ወያኔ ኢህአዴግ : — · ዋልድባ ገዳምን ጨምሮ በሁሉም የእምነት ተቋማት ላይ እያካሄደ ያለውን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ፣ · የሽብርተኝነት ታርጋ እየለጠፈ በንጹሐን ዜጎች ላይ የሚያካሄደውን አፈናና የመብት ረገጣ በመቃወም ፣ · የዜጎችን ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብት በመገደብ በሕዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን መፈናቀል በመቃወም ፣ · በኢንቨስትመንት ስም በውጭ ባለሀብቶች አማካይነት እየተካሄደ ያለውን የመሬት ቅርምትና […]

ይህ ጦማር የተጻፈበት ዕለት 14/8/2004ዓ.ም፡፡ ‹ኢትዮፒካሊንክ› በሚሰኝ አዝናኝ ፕሮግራሙ ይበልጥ የሚታወቅ ኤፌ’ም 98.1 እሚባል ሬዲዮ አለ – አዲስ አበባ፡፡ በሬዲዮ ፋና ሥር በፕሮፓጋንዳው ግምባር ተኮልኩለው በወያኔው በሬ ወለደ ቱሪናፋና በግድባዊው ዘመነኛ ፈሊጥ የላም አለኝ በሰማይ ቀቢፀ ተስፋ ሕዝቡን እያደነዘዙ የኢሕአዲግን ዕድሜ ለመቀጠል ሌት ከቀን ከሚባዝኑ ኃይሎች ጎን ስለሚመደብ ባለቤትነቱ ሙሉ በሙሉ የወያኔ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ የዚህን […]

ይድረስ ላስጠራዥ – መለስ ዜናዊ ከተጠራዥ ስደተኛ – ዳዊት አበበ / ኦስሎ ኖርዌይ በሽተኛ – የማስታወስ ችሎታዬ ከጠፋ ሰነባብቷል ፣አንዳንድ ጊዜ በመንገድ ላይ ሆኘ ሳለሁ ከቤቴ ተነስቼ ወደ ቢሮዬ መሄዴን ? ፣ ወይ ደግሞ ከቢሮዬ ወጥቼ ወደ ቤቴ መመለሴን እስከማላውቅበት ድረስ ይምታታብኛል መድሃኒቱ ምንድነው ብሎ ይጠይቃል ዝንጉው- ህመምተኛ ሳይካትሪስቱን ፡፡ ሳይካትሪስቱ – በእንደዚህ ባለ ሁኔታ […]

ማንኛውም የኪነጥበብ ስራ ለህዝብ ሲቀርብ ከባለሙያም ሂስ ፣ ከታዳሚ ደግሞ አስተያየት መሰጠቱ የሚጠበቅ ነው። ሆኖም ግን የግለሰቦች አስተያየት ፣ ከአስተያየትነት አልፎ ሄዶ ፣ ተጠባቢውን በመናቅ የጥበብ ስራውን አፍርሶ እንዲሰራ ለመጠቆም መሞከር ፣ እጅግ ከጥበብ አለም ከራቀ ሰው ብቻ የሚደረግ ድፈረት ይመሰለኛል። “የቴዲ አፍሮ “ጥቁር ሰው” እና ጥቂት የተዛቡ የታሪክ እውነቶች” በሚል አርዕስት ስር የቀረበውን መጣጥፍ […]

“ታጠቅ ህሉፍ የተባለ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ሰራተኛ በደረሰበት አስተዳደራዊ በደል በሰውነቱ ላይ ነዳጅ አርከፍክፎ በደብረ ማርቆስ ከተማ ውስጥ ራሱን አቃጥሎ መሞቱን” የዓይን እማኞች ለዝግጅት ክፍላችን አስታወቁ፡፡ የአካባቢ ነዋሪዎች እንደሚሉት “በደብረማርቆስ ከተማ ልዩ ቦታው አብማ 04 ቀበሌ በአቶ ጫኔ ቤት ውስጥ ተከራይቶ ይኖር የነበረው ታጠቅ ህሉፍ ራሱን አቃጥሎ ገሏል” ብለዋል፡፡ በአካባቢው የነበሩ የዓይን ምስክሮች እንደሚሉት “ታጠቅ ህሉፍ […]

ኢትዮጵያዊ ተዋዶ፣ ተዋልዶና ተዛምዶ ኖሯል ለዘላለምም ይኖራል! እንዳትሰደድ የሚለውን የወዳጅ ዘመድ ምክር ችላ ብለህ ብትሰደድ ከሁሉ በላይ ሕውሓትን አስደስተህ አንተም ይብዛም ይነስም ችግር ውስጥ ለመባዘን ተዘጋጅ። ከዲያስፖራው ወገን ጋዜጠኛ ወይ ባለጠጋ ካልሆንክ ስለተሰደድክ እምቢልታ አይነፋልህም፣ ነጋሪት አይጎሰምልህም። በስደትህ ምክንያት ስለአገርህ የዲሞክራሲና የነፃነት ዝቅጠት አይነገርም፣ አይወራም ወይም አይፃፍም። እንደዘበት በአንድ ውድቅት ሻንጣህን አንጠልጥለህ ትወጣለህ። ባንተ መሰደድ […]

ያቺን የማትረሳ ቆንጆ ልጅ የተዋወቅሁዋት አስመራ ላይ ሲሆን፣ ከካቴድሪያል ወደ ቲራቮሎ በሚጓዘው ታክሲ ላይ ተሳፍሬ ነበር። ልጅቱ ፒኮክ የተባለችውን ወፍ ነበር የምትመስለው። ታክሲው ላይ ከሁዋላ አብረን ነበር የተቀመጥነው። “ላናግራት ወይስ ይቅርብኝ?” እያልኩ ሁለት ልብ ሆኜ እያመነታሁ ቆየሁ። እኔ ደጋግሜ ባያትም፣ እሷ አንድ ጊዜ እንኳ ዘወር ብላ አላየችኝም። ከሞባይል ቴሌፎኗ ጋር ተመስጣ እየተጫወተች ነበር። (መቸም እንዲህ […]

የጋምቤላ ልዩ ኃይል አመራር መኮንንና አንድ የፖሊስ አባል መገደል እንዲሁም ንብረትነቱ የሼክ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ የሆነው ሳዑዲ ስታር እርሻ ልማት ኩባንያ የፋይናንስ ኃላፊና ሾፌራቸው መቁሰላቸውን ተከትሎ በጋምቤላ ጥበቃና ቁጥጥር መጠናከሩ ተሰማ። የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ምንጮች ከስፍራው በላኩት መረጃ እንዳስታወቁት ግድያውን ያከናወኑት የዛሬ ስምንት ዓመት ገደማ በአኙዋክ ንጹሃን ላይ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት አስቆጥቷቸው የሸፈቱ […]

የምድር ፈራጅ ሆይ ከፍ ከፍ በል፤ ለትዕቢተኞች ፍዳቸውን ክፈላቸው። አቤቱ ህዝብህን አዋረዱ፤ ርስትህንም አስቸገሩ። መዝሙረ ዳዊት 93/4 ቁ 2-5 በ1993 ዓ.ም በዋናው መሥሪያ ቤት “ትልቅ” ብለው የጠሩት ሥብሰባ ይካሄዳል በመባሉ አምባሳደሮች ከያሉበት አዲስ አበባ ገስግሰው ደርሰዋል።ወጪያቸውም በሙሉ በመሥሪያ ቤቱ ይሸፈናል በመባሉም ደስታቸው ልክ አጥቷል።በዋናው መሥሪያ ቤት ውስጥም ከሶስተኛ ጸሃፊ በላይ ያሉ ብቻ በስብሰባው እንዲሳተፍ ማስተወቂያ […]

አሁን ሰሞኑን በህዝቦች መካከል እየደመቀ የመጣው የመተባበር እና አብሮ የመስራት መልካም ፍላጎት ጥቂቶችን እያሸበረ ነው።መለስ ዜናዊና ግብረ አበሮቹስ በብሄሮች መካከል የገነቡት የጠብ ግድግዳ ሲናድ አይተው ብዙ ቢጮኹ የቆሙበት መሠረታቸው ቀስ በቀስ እየተናደ በመሆኑ ተሸበርን ቢሉ እውነት ስላላቸው አይገርምም።የሚገርመው ግን “መለስ ዜናዊ የገነባው የጭቆና መረብ መበጣጠስ አለበት ብለን” ተነስተናል ብለው ሲያበቁ እየደመቀ የመጣውን የትግል አንድነት ጥሪ […]

ከአምስት ቀናት በፊት በቃሊት እሥር ቤት ሃላፊዎች ቤት ትእዛዝ፣ በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አንዱዋለም አራጌ ላይ፣ ጭካኔ የተሞላበት ድብደባ የፈጸመዉ ኢብሳ አስፋዉ የተባለ ግለሰብ፣ ሶስት መቶ እስረኞች በሚገኙበት የቃሊት እሥር ቤት ዞን እንደተሸጋገረ ፣ ከአዲስ አበባ የደረሰን ዜና ያመለክታል። ከነዚህ ሶስት መቶ ሰዎች መካከል፣ መሰረት በሌለዉ የሽብር ተግባር የተከሰሰዉ፣ ሌላዉ የአንድነት ፓርቲ […]

ከአምስት ቀናት በፊት በቃሊት እሥር ቤት ሃላፊዎች ቤት ትእዛዝ፣ በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አንዱዋለም አራጌ ላይ፣ ጭካኔ የተሞላበት ድብደባ የፈጸመዉ ኢብሳ አስፋዉ የተባለ ግለሰብ፣ ሶስት መቶ እስረኞች በሚገኙበት የቃሊት እሥር ቤት ዞን እንደተሸጋገረ ፣ ከአዲስ አበባ የደረሰን ዜና ያመለክታል። ከነዚህ ሶስት መቶ ሰዎች መካከል፣ መሰረት በሌለዉ የሽብር ተግባር የተከሰሰዉ፣ ሌላዉ የአንድነት ፓርቲ […]

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ምክትል ፕሬዘዳንት፣ አቶ አንዱዋለም አራጌ በእሥር ቤት ፣ ከእሥር ቤት ሃላፊዎች በተላከ ሌላ እስረኛ እጅ፣ ከፍተኛ ድብደባ እንደደረሰባቸው ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል። አቶ አንዱዋለም የተደበደቡት ከትላንትና ወዲያ እሮብ ቀን ሲሆን ፣ ጉዳዩን ለመከታተልና አቶ አንዱዋለም ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ፣ ዛሬ ጠዋት ወደ እሥር ቤት የሄዱት የአቶ አንዱዋለም ቤተሰቦችና የአቶ አድንዋለም ጠበቃ፣ […]

ሳቂታ ውብ ጥርሶችና ታማኝ አይኖች ያሏት ሸዋረጋ የምትባል አንዲት ልጅ ነበረች። ነዋሪነቷ ወሎ ላይ ነበር። ገና የስምንት አመት ህፃን ሳለች ወላጅ እናቷ ስለሞተችባት ለአንዲት አሮጊት በግርድና ለማገልገል ተቀጠረች። ይህች እድለቢስ ልጅ አባቷን አታውቀውም። እንጀራ ጋጋሪ ከነበረች ወላጅ እናቷ የተገኘ ውርስም አልነበራትም። አሮጊቷ በበቅሎ ሲጓዙ፣ እየተከተለች ከበቅሎዋ እኩል መስገር ዋና ስራዋ ሆነ። ምሽት ላይ የአሮጊቷን እግር […]

በቅርብ ዓመታት ውስጥ በአገራችን የሚገኙ የመገናኛ ብዙኃን፣ ጋዜጦችና መጽሔቶች እንዲሁም የመዝናኛ ስፍራዎች ‹‹የቫለንታይን ቀን›› ወይም በሀገሪኛው አገላለፅ ‹‹የፍቅረኞች ቀንን›› በተመለከተ እለቱን በሚያዘክሩ የተለያዩ ዝግጅቶችና የሙዚቃ ድግሶችን በማዘጋጀት ፍቅረኞች እለቱን በደስታና በሐሴት እንዲያከብሩት ሽር ጉድ የሚሉበትን ሁኔታ እየታዘብን ነው፡፡ ይህ እለትም ለአበባ ሻጮች፣ ለስጦታ ዕቃ መሸጫ ሱቆችና መዝናኛ ስፍራዎች ሞቅ ያለ ገቢ የሚያገኙበት የሞቀና የደራ የገበያ […]

[email protected] የጦርነት ነጋሪት እየሰማን ነዉ። ገዢዉን ፓርቲ የሚደግፉ በሰሜን አሜሪካ የሚገኘዉ የትግራይ ተወላጆች ማህበር አባላት፣ እንደ አይጋ ፎረም ያሉ ድህረ ገጾች፣ ሕወሃት/ኢሕአዴግ በኤርትራ ላይ ጦርነት እንዲከፍት ከፍተኛ ግፊት እያደረጉ ነዉ። እነዚህ ወገኖች ከኤርትራ ጋር ጦርነት ቢከፈት በቀላሉ አስመራ መግባት የሚቻል ሳይመስላቸው አይቀርም። ትክክል ሊሆኑ ይችላሉ ። የኤርትራ ጦር ተዳክሟል። ወታደሮቹ መዋጋት አይፈልጉም። በተባበሩት መንግስታት እቀባ […]

የሚበዙት ነገሥቶቻችን በታሪክ ረገድ የተፃፈላቸው የጦርነትና የግዛት ማስፋፋት ታሪካቸው እንጂ ለእውቀትና ለጥበብ ሥራዎች እንዲሁም ለስነ ጹሁፍ ያላቸውን ልዩ ዝንባሌና ትኩረት የታሪክ ጸሐፍቶቻችን እምብዛም ትኩረት የሰጡት አይመስሉም፤ እኛም በዚህ ረገድ ለማወቅም ሆነ ለማጥናት ያለን ፍላጎት እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ ስለዚህም በዚህ ጹሁፍ የኢትዮጵያውያንን ነገሥታት ከስነ ጹሁፍ ጋር የነበራቸውን ትውውቅ፣ መንፈሳዊ መጻሕፍትን ለመመርመር የነበራቸውን ብርቱ ፍላጎትና ጥረት […]

በተወካዮች ም/ቤት ብቸኛው የተቀዋሚ ፓርቲ አባልና የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ም/ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ ጠ/ሚኒስትሩ ሰሞኑን በፓርላማ በሰጡት መግለጫ ዙሪያና በሌሎች ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ከአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ሰላም ገረመው ጋር ቃለምልልስ አድርገዋል፡፡ ህገ መንግስቱን በተደጋጋሚ የምትጠቅሱት ስለምታምኑበት ሳይሆን እንደ ሁኔታው ልትጠቀሙበት ስለምትፈልጉ ብቻ ነው ሲሉ ጠ/ሚኒስትሩ ተችተዋችኋል…ህገመንግስቱን የምንጠቅሰው ስለሚጠቅመን ነው፡፡ ለምሳሌ እኔ ህገመንግስቱ ቤቴ፣ ቢሮዬ፣ […]

አቶ መለስ ዜናዊ ሰሞኑን ለፓርላማቸው የበጀት ዓመቱን የስድስት ወራት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ማቅረባቸውን ተከትሎ፤ከብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ ከአቶ ግርማ ሰይፉ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጧቸውን “መልሶች” አዳመጥኩ።አውቀውም ይሁን ሳያውቁት ፤በብዙዎቹ ነጥቦች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ግርማን ሊያገኟቸው አልቻሉም። አቶ ግርማ ፦”ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እንደምን አደሩ?” ሲሏቸው፤ አቶ መለስ፦”ተልባ እየዘራሁ ነው” ሲሉ ነው የተስተዋሉት።ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ፦”ክቡርነትዎ! ከፍየልና […]

አቶ መለስ ዜናዊ በሚቆጣጠሩት ፓርላማ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ወቅት፣ በኤርትራ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ ገለጻ አቀረቡ። የኢትዮጵያ ሕዝብ እና የኤርትራ ህዝብ ወንድማማች ሕዝቦች እንደሆኑ የገለጹት አቶ መለስ ያላቸው ጠብ በስልጣን ላይ ካለዉ ቡድን ጋር እንደሆነም አስረድተዋል። የኤርትራ መንግስት አካባቢዉን የማተራመስ ሥራ እየሰራ እንደሆነ የተናገሩት አቶ መለስ፣ እንደዚያም ሆነ ግን ከአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በማንኛዉም […]

የጋራ ዓላማዎች ምንድናቸው? እውነት የጋራ ግቦች አሉን? ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ፍትሕ ነጻነት እኩልነት ብልጽግና ሁሉም ሰው እመኛለሁ ይላል። ይኼንኑም እውን ለማድረግ በተናጠልና ተበታትኖ ከመልፋት በጋራ ተደራጅቶ የጋራ ዓላማ ሰንቆ መታገል አማራጭ የለውም እያለ ደቂቁም ግዙፍም የፓለቲካ ድርጅት ይሰብካል። ታዲያ ልምዳችን የሚመሰክረው ይኼንኑ ነው? ለመሆኑ የጋራ ዓላማ ምንድ ነው? እንዴትስ ይገነባል? የጋራ ዓላማ ባለቤቶችስ እነማን ናቸው? መጋራትና […]

ይህ ፌደሬሽን በሂውስተንና በዳላስ ሁለት ቡድኖች ተመሰረተ። በቀጣዩ አመት ዳላስ ጨዋታው ሲካሄድ ለመጀመሪያ ጊዜ ሜዳ በመሄድ የታደምሁ ነኝ። ይህ ፌደሬሽን ሲመሰረት ሁሉም እንደሚያስታውሰው ከቀይሽብር አምልጠውና ተርፈው የመጡ ስደተኞችና ትቂት በዚሁ በዳላስና ሄውስተን አካባቢ ለትምህርት መጠው የቀሩ ወገኖች የጀመሩት ነበር። በቀጣይ አመታት ከተለያዩ የሰሜን አሜሪካ ከተሞች የተመሰረቱ ቲሞች ወደፌደሬሽኑ በመቀላቀል እድገት እንዲያገኝ አርገውታል። በየአመቱ በአሜሪካ የነጻነት […]

“እኔ ወንጀል አልፈፀምኩም፡፡ ጥፋተኛም አይደለሁም፡፡ ታሪክ ነፃ ያወጣኛል” አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚሐብሄር “ማስረጃ ባልቀረበበት ክስ ፈርዳችሁብኛል” ጋዜጠኛ ውብሼት ታዬ “ይህ የሰው ፍርድ እንጂ የእግዚሐብሄር ፍርድ አይደለም” ወ/ሮ ሂሩት ክፍሌ ባለፉት 20 ዓመት አገራችን በርካታ ክስተቶችን አስተናግዳለች፡፡ በተለይ በፍ/ቤት ዙሪያ ብዙ አሳዛኝም፤ አስገራሚም የሚባሉ ነገሮች ተፈጽመዋል፡፡ በወቅቱ አንድ ግዙፍና ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲ በመመስረት፣ በህክምና ሞያቸውና በአዲስ አበባ […]

ግሪን ፕሮፌት የተሰኘዉ የግብጽን አቋም በስፋት የሚያንጸባርቀዉ ድህረ ገጽ፣ የአባይን ውሃ አጠቃቀም በተመለከተ ጥናት የሚያደርግ ኮሚቴ እንደሚቋቋም ዘገበ። የኮሚቴው አባላት ሁለት ከሱዳን፣ ሁለት ከግብጽ እና ሁለት ከኢትዮጵያ ሲሆኑ፣ አራት በሶስቱም አገሮች ተቀባይነት ያላቸው ባለሞያዎች እንደሚካተቱበት ድህረ ገጹ ያትታል። ኢትዮጵያ ከሌሎች ስድስት የአባይ ተፋሰስ አገሮች ጋር በመሆን ስምምነት መፈረሟ ይታወሳል። በቅርቡም ደቡብ ሱዳን ከሱዳን ተገንጥላ የራሷን […]

አቶ መለስ ዜናዊና አቶ ኢሳያስ እስከ አሁን ድረስ የቅርብ ወዳጆች እንደሆኑ የሚጠረጥሩ ብዙዎች ናቸዉ። በተለይም በባድመ ጦርነት ወቅት ሙሉ እልባት ያገኝ የነበረዉን የኤርትራ ችግር እንዲራዘም በማድረጉና የአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ስልጣን በማራዘሙ አንጻር አቶ መለስ ዜናዊ ትልቅ ሚና የተጫወቱ ሰዉ መሆናቸዉን የሚረሳ ኢትዮጵያዊ ይኖራል ተብሎ አይታሰብም። በባድመ ግጭት ወቅት አቶ መለስና አቶ ኢሳያስ ችግሩን ለመፍታት በቅርበት […]

ገዢዉ ፓርቲ በአፋር ክልል ተፈጸመ ባለዉ የሽብር ተግባርን አስመልክቶ፣ አፍቃሪ ሕወሃት የሆነዉ የትግራይ ተወላጆች ማህበር በሰሜን አሜሪካ፣ በሰጠዉ መግለጫ የመለስ አገዛዝ እርምጃ እንዲወስድ ጠየቀ። የገዢዉ ፓርቲ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት፣ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታዉ ምክር ቤት በሻእቢያ መንግስት ላይ ተገቢዉን እርምጃ የማይወስድ ከሆነ ኢትዮጵያ እርምጃ እንድምትወስድ መግለጹን ያስታወሰዉ የማህበሩ መግለጫ፣ የተባበሩት መንግስታት ማእቀብ ቢጥልም የሻእቢያን እኩይ […]

ሳር ቅጠል፤ ግማዱ፤ ተፍተለተለና፤ ሽምቀቅ ማተብ ሆነ፤እምነቱ፤ቀረና፤ በላይን ሰቀሉት፤የላቀውን ጀግና፤ ከጠላት ባዳናት፤በአገሩ፤መዲና፤ በግፍ፤ተሰቀለ፤‘እሙን ዋስ’፤ጠፋና፤ ማነቆ አደባባይ፤የትውልድ ገመና፤ ስቅላት ውለታው፤እርግምት ሆነና፤ ብርክ መዳህ ጀመርን ነፃነት፤ልመና፤ ያውም ከባዕድ አገር ተሰፍሮ፤በቁና፤ በላይ እምቢ ብሎ አኛ እጅ ሰጠንና፤ እንጠፋፋለን ‘በአሳር’፤ እንደገና፤ ይድረስ፤ለአገር ዳኛው፤‘ሕዝቡ በደፈና’፤ ዛሬም ‘ክህደታችን’፤አልተፋቀምና፤ ጀግኖች፤እየገብርን፤‘ቃሊቲ፤ ቀጠና’፤ ስንት ‘በላይ’ ሰቅለን እንሰይም ጐዳና፤ ሰንሰለት እንስበር ጸንተን እንቁምና። በዘመነ ንጉሥ፤‘በግርማሜ’፤ሞት፤ […]