መግቢያ በጄኔራል ከማል ገልቹ የሚመራዉ ኦነግ «ኦሮሞ የኢትዮጵያ ግንድ ነዉ። ቅርንጫፍ ከግንድ ይገነጠላል እንጂ ግንድ ከቅርጫፍ አይገነጠልም» በሚል፣ የኢትዮጵያን አንድነት ተቀብሎ፣ ለኦሮሞ ባህልና ቋንቋ መስፋፋት፣ ለዜጎች ሁሉ መብት መከበር፣ ከተቀረዉ ኢትዮጵያዊ ወንድሙ ጎን በመቆም ትግሉን እንደሚቀጥል ይፋ አድርጓል። ይህ ከኦነግ ዘንድ ይፋ የተደረገዉ የፖለቲካ አቋም ለዉጥ ፣ ኦሮሞ ነን የሚሉትን ጨመሮ በበርካታ ኢትዮጵያዉያን ዘንድ ከፍተኛ […]

አፍሪቃውያን በአረቦች እየተፈነገሉ ለነጮች ተሽጠው ባህር ሲሻገሩ ንብረታቸውም ወደ አውሮፓና አሜሪካ ሲጋዝ ብዙ ምዕተ ዓመታት እንዳስቆጠሩና ከሃያ ሚልዮን ያላነሱ አፍሪቃውያን በዓለም ዙሪያ እንደተበተኑ ታሪክ ዘግቦአል፡፡ እነዚህኑ አፍሪቃውያን ባህር ማዶ ለማሸጋገር፣ በመርከብ ውስጥ ከታጨቁበት ቀን አንስቶ የተለያዩ ግብታዊ አመጽ ቢያካሄዱም ወደ ካሬ ቢያን የተጋዙት ባሮች እንዲሁም ዘግይተው ነፃ የወጡት ተሳብስበው በ18ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ መላው ጥቁር […]

ሲሞላልኝ በሳምንት ካልሆነልኝ ደግሞ በአስራ አምስቱ ሰላምታዬን ካሉበት የማደርሳቸው ወዳጆች አሉኝ። ለአገር ምድሩ ሳይሆን በጣት የሚቆጠሩ። ከእነዚህ መካከል አንዱ የሙያ ባልደረባዬ ኤልያስ ወንድሙ ነው። ትውውቃችን የመንገድ ላይ አይደለም። የኔዎቹ የነፃ ፕሬስ አባላትና የሃገሬ ሰላም ወዳድ ኃይሎች በግፈኞቹ የሕወሃት አባላትና ሹመኞች የሚሰደዱበት የሚታሰሩበት ብሎም የግፍ ፅዋ የሚቃመሱበት በእነዚያ የትግል፣ የፈተናና የፍልምያ ዓመታት የልብ ወዳጅና ለእውነት የቆሙ […]

– መድረክ የአደባባይ ስብሰባ እጠራለሁ እያለ ነው አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ባለፈው እሑድ የሊዝ አዋጅን ለመቃወም የጠራው ስብሰባ ሳይካሄድ ቀረ፡፡ ነገር ግን ይኼንኑ ስብሰባ የፊታችን እሑድ ለማካሄድ ዕቅድ ይዟል፡፡ ፓርቲው አዲሱ የሊዝ አዋጅ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ በሚመለከት ከምሁራን ጋር ለመምከር በእየሩሳሌም ሆቴል ስብሰባ መጥራቱ ይታወሳል፡፡ ይህንን ስብሰባ ለማካሄድ የፓርቲው መሪዎችና ምሁራን በማለዳ በሆቴሉ ቢደርሱም፣ የሆቴሉ […]

የፍትህ ጋዜጣ አገር ዉስጥ የምትታተም ነጻ ጋዜጣ ናት። የፍትህ ጋዜጣ አምደኛ ርዮት አለሙ ፣ የፍትህ ጋዜጣ ዘጋቢ ሂሩት ክፍሌ፣ ለአሥራ አራት እና ለአሥራ ዘጠኝ አመታት ኢሰብዓዊና ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ መሰረተ ቢስ በሆነ የሽብር ተግባር ተሰማርታችኋል በሚል በቃሊቲ እሥር ቤት እየተሰቃዩ ነዉ። ከነዚህ ጀግና ወገኖቻችን ጎን እንቁም። የፍትህ ጋዜጣን እንዲሁም በጽሁፍን እና ንግግር የሚደረግን ሰላማዊ […]

የአለም አቀፍ ግንኙነት ፖለቲካን የሚያጠኑ ምሁራን በሁለት ሀገራት መካከል ስለሚኖር ግንኙነት ሲገልፁ እንዲህ ይላሉ ‹‹በአለም አቀፍ መድረክ ዘላቂ ወዳጅም ይሁን ዘላቂ ጠላት የለም›› ፡፡ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በአንድ የታሪክ አጋጣሚ በተመሳሳይ ስም በአንድ ገዢ የሚተዳደሩ አንድ ወጥ በሆነ የፖለቲካ ስርዓት ማዕቀፍ ውስጥ የነበሩ ወንድምና እህታማች አገራት ነበሩ፡፡ አሁንም በአንድ የታሪክ አጋጣሚ አንዱ ራሱን ቅኝ ተገዢ ሌላው […]

ከመቼውም ጊዜ በላይ ከአገሪቱ አነጋጋሪ ጉዳዮች በላይ የሊዝ አዋጁ አወዛጋቢነት ተፋፍሞ በቀጠለበት ወቅት፣ የኢሕአዴግ ዋነኛው ተቀናቃኝ ነኝ የሚለው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ፣ በሳምንቱ መገባደጃ ላይ በአዋጁ ላይ ጠንከር ያለ ተቃውሞ ይዞ ቀርቧል፡፡ አዋጁን የሚቃወም ሕዝባዊ ስብሰባ ለመጥራት ማቀዱን አስታውቋል፡፡ መድረክ ባለፈው ሐሙስ በጽሕፈት ቤቱ አዋጁን በፅኑ የሚቃወም መግለጫ ሰጥቷል፡፡ ከዚህ የተቃውሞ መግለጫ በተጨማሪ በትልቅ […]

በዛሬይቱ ኢትዮጵያ የህግ የበላይነት እንዲከበር፤ ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር እና በዲሞክራሲያዊ ስርኣት ዉስጥ ዜጎች በእኩልነት ሰብኣዊ መብታቸዉ ተጠብቆ እንዲኖሩ የሚያስቡ፡ የሚናገሩ፤ የሚፅፉና የሚቆረቆሩ በጠቅላላዉ ለነዚህ ፅንሰ ሃሳቦች ዘብ የሚቆሙ በሙሉ የስርኣቱ ጠላቶች ተደርገዉ በመቆጠር ላይ ናቸዉ። ለአገሪቱ አንድነትና ሉኣላዊነት፤ እድገትና ብልፅግና በጣት ከሚቆጠሩ መሪዎቿና የፓርቲያቸዉ ጠባብ ጎሰኛ ፖሊሲ የተለየ የሚያስቡ ዜጎችና ቡድኖች ሁሉ “የስርዓቱ ጠላት” እና […]

በአገር ቤት የሚንቀሳቀሱ ጋዜጠኖች ላይ አምባገነኑን የመለስ አገዛዝ እየወሰደ ያለዉን አሳፋሪ ድርጊት አስመልክቶ፣ በዉጭ አገር የሚገኘዉ የነጻዉ ፕሬስ ማህበር፣ ኢትዮጵያዉያን ከታሰሩ ጋዜጠኖች ጎን እንዲቆሙ፣ «በጠመንጃ አስገዳጅነት የእዉነት እጆች ቢታሰሩም. ህዝብ እዉነታዉን ይረዳ፣ ታሪክም ሃቅ ይፈርዳል» በሚል አርእስትብ ሥር ባወጣዉ መግለጫ፣ ጥሪ አቀረበ። «እነ እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ እና ርዕዮት አለሙ በሃሰት ክስ “አሸባሪ” ተብለው ለእስር […]

በአንድ አገር ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች የባለአገርነት ስሜት እንዲኖራቸው የሚወጡ አዋጆች መመሪያዎችና ድንጋጌዎች ሁሉ አብዛኛውን የሕብረተሰብ ክፍል ስምምነት ያገኘ መሆን ይኖርበታል፡፡ መንግሥት ሕዝቡ የሚተዳደርበትን የትኛውንም አይነት ሕግ ሲያወጣ ማዕከል ማድረግ ያለበት የዜግነት መብትን ለማስጠበቅ ለማጎናጸፍ እንጂ አንገት የሚያስደፋ የሚያሸማቅቅ የሚያስፈራራ አፋኝና ባጠቃላይ በመብት ገፈፋ ላይ የተመረኮዙ መሆን አይኖርበትም፡፡ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 […]

«ፍርድን ፈልጉ፣ የተገፋውን አድኑ፣ ለድሃ አደጉ ፍረዱለት፣ ስለመበለቲቱ ተሟገቱ» ኢሳያስ 1፡ 17 በአዲስ አበባ ከተማ ነበር የተወለዱት። ገና የሶስት አመት ሕጻን የነበሩ ጊዜ ቤተሰባቸዉ ወደ ድሬዳዋ ይዞራሉ። ፋሺስት ጣሊያን አገራችንን ሲወር፣ የስምንት አመት ልጅ ነበሩ። በግራዚያኒ ላይ ቦምብ ከተወረወረ በኋላ፣ ጣሊያኖች በፈጸሙት የብዙ መቶ ሺህ ዜጎች ጭፍጨፋ፣ የእኝህ ሰው አባት ተገደሉ። እናታቸው ብዙ ሳይቆዩ አረፉ። […]

«ፍርድን ፈልጉ፣ የተገፋውን አድኑ፣ ለድሃ አደጉ ፍረዱለት፣ ስለመበለቲቱ ተሟገቱ» ኢሳያስ 1፡ 17 በአዲስ አበባ ከተማ ነበር የተወለዱት። ገና የሶስት አመት ሕጻን የነበሩ ጊዜ ቤተሰባቸዉ ወደ ድሬዳዋ ይዞራሉ። ፋሺስት ጣሊያን አገራችንን ሲወር፣ የስምንት አመት ልጅ ነበሩ። በግራዚያኒ ላይ ቦምብ ከተወረወረ በኋላ፣ ጣሊያኖች በፈጸሙት የብዙ መቶ ሺህ ዜጎች ጭፍጨፋ፣ የእኝህ ሰው አባት ተገደሉ። እናታቸው ብዙ ሳይቆዩ አረፉ። […]

በሽብር ሥራ ተሰማርታቿል በሚል ክስ በታሰሩት የፍትህ እና የአዉራምባ ታይምስ ጋዜጠኞች ርዮት አለሙ፣ ሂሩት ክፍሌ፣ ዉብሸት ታዬ እንዲሁም የብሄራዊ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ፕሬዘዳንት የሆኑት አቶ ዘሪሁን ገብረ እግዚአብሄር ላይ፣ የመለስ አገዛዝ በሚቆጣጠረዉ ፍርድ ቤት በኩል የቅጣት ዉሳኔ እንዳሳለፈ፣ ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ያመልክታል። እንደ ደረሰን ዘገባ መሰረት ሂሩ ክፍሌ ለአሥራ ዘጠኝ አመታት፣ አቶ ዘሪሁን ለአሥራ ሰባት […]

በጋምቤላ የፉኝዶ ወረዳ የአንድ አባ ወራ አህያ ወደ ጎረቤቱ ዘልቆ አንዲት የሌላ አባወራ ንብረት የሆነች ሴት አህያ ላይ ይንጠላጠልና የልቡን ያደርሳል። የሴቷ አህያ ባለቤትም አህያዬ “ተደፈረችብኝ” በሚል ክስ ይመሰርታሉ። የወንዱ አህያ /ደፋሪው መሆኑ ነው/ ባለቤት ፖሊስ ዘንድ ይወሰዳሉ ክስ ይመሰረትባቸውና ይቀጣሉ። የወረዳው የፍትህ አካላት ጠርተውን የክሱንና የፍርዱን ሂደት አስረዱን። እኛም በተነገረን መሰረት ዜና ሰራን። ኃላፊው […]

የዘጠኝ ዓመት ልጅ ነው። አንድ ቀን አባቱን ጠየቀው፤ ” አባባ ፖለቲካ ምንድነው?” “ ጥሩ ጥያቄ ነው ልጄ! ቁጭ በል በምሳሌ አስረዳሀለሁ። “ ይልና አባት ልጁን ካስቀመጠ በሗላ ‘’ፖለቲካ ማለት እንግዲህ ይህን ቤታችንን እንደ ሀገር ቁጠረው። ቤታችን ሀገር ማለት ነው። በቤታችን ውስጥ ስራ እየሰራሁ ገንዘብ የማመጣ እኔ ነኝ። እኔን እንደ ካፒታሊዝም ቁጠረኝ። እኔ ካፒታሊዝም እባላለሁ። እናትህ […]

የኢትዮጵያ የውጭ ብድር ክምችት በከፍተኛ እያሻቀበ በመሄድ ላይ ሲሆን፣ ባለፈው ዓመት የነበረው 134 ቢሊዮን ብር ወደ 200 ቢሊዮን ብር ማደጉን መረጃዎችና የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባለሙያዎች አመለከቱ፡፡ የመንግሥት የአገር ውስጥ ዕዳም ከ60 ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር መገባደጃ ላይ የአገሪቱ የውጭ ዕዳ በወቅቱ በነበረው ምንዛሪ 134 ቢሊዮን ብር መድረሱን መረጃዎቹ አመልክተው፣ […]

ሩሲያውያን እስከዛሬ ያሳለፏቸውን የምርጫ ሂደቶች አስመልክቶ ተንታኞቹ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በስልጣን ላይ ያለው ፓርቲ ከምርጫው ሁነት በፊት የገነቧቸውን መሰረታዊ አደረጃጀቶች ሳይጠቅሱ አያልፉም፡፡ በሀገሪቱ ምርጫ ፖለቲካ ላይ ጥናት ያደረጉ ምሁራን የሀገሪቷን የፖለቲካ መሪዎች በምርጫ ላይ ያላቸውን አቋም ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ ‹‹የምርጫዎቹ ውጤት የሚወስነው ለመፎካከር በሚቀርቡ አሳማኝ አጀንዳዎች ሳይሆን በመሰረትከው የኃይል ሚዛን ነው››፡፡ የኃይል ሚዛኑን ከምርጫው በፊት […]

የዘንድሮ የልደት በአል ከወትሮው ለየት ያለ ነበር ፡፡ ገፀ በረከትም ነበረው፣ ያውም ሁለት ፡፡ በረከት ስምኦንና ሌተና ኮሎኔል መንግስቱ ያቀረቡልን ሰጦታ ፡፡ ስጦታዎቹንም ከከፈትሁ በሁዋላ እኔም ስለሁለቱ አምባዎች ወግ ላወጋችሁ አሰብኩ ፡፡ አንዱ አምባ የኢህአዴግ መሆኑ ነው ሌላው ደግሞ የደርግ ፡፡ አምባ ላይ የሚሸልል ደግሞ አምባገነን ነው ፡፡ እናንተዬ ይህን ቃል የፈጠረ መንዜ የኖቤል ሽልማት […]

ሐሙስ ጥር 10 ቀን 2004 ዓ.ም፡- የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት መንግሥት በነኤልያስ ክፍሌ የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት ወንጀል በከሰሳቸው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፣ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ዘሪሁን ገብረእግዚአብሔር እና ወ/ሮ ሂሩት ክፍሌ ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ አሳለፈ፡፡ የቅጣትውሳኔ ለማስተላለፍ ለጥር 17 ቀን 2004 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡ […]

ለበርካታ አመታት ኢትዮጵያዉያንን ሲያሰባሰብ የነበረዉ የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያዉያን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለሁለት ተክፈለ። ከሼክ አላሙዲ ጋር ግንኙነት ባላቸዉ ጥቂት ግለሰቦች ችግር ላይ የወደቀዉ ይህ ፌዴሬሽን፣ ያለፈዉ አመት ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን በክብር እንግድነት በመጋበዙ ዙሪያ በዉስጡ በተፈጠረዉ አለመግባባት፣ ትልግ ዉዝግብ ዉስጥ ገብቶ እንደነበረ ይታወቃል። በከፍተኛ የሕዝብ ግፊት ወ/.ት ብርቱካን አትላንታ በተደረገዉ የፌዴሬሽኑ ዝግጅት ላይ ንግግር እንዳደረጉም […]

የፌደራሉ አቃቤ ሕግ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር በሆኑት በአቶ በቀለ ገርባ የክስ መዝገብ ቁጥር 113633 በ9 ሰዎች ላይ 3 ክሶችን መስርቶ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ሰኞ ታህሳስ 30 ቀን 2004 ዓ.ም ክሳቸው ተሰምቷል፡፡ ይህ የክስ ጭብጥ ተጠርጣሪዎቹ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አሸባሪ ተብሎ ከተሰየመው ኦነግ ጋር ተባብረዋል፣ ሰዎችን አደራጅተዋል፣በድርጅቱ ኬንያ ሄደው ሥልጠና ወስደዋል የሚል […]

ጥቆማዬም መንግስት አዲስ የጡረታ አዋጅ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ በዚህም የተነሣ የግል ድርጅቶች ጡረታ እንዲከፍሉ እየተደረገ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በግል ድርጅቶች ውስጥ 15,16 አመት የሰሩ ሰራተኞች አሉ፡፡ በድርጅቱ በኩል የአገልግሎት እየተቆረጠ ሲጠራቀምላቸው ነበር፡፡ ገንዘቡም በርካታ ነው፡፡ የተማረ የሰው ሀይል ያለባቸው ድርጅቶች ለምሳሌ፡- የግል ትምህርት ቤቶች ሆስፒታሎች ወዘተ የመሳሰሉት ሰራተኞችን በመወያየት ሰራተኛው ይሄ ገንዘብ ይመለስልን በማለቱ ገንዘቡ […]

ባለፈው ሳምንት ሰማያዊ የተባለ አዲስ ፓርቲ የምሥረታ ጉባኤውን ሲያካሂድ በአብዛኛው አባላት ከአንድነት ፓርቲ ጋር በታክቲክም ሆነ በስትራቴጂ አብረው ሊሠሩ ያልቻሉ፤ ሆኖም ግን ለሃገርም ሆነ ለዴሞክራሲያዊ ግንባታ አስተዋፅኦ እናደርጋለን ያሉ ኃይሎች ፓርቲ መሠረቱ፡፡ በፓርቲ ምስረታቸውም ዕለት የአንድነት ፓርቲ በእንግድነት እንዲገኝላቸው ጥሪ አደረጉ፡፡ አንድነት ፓርቲ ጥሪያቸውን በማክበር አጀንዳ ይዞ ውይይት ካደረገ በኋላ የፓርቲው ሊቀመንበር የተከበሩ ዶ/ር ነጋሶ […]

ሀገራችን ኢትዮጵያ ረጅም የመንግስትና የፖለቲካ ታሪክ ካላቸው ሀገሮች ተርታ የምትመደብ ናት፡፡ ይችው እድሜ ጠገብ ውድ ሀገራችን መንግስት በማቋቋም፣ በስልጣኔ በንግድና ሉዓላዊነቷን በመጠበቅ ፈር ቀዳጅ ከሆኑ ጥንታዊ ሀገሮች የምትመደብ ቢሆንም ቀዳሚነቷን አስጠብቃ መጓዝ ግን አልቻለችም፡፡ ኢትዮጵያችን በድህነትና በኋላቀርነት፣ እንዲሁም በበሽታና በእርዛት መታወቅ መቻሏ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ በቁጭት የሚያንገበግብ፤ የእኛ ባህሪ የሆነውን አይነኬነት የሚፈትንና እልህ የሚያስይዝ ጉዳይ ነው፡፡ […]

ለቀምት ከተማ በሚገኘው የወለጋ ዩኒቨርስቲ በተፈጠረ ግጭት ሁለት የሕግ ተማሪዎች ሞተው ከትላንት በስቲያ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው መፈፀሙን የዜና ምንጮቻችን ለዝግጅት ክፍላችን አስታወቁ፡፡ አንድ የውስጥ አዋቂ እደሚሉት ከሆነ ደግሞ “ተማሪዎቹ የሞቱት በምግብ መመረዝ ነው” ይላሉ፡፡ የዜና ምንጮቻችን እንደሚሉት ሲራጅና ከማል የተባሉ ሁለቱ የሕግ ተማሪዎች መሞታቸውንና ከትላንት በስቲያ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው የተፈፀመ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ጉዳዩን ለማጣራት […]

[email protected] ዶር ብርሃኑ ነጋ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ዙሪያ ለአንባቢያ ያቀረብኳቸው ሁለት መጣጥፍት ከፍተኛ የአንባቢያን አስተያየቶችን እንደጫሩ ለማየት ችያለሁ። የድጋፍም ሆነ የተቃዉሞ ኤሜሎች በብዛት የደረሱኝ ሲሆን፣ በአቡጊዳ ድህረ ገጽ ላይ የቀረቡ አሰትያየቶች ከወትሮ እጅግ የበዙ ነበሩ ። በጽሑፌ ቅር የተሰኙ ፣ ለምን ቅር እንደተሰኙ በአግባቡ ለመግለጽ ያልቻሉ፣ ያቀረብኳቸዉን ነጥቦች ትክክል እንዳልሆኑ ለማሳመን የራሳቸዉን መከራከሪያ […]

መግቢያ፥ ይህ አዲስ ዘመን፣ ያሳለፍነው የ‘አጥፍቶ-ልማት ጥፋት ዘመን’ ፍጻሜ ማግስት ነው ብለን ማመን ይገባል። ሁለንተናችን በምንላት እናት አገራችን ውስጥም ሆነ በውጭ ያለው ወገን፣ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ከገዢውና አገልጋዩ በስተቀር ያልተጎዳ ሰው አለ ማለት ክህደት ይሆናል። ወያኔ ከፈለቀበት ምድርም ቢሆን የከፋ ዕልቂት የፈጸመ መሆኑ ለታሪክ በተረፉት ሰዎች አፍ እየተነገረ ሲሆን፣ በየሸለቆውና ሜዳው ያለው እጽም ደግሞ […]