የኢትዮቴሌኮም ዋና ድረገፅ በሀከሮች ተጠለፈ
ሳሚ ቺቺሮቮ ከ አልጄሪያ ነኝ የሚለው ይህ ግለሰብ የኢትዮቴሌኮም ዋና ድረገፅ ሙሉ ለሙሉ በመቆጣጠር የድርጅቱን መልዕክት በራሱ መቀየሩን ድሬቲዩብ ድረገፅ ተመልክቷል። ኢትዮቴሌኮም በዚህ ጉዳይ ላይ የሰጠው መግለጫ የለም። በደንበኞች ላይ ሊያደርስ የሚችለው ጉዳት ወይም እያደረሰ ያለውን ጥቃት ለማወቅ አልተቻለም። ኢትዮቴሌኮም ይህ ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ኢትዮ ቴሌኮም ድረገፁን መቆጣጠር አልቻለም።