ነሃሴ ፳፪(ሃያሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግብጽ ጋዜጦች እንደዘገቡት ኢትዮጵያ ለወራት ውድቅ ስታደርገው የነበረውን ስምምነት ከግብጽ ጋር ተፈራርማለች። አዲሱ ስምምነት የአባይ ግድብ ግንባታ በውጭ አገር ገለልተኛ አጥኚዎች እንዲጠናና ኢትዮጵያም የጥናቱን ውጤት እንድታከብር የሚያስገድድ ነው። በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ሲደራደሩ የቆዩት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑ ከወራት በፊት ሱዳን ላይ ተካሂዶ በነበረው የሰላም ስምምነት ላይ ግብጽ …

ነሃሴ ፳፪(ሃያሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደሚሉት በመቀሌ፣ ባህር ዳርና በተለያዩ የጤና ተቋማት የሚሰሩ ሙያተኞች መንግስት በቅርቡ ያደረገው የደሞዝ ጭማሪ ሙያችንን ግምት ውስጥ ያስገባ አይደለም በማለት ስራቸውን እየሰሩ ቀይ ሪባን በመልበስ ተቃውሞ እንደሚጀምሩ ታውቋል።ዲፕሎማ እንዳላቸው የሚገልጹት ሰራተኞች መንግስት የስራ ዝርዝራቸውን ለይቶ እንዲያስቀምጥላቸውም ይጠይቃሉ። በሀረር ከተማ ደግሞ ከ400 ያላነሱ በጽዳት ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች …

ነሃሴ ፳፪(ሃያሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮ- ቴሌኮም በአዲስ አበባ የኢንተርኔት አገልግሎትን በማሳደግ የ4ጂ አገልግሎት መስጠት የሚችልበትደረጃደርሻለሁቢልምየአገልግሎቱጥራት በከፍተኛደረጃእየወደቀመምጣቱተጠቃሚዎችበከፍተኛደረጃምሬትውስጥእየከተተነው፡፡ በ1 ነጥብ 6 ቢሊየንዶላርወጪየቻይናዎቹሁዋዌእናዜድቲኢየሚባሉኩባንያዎችየማስፋፋፊያውንፕሮጀክትለመስራትከኢትዮቴሎኮምጋር በዚህዓመትመጀመሪያየተፈራረሙሲሆንየአዲስአበባውፕሮጀክትእስከሰኔወር 2006 ዓ.ምመጨረሻተጠናቆየተሻለአገልግሎትመስጠት ይጀምራልተብሎነበር፡፡ ኢትዮቴሌኮምየማስፋፊያፕሮጀክቱበስኬትተጠናቋልበሚልተደጋጋሚመግለጫየሰጠሲሆንነገርግንበአሁኑወቅትየሞባይልሒሳብለመሙላትና ቀሪሒሳብለመጠየቅአለመቻል፣የፈለጉትንሰውበቀላሉደውሎማግኘትአለመቻል፣ያልደወሉበትሒሳብ መቆረጥ፣የሞባይልኢንተርኔትበተለይፈጣንነውየተባለውን 3ጂጨምሮደካማመሆን፣  የፌስቡክአካውንትአለመከፈት፣የገመድአልባኢንተርኔትና ብሮድባንድኢንተርኔትአገልግሎትመቆራረጥናደካማመሆንበስፋትእየታየነው፡፡ ያነጋገርናቸውተጠቃሚዎችየአፍሪካህብረትናየሌሎችዓለምአቀፍተቋማትየሆነችውአዲስአበባጥራትያለውየሞባይልናኢንተርኔትአገልግሎት ብርቋመሆኑእንደሚያሳዝናቸውተናግረዋል፡፡አንድአስተያየትሰጪእንዳሉትኢትዮቴሌኮምየተሻለማስፋፊያአድርጌለሁእያለበተግባርይህ አለመታየቱምናልባትምመንግሥትበተለይበማህበራዊ ድረገጾችእየተሰነዘረበትያለውንጠንካራተቃውሞናትችትለማፈንየተጠቀመበትአዲስዘዴሊሆንይችላልየሚልጥርጣሬእንደገባውተናግሮአል፡፡ የኢንተርኔትኔትወርክእንደመብራትብልጭድርግምእያለብዙዎችበመበሳጨት አገልግሎቱንእየተውነውያለውአስተያየትሰጪያችንመንግሥት በዚህሒደትከሚያጣውገንዘብይልቅተቃዋሚዎቹን ለማፈንትልቅግምትሳይሰጠውእንዳልቀረአስረድቷል፡፡

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የዓለም አቀፉ የ «ጋዝፕሮም » ኩባንያ ባንክ (GPB Global)በሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ በአፋር መስተዳድር፤ ነዳጅ ዘይ ት ለመፈለግ ከአንድ ወር ገደማ በፊት ውል መፈራረሙ ተመልክቷል።በኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጋዝና ነዳጅ ዘይት አሳሽ ኩባንያዎች፣ እስካሁን

ሚንስትሩ ግብፅ ኮሚቴዉ እንዲስየም ተስማማች ማለት «የግድቡን ግንባታ በይፋ ተቀበለች ማለት አይደለም» በማለት አጠቃላይ ዉዝግቡን ለማስወገድ ሰወስቱ ሀገራት አሁንም ብዙ መራቃቸዉን አልሸሸጉም።

ካለፈው ግንቦት ወር ጀምሮ በዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ማኅበር አዘጋጅነት በተለያዩ ከተሞች በመካሄድ ላይ ያለው የዳይመንድስ ሊግ ዛሬ ምሽት በስዊትዘርላንድ የዙሪኽ ከተማ በሚደረጉ ውድድሮች ይፈፀማል።

የሩዋንዳ ከፍተኛ ባለስልጣናት በያዝነዉ ሳምንት መጀመርያ ለእስር ተዳርገዋል፤ በርካታ ሰዎችም ያሉበት ቦታ አይታወቅም። የደረሱበት እስካሁን ያልታወቁት ዜጎች ከመንግሥት ተቃዋሚ ወገን ብቻ ሳይሆን፤ ከደጋፊዎችም በኩል መሆኑ ተመልክቶአል። በዚህም ምክንያት የፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ የአገዛዛዊ መንግሥት ሃገሪቱን ሥጋት ላይ መጣሉ እየተነገረ ነዉ።

መንግሥት በአንዳንድ የግል ጋዜጦች ላይ ክስ ከመሠረተ እና ባለፈው ግንቦትም ዘጠኝ ጋዜጠኞች እና የድረ ገፅ አምደኞች ከታሰሩ ወዲህ ቁጥራቸው ትንሽ የማይባል ጋዜጠኞች ኢትዮጵያን ለቀው ወጥተዋል።

ቡሄን አስታከን ሆያ ሆዬን ይዘን ብቅ ያልነዉ ዘግየት ብለን ቢሆንም፤ እንደ ባህላችን አዲስ ዓመት ጠብቶ መስቀል በዓል እስኪከበር ሆያሆዬን መጨፈራችን የታወቀ ነዉና፤ ዛሬም ጀርመናዉያኑ ሆያ ሆዬ ባስጨፈሩበት የኢትዮጵያ ባህላዊ የቡሄ ዜማ የዕለቱን ዝግጅት ለመጀመር ወሰን። ሆያሆዬ ያስጨፈሩት ጀርመናዉያኑ የሙዚቃ ባንድ ካሪቡኒ አዲስ ይባላል።

የጀርመን መንግሥት ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ስደተኞች የምግብ ርዳታ አቅርቦት የሚውል 750,000 ዩሮ ርዳታ ሰጠ። በአፍሪቃ ስደተኞችን በማስተናገድ ረገድ በወቅቱ የአንደኛውን ደረጃ የያዘችው ኢትዮጵያ ገንዘቡ ለሚቀጥሉት አራት ወራት የሚያስፈልገውን ምግብ ለማቅረቢያ እንደምታውለው የጀርመን ኤምባሲ አስታውቋል።

በጥፍሩም በጥርሱም ለስልጣኑ የሚተጋን መንግስት በሁሉን አቀፍ ትግል መጣል አለብን ብለው ጠብ መንጃ ቢያነሱ ክፋቱ ምን ላይ እንደሆነ አልታይህም እያለኝ ነው፡፡ ለምን በጠብ መንጃ ፍልሚያ ስልጣን መያዝ እንዳለብኝ በግሌ ባይገባኝም አሁን ግን የኢህአዴግ ዓይነት መንግሰት ከደርግ እንዴት እንደሚሻል ማሰብ እያቃተኝ ነው፡፡ የሰላማዊ ትግል ሰራዊት እንዴት እንገንባ ለሚለው ጥያቄ አፋጣኝ ምለሽ ካልሰጠን በስተቀር መንግሰት በግልፅ እየደገፈ […]

ስለ ብሔራዊ እርቅና መግባባት ጉዳይ አጠር ምጥን ተደርጎ የተዘጋጀውን ባለ አምስት ነጥብ የዳሰሳ ጥናት (survey) ለዚሁ ጉዳይ ሲባል ብቻ ወደ ተዘጋጀው ድህረ ገፅ www.MyEthiopia.com በመሄድ ድምፅዎን ያሰሙ። የዝምተኛው ብዙሃን ድምፅ ጭምር ሳይቀር እስቲ ይሰማ! ፖለቲካውንና ፍልስፍናውን አርባ አመት አውጠንጥነን አረጀንበት። እንዲሁ ስንባዝን እድሜያችን አልቆ አንድ ባንድ ወደ ሞት ልንሄድ ነው። እርቅና መግባባትን ማን ጠላ? መላው […]

ዋና መቀመጫቸው አስመራ የሆኑ ፣ ሕወሃት/ኢሕአዴግን በኋይል ለማስወገድ እንቀሳቀሳለን የሚሉ ሶስት ድርጅቶች ለመዋሃድ እንደተስማሙ በጋራ ባወጡት መግለጫ ገለጹ። የትጥቅ ትግል እናደርጋለን የሚሉ ድርጅቶች ይሄን አይነት ስምምነት ሲያደርጉ በአይነቱ የመጀመሪያ እንደሆነ ይነገራል። እንደተባለውም ስምምነቱ በተግባር ዉሎ ድርጅቶቹ ከተዋሃዱ፣ በዚያ አካባቢ ለሚደረገዉ የትጥቅ ትግል ትልቅ እድምታ ሊኖረው እንደሚችል የሚናገሩ ጥቂቶች አይደሉም። የድርጅቶቹን መግለጫ እንደሚከተለው አቅርበናል፡ ================================================ የወያኔን […]

ዝሆኖች ለቤተሰባዊ ሕይወት ልዩ ቦታ አላቸው፡፡ የዝሆን መንጋ በእናት የሚመራ ነው፡፡ የሰው ልጅ ሴቶችን ወደ መሪነት ሳያመጣ፣ እነ ንግሥተ ሳባና ንግሥት ሕንደኬም ሀገር ሳይመሩ በፊት ዝሆኖች የእናቶችን መሪነት ተቀብለዋል፡፡ በዝሆኖች መንጋ ውስጥ ታላቅ መሆን ክብርንም ያመጣል ኃላፊነትንም ያስከትላል፡፡ እኛ ሀገር ብዙ ጊዜ ‹ታላቅነት› ክብርን ብቻ እንዲያመጣ ይታሰባል እንጂ ኃላፊነትን እንዲያስከትል አይፈለግም፡፡ በዝሆኖች ዘንድ ግን ታላቅ እናት ትከበራለችም፣ ኃላፊነት ትወስዳለችም፡፡

በማለዳ የዝሆኖች ውሎ ሲጀመር የዝሆን ቤተሰብ ለተግባር ሥምሪት ይወጣል፡፡ ብዙ ጊዜ አንድ ቤተሰብ ከ12 አባላት በላይ አይበልጥም፡፡ ይህም ልጆችንና የቅርብ ዘመዶችን ያካትታል፡፡ እናት ዝሆን ይህን ቤተሰብ በመምራት ወደ ምግብ ሥምሪት ስትነቃነቅ አመራርዋን የሚፈልጉ ሌሎች ዝሆኖች ይቀላቀሏታል፡፡ ወደ ረፋድ ላይ የመንጋው ቁጥር ወደ 25 ይደርሳል፡፡ ፀሐይ ልታቆለቁል ስታስፈራራ የመንጋው ቁጥር ወደ አንድ መቶ ያሻቅባል፡፡ ሲመሽ የመንጋው ቁጥር እየቀነሰና ሁሉም በየቤቱ እየገባ ይሄድና ወደ ቀደመው አሥራ ሁለት የቤተሰብ አባላት ይመለሳል፡፡ ይህ ሁሉ የሚመራው በአንዲት አረጋዊት ታላቅ እናት ነው፡፡

አንዳንድ የዝሆንን ጠባይ ያጠኑ ሊቃውንት ይህንን የዝሆኖች የዕለት ጉዞ ከሰዎች የዕለት ጉዞ ጋር አያይዘው አይተውታል፡፡ በየማለዳው ኑሮን ስንወጥን የምንጀምረው ከቤተሰባችን ነው፡፡ ወጣ ብለን ሠፈርተኛውን እናገኛለን፤ በመንገዳችንና በሥራ ቦታችን ደግሞ ከከተማው ነዋሪ፣ ከደንበኞች፣ ከሻጮች፣ ከተማሪዎች፣ ከገበያተኞች፣ ከተሳፋሪዎችና ከሌሎቹም ጋር እየተቀላቀልን ቁጥራችን እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ፀሐይ ወደ ማደሪያዋ ልትገባ ስትል በሄድንበት መንገድ ወደ ኋላ በመመለስ ቁጥራችን እየቀነሰ ይመጣና የመጨረሻ ማረፊያችን ቤተሰባችን ይሆናል፡፡


በዝሆኖች ላይ ጥናት ያደረጉ ሊቃውንት ለመሪነት የምትመረጠው ታላቅ እናት ሁለት ዋና ዋና ብቃቶች እንዳሏት አስተውለዋል፡፡ ጽናትና ችግርን የመፍታት ብቃት፡፡ ባለሞያዎቹ ‹ጽናት› ሲሉ ‹‹ችግርን የመቋቋም ችሎታ፣ ከፈተና ለመውጣት መንገዶችን የመተለም ዐቅም፣ ከችግር በአፋጣኝ ወጥቶ በአስቸኳይ ወደ ነበሩበት ጤናማ ሁኔታ ለመመለስ መቻልና ሳይረበሹ፣ ሳይደናገጡና ተስፋ ሳይቆርጡ ከችግሮች በኋላ አመራርን በብስለት ለመቀጠል መቻል› ማለታቸው ነው፡፡ የሀገራችንን የመልካም አስተዳደር እጦት ችግር ለመፍታትም እነዚህ ሁለቱ ችሎታዎች ያሏቸውን መሪዎች መመደብ ሳይኖርብ አይቀርም፡፡ ችግር ፈጣሪዎችን ሳይሆን ችግር ፈችዎችን፡፡ በሚከሰቱ ነገሮች ተደናግጠው መሥመራቸውን የሚስቱትን ሳይሆን ማዕበሉን ተቋቁመው ወደ ጥንት ግብራቸው ለመመለስ ዐቅም ያላቸውን፡፡

የዝሆንን መንጋ የምትመራው ታላቅ እናት እንዲሁ አትመረጥም፡፡ ሊመጣ የሚችለውን አደጋ ቀድማ የመገመት፣ የተሻለውን የምግብ ማግኛ ቦታ የማወቅ፣ ለግልገል ዝሆኖች ልምዷን የማካፈል፣ አስቸጋሪ ዝሆኖችን ሊታረሙ በሚችሉበት መንገድ የመቅጣት የካበተ ልምድ ያላት ናት፡፡ ብዙ ጊዜ መሪ እናቶች በጠባያቸው ጭምቶች፣ የተረጋጉ፣ ከግንፍልተኛነት የጸዱ እንደሆኑ ጥናቶቹ አሳይተዋል፡፡ የሚያስቆጡና ግብታዊ ርምጃ እንዲወሰድ የሚያስገድዱ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ እንኳን ቀድማ የኃይልና የጉልበት ርምጃ ለመውሰድ አትቸኩልም፡፡ መንጋውን ማረጋጋትና ችግሩ ሳይከሰት ከፈተናው የሚወጣበትን መንገድ ማመላከትን ታስቀድማች፡፡ ግልገሎቹ ሲያጠፉም ማረምን እንጂ መቅጣትን የመጀመሪያ ተግባሯ አታደርገውም፡፡

ዝሆን ቆዳው ጠንካራ ነው፡፡ አያሌ ቆንጥሮችን፣ እሾህና አሜከላዎችን፣ ቁጥቆጦዎችንና ጥሻዎችን ያቋርጣል፡፡ ቅጠሎችን ለማግኘት ወደ ዛፎቹ ሲንጠራራ ከተጎረዱ ቅርንጫፎችና ካገጠጡ ቅርፊቶች ጋር ይታገላል፡፡ ይህንን ሁሉ እንዲቋቋም ፈጣሪ ለዝሆን ደንዳና ቆዳ ሰጥቶታል፡፡ የዝሆን ቆዳ እስከ አንድ ኢንች የሚደርስ ውፍረት አለው፡፡ ይህ የቆዳ ውፍረት ለሁለት ነገሮች ጠቅሞታል፡፤ በአንድ በኩል በመቧጨርና በመጎንተል ከሚመጡበት አደጋዎች ለመቋቋም በሌላ በኩል ደግሞ በመንገዱ ላይ የሚገኙ ቆንጥሮች እሾሆች፣ ቁጥቋዎችና ጥሻዎች እዚህመ፣ እዚያም ለሚፈጥሩበት ውጋትና ቡጭረት ትኩረት ሳይሰጥ መንገዱን እንዲቀጥል፡፡


ሰው እንደ ዝሆን ቢሆን እንዴት መልካም ነበር፡፡ በመንገድ ላይ ለሚገኙት ቁጥቋጦዎች፣ ቡጭሪያዎችና ውጊያዎች ሁሉ ተበሳጭተን፣ አልቅሰን፣ ተናድደን፣ መልስ ሰጥተን እንዴት እንችለዋለን፡፡ ታማን፣ ተሰደብን፣ ስማችን ጠፋ፣ ተነካን፣ እያልን በየዕለቱ የምንንገበገብ ከሆነ ወደ ዓላማችን መድረስ እጅግ ከባድ ይሆንብናል፡፡ ለዋናው ግብ ሲባል አንዳንዱን ነገር መሻገር፣ አንዳንዱን ነገር ችሎ ማለፍ፣ አንዳንዱን ነገር እንዳላዩ መሆን፣ አንዳንዱንም ነገር ቁብ አለመስጠት ይገባል፡፡ አቡነ ጎርጎርዮስ ታላቁ ‹ሥራህን ሥራ፤ አንበሳው ሲያጓራ ፍንክች አትበል፤ የሰይጣንን ውሻዎች ለመውገር አትቁም፤ ጥንቸሎቹን በማባረር ጊዜህን አታጥፋ፤ ዝም ብለህ ሥራህን ሥራ› ሲሉ የመከሩት ለዚህ ሳይሆን አይቀርም፡፡

ዝሆኖች ወገኖቻቸውን አይረሱም፡፡ የሞቱ ወገኖቻቸውን ከማይረሱ ጥቂት እንስሳት መካከል ዝሆኖች አንዱ ናቸው፡፡ የሞተበትን አካባቢ በተደጋጋሚ ይጎበኙታል፡፡ አንድ ዝሆን ከመንጋው ተለይቶ ለብዙ ጊዜ ቆይቶ ቢመለስ ልዩ የሆነ የደስታ አቀባበል ይጠብቀዋል፡፡ ኩንቢያቸውን በማነካካትና በማጠላለፍ አገላብጠው ይስሙታል፡፡ ጤንነቱን በሚጠይቅ መልኩ የሚያወጡት የተለየ ድምጽም አላቸው፡፡ ፍቅርና ደኅንነት ተሰምቶት ከመንጋው ጋር እንደገና እንዲቀላቀል እንጂ እንዲገለል አያደርጉም፡፡ እንዲያውም ሰዎች በዚህ ረገድ ሲቸግረን ያታያል፡፡ አንድን ያጠፋ ሰው መልሶ ለመቀበል፤ አንድን የበደለንን ሰው ይቅር ብሎ እንደ ቀደመው ለመሆን፣ ወይም አንድን ከወኅኒ ታርሞ የመጣን ሰው ደኅና ነው ብሎ ለመቀበል ይቸግረናል፡፡

(ይቀጥላል)

ነሃሴ ፳፩(ሃያአንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የምስራቅ አፍሪካ የሰብአዊ መብቶች ሊግ ለኢሳት በላከው መግለጫ ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተጀመረውን የፖለቲካ ስልጠና ተከትሎ በአምቦ ዩኒቨርስቲ ከ100 በላይ  እንዲሁም ከወለጋ የኑቨርስቲ 5 ተማሪዎች ታፍነው ተወስደዋል። የፖለቲካ ስልጠናው አጀንዳ የአገር አንድነት የሚል አላማ ቢኖረውም ፣ በተግባር እየታየ ያለው ግን ተማሪዎችን እየለዩ ማሰር ነው ነው ብሎአል። ከአምቦ …

ነሃሴ ፳፩(ሃያአንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኩሬበረት እና እምባይድ  ቀበሌ የሚገኙ ነዋሪዎች እንደገለጹት ከአፋር አካባቢ የሚመጡ ማንነታቸው ያልተወቁ ታጣቂዎች ንብረታቸውን በተደጋጋሚ  እየዘረፉና ግድያም እየፈጸሙባቸው መሆኑን ተናግረው፤መንግስት ጉዳዩን ተከታትሎ የእርምት እርምጃ አለመውሰዱ በግድያው ላይ ጥርጣሬ እንዲያድርባቸው ማድረጉን ገልጸዋል። ግድያ እና ዘረፋ ሲካሄድ ጥበቃ ከማድረግ ይልቅ “-ራሳችሁን ጠብቁ ፣ንብረታችሁን ጠብቁ እና ወደ ጫካ አትውጡ ” በማለት የሚሰጠው መልስ ግዴለሽነቱን እያሳየን ነው …

ነሃሴ ፳፩(ሃያአንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የከሚሴ ከተማ ነዋሪዎች በመልካም አስተዳደር ፣በመንገድ ፣በውሃ ፣በመብራት እና በማፋሰ ሻዙሪያ ባሉትችግሮችለረጂምአመታትያቀረብናቸውጥያቄዎችአልተመለሱልንም፣ አመራሩበተቀያየረቁጥርየሚሰራውሕዝብመረበሽየለበትምበማለትአማረዋል። እሁድነሐሴ 18/2006 ዓ.ምበከሚሴከተማበተካሄደውህዝባዊስብሰባየከተማዋነዋሪዎችለአመታትየጠየቁት  የመልካምአስተዳደርጥያቄዎች ባለመመለሳቸውህብረተሰቡንወደማይፈለግአቅጣጫእየከተቱንነውበማለትተናግረዋል፡፡ የከተማአስተዳደሩየግለሰቦችንየድርጅትቦታበመንጠቅበሙስናለመኖሪቤትአገልግሎት 1000 ካሬሜትርተሰጥቷልበማለትብሶታቸውንተናግረዋል፡፡ ቅሬታአቅራቢዎችበከተማዋውስጥበመብራትናውሃከፍተኛችግርሆኖብንእያለያለመፍትሄመዝለቁ፤ዝናብ በዘነበ ቁጥር ከከተማዋ የተለያ የአቅጣጫየሚመጣውጎርፍ በዋናገበያውላይእናበየሰፈሩበመግባትያስቸገረመሆኑንተናግረዋል፡፡ የከተማአስተዳደሩበፀጥታዙሪያሰራሁበማለትይናገራልእንጅበምሽትመሳሪያበታጠቁሰዎችበየቤቱእየገቡዘረፋቢያካሂዱምተከታትለውወንጀለኛውን ተከታትሎእርምጃአልወሰደልንም፣  በከተማይቱጫፍ አካባቢየጥይትጩኸትበየጊዜውእየተሰማዝም ለምንተባለበማለትጠይቀዋል። ከአረብ አገራት የተመለሱ ኢትዮጵያውያን 50 እና 60 ሺ ብር ይዘው ቢገቡም እየከሰሩ፣ የሚሰሩት ስራ እያጡ ተመልሰው ስደትን መምረጣቸውን አንድ …

 

 

 

ሰሞኑን ኻርቱም ላይ የተካሄደው የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ የውኃ ሚኒስትሮች ስብሰባ ኢትዮጵያ እየገነባች ባለችው ኅዳሴ ግድብ ላይ ለተነሱ ውዝግቦች ከሰማንያ አምስት ከመቶ በላይ መልስ ሰጥቷል ሲሉ የግብፅ የመስኖ ሚኒስትር መናገራቸውን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡

ሦስቱ ሃገሮች ተቋርጦ የቆየውን ምክክራቸውን እንደገና ባደሱበት በዚህ ስብሰባ ማብቂያ ላይ የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

“ኢትዮጵያ በግድቧ ላይ ተጨማሪ ጥናቶችን እንድታካሂድ የሚያሳስብ መልዕክት አዝሏል” ያሉትን ዓለምአቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ሃሣቦች ተቀብለው ለመተግበር መስማማታቸውንና ይህንኑም የስምምነት ሰነድ ትናንት መፈረማቸውን የግብፅ የመስኖ ሚኒስትር ዶ/ር ሁሣም አል ማግሃዚ የነገሩት መሆኑን አል ጣህሪር የሚባለው ሃገሪቱ…

 

 

 

የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ወገኖች ባለፈው ጥር የደረሱበትን የተኩስ አቁም ስምምነት መፈራረማቸው በኢጋድ በተነገረ በማግሥቱ ተቃዋሚዎቹ አልፈረምንም ሲሉ አስተባብለዋል።

የተቃዋሚዎቹ ዋነኛ ተደራዳሪ ለቪኦኤ ሲናገሩ “ስምምነቱን ፈረሙ” ተብሎ በኢጋድ የተሠራጨው መረጃ ሃሰት ነው ብለዋል።

የደቡብ ሱዳን መንግሥት ዋነኛ ተደራዳሪ ግን “ተቃዋሚዎቹ ስምምነቱን የፈረሙት በዓለም ፊት ነው” ብለዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ግብርና-ቀመስ የሥነ-ሕይወት ዕውቀት፣ በሳይንሳዊ ዘዴዎች የዕጽዋትንና አዝርእትን እንዲሁም የእንስሳትን ተፈጥሯዊ ይዞታም ሆነ መለያ ማሻሻልም ሆነ መለወጥ የሚቻልበት አሠራር ነው። በርከት ያለ የእህል ምርት ለማፈስ፤ ከጥንት ጀማሮ አርሶ አደሮች፣ የዘር እኽል እየመረጡ በመዝራት አያሌ ዘመናት ጠብቀው ለማቆየት መቻላቸው የሚታበል አይደለም።

ተማሪዎችና የፖለቲካ ተቋዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ፖሊሲ ላይ ያተኮረው ለከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ተማሪዎች የሚሰጠውሥልጠና ከጥሪው አንስቶ በግዳጅ የሚካሄድ መሆኑን ነው የሚናገሩት የኢትዮጵያ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የሁለት ሳምንታት የፖሊሲ ስልጠና ላይ መሆናቸውን መንግስት አስታውቋል ።

የፖለቲካ ተንታኝ ዩሱፍ ያሲን እንደሚሉት ግን ያሁኑ ስብሰባ እንደተባለዉ ከወሳኝ መፍትሔ ባይደርስ እንኳ ሰወሥቱ ሐገራት በተለይ ኢትዮጵያና ግብፅ ጦር የያሰብቅ መሠሎ የበረዉ ዉዝግባቸዉን በድርድር ለመፍታት መስማማታቸዉ ራሱ ጥሩ ጅምር ነዉ።

እስራኤል እና ሀማስ ትናንት የደረሱት የተኩስ አቁም ስምምነት ከትናንት አስራ ሁለት ሰዓት ጀምሮ እንደፀና ይገኛል። ተቀናቃኞቹ ወገኖች በግብፅ ሸምጋይነት ነበር ሰባት ሳምንታት ለሆነው የ2,002 ሰዎች ሕይወት ላጠፋው ውጊያ ገደብ ያልተደረገበት ስምምነት የደረሱት። በስምምነቱ መሠረት፣ በጋዛ ላይ የተጣለው ዕገዳም በከፊል እንደሚነሳ ተገልጾዋል።

ተቃውሞ:- በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች፥ የኢንተርኔት አምደኞች፥ የፖለቲካ መሪዎኞች ሌሎች ዜጎች እስርና የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ዘገባዎች፤

ከሁለት ሰአቱ የኢቲቪ ዜና አወጃ ተከትሎ የቀረበውን ” ያልተገሩ ብዕሮች ” ዶክመንተሪ በደረቁ ሌሊት ድጋሜ ስርጭቱ ተከታትየ ጨረስኩት … ላፍታ እንደተጠናቀቀ ዝም ፣ ጭጭ አልኩና በሃሳቤ በህዝብ ገንዘብ ከፍተኛ ወጭ እየተደረገባቸው የሚሰራጩትን የመንግስት የህትመት ጽሁፍና የኤሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙሃንን አሰብኳቸው … በምናብ ብዙ ርቄ ሔጀ በዶደመ ፣ ባልተገራ እና በተባውና በተገራው ብዕር ውስጥ ራሴን አትኩሮት ሰጥቸ […]

ነሃሴ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር፣ የግንቦት 7፣የፍትህ፣የነፃነትናየዲሞክራሲ ንቅናቄ እንዲሁም የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ በጋራ ባወጡት መግለጫ ”  ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ካሉበት አዘቅት በማውጣት ሕዝቡ የስልጣን ባለቤት የሚሆንበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የጋራ ትግልና መስዋዕትነት የግድ የሚለን ደረጃ ላይ ደርሰናል ብለዋል። ድርጅቶቹ አያይዘውም ” አገራችንና ሕዝባችንን ከአዘቅት ለማውጣት በመጣመር ብቻ ሳይሆን በውህደት አንድ ሆነን …

ነሃሴ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በክልሉ ፕሬዚዳንት አብዲ ኢሌ ፣ በሶማሊ ህዝብ ዴሞክራሲያ ፓርተ (ሶህዴፓ) ሊቀመንበርና ከፕሬዚዳንቱ ጎሳ የሆኑ በአንድ ወገን፣ 3 ምክትል ፕሬዚዳንቶችና የ4 ካቢኔ አባላት በሌላ በኩል ሆነው የጀመሩት እሰጥ አገባ ጠ/ሚኒስትሩ ጋር ደርሶና በድርጅት ደረጃ ግምገማ አድርገው መፍትሄ እንዲሰጡት ስምምነት ከተደረሰ በሁዋላ፣ ፕሬዚዳንቱ ግምገማውን ለማደናቀፍ በዛሬው እለት ከጄኔራል አብርሃ ጋር ለአስቸኳይ …

ነሃሴ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በወረታ ከተማ በተካሄደው ሁለተኛው የንግድ ቀን ስብሰባ ስብሰባውን የመሩት የንግድናትራንስፖርት ሃልፊ  ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የሃገራችን የንግድ አሰራር የሸማቹን መብትና ጥቅም ያላከበረ  በኋላቀርነት እና ውስብስብ አሰራር ውስጥ የቆየ በሆንምአሁንግንፍትህአዊእና ተደራሽነትያለውአሰራርእንዲሰፍንእየሰራይገኛልቢሉም  እስካሁን ምንምአይነት መሻሻል የታየበት አሰራር እንዳልተያዘ ነጋዴዎቹተናግረዋል፡፡ በቤትክራይምክንያትቦታ ሲቀይሩፈቃድአናድስምበማለትተጨማሪክፍያመጠየቅ ፣ ውዝፍግብርበማለትበየጊዜውያልተገባግብርእንዲከፍሉ መደረጉ ፣ የቫትተመዝጋቢነጋዴዎችንየግምትግብርእንዲከፍሉማስገደድ፣  የሚሉት ችግሮች ተዘርዝረው እነዚህችግሮችአለመፈታታቸውየንግዱ ማህበረሰብበነጻነትለመስራትእንዳላስቻለው ተናግረዋል፡፡መመሪያናትእዛዞችንአክብሮ የሚሰራውንነጋዴየማስቸገርስራየሚሰራበትአፈጻጸም ችግርበስፋትእየታየመሆኑንአስተያየትሰጪዎቹ አክለው …

(አፈንዲ ሙተቂ)

የኢትኖግራፊ ፈረሳችን አንዳንዴ ከሰዎች ዓለም ይወጣል፤ ከዚህ ቀደም ወደ ጂንኒዎች ዓለም ሄደን ከዚያ ያገኘነውን ጨዋታ እያጫወትናችሁ በፍርሃት አርበድብደናችሁ ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ ፈረሳችን ወደ እንስሳት ዓለም በመሸጋገር እንደርሱ ጋላቢ ከሆነው ተአምረኛው “ግመል” ጋር ተፋጧል፡፡

        

ፈረሱም ፈረስ ነው፡ ግመሉም ግመል

ግመል ግን ይበልጣል በረሃ “እሚሸቅል”

እውነት ነው! ፈረስ በፍጥነቱ አንጀት አርስ ነው፡፡ በእሽቅድምድምና በግልቢያ አንደኛ ነው፡፡ በድሮ ዘመን ጦርነት ሲካሄድም ይህ ቀረሽ የማይባል አገልግሎት ሰጥቷል፡፡ የሰው ልጅ እንስሳትን አላምዶ መጠቀም ከጀመረበት ዘመን አንስቶ ለሰዎች የሰጠው አገልግሎት ቢመዘን ግን ከግመል አይበልጥም፡፡ ለዚህም ብዙ ማስረጃዎች አሉን፡፡ አሁን እነርሱን አናስቆጥራችሁም፡፡ ጊዜው ሲደርስ ማስረጃዎቹ ራሳቸው እየጮኹ ይናገራሉ፡፡ Let the facts speak themselves እንዲሉ ፈረንጆች!!

ይልቅስ የዛሬው ጉዞአችን በረሀ ለበረሀ ስለሚያዟዙረን ግመልን ራሱኑ መጓጓዣችን ብናደርገውስ?… ይገባዋል! ለበረሃ ሐሩር፣ ለአሸዋ ውሽንፍር የማይበገረው “ግመሌ” ነው፡፡ ስለዚህ ፈረሳችንን በቆላው መሬት ውስጥ ለገበሬዎች በአደራ ሰጥተናቸው በግመል ጀርባ እየጋለብን ስለተአምረኛው እንስሳ እንዲህ እናወጋችኋለን፡፡

*****

የእንስሳው ስም “ግመል” ነው ብለናል፡፡ ይህንን ስም ልብ ብላችኋልን?….! እንግዲህ ተአምሩ የሚጀምረው ከዚህ ነው፡፡ “ግመል” የአማርኛው ስሙ ነው፡፡ በትግርኛም “ግመል” ነው፡፡ በእብራይስጥ ደግሞ “ጊመል” ነው፡፡ በግዕዝ “ገመል” ተብሎ ይጠራል፡፡ ዐረብኛው “ጀመል” ይለዋል፡፡ በሀረሪ ቋንቋ “ጋሚላ” እንለዋለን፡፡ እነዚህ ቋንቋዎች በሙሉ ሴማዊ ናቸው፡፡ እንስሳው በነዚህ ቋንቋዎች በተመሳሳይ/ተቀራራቢ ስም የሚጠራው ቋንቋዎቹ ስሙን በመወራረሳቸው አይደለም፡፡ ስያሜው የሴም ቋንቋዎች መነሻ ነው ተብሎ ከሚታመነበት ግንደ ሴማዊ ቋንቋ (Proto-Semitic Language) ተነስቶ በያንዳንዱ ቋንቋ ውስጥ እየተላለፈ ወደዚህ ዘመን ስለደረሰ ነው፡፡ ይህ ጉዳይ እንስሳው ራሱ ከሰው ልጅ ጋር የተላመደው የሴም ህዝቦች መነሻ ከሆነው መካከለኛው ምስራቅ ውስጥ እንደሆነ ይጠቁመን ይሆን?..

በሚገባ! የሰው ልጅን የስልጣኔ ታሪክ ያጠኑ ምሁራን እንደሚመሰክሩት ግመልን ለመጀመሪያ ጊዜ ያላመዱት የሴማዊ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝቦች ናቸው፡፡ በመሆኑም በአንዳንድ ቋንቋዎች (ኦሮምኛ፣ ሶማሊኛ ወዘተ…) እንስሳው የተለየ ስያሜ ቢኖረውም በዛሬው ዘመን አብዛኛው የዓለም ህዝብ ግመልን የሚጠራው ከሴማዊ ቋንቋዎች የወረሰውን ቃል በ“ማንሻፈፍ” (corrupt በማድረግ) ነው፡፡ ለምሳሌ እንግሊዛዊያን “ካሜል” ይሉታል፡፡ በጀርመንም “ካሜል” ይባላል፡፡ በፈረንሳይኛ፣ በስጳኝ፣ በጣሊያንኛና በሌሎችም የአውሮጳ ቋንቋዎች በተቀራራቢ ስም ይጠራል፡፡ እነዚህ ቋንቋዎች ቃሉን የወረሱት ከላቲን ነው፡፡ ላቲንም ከግሪክ ነው የወረሰው፡፡ ግሪክ ደግሞ በጥንቱ ዘመን በሶሪያና በፍልስጥኤም የብዙ ህዝቦች መግባቢያ ከነበረው የአረማይስጥ ቋንቋ ነው የወሰደው፡፡

ታዲያ ዛሬ ከምንጽፍባቸው ፊደላት መካከል አንዱ በዚህ እንስሳ ስም የተሰየመ መሆኑን የምታውቁት ስንቶቻችሁ ናችሁ?… በሮማዊያንም ሆነ በሳባ፣ በዐረብም ሆነ በግሪክ ፊደላት የምትጠቀሙት ሁሉ ከምትጽፉባቸው ፊደላት መካከል አንዱ በዚህ እንስሳ ስም የተሰየመ መሆኑን ተገንዘቡት፡፡ እንዴት ማለት “አሪፍ” ነገር ነው፡፡

“ሀረር ጌይ” በተሰኘው መጽሐፌ ለማስረዳት እንደሞከርኩት በዓለም ላይ ከሚሰራባቸው የፊደል ገበታዎች መካከል በጣም የሚበዙት ከአንድ ምንጭ ነው የተቀዱት፡፡ የሮማ ፊደል፣ የግሪክ ፊደል፣ የሳባ (ግዕዝ) ፊደል፣ የዐረቢያ ፊደል፣ የቄርሎሳዊያን (የሩሲያ) ፊደል እና የሳንስክሪት (ህንድ) ፊደል ምንጫቸው አንድ ነው፡፡ እርሱም የጥንቱ የፊንቃዊያን (Phoenicians) የፊደል ገበታ ነው፡፡ እነኚያ ፊንቃዊያን የመጻፊያ ፊደላትን ሲፈጥሩ እያንዳንዱን ፊደል በቅርብ በሚያውቋቸው ፍጥረታትና የሰው ልጅ የስራ ውጤቶች ነው የሰየሙት፡፡ ለምሳሌ “አሌፍ” ሲባል “በሬ” ማለት ነው፡፡ “ቤት” ደግሞ መጠለያችን የሆነው “ቤት” ነው፡፡ “ጊመል” ሲባል “ግመል” ነው፡፡ “ዳሌጥ” ደግሞ የቤት መግቢያ ምድራክ ነው፡፡ “ሚም” የሚፈስ ውሃ ማለት ነው፡፡ “ኑን” አሳ ማለት ነው፡፡  “ዐይን” ዐይን ነው፡፡ ወዘተ….

    

  የፊንቃዊያኑን ፊደል እንደ መነሻ በማድረግ የተፈጠሩት ልዩ ልዩ የፊደል ገበታዎች ሆሄያትን ያስቀመጡበት ቅደም ተከተል፣ የፊደላቱ ቅርጽና የመጠሪያ ስማቸው በዘመናት ሂደት ተለውጧል፡፡ ነገር ግን ወደ ኦሪጂናሌ አቀማመጣቸው ስንመልሳቸው ሁሉም ከአንድ ምንጭ የተነሱ መሆናቸውን በቀላሉ ማስተዋል ይቻላል፡፡ በዚህ መሰረት የዐረብኛ የፊደል ገበታ “አብጀድ” በተሰኘው ጥንታዊ አሰላለፉ ሲቀመጥ “ጂም” የሚባለው ሶስተኛ ፊደል በጥንቱ የፊንቂ ገበታ ላይ ከነበረው “ጊመል” የተገኘ መሆኑን ያዙልኝ፡፡ የኛው የሳባ ፊደል ገበታ በ“አቡጊዳ” ተራው ሲቀመጥ “ጊ” ከጥንቱ “ጊመል” የተገኘ መሆኑን እወቁልኝ፡፡ የእብራይስጡ “ጊመል”ም እንደዚያው፡፡ የግሪካዊያኑ “ጋማ”ም እንደዚያው፡፡ የእንግሊዝኛው (የ“ሮማ”ው) “ጂ”ም እንደዚያው…. ወዘተ….፡፡ እነዚህ ፊደላት ሁሉ አጠራራቸው ቢለያይም የፊንቃዊያኑን “ጊመል” መነሻ በማድረግ የተቀረጹ ናቸው፡፡ “ጊመል” ደግሞ የኛው “ግመል” ነው፡፡ ተአምረኛው እንስሳ!!  

*****

አላህ በቅዱስ ቁርኣን እንዲህ ይላል፡፡

 “ወደ ግመል አይመለከቱምን? እንዴት እንደተፈጠረች”

(አል-ጋሺያህ-17)

ቅዱስ ቁርኣን እንዲህ ያለው ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ›ወ) እስልምናን ማስተማር ሲጀምሩ “ፈጣሪ የለም” ብለው በማስተባበል በተቃውሞ ለተነሱባቸው ሰዎች ነው፡፡ እነዚያ ሰዎች በንዳዱ ከታወቀው የዐረቢያ በረሃ ነው የተገኙት፡፡ በዚያ በረሃ ከምንም በላይ ዋጋ ያለው እንስሳ ግመል ነው፡፡ ግመሉ በአስቸጋሪው በረሃ እየኖረ በሚሰጠው አገልግሎት የሰዎች ኑሮ የተቃና እንዲሆን አድርጓል፡፡ እናም የቅዱስ ቁርኣን መልዕክት “እነዚያ ‘ፈጣሪን አናውቅም’ ባዮች የዚህን ድንቅዬ እንስሳ ባህሪ በማየት ብቻ የፈጣሪ መኖር በተከሰተላቸው ነበር” የሚል ነው፡፡

   እውነት ነው!! የበረሃው ሙቀት የቱንም ያህል ቢጨምር ግመሉ የመቋቋም ብቃት አለው፡፡ ግራር በቀል ከሆኑት የአዳማና የሀርዲም ቆላዎች አንስቶ እስከ ሰሜን አፍሪቃው የሰሐራ በረሃ እና የአፋር የዳሎል ስምጥ ቦታ ባሉት ሞቃት የዓለማችን ክልሎች ሁሉ የመኖር ብቃት አለው፡፡ ሌላው ቀርቶ ለርሱ የሚስማማ መኖ ካገኘ በደጋማ አካባቢዎችም (ውርጭ በሌለባቸው ማለቴ ነው) መኖር ይችላል፡፡

  በረሃው እንደ እሳት የሚፋጀው ቀን ቀን ነው፡፡ ሌሊት ላይ በተቃራኒው ብርዱ አይቻልም፡፡ ሙቀቱ በጣም ወርዶ “ደብረ ብርሃን ነው ያለሁት እንዴ?” ከሚያሰኝበት ደረጃ ይደርሳል፡፡ ሌሎች እንስሳት ለእንዲህ ዓይነቱ የአየር ለውጥ የተመቹ አይደሉም፡፡ ግመል ግን ሁሉንም ሳይቸገር ይቋቋማል፡፡

   ግመል ለምግቡም ቢሆን አይቸገርም፡፡ ዝናብ በተከታታይ ዓመታት ቢጠፋ እንኳ “መኖ ካላመጣህ” በማለት ባለቤቱን አያስጨንቀውም፡፡ ያገኘውን ዛፍና ቁጥቋጦ እየቀነጠበ ህይወቱን ማቆየት ይችልበታል፡፡ ለህይወቱ የሚያሰጋ በሽታም እምብዛም አያጋጥመውም፡፡ እርሱን የሚገድለው ወይ እርጅና ነው፣ ወይ የአንበሳ መንጋ ነው፡፡

 

   አዎን! ግመል የሚበላውንና የሚጠጣውን አጥቶ ሞተ ሲባል ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅ!…! ግመል ከብትና ፍየል አይደለም፡፡ ምንም ነገር ሳይቀምስ ለብዙ ቀናት መቆየት ይችላል፡፡ ውሃ ሳይጠጣም ለሁለት ወር ያህል መቆየት ይችላል፡፡ ውሃ ከአካባቢው ጭራሹኑ ከጠፋ ባለቤቱን ራሱ እየመራው ውሃው ከሚገኝበት ስፍራ ይወስደዋል፡፡ ውሃውን ሲያገኝ ደግሞ አጠጣጡ ለጉድ ነው!! አንድ የፍየል መንጋ የሚያጠግበውን አሊያም አምስት በሬዎች የማይጨርሱትን ውሃ በአንድ ጊዜ ዥው አድርጎ መጠጣት ይችላል፡፡ ሆኖም ኢኮኖሚ የማያውቅ አይምሰላችሁ! ግመል እንዲህ የሚጠጣው በቂ ውሃ ባለበት አካባቢ ነው፡፡ ለምሳሌ የከረዩና የአፋር አርብቶ አደሮች ወደ አዋሽ ወንዝ እየመሩ ሲወስዱት ከወንዙ ውሃ እስኪበቃው ድረስ ይጎነጫል፡፡ ትንሽዬ የውሃ ጉድጓድ (ኤላ) ብቻ ባለበት ጭው ያለ በረሃ ግን ባለቤቶቹ በኦኮሌ እየጨለፉ የሰጡትን ብቻ ይጠጣና ያችኑ አብቃቅቶ ለወር ያህል ይቆያል፡፡

  የግመል ዋነኛው ተአምር “ሻኛው” ነው፡፡ እጅግ የደለበ የቅባት ስብስብ!! የሰውነቱ ስብና ሞራ በዚያ ላይ ነው የሚሰባሰበው፡፡ ምግብ ባጣ ጊዜ፣ አሊያም ውሃ በጠፋ ጊዜ በሻኛው ከተጠራቀመው ቅባት እየቆነጠረ እንደምግብ ይጠቀምበታል፡፡ ውሃውንም ከርሱ ያገኛል፡፡ አስቸጋሪ በሆነው የበረሃ ክልል ለመኖር የቻለውም ፈጣሪ “ሻኛ” የሚባለውን ድልብ ስለፈጠረለት ነው፡፡ ከሻኛው ጋር ሻኛውን እያቀለጠ የሚጠቀምበትንም ችሎታ ፈጥሮለታል፡፡ ታዲያ ይህ ችሎታ የተሰጠው ለርሱ ብቻ እንደሆነ ልብ በሉ!! ሻኛ ያላቸው ሌሎች እንስሳት በሙሉ ሻኛቸውን እያቀለጡ እንደ ምግብ ሊጠቀሙበት አይችሉም፡፡ ግመል ብቻ ነው ይህንን ማድረግ የሚችለው፡፡ የፈጣሪ ተአምር!!

(ይቀጥላል)

—-

አፈንዲ ሙተቂ

ነሐሴ 19/2006

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የጀርመን መንግሥት የኢራቅ ኩርዶችን ለማስታጠቅ መወሰኑ የሰሞኑ የጀርመናውያን አብይ የመነጋገሪያ ርዕስ ነው ። የጀርመን መንግሥት ባለሥልጣናት እስከ ዛሬ ሳምንት ሐሙስ ድረስ የሚሰጧቸው መግለጫዎች ጀርመን ጦርነት ወደ ተባባሰባት ኢራቅ የጦር መሣሪያዎችን አትልክም የሚል ነበር ።

(ክፍል አንድ)
የዝሆን ሥዕል፣ ወሎ ገነተማርያም ቤተ ክርስቲያን
በሰው ልጆች የአደን፣ የጦርነት፣ የንግድ፣ የባሕልና የሃይማኖት ታሪክ ውስጥ ቦታ ካላቸው እንስሳት አንዱ ዝሆን ነው፡፡ ዝሆን ማደን የጀግንነት መገለጫ ሆኖ አዳኞቹን ሲያስመሰግንና ሲያስወድስ ኖሯል፡፡ በቀደምት ዘመናት በተደረጉ ጦርነቶችም ዝሆኖች የዛሬዎቹን ታንኮች ቦታ ተክተው አገልግለዋል፡፡ የአኩስሙ አብርሃ ከደቡብ የመን ወደ መካ ባደረገው የጦርነት ጉዞ አያሌ ዝሆኖችን ተጠቅሞ ስለነበር ዘመኑ ‹የዝሆኖች ዓመት› እየተባለ እስከ መጠራት ደርሶ ነበር፡፡ በበጥሊሞሳያን ዘመንም ግብጻውያን ከኢትዮጵያና አካባቢዋ ዝሆኖችን በመውሰድ ለጦርነት ተጠቅመውባቸዋል፡፡ 

የዝሆን ጥርስ ለጌጣጌጥ መሥሪያ መዋል የጀመረው ከክርስቶስ ልደት በፊት በነበሩ ጥንታውያን ሥልጣኔዎች ዘመን ነው፡፡ ይህ የዝሆን ጥርስ ንግድ ዝሆኖችን ከልዩ ልዩ አካባቢዎች እንዲጠፉና ዛሬም ቁጥራቸው እንዲመነምን ዋናውን ክፉ አስተዋጽዖ አድርጓል፡፡

ዝሆን በልዩ ልዩ ባሕሎችና ሃይማኖቶች ዘንድ የጥንካሬ፣ ወድቆ የመነሣት፣ ታላቅን የማክበርና የማስታወስ ተምሳሌት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ ላይ የምናገኘው የ‹ዐቢይ ነጌና የውርዝው ነጌያት› ምሳሌ ለዚህ ማሳያ ይሆናል፡፡ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍልም ‹ሔርማዝ› የሚለው ጥንታዊ የዝሆን መጠሪያ  ለ‹ጀግና› የሚሰጥ ስያሜ ሆኗል፡፡ በሀገራችን የአደን ታሪክ ውስጥ ከአንበሳ ገዳይ ቀጥሎ ክብር የነበረው ዝሆን ገዳይ መሆኑ ይነገራል፡፡

በሀገራችን ጥንታዊ ሥዕሎች ውስጥ የዝሆንን ሥዕል በስፋት እናገኛለን፡፡ በተለይም ከ15ኛው መክዘ በፊት የተሣሉ የግድግዳ ሥዕሎች ዝሆንን በየማዕዘናቱ ያስቀምጡታል፡፡ በወሎ እመኪና ልደታ ለማርያምና ገነተ ማርያም አብያተ ክርስቲያናት ግድግዳ ላይ የሚገኘው የ14ኛው መክዘና ከዚያ ቀደም ብሎ የተሳሉት የዝሆን ሥዕሎች ለዚህ ምሳሌ ሆነው ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡
የዝሆን ሥዕል፣ ወሎ እመኪና ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን

በአሁኑ ጊዜ በአፍሪካ ወደ ስድስት መቶ ሺ፣ በሕንድ ደግሞ ከ30 እስከ ሃምሳ ሺ የሚደርሱ ዝሆኖች እንደሚገኙ ይገመታል፡፡ 1.3 ሚሊዮን ይደርስ የነበረው የአፍሪካ ዝሆኖች ቁጥር አሁን ወዳለበት መጠን ያሽቆለቆለው እኤአ ከ1979-1989 ዓም ባለው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ በኢትዮጵያ እኤአ በ2007 ዓም በተደረገው ጥናት 1200 የሚደርሱ ዝሆኖች እንደነበሩ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በዓለም እንደደረሰው የዝሆኖች እልቂት ሁሉ በ1980ዎቹ ብቻ 90 በመቶ የሚሆኑት የኢትዮጵያ ዝሆኖች ከምድረ ገጽ ጠፍተዋል፡፡
የጥንት ሰዎች የዝሆንን የተፈጥሮ ጠባያት በመረዳት ለእምነታቸው መግለጫ፣ ለሥነ ምግባራቸው ማስተማሪያና ለፍልስፍናቸው ማሳያ አድርገውት ነበር፡፡ በሕንድ፣ በፋርስና በመካከለኛው ምሥራቅ ከ8ኛው መክዘ ጀምሮ የታወቀው ‹የዝሆኑና የስድስቱ ዓይነ ሥውራን› ታሪክ በብዙ ጥንታውያን አስተምህሮዎች ውስጥ ለልዩ ልዩ ጥበብ፣ ፍልስፍናና ሞራል ማስተማሪያነት ውሎ ነበር፡፡

ዝሆን የጠንካራ ነገር ግን ተጣጣፊ ኩምቢ ባለቤት ነው፡፡ ይህ 150 ሺ ጡንቻዎች ያሉት የዝሆን ኩምቢ 600 ጡንቻዎችን ብቻ ከያዘው የሰው ዘር ጋር ሲነጻጻር ጥንካሬውን ማሳየት ይችላል፡፡ የዝሆን ኩምቢ ይህንን ያህል ጠንካራ ቢሆንም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ግን የሚገባውን አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችለው ወደፈለገው አቅጣጫ ያጣጥፈዋል፡፡ ሰውም በአቋሙ እንደ ዝሆን ኩምቢ ጠንካራ መሆን አለበት፡፡ ነገር ግን አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ከነገሮችም ጋር አብሮ ለመጓዝ የሚችል፡፡ ጥንካሬው እንደ እንጨት ሳይሆን እንደ ብረት፡፡ እንጨት ይሰበራል እንጂ መተጣጠፍ አይችልም፡፡ ብረት ግን ጠንካራ ቢሆንም ተጣጣፊ ነው፡፡ የሰው ዓላማ ተጣጣፊ ብቻ መሆን የለበትም፡፡ እንዲያ ከሆነ የመጣ ጎርፍ ሁሉ የሚወስደው፣ የበረታ ዱላ ሁሉ የሚነዳው ይሆናል፡፡ በሌላም በኩል ደግሞ ሰው እንደ ጅብራ የሚገተር፣ እንደ እንጨትም ደርቆ የሚቀር መሆን የለበትም፡፡ እንዲያ ከሆነ እኔ ብቻ ትክክል ነኝ፣ እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን የሚል ግለኝነት ይጠናወተዋል፡፡ ሰው እንደ ዝሆን ኩምቢ በዓላማው ጠንካራ ሆኖ፣ ደግሞም ዓላማውን ሳይለቅ አማራጮችንና የተሻሉ መንገዶችን ለማየት ዕድል የሚሰጥ፣ አመዛዝኖ ለመቀበልና ከተሻለው ነገር ጋር ለመራመድ የሚችል መሆን አለበት፡፡

የዝሆን ኩምቢ

ዝሆን ሚዛናዊ ነው፡፡ ዝሆን በዓለማችን ትልቁ አጥቢ እንስሳ ነው፡፡ ክብደቱ እስከ ስድስት ሺ ኪሎ ግራም ይደርሳል፡፡ ይህንን ያህል ክብደቱን እስከ 3.3 ሜትር በሚደርሰው ቁመቱ ውስጥ ይይዘዋል፡፡ ይህንን ሁሉ ክብደት የያዘው ዝሆን ቅጠል በል መሆኑ የተነሣ የዛፎቹን ቁመት ተከትሎ ቀጭኔ በአንገቷ የምትደርስበት ቦታ ድረስ መድረስ የግድ ይለዋል፡፡ እዚህ ላይ ትልቁ ጥያቄ እንዴት? የሚለው ነው፡፡

የዝሆን አንዱ ችሎታ የሚለካው ለዚህ ጥያቄ በሚሰጠው መልስ ነው፡፡ ሁለት የፊት እግሮቹን ወደ ላይ በማውጣት በሁለት የኋላ እግሮቹ መሬቱን እንደ ችካል ተክሎ ይይዘዋል፡፡ ከዚያም ኩምቢውን እንደ ሰጎን አንገት በመምዘዝ የዛፉ ጫፍ ላይ ይደርሳል፡፡ ይህንን ተግባር ለማከናወን የሚችለው ዝሆን ሚዛናዊ ስለሆነ ነው፡፡ ክብደቱን፣ ቁመቱን፣ የነፋሱን ኃይል፣ የዛፎቹን ንቅናቄና የሚገነድሰውን ዛፍ ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ መልኩ ሚዛኑን ሳያዛንፍ በሁለት እግሮቹ መጠበቅ ይችላል፡፡ ጠንካራ ሰው ማለትም እንዲህ ነው፡፡ ምንም ያህል ከባድ ኃላፊነት ቢኖርበት፣ ምንም ያህል አስቸጋሪ ሥራ ቢሠራ፣ ምንም ያህል ወደ ላይ ቢንጠራራ፣ ምንም ያህል እንደ ነፋስ ጠንካራ የሆነ ፈተናና ትችት ቢዘንብበትም ሚዛኑን ሳይስት ወደ ዓላማው መጓዝ አለበት፡፡ ለዚያ ደግሞ ሁለት ነገሮች ያስፈልጋሉ፡፡ እንደ ዝሆን ሁለት እግሮች ጸንተው የሚተከሉ መሠረታዊ እምነቶች፣ እንደ ሁለቱ የፊት እግሮችም ወደ ላይ የሚንጠራሩ ራእዮችና ግቦች ያስፈልጋሉ፡፡

ወደፊት ለመጓዝ ዛሬ የምንተከልበት፣ ተተክለንም የምንቆምበት ነገር ያስፈልጋል፡፡ ትናንት ላይ ሳይተከሉ ወደ ዛሬ፣ ዛሬ ላይ ሳይተከሉ ወደ ነገ መጓዝ አይቻልም፡፡ ማንኛውም አውሮፕላን በሰማይ ላይ ለመብረር ከፈለገ ማኮብኮቢያ ሜዳ ያስፈልገዋል፡፡ ወደ ነገ የሚጓዝ ማንም ቢኖር የሚተከልበት የትናንት ታሪክ፣ ባሕል፣ ቅርስና ጥሪት ያስፈልገዋል፡፡
ዝሆን የሚተኛው ለመነሣት እንዲመቸው ሆኖ ነው፡፡ መሬት ላይ ከወደቀ ለመነሣት ይቸገራል፡፡ ክብደቱ ትልቅ ነውና፡፡ ስለዚህም የሚተኛው ዛፍ ተደግፎ ነው፡፡ የዝሆን ዕንቅልፍ ፍጹም ዕንቅልፍ አይደለም፡፡ ለመነሣት ያኮበኮበ ዕንቅልፍ ነው፡፡ የሚተኛው ለመነሣት በሚችልበት መንገድ ነው፡፡ ሰውም ሞቱ ለትንሣኤ፣ ድካሙ ለብርታት፣ ዕረፍቱ ለሥራ፣ ኀዘኑ ለደስታ፣ ውድቀቱ ለመነሣት፣ ስሕተቱ ለእርማት፣ ማጣቱ ለማግኘት፣ ሕመሙ ለድኅነት በሚሆን መልኩ መሆን አለበት፡፡ እንዳይነሣ ሆኖ መውደቅ፣ እንዳይተርፍ ሆኖ መክሰር፣ እንዳይከብር ሆኖ መዋረድ፣ እንዳይፈታ ሆኖ መታሠር፣ እንዳይመለስ ሆኖ መሄድ፣ እንዳይታረቅ ሆኖ መጣላት የለበትም፡፡ የማርያም መንገድ መተው ያስፈልጋል፡፡ የአንድ ነገር መጨረሻ የሌላ ነገር መጀመሪያ መሆን አለበት፡፡ ከሥራ ማረፍ ለሌላ ሥራ መዘጋጃ፣ የዛሬ ዕንቅልፍ ለነገ ብርታት ኃይል መሰብሰቢያ፣ የዛሬ ሞት ለነገ ትንሣኤ መራመጃ መሆን አለበት፡፡

በዝሆን መንጋ ዘንድ ታላላቆች ወሳኝ ቦታ አላቸው፡፡ ይከበራሉ፤ ይሰማሉ፤ ይመራሉ፤ ያስተምራሉ፤ ትውልድም ቀርፀው ያፈራሉ፡፡ መንጋው ሲጓዝ መንገድ የሚመሩት፤ ለአዳጊዎች ልምዳቸውን የሚያካፍሉት፤ መንጋውን ከአደጋ የሚጠብቁት፤ ጥፋተኛውን ጎረምሳም የሚቀጡት ታላላቆች ናቸው፡፡ ታላላቆች የሌሉበት መንጋ እሥር ቤት እንደሰበረ ማፊያ ይሆናል፡፡ በአንድ ወቅት በደቡብ አፍሪካ ክሩገር ፓርክ ውስጥ የሚገኙ ዝሆኖች ቁጥራቸው ጨመረና ከፓርኩ ዐቅም በላይ ሆኑ፡፡ ቁጥራቸውን ከፓርኩ ዐቅም ጋር ለማመጣጠን እንዲቻል የተወሰኑትን ዝሆኖች ወደ ሌላ ፓርክ ለመውሰድ ተወሰነ፡፡ ዝሆኖቹ እንዲሄዱ የታሰበው በሄሊኮፕተር እየተንጠለጠሉ ነበር፡፡ ሄሊኮፕተሩ ትልልቆቹን ዝሆኖች ለመጫን ዐቅም ስላነሰው ወጣቶቹ ዝሆኖች እየተመረጡ ወደ ሌላኛው ፓርክ ተወሰዱ፡፡

ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወጣቶቹ ዝሆኖች የገቡበት ፓርክ ተናወጠ፡፡ በፓርኩ ውስጥ የሚገኙት አውራሪሶች በየቀኑ ይገደሉ ጀመር፤ ዛፎች ይገነደሳሉ፤ ቁጥቋጦዎች ይተራመሳሉ፤ በዝሆኖቹ መካከል ጦርነት ተፈጠረ፡፡ በዚህም ምክንያት ዐቅመ ደካሞቹ እንስሳት ይጎዱ ጀመር፡፡ ነገሩ ያሳሰባቸው የፓርኩ ኃላፊዎች ሥውር ካሜራ ገጥመው ሁኔታውን መከታተል ያዙ፡፡ በመጨረሻም ወጣቶቹ ዝሆኖች የዚህ ሁሉ ችግር ፈጣሪዎች መሆናቸውን ደረሱበት፡፡ ሳይታሰብ አንድ ‹የዱርዬ ዝሆኖች ቡድን› ተመሥርቷል፡፡

የዝሆን አመራር
አንድ የጥናት ቡድን ተቀዋቁሞ የችግሩን መነሻ ማጣራት ሲጀምር ዋናው ጉድለት በዝሆኖቹ መካከል የሚመራና የሚፈራ ሽማግሌ አለመኖሩ መሆኑ ተደረሰበት፡፡ ወዲያውም የተወሰኑ ታላላቅ ዝሆኖችን እንደምንም ብለው ወደ ፓርኩ ሲያመጧቸው ሁሉም ነገር ሥነ ሥርዓት ያዘ፡፡ ‹መካሪ ዘካሪ አያሳጣ› ይባል የለ፡፡

በሰው ልጆችም ውስጥ ታላላቆች ተመሳሳይ ሚና አላቸው፡፡ ወላጆች ልጆችን፣ አያቶች የልጅ ልጆችን፤ ሽማግሌዎች መንደርተኞችን በባሕል፣ በእምነት፣ በሞራል ይመራሉ፡፡ አንዲት ሀገር ተው የሚል አባትና እናት፣ የሚያስታርቅ ሽማግሌ፤ ተሞክሮውን የሚያካፍል ታላቅ፤ ታሪክና ባሕል ዐዋቂ ጠቢብ፤ የሚፈራና የሚታፈር፣ የሚታይና የሚከበር ልዑል ዜጋ (Senior citizen) ከሌላት ሕግና ሥርዓት፣ ባሕልና ሞራል፣ የሀገርና የወገን ክብር ገደል ይገባሉ፡፡

ሀገር ከፍ ብለው የሚታዩ ኮከቦችን ትፈልጋለች፤ ትውልድ አርአያ የሚያደርጋቸው፡፡ ከጣት ጣት እንደሚበልጠው ሁሉ ከዜጋም ዜጋ ይከብራል፡፡ ለሀገር በዋለው ውለታ፣ ለትውልድ በሠራው ሥራ፣ በከፈለው መሥዋዕትነትና ባመጣው ውጤት ዜጋ ከዜጋ ይለያል፡፡ እንደ ብርሃ ድምቀት፣ እንደ ጥበቡ ምጥቀት ከዜጋ ዜጋ ይበልጣል፡፡ ‹ኮከብ እም ኮከብ ይኄይስ ክብሩ- ኮከብ ከኮከብ ክብሩ ይበልጣል› እንዲል፡፡ እነዚህ ዜጎች ናቸው የመንጋው አባቶችና እናቶች፡፡ ትውልዱን በሞራል፣ በባሕል፣ በእምነት፣ በሥራ፣ በሕግና በሥርዓት የሚቀርጹ፡፡ የሚፈራና የሚታፈር በሌለበት ሀገር የዱርዬ ቡድን መመሥረቱ አይቀሬ ነው፡፡ ሀገርን ሲዘርፍ፣ ዜጋን ሲገድል፣ ፍርድ ሲያጓድል፣ ድኻን ሲበድል፣ በሥልጣን ሲባልግ፣ በዘመድ ሲሠራ ምንም የማይመስለው፡፡ ነውሩ ክብሩ የሆነ፡፡ ‹እንብላት እንዝራት› ሲሉት ‹እንብላት› ብቻ የሚል ቡድን መፈጠሩ አይቀሬ ነው፡፡

(ይቀጥላል)

ምዕራብ አፍሪቃ ዉስጥ ከአንድ ሺህ አምስት መቶ በላይ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈዉ የኤቦላ ተኀዋሲ ምሥራቅ አፍሪቃ ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ ዉስጥም መከሰቱን በሳምንቱ መጨረሻ የሀገሩቱ ባለስልጣናት ይፋ አድርገዋል።

የምሥራቃዊ ዩክሬን አማፂያን ከሐገሪቱ መንግሥት ጦር ጋር መዋጋት ከጀመሩበት ካለፈዉ ሚያዚያ ወዲሕ ከሁለት ሺሕ በላይ ሰዎች ተገድለዋል።በአስር ሺሕ የሚቆጠሩ ተፈናቅለዋል።ጦርነቱ አማፂያኑን ትረዳለች በምትባለዉ ሩሲያና የኪየቭን መንግሥት በሚደግፉት ምዕራባዉያን መካካል ከማዕቀብ-ቅጣትና አፀፋ ቅጣት ያደረሰ ጠብ ቀስቅሷል።

በእስራኤልና ሃማስ ታጣቂ ኃይሎች መካከል የተኩስ አቁም ዉል ድርድር ከተቋረጠ ወዲህ ሁለቱ ወገኖች ተመልሰዉ አንዱ ሌላዉ ላይ ጥቃት መሠንዘር ቀጥለዋል። ዘገባዎች እንደሚሉት እስራኤል ዛሬ ባጠናከረችዉ የጦር አዉሮፕላን ድብደባ ጋዛ ዉስጥ ሁለት ትላልቅ ሕንፃዎችን መትታለች።

ተቃውሞ:- በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች፥ የኢንተርኔት አምደኞች፥ የፖለቲካ መሪዎኞችና ሌሎች ዜጎች ጉዳይና የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ዘገባዎች፤