ወንድሜ ሆይ ይህን ለኢትዮጵያ ህዝብ አድርስልኝ።ነገሩ እንዲህ ነው። ምንአልባት አጋዚ ስለሚባል ልዬ ሃይል ሰምተህ ይሆናል። አጋዚ ማለት ከትግራይ ገጠር ቦታወች የሚመለመሉ ወጣቶች ስብስብ ነው። እኒህ ወጣቶች ገና የስምንት አመት እድሜ እያሉ ነው የሚመለመሉት። ከትግረኛ ውጭ ምንም አይነት ሌላ ቋንቋ አይናገሩም። …

የአጋዚ ጦርና የወያኔ ሴራ በውስጥ አወቅ ሲጋለጥ! (የውስጥ መልዕክት) Read more »

**የኦባማ ጉብኝት ለውይይት እንጂ ወንጀለኛን መንግስት ለማጽደቅ እንዳልሆነ አስረዱ ** “የተፈቱት የዞን ዘጠኝ ጋዜጠኞች ፓስፖርታቸው እንኳን እንዳልተመለሰ እናውቃለን:: መጀመርያውኑ መታሰር እልነበረባቸውም:: ሲፈቱም አፈታታቸው ሙሉ አይደለም” ዛሬ እዚህ ዋሺንገተን ዲሲ ላይ ጠንካራ ውይይት ሲካሄድ ነበር:: ውይይቱ የኦባማን የምስራቅ አፍሪካ ጉዞ በተመለከተ ሲሆን : አሜሪካኖቹ መራር መልሶችን ሲመልሱ ተደምጠዋል:: የኦባማ ጉብኝት ለአምባገነኖች ሽፋን መስጠት ሳይሆን ሌሎች በርካታ […]

የሜክሲኮው አደጋኛ የእጽ አዘዋዋሪ ከጥብቁ እስር ቤት እንዴት አመለጠ? በዚህ ቪዲዮ ይመልከቱት አደገኛው የእጽ ነጋዴ ጆአኪም ጉዝማን (ኤልቻፖ) ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግበት ከሜክሲኮ እስር ቤት ባለፈው ቅዳሜ ምሽት ማምለጡ አይዘነጋም፡፡ ይህ ሲናሎአ የተባለውን የእጽ ዝውውር ወንጀል መረብን የሚመራና በመላው አለም ግዙፍ መረብና የዘረጋ ወንጀለኛ በእስር ክፍሉ ሻወር ቤት አካባቢ በተከፈተ አነስተኛ ጉድጓድ በመጠቀም መሬት ለመሬት ተሸሎክሉኮ […]

*በደቡብ ክልል ጋሙ ጎፋ ዞን አስተዳደር የህወሓት አሻንጉሊት ባለስልጣናት መካከል መከፋፈል ተፈጠረ፡፡ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ የሚከተለው ከቅኝ ገዥዎች የተወረሰ ህዝብን በመከፋፈል ለረዥም ጊዜ የመግዛት ፀረ ኢትዮጵያዊ አንድነት የሆነ የበሰበሰ አውዳሚ ፖለቲካዊ ቀመር ከጎሳዎች አልፎ በመንደርና ቤተሰብ ውስጥ ገብቶ ስር በመስደድ ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በደቡብ ክልል ጋሙ ጎፋ ዞን አስተዳደር የህወሓት አሻንጉሊት ባለስልጣናት መካከል መንደርንና […]

‹እጄን ወደ ላይ አስረው ብልቴ ላይ ሀይላንድ አንጠልጥለውበታል፡፡ ሴቶቹ ሀይላንዱን የሚበቃቸውን ያህል ያወዛውዙታል፡፡ በዚህም ምክንያት ከጥቅም ውጭ ሆኗል፡፡ የዘር ፍሬየን ከጥቅም ውጭ አድርገው ዘሬን እንዳልተካ አድርገውኛል፡፡ ሽንቴንም መቆጣጠር አልችልም፡፡›› አበበ ካሴ እኔ አበበ ካሴ እባላለሁ፡፡ የሰሜን ጎንደር ተወላጅ ነኝ፡፡ በማዕከላዊ እስር ቤት ከ5 ወር በላይ ታስሬለሁ፡፡ ከዚህ መካከል 4 ወር ከ25 ቀናት በጨለማ ቤት ተቆልፎብኝ […]

የአሜሪካው ፕሬዘዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝት ሰርግና ምላሽ በኢትዮጵያ ከወዲሁ የተወሰኑ እስረኞችና በመፍታትና ብዛት ያላቸውን የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን በማሰር ወደ ቀኑ እየገሰገሰ ይገኛል፡፡የሰማያዊና የቀድሞው አንደነት አመራሮችና አባላት ኦባማ ወደ አገራችን ሲመጡ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እያሴራችሁ እንደሆነ ደርሰንበታል በማለት ለእስር ተዳርገዋል፡፡ ባሳለፍነው ሐሙስ የሞያ አጋሮቹ መፈተታት የፈጠረበትን ደስታ አጣጥሞ ሳይጨርስ በቁጥጥር ስር የዋለው ጋዜጠኛ ሐብታሙ ምናለ ከአምስት […]

በተለያዩ ፊልሞችና የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ በመተወን የምትታወቀው ተዋናይት ቤዛዊት መስፍን እና ግብረ አበሯ በእስራት ተቀጡ። በአዲስ አበባ ከተማ በኮልፌ ቀራንዮ ነዋሪ የሆኑት ተከሳሾቹ በእስራት የተቀጡት ከታዘዘላቸው ውጭ ተጨማሪ ገንዘብ ከባንክ ቤት በማውጣት ለግል ጥቅማቸው በማዋላቸው ነው። የ22 አመቷ ተዋናይት ከግብረ አበሯ ጋር በመሆን በተሰጣቸው የ4 ሺህ ብር ቼክ ላይ ከፊት ለፊቱ ሁለት ቁጥርን በመጨመር ያልተፈቀደላቸውን […]

በናይሮቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ከደላሎች ጋር እንደሚሰራ ብዙዎች በምሬት ይገልጻሉ ‹‹ወተትና ማር ታፈልቃለች››ወደሚሏት ደቡብ አፍሪካ ለመሻገር በተለይ ከደቡብ ኢትዮጵያ በመነሳት በሞያሌ በኩል ወደ ኬንያ በመግባት ረዥሙን ጉዞ ለመያያዝ ራሳቸውን በሚያዘጋጁበት ቅጽበት እየተያዙ ወህኒ የሚወርዱ ወጣቶች ቁጥር በኬንያ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ኢትዮጵያዊያኑ በኬንያ ለመቆየት፣ስራ ለመስራት አልያም የሽብር ተግባር ለመፈጸም የመጡ እንዳልሆኑ ቢታወቁም በአገሪቱ ፖሊሶች […]

በዚህ ወር መጨረሻ የአባታቸውን ሀገር ለሁለት ቀናት ይጎበኛሉ ተብለው የሚጠበቁት ባራክ ኦባማ ወደ ኬኒያ ምድር ሲመጡ በግብረ ሰዶማውያን ጉዳይ ላይ አንዳችም ነገር እንዳይናገሩ በከፍተኛ ሁኔታ ሲያስጠነቅቁ ሰንብተዋል። የተለያዩ እምነት መሪዎችና የፓርላማ አባላት ጭምር ደብዳቤዎችን ለዋይት ሀውስ አስገብተዋል። የኬኒያ ምክትል ፕሬዚዳንት በበኩላቸው “ይህ የአፍሪካውያን ባህል ካለመሆኑም በላይ ድርጊቱ የሀይማኖታችንን ህግ የሚጥስ ነው።” በማለት ተችተዋል። አንድ የቤተክርስትያን […]

ኢትዮጵያዊ ስለሆንን? (የኢትዮጵያ ከ20አመት በታች የሴቶች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን እሁድ እለት ከካሜሮን አቻው ያለግብ ከተለያየ በኋላ ወደ ሀገሩ ሊመለስ ሲል በረራ ተሰርዟል ተብሎ እንዲህ ነበር የሆነው። ምስል፦ ኢ/ያ እ.ፌ. የህዝብ ግንኙነት ወንድኩም አላዩ) ኢትዮጵያዊ ስለሆንን? ቆንጅት ተሾመ አውቃለሁ…. ሀገራቸውን ወክለው ካሜሮን የሄዱ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች በረራ ተሰርዟል ተብሎ በአየር ማረፊያ ውስጥ በየጥጋ ጥጉ..በየመቀመጫው […]

ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው ሰማያዊ ፓርቲ ከ2007 ሀገራዊ ‹‹የውሸት ምርጫ›› ማግስት በገዥው አካል እየተወሰደ የሚገኘው ግድያ፣ እስር፣ ከስራ ማፈናቀል፣ ማሸማቀቅና ድብደባ በአስቸኳይ እንዲቆም ጠየቀ፡፡ ፓርቲው ዛሬ ሐምሌ 7/2007 ዓ.ም ‹‹የወለደውን የረሳ ብሶት የወለደው ስርዓት! የዘመቻ እስርና ግድያ ተጠናክሮ ቀጥሏል!›› በሚል በጽ/ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እዳመለከተው፣ ምርጫው ከተጠናቀቀበት ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም ማግስት በምርጫው በንቃት ይሳተፉ […]

የትጥቅ ትግሉ በአራቱም አቅጣጫ ተጠናክሮ ቀጥላል  የወያኔም ስጋቱ አይላል፤ ተባላ አርበኞች ግንቦት 7 በተለያዩ ግንባሮች በወያኔ ላይ የከፈተውን ማጥቃት ተከትሎ ከወያኔ ጎራ የተምታቱ ዜናዎች እየተደመጡ ነው። የቴፒው ትንቅንቅ አሁንም ቀጥሏል። ርዕዮት ዓለሙና የዞን 9 ጦማሪዎች በድንገት መፈታት እያነጋገረ ነው የሚኒስትር-ሬድዋን ሁሴን-አማካሪ-መኮብለላቸው ተሰማ እግዚአብሔር 10ቱን ለሙሴ የተሰጡትን ትእዛዝ እንዳሻሽላቸው አዞኛል “” የሮማው ካቶሊክ ጳጳስ ፍራንሲስ   አሰግድ […]

  የሸዋሮቢት ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ አመራርና የቀድሞው አንድነት አባላት ዛሬ ከ3:00— 4:00 ሰአት በታጠቁ የመንግስት ሀይሎች ከያሉበት ታድነው በመታሰር ላይ መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በዚህም መሰረት እስካሁን ድረስ 1 አቶ ዘነበ ደሳለኝ (የተወካይ ም/ቤት እጩ የነበረ። 2 አቶ ቴዎድሮስ ሀብቴ (የቀድሞ አንድነት አባል የነበረ።) 3 አቶ መንግስቱ ደባይ 4 አቶ በቀለ (የአባት ስም ያልተገለፀ) […]

ዛሬ ሐምሌ 4 2007ዓ.ም ረፋዱ ላይ አቶ መርከቡ ሃይሌ ሰሞኑን ሲከታተሉት በነበሩ ደህንነቶች እና ፖሊስ ታፍኖ ለጊዜው ወደአልታወቀ ቦታ ተወስዷል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ትናንት በኢህአዴግ የታሰረው አቶ ደብሬ አሸናፊ ዛሬ ረፋዱ ላይ ቤቱ በከፍተኛ የታጠቁ ሃይሎች ተከቦ ፍተሻ የተካሄደበት ሲሆን አሁን በጉለሌ አካባባቢ ላዛሪስት ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ እንደሚገኝ ተረጋጧል፡፡ በሌላ በኩል ትናንት ታፍነው የታሰሩት በሰሜን ሸዋ […]

የሮማው ካቶሊክ ጳጳስ ፍራንሲስ ሰሞኑን በላቲን አሜርካ ባደረጉት የስራ ጉብኝት በኢኮዶር በሚሊዮን ለሚቆጠሩ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች አዲስ መልእክት አስተላልፈዋል:: ጳጳስ ፍራንሲስ ካስተላለፉት አዳዲሶቹ መልእክቶች ዋናዎቹ እግዚአብሔር 10ቱን ለሙሴ የተሰጡትን ትእዛዝ እንዳሻሽላቸው አዞኛል:: ከ10 ትእዛዛት ውጪ 2 ሌላ አዲስ የእግዚአብሔር ትእዛዛት በ10ቱ ትእዛዛት ውስጥ በተጨማሪ የሚካተቱ መሆኑን ጳጳስ ፍራንሲስ አስታውቀዋል:: ከሚጨመሩት እና ከሚሻሻሉት ከ10ቱ አዳዲስ ትእዛዞች […]

የወያኔው ሬድዋን ሁሴን ፣ እነ ርዮት አለሙ የተፈቱት መንግስት ማግናኒመስ (ትልቅ) ስለሆነ ነው እያለን ነው፣ ድርጅታችውን መልአካዊ አድርጎ ለማቅረብ ሲሞከር። ሆኖም፣ የገዢውች ማንነትን፣አ አዉሬነትን አሁን በአገሪቷ ዙሪያ ሁሉ ካሉ የቶርቸር ቻምበሮች (ክፍሎች) የሚሰሙ የሰቆቃ ጩኸቶች በትልቁ እያጋለጡ ነው። ባልሰሩትና ባልፈጸሙት ወንጀል፣ ቢያንስ ሃያ ዘጠኝ የሚሆኑ በእሥር የሚማቁ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን አባላት አሉ። ፍርድ ተነፍገው […]

        በጥብቅና ሙያ የሚተዳደሩት አቶ ተማም አባቡልጉ አባዲኮን ከስነ ምግባር ጋር በተያያዘ በሚል ለ፩ አመት ከሰባት ወር የጥብቅና ፍቃዳቸውን ታግዳል። አቶ ተማም አባቡልጉ በግፍ ለታሰሩት ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጥብቅና በመቆም የወያኔን መሰሪ አሰራር ለአለም በማጋለጥ የሚታወቁ ሲሆን የካንጋሮ ፍርድ ቤት ፍርደ  ገምድልነት ቁልጭ ብሎ እንዲታይ ያደረጉ የሀገር አብት ጠበቃ ናቸው። ይህ ያልተመቸው […]

በሰሜን ጎንደር ዳባት ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ውስጥ የከረረ ተቃውሞ በፖሊስ አባላቱ በመነሳቱ በርካታ ቁጥር ያላቸው ፖሊሶች መታሰራቸው ተሰማ፡፡ ቅዳሜ ዕለት ሰኔ 27 2007 ዓ.ም ዳባት ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት በተካሄደው ስብሰባ ላይ የከረረ ተቃውሞ የተነሳ ሲሆን ተቃውሞውን ተከትሎ የበርካታ ፖሊስ አባላት እስር እና ከአካባቢው መሰወር ተከስቷል፡፡ በስብሰባው ላይ የተነሳው ተቃውሞ ዋነኛ ምክንያትና ሰበብ የፖሊስ ፅ/ቤቱ ዋና […]

በሽብር ወንጀል ተፈርዶባት በይግባኝ በአምስት ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጥታ በማረሚያ የነበረችው ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ትናንት የአመክሮ ጊዜዋ ተጠናቆ ከእስር ተለቀቀች። በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ የወንጀል ችሎት ግለሰቧ በእነ ኤልያስ ክፍሌ መዝገብ በሶስት የሽብ በይግባኝ ባደረገችው ክርክር የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጋዜጠኝነት ሙዋየዋን በመጠቀም የሽብር ቡድንን ደግፋለች በሚል ወንጀል ብቻ ጥፋተኛ ናት በማለት የ14 ዓመቱን […]

‹‹ሁላችንም በአንድ ነገር ላይ ዕምነት ነበረን – ከዚህ በኋላ ያለው የእስራቸው ጊዜ ጊዜ አጭር ሊሆን እንደሚችል፡፡ ማን ያውቃል …›› ሰኔ 05 ቀን 2005 ዓ.ም (ከ25 ቀናት በፊት) እነተስፍሽን በቂሊንጦ በጠየኳቸው ቀን ይህንን አውግተን ነበር፡፡ ዛሬ እውነት ሆነ! ደስስስስ! ——————-የዞን 9 ጦማሪ ዘላለም ክብረት፣ ጋዜጠኞቹ ተስፋለም ወልደየስ እና አስማማው ሃይለጊዮርጊስ ከእስር ተፈቱ። ‹‹…ተስፍሽ፣ በፍቄና አጥናፍ መጡ፡፡ […]

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና ሌሎች በተመሳሳይ መዝገብ የተካተቱ ተከሳሾች ላይ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለዛሬ ተከሳሾች በነጻ ይሰናበቱ ወይስ ይከላከሉ በሚለው ላይ ብይን ይሰጣል ተብሎ ተጠብቆ የነበር ቢሆንም ብይኑ ሳይሰጥ ተቀጥሯል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ፣ የአንድነት እና የዓረና ትግራይ አመራሮች የሺዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታ፣ ሀብታሙ አያሌው እና […]

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ነው ። ወ/ ሮ ሚልድሬድ ማሼጎ እና የአብራካቸው ክፋይ የሆነችው ፓትሪሲያ ስማቸው የአለማችን የድንቆች መዝገብ ውስጥ የሰፈረው። በደቡብ አፍሪካ ካስቲል ነዋሪ የሆኑት የ38 አመቷ እናት ወ/ሮ ማሼንጎና የ19 አመቷ ወጣት ልጃቸው ፓትሪሲያ በአንድ ወር ውስጥ፣ በአንድ ሣምንት ውስጥ እንዲሁም ከተመሳሳይ ሰው በመውለድ ወ/ሮ ማሼንጎ ልጅና የልጅ ልጅ አገኙ ፣ ወጣት ፓትሪሲያ ልጅና […]

ቴዲ አፍሮ ከጎሳዬ ጋር ተጣምረው ያቀርቡታል የተባለው ኮንሰርት በቪዛ ምክንያት ፕሮግራሙ መፋለሱ የሚታወስ ሲሆን ቴዲ ግን ዛሬ የበረራ ጉዞ ነበረው።ጉዳዩ ከሙዚቃ ስራ ጋር የተያያዘ አልነበረም።ባለቤቱ አምለሰት ሙጬ በአሁኑ ሰአት ለጤንነት ቼክሃፕ ኬንያ ናይሮቢ ትገኛለች።ቀደም ብላ የሄደችው ሚስቱን እንዴት ነሽ? ለማለትና ከጎኗ ለመሆን ፈልጎ ለጉዞ የሚያስፈልጉትን የነፍስ ወከፍ እቃዎች በሻንጣ በመሸከፍ በዛሬው አለት ከቀኑ 11 ሰአት […]

ህወሃት የሚመራዉ የመከላከያ ሰራዊት የዘመቻ መምሪያና ክትትል ቢሮ እንዲሁም የመከላከያ ደህንነት የበላይ ሃላፊዎች በአርበኞች ግንቦት 7 የከፈተበትን ጦርነት ለመከላከያ ሚኒስቴር በማመልከት በአስቸኳይ የመከላከያ ሐይል ተጨምሮ ስፍራዉን የመልሶ ማጥቃት የጦር ክልል ካላደረግነዉ በስተቀር የተዋጊዎቻችዉ የጦር ስልት ከባድና የሚያሰጋ መሆኑን ገልጿል። በመሆኑም የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት የከፈተዉን ጦርነት መልሶ ያጠቃል የተባለ ሐይል ከጎንደርና ከወሎ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን በሰሞኑ በተደረገ ጦርነት ብቻ የ 44 ተኛ […]

…ከዚህ በኋላ ህዝብ ሰብስቦ ማውራት ላቆም ነው ። ጊዜው ተቀይሯል.. ትግል ለደካማ መንፈስ አይሆንም ።ትግል መውደቅን ይጠይቃል። ሲወድቁ ግን ለመነሳት መሞከርን ይጠይቃል። ስንወድቅ ልታዩን ትችላላችሁ ስንነሳ ግን ታዩናላችሁ …Filed under: political opinion

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት በእነ አቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ የአቃቤ ህግን እና የመከላከያ ምስክሮችን ቃል በንባብ አሰምቶ ማጠናቀቁን ተከትሎ ዛሬ በ18 ተከሳሾች ላይ ፍርድ ሰጥቷል። በዚህም መሰረት አቡበከር አህመድ፣ አህመዲን ጀበል፣ ያሲን ኑሩ፣ ካሚል ሸምሱ፣ በድሩ ሁሴን፣ ሼህ መከተ ሙሄ መኮንን፣ ሳቢር ይርጉ፣ መሀመድ አባተ፣ አህመድ ሙስጠፋ፣ አቡበከር አለሙ፣ ሙኒር ሁሴን፣ ሼህ […]

«ወደ ዝዋይ ማረሚያ ቤት እንደተዘዋወርኩ ከጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እና አበበ ቀስቶ ጋር ነበርን፡፡ ከጥቂት ጊዜያቶች በኋላ አበበ ቀስቶ ለህክምና ወደ አዲስ አበባ ሲዘዋወር ውብሸት ታዬ ወደ ሌላ ዞን ተቀየሯል፡፡ ዛሬ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ በማንም እንዳይጎበኝ ተከልክሏል፡፡ እኔም ለተወሰኑ ወራት በማንም እንዳልጎበኝ እግድ ተጥሎብኝ እንደነበር ታውቃላችሁ፡፡ በኋላ ላይ ቤተሰቦቼ እና ወዳጆቼ እንዲጠይቁኝ ተፈቅዶ ነበር፡፡ ሰሞኑን ግን […]

  አፕሪል 18፣ 2012 ከሚላን የ”ሐኪንግ ቲም” ቢሮ የወጣው የክፍያ መጠየቂያ የተላከው ለኢንሳ (የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ)ነው። ክፍያው የተፈጸመለት ሐኪንግ ቲም መቀመጫውን ጣልያን ያደረገ የኢንተርኔት ስለላ መሣሪያዎችና አግልግልቶችን የሚሰጥ ድርጅት ነው። ዜናው አክሎ እንደሚያተተው፣ ከመለስ ዜናዊ ሞት ከስምንት ወራት በኋላ ቢንያም ተወልደ የተባለ ግለሰብ ከመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን ጋራ ግንኙነት ያላቸው ስምንት ዶሜኖችን (የድረ ገጽ ስያሜና […]

አርበኞች ግንቦት 7 ጥቃት መሰንዘር መጀመሩን ዛሬ አስታወቀ። የአርባ ምንጭና አካባቢው ነዋሪዎች በወያኔ የፀጥታ ኃይሎችና ደህንነቶች ያልተቋረጠ እስር፣እና አፈና  እየተፈፀመባቸው መሆኑ ተገለፀ፡፡  ኢትዮጵያዊው ወታደር አልሸባብን መቀላቀሉ ተሰማ ብሀዴን መቢያስተዳድረው የአማራ ክልል  የተለያዩ ተቋማት ውጤት አልባ በመሆናቸው  እየፈረሱ መሆኑ ተነገረ በላይቤሪያ አዲስ በኢቮላ ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ለሁለተኛ ጊዜ ተገኙ።   አሰግድ ታመነ Filed under: NEWS, political […]

የኢትዬጵያ ቡና የተጫዋቾች ሰርቪስ የመጋጨት አደጋ ገጠመው ፡፡ የኢትዬጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ከ17 አመት በታች ቡድን ለጥሎ ማለፍ ዋንጫ ለዋንጫ ለማለፍ   ሰኔ 28/2007 ዓ.ም ከደደቢት ጋር ወሳኝ ግጥሚያ ነበረባቸው ፡፡ ይህን ተከትሎ ዛሬ ልምምዳቸውን በሱሉልታ ሜዳ አድርገው በሰርቪሱ ሲመለሱ ከቀኑ 4፡30 ሰዓት አካባቢ ወደ 18 ማዞሪያ የመኪና አደጋ አጋጥሟቸዋል ፡፡ በአደጋው ሶስት ተጫዋቾች ላይ […]

ከ1.9 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል -የጋላፊንና የሚሌን ፍተሻ ጣቢያዎች ማለፉ ግርምት ፈጥሯል -ተጠያቂዎቹ ንግድ መርከብና የቻይና ድርጅት መሆናቸው ተጠቁሟል በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የሚገኘው አሚድአብ ጄኔራል ቢዝነስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ከቻይናው ዌይፋንግ ሹኦፌንግ ኢምፖርትና ኤክስፖርት ኩባንያ ገዝቶ ወደ ኢትዮጵያ ያስመጣው በአራት ኮንቴይነሮች የአኩሪ አተር ዘይት፣ ሰኔ 23 ቀን 2007 ዓ.ም. መቐለ ደረቅ ወደብ […]

ባለፉት ሦስት ቀናት የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ትግራይ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የወያኔን ሃይል ገጥመው የወያኔ መኮንኖችን ጨምሮ በርካታ የወያኔ ሰራዊት አባላትን እንደገደሉ በቃል-አቀባያቸው አማካኝነት ለኢሳት ቴሌቪዥን ገልጸዋል። ለጥቀውም እስከ ትላንት ድረስ ውጊያው ቀጥሎ እንደሚገኝ በድጋሜ ዜናውን አብስረዋል። በወያኔ ዘረኛና ግፈኛ አገዛዝ የተንገፈገፈው የኢትዮጵያ ህዝብም ጆሮውን አቅንቶ ሁኔታውን በመከታተል ላይ ነው። ቀድሞውንም የወያኔ ሥርዓት ያለ ሃይል […]

በኢትዮጵያ ስላለው የመብት ረገጣ 90 ሚሊዮን ህዝብ ምስክር ነው” – ለእድገታችን አሜriካ ምስክር ሆነችልን ማለት ውጤት አያመጣም – ዶ/ር መረራ በአለማቀፍ ታላላቅ የሚዲያ አውታሮች መነጋገሪያ ሆኖ የዘለቀው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን የመጐብኘት ውጥን አሜሪካ አምባገነን መንግስታትን ከመደገፍ የመነጨ በመሆኑ እምብዛም ትኩረት የሚሠጠው ጉዳይ አይደለም ብለዋል – የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፡፡ ዶ/ር መራራ ጉዲና በአዲስ አበባ […]

ሰበር ዜና ================================================ ትናንት ሀሙስ ዕለት ሰኔ 25 2007 ዓ.ም የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት በትግራይ ክልል ቀፍታ መሲል፣ ሆርጃሞ እና ማይሰገል ላይ ህወሓት ከሚቆጣጠረው የ24ኛ ክፍለ ጦር፣ ፌደራል ፖሊስና ልዩ ኃይል ጋር ባደረገው ለአራት ሰዓታት የዘለቀ ከባድ ጦርት ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ፡፡ የአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ተጋዮች በትግራይ ቀፍታ መሲልና ሆርጃሞ ላይ መሽጎ […]

በህወሓት መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ተፈጥሮ የቆየው መከፋፈል በሁለት ፅንፍ የቆመ ሲሆን አንደኛው ቡድን በኤታማጆር ሹሙ ጀነራል ሳሞራ የኑስ ስር ሁለተኛው ቡድን ደግሞ የምስራቅ ዕዝ አዛዥ ከነበረው ሌ/ጀነራል አብርሃ ወ/ማርያም ጎን የተሰለፉ ናቸው፡፡ ሌ/ጀነራል አብርሃ ወ/ማርምን ከዕዝ አዛዥነቱ አንስቶ ወደ መከላከያ መምሪያ የማዛወሩ የእነ ጀነራል ሳሞራ የኑስ ቡድን ዕቅድ በሌ/ጀነራል አብርሃ ቡድን የበላይነት ሊከሽፍ ችሏል፡፡ ሆኖም […]

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ ታስራ ‹‹ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ በማወክ›› የተከሰሰችው ሜሮን አለማየሁ የ6 ወር እስር ተፈረደባት፡፡ ሜሮን አለማየሁ ሚያዝያ 14 በተጠራው ሰልፍ ላይ ‹‹ወያኔ ሌባ፣ መንግስት የለም፣ አትነሳም ወይ፣ የታረደው ወገን ያነተ አይደለም ወይ›› በሚል ሁከትና ብጥብጥ ፈጥራለች ተብላ በተከሰሰችበት በዋስ ወጥታ ጉዳዩን ስትከታተል የቆየች ሲሆን ዛሬ […]

ዜጎች በፖለቲካ አመለካከታቸው ከቀያቸው እየተፈናቀሉ ነው በምስራቅ ጎጃም ዞን አርሶ አደሮች ‹‹የማዳበሪያ ዕዳ አልከፈላችሁም›› በሚል በገፍ እየታሰሩ መሆኑን ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ አርሶ አደሮቹ ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ ወስዳችኋል የተባሉትን የማዳበሪያ እዳ እንዲከፍሉ እየተጠየቁ እንደሆነ የገለጹት ምንጮች በአንድ ቀበሌ ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች በጅምላ መታሰራቸውን ገልጸዋል፡፡ አርሶ አደሮች እነሱ ወስደውታል የተባለውን ብቻ ሳይሆን በሞት የተለዩትን […]

በመወያኔ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ አለመግባባቱ ተባብሶ መቀጠሉ ታወቀ በታላቁ አንዋር መሰጂድ ከባድ ተቃውሞ ተደረገ የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት በዓለም ዙርያ ቁጣ ቀስቅሷል።  አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ  ዘመቻ ተጀመረ የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአቶ አንዳርጋቸው አያያዝ ዙሪያ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸው ተሰማ በመወያኔ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ አለመግባባቱ ተባብሶ መቀጠሉ ታወቀ በመከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ አባላት የሆኑት ወታደሮች በአገልግሎት ማብቂያ በሚል […]

ዛሬ ሰኔ 26 ቀን 2007 ዓ.ም ልደታ ፍርድ ቤት 11ኛ ችሎት ቀርበው በቂሊንጦ ታስሮ ሚገኘው ማስተዋል ፈቃዱ ባለመቅረቡ የአቃቢ ህግ ይግባኝ ሳይታይ ቀርቶአል፡፡ ወይንሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬ እና ቤተለሄም አካለወርቅ ትናንት በዛቻ እና ማስፈራራት ክስ ቄራ ምድብ ችሎት ቀርበው በዋስ እንዲወጡ ቢታዘዝም ካሳንቺዝ ስድስተኛ ፖሊስ ግን ታሳሪዎቹን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ጠዋት በልደታ […]

ሁለት የአላባማ ካውንቲ ፍርድ ቤቶች ውሳኔውን ውድቅ በማድረግ ምንም አይነት የተመሳሳይ ጋብቻ የምስክር ወረቀት የማይሰጡ መሆናቸውን ገልጸው ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ዳግም እንዲያጤነው ጠይቀዋል። ከዚህም በተጨማሪ የቴክሳስ ከፍተኛ አተርኒ ተመሳሳይ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በግለሰብ ነጻነት ስም ሰዎች ሰብአዊ ክብራቸውን እንዲያዋርዱ መፍቀድ የለብንም የሚሉ አሜሪካውያን በየግዛቱ ተቃውሞ በማሰማት ላይ ናቸው። አንድ ታዋቂ የቤተክርስትያን ፓስተር በበኩላቸው በሚያገለግሉበት […]

32ኛው በሰሜን አሜሪካ በድምቀት እየተከበረ የሚገኘው የኢትዮጲያዊያን የሰፖርትና የባህል ፌስቲቫል ላይ ከተዘጋጁት ዝግጅቶች መሀከል በጉጉት የሚጠበቁት የሃሙስ እና የዓርብ የሙዚቃ ዝግጅቶች በወጣላቸው ፕሮግራም መሰረት እንደሚደረጉ ተረጋገጠ። ቴዲ አፍሮና ጎሳዬ ተስፋዬ ቪዛቸውን ለማግኘት የአሜሪካ ኤምባሲ የሲስተም መበላሸት ያዘገየው ቢሆንም አሁን ከደቂቃዎች በፊት ኤንባሲው ችግሩን እንዳስተካከለ የሚከተለውን መግለጫ አውጥቷል። U.S. Embassy Addis Ababa በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካን […]

በቱርክ ዋና ከተማ ኢስታንቡል የተሰባሰቡ ግብረሰዶማውያን ሊያደርጉት አቅደው የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ የአገሪቱ መንግስት ህገወጥ ነው ሲል በውሃ መርጫ ካኖን መበተኑ ተሰምቷል። ከሰሞኑ በዓለም ላይ እየተከበረ ያለውን የግብረሰዶማውያን ቀን ለማክበር ወጥተው የነበሩት እነዚህ ሰልፈኞች በታቅሲም አደባባይ አቅራቢያ በመሰባሰብ ላይ እንዳሉ በፖሊሶች እንዲበተኑ መደረጉን በስፍራው የነበረ የሮይተርስ ዘጋቢ ተናግሯል። ፓሊሶች የሰልፉ መሪዎችን ካሰሩ በኋላ ከተማዋ ወደ ቀድሞው […]

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር መንግስት አይ.ኤስ.አይ.ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ እስር ላይ ቆይተው ሰኔ 15/2007 ዓ.ም በቄራ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት እንዲፈቱ ተወስኖላቸው ሰኔ 16/2007 ዓ.ም ከእስር ቤት ሲወጡ እንደገና በፖሊስ ተይዘው የታሰሩት ወንይሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለወርቅ ዛሬ ሰኔ 22/2007 ልደታ ፍርድ ቤት 11ኛ ምድብ ችሎት ቀርበው ቀደም ሲል ‹‹ሁከትና ብጥብጥ አስነስተዋል›› […]

አይ ኤስን ለመቃወም ከተጠራው ሰልፍ በኋላ ፖሊስና አቃቤ ህግ በየ ችሎቱ ኢህአዴግ ላይ ሰልፍ በመጥራት ስድብ እያዘነቡበት ነው፡፡ በሚያዝያ 14ቱ ሰልፍ ላይ በቦታው ያልነበሩት የሰማያዊ፣ የቀድሞው አንድነትና የቀድሞው መኢአድ አባላትና አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ወጣቶችን ያስሩና እነዚህ ወጣቶች ያላሉትን ክስ ብለው ያቀርባሉ፡፡ ይህ ክስ ደግሞ ለእነሱ የሰልፍ መፈክር መሆኑ ነው፡፡ የስድብ ውርጅብኝ፡፡ በቃ ችሎት የቁጭት መውጫቸው […]

ዛሬ በጥዋት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ሊሰጥ የተቀጠረውን ውሳኔ ተመልክቼ ለመዘገብ ልደታ በሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አምርቼ ነበር፡፡ 3፡30 ሰዓት ገደባ በታችኛው መግቢያ በር ጋር ስደርስ፣ ቁጥራቸው በዛ ያሉ፣ የሚሊተሪ ልብስ የለበሱ የጸጥታ ሃይሎች እና የአዲስ አበባ ፖሊሶች በፍርድ ቤቴ ቅጥር ግቢ በር ላይ ሆነው ሰዎችን በጥብቅ እየተፈሹ ሲያስገቡ አስተዋልኩ፡፡ በአጋጣሚ ከጠበቃ […]

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ እንዲሰፍን እየታገልኩ መሆኔ በክስ ማቅለያነት እንዲወሰድልኝ›› ወጣት ቴዎድሮስ አስፋው በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም መንግስት በጠራው ሰልፍ ሰበብ ታስረው ‹‹ኢህአዴግ ሌባ ነው፣ ህገ መንግስቱ ወረቀት ነው፣ ታፍነናል፣ ታስረናል፣ መለስ የሞተው ደንግጦ ነው፣ ሀይለማሪያም ደሳለኝ በቁሙ የሞተ ነው፣ ቴዎድሮስ ለህዝብ ነው የሞተው›› በሚል ብጥብጥና ሁከት ፈጥራችኋል፣ የሀሰት […]

በነ ዘመነ ካሴ መዝገብ የተከሰሱት 5 የመኢአድ አባሎች ናቸው አንዳርጋቸው ፅጌን በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርብላቸው ነው የጠየቁት የተከሰሱት የግንቦት 7 አባል ናችሁ ተብለው ነው በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ስልጠና ተሰጥቷችሁ የሽብር ተግባር ለመፈጸም ስትንቀሳቀሱ ነበር ተብለው ላለፉት ሁለት አመታት በእስር የሚገኙት እነዚህ ተከሳሾች አንዳርጋቸው ፅጌ የሚባል ሰው አናውቅም አንዳርጋቸው አሱ አውቃቸዋለሁ አሰልጥኛቸዋለሁ የሚል ከሆነም በናንተ ቁጥጥር ስር […]

መንግስት አይ.ኤስ.አይ.ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ እስር ላይ ቆይተው እንዲፈቱ ተወስኖላቸው ከእስር ቤት ሲወጡ እንደገና በፖሊስ ተይዘው የታሰሩት ወንይሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለወርቅ ላይ ፖሊስ አዲስ ክስ አቀረበ፡፡ እነ ወይንሸት ሰኔ 18/2007 ዓ.ም ቀደም ብለው ተከሰውበት በነበረው ተመሳሳይ ‹ወንጀል› ፖሊስ የምርመራ መዝገብ ይዞ ቀደም ብለው ውሳኔ ባገኙበት በተመሳሳይ ቄራ ፍርድ ቤት ቀርበው ዳኞቹ ‹‹እኛ ፈርደናል፤ እንዲለቀቁም […]

የእንግሊዝ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 18/2007 ዓም በአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ ባወጣው መግለጫ የኢህአዴግ/ወያኔን መንግስትን ማስጠንቀቁን ሮይተርስ ዘገበ አቶ አንዳርጋቸው የህግ ድጋፍ በማያገኙበትና ይግባኝ ሊጠይቁ በማይችሉበት ሁኔታ በአስከፊ ሁኔታ መታሰራቸውን የእንግሊዝ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ፊሊፕ ሀሞንድ አውግዘዋል። የአቶ አንዳርጋቸው አያያዝ እና ደህንነት እንደሚያሳስበን በተደጋጋሚ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሃኖም ብንገልጽም ከቃል ያለፈ መልስ አለገኘንም፣ […]