ጄ/ል ባጫ ደበሌ በአሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት በ350ሺህ ዶላር ቤት መግዛታቸው ታውቋል። የባጫ ባለቤትና አንድ ልጃቸው እንደሚኖሩበት ሲታወቅ ልጃቸው በተርም ከ20ሺህ ዶላር በላይ እየተከፈለለት እንደሚማር ማወቅ ተችሏል። በከፍተኛ ሙስና ውስጥ ከተዘፈቁ የመከላከያ ከፍተኛ የጦር አዛዦች አንዱ የሆኑት ባጫ ደበሌ በቦሌ ከለንደን ካፌ ፊት ለፊት ባለሁለት ፎቅ ዘመናዊ ቪላ ገንብተው እንደሚያከራዩ ይታወቃል። በኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት ወቅት አሰብን […]

“ ኢትዮጵያዊነት ማለት፤ ኢትዮጵያዊያንን መውደድ፣ ኢትዮጵያን ማፍቀር፤ የኢትዮጵያን መንግሥት በተገቢው መንገድ መደገፍና፤ ይህ መንግሥት የተሳሳተ መንገድ ሲይዝ መቃወም ማለት ነው። በሥልጣን ላይ ያለው ክፍል ፀረ-ኢትዮጵያዊያንና ፀረ-ኢትዮጵያ ሲሆን፤ ያንን ክፍል በማንኛውም መንገድ ማስወገድ፤ የያንዳንዱ ኢትዮጵያዊና የያንዳንዷ ኢትዮጵያዊት፤ ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው። ” አብዛኛዎቻችን በየጊዜው የምናነሳው ጉዳይ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለችበትን የፖለቲካ ሀቅና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን በደል […]

ዘላለም ክብረት 

ወዳጄ ልቤ ከቶ እንደምንድን ነሽ? እውን እኔና አንቺ በአለም ስንኖር ሌላ የመገናኛ ዘዴ አጥተን ወደ snail mail እንመላለሳለን ብለሽ አስበሽ ታውቂያለሽ? ለማንኛውም እንዲህ ሆነ፡፡ ጥጋበኛ ሰው ያስቀናኝ ጀምሮልሻል፣ ጥጋበኛ እንዲህ የሚለው ትዝ አለኝ፡፡

‹‹ ….ደብዳቤ ቢጽፉት እንደ ቃል አይሆንም፣
እንገናኝ እና ልንገርሽ ሁሉንም….››

የደላው! ቢያሻው በደብዳቤ፣ ሲፈልግ በአካል እያማረጠ እኮ ነው፡፡ ለእኔ አሁን ባለሁበት ሁኔታ ሁለቱም ቅንጦት ነው (ወይ ደብዳቤው አይደርስሽም ወይም አንቺን ማየቴ ሊገደብ ይችላል)፡፡ ቆይ ትንሽ የጎን ወሬ ላዋራሽና ምክንያቱን እነግርሻለሁ፡፡ ‹‹አንቺ›› ተብለሽ በዚህ ደብዳቤ ስለተጠቀስሽው ‹‹አንቺ››ና ይሄን ደብዳቤ ለሚያነቡ ወዳጆች የዕምነት ክህደት ቃሌን በትንሹ ላስፍር፡፡

እመቤት ሲልቪያ ፓንክረስት የኢትዮጵያ ፍቅረኛ (Ethiopian by choice) ዱቼ ሞሶሎኒ እትዮጵያን በወረረ ጊዜ፤ ወራሪው ሃይል በመላው ኢትዮጵያ ‹‹ የኢትዮጵያን ስም እያነሱ መፃፍ ክልክል ነው›› የሚል ያልተፃፈ አዋጅ አውጆ እንደነበር ይነግሩናል፡፡ በዚህም ምክንያት ፀሀፍቱና አዝማሪያኑ ስውር መጠሪያ መጠቀም ስላስፈለጋቸው እስከ ዛሬ ድረስ ተወዳጁ ሕዝባዊ ዘፈን አንቺ ልጅ አንቺ ልጅ እንደ ስውር የፍቅር ዘፈን ተበርክቷል፡፡ በዘፈኑ ‹‹አንቺ ልጅ ›› የተባለችውም ኢትዮጵያ ናት፡፡ እኔስ በዚህ ዘመን ‹ይድረስ ለባለ ታሪኩ›፣ ‹ይድረስ ለባለ ንብረቱ›… እንደሱ የሀዘን ደብዳቤ ርእስ ‹ይድረስ ለኢትዮጵያ › በማለት ፋንታ ‹ይድረስ ለአንቺ› ለማለት ስውር መጠሪያ ተጠቅሜያለሁ? ፤ በፍፁም! ጌቶች እንደሚሉት ሕገ መንግስቱ የመናገር ነፃነቴን ሙሉ ለሙሉ አስከብሮልኛልናi
ቧልቱ ይቆየንና በዚህ ደብዳቤ ርዕስ ዙሪያ ያለማንም አስገዳጅነት የእምነት ክህደት ቃሌን ላስፍር አንቺ የተባለችው ኢትዮጵያ አይደለችም፡፡ ‹አንቺ› የኔዋ ሀቢቢ ግን ባለሽበት ይድረስሽ፡፡ ውዴ እንግዲህ በዚህ ደብዳቤ ያለፈውን እያነሳሁ እነግርሻለሁ፡፡ወይ ትስቂያለሽ (ሳቅሽ እንዴት ያምራል?) ወይ ደግሞ ታዝኛለሽ (እኔን!)

ይህንን ደብዳቤ የመፃፍ መብት
እነሆ ላንቺ ስለሆነው ሁሉ ላጫውትሽ ስጀምር፤ በመነሻው ያሰብኩት ነገር ይሄን ደብዳቤ የመፃፍ ሕጋዊ መብት አለኝን? የሚለውን ጥያቄ ነው፡፡ ለዚህም መነሻዬ አሁን ያለሁበት ሁኔታ ነው፡፡ በመጀመሪያ “ሕገ-መንግስታዊ ስርአቱንና ሕገ-መንግስቱን በሀይል ፣በዛቻና በአድማ ለመናድ በመምከር/ በመናድ” ወንጀል ተጠርጥሬ የታሰርኩ ቢሆንም፤ በታሰርኩ በ23ኛው ቀን ወንጀል ወንጀልን፤ ጥርጣሬ ሌላ ጥርጣሬን እየወለደ የተለያዩ የሽብር ተግባራትን ለመፈፀም ለማሴርና ለማነሳሳት ወንጀል ተጨማሪ ጥርጣሬ በፓሊስ ዘንድ በማሳደሬ የክፋት ልኬ ከፍ ያለ ሲሆን፤ በመጨረሻም ሕገ-መንግስቱን እንደ እያሪኮ ግንብ ለመናድ በመሞከር፤ ሕብረተሰቡን ደግሞ ከሚተነፍሱት የሰላም አየር ለማቆራረጥ ከማሰብ የተለያዩ የሽብር ተግባራትን ለመፈፀም ሲንቀሳቀስ ተይዟል በሚል ወንጀሎች ተከስሼ በማረፊያ ቤት እገኛለሁ፡፡ ይሄን ሁሉ የምነግርሽ ‹ለ አንቺ› አዲስ ነገር ነው በማለት አይደለም፡፡ ይልቁንስ ያለሁበት የእስር ሁኔታ ደብዳቤ ካንቺ ጋር እንዳልፃፃፍ ይከለክለኛልን?  የሚለውን ለማስረዳት በማሰብ ነው፡፡

መቼም አሁን ያለሁበት ሁኔታ ተገቢ ነው ብዬ ባላምንም ‹ ዋስ ጠበቃዬ ነውና› ስለመብቴ ስናገር ያን የፈረደበት ህግ መጥቀሴ አልቀረም፡፡ ታዲያስ በእስር ላይ ያለ ሰው ከወዳጁና በሕይወቱ ጋር ደብዳቤ ሊፃፃፍ ምን ገደብ አለበት? ይላል ስል፤ ስለፌደራል ታራሚዎች አያያዝ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 138/1999 በአንቀፅ 18 ላይ “ታራሚዎች (ተጠርጣሪዎች) ከማረሚያ ቤቱ (ከማረፊያ ቤቱ) ውጭ ካሉ ሰዎች ጋር መፃፃፍ ይፈቀድላቸዋል፡፡ ሆኖም ለጥበቃ ስራ ተቃራኒ የሆነ ተግባር እንዳይፈፀም በፅሁፎቹ ላይ ቁጥጥር ይደረጋል” በማለት የኔና አንቺ ደብዳቤ መፃፃፍ በሕግ የተፈቀደ ነገር እንደሆነ ደንግጎልናል፡፡ አሜን! (እንዲያው ይሄ ልጅ አሁንስ ተስፋዬ.. ማነው ? ሕጉ አይደለምን… የሚል የጅል ዘፈኑን አላቆምም እንዴ? ብለሽ እንደማታሾፊብኝ እምነቴ ነው)  ጓድ ሌኒን በዛች የፒተርስበርግ እስር ቤት ውስጥ ደብዳቤ መፃፃፍ አትችልም ተብሎ ተከለከለ እርሱ ግን የ Russia Social Democratic Party ን ፕሮግራም መፅሀፍ ውስጥ በየመስመሮቹ መሀል በ Invisible Ink በመፃፍ ታሪክ ስራ፡፡ እነሆ እኔ ግን በትናንት ሌኒኒስቶች (ፋና)፤ በዛሬ አሳሪዎቻችን መልካም ፈቃድ ደብዳቤ የመፃፃፍ ሕጋዊ መብቴ ተከብሮልኝ ይሔው በነጩ ወረቀት ላይ እንደ ሕዳሴው ባቡር እፈነጭበታለሁ፡፡

እንዲህ ሆነልሽ
አበባዬ- አፄ ሀይለስላሴ ከማንኛውም ባለስልጣን በሕይወት ዘመናቸው የበለጠ የቀረቧቸው የነበሩት ከ1934-1948 ድረስ ለ14 ዓመታት በፅህፈት ሚንስትርነት ያገለገሏቸውን ፀሀፊ ትዕዛዝ ወልደ ጊዎርጊስ ወልደ ዮሀንስን እንደ ነበር ነግሬሻለሁ? ወዳጅነትና ፍቅር ያልፋልና ሀይለስላሴና ወልደ ጊዎርጊስ ተጣሉ፡፡ የአፄ ሀይለስላሴ መንግስት መፅሀፍ ፀሀፊ አቶ ዘውዴ ረታ የወልደጊዎርጊስን መጨረሻ ሲተርኩ፡፡

‹‹ ፀሃያማው ሚያዚያ 17/1948 ቀን ለ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሀንስ እንደ ሌሎቹ ቀናት ብሩህ ሁና ነበር የነጋችው፡፡ ብሩህ ሁና እንደምታመሽም አልተጠራጠሩም ነበር፡፡ ምን ያደርጋል! ያች ክፉ ሰኞ የወልደጊዎርጊስ ከፍተኛ ስልጣን መጨረሻ ሆነች፡፡ በእኩለ ቀን ገደማ ቤተ መንግስት ተጠርተው ከፅህፈት ሚንስተርነታቸው ተነስተው የአሪሲ ጠቅላይግዛት ደረሳቸው››
(መፅሀፉ አጠገቤ ስለሌለ ቃል በቃል አልጠቀስኩም)

ወልደጊዮርጊስ ተሽረው ከቤተ-መንግስት እንዲርቁ የተደረገበት ምክንያት የሀይለስላሴን ወንበር በሰዒረ መንግስት ለመገልበጥ አስበዋል በሚል ምክንያት ነበር፡፡ወልደጊዎርጊስን እዚህ ጋር ማንሳቴ የሚያዚያ 17 ስለት እኔም ጋር በመድረሷ ነው፡፡ ውዴ! የእኔዋን ሚያዚያ 17/2006 ዓ.ም ውሎ እንደ ዘውዴ ረታ ስተርክልሽ ይሔን መሳይ ይሆናል፡፡

 ‹‹ ፀሃያማዋ ዓርብ ሜያዚያ 17/2006 ዓ.ም አጀማመር እንደ ወትሮው አልነበረም፡፡የጠዋት ትምህርት ክፍለ ጊዜ እንዳይረፍድብኝ እየተቻኮልኩ ወደማስተምርበት (የመጨረሻ ክላስ ነበር) አምቦ ዩንቨርሲቲ ስሄድ፤ ተማሪዎች አዲስ የተዘጋጀውን የአዲስ አበባ ከተማ መሪ እቅድ ‹ሕገ-መንግስታዊ አይደለም በሚል መነሻ የተለያዩ መፈክሮችን እያሰሙ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው ነበር፡፡ ሰልፉ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተካሂዶ እንደተጠናቀቀ በሰልፍ ምክንያት የቀረውን የመጨረሻ ክላስ ሚያዚያ 18/2006 ዓ.ም ለማካሄድ ተማሪዎቼ ጋር ቀጠሮ ይዤ ብለይም ‹ሰው ያቅዳል ፣ እግዜር ይስቃል› እንደሚባለው ሆነና በዛች ሚያዚያ 17/2006 ዓ.ም ማምሻ ላይ እንደ ወልደጊዎርጊስ ወልደ ዮሃንስ ‹የመንግስትን ዙፋን በሕዝባዊ አመፅ ልትነጥቅ አሲረሀል› በሚል ክስ በቁጥጥር ስር እንደዋልኩ የደህንነት ግሪሳዎች (8 ወይም 9 የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አባላት ) አበሰሩኝ፡፡

 ነገሩ ብዙም አልገረመኝም፡፡ ትንሽ ያበሳጨኝ አቶ ዘላለም ለጥያቄ ስለምንፈልጎት አዲስ አበባ የፌደራል ወንጀል ምርመራ ዘርፍ (ማእከላዊ) ነገ ጠዋት 3 ሰዓት እንዲገኙ ብለው በስልክ ቢጠሩኝ ‹እሺ ነገ ሶስት ሰአት ላይ ክላስ አለኝ ከክላስ ወደ 9 ሰዓት አካባቢ አመጣለሁ › ብዬ የምቀርበውን ሰው ይሔን ሁሉ ሀይል ከሁለት መኪና ጋር በመመደብ ላከበረኝ መንግስቴ ‹ጉዳት› ባሰብኩ ግዜ ነው፡፡ ላክባሪዬ ውለታ መላሽ ያርገኝ i

ዓለሜ- ደብዳቤዬን እያነበብሽው እንደሆነ ተስፋ አለኝ፡፡ በቁጥጥር ስር ውሏል የምትለው ሀረግ ድሮም ትንሽ ፈገግ ታደርገኝ ነበር፤ አሁን ደሞ እኔን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከአዲስ አበባ የመጣው የደህንነት ቡድን መሪ የመሰለኝ እድሜው ትንሽ ገፋ ያለ ሰው አንድ ሶስቴ ስልክ እየደወለ (ለማን ይሆን) ‹በቁጥጥር ስር አውለነዋል› እያለ መልክት ሲያስተላልፍ ስሰማ ፈገግ ማለቴ አልቀረም፡፡ ሀሳቤ ልቤ ፣ ይሄውልሽ ከስራ ቦታዬ  ‹ሀገር ሰላም› ሕዝባዊ አመፅ ለመቀስቀስ አስበሃል በሚል ጥርጣሬ በቁጥጥር ስር የዋልኩት እንዲህ እንደገለፅኩት ነበር፡፡ ከሚያዚያ 17/2006 -ሀምሌ 11/2006 ዓ.ም ያሉት 84 ቀናት የተደጋገሙና ሕይወት አልባ በመሆናቸው እንዲሁ ከማሰለችሽ 5 ሁነቶችን ልፃፍልሽና ዘና በይ፡፡ ከሁነቶቹ በፊት ግን ስለ 84 ቀናቱ አጭር መግለጫ ልስጥሽ፡፡

የመጀመሪያዎቹን 75 ቀናት በፌደራል ወንጀል ምርመራ ዘርፍ (ማዕከላዊ) ጥብቅ ጥበቃ ክፍል (Siberia) ውስጥ 5 ቁጥር የተባለ 4 ሜትር በ5 ሜትር የሆነችና 5 ፍራሾችን በምትይዝ ክፍል ውስጥ ከረምኩ፡፡ ክፍሉ የተፈጥሮ ብርሀን በምንም አይነት መንገድ (ቀንን ጨምሮ) የማይገባበት ሲሆን፣ ለ24 ሰዓታት የመብራት ብርሀን ይበራበታል፣ መብራት ሲጠፋ በጄኔሬተር ሀይል ይተካል፡፡ ጄኔሬተሩ ነዳጅ ሲጨርስ ደግሞ ቀንም ሆነ ማታ ጨለማ ነው ባትሪ፣ ሻማ፣ ማንኛውንም አይነት ሰዓት መያዝ አይቻልም፡፡ ጠዋት 12 ላይ ለ10 ደቂቃ ፤ ማታ ከ10 ሰዓት አስከ 12 ሰዓት ለ 10 ደቂቃ ሽንት ቤት ለመጠቀም የክፍላችን በር የሚከፈት ሲሆን፤ በቀን ውስጥ ከ15 – 20 ደቂቃ ለሚሆን ጊዜ ደግሞ ከክፍላችን በየተራ ወጥተን ነፋስ/ፀሀይ እናየለን፡፡ ከዛ ውጭ በቀን ውስጥ ከ23 ለሚበልጠው ሰዓት የክፍሉ በር ዝግ ሲሆን ጮክ ብሎ ማውራትና መዝፈንም ቅጣት ያስከትላል፡፡

ወዳጄ በነዚህ 75 ቀናት ስንት ‹አሸባሪ› ወዳጆችን አፈራሁ መሰለሽ፡፡ መንግስቴ የ 15 እና የ14 ዓመት ልጆችን በአሸባሪነት ጠርጥሮ እንደሚያስርም ለመረዳት ችያለሁ፡፡ አብረውኝ በእስር የነበሩት ወዳጆቼ ጥርጣሬ አጅግ የተለየ ነው፡፡ ከአል-ሸባብ አስከ ኦብነግ እስከ ኦነግ እስከ የቤኒሻንጉል ጉምዝ ሕዝቦች ነፃ እውጭ ግንባር እስከ አቂዳ(አዲስ የሽብር ቡድን)… ስቃይን መማር ጥሩ ነውና ሁለት ለሚሆኑ ቀናት ብቻዬን በመታሰሬም solitary confinement ን experience ለማድረግ ‹ታድያለሁ›፡፡ በርግጥ ብቻዬን ታስሬ ነበር ከምል ካንቺ ሀሳብ ጋር ታሰርኩ ብል ይቀለኛል፡፡

አምስቱን ሁነቶች ዘንግቼ ስለ ስቃዬ ተንዛዛሁብሽ ይሆን? ለዚህ ተግባሬ በእስረኛ ቋንቋ ‹ተፀፅቻለሁ›፡፡ በቃ ወደ ጉዳዮቹ፡፡ ከዚህ በታች የምገልፃቸው ሁነቶች የ84 ቀናቱ የእስር ወቅት (የምርመራ) ጊዜ ምን እንደሚመስል እንደነበር ያስረዱሻል ብዬ አስባለሁ፡፡ (ሁሉም በእውነት እኔ ላይ የደረሱ ጉዳዮች ናቸው)፡

1.    ተማሪዎቼን እንዳላበላሻቸው በማሰብ በቁጥጥር ስር ስላዋለኝ አመሰግናለሁ
ሚያዝያ 17/2006 ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ ከምኖርበት አምቦ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ከደህንነቶች ጋር በቤት አውቶሞቢል እየተጓዝኩ ነው፡፡ አንድ ልጅ እግር ደህንነት ጠየቀኝ
‹‹ዘላለም የህግ መምሕር ነህ አይደል..››
            እኔ፡ አዎ
            ደህንነቱ  “ስንት ጠበቆች ዳኞች ማፍራት ሲጠበቅብህ አንተ ‹ልማቱን ካላደናቀፍኩ› ማለትህ እጅግ ያሳዝናል፡፡ ለማንኛውም እንኳን ተማሪዎቹን ሳታበላሻቸው በጊዜ በቁጥጥር ስር ዋልክ፡፡ ኧረ                  ለመሆኑ ከውጭ ስንት ሽህ ደላዮችን አግኝተሻል? Any way በልማታችን ቀልድ የለም” አለኝ፡፡ (እኔም ባስተማርኩባቸው 4 አመታት ስንት ተማሪዎችን ‹እንዳበላሸሁ › እያሰብኩና ልማታችን                  በወለደው የአስፋልት መንገድ ፏ ብዬ ከምሽቱ 3፡50 ላይ ማዕከላዊ ከቸች፡፡

2.   አላማችሁ ምንድን ነው?
እመቤቴ – መንግስት ሕዝባዊ አመፅ ለመቀስቀስ አሲራችኋል፤ ለዚህም በቂ ማስረጃ አለኝ በማለት ያሰረን ቢሆንም መንግስት ሀሳቡ እውነት ይሆንለት ዘንድ የእኛን ‹አዎ አሲረናል› የሚል መልስ በማባበልና በሀይል ለማግኘት ከመሞከር ውጭ ሌላ ያቀረበው አንዳችም ማስረጃም ሆነ መረጃ(በጠ/ሚንስትሮች ቋንቋ) አልነበረም/የለምም፡፡ ለዚህም ይመስላል በማእከላዊ የቆየሁባቸው ቀናት ምርመራው በሙሉ ‹አላማችሁ ምንድን ነው? በሚል ሕይወት አልባና አሰልቺ ጥያቄ የተሞላው፡፡ እኔም የዚህ ጥያቄ ሰለባ ሁኜ ከረምኩልሽ፡፡ እንዲህ ላጫውትሽ፣
           መርማሪ ፖሊስ (በተደጋጋሚ) – እንደ ዞን 9 አላማችሁ ምንድን ነው?
           እኔ፡ ዓላማችን ግልፅ ነው፡፡ ማንም ብሎጋችንን የተመለከተ ሰው በቀላሉ ሊረዳው ይችላል፡፡ባጭሩ የተለያዩ ተረኮችን የሚያስተናግድ እና ሕብረተሰባዊ ተዋጾን የሚያሳድግ ፕሮፋይል ነው፡፡
           መርማሪ ፖሊስ፡ እሱ ሽፋን ነው፤ እውነተኛ ዓላማችሁን ተናገር?
           እኔ፡ ከዚህ የተለየ አላማ የለንም!

መርማሪ ፖሊሱ እንድንመልስለት የሚፈልገው ‹ከበላይ አካል› ይዞ እንዲመጣ የታዘዘውን መልስ፤ “አላማችን እንደ ጭቃ ተረግጦ፤ እንደ ገል ተቀጥቅጦ የሚገኘውን ጭቁን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከተጫነበት ቀንበር ነፃ ማውጣት ነው፡፡ ለዚህም መሳካት ሕዝባዊ አመፅ ማደራጀትን እንደ ዋነኛ ዓላማ አድርገን ነው የተቋቋምነው፡፡”
ሲሆን ይህ ደግሞ ከአላማችን ጋር የማይገናኝ መንግስታዊ ፍላጎት በመሆኑ እንዲህ አይነት መልስ ከእኔ ማግኘት እንደማይችል የተረዳው መርማሪ በተደጋጋሚ አስብበት በማለት ይሰናበተኝ ነበር፡

3.   ከመርማሪዎች ጋር የነበረኝ ቆይታ
የእኔ ፅጌሬዳ አላማችን እንደ ቡድን ባይጠይቁኝ ኑሮና የግል ዓላማዬን ቢጠይቁኝ አላማዬ ‹አንቺ› እንደሆንሽ ከመናገር ወደኋላ እንደማልል ታውቂያለሽ አይደል? የሆንሽ ‹አሸባሪ› ነገር፡፡ Any way ምርመራዬ ቀጥሎልኛል፡፡ ሁለት መርማሪዎች እየተፈራረቁ ገራሚ ገራሚ ጥያቄዎችን እየጠየቁኝ ነው፡፡ እነሆ ፡
         መርማሪ ፖሊስከአለም መሪዎች ማን ማንን አግኝተህ ታውቃለህ?
         እኔ፡ ማንንም
         መርማሪ ፖሊስእኛ እኮ ያለመረጃ አይደለም እየጠየቅን ያለነው፡፡ ጉድ ሳይመጣብህ ብትናገር ይሻላል፡፡
         እኔእስኪ አስታውሱኝና ምን እንደተነጋገርን ልናገር፡፡ በርግጥ ባለፈው የኔልሰን ማንዴላ ማስታወሻ ፕሮግራም በ አፍሪካ ህብረት በተከበረበት ወቅት ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ አግኝቻቸዋለሁ፡፡ ሌላ         የማስታውሰው የለም፡፡
        መርማሪ ፖሊስ፡ ህም! እሺ ዘንድሮ ኦባማ ፊት ንግግር ለማድረግ ከተመረጡ 3 ኢትዮጵያውያን አንዱ አንተ አይደለህም? አሜሪካ በ አፍሪካ ጉዳይ ምን አግብቷት ነው፡፡ ወጣት አመራሮች ምናምን             እያለች የምታሰለጥነው?
        እኔ፡ ‹‹እንዴ ኦባማ ፊት ንግግር ነው ያልከኝ? ድንገት ከታሰርኩ በኋላ ተመርጬ (በማሾፍ ድምፀት) ከሆነ አላውቅም፡፡ወይ በስም መመሳሰል ሊሆን ይችላል፡፡ አሜሪካ በአፍሪካ ጉዳይ ምን አግብቷት           ነው? ላልከኝ ግን ወጣቶችን Empower ማድረግ ችግር ያለው አይመስለኝም ፤ ደግሞ በረሀቡም በድርቁም ጊዜ ርዳታ የምታደርገው እኮ አሜሪካ ነች፡፡ ምን አግብቷት ነው የምትረዳው አይባልም               መቼም?!››
        መርማሪ ፖሊስ፡ አሁን ዘመኑ የልማት ነው፤የምን ረሀብ ነው የምታወራው? በል ተወው፡፡

            (‹ፈሪ ውሃ ውስጥ ያልበዋል› ሰምተሻል ውቤ? መንግስቴ ብቻውን እየሮጠም ፍርሃቱና ስጋቱ ብዛቱ፡፡ የሚቆጨኝ ነገር ከዓለም መሪዎች ማን ማንን አግኝተሃል? ‹ስባል› ከሲሪላንካ ፕሬዜዳንት ጋር ተገናኝቼ ወደ ደቡብ አሜሪካ ፔሩ በመጓዝ ማቹፒቹን ጎብኝቻለሁ ብዬ ብናገር ኑሮ፤ ክሳችን ላይ ‹ከሲሪላንካ መንግስት ባገኘው የገንዘብና የመሳሪያ ድጋፍ ወደ ፔሩ በመጓዝ ሕገ-መንግስት እንዴት እንደሚናድ በማቹፒቹ ኮረብታ ስልጠና ወስዶ ተመልሷል፡፡ ለዚህ እንደ ማስረጃ ይሆን ዘንድ ላፕቶፔ ውስጥ የተገኙት ከ300 በላይ የቼጉቬራ ምስሎችና Machu Pichu: The Mecca of Hippies” የሚል ባለ 22 ገጽ ‹ሰነድ› አብሮ ይያዝልኝ ነበር፡፡ ሲያበሳጭ

4.   ‹አሸባሪው› ገብረሕይወት ባይከዳኝና ሀገሪቱን በሀራጅ የመሸጥ ጉዳይ
ፍቅር አደከምኩሽ አይደል?! ልጨርስ ስለሆነ ትንሽ ታገሺኝ፡ በዛውም ‹ፍቅር ታጋሽ ነው› የሚለውን Paulian ወንዴነት፤ ‹ፍቅር ታጋሽ ናት› በሚል ማስተካከያ እንድናርመው፡፡ የዚህ የምርመራ ነገር እኮ አላልቅልኝ አለ፡፡ በእስሬ ወቅት ሌላው በተደጋጋሚ እንዳስረዳ ስጨቀጨቅበት የነበረው ጉዳይ ‹ኒዮ-ሊብራልነቴና ልማትና ዲሞክራሲ ጎን ለጎን አብረው ይሄዳሉ ማለቴ ነበር፡፡
መርማሪ ፖሊሶቹ እየተቀያየሩ ስለኢህአዴግ የፖሊሲ ትክክለኛነት ‹ያስረዱኝ› ነበር፡፡ “አንተ ምን ጎደለብኝ ብለህ ነው ነጭ አምላኪ የሆንከው ? ትንሽ የተስፋ ጭላንጭል ስናይ አንተና ጓደኞችህ አይናችሁ ለምን እንደሚቀላ እስኪ ንገረን ? ይህች አባቶቻችን ‹በደምና በጾም› ያቆዩልንን አገር አንተና ያንተ ትውልድ ግን ውበቷ እና ድንቅነቷ ላስጎመጃቸው ነጮች ለመሸጥ መደራደር ጀመራችሁ….” እያሉ ‹በባንዳነት› ሲከሱኝ ከረሙ፡፡ የሀገሪቱ ውበትና የነጮች በውበቷ መጎምጀት ነገር ሲነሳ ጊዜ ‹አንቺ› ትስቂ ዘንድ የሚከተለውን አንቀፅ አሻግሬ ታደሰ የተባሉ ፀሐፊ ከ 50 ዓመት በፊት ‹እኔና አንተ› ካሉት ጽሁፋቸው ላይ እጠቅስልሻለሁ

“ኢትዮጵያ እጅግ ያማረች፤ የተዋበች ፤የተደነቀች፤ላያት ሁሉ የምታማልል፤የምታዘናጋ…….ናት፡፡ ዓይኗ የብር አሎሎ መለሎ ከአጥቢያ ኮከብ የተፎካከረ….. ነው፤ አገራችን ኢትዮጵያ ፅጌረዳ መስላ የሰኔን ቡቃያ ትመስላለች፡፡ የመስከረም አበባ ሆና በሩቅ ትስባለች፤የመስህቧ ኃይል ማግኔት ምስጋን ይንሳው፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ ጥርሷ እንደ በረዶ ሆና ለፈገግታ ያህል ትንሽ ከንፈሯን ስትገልፀው እንኳንስ ለሰው ግብዙ መልዓክ ያብዳል፡፡ ኢትዮጵያ ፀጉሯ የሀር ነዶ ነው፤ኢትዮጵያ አጠረች ፤ረዘመች፤ወፈረች፤ብሎ ስለአካሏ መናገር አይቻልም፡፡ እንዲያው ዝም ይሻላል፡፡ በጠቅላላው ኢትዮጵያ ውበቷ ሰነፉን ይገድላል፡፡ ብርቱውን አነሁልሎ ያሳብዳል፡፡ እግዚአብሔር፤ኢትዮጵያን ሲፈጥር በብዙ ተራቋል፤ተጠቧል፤ ውበቷ በሩቅ ይስባል፤ አጥንትም ይሰብራል፤አዕምሮን ይሰውራል፡፡ ይገርማል!” ይላሉ፡፡

 ምንም እንኳን ውበት እንደተመልካቹ ነው ቢባልም፤ መርማሪዎቹ በዚህ ዓይነት Vulgar Natioanlism ሰክረው እኔና የእኔ ትውልድ ሀገሪቱን ‹በውበቷ ለሰከሩ› ነጮች ልንሸጣት እንደተዋዋልን እየነገሩኝ ነው፡፡ ይገርማል! ዲሞክራሲን ከልማት እኩል ማስኬድ ነውር የለበትም፤ ተገቢም ነው ማለት እንደ አገር ሽያጭ ውል የሚቆጠርበት ብሎም ‹ሩቅ አስባ ሩቅ ለማደር እየተጋች ያለችን አገር› መንገድ ላይ በጠረባ ለመጣል የተደረገ ሙከራ ተደርጎ የሚወለድባትና ‹አሸባሪ› የምንሰኝባት፣ ‹ለፈገግታ ያህል ትንሽ ከንፈሯን ስትገልጠው እንኳን ሰውን ግብዙን መልዓክ የምታሳብደው ኢትዮጵያ!

ሊቁ ገብረሕይወት ባይከዳኝ ‹ልማትን ሲተች›  “እውቀት በሌለው ሕዝብ አገር መንገድና የምድር ባቡር ቢሰራ ሕዝቡ እንዲደኸይ ያፋጥናል እንጂ አይጠቅመውም፡፡ ጥቅሙ ከርሱ ጋር የሚገበያዩ አዋቂ ሕዝቦች ነው”  በማለት ‹ልማት ብቻውን ዋጋ የለውም› ሲል ይበይናል፡፡ ገብረሕይወት የእኛው ትውልድ አባል ቢሆን ኖሮ  “የኢኮኖሚ እድገቱን በመካድ፤ ሕዝቡ በአዕምሮ መናወጥ ምክንያት የዘረጋነውን የባቡር ሀዲድ ፈነቃቅሎ እንዲጥልና ሌሎች የሽብር ተግባራትን እንዲፈፀም በማነሳሳት ‹ወንጀል›” መመርመሩና መከሰሱ አይቀሬ ነበር፡፡
ውዴ! ያን ‹አሸባሪ› ሳቅሽን ሳስብ በፀረ-ሽብር ሕጉ መሠረት ጉዳይሽ ሊታይ ይችላል የሚል ስጋቴ የበዛ ነው፡

5.   ናፍቆቴ ሆይ!
እንዲያው ለዚህ 84 ቀናት ውስጥ የሆንኩትን ሁሉ እንዳልፅፍልሽ እንዳትሰለችብኝ ፈራሁ፡፡ እያንዳንዱን ሁነት በ Diary መልክ ከትቤ እንዳልክልሽ በነዛ ቀናት ውስጥ ብዕርም ሆነ ነጭ ወረቀት ይዞ መገኘት ‹ከፍ ብሎ አንገትን፣ ዝቅ ብሎ ባትን› ባያስቆርጥም ዛቻና ዱላን ማስከተሉ አይቀርም ነበርና ልከትብ አልቻልኩም፡፡ እንዲሁ በደፈናው ግን አንዳንድ ጉዳዮችን ብዘረዝርልሽ፡

  •  በነዛ ክፉ ቀናት ከምሽቱ 12 ሰዓት እንቅልፍ መተኛትን ለመድኩ፡፡ ይሔም ነገር መልካም እንደሆነ አየሁ፡፡ ምክንያቱም ሌሊት ከእንቅልፍ ተቀስቅሰው ራቁታቸውን ሲደበደቡ አድረው ከ 3 እና 4 ሰዓታት ቆይታ በኋላ በነፍስ ወደ መኝታ ክፍላችን የሚመጡ የእስር ጓደኞቼን  (Cellmates) ስቃይና ሰቆቃ ላለመስማት፡፡
  •  በ2004 ዓ.ም የፌዴራል ፖሊስ ‘Cyber crime Laboratory’ ተቋቁሟል መባሉን ሰምቼ ‹እንግዲህ cyber criminal ሁሉ የት ትገቢ? አለቀልሽ!› ብዬ ነበር፡፡ በጊዜ ቀጠሮ ጊዜ እንደተረዳሁት ደግሞ ‹ያለችን አንዲት ኮምፒውተር ናት የእነዚህ ልጆች ዳታ በአንድ ኮምፒውተር መርምረን መጨረስ ስላልቻልን የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠን› ሲባል ነው፡፡ አረ እንዲያውም ‹እስኪ Anti-virus ካለህ ኮምፒውተሬ ላይ ጫንልኝ› ተብዩ ሁሉ ነበር፡፡ ‹ለሽብር ተግባራት› መመርመሪያ ያልሆነ ‘Cyber crime laboratory’ ለመች ሊሆን ነው?
  • አንድ ቀኑንና ወሩን በማላስታውሰው ቀን አንድ ጎልማሳ የታሰርንበትን ክፍል አስከፍተው ገቡና እያንዳንዳችን መጠየቅ ጀመሩ፡

–   ‹አንተ ከየት ነው የመጣኸው?› (አንድ ተማሪ ወዳጄን)
–   ‹ከሀሮማያ ዩኒቨርስቲ›
–   ‹አሀ እናንተ ናችኋ…..›
****
–   ‹አንተኛውስ ከየት ነው የመጣኸው?!›
–   ‹ከወለጋ ዩኒቨርስቲ›
–   ‹አሁን ኦሮሚያ ብትለማ ምን የሚያስከፋ ነገር አለው?!….›
*****
–   ‹አንተስ ከየት ነው የመጣኸው› (እኔን ነው)
–   ‹ከአምቦ ዩኒቨርስቲ›
–   ‹ሕዝቡን እርስ በ&

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእስልምና በኦርቶዶክስና በፕሮቴስታንት ሃይማኖቶች እየታየ ያለው የአክራሪነት አደጋ ለስርዓቱ ፈተኝ ሆኗል በሚል አላማ የተሰናዳው አዲስ ስትራቴጂ በአማራ፣ በኦሮምያና በደቡብ ክልሎች ከመጪው አመት ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል። በሰነዱ ዙሪያ  ላይ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የዞን እና ለአክራሪነት ተጋላጭ ናቸው የተባሉ የአንዳንድ ወረዳ አመራሮች እንዲሁም የሚመለከታቸው የተለያዩ መስሪያ ቤት አመራሮች ውይይት …

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አስቀድሞ የህዝብ ግንኙነት ስራ መሰራቱን ተከትሎ በመንግስት ሰራተኞች ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት የነበረው የደሞዝ ጭማሪ የታሰበውን ያክል አለመሆኑን ተከትሎ በሰራተኛው ዘንድ ቅሬታ ከፈጠረ በሁዋላ መንግስት  ተጨማሪ ምርመራ ሊያደርግ መሆኑ ታውቋል። “የደሞዝ ማስተካከያ የተባለው የታለመውን የፖለቲካ ትርፍ አለማስገኘቱ ብቻ ሳይሆን በእቃዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ በማስከተሉና የኑሮ ውድነቱን በማባባሱ በየመድረኩ …

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው ” ለተማሪዎች በግዳጅ የሚሰጠውን ካድሬያዊ ስልጠና እና ትውልድን የማኮላሸት ሴራአጥብ ቀንእናወግዛለን!” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ፣ ላለፉት 23 ዓመታትህወሓት/ኢህአዴግስራዬብሎካዳከማቸውናጉዳዬከማይላቸውዘርፎችውስጥ የሚመደበውየትምህርትስርዓቱመሆኑን ገልጾ፣  ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው የገዢው ፓርቲ አባል እንዲሆኑ ሲገደዱ መቆየታቸውና የኢህአዲግአባልካልሆኑምስራሊያገኙእንደማይችሉእየተነገራቸውበፍራቻለአባልነትየተመዘገቡብዙዎችእንደሆኑየአደባባይሚስጥርነው ብሎአል። በያዝነውወርበሁሉምዩኒቨርስቲዎችተማሪዎችእንዲሰበሰቡናስልጠናእንዲወስዱ፣ ስልጠናውን ያልተከታተለም መደበኛ ትምህርቱን እንደማይቀጥል ማስፈራሪያአይሉትማሳሰቢያበገዢውፓርቲበኩልመተላለፉንናተማሪዎቹበግድስልጠናውንእንዲወስዱመገደዳቸውሳያንስወደግቢከገቡበኋላ ተመልሰውመውጣትእንደማይችሉመደረጉን አስታውሰዋል። ህወሓት/ኢህአዴግይህንንስልጠናሲያካሂድም ህግንበጣሰመልኩየትምህርትማዕከላትንየፖለቲካማራመጃእናየአንድፓርቲርዕዮተ-ዓለም ማስፈፀሚያማድረጉን፣ይህንፋይዳቢስስልጠናበሁሉምዩኒቨርሲቲዎችናከ800.000 በላይለሚሆኑተማሪዎችበሚሰጥበትወቅትከፍተኛ የህዝብሀብትእያባከነመሆኑን፣  ተማሪዎችየእረፍትጊዜያቸውንበነፃነትማሳለፍሳይችሉበአስቸኳይወደዩኒቨርስቲዎችእንዲመለሱመገደዳቸው …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የኤቦላ በሽታ ዩጋንዳ ውስጥ አራት ጊዜ ተከስቶ ነበር። በኤቦላ ተኀዋሲ የተያዘው ሰው ቁጥር ግን በእጅ ጣት የሚቆጠር ነበር። ይህችው የምሥራቅ አፍሪቃ ሀገር ምን ብታደርግ ነበር ያኔ የበሽታውን ስርጭት ባለበት ማስቆም የቻለችው? በምዕራብ አፍሪቃ ለምን ይህን ማድረግ አልተቻለም?

ኢራቅ ውስጥ አክራሪ እስላማዊ ኃይል የተሰኘውን ፣ (IS) በሚል ምህጻረ ቃል የታወቀውን የሱኒዎች ታጣቂ ኃይል ለመመከት ፤ የሰሜን ኢራቅ ራስ ገዝ መስተዳድር፣ ኩርዲስታን ፣ ምን ዓይነት የጦር መሣሪያ ያስፈልገዋል? ከጀርመን ፌደራል ሪፓብሊክ

«ሁሌም ሰባት ቀን ሰርቼ ሶስት ቀን እረፍት፤ ሰባት ቀን ሰርቼ አራት ቀን ረፍት ቋሚ ፕላን ባለበት የኤርፖርት ስራዬ ከቀኑ ሶስት ሰዓት እገባና ስድስት ሰዓት ሰርቼ ማታ ዘጠኝ ሰዓት እወጣለሁ፤ ማታ ዘጠኝ ሰዓት ተኩል ላይ እጀምርና፤ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ተኩል የሚያልቅ የሁለት ሰዓት ሥራ እገባና እንደጨረስኩ፤

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) ባለፈው ወር ማለቂያ ገደማ የስደተኞችን መስተንግዶ በተመለከተ፣ ኢትዮጵያ በአፍሪቃ ክፍለ ዓለም በዚህ ረገድ ከኬንያ ልቃ መገኘቷን ከሰሞኑ በሰጠው መግለጫ ላይ ይፋ አድርጓል።

የኤቦላ በሽታ ዩጋንዳ ውስጥ አራት ጊዜ ተከስቶ ነበር። በኤቦላ ተኀዋሲ የተያዘው ሰው ቁጥር ግን በእጅ ጣት የሚቆጠር ነበር። ይህችው የምሥራቅ አፍሪቃ ሀገር ምን ብታደርግ ነበር ያኔ የበሽታውን ስርጭት ባለበት ማስቆም የቻለችው? በምዕራብ አፍሪቃ ለምን ይህን ማድረግ አልተቻለም?

ክረምቱን በማጠናከሪያ ትምህርት በንባብ ወይም በእረፍት ያሳለፉ ተማሪዎች ለመጪው የትምህርት ዘመን የሚያስፈልጓቸውን እንደ ደብተር ብዕር መፃህፍትና የመሳሰሉትን በብዛት ሲገዙ የሚታዩት በዚህ ወቅት ላይ ነው ።

ላለፉት 23 ዓመታት ህወሓት/ኢህአዴግ ስራዬ ብሎ ካዳከማቸውና ጉዳዬ ከማይላቸው ዘርፎች ውስጥ የሚመደበው የትምህርት ስርዓቱ ሲሆን ይህም ከኢህአዴግ ስህተቶች ሁሉ ዋነኛው እና አሳፋሪ ተግባሩ ነው፡፡ ለሁለት አስርት አመታት ትውልዱን በማምከን በሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ ከገፉት ጉዳዮችም ግንባር ቀደሙ የህወሓት/ኢህአዴግ የተምታታበት የትምህርት ፖሊሲ መሆኑም ይታወቃል፡፡ ትምህርት ለአንድ ሀገር እድገት የጀርባ አጥንት መሆኑ እየታመነ የትምህርት ስርዓቱ ሆን ተብሎ በንቀት […]

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

ለተማሪዎች በግዳጅ የሚሰጠውን ካድሬያዊ ስልጠና እና ትውልድን የማኮላሸት ሴራ አጥብቀን እናወግዛለን!

ላለፉት 23 ዓመታት ህወሓት/ኢህአዴግ ስራዬ ብሎ ካዳከማቸውና ጉዳዬ ከማይላቸው ዘርፎች ውስጥ የሚመደበው የትምህርት ስርዓቱ ሲሆን ይህም ከኢህአዴግ ስህተቶች ሁሉ ዋነኛው እና አሳፋሪ ተግባሩ ነው፡፡ ለሁለት አስርት አመታት ትውልዱን በማምከን በሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ ከገፉት ጉዳዮችም ግንባር ቀደሙ የህወሓት/ኢህአዴግ የተምታታበት የትምህርት ፖሊሲ መሆኑም ይታወቃል፡፡ ትምህርት ለአንድ ሀገር እድገት የጀርባ አጥንት መሆኑ እየታመነ የትምህርት ስርዓቱ ሆን ተብሎ በንቀት እና በዝርክር አሰራር እንዳያድግና ጥራት እንዳይኖረው ኢህአዴግ እየተጋ አሁን ድረስ ዘልቋል፡፡ በዚህ አይነቱ አጥፊ አካሄድ ምክንያትም ሀገራችን በዓለም ደሃ ሀገራት ተርታ ቀዳሚዋ ሆናለች፡፡

የተማረ እየተገፋ በስራ አጥነት ሲንከራተት እና ለስደት ሲዳረግ በካድሬነት የስርዓቱ አገልጋይ መሆን ደግሞ በተቃራኒው ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል፡፡ በተለይም ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው የገዢው ፓርቲ አባል እንዲሆኑ ሲገደዱ መቆየታቸውና የኢህአዲግ አባል ካልሆኑም ስራ ሊያገኙ እንደማይችሉ እየተነገራቸው በፍራቻ ለአባልነት የተመዘገቡ ብዙዎች እንደሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ በዚህ ሳያበቃ አሁን አሁን ደግሞ የገዢውን ፓርቲ ያረጀና ያፈጀ ኋላቀር አስተሳሰብና ርዕዮተ-ዓለም በተማሪዎች ላይ ለመጫን በየዓመቱ መጀመሪያ ‹ስልጠና› በሚል ፈሊጥ በጀት በጅቶ በግድ ሊግታቸው እየሞከረ ይገኛል፡፡

በዚሁ በያዝነው ወርም በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎች እንዲሰበሰቡና ስልጠና እንዲወስዱ ጥሪ የተላለፈ ሲሆን ስልጠናውን ያልተከታተለም መደበኛ ትምህርቱን እንደማይቀጥል ማስፈራሪያ አይሉት ማሳሰቢያ በገዢው ፓርቲ በኩል ተላልፏል፡፡ ሌላው አስገራሚ ዜና ደግሞ ተማሪዎቹ በግድ ስልጠናውን እንዲወስዱ መገደዳቸው ሳያንስ ወደ ግቢ ከገቡ በኋላ ተመልሰው መውጣት እንደማይችሉ መሰማቱ ነው፡፡

ይህም ኢህአዴግ ካድሬዎቹን የሚያሰለጥንበት ዝግ የስብሰባ ስልት መሆኑ ጉዳዩን የበለጠ አስገራሚ ያደርገዋል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ ይህንን ስልጠና ሲያካሂድም፡-
1. ህግን በጣሰ መልኩ የትምህርት ማዕከላትን የፖለቲካ ማራመጃ እና የአንድ ፓርቲ ርዕዮተ-ዓለም ማስፈፀሚያ አድርጓል፡፡

2. ይህን ፋይዳ ቢስ ስልጠና በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎችና ከ800.000 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች በሚሰጥበት ወቅት ከፍተኛ የህዝብ ሀብት እያባከነ ይገኛል፡፡

3. ተማሪዎች የእረፍት ጊዜያቸውን በነፃነት ማሳለፍ ሳይችሉ በአስቸኳይ ወደ ዩኒቨርስቲዎች እንዲመለሱ ተገድደዋል፡፡

4. በሚሰጠው ስልጠናም ላይ በአክራሪነት በብሔርተኝነትና በመሳሰሉት ጉዳዩች ሽፋን በተማሪዎች ዘንድ መርዛማ ጥላቻን እየረጨ ይገኛል፡፡

5. በአጠቃላይ በስልጠናው ወቅት ርካሽ የፕሮፖጋንዳ ስልትን በመጠቀም መጪውን ምርጫ በማምታታት ለማለፍ እየሞከረ ሲሆን ይህም በአምባገነንነቱ ቀጥሎ ህብረተሰቡን አማራጭ ለማሳጣትና ሀገሪቷን ወዳልተፈለገ አለመረጋጋት ሊወስድ እየሞከረ መሆኑን ያሳያል፡፡ በመሆኑም ሰማያዊ ፓርቲ ይህን የገዢው ፓርቲ ህገ ወጥ አድራጎት አጥብቆ እያወገዘ ጉዳዩን እየተከታተለም አቋሙን ይፋ የሚያደርግ መሆኑንን ይገልፃል፡፡ ተማሪዎችም በዚህ ህገ ወጥ ተግባር ሳይደናገጡ ያለምንም ፍርሃት ህጋዊ በሆነ መንገድ ይህን ካድሬያዊ ስልጠና በማውገዝ፣ የገዢውን ፓርቲ ድብቅ ሴራ በማጋለጥ እና ለህወሓት/ኢህአዴግ የተለመደ አጥፊ ፕሮፖጋንዳ ባለመታለል ተማሪዎች በአንድነት እንዲቆሙ ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
ነሀሴ 15/2006 ዓ.ም
ሰማያዊ ፓርቲ
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ሐይላትን ለመሸምገል የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ)የሚያደርገዉ ጥረት ጦርነቱን ሙሉ በሙሉ ለማስቆም እስካሁን ያስገኘዉ ተጨባጭ ዉጤት የለም። በፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር በሚመራው በመንግሥት ጦር እና በቀድሞው ምክትል ፕሬዝደንት በሪያክ ማቻር በሚመራው አማፂ ሐይል

ነሃሴ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ” የመንግስትን ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን ለከፍተኛ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ማስተዋወቅ” በሚል የጀመረው  ስልጠና በወሎ ዩኒቨርስቲ በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ ተማሪዎች በአገሪቱ ውስጥ የሚታዩ በርካታ ችግሮችን እያነሱ ጥያቄዎችን እየጠየቁና አስተያየቶችንም እየሰጡ ነው። በወሎ ዩኒቨርስቲ በመካሄድ ላይ ባለው ስልጠና ተማሪዎች ኢህአዴግ እራሱን ከቀድሞ ስርአቶች ጋር ማወዳዳሩን እንዲያቆም ጠይቀዋል። ቀድሞ ስርአቶች ያልተማሩ በመሆናቸው …

ነሃሴ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየወረዳዎች የተለጠፉት ማስታወቂያዎች ” በተለያዩ ጊዜያት በአገር መከላከያ ሰራዊት ስታገለግሉ የነበሩና በተለያዩ ጊዜያት ወደ ወረዳችን የተመለሳችሁ የሰራዊት አባላት በሙሉ የወረዳው አስተዳደርና ጸጥታ ጽ/ቤት ለመዝግባ ስለሚፈልጋችሁ እስከ ነሃሴ 21 እየቀረባችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን” ይላሉ። ማስታወቂያዎቹን ለማውጣት ለምን እንዳስፈለገ ግልጽ ባይሆንም፣ መከላከያን እየከዱ የሚጠፉ የሰራዊት አባላት በመበራከታቸውና አዳዲስ ተመልማዮችም በመጥፋታቸው ምናልባትም …

ነሃሴ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዛሬውዕለት 2ኛሙትዓመታቸውበመታሰብላይየሚገኙትየቀድሞጠ/ሚኒስትርእናየኢህአዴግሊቀመንበር አቶ መለስ ዜናዊ ራዕያቸውን ለማስቀጠል ይረዳል በሚል መጋቢት 28 ቀን 2005 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ የመለስ ፋውንዴሽን ምስረታ በይፋ ከተበሰረ በኋላበሕዝብየሚጎበኝመናፈሻእናደረጃውንየጠበቀቤተመጻህፍትለመገንባት፣ለችግረኞችነጻየትምህርትዕድልለመስጠትየሚያስችልህንጻለመገንባት ሕዝቡገንዘብ እንዲዋያጣበቴሌቭዥን፣በራዲዮእናበጋዜጣለበርካታወራትተከታታይቅስቀሳሲደረግ ቆይቷል። ለጉዳዩቅርበትያላቸውምንጮችእንደጠቆሙትሕዝቡበተለይምየመንግሥትሠራተኛውእምቢታውንበተግባርካሳየበኋላሠራተኛውየአባይግድብን መዋጮስላለበትለ ጊዜውለመለስፋውንዴሽንተጨማሪመዋጮመጠየቅእንዲቆምከበላይአካላትትዕዛዝበመተላለፉማስታወቂውምበመንግሥት መገናኛብዙሃንመተላለፉ እንዲቆምመደረጉንአስታውሰዋል፡፡አንድበመንግሥትሥራላይየሚገኙባለሙያለዘጋቢያችንእንደተናገሩትየመንግሥትሠራተኛው ከአነስተኛደመወዙለአባይግድብ እየተቆረጠመሆኑንአስታውሰውየመለስፋውንዴሽንዕርዳታጥያቄበመ/ቤታችንበመጣጊዜሁሉምሠራተኛበአንድድምጽ «አሁንስአልበዛምወይ» ሲልምሬቱንና ቁጣውንበመግለጹየመ/ቤቱአመራሮችክፉኛበመደናገጥዳግምጥያቄውንሳያነሱመቅረታቸውንአስታውሰዋል፡፡ “ሠራተኛውበከፋየኑሮውድነትእየተገረፈ፣በዚህላይ ደግሞለቦንድግዥወዶም፣ሳይወድምደመወዙእየተቆረጠባለበትበዚህወቅትሌላዙርመዋጮጨርሶ የሚሰማበትጆሮ፣የሚሸከምበትትከሻየለውም፣በዚህምክንያትመዋጮየመሰብሰብዕቅዳቸውድጋፍአላገኘም”ሲሉተናግረዋል፡፡ ፋውንዴሽኑመጋቢት 28 ቀን 2005 ዓ.ምበተመሰረተበትዕለትማምሻውንበሸራተንሆቴልበተካሄደየገንዘብማሰባሰብሥነሥርዓትባለሃብቶችንናየጎረቤትአገራትን ድጋፍሳይጨምርከክልሎችብቻከ74 ሚሊየንብርበላይመሰብሰቡይታወሳል፡፡ በወ/ሮአዜብመስፍንየሚመራውፋውንዴሽኑከተመሠረተአንድዓመትተኩልገደማቢያስቆጥርምእስካሁንገንዘብከመሰብሰብ፣የመሠረትድንጋይከማስቀመጥናችግኝ ከመትከልየዘለለሥራአለማከናወኑን  …

ሳይንስ በአመዛኙ ለሰዎች የተሻሻለ ኑሮ በጅቷል ወይም በረከት ሆኗል ቢባልም በአንዳንድ ረገድ የርግማን ያህል የሚታይበት እንዳልታጣ የታወቀ ነው። ይህ የሆነው ግን በመሠረቱ፣ ምርምሩ፣ የፈጠራው ውጤት ፤ ግኝቱ ፣ መጥፎ

ነሃሴ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጹት  የገዢውመደብየፓርቲአባላትእናአመራሮች ቀድም ብሎ የግቢውንጽዳት ሲያከናውኑ የነበረውን ድርጅት በማባረር እና የራሳቸውን ድርጅት በማቋቋም ከዚህ ቀደም በወርይከፈልከነበረው 150 ሽህብርላይ 350 ሺህብርበመጨመርዩንቨርስቲውለጽዳት ብቻበየወሩከ500 ሺህብርበላይእንዲያወጣበማድረግበአራትወርውስጥ 1.4ሚሊዮንብርለግልጥቅማቸውአውለዋል። በዚህግቢውስጥየሚሰራውጽዳትስራከመጀመሪያዎቹስምንትወራትጀምሮ ውል ተቀብሎሲሰራበቆየውድርጅትእናአሁንበዩንቨርስቲውአመራሮችየሚሰራውስራምንም ዓይነትልዩነትአለመታየቱን ፣ በፊትምምንምዓይነትየጽዳትጉደለትእንዳላዩበማጽዳትስራውላይተሰማርተውበመስራትላይያሉሰራተኞች፣ፕሮክተሮችእናተማሪዎች በተደረገላቸውቃለመጠየቅተናግረዋል፡፡ በማጽዳትስራውያሉተቀጣሪሰራተኞች፣ፕሮክተሮችእናተማሪዎችየተከሰተውስራአሳዛኝእናሆንተብሎየራስን ጥቅም ለማጋበስ የታሰበበትመሆኑንተናግረዋል፡፡ በጽዳትስራውምንምዓይነትየአደረጃጀትምሆነጽዳትዕቃዎች  የአቅርቦትልዩነትሳይኖርይህንየተጋነነክፍያተመካክረውበመውሰድ የጽዳትስራውንሲሰራየነበረውንድርጅትከጨዋታውጭበማድረግለኪሳራመዳረጋቸውትክክል አለመሆኑን   ተናግረዋል፡፡ ስማቸውንመግለጽያልፈለጉየዩኒቨርስቲውነባርየአስተዳደርሰራተኞችእንደተናገሩትጉዳዩለዩኒቨርስቲውከፍተኛአመራሮችበተደጋጋሚቀርቦላቸው  ነገዛሬ በሚልቸልበማለትችግሩንሳይፈቱትየበጀትአመቱመጠናቀቁ፣  ሆንተብሎየተወሰኑግለሰቦችእንዲጠቀሙየተተወየአደባባይሚስጥርመሆኑን መታዘባቸውንና በዩኒቨርስቲው ከፍተኛአመራሮችአሰራርማፈራቸውንበምሬትተናግረዋል፡፡ …

በዩናይትድ ስቴትስዋ የሚዙሪ ግዛትበምትገኘው በፈርግሰን ከተማ አንድ ጥቁር ወጣት በነጭ ፖሊስ ከተገደለ በኋላ የተነሳው ተቃውሞ አሁንም አልቆመም ። ትናንት ማታም ተቃዋሚዎች በፖሊስ ላይ ጥቃት መሰንዘራቸው ተሰምቷል ። ትንናት ማታ ተቃዋሚዎች ውሃና ሽንት የያዙ ፕላስቲኮች ወደ ፖሊስ መወርወራቸውን ፓሊስ አስታውቋል ።

አገሩን እና ሕዝቡን የሚወድ ። እንደ ሌሎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን፣ ኢትዮጵያ ከግፍ አገዛዝ ተላቃ ዜጎች መብታቸዉና ነጻነታቸው ተጠበቆ፣ ተከባብረዉ በስላም የሚኖሩባት አገር እንድትሆን፣ የሚያደርጉትን ትግል የተቀላቀለ ነው። ወጣት ነው። ጉልበትና አቅም አለው። እንደ አንዳንዶች በጥቅም ተታሎ አደርባይነትን መምረጥ ይችል ነበር። ነገር ግን አላደረገዉም። «ሰዉ ያለ ነጻነቱ ምንድን ነው ? » ብሎ ለነጻነቱ ቆመ። የባለ ራእዩ […]

በስዊድን፣ ስቶክሆልም የደብረ ታቦር በዓል ተከበረ በመድኃኒዓም ቤተክርስቲያን ሲከበር፣ ማክሰኞ ሐምሌ 13 ቀን 2006 ዓ.ም. Demera in Stockholm, Sweden

Ethiopia Zare (ረቡዕ ሐምሌ 14 ቀን 2006 ዓ.ም. August 20, 2014)፡- በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም በሚገኘው የደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን የደብረታቦር በዓል ሁኔታ በትናንትናው ዕለት በደማቅ ተከበረ። ጸሎትና የትምህርቱ በኃይማኖት አባቶች ለምዕመናኑ ከተሰጠ በኋላ፣ ከምሽቱ አንድ ሰዓት (13፡00 ሰዓት) ላይ የበዓሉ መገለጫ የሆነ ችቦ በርቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

#Ethiopia #FreeZone9bloggers #FreeEdom #FreeTesfalem #FreeAsemamaw 

የልደታ ፍርድ ቤት 19 ወንጀል ችሎት የዞን9 ጦማርያኑን እና የጋዜጠኞቹን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አደረገ 

ስድስቱን የዞን ዘጠኝ አባላት ማለትም በፍቃዱ ኃይሉ፣ አቤል ዋበላ፣ ማኅሌት ታሁን፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ዘላለም ክብረት እና አጥናፍ ብርሃነ እንዲሁም በሌለችበት ክሷ እየታየ ያለው በሶልያና ሽመልስ እንዲሁም በጋዜጠኞቹ ኤዶም ካሳዬ፣ ተስፋለም ወልደየስ እና አስማማው /ጊዮርጊስ በልደታ 19ኛው የወንጀል ችሎት ዛሬ ጠዋት የተሰየመ ሲሆን ከሙስሊም ኮሚቴ አመራሮች ጋር በአንድ ችሎት እንዲታደሙ በመደረጉ የታሳሪዎችን ቤተሰቦችም ሆነ ወዳጆችን ለማስተናገድ ቦታ የለም በሚል ለጋዜጠኞች ብቻ የፍርድ ሂደቱ እንዲታይ በፖሊስ ተፈቅዶ ነበር፡፡

በሌለችበት የተከሰሰችው ሶልያና ሽመልስ መጥሪያ በጋዜጣ መውጣቱን ፍርድ ቤቱ ያረጋገጠ ሲሆን የዋስትና መብትን በተመለከተ በዛሬው ዕለት ተሰይሞ የነበረው ችሎት በጸረ ሽብር አዋጁ መሰረት በአንቀጽ 3 የሽብር ተግባራት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ አንድም ወይም ሁለትም ከዚያም በላይ ወንጀል የፈጸመ መሆኑ ወይም ለመፈጸም ያቀደ ለመሆኑ ተገልጾ ክስ ሲቀርብ ነው በተመሰረተባቸው ክስ ዋስትናን ሊያሳጣቸው የሚችለው ብለው ጠበቆቻቸው የተከራከሩ ሲሆን ደንበኞቻቸው በአዋጁ መሰረት የሰሩት የሽብር ተግባር ክስ አልቀረበባቸውም ስለዚህ በአዋጁ ተጠቀሰ ማለት በአዋጁ መሰረት ክስ ቀርቧል ማለት ስለማይቻል የዋስትናው ጥያቄ በመደበኛ ስርዓት እንጂ በጸረሽብር ሕጉ መሰረት ሊታይ አይገባም፤ በተጨማሪም አዋጁ ዋስትና ይከለክላል ተብሎ ቢተረጎምም ከሕገመንግስቱ ጋር ስለሚጋጭ ዋስትና ሊፈቀድላቸው ይገባል ቢሉም፤ ፍርድ ቤቱ አንቀጽ ተጠቅሶ መከሰሳቸውን እንጂ በዚህ መከሰስ ነበረባቸው ወይም አልነበረባቸውም ብሎ ለማየት ፍርድ ቤቱ አይገደድም እንዲሁም የጸረሽብር አዋጁ ከሕገመንግስቱ ጋር አይጋጭም ብለዋል በዚሁም መሰረት የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ ተደርጎ ለጥቅምት 5 ቀን2007. ቀጠሮ በመስጠት የዛሬው ችሎት የተጠናቀቀ ሲሆን ጠበቆቻቸውም የዋስትና ጉዳይ በተመለከተ ለጠቅላይ ፍረድ ቤት ይግባኝ እንደሚያቀርቡም ታውቋል፡፡

ችሎት ውስጥ መግባት የቻሉት ጥቂት ጋዜጠኞች እና ጉዳዩን ለመታዘብ የተገኙ ዲፕሎማቶች ብቻ ናቸው፡፡

በቦታው በመገኘት አጋርነታችሁን ላሳያችሁ ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋናችን ይድረሳችሁ፡፡

ባለፈዉ ሰሞን ቻይና አፍሪካ ዉስጥ ሰላሳ አመት በማይሞላ ግዜ ዉስጥ ያደረገችዉ የኤኮኖሚና የፖለቲካ መስፋፋት ያሳሰባቸዉ የአሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ምነዉ ምን አድረግናችሁና ነዉ ፊታችሁን ያዞራችሁብን ብለዉ ለመጠየቅ በርከት ያሉ የአፍሪካ መሪዎችን ቤተ መንግስታቸዉ ድረስ ጋብዘዋቸዉ ነበር። በዚህ የሃሳብ ልዉዉጥ፤ ምክር፤ የእራት ግብዣና የዋሺንግተን ዲሲን ጉብኝት ባጠቃለለዉ የፕሬዚዳንት ኦባማ ድግስ ላይ በመልካም የዲሞክራሲ ጅምራቸዉ የሚወደሱት የጋናና […]

በቅድሚያ የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን፤ “እንኳን ለመጪው የ2007 አዲስ ዓመት በዓል በሰላም አደረስዎ!!“ እያልን ይህንንው የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት በዓል አስመልከቶ በቦስተን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያኖች በጋራ፤ በዓሉን በጨዋና በኢትዮጵያዊነት መንፈስ በደመቀ ሁኔታ በየአመቱ እንደሚያከበሩ ይታወቃል። በዚሁ መሰረት የዘንድሮውን የ2007 ዓ. ም. የአዲስ ዓመት በዓልን በደመቀ ሁኔታ ሁሉም ኢትዮጵያውያኖች፤ በዘር፤ በሃይማኖት፤ በፖለቲካ፤ በጾታ ሳይከፋፈሉ በሕብረት ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን እያስታዋሱ […]

ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለፖሊስ ከፍተኛ አዛዦች በኮልፌ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ከተጠናቀቀ በሁዋላ መደበኛ ፖሊሶች ደግሞ በተለያዩ የማሰልጠኛ ቦታዎች በግዳጅ ገብተው ስለመንግስት ፖሊሲና እቅድ ስልጠና እየተሰጣቸው ነው። በኮልፌ በአዛዥ ፖሊሶች ሲጠየቁ የነበሩት ጥያቄዎች በመደበኛ ፖሊሶች ተጠናክረው መቅረባቸው ታውቋል። ከትናንት ጀምሮ በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ግንቦት 20 እየተባለ በሚጠራው ትምህርት ቤት ውስጥ 500 …

ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የምስራቅ ኢትዮጵያ ወኪል እንደዘገበው በምስራቅ ሃረርጌ ኦሮምያ ቆላማ ክፍል በሚገኙ ግራዋ ወረዳ ቡርቃ ቀበሌ፣ ፈዲስ ፣ ሚዲጋ እና  ሚደጋ ቶላ ወረዳዎች የተከሰተው ረሃብ አፋጣኝ እርምጃ ካልተወሰደ በስተቀር ህዝቡን ለስደት ሊያደርገው ይችላል። ባለፈው እሁድ 50 የሚሆኑ የወረዳው ህዝብ ተወካዮች ሀረር ከተማ በመግባት አቤቱታቸውን ያሰሙ ሲሆን፣ ተወካዮቹ ህዝቡ አንድ …

ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ዘጋቢ በቦታው ተገኝቶ ያነሳቸው ፎቶዎች  ወታደሮች ከመቃብሩ ፊት ለፊት ተቀምጠው ሲጠብቁ ያሳያል። መቃብሩ ለምን መጠበቅ እንዳስፈለገ ግልጽ የሆነ ነገር የለም። የአንድ ሰው መቃብር በወታደሮች በእየቀኑ እንዲጠበቅ ሲደርግ ይህ በአለም ታሪክ የመጀመሪያው ሳይሆን አይቀርም በማለት ዘጋቢያችን አስተያየቱን ገልጿል።  የመለስ 2ኛ የሙት አመት በመላ አገሪቱ በሚገኙ የኢህአዴግ ደጋፊዎች ዘንድ …

ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በጋሞ ጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ ከታሰሩ በርካታ ወራትን ያስቆጠሩት የአገር ሽማግሌዎች ፍትህ አጥተው እየተሰቃዩ መሆኑን ገልጸዋል። የአገር ሽማግሌዎቹ የወረዳ  እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በማንሳታቸው እና የጸጥታ ሃይሎች የሃይል እርምጃ መውሰዳቸውን ለጠ/ሚኒስትሩና ለሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በማመልከታቸው መታሰራቸው ይታውቃል። ከ400 ያማያንሱት እስረኞች ዛሬ ነገ እንፈታለን ብለው ተስፋ …

ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ከደቡብ ሱዳን ተይዘው ወደ ኢትዮጵያ ያለፈቃዳቸው እንዲላኩ የተደረጉት የቀድሞው የጋምቤላ መሪ አቶ ኦኬሎ አኳይ እና ሌሎች ስድስት ተከሳሾች መንግስት ያቀረበባቸውን የሽብርተኝነት ክስ በማስተባባል የመቃወሚያ መልስ ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ መቃወሚያቸውን ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ የክስ መቃወሚያውን ወድቅ ማድረጉን ተከትሎ የጥፋተኝነት ቃላቸውን እንዲሰጡ የታዘዙት እስረኞቹ፣ አቃቢ ህግ የመሰረተባቸውን ክስ …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

እስከከዛሬ ከ1,100 ሰዎች በላይ ሕይወት ያጠፋው እና ምልክቱም ከ2,100 በሚበልጡ ሰዎች ላይ የታየው የኤቦላ በሽታ የብዙዎቹን የምዕራብ አፍሪቃ ሀገራት መንግሥታትን አሳስቦዋል። ኤቦላ ወደየሀገሮቻቸው እንዳይዛመት የሰጉት ሀገራት ያየር ማረፊያዎቻቸውን እና ወደቦቻቸውን በሽታው ከተከሰተባቸው ሀገራት ለሚመጡ መንገደኞች ዘግተዋል።

በዓለማችን ከአራት ሰዎች አንዱ በህይወት ዘመኑ አንዴ የአእምሮ ወይም የስርዓተ ነርቭ መዛባት ሊያጋጥመዉ እንደሚችል የዓለም የጤና ድርጅት ያመለክታል። ለችግሩ የሚሆነዉ ህክምና ቢኖርም ፍፁም ባለማወቅ ወይም በቸልተኝነት የሚጠቀምበት እንደሌለ ነዉ ድርጅቱ የሚያመለክተዉ።

ሐምሌ 11/2006 ዓ.ም. በአንዋር መስጊድ በተፈጠረው ግጭት ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወ/ሪት ወይንሸት ሞላና የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ፎቶ ጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድን በዋስ ተፈተዋል።

የጀርመን ፊደራል የስለላ መሥሪያ ቤት ቱርክን ሲሰልል ቆይቷል የቀድሞዋንና የአሁኑን የአሜሪካን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስልኮች ጠልፏል መባሉ ማነጋገሩን ቀጥሏል ። የጀርመን ፖለቲከኞች እስካሁን በጉዳዩ ላይ ምንም ያልተናገረው የሐገሪቱ መንግስት ማብራሪያ እንዲሰጥ ግፊት እያደረጉ ነው ።

በዓለማችን ከአራት ሰዎች አንዱ በህይወት ዘመኑ አንዴ የአእምሮ ወይም የስርዓተ ነርቭ መዛባት ሊያጋጥመዉ እንደሚችል የዓለም የጤና ድርጅት ያመለክታል። ለችግሩ የሚሆነዉ ህክምና ቢኖርም ፍፁም ባለማወቅ ወይም በቸልተኝነት የሚጠቀምበት እንደሌለ ነዉ ድርጅቱ የሚያመለክተዉ።

በግጭት ጦርነት እንዲሁም በተፈጥሮ አደጋዎች ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን ለመርዳት የተሠማሩ ወገኖች ተግባር ማለትም ሰብዓዊነት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የሚታሰብበት ዕለት ነዉ ዛሬ። ለሰብዓዊ ተግባራት ተሠማርተዉ ለተለያዩ አደጋዎች ተጋልጠዉ ህይወታቸዉን የሚያጡ ወገኖች ዛሬ ዛሬ ቁጥራቸዉ እየጨመረ ነዉ።

15 ቱ የደቡባዊ አፍሪቃ መንግሥታት የልማት ትብብር ድርጅት፣ በምኅፃሩ የ«ሳዴክ» መሪዎች ያካባቢያቸውን የኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማስፋፋት ተስማሙ። የኢንዱስትሪው ዘርፍ በ«ሳዴክ» የትብብር አጀንዳ ውስጥ ዓቢይ ሚና ሊኖረው እንደሚገባ ርዕሳነ ብሔራቱ ትናንት በዚምባብዌ የሁለት ቀናት ጉባያቸውን ባጠናቀቁበት ጊዜ አስታውቀዋል።