የኢትዮጵያ ወታደሮች በሂራን አዉራጃ የምትገኘዋን በለትወኔ የምትባለዉን ስትራቴጂክ ከተማ እንደተቆጣጠሩ ቢቢሲ ዘገበ። ኢጋድ የተሰኘዉ የምስራቅ አፍሪካ አገራት ስብሰብ፣ የሶማሊያ የጎሮቤት አገሮች ለአፍሪካ ሕብረት ጦር አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ መጠየቁ ይታወቃል። በዚህም መሰረት ኬንያ በደቡብ በኩል አልሻባብ ላይ ጥቃቷን ስታጠናክር ፣ ኢትዮጵያም በደቡብ ምእራብ በኩል ልትንቀሳቀስ እንደምትችልም ብዙዎች ይጠብቁ ነበር። በደቡብ በኩል በኬንያ ፣ በሰሜን በኩል በቡሩንዲ ጅቡቲና […]

[email protected] የአሥራ ሰባት አመት ወጣት ነዉ። ጥይት የጎረሰ ሽጉጥ በእጁ ይዟል። እጅግ በጣም ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ፣ ንግግር አድርገዉ ወደ ጨረሱ አንድ የእድሜ ባለጸጋ ሰዉዬ ቀስ በቀስ ይጠጋል። ሳያስቡት የያዘዉን ሽጉጥ ወደ እርሳቸዉ ደቅኖ ይተኩሳል። ሰውየዉ ይወድቃሉ። አካባቢዉ ተረበሸ። ተናወጠ። አምቡላንስ ተጠርቶ በአፋጣኝ በስፍራዉ ደረሰ። የወደቁትን አባት በአምቡላንሱ የነበሩ የህክምና ባለሞያዎች አነሷቸዉ። የፍጥነት ጉዞ ወደ […]

የመድረክ አባል የሆነው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለየ ሁኔታ ጐላ ያለ እንቅስቃሴ እያካሄደ መጥቷል፡፡ ባለፈው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ረጅም ጊዜ የወሰደ የውስጥ ግምገማ ካካሄደ በኋላ ፓርቲው የአምስት ዓመት ስትራቴጂ ሰነድ ለማዘጋጀት መቻሉ ይነገራል፡፡ አንድነት ፓርቲ ፍኖተ ነፃነት የተሰኘ ልሳኑን በየሳምንቱ ያሳትማል፡፡ በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ምሁራንን በተለያዩ ጉዳዮች […]

የጥፋት ሀይል ነው፤ ይህ ቡድን ጭራሽ ለሀዝብ ከበሬታና ፍቅር የለውም፤ አገር ሻጭ ነው፤ በጭራሽ የሚታመን አይደለም፤ ጨፍጫፊ ነው። በአጠቃላይ ከሴጣን ነው የምትጋቡ፤ በርምጃችሁ አናንተም ወገኖቻችሁንም ትጎድበታላችሁ። የመለስን መንግስት በሚመለከት እነዚህን በመሰሉ ጉዳዬች ላይ ለያንዳንዳቸው ይዘቱ ቅዱሱን መፀሀፍ የሚያካክል መረጃዎች ሊቀርብበት የሚችል ፍፁም የሆነ እውነትነት ያላቸው ክሶች ናቸው የሚነሱት። ጊዜው ሲመጣ በሀገር ክህደት፤ በዘር ማጣፍት በመሳሰሉ […]

ረሃብ በሀገራችን እንደማንኛውም የዓለም ሕዝብ የሚታወቅ ሲሆን በኢትዮጵያ ለየት የሚያደርገው ባለፉት አርባ ዓመታት ከረሃብ የተለችበት ጊዜ አለመኖሩና መለመዱ ነው። በየአገሩ ያለው ረሓብ እንደማኅበረሰቡ ባህልና የኑሮ ደረጃ የሚገለጽ ሲሆን በኢትዮጵያ ረሓብ አለ የሚባለው በርካታ ሰዎች ሲሞትና ዓለም አቀፍ ዜና ማሰራጫዎች መዘገብ ሲጀምሩ ነው። ለመሆኑ “ረህብ” ምንድነው? እንዴትስ ይገለጣል? ረሓብና ሰው? ረሓብና እንሣት፤ አእዋፍ፤ እጸዋት፤ በምድሩ ላይ […]

የበረከትን መፅሃፍ አነበብኩት… በእውነቱ ህትመቱ ቆንጆ ነበር። ሽፋኑ እንደ ሃብታም ጉንጭ ይለሰልሳል። ከቻርልስ ዲክንስ ታዋቂ መፅሃፍ የተኮረጀ ቢሆንም ርእሱም ቢሆን አሪፍ ነው – የሁለት ምርጫዎች ወግ። የበረከትን መፅሃፍ ያሳተመው መሃመድ አላሙዲ የተባለው ነጋዴ መሆኑን ፍትህ ጋዜጣ ላይ አንብቤ ነበር። መፅሃፉ 314 ገፆች እና 10 ምእራፎች ይዞአል። ዋጋው 90 ብር ነው። ሪፖርተር በዜና ዘገባው፣ ሼክ መሃመድ […]

ባለፈው ጊዜ ሌጋተም የተባለው ድርጅት የ 110 አገሮችን የብልጽግና ደረጃ ሲያጠና ሰንብቶ ባወጣው ሪፖርት ላይ በ አጠቃላይ ውጤት ኢትዮጵያ እንደተለመደው ወደ መጨረሻው ሆና 108 ኛ ወጥታለች:: እንዲህ አይነቱ የመጨረሻ አካባቢ ውጤት የተለመደ በመሆኑ እምብዛም አልተገረምን:: ለዛሬው ጽሁፌ መነሻ የሆነኝ ታዲያ ካሉት የብልጽግና መለኪያ ተለዋዋጮች(variables) መካከል በጣም አስፈለጊ በሆነው የግለሰቦች መብት(personal freedom) ከ110ሩ 110ኛ የመሆኑዋ ነገር […]

አቃቢ ሕግ ሰባተኛ ተከሳሽ በሆነዉ ፣ አቶ እስክንድር ነጋ፣ ግንቦት 20 2002 ዓ.ም የተጠለፈ፣ ከአዲስ ድምጽ ራዲዮ አዘጋጅ አቶ አበበ በለዉ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስን እንዲሁም በከረንት አፌር ፓልቶክ ክፍል በብዙ ወንድማገኘዉ (ሞያዬ ምስክር) አወያይነት የተደረገን ዉይይት፣ ትላንት ዴሴምበር 29 ቀን በተቀመጠዉ የፍርድ ችሎት፣ እንደ መረጃ ማቅረቡን፣ የአማርኛዉ ክፍል ጀርመን ድምጽ ራድዮ ሪፖርተር ከአዲስ አበባ […]

የኦሮሞ ነጻ አዉጭ ግንባር፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያዉያንን ሁሉ የጋበዛ አገራዊ ስብሰባ በሜኔሶታ እንደጠራ የዘሐበሻ ጋዜጣ ድህረ ገጽ ገለፀ። «እሁድ ጃንዋሪ አንድ ቀን በኢን ሆቴል ሴንት ፖል በሚደረገዉ በዚሁ ስብሰባ ላይ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከሌሎች ኢትዮጵያዉያን ወንድሞቹ ጋር በጽናትና በአንድነት የሚታገልበትን ሁኔታ ያበስራል ተብሎ ይጠበቃል» ሲል ያተተዉ ዘሃበሻ፣ በአካካቢዉ ካሉ በርካታ ስቴቶች ብዙዎች የሰብሰባዉ ተካፋይ ለመሆን […]

አገር ዉስጥ የሚታተመዉን ካፒታል ኢትዮጵያ የተሰኘዉን የእንግሊዘኛ ጋዜጣ ጠቅሰን፣ ወደ ሶስት መቶ የሚሆኑ ከፍተኛ የኢትዮጵያ መኮንኖች ስራቸዉን እንዲለቁ መደረጉን መዘገባችን ይታወሳል። ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ እንደሚጠቁመዉ ከስራ እንዲሰናበቱ ከተደረጉት መኮንኖች መካከል ጄነራል ሳሞራ የኑስ እና ከርሳቸው ጋር ቅርበት ያላቸዉ ሞኮንኖች እንዳልተነኩ ለማወቅ ችለናል። ለአቶ መለስ ዜናዊ በጣም ታማኝ የነበሩትና በቅርቡ ግን ከጄነራል ሳሞራ የኑስ ጋር […]

በሽብር ስራ ተሰማርታችኋል በሚል መስረት የሌለዉ ክስ የታሰሩ፣ የአቶ አንድዋለም አራጌ፣ የአቶ እስክንድርና ነጋ እና ሌሎች ሰላማዊ ታጋዮችን ጉዳይ የሚያዳምጠዉ ችሎት፣ ዲሴምበር 24 ቀን ፣ አቃቢ ሕግ ያቀረባቸዉን ቪዲዮዎችና ኦዲዮዎች አዳምጧል። ፍርድ ቤቱ በመጀመሪያ ያዳመጠዉ በአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት ዉስጥ በይፋና በግልጽ የተደረገዉን፣ አቶ እስክንድር ነጋ በእንግድነት የተገኙበትን እና በአቶ አንዱዋልም አራጌ የተመራዉን ስብሰባ ነበር። በዚህ […]

አቡጊዳ – የናዝሬት ድህረ ገጽ አቶ እስክንድር ነጋን የአመቱ ሰዉ ብሎ ሰየመ ! ሁሉንም ወገኖች ፣ የኢሕአዴግ ደጋፊዎችን ሆነ የሕወሃት/ኢሕአዴግ ተቃዋሚዎችን የሚያስተናግደዉ ገለልተኛው የናዝሬት ድህረ ገጽ፣ አንጋፋዉ ጋዜጣኛ እስክንድር ነጋን የአመቱ ሰዉ ብሉ ሰይሞታል። ድህረ ገጹ፣ ሃሳብን በነጻነት የመግልጽ መብት ይከበር ዘንድ አቶ እስክንድር በየሳምንቱ ለአንባቢያን ፣ ትምህርት ሰጪ ጽሁፎች ያለ ማቋረጥ ማበርከቱን ያስታወሰ ሲሆን፣ […]

ቅዳሜ መታተም የነበረበት የፍትህ ጋዜጣ፣ አንድ ቀን ቆይቶ እሑድ እንደታተመ፣ የኢኤምኤፍ ድህረ ገጽ ገለጸ። በፍትህ ጋዜጣ አዘጋጆችና ዘገባዊዎች ላይ ከመቼዉም በበለጠ ጫናና ወከባ እየደረሰ እንደሆነ ይታወቃል። የጋዘጣዉ አምደኛ የሆነችዉ ርዮት አለሙ መሰረት በሌለዉ የሽብር ክስ ተከሳ በወህኒ የምትገኝ ሲሆን የርሷ ጠበቃ በፍርድ ቤት የሚያቀርባቸዉ፣ የጋዜጣዉ አዘጋጆችን ጨመሮ በርካታ ምስክሮች ማስፈራሪያ እንደሚደርስባቸዉ ኢኤምኤፍ አዲስ አበባ ያሉ […]

ዶር በረከተ ሃብተ ስላሴ ከጥቂት ወራት በፊት፣ የቆሰለች አገር ( Wounded Nation) የተባለዉን መጽሃፋቸዉን፣ በርካታ ኢትዮጵያዉያን በተገኙበት ፣ ኒዉዮርክ በሚጘኝ የባርስን ኤንድ ኖብልስ መጽሃፍት ቤት አስመርቀዋል። በዚሁ ወቅትም፣ በኤርትራ ስላለዉ ሁኔታ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ በዚያ ከነበሩ ወገኖችም ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ግልጽ ምላሾች ሰጥተዋል። ዶር በረከት ፣ አስመራ የተወለዱ የሕግ ባለሞያ ሲሆኑ፣ በአጼ ኃይለስላሴ ዘመን፣ የሃር […]

[email protected] ዲሴምበር 20 2011 «እነ መለስ ናቸዉ ሕግ። መለስ የፈለገዉን ነገር ሕገ ወጥ ነዉ ካለ ሕገ ወጥ ነዉ። ይህን አዉቀህ ምኑን ነዉ ታገል የምትለዉ? ምኑን ነዉ በሰላማዊ መንገድ ለዉጥ አመጣለሁ የምትለዉ ? እርሱ እኔ በፍጹም ትርጉም ያለዉ እዉነተኛ ለዉጥ ለማምጣት የሚደረግ እንቅስቃሴ ነዉ ብዬ አላምንም ….. ጊዜ ማጥፋትና እራስን መሸንገል ካልሆነ በቀር» « ..ግን መገፋት […]

አቶ በረከት ስምዖን መጽሀፍ አሳተመ ሊያስመረቅም ነው የሚል ዜና ከወደ ሸገር ሰማንና ተደመምን ። እ ህ ህ ም አልን። የአረም እርሻን ያስታውሷል ! የደርጉ ካሳዬ አራጋው በዘመነ ደርግ መገባደጃ የሆነ መጽሀፍ ጽፈው ነበር እናም እቀድሞው ወመዘክር አግኝቼ ሳነበው ለአማርኛ አስተማሪዬ አዘንኩላቸው ፤ ለካንስ በእነ ካሳዬ አንጻር እርሳቸው ሊቅ ነበሩና ! ዛሬ ደግሞ ምስጋና ለእድገትና ትራንስፎርሜሽን […]

በአዲስ አበባ በተደረገዉ ታላቁ ሩጫ እንደ ወትሮው ሕዝቡ በሕወሃት/ኢሕአዴግ አገዛዝ ላይ ያለዉን ብሶት ምሬት ገለጸ። በሩጫዉ የተሳተፉ ቁጥራቸው እጅግ በጣም በርካታ የሆኑ ወጣቶች በተቀናጀና በተቀነባበረ መልኩ የተለያዩ ዜማዎችን ያሰሙ የነበረ ሲሆን፣ አቶ መለስ ዜናዊ የሙአመር ጋዳፊ እድል እንደሚገጥማቸዉ በመግልጽ ለእኝሁ አምባገነን መሪ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። ጋዳፊ የተመኩበት ሰራዊታቸዉና የደህንነት አባሎቻቸዉ በጥቅምና በገንዘብ የገዟቸዉ ባሪያዎቻ ከሕዝብ ቁጣ […]

ማክሰኞ ታህሳስ 10 ቀን 2004 ዓ.ም ፡- የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በሽብርተኝነት ወንጀል በከሰሳቸው 24 የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላት፣ የመብት ተሟጋቾችና ጋዜጠኞች ላይ በኢቲቪ አኬልዳማ ዶኩመንተሪ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ሰዎችን በዋና ምስክርነት አቀረበ፡፡ ብዙዎቹ መስካሪዎች በጭንቀትና በመርበትበት ሲናገሩ፣ አንዳንዶቹም ሲያለቅሱ ነበር። ዛሬ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ አርቲስት ደበበ እሸቱ 29ነኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክር ሆኖ ከፍተኛው ፍርድ […]

ሁልጊዜ የክፉዎች፣ ገፊዎች፣ የአመጸኞችና አስጨናቂዎች መዝገበ ታሪክ እያገለባበጥን ግድፈት፣ ክፋት፣ ሴረኝነትና አረመኔነት ማተት ብቻ ሳይሆን አንዳንድ ጊዜ ደግሞ (በተለይ በአሁን ሰዓት) ዓይን የማፍረጥና እጅ የመቆረጥ ያክል ቢያመንም፣ ባንፈልገውም የሚያስፈልገን፣ ጀሮአችን ይሰማው ዘንድ ባይወድም ነፍሳችን ማወቅ የሚገባትን፣ የሚበጀንና ህልማችንን እውን የሚያደርግ፣ የሚፈለገውንም ስፍራ የሚያደርሰን እስከሆነ ድረስ እርስ በርሳችን በግላጭ መነጋገሩ፤ ከዚህም አልፎ እንደሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም ሆነ […]

[email protected] የአንድነት ፓርቲ በቅርቡ ባደረገዉ ጠቅላላ ጉባዔው ፣ ዶር ነጋሶ ጊዳዳን የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል። ይህን አስመልክቶ አጭር አስተያየት የሰጠዉ አፍቃሪ ኢሕአዴጉ አይጋ ፎረም፣ የቅንጅት ነገር እንዳበቃለት ይናገራል። “With Gebru Asrat leading ARENA and Dr Negasso leading UDJ, MEDREK may finally shed its “tseguri hemeq” inherited from Kinjit! It will also mean EPRDF will have […]

ማንም የዳስሰው አይመስለኝም፡፡ የቀይ ባህር እና ህንድ ውቅያኖስ መጋጠሚያ Gulf of aden አሰቃቂ ጉዞ እና የሱማሊያውያኑን ኢሰብአዊ ድርጊት፣የእኛም በጉዞ ላይ የዘቀጠ ማንነት.የሚካተትበት ትረካ ነው፡፡ መሳፈሪያው ቦታ እስክንደርስ እና ለመሳፈር ባህሩ ጋር ስላለው ነገር ያለውን እንዝለለው፡፡ አሁን ምናቦትን አውሱኝ እና የትራንስፖርት ሳይከፍሉ እንጓዝ……. በጀልባው ላይ ያለው የመጫን ስርዓት ፣ወደ ጀልባ መጫኛው ቦታ ያለው ጉዞ ሁሉ በጣም […]

([email protected]) «የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የዲያስፖራ ረቂቅ ፖሊሲ» በሚል ርእስ፣ በኅዳር ወር 2004 ዓ.ም ፣ በኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የተዘጋጀ 24 ገጾችን የያዘ አንድ ሰነድ አነበብኩኝ። «የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ከትዉልድ ሀገሩ ጋር ያለዉን ትሥሥር በማጠናከር በአገሩ ልማት ሰላምና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ጠንካራ ተሳታፊ ሆኖ፣ ራሱን ጠቅሞ ትዉልድ አገሩንም በመጥቀም፣ በጋራ ለማደግ የሚያስችል አመቺ ሁኔታ መፍጠርና […]

ገሊላ ወረዳ ሰሜን አሪ በሚባል ቦታ ሕዳር 12 ቀን 2004 ዓ.ም በግብርና ሙያ ቨሚተዳደር አቶ ለጊዜ ወርቅማ በፖሊሶች ተዘርፎ ጉዳት እንደደረሰበት ከሥፍራው ያገኘነው መረጃ ጠቁሟል፡፡ አቶ ለጊዜ ወርቅማ ከማሳው ቡና ለቅሞ ወደ ቤቱ እየሄደ ሳለ ወረዳው በሚገኙ በመንግሥት ፖሊሶች ዝርፊያና ጉዳት ከደረሰበት በኋላ ሕዳር 13 ቀን 2004 ዓ.ም ለሕክምና ዕርዳታ ሄዶ ሕይወቱ አልፏል፡፡ በአቶ ለጊዜ […]

“እኛ ጭቁን ብሄረሰቦች ከዚህ ቀደም በየሰው ቤት ተቀጥረን የምንሰራ፣ አሽከሮች እየተባልን ነበር የኖርነው፡፡ አሁን ግን ይኸውና ህገ-መንግስታችን መብታችንን ሰጥቶናል… ኑሯችንም ተሻሽሎ ዛሬ ዘመናዊ ኑሮ እየኖርን ነው፡፡” እያለ የሚናገርን አንድ ጎልማሳ የቴሌቪዥኑ መስኮት ያሳያል፡፡ የደቡብ ቅላጼና ዘዬ ባለው አማርኛ ከደቡብ የመጣ ጎልማሳ ነው በቴሌቪዥን ቀርቦ መግለጫ እየሰጠ ያለው፡፡ ከአነጋገሩ በቀን ሶስቴ የሚበላ፣ የባቡር ሃዲድ እና የኤሌክትሪክ […]

ጥይት በስቶት ሲያፈስ ተናግሮ ጦር ሜዳ:- በመለስ ማንነት መስክሯል ይህ ኮዳ:: መኮንን ዘለለው አብራርቷል በይፋ:- ዶክተር ገብረ-መድህን ጠይቁት አይጠፋ:: በኮዳ ቀዳዳ መለስ እንደታየው:- በቁሙ የሞተ የፈሪ ገዳይ ነው:: የፈሪ ክፋቱ መግደል ብቻ አይደለም:- አፍ ያበዛል በሕዝብ ያለ እሱም ሰው የለም:: ጀግና ነኝ እያለ በመግደል ያበጠው:- የትግል ጓዶቹን ገድሎ ያሟጠጠው:- መለስ ዜናዊ ነው ተንኮል የመለጠው:: ዛሬም […]

የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስቴር የነበሩት፣ አቶ ስዬ አብርሃ፣ ዛሬ ታህሳስ 1 ቀን የአንድነት ፓርቲ ያደረገዉን የጠቅላላ ጉባዔ በሳካይፒ የተካፈሉ ሲሆን ፣ ድርጅታቸዉ በፈታኝና ከባድ ሁኔታ ዉስጥም እያለ አሁን ያለበት ደረጅ መድረሱ በጣም የሚያስደስት እንደሆነ ገልጸዋል። አቶ ስዬ ገዢዉ፣ ፓርቲ ከጦር በላይ የሚፈራዉ የሰላማዊ ትግል እንደሆነ በማስመር፣ የሰላማዊ ትግሉ ከመቼዉም በላይ መቀጠል እንዳለበት ያሳሰቡ ሲሆን፣ በተለይም የነ […]

የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስቴር የነበሩት፣ አቶ ስዬ አብርሃ፣ ዛሬ ታህሳስ 1 ቀን የአንድነት ፓርቲ ያደረገዉን የጠቅላላ ጉባዔ በሳካይፒ የተካፈሉ ሲሆን ፣ ድርጅታቸዉ በፈታኝና ከባድ ሁኔታ ዉስጥም እያለ አሁን ያለበት ደረጅ መድረሱ በጣም የሚያስደስት እንደሆነ ገልጸዋል። አቶ ስዬ ገዢዉ፣ ፓርቲ ከጦር በላይ የሚፈራዉ የሰላማዊ ትግል እንደሆነ በማስመር፣ የሰላማዊ ትግሉ ከመቼዉም በላይ መቀጠል እንዳለበት ያሳሰቡ ሲሆን፣ በተለይም የነ […]

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ዛሬ እሁድ ታህሳስ 1 ቀን 2004 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባዔዉን አጠናቀቀ። ለሚቀጥሉት አመታት ድርጅቱን በሊቀመንበርነት የሚመሩትን እንዲሁም የድርጅቱ የላእላይ ምክር ቤት አባላትን ጠቅላላ ጉባዔዉ የመረጠ ሲሆን ስብሰባዉ በተሳሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዜና ያመለክታል። የድርጅቱ ሊቀመንበር ለመሆን ዶር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የአዲስ አበባ የአንድነት ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶር ንጋት አስፋዉ እንዲሁም ከአንድነት […]

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ነገ ጠቅላላ ጉባዔዉን ያደርጋል። በአገሪቷ ካሉ ክልሎች በሙሉ፣ በአካባቢዉ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ተመርጠዉ የመጡ የአንድነት ፓርቲ የጠቅላላ ጉባዔ አባላት ፣ የፓርቲዉ የላእላይ ምክር ቤትም የሚመርጡ ሲሆን፣ የድርጅቱ የወደፊት አቅጣጫ ላይ ሰፊ ዉይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። በተሻሻለዉ የድርጅቱ ደንብ መሰረት ጠቅላላ ጉባዔዉ የድርጅቱን ፕሬዘዳንት የሚመርጥ ሲሆን የተመረጡት ፕሬዘዳንት የካቢኔዉ ወይንም የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ […]

በመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ ላዕላይ ም/ቤት ሥራ አስፈጻሚ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት በሁለት ቦታ ተከፍሎ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ የሁለቱንም አመራር አካላት አቤቱታ የተቀበለው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሁለቱም በጋራ በመሆን እስከ ህዳር 30 ቀን 2004 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ ጠርተው አለመግባባታቸው በጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ እንዲያገኝ መመሪያ ሰጥቶ ነበር፡ ፡ ዋናው ጽ/ቤት የሚገኘው በፓርቲው ፕሬዘዳንት ኢንጂነር ኃይሉ ሻወል የሚመራው […]