ኮዳው ያጋለጠው አቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ-ወመንፈሳዊ.

ጥይት በስቶት ሲያፈስ
ተናግሮ ጦር ሜዳ:-
በመለስ ማንነት
መስክሯል ይህ ኮዳ::
መኮንን ዘለለው አብራርቷል በይፋ:-
ዶክተር ገብረ-መድህን ጠይቁት አይጠፋ::
በኮዳ ቀዳዳ መለስ እንደታየው:-
በቁሙ የሞተ የፈሪ ገዳይ ነው::
የፈሪ ክፋቱ መግደል ብቻ አይደለም:-
አፍ ያበዛል በሕዝብ ያለ እሱም ሰው የለም::
ጀግና ነኝ እያለ በመግደል ያበጠው:-
የትግል ጓዶቹን ገድሎ ያሟጠጠው:-
መለስ ዜናዊ ነው ተንኮል የመለጠው::
ዛሬም በሕዝብ ደም የሚበጠብጠው:-
በኮዳ ቀዳዳ ኢሣት ያጋለጠው::
ጥይት በስቶት ሲያፈስ
አስቛል ጦር ሜዳ:-
በመለስ ማንነት
መስክሯል ይህ ኮዳ::
ውሸትም ከሆነ ከኢሣት አጣሩ:-
አብረው የተዋጉት አለ ምሥክሩ::
ዛሬም በሕዝብ ደም
የሚበጠብጠው:-
መለስ ዜናዊ ነው
ኮዳ ው ያጋለጠው::