የጦማሪያኑ የፍርድ ቤት ውሎና የልደታው ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት
በማለዳ ከእንቅልፌ በመንቃት ጉዞዬን ልደታ ወደሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት አደረኩ፡፡ ጉዞዬን ወደ የልደታው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያደረኩት ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት፣ በዛሬው ዕለት ‹‹በእነሶልያና ሽመልስ›› የክስ መዝገብ ስር ለሚገኙትና ከእስር ያልተለቀቁት ጦማሪያን አጥናፍ ብርሃኔ፣ በፍቃዱ ሀይሉና ናትናኤል ፈለቀ ላይ ፍርድ ቤቱ ብይን ለመስጠት መዝገቡን ለሐምሌ 22 ቀን 2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቶበት ስለነበረ ነው፡፡ […]![]()