ ወጣቶችንናሙህራንን በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ አሳዷል፣አዋክቧል፣ዘግናኝ ሰቆቃና ግድያ ፈጽሟል።አሁንም አጠናክሮ ቀጥሎበታል።ወያኔወች ከስልጣን ለመውረድ የማይፈልጉት አንዱ ትልቁ ምክንያትም ይህ በየቦታው በፍጹም አረመኔያዊነት በገፍ የገደሏቸው እና በጅምላ የቀበሯቸው የንጹሀን ደም ጩኸት እያሸበረቸው እና የፈጸሙት ዘግናኝ ወንጀል ከተጠያቂነት የማያስመልጣቸው ወቅቱን ጠብቆ የሚፈነዳ ቦንብ(timebomb) መሆኑን ጠንቅቀው ስለሚያውቁም ጭምር ነው። በአማራ ሰሜን ሸዋ […]

የወያኔ ቅጥር ሰራዊት የሽምቅ ሐይል ስምሪት ክፍል በሶስት አቅጣጫዎች በተለይም በትግራይ ጠረፍ በአብረሐ ጅራ በጎንደር ወልቃይት ጠገዴ በባሌ በኩል ከባድ ዉግያ እንደገጠመዉ የሚጠቁሙ መረጃዎች ትናንት ማምሻዉን በስቸኳይ መልእክት ለበላይ አካላት የተላለፉ ሲሆን፡ እንዲሁም በአርማጭሆ ህዝብ እና በሰራዊቱ መካከል እየተጧጧፈ የሚገኘዉ አለመግባባት ከአሳሳቢነቱ በመዝለል በየትኛዉም አቅጣጫ በሽምቅ ዉጊያ ቀላል ጉዳት የደረሰባቸዉ ወታደሮቻችን ወደ ኋላቸዉ በመሸሽ ላይ […]

ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት ሴነተር ማርኮ ሩቢዮ ፕሬዝዳንት ኦባማ ኢትዮጵያን በሚጎበኙበት ጊዜ ሰብዓዊ መብት ቀዳሚ አጀንዳቸው እንዲያደርጉ አሳስበዋል:: ሴነተሩ ለፕሬዝዳንት ኦባማ በጻፉ ደብዳቤ “ምንም እንኳን አሜሪካና ኢትዮጵያ አሸባሪነት በመዋጋትና አካባቢዉ የተረጋጋ በማድረግ የጋራ ጥቅሞች ቢኖሯቸውም: አሜሪካ ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶችን ስትጥስ እንዳላየች ማለፍ የለባትም” ብለዋል:: አስከትለውም “አማራጭ ሃሳቦችን የማንሸራሸሪያ ጎዳናዎችን በፖለቲካ ሂደቱ: በሲቭል ሶሳይቲውና: በሚዲያ […]

ዘረኛውና ፋሽስቱ የህወሓት አገዛዝ፣ በሕዝባዊ ኃይሎች ላይ ሊወስድ ያሰበው እርምጃ ተቀባይነት እንዲያገኝለት የሽብር ተግባር ፈጽሞ በአርበኞች ግንቦት 7 ላይ ለማላከክ ወስኗል። እንዲህ ዓይነቱ እኩይ ተግባር ህወሓት ስልጣን ከመያዙ በፊትም በኋላም ሲያደርገው የነበረ መሆኑ የሚታወቅ ነው። ህወሓት እንዲህ ዓይነቱ ኢሰብዓዊና ዘግናኝ ተግባር ለመፈፀም የሚያስችሉ እኩይ ስለልቦና እና ልምድ አለው። አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ በቅርቡ […]

በሽብርተኝነት ተከሶ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ ፀኃፊ አቶ በፍቃዱ አበበ በትናንት ሀምሌ 15/2007 ዓ.ም በልደታ ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት የመከላከያ ምስክሮቹን አሰምቷል፡፡ ከአምስቱ የመከላከያ ምስክሮች መካከል አራቱ የአርባ ምንጭ ፖሊስና ደህንነቶች በፍቃዱ አበበ ላይ በሀሰት ከመሰከሩ የተሻለ ጥቅም እንደሚሰጣቸው ቃል ገብተውላቸው እንደነበር ገልጸው መስክረዋል፡፡ ከአመት በፊት አንድነት ፓርቲ በአርባምንጭ ያደርገው […]

የፕሬስ ነፃነትን በማፈንና የሰብአዊ መብትን በመርገጥ የሚታወቀው የኢህአዴግ መንግስት የፈፀመብኝን እስር በመቃወምና በማውገዝ እንዲሁም ያለቅድመ ሁኔታ እፈታ ዘንድ በመጠየቅ ከጎኔ ለነበራችሁ በሙሉ ምስጋናዬን የማቀርበው በታላቅ ትህትናና አድናቆት ነው፡፡ በነዚያ የጨለማ ቀናት አብሮነታችሁ ያልተለየኝ አለምአቀፍና ሀገር አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡ ዩኔስኮ፣ አለምአቀፍ የሴቶች ሚዲያ ፋውንዴሽን፣ ሚዲያ ሌጋል ዲፈንስ ኢንሼቲቭ፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሂዩማን ራይትስዎች፣ ሲፒጄ፣ ፔን […]

ወያኔ እንደለመደዉ ከተቃዋሚዎች ጋር ለማገናኘት እየጣረ ነዉ የደርባን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ሳሙኤል በዘራፊዎች በተተኮሰ ጥይት ተመተው ህይወታቸው አለፈች ፡፡ አዎ ይህንን በተንተራሰ መልኩ በደቡብ አፍሪካ የሚገኘዉ የወያኔ ስራ አስፈጻሚ መስሪያ ቤ/ት የህወሃት ቀኝ እጅ የኢቶፕያ ኢንባሲ በደቡብ አፍሪካ ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የወያኔ ደጋፊዎችን ” የናንተም እጣ ፋንታ ይህዉ ነዉ ” ። […]

“የማንዴላ ቀን” ህወሃቶች “የማንዴላን ቀን” ለማክበር ሽርጉድ ሲሉ አለማፈራቸው ባይገርምም ያሳዝናል። የማንዴላን ፎቶ ሰቅሎ መብላትና መጠጣት ሆድ ከመሙላት የዘለለ ምንም ፋይዳ የለውም። ስንቱን ኢትዮጵያዊ ማንዴላ በየእስር ቤቱ አጉረው እያሰቃዩና እየገረፍ፣ የተረፈውን ለስደትና ሞት እየዳረጉ የማንዴላ ቀን በድግስ ማክበር የቆመለት አላማ ምን እንደ ነበር መዘንጋት ብቻ ሳይሆን የለየለት አስመሳይነት ነው። ማንዴላ መስዋነትነት የከፈለው ህወሃት በኢትዮጵያ ህዝብ […]

ህወሓት ጥቂት አባላትና ደጋፊዎች ይዞ ታላቂቷን ኢትዮጵያ ለማንበርከክ እና ሀብቷን ለመመዝበር  እናንተን መጠቀሚያ ያደረጋችሁ መሆኑን የምታውቁት ነው። እናንተ አባል የሆናችሁባቸው ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴድ የተባሉ ድርጅቶች የራሳቸው ድርጅታዊ ነፃነት የሌላቸው የህወሓት አገልጋዮች መሆናቸው እነሱ ራሳቸው የሚነግሯችሁ ከመሆኑም በላይ እናንተም በዕለት ተዕለት ተግባራችሁ የምትታዘቡት ሀቅ ነው። እነዚህ ድርጅቶች ህወሓትን ለማስደሰት ሲሉ የራሳቸውን ሕዝብ የሚያስሩ፣ የሚገድሉ፣ የሚዘርፉ፣ ከቀየው […]

  ሮናልዶ እንዲህ ይላል… “ለኔ ለዚህ ስኬት መድረስ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደረገልኝን የልጅነት ጓደኛዬን አልበርት ፎንትራኦን አመሰግነዋለሁ! በጊዜዉ እኔና እሱ ከ18 አመት በታች ለታዳጊ ሻምፕዮና በአንድ ክለብ አብረን እንጫወት ነበር…አንድ ቀን የሊዝበን አሰልጣኝ ወደ እኛ መጣና እንዲህ አለን:- “ዛሬ ብዙ ጎል ያስቆጠረ ወደ እኛ አካዳሚ ይገባል” አለን! በእለቱም ጨዋታውን 3ለ0 ስናሸንፍ ጎሎቹንም የመጀመሪያውን እኔ 2ኛውን ደግሞ […]

Sur Construction Ethiopiaየአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት ጋዜጣዊ መግለጫ:- የአርበኞች ግንቦት 7 ጀግና የነፃነት ፋኖዎች በኢትዮጵያ መሬት ላይ በህዝቡ ጉያ ውስጥ ሆነው በወልቃይት የጀመሩትን ወታደራዊ ጥቃት አሁንም አጠናክረው በመቀጠል የህወሓትን አገዛዝ እያሽመደመዱት ነው፡፡ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ የተባለውን በቁሙ ደርቆ የበሰበሰ ዛፍ ከስሩ ገዝግዞ ለመቁረጥ የተጀመረው ትግል ሰሞኑን በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ልዩ ልዩ አካባቢዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ከወታደራዊ ጥቅምና ደህንነት አንፃር ስማቸውን ለመግለፅ በማይቻልባቸው የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ልዩ ልዩ አካባቢዎች ላይ በሚንቀሳቀሰው የህወሓት ፀረ-ሽምቅና ሚሊሻ ኃይል ላይ ደፈጣ በመጣል ደምስሰውታል፡፡

በአዘዞ እና ጠዳ ከተሞች መካከል ከሚገኘው መገጭ ወንዝ አጠገብ በግንባታ ስራ ላይ የነበረው የሱር ኮንስትራክሽን የድንጋይ መፍጫ ማሽነሪዎች እና ሌሎችን የግንባታ ቁሳቁሶች በአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች ሙሉ በሙሉ በመውደሙ ስራውን አቁሞ እንዲሸሽ ተገዷል፡፡ ሱር ኮንስትራክሽን የህወሓቶች የግል ንብረት የሆነው ኤፈርት በስሩ ካሉት ከ60 በላይ የንግድ ኩባንያዎች አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ሱር ኮንስትራክሽን ውድመት በደረሰበት አካባቢ የግንባታ ስራውን በብቸኝነት የያዘው እንደተለመደው ያልምንም ጨረታ ነው፡፡ በተያያዘ ዜና ከዚያው ጎንደር ዙሪያ ወረዳ ውስጥ የሚኖር አቶ ጎሸ ሽባባው የተባለ ገበሬ ለአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች ስንቅ አቀብለሃል በሚል በህወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ውሎ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሞበታል፡፡ አቶ ጎሸ ሽባባው አሁን በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ማክሰኝት እስር ቤት ውስጥ ይገኛል፡፡

በላይ አርማጭሆ አንገረባ ቀበሌ የአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች እና የህወሓት ጸረ-ሽምቅ ኃይል ለአንድ ሰዓት የዘለቀ ጦርነት አድርገዋል፡፡ ጦርነቱም የተካሄደው ሀምሌ 11 2007 ዓ.ም ሲሆን በአካባቢው ለአሰሳ ሲንቀሳቀስ የነበረውን የህወሓት ፀረ-ሽምቅ ኃይል በውስጥ አርበኞች የተከፈተበትን ድንገተኛ የደፈጣ ጥቃት መቋቋም ስላልቻለ አንድ ሰዓት ከፈጀ የተኩስ ልውውጥ በኋላ ለጊዜው ቁጥራቸው በትክክል ያልታወቁ በርካታ አባላቱ ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል፡፡ የሱዳን መከላከያ ኃይል የኢትዮጵያን ወሰን ጥሶ ገብቶ ከሆር ሁመር ገበሬዎች ጋር መታኮሱ ታውቋል፡፡ በተደረገው የተኩስ ልውውጥ 2 ገበሬዎች ለሞት ተዳርገዋል፡፡ በአካባቢው ሰፍሮ የሚገኘው ህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊት የሱዳን መከላከያ ኃይል ድንበር ሰብሮ ገብቶ በገሬው ህዝብ ላይ የጦር ጥቃት ሲያደርስ እየተመለከተ እንዳላየ በዝምታ አልፎታል፡፡

ከአርበኞች ግንቦት 7 የጥቃት ማግስት ጀምሮ የተለያዩ የነጻነት ሐይሎች ጦርነት እያካሄዱ እንደሚገኙ ከወያኔ ወታደራዊ ግንኙነት ክፍል የወጣ መረጃ አመለከተ። መረጃዉ እንደሚጠቁመዉ ኦነግና የኦጋዴን ነጻ አዉጪ ሀይሎችም ተመሳሳይ የሆነ ሽምቅ ዉጊያ ተያይዘዉታል። የአሜሪካዉ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማን መምጣት ምክንያት ባደረገ መልኩ ኢትዮጵያ ምንም አይነት የጦርነት አዋጅ እንደማታዉጅ ወታደራዊ ደህንነቱ ለየ እዝ ባለስልጣናቱ ሚስጢራዊ ትዕዛዝ በማሳለፉ የእዝ አመራሮችን […]

  አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ድረስ ለተጠቀሱት ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ የወሰነው የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በምስክርነት እንዲያቀርብ ለሀምሌ 29/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጠ፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሀምሌ 13/2007 ዓ.ም ልደታ ፍርድ ቤት ቀርበው የመከላከያ ምስክር እንዲሆኑ ፍርድ ቤቱ ወስኖ የነበር […]

መንግስት አይ.ኤስ.አይ.ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ እስር ላይ የቆዩት እነ ወይንሸት ሞላ ሰኔ 15/2007 ዓ.ም በቄራ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት እንዲፈቱ ከተፈረደላቸው በኋላ ሰኔ 22/2007 አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆባቸው ነበር፡፡ ይሁንና የልደታ ፍርድ ቤት ዛሬ ሀምሌ 14/2007 ዓ.ም በዋለው ችሎት የቄራ ፍርድ ቤት በእነ ወይንሸት ላይ የወሰነውን ውሳኔ በማፅናት አቃቤ ህግ የጠየቀውን ይግባኝ ውድቅ አድርጎታል፡፡ […]

በእነ ዘላለም ወርቃገኘው የክስ መዝገብ ከ1-6ኛ እንዲሁም የ9ኛ ተከሳሾች ጠበቃ የሆኑት ተማም አባቡልጉ በደንበኞቻቸው ላይ በቀረበባቸው የክስ ማስረጃ ላይ ያቀረቡት ባለ 10 ገፅ መቃወሚያ በፍርድ ቤቱ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ ተደርጓል፡፡ ጠበቃው ተከሳሾቹ ሀምሌ 1/2006 ዓ.ም ተይዘው ከሶስት ወር በኋላ ጥቅምት 7/2006 ዓ.ም ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት ተገኘ የተባለ መረጃ ከአቃቤ ህግ ማስረጃዎች ማስረጃ ዝርዝርነት እንዲወጣ፣ ተከሳሾቹ […]

ከርበኞች ግንቦት 7 የጥቃት ማግስት ጀምሮ የተለያዩ የነጻነት ሐይሎች ጦርነት እያካሄዱ እንደሚገኙ ከወያኔ ወታደራዊ ግንኙነት ክፍል የወጣ መረጃ አመለከተ። መረጃዉ እንደሚጠቁመዉ ኦነግና የኦጋዴን ነጻ አዉጪ ሀይሎችም ተመሳሳይ የሆነ ሽምቅ ዉጊያ ተያይዘዉታል። የአሜሪካዉ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማን መምጣት ምክንያት ባደረገ መልኩ ኢትዮጵያ ምንም አይነት የጦርነት አዋጅ እንደማታዉጅ ወታደራዊ ደህንነቱ ለየ እዝ ባለስልጣናቱ ሚስጢራዊ ትእዛዝ በማሳለፉ የእዝ አመራሮችን […]

የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆኑት አቶ መኳንንት ብርሃኑ መኖሪያ ቤታቸው ተክብቦ በፖሊስ እየታደኑ መሆኑንን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች አመልክተዋል፡፡ የአቶ መኳንንት ቤት በፌደራል ፖሊስ መከበቡ የታወቀ ሲሆን፣ አቶ መኳንንት ግን ለሳምንት ያህል ቤታቸው እንዳልገቡ ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል፡፡ ቤታቸው የካ ክፍለ ከተማ ኮተቤ አካባቢ የሚገኘው አቶ መኳንንት ብርሃኑ፣ መኖሪያ ቤታቸው እሳቸውን ለመያዝ በታዘዙ ፖሊሶች ተከብቦ ይገኛል ተብሏል፡፡ ፖሊስ አቶ […]

በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ቀርቦባቸው ጉዳያቸው እየታየ የሚገኙት የዞን 9 ጦማርያን ዛሬ ሐምሌ 13/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ሐምሌ 1/2007 ዓ.ም ‹‹ክሳችሁ ተቋርጧል›› በሚል ከእስር ከተፈቱት ተለይተው በእስር ላይ የሚገኙት በፍቃዱ ኃይሉ፣ አጥናፍ ብርሃኔ፣ ናትናኤል ፈለቀ እና አቤል ዋበላ ዛሬ ለ31ኛ ጊዜ […]

አገዛዙ 11ኛዋ ሰአት ላይ በደጋፊወቹ ክፉኛ እየተሞገተ መሆኑ ተሰማ! የወያኔ ስራ አስፈጻሚዎች በደጋፊዎቹ ክፉኛ እየተሞገተ መሆኑን ከውስጥ አወቅ ምንጮች ያገኘናቸው የግምገማ መርጃወች አመላከቱ።የስር አቱ ደጋፊዎችና ታማኝ የሚባሉ ካድሬወች ያነሱት ነጥብ ሲጨመቅ እንደሚከተለው ቀርቧል። “በተለይ ለእኛ ስለ ወቅታዊ ሁኔታወች ስውር የሆነብን ምክንያት ምንድን ነው፧ እኛም የፓርቲያችን እና የአገራችን ጉዳይ ያገባናል። እርስ በእርሳቸው የሚጣረሱ ዜናወችና መረጃወችስ እንዲደርሱን […]

የአሜሪካው ፕ/ት ባራክ ኦባማ ይህን የተናገሩት ” በአሜሪካና በኤርትራ የሚገኙ የተቃዋሚ ድርጅቶች ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን ለመወጋት የምታደርገውን ጥረት እያደናቀፉ በመሆኑ የእርስዎ መንግስት የኢትዮጵያን መንግስት ለመርዳት ምን ያክል ዝግጁ ነው ተብሎ ከኢቢሲ ጋዜጠኛ ጥያቄ መቅረቡን ተከትሎ ነው። ጋዜጠኛው የድርጅቱን ስም በግልጽ ከመግለጽ ቢቆጠብም፣ ፕ/ት ኦባማ የሰጡት መልስ ፣ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ከዚህ ቀደም ለአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ምክትል ሃላፊ […]

‹‹የታሰርኩት ቤተሰቦቼን በእሳት አቃጠሉብኝ ብዬ ስለከሰስኩ ነው›› አቶ አንጋው ተገኝ በእነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት የተከሰሱት 16 የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ለሀምሌ 17/2007 ዓ.ም ለብይን ተቀጠሩ፡፡ አመራሮቹ ሀምሌ 1/2007 ዓ.ም በጠበቆቻቸው በኩል የክስ መቃወሚያና የዋስትና ጥያቄ አቅርበው የነበር በመሆኑ ዛሬ ሀምሌ 13/2007 ዓ.ም አቃቤ ህግ ለጥያቄው መቃወሚያ እንዲያሰማ ቀጠሮ ተሰጥቶት የነበር ቢሆንም ሳይቀርብ […]

. የትጥቅ ትግሉ ያሰጋው ወያኔ የጎንደር ህዝብን እያሰቃየ መሆኑ ተነገረ፡፡ . ‹ባራክ ኦባማ ሲመጣ ሰልፍ ለመጥራት እያደራጁ ነው በሚል የተከሰሱት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን ጉዳይ ፍርድ ቤቱ ለሶስተኛ ጊዜ አላይም ማለቱ . አንድ ሣምንት የዘለቀው የልኳንዳ ቤቶች አድማ እደቀጠለ ነው፤ . የስዊድን ጠቅላይ ሚኒስትር  ከአዲስ አበባ መልስ ወደ ሆስፒታል አመሩ። . የወያኔ መንግስት በአሜሪካ ፍርድ ቤት  ተከሰሰ አሰግድ […]

(ክንፉ አሰፋ ቶሮንቶ) ሰብለ (ሚሚ) ዲትሪች ለመጨረሻ ግዜ የታየችው እ.ኤ. አ. ጁላይ 10 2014 (ባለፈው አመት) ነበር። የሶስት ልጆች እናት የነበረች የዚህች ኢትዮጵያዊት በድንገት መሰወር ለብዙዎች እንቆቅልሽ ሆኖ ሰንብቷል። ለአመት የጠፋችው ይህች ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሴት በህይወት እንደማትኖር በርካቶች ቢጠረጥሩም፣ ማንንም ሳታማክር በድብቅ ወደ ሃገርዋ ገብታለች የሚሉ አልጠፉም። አለም አቀፍ ፖሊስ በአለም ዙርያ ፍለጋውን ተያያዘው። ሰብለ-ቀብር […]