ጥር ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለሚገኙ ለአንዳንድ አንደኛና መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የወጣው የደረጃ እድገት ማስታወቂያ በርካታ መምህራንን እንዳሳዘነ መምህራኑ ለኢሳት ገለጹ:: መምህራን እንዳሉት ለደረጃ እድገቱ እንደዋነኛ መስፈርት ሆነው የተቀመጡት፦ “በልማት ቡድንና በ1 ለ5 አደረጃጀቶች የሚያምን” ፣ ” በቡድኖቹ  በመሳተፍ ውጤት ያስመዘገበ”  የሚሉ  እና  ሌሎች ተመሳሳይ ፖለቲካዊ ይዘት …

የብሪታንያ ፤ የሕዝብ እንደራሴዎች ፣ ትናንት ከቀትር በኋላ ፣ በአዲስ የሥነ ተዋልዶ ሥነ ቴክኒክ በመታገዝ ፣ አንድ ሕጻን ከሦስት ግለሰቦች ፤ ማለትም ከእናትና አባት ሌላ የአንዲት ሌላ ሴት ዘረ መል እንዲወርስ ማድረግ የሚቻልበትን ሁኔታ ፤ በድምፅ ብልጫ ፤ በሕግ መምሪያው ም/ቤት

ከአማን ዉሎዉን የተሰማዉ ግን የዚያች ሐገር ሕዝብ ለሁለት መከፈሉን ጠቋሚ ነዉ።ገሚሱ እንደ ገዢዎቹ ሁሉ ሶሪያና ኢራቅ የመሸጉትን አማፂያን መዉጋት አለብን ይላል።ሌላዉ ደግሞ ምን አግብቶን

የስፖርቱ ድግስ ግን አልተጓደለም።በየስታዲዮሙ ይዘምራል፤ይዘፍናል፤ ይጨፈራል፤ይደነሳል።-ተመልካች።ተጫዋቹም፤ የኮትዲቫሩ ያያ ቶሬ እንደሚለዉ ለየብሔራዊ ክብሩ ይፋለማል-በኳስ ሥለ ኳስ።

‹‹ኢትዮጵያ ሁሌም የአፍሪካ ባለውለታ ናት›› አዲሱ የኅብረቱ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ በድንበር ኮሚሽኑ ውሳኔ መሠረት የኢትዮ ኤርትራ ድንበር እንዲካለል በኤርትራ የቀረበው ጥያቄ፣ በአፍሪካ ኅብረት መሪዎች ውድቅ ተደረገ፡፡ ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ሲካሄድ በሰነበተው የአፍሪካ ኅብረት 24ኛ መደበኛ የመሪዎች ጉባዔ መጠናቀቂያ ላይ የኤርትራ መንግሥት አጀንዳ አስይዞ ነበር፡፡ በኮሚሽኑ ውሳኔ መሠረት የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር እንዲካለልና የኢትዮጵያ ወታደሮችም በኃይል ከያዙት […]

The post ኤርትራ ያቀረበችው የ‹‹ድንበር ይከለልልኝ›› ጥያቄ በአፍሪካ መሪዎች ውድቅ ተደረገ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

ባለፈው ሳምንት የተላለፈውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔን ተከትሎ ዕውቅና የተነፈገው የአንድነት ፓርቲ የአቶ በላይ ፍቃዱ ቡድን አብዛኛው አባላት፣ ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን የሰማያዊ ርቲ ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት አስታወቁ፡፡ ፕሬዚዳንቱ ይህን ያስታወቁት ጥር 26 ቀን 2007 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ በፓርቲው ጽሕፈት ቤት ተገኝተው ፎረም የሞሉ የአንድነት አባላትን በተቀበሉበት ወቅት ነው፡፡ ፓርቲውን መቀላቀላቸው ካስታወቁት የቀድሞው አንድነት […]

The post አብዛኛዎቹ የቀድሞ አንድነት ፓርቲ አባላት ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

የአክሰስ ሪል ስቴት አክሲዮን ማኅበር መሥራችና የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ኤርሚያስ አመልጋ፣ ወደ አገር ቤት ተመልሰው እንዲሠሩ በሕግ ያለመጠየቅ ጥበቃ በማግኘታቸው ምክንያት፣ በሚቀጥለው ሳምንት ወደ አዲስ አበባ እንደሚመለሱ ተረጋገጠ፡፡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደገለጹት፣ አቶ ኤርሚያስ ወደ አገር ቤት የሚመለሱት መንግሥት በሕግ ያለመጠየቅ ጥበቃ ስለሰጣቸው ነው፡፡ አቶ ኤርሚያስ ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ ጥበቃው የተሰጣቸው ከአገር ከወጡ […]

The post አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ሊመጡ ነው appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

ቁምነገር መፅሄት 196

ዶ/ር ዘውዱ ተረፈ ወርቅ በአዲስ አበባ አራት ኪሎ ሊጋባ ቢሮ የሚባለው አካባቢ ባህታ ሰፈር ነው የተወለዱት፡የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ኢትዮጵያ አንድነት ሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በቀድሞው በዳግማዊ ምንሊክ የአሁኑ መስከረም ሁለት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው ያጠናቀቁት፡፡ዘጠነኛና አስረኛ ዳግማዊ ምንሊክ ተምረዋል፡፡ አስራ አንደኛና አስራ ሁለተኛን አለማያ የተማሩ ሲሆን…

ትዕግስት ታደለ – ቁምነገር መፅሄት 196

ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ፈረንሳይ ለጋሲዩን አካባቢ አንቀጸ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል
ቤተክርስቲያን አጠገብ ነው፡፡ በልጅነቱ ከገጠር በእንግድነት ወደ ቤታቸው የሚመጡ ሰዎችን ያነጋገር ዘይቤ
ለማስመሰል በመጣር ለቤተሰብና ለት/ቤት ጓደኞቹ…


መቼም ከጓደኞቹ ጋር ምሳ እንደመብላት የሚያስደስተው ነገር የለም፡፡ ከየትም ቦታ ተሯሩጦ ወደ ቀጠሮው ቦታ ይመጣል፡፡ ምንም እንኳን አንዳንድ ጊዜ ያቺ ያረጀች መኪናው ድንገት እየቆመች ብታስቸግረውም ቀጠሮውን ግን አይሰርዝም፡፡ አሁን የመኪና ማቆሚያ እየፈለገ ነው፡፡ አዲስ አበቤ ሁሉ ለሦስት ቀን ነነዌ ቅበላ ሀገሪቱን በቀንድ ከብት ሀብት አንደኛ ከመሆን ገፍትሮ ሊጥላት በየ ሥጋ ቤቱ ተጠቅጥቋል፡፡ መንገዱም አጥንት እንዳየ ጉንዳን በሚተራመሱ መኪኖች ተሞልቷል፡፡ እዚህ ነው ጓደኞቹ የቀጠሩት፡፡
በዋናው መንገድ በኩል ለመግባት ሞከረና ያለ ማስጠንቀቂያ የሚቆፈረው መንገድ ተዘግቶ አገኘው፡፡ እለፉም አትለፉም የማይል የአፈር ክምር መንገዱን ዘግቶታል፡፡ በታችኛው በኩል ዞረና መጣ፡፡ እንደ ደብረ ዕንቁ አንድ መውጫ ብቻ የቀረለት መንደር በግራ በቀኙ በቆሙት መኪኖች ተጣብቦ ጉርሻ እንዳነቀው ጉሮሮ ውጭ ነፍስ ግቢ ነፍስ ይላል፡፡ በወዲህና በወዲያ ምንም መቆሚያ አልተረፈም፡፡ 

‹በተወደደ ቁጥር ደንበኞቹን የሚጨመር ነገር ቢኖር ሥጋ ቤት ነው› ይላሉ አንድ በላተኛ የታጠቡትን እጃቸውን እያራገፉ ከሥጋ ቤት ወጥተው፡፡ ‹በዚህ የሥጋ ፍቅራችን የጾም ወቅት ባይኖር ምን ይውጠን ነበር› አሉ አብረዋቸው የወጡት ሰው፡፡ እርሱ ግን መሐል መንገድ ቆሞ ማቆሚያ ፍለጋ ያማትራል፡፡ ከኋላው ማለፊያ ያጡት መኪኖች እንደ ገጠር ሠርግ ጡሩንባቸውን ያንጣጡታል፡፡ ከፊት ለፊት ገበያቸው የቀረባቸው መኪና ጠባቂዎች ‹እባክህ እለፍ› ይሉታል፡፡ እርሱ ግን ‹አልበር እንዳሞራ ሰው አርጎ ፈጥሮኛል› እያለ ክንዱን መስኮት ላይ አስደግፎ ቆሟል፡፡
በመሐል ስልኩ ተደወለ፡፡ እኅቱ ነበረች፡፡ ‹‹ምጡ ሊጀምረኝ ነው መሰል ወገቤን እያመመኝ ነው› አለቺው፡፡ ‹‹አይዞሽ፣ በሦስተኛሽ ትጨነቂያለሽ እንዴ፤ ከፈለግሺኝ ደውዪልኝ›› አላትና ዘጋው፡፡ የእኅቱ ባለቤት ለሥራ ወደ ቻይና ሄዷል፡፡ አደራው ያለው እርሱ ጋ ነው፡፡ የጓደኞቹ ነገር ባይሆንበት አብሯት ቢሆን ነበር የሚመርጠው፡፡
አንድ የመኪና ጠባቂ መጣና ‹ቦታ ላሳይህ› አለው፡፡ ተከትሎት ነዳ፡፡ ወደ ውስጥ መግቢያ መንገድ ነው፡፡ ‹‹እዚህ ጋር አቁመው የሚገባ መኪና የለም› አለው፡፡ ስለሰለቸው ብቻ ወስዶ መንገዱን ዘጋና ገተረው፡፡ አንዳንድ ልጆች ‹እ ፍሬንድ ምነው መንገዱን ከረቸምሺውኮ› አሉት፡፡  ዝም ብሏቸው በሩን ቆልፎ ወደ ሥጋ ቤቱ ተጣደፈ፡፡ ማቆሙን አንጂ አቋቋሙን አላየውም፡፡ ከቀጠሮው ሠላሳ ደቂቃ አሳልፏል፡፡ ሥጋ ቤቱ ከጠጅ ቤት ጫጫታን ተውሶ ድብልቅልቁ ወጥቷል፡፡ ማን ምን እንደሚል አይሰማም፡፡ የሚሰማው የቢላዋ ፍጭት ብቻ ነው፡፡ ሁሉም ይጮኻል፣ ሁሉም ይሰማል፡፡ ሁሉም ግን አያዳምጥም፡፡  
በዓይኑ እያማተረ ፈለጋቸው፡፡ እንደ ሞባይል ሠሪ ሁሉም አጎንብሰው ያስነኩታል፡፡ በቅርጻቸው እንጂ በመልካቸው ለመለየት አልቻለም ነበር፡፡የመጀመሪያው ትእዛዝ ተጋምሶ ደረሰ፡፡ ከአራት አቅጣጫ በመጣለት ጉርሻም ከቡድኑ ተቀላቀለ፡፡
                            ***                    ****                    ***             ***            ***
እኅቱ ምጧ እየተፋፋመ መጣ፡፡ ምን እንደሆነ እርሷም አታውቀውም እንጂ ይኼኛውን እርግዝና ቀድሞም ፈርታዋለች፡፡ እንዳመማት ነው የከረመው፡፡ የበካር እርግዝና ይመስላል፡፡ ለወንድሟ ደወለችለት፡፡ ስልኩ ይጠራል፣ ግን አይነሣም፡፡ እየደጋገመች ደወለች፡፡ ለውጥ አልነበረውም፡፡ ሌላ መኪና ያለው ሰው ደግሞ አታውቅም፡፡ የመጨረሻ አማራጯ ይከታተላት የነበረው ሐኪም የነገራትን የስልክ ቁጥር መጠቀም ነበር፡፡ ወደ ሆስፒታሉ ደወለች፡፡ ስልኩን ያነሣው ሰው አምቡላንሱን በአስቸኳይ እንደሚልክላት ቃል ገብቶ አድራሻዋን ወሰደ፡፡
ወገቧን እያመማት፣ ድካምም እየተሰማት አምቡላንሱን መጠበቅ ጀመረች፡፡ ዐሥር፣ ዐሥራ አምስት፣ ሃያ፣ ሠላሳ፣ ዐርባ ደቂቃዎች አለፉ፡፡ መልሳ ወደ አምቡላንሱ ደወለች፡፡ ያነሳው ሰውዬ ‹‹ይቅርታ አንድ ሰው መኪና አቁሞ መንገዱን ስለዘጋብን ነው፣ ትንሽ ታገሽን› አላት፡፡ ምን አማራጭ አለኝ ብላ ጠበቀች፡፡ ሕመሟ ሲበረታ ታክሲ እንዲጠሩላት ጎረቤቷን አስጠራቻቸው፡፡ ቤታቸው ከመንገድ ገባ ያለ በመሆኑ ዋናው መንገድ ድረስ በእግር መጓዝ ነበረባቸው፡፡
እርሳቸው ወደ ዋናው መንገድ ሲያዘግሙ እርሷም ወደ ድካምና ሽንፈት እያዘገመች ነበረች፡፡ መንገዱ ዳር ሲወጡ ሁሉም ባለ ታክሲዎች ለቅበላው ሥጋ ቤት ከትመዋል መሰል ትንንሾ ታክሲዎች የሉም፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ በቅበላ፣ በገብርኤል፣ በአርሴናልና ማንቸስተር የጨዋታ ቀናት ታክሲ ማግኘት ሕልም ነው፡፡ ትልልቆቹም እየሞሉ በኩራት ያልፋሉ፡፡ መቼም ትልልቅ ታክሲዎች ባዷቸውን ሲሆኑ የሚደርስባቸውን የመጠበቅ መከራ የሚበቀሉት ሲሞሉ  በኩራት ገልምጠው በማለፍ ይመስላል፡፡ እንደ መቆም ይሉና እንቁልልጭ ብለው እንደ መሸምጠጥ ይላሉ፡፡  
ጎረቤቷ ሲዘገዩባት ያለ የሌለ ኃይሏን አስተባብራ ወደ ሆስፒታሉ ደወለች፡፡ ስልኩን ያነሣው ሰውዬ ‹‹እባክሽ አንድ ምን እንደምለው የማላውቅ ሰው መንገድ ዘግቶ ጠፍቷል፡፡ እዚያ ሥጋ ቤት ሳይገባ አልቀረም፡፡ ሰው ልከን በታርጋ ቁጥሩ ብንፈልገውም ጫጫታው ነው መሰል ሊሰማን አልቻለም፡፡ በወዲያ በኩል ያለው መንገድ ደግሞ ተቆፍሯል፡፡ ከቻልሽ ሌላ መኪና ይዘሽ ነዪ›› አላት፡፡ ተስፋ ወደ መቁረጥ ልትገባ ስትል ጎረቤቷ ከቅበላ የተረፈች ታክሲ ይዘው መጡና ከቤት ሠራተኛዋና ከሹፌሩ ጋር አፋፍሰው ይዘዋት በረሩ፡፡
የሥጋ ቤቱ መንገድ እንደተጨናነቀ ነው፡፡ ቅበላውን ተቀብለው፣ ጾሙንም በሙዳ ሥጋ ይዘው የሚወጡት ተመጋቢዎች አልፋለሁ አታልፍም እየተነታረኩ ነው፡፡ የታክሲው ሾፌር ‹‹ኧረ እባካችሁ ወላድ ይዘን ነው›› እያለ በመስኮቱ በኩል ይለምናል፡፡ አንዳንዶቹ ጩኸቱን በመከራ ሰምተው ለመጠጋት ይሞክራሉ፡፡ ይገጩናል ብለው የፈሩ ሌሎች ደግሞ በጡሩንባ ድምጽ ያባርሯቸዋል፡፡ የሞተ አህያ ለመብላት አሞሮች የሚያሳዩት ትርዒት ይመስል ነበር፡፡
እንደምንም ብሎ የጎንና ጎን መመልከቻ መስተዋቱን እያጠፈ፣ በዔሊ ፍጥነት የውስጥ መንገዱን አለፈውና ወደ ሆስፒታሉ ለመግባት ወደ ግራ ሲታጠፍ መንገዱ ተዘግቷል፡፡ ከወዲያ ማዶ አንድ አምቡላንስ ቆሟል፡፡ ነጭ ገዋን የለበሱ የሆስፒታሉ ሰዎች ወዲያና ወዲህ ይራወጣሉ፡፡ ፖሊሶች መኪና አቋሚውን ቢያገኙት ሊቦጫጭቁት በሚደርስ ንዴት ውስጥ ናቸው፡፡ የትራፊክ ፖሊሶች ታርጋ ይፈታሉ፡፡ የታክሲው ሾፌር ደግሞ ‹አሳልፉኝ› እያለ ይጮኻል፡፡
አንድ አልፎ ሂያጅ ሽማግሌ ግን ግራ ቀኙን ሲያዳምጡና ሲቃኙ ቆዩና ‹‹ሰው ማለትኮ ለሚፈጽመው ነገር አንዳች ምክንያት ያለው፣ የሚሠራው ነገር ሊያስከትል የሚችለውን ነገር ቀድሞ አስቦ የሚሠራ ፍጡር ማለት ነው፡፡ የሚያደርጉት ነገር ምን ሊያስከትል እንደሚችል የማያስቡ፣ በዚህም የተነሣ ኃላፊነት ሊሰማቸው የማይችል እንስሳት ብቻ ናቸው፡፡ እስካሁን እንደ ሰው የሚኖሩና የሚያስቡ እንስሳት አልተገኙም፤ እንደ እንስሳት የሚኖሩና የሚያስቡ ሰዎች ግን በብዛት አሉ፡፡ ኃላፊነት ሁለት ዓይነት ነው፤ የሹመት ኃላፊነት አለ፡፡ ለሥራና ለአገልግሎት የሚሰጥ፡፡ ዋናው ግን እርሱ አይደለም፡፡ ዋናው ሁለተኛው ነው፡፡ ሰው በመሆን ምክንያት ብቻ የሚመጣ ኃላፊነት፡፡ ሰው ስለሆንክ ብቻ ነገሮችን ሁሉ በኃላፊነት ስሜት እንድታከናውን የሚያስገድድህ የሰውነት ኃላፊነት አለብህ፡፡አንድን ፈረስ ከነ ጋሪው ብትለቅቀው ልክ እንደዚህ ሰውዬ አንዱ ቦታ ላይ ይቆማል፡፡ የቆመበት ምክንያት ሣር ስላገኘ ብቻ ነው፣ ወይም ጥላ፡፡ አለቀ በቃ፡፡ በመቆሙ የሚያመጣውን ነገር እንዲያስብ አይጠበቅበትም፡፡ ኃላፊነት የማይሰማቸው ሰዎችም እንደዚህ ፈረስ ናቸው፡፡›› አሉና እየተራገሙ ሄዱ፡፡
ሁለት ነርሶች መጡና እርጉዟን ተሸከሟት፡፡ ግርግሩን ሲያደምቅ የነበረው ሁሉ ከፊት ከኋላ ከቀኝ ከግራ ደግፎ መንገድ ዘግቶ የቆመውን መኪና አሻገራት፡፡ አምቡላንሱ እንደምንም ፊቱን መልሶ ይዟት ወደ ሆስፒታሉ ሸመጠጠ፡፡
መንገድ ዘግቶ በቆመው መኪና ዙሪያ ፖሊሱ፣ መኪና ጠባቂው፣ በልቶ ተመላሹ፣ ወሬ ጠምቶት የቆመው አላፊ አግዳሚ ወጉን ጮክ እያለ ይሰልቃል፡፤ አንዳንዱ ያወግዛል፤ አንዳንዱ ባለ መኪናው ሲመጣ ሊፈጠር የሚችለውን እየገመተ ይተነትናል፤ሌላው ደግሞ መወሰድ ስላለበት ርምጃ ሐሳብ ይሰጣል፤የባሰበትም ‹አይ አበሻ› እያለ ራሱን ጨምሮ ይረግማል፡፡ በዚህ መሐል የታጠቡበትን እጅ እያፍተለተሉ አንድ አምስት ጎልማሶች ጮክ ብለው እያወሩ መጡ፡፡ አንዱ ከመካከላቸው ነጠል ብሎ ሰዎቹ ወደተሰበሰቡበት አቀና፡፡ የተሰበሰቡት የርሱን መኪና ከበው መሆኑን፣ ፖሊሶቹ መቁነጥነጣቸውን ሲያይ አንዳች ክፉ ነገር ሸተተው፡፡
‹‹አንተ ነህ ባለ መኪናው›› አለ የትራፊክ ፖሊሱ፡፡
‹‹አዎ›› ሲለው ምን ሊመጣ ይሆን ብሎ እያሰበ ነበር፡፡
‹‹መንጃ ፈቃድህን ከመንገድ ላይ ነው እንዴ ያገኘኸው›› አለው ፖሊሱ፡፡
ባለ መኪናው ዝም አለ፡፡
ከግራ ከቀኝ የስድብና የርግማን መዓት ይወረወርበታል፡፡ ጓደኞቹ ሁኔታውን አይተው መጡ፡፡ 
‹‹በል አስነሣና ወደ ፖሊስ ጣቢያ›› አለው ፖሊሱ፡፡ ጓደኞቹ የተፈጠረውን ነገር ከከበቡት ሰዎች እየጠያየቁ ነው፡፡ መኪናውን ለማስነሣት በሩን ከፈተ፡፡ ጥሎት የሄደውን ስልኩን አንሥቶ ሲያየው ከሃያ በላይ አምላጭ ስልክ አለው፡፡ ፖሊሱ እያጣደፈው እንደምንም ያመለጡትን ስልኮች አየ፤ አብዛኛው የእኅቱ ነው፡፡ ግራ ገባው፡፡
‹‹አንዴ ልደውል›› አለው ፖሊሱን
‹‹ባክህ ወደ ጣቢያ ሂድ፤ ስንት ችግር እንደፈጠርክ እዚያ እንነግርሃለን›› አለው ፖሊሱ፡፡
‹‹እኅቴ ስለሆነች ነው›› አለ፡፡
‹‹እዚህ መኪናውን ገትረህ የስንቱን እኅት ስታስለቅስ ነው የቆየኸው፤ ባክህ ንዳው›› አለ ፖሊሱ፡፡
ቁልፉን ተረክ አድርጎ አስነሣው፡፡ ልቡ ግን በድንጋጤና በሥጋት እንደ ጥምቀት ከበሮ ይመታል፡፡ ፖሊስ ጣቢያ ሲደርስ ፖሊሱ ቁጣው አልበረደም ነበር፡፡
‹‹እንዴት አንተ የሆስፒታል መንገድ ትዘጋለህ?›› አለው በንዴት
‹‹አላወቅኩም ነበር›› ብሎ መለሰለት፡፡
‹‹እንዴት ነው የማታውቀው፤ ምልክት ማየት አቅቶህ ነው››
‹‹ስለቸኮልኩ ልጆቹ አቁመው ሲሉኝ አቆምኩት››
ጣቢያ ያሉት ሁሉ ከራሱ ውጭ ግድ የሌለው፣ ለሌላው የማያስብ፣ ሥርዓት የለሽ፣ ማን አለብኝ ባይ ጎረምሳ አድርገው ገመቱት፡፡ ለማስረዳት ብዙም አልጣረም፡፡ ልቡ ከእኅቱ ጋር ነበር፡፡ ጣጣውን በግማሽ ሰዓት ውስጥ ጨርሶ ቅጣቱን በቀሪው ግማሽ ሰዓት ተቀጥቶ፣ ወደ እኅቱ ደወለ፡፡ አንድ ሴትዮ አነሡና ‹‹ሐኪሞቹ አትግቡ ስላሉ ሰው አታናግርም›› አሉት፡፡ ጎረቤቷ ነበሩ፡፡
‹‹የት ነው ያለቺው›› ሲል ጠየቃቸው፡፡ ቦታውን ሲነግሩት እዚያው አካባቢ ነበር፡፡ ከፖሊስ ጣቢያ በር ላይ የቆመውን ፖሊስ ሲጠይቀው ‹‹ቅድም ያንን ሆስፒታል ዘግተህ አይደል እንዴ የቆምከው›› አለው፡፡ ሌላ ነገር ከመከሰቱ በፊት አመስግኖት ወጣ፡፡ ልቡ ግም ገጭ ይላል፡፡ መኪና አቁሞ በነበረበት መንገድ በኩል ወደ ሆስፒታሉ ሲገባ መንገደኞቹ በሙሉ መኪናውን የለዩት ይመስል በክፉ ዓይን ነበር የሚያዩት፡፡ መኪናውን ግቢው ውስጥ ሲያቆም ብዙዎች ይጠቋቆሙበታል፡፡ ወደ ሕንፃው ገባና የእኅቱን ስም ጠርቶ የአልጋ ክፍሏን ጠየቀ፡፡ ከመስኮቱ ኋላ ያለቺው ልጅ ቁጥሩን ነገረቺውና ‹‹የበደልካትን ልትክሳት ነው እንዴ›› አለቺው፡፡
‹‹ለምን እክሳታለሁ›› አለ ገርሞት
‹‹አንተ አይደለህ እንዴ መንገድ ዘግተህ አምቡላንስ የከለከልካት›› አለቺው በዓይኗ እየገረፈች
‹ዋት?› አለና ወደ ደረጃው በሩጫ ወጣ፡፡ ልቡ ከደረቱ ውጭ ያለ መሰለውና በእጁ ዳሰሰው፡፡
የሠፈሩ ሰው በሩ ላይ ከብቧል፡፡ ማንም በበጎ አልተቀበለውም፡፡
ጎረቤቷን ሴትዮ ፈለገና ‹‹እንዴት ናት›› አላቸው
‹‹ሐኪሞቹ ደኅና ናት ብለዋል›› አሉት፡፡
‹‹ምነው ባሰባት እንዴ››
ጎረቤቷ በኀዘን መሬት መሬት እያዩ ‹‹ምን አንድ የተረገመ ሰውዬ የሆስፒታሉ መንገድ ላይ መኪናውን አቁሞ አምቡላንሱስ በየት ይምጣ፣ እርሷን በታክሲ ስናመጣት በየት ትግባ፡፡ በዚህ የተነሣ አደጋ ውስጥ ልትወድቅብን ነበር፤ መድኃኔዓለም አተረፈልን፤ አንተም ስልክህን አታነሣውም›› አሉና ቀና ሲሉ  እርሱ የለም፡፡ የመጀመሪያውን ርግማን እንደሰማ አእምሮውን ስቶ ተንሸራትቶ ወድቋል፡፡

በመድብለ ፓርቲ ሰርዓት ስልጣን ይያዛል ብሎ ማመን ህዝቡን ማታለል ነው

የአንድነት ፓርቲ አላማዎችና እሴቶች በገዢው ፓርቲ እና ምርጫ ቦርድ ህገወጥ ሴራ አይጠፋም!!! – ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሠጠ መግለጫ

ገዢው ፓርቲ ለጻፋቸው ህጎችም ሆነ ይህን እንዲተገብሩ ኃላፊነት የወሰዱትን ሰዎች ክብር በሚያዋርድ መንገድ፤ በየደረጃው ያሉ ምርጫ ቦርድ ኃላፊዎችም ለመዋረድ ፈቃደኛ ሆነው በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) አባላት አንድ ድምፅ ለማግኘት ለተቸገረ፤ ነገር ግን ለገዢው ፓርቲ ለመላላክ ቁርጠኛ ለሆነ ግለሰብ ዕውቅና ሰጥቻለሁ ማለቱ የሚታወስ ነው፡፡ ይሁን እንጂ አንድነት ፓርቲ የተቋቋመበት መሰረት የምርጫ ቦርድ ዕውቅና ሳይሆን በእያንዳንዱ አባላት ዘንድ የሚቀጣጠለው የነፃነት ስሜት እና ኢትዮጵያዊነት ነው፡፡ የአንድነት ፓርቲን መንፈስ፣ አላማዎቸና እሴቶች በዚህ ዓይነት እኩይ ደባ ከአባላትና ደጋፊ አዕምሮ ማውጣት አይቻለም፡፡

የምርጫ ቦርድ ተብዬው ተቋም በገዢው ፓርቲ ደህንነት የተደራጁ የፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ አባላት ያልሆኑ ሰዎች ያካሄዱትን ህገወጥ ስብሰባ ጉባዔ ነው በማለት እውቅና ሰጥቻለሁ ሲል፤ የተሰበሰቡት ሰዎች የአንድነት አባላት መሆናቸውን እና የጠቅላላ ጉባዔ ተወካይ መሆናቸውን አረጋግጣችኃል ወይ? ለሚል ቀላል የጋዜጠኛ ጥያቄ መልስ መስጠት አልቻሉም፡፡ ዕቅዱም አንድነትን እንደተቋም ማፍረስ ስለነበር ይህን ሊያስፈፅም ለሚችል ተላላኪ መስጠታቸውን በይፋ ከተናገሩ በኋላ በማግስቱም የፓርቲውን ፅ/ቤት በጠብመንጃ አፈሙዝ አስወርረው ለህገወጥ ቡድን በህገወጥ መንገድ አስረክበዋል፡፡
የአንድነት ፓርቲ በዚህ ዓይነት ህገወጥ ድርጊት የሚፈርስ አይደለም፡፡ የአንድነት አባላት በየትም ቦታ የምትገኙ ሁሉ ይህን ህገወጥ እርምጃ በፅኑ እየተቃወማችሁ ለነፃነትና ለኢትዮጵያዊነት የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመከፍል ዝግጁ መሆን ይኖርባቸኋል፡፡ አንድነት ፓርቲ በሰላማዊ ትግል ስልት የሚያምን በመሆኑ ይህን ትግል በላቀ ደረጃ ለማስቀጠል አበክሮ ይስራል፡፡ እያንዳንዱ አባልም አሁን በተፈጠረው ሁኔታ ሳይደናገጥ ለሰላማዊ ትግል ያለውን ፅናት እንደሚያስቀጥል እምነታችን ነው። በአንድነት ስራ አስፈፃሚ እምነት አሁን ባለው ሁኔታ የመድብለ ፓርቲ ፖለቲካ ተቀበረዋል የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰናል።

በመሆኑም ስርዓቱ ለመድብለ ፓርቲ ፖለቲካ የሚመች የአስተሳሰብ ለውጥ እሰካላመጣ ድረስ ምርጫን በየአምሰት ዓመት የሚደረግ ክብረ በዓል አድርጎ ለማድመቅ እና የህዝብ ሀብት ለማባከን በሚደረግ ሂደት ተሳተፊ ለመሆን አዲስ ፓርቲ መመስረትም ሆኖ አሁን ካሉት ፓርቲዎች ጋር ተቀላቅሎ መታገል የሚያመጣው ለውጥ የለም፡፡ ምክንያቱም እነርሱም ልከ በአንድነት ላይ እንደተደረገው በሀይል እንዲፈርሱ የማይደረጉበት ምንም ዓይነት ዋስትና አለ ብለን ስለማናምን ነው። ከዚህ በኋላ በመድብለ ፓርቲ ሰርዓት ስልጣን ይያዛል ብሎ ማመን ህዝቡን ማታለል ነው የሚል ፅኑ እምነት አለን፡፡ ነገር ግን አሁንም የፓርቲ ፖለቲካ አላበቃም ብለው የሚያምኑ የአንድነት አባላት ካሉ በራሳቸው ነፃ ውሳኔ ወደ ፈለጉት ፓርቲ ተቀላቅለው የመታግል መብታቸው የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ አሁን ካለበት አምባገነናዊ ስርዓት ተላቆ ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲሸጋገር ለማድረግ ህዝቡ የትግሉ ባለቤት ሆኖ የስርዓት ለውጥ እንዲመጣ እኛም የበኩላችንን ሀገራዊ ግዴታችንን ለመወጣት ቁርጠኞች ነን፡፡

ድል የህዝብ ነው!!!
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)

በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ለ16 ጊዜ ያህል ለስድስት ወራት ፍርድ ቤት የተመላለሱት እና ለ9 ወራት በእስር የሚገኙት የዞን9 ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች ዛሬ ለ17ተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበዋል ፡፡
በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃላቸውን አንዲሰጡ የተጠበቀ ቢሆንም በተቃራኒው ተከሳሾች አቤቱታ አለን አቤቱታችን የእምነት ክህደት ቃል ከመስጠታችን በፌት መቅደም አለበት ብለው ተከራክረዋል፡፡ ዳኛው ዛሬ የእምነት ክህደት ቀጠሮ ነው ሌላ አቤቴታ አንቀበልም ቢሉም ፍርድ ቤቱ የራሱን ቃል አጥፏል ስለዚህም የመሃል ዳኛው አፋጣኝ ፍትህ የማግኘት መብታችንን ስለነፈጉን እንዲሁም ራሱ ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ትእዛዝ ሽሮ ያልተሻሻሉ ክሶችን በማካተት መከላከል የማንችልበት ሁኔታ ላይ ስላስቀመጡን መሃል ዳኛው የፍትህ ሂደቱን ዳኛ ሸለመ በቀለ ከቦታቸው ካልተነሱልን የእምነት ክህደት ቃላችንን ለመስጠት አንቸገራለን የሚል አቤቱታቸውን አቅርበዋል ፡፡
በዚህም መሰረት አቤቱታው ያልተጠበቀ የሆነባቸው ዳኛ የመገረም ፌት ያሳዬ ሲሆን አቤቱታው ላይ ለመወሰን ለነገ ጠዋት በ3 ሰአት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ችሎቱ ነገ ጠዋት ለ18ተኛ ጊዜ ደግሞ ይሰየማል፡፡


ጥር ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-<<ብሄራዊ ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ በወሰኑብን ፖለቲካዊ ውሳኔ ምክንያት አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ተነጥቀናል>> ያሉ የአንድነት ፓርቲ አባላት› በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን ሰማያዊ ፓርቲ አስታውቋል፡፡ በእነ በላይ ፍቃዱ አመራርነት አንድነት ፓርቲን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሲመሩ የነበሩ አመራሮች ዛሬ ጥር 26 ቀን 2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ …

ጥር ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ላለፉት 9 ወራት በ እስር ላይ ይሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማርያንና ጋዜጠኞች ሰብሳቢ ዳኛው ከችሎት እንዲነሱ ጠየቁ፡፡ ጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ ለ17ኛ ጊዜ ጥር 26/2007 ዓ.ም  በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ልደታ ምድብ  ቸሎት ሲቀርቡ  በጽሁፍ ባቀረቡት አቤቱታ፦ የችሎቱ ሰብሳቢ …

ገዢው ፓርቲ ለጻፋቸው ህጎችም ሆነ ይህን እንዲተገብሩ ኃላፊነት የወሰዱትን ሰዎች ክብር በሚያዋርድ መንገድ፤ በየደረጃው ያሉ ምርጫ ቦርድ ኃላፊዎችም ለመዋረድ ፈቃደኛ ሆነው በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) አባላት አንድ ድምፅ ለማግኘት ለተቸገረ፤ ነገር ግን ለገዢው ፓርቲ ለመላላክ ቁርጠኛ ለሆነ ግለሰብ ዕውቅና ሰጥቻለሁ ማለቱ የሚታወስ ነው፡፡ ይሁን እንጂ አንድነት ፓርቲ የተቋቋመበት መሰረት የምርጫ ቦርድ ዕውቅና ሳይሆን በእያንዳንዱ […]

ጥር ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአመዛኙ  ኢትዮጵያውያን፣ ሶማሊያውያንና የአካባቢው ሀገራት ዜጎች እንደሆኑ የሚገመቱ  ስደተኞች ሲጓዙባት የነበረች አነስተኛ ጀልባ ቀይ ባህር ሰጠመች። <<ሳባ>>የተሰኘው የየመን መንግስት የዜና አገልግሎት ጀነራለ ሳሊህ አልሰብሪ የተባሉ የሀገሪቱን ባለስልጣናት  ዋቢ በማድረግ  እንደዘገበው   ስደተኞቹን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረችው ጀልባ  <<ታይዚ>>ተብላ ወደምትጠራው  የየመን ደቡባዊ ምእራብ  ግዛት ስታመራ  ነው በመጥፎ አየር ሳቢያ የሰጠመችው። …

ጥር ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቱርክ ዜጎች በመሰረቱት አይካ ጨርቃጨርቅ ውስጥ የሚሰሩ ከ8 ሺ ያላነሱ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ጠይቀው የጠበቁትን ጭማሪ ባለማግኘታቸው አድማ መተዋል። አድማው የተጀመረው ባለፈው ቅዳሜ ሲሆን ፣ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ አድማው ቀጥሎአል።

የፕሮግራም መግለጫ

ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡

የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡

ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡

ርዕሠ-ከተማ ሠነዓን ጨምሮ አብዛኛ ሐገሪቱን የሚቆጣጠሩት የሁቲ አማፂያን፤ ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች የሽግግር መንግሥት እንዲመሠረቱ የሠጡት የሠወስት ቀን ቀነ-ገደብ ነገ ማምሻዉን ያበቃል።

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ሃይሎች ትናንት አዲስ አበባ ላይ አዲስ የተኩስ አቁም ስምምነት ተፈራረሙ መባሉ ይታወሳል።ካሁን ቀደም ሶስት ተመሳሳይ ስምምነቶችን ፈርመው ተግባራዊ ማድረግ ያልቻሉት ሳልቫ ኪር እና ሪየክ ማቻር ወደ ጦርነት ለመግባት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ሱዳን ትሪቢዩን ዛሬ ዘግቧል።

የቀድሞው የጀርመን ፕሬዝዳንት ሪቻርድ ፎን ቫይሴከር ባለፈው ቅዳሜ አርፈዋል ። ለ10 ዓመታት የጀርመን ፕሬዝዳንት የነበሩት የፎን ቫይሴከር ማንነት የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው ።

በሕፃንነት ተገቢዉን ክትባት ማግኘት አስቀድሞ በመከተብ ለመከላከል ከሚቻሉ በሽታዎች፣ የአካል ጉዳት እንዲሁም ሞት ለመዳን እንደሚረዳ ይታመናል። ባለፉት አስራ አምስት ዓመታት ከአምስት ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት በሚሰጠዉ ክትባት የስድት ሚሊዮን ሕፃናትን ሕይወት ማትረፍ ተችሏል።

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ በወሰኑብን ፖለቲካዊ ውሳኔ ምክንያት አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ተነጥቀናል ያሉ የአንድነት ፓርቲ አባላት› በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አስታወቁ፡፡ በእነ በላይ ፍቃዱ አመራርነት አንድነት ፓርቲን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሲመሩ የነበሩ አመራሮች ዛሬ ጥር 26 ቀን 2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት ከቀድሞ ፓርቲያቸው አንድነት ጋር የፕሮግራምም ሆነ የስትራቴጂ ተመሳሳይነት […]

‪- ጋዜጠኛ ኤዶም ጸጉሯን በመላጨት ኢፍትሃእኢነት እና ዘረኝነት መስፋፋቱን በይፋ ተቃውማለች:: – የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ዳኛ እንዲቀየርላቸው ማመልከቻ አቅርበዋል:: በዛሬው እለት ፍርድ ቤት የቀረቡት ዞን ዘጠኝ ጦማርያን ጋዜጠኞች እንዲሁም የዲብርሃን አዘጋጅ የሆነው ዘላለም ወርቃለማሁ እና ከጋምቤላ በአሸባሪነት የተፈረጁ ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል::በኢትዮጵያ የሆላንድ ኤምባሲና ሌሎች ዲፕሎማቶች በፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለመከታተል ተገኝተዋል:: በዛሬው እለት ጋዜጠኛ ኢዶም […]

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ በወሰኑብን ፖለቲካዊ ውሳኔ ምክንያት አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ተነጥቀናል ያሉ የአንድነት ፓርቲ አባላት› በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አስታወቁ፡፡ በእነ በላይ ፍቃዱ አመራርነት አንድነት ፓርቲን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሲመሩ የነበሩ አመራሮች ዛሬ ጥር 26 ቀን 2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት ከቀድሞ ፓርቲያቸው አንድነት ጋር የፕሮግራምም ሆነ የስትራቴጂ ተመሳሳይነት […]

The post ሰበር ዜና – የአንድነት አባላት በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

የአንድነት አባላት በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ በወሰኑብን ፖለቲካዊ ውሳኔ ምክንያት አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ተነጥቀናል ያሉ የአንድነት ፓርቲ አባላት› በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አስታወቁ፡፡
በእነ በላይ ፍቃዱ አመራርነት አንድነት ፓርቲን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሲመሩ የነበሩ አመራሮች ዛሬ ጥር 26 ቀን 2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት ከቀድሞ ፓርቲያቸው አንድነት ጋር የፕሮግራምም ሆነ የስትራቴጂ ተመሳሳይነት ወዳለው ሰማያዊ ፓርቲ ተቀላቅለው ሰላማዊ ትግላቸውን ለመቀጠል መወሰናቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡
መግለጫውን የ‹ቀድሞው አንድነት ፓርቲ› አፈ ጉባዔ የነበሩት አቶ አበበ አካሉ፣ ምክትል አፈ ጉባዔው አቶ ፀጋዬ አላምረው፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ነገሰ ተፋረደኝ እንዲሁም የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ሌሎችን በመወከል ሰጥተዋል፡፡

‹‹የምናምነው በሰላማዊ ትግል ብቻ ነው፡፡ ይህን ሰላማዊ ትግል ለመምራት ደግሞ ሰማያዊ ፓርቲ ብቁ ነው ብለን በማመን ፓርቲውን ተቀላቅለናል›› ብለዋል በመግለጫው ላይ የተወከሉት አዲሶቹ የሰማያዊ አባላት፡፡
በዚህ መሰረትም በርከት ያሉ አመራሮችና አባላት በይፋ የሰማያዊ ፓርቲ የአባልነት ፎርም ሞልተዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአንድነት አባላት ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አስመልክቶ መግለጫ ለመስጠት ወደ ሰማያዊ ቢሮ ባቀኑበት ወቅት ፖሊስ ሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ድረስ በመግባት ‹‹በሰማያዊ ስም መግለጫ የሚሰጡ አካላት እንዳሉ ሰለሰማን ነው›› በሚል ለፓርቲው አመራሮች ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡
Image

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር በፌደራል አቃቤ ህግ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት እየታየ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮችና ሌሎች በተመሳሳይ መዝገብ የተከሰሱት ተከሳሾች በቀረበባቸው ክስ ላይ ያቀረቡት መቃወሚያ ውድቅ ተደረገባቸው፡፡ አመራሮቹ ጥር 26 ቀን 2007 ዓ.ም ችሎት ቀርበዋል፡፡ በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የተከሰሱት የአንድነት፣ የሰማያዊና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች የሆኑት […]

The post የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች የክስ መቃወሚያ ውድቅ ተደረገ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች በዛሬው እለት ካንጋሮ ፍርድ ቤት ቀርበዋል::
Image
– ጋዜጠኛ ኤዶም ጸጉሯን በመላጨት ኢፍትሃእኢነት እና ዘረኝነት መስፋፋቱን በይፋ ተቃውማለች::
– የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ዳኛ እንዲቀየርላቸው ማመልከቻ አቅርበዋል::
Minilik Salsawi
በዛሬው እለት ፍርድ ቤት የቀረቡት ዞን ዘጠኝ ጦማርያን ጋዜጠኞች እንዲሁም የዲብርሃን አዘጋጅ የሆነው ዘላለም ወርቃለማሁ እና ከጋምቤላ በአሸባሪነት የተፈረጁ ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል::በኢትዮጵያ የሆላንድ ኤምባሲና ሌሎች ዲፕሎማቶች በፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለመከታተል ተገኝተዋል::

በዛሬው እለት ጋዜጠኛ ኢዶም ጸጉሯን በመላጨት በወያኔ መንግስት እና በእስር ቤቱ ያለውን በፍርድ ቤቱ የሚታየውን አድልዎ የሚደርሰውን ኢፍትሃዊነት እና ዘረኝነት በመቃወም አሳይታለች::..ተከሳሽ ተብለው በወያኔ የተፈረጁት ወገኖቻችን ዳኛው እንዲቀየሩላቸው የተየቁበትን አቤቱታ ከታች ያንብቡት::
ImageImage

Image

በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው የዞን ዘጠኝ ጦማርያንና ጋዜጠኞች ሰብሳቢ ዳኛው ከችሎት እንዲነሱ ጠየቁ፡፡ ጥር 26/2007 ዓ.ም ለ17ኛ ጊዜ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ልደታ ምድብ የቀረቡት ጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ የችሎቱ ሰብሳቢ ዳኛ የሆኑት አቶ ሸለመ በቀለ ‹‹የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብታችንን አላስከበሩልንም›› በሚል ከችሎት እንዲነሱ በጽሑፍ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የተሰየመው […]

The post ጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ ሰብሳቢ ዳኛው ከችሎት እንዲነሱ ጠየቁ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

(ከቶፋ ቆርቾ) ሴትዮዋ (ወ/ሮ ሆሰሃና አዳዳ)…. በጣም ትገርማለች…. ክስ ስታቀርብ ልክ እንደ አደቬነቸር ነዉ የምታወራዉ…. በሆነዉ ነገር የማፈርና የመፀፀት ስሜት አይታይባትም… እንደዉም ዘና ብላ ‘ከሴሌበሪቲ’ ጋር መማገጧን እንደ ዝና የምታወራ ነዉ የምትመስለዉ…. ‘ሴቶች ሆይ ፓስተር ተከስተን አወጣሁት …እንቁልልጭ!’ የሚል አይነት ድምፀት አላት… እንደዉም…እንደዉም ዝነኛ ለመሆን ያደረገችዉ ነዉ የሚመስለዉ….ፍራጅ አትበሉኝ እና! ቀሚሳን ግለባ ሙታንታዋን አዉልቃ ከአንዴም […]

The post ፓስተር ተከስተ እና ወዘሮዋ ….. ወስባዊ ቅሌት….(ከቶፋ ቆርቾ) appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሠጠ መግለጫ ገዢው ፓርቲ ለጻፋቸው ህጎችም ሆነ ይህን እንዲተገብሩ ኃላፊነት የወሰዱትን ሰዎች ክብር በሚያዋርድ መንገድ፤ በየደረጃው ያሉ ምርጫ ቦርድ ኃላፊዎችም ለመዋረድ ፈቃደኛ ሆነው በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) አባላት አንድ ድምፅ ለማግኘት ለተቸገረ፤ ነገር ግን ለገዢው ፓርቲ ለመላላክ ቁርጠኛ ለሆነ ግለሰብ ዕውቅና ሰጥቻለሁ ማለቱ የሚታወስ ነው፡፡ ይሁን እንጂ አንድነት ፓርቲ […]

The post የአንድነት ፓርቲ አላማዎችና እሴቶች በገዢው ፓርቲ እና ምርጫ ቦርድ ህገወጥ ሴራ አይጠፋም!!! – ከአንድነት ፓርቲ የተሠጠ መግለጫ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

ትዕግስት ታደለ : ቁም ነገር መፅሄት 195

የተወለደችው በደብረ ማርቆስ ከተማ ቀበሌ ዘጠኝ የሚባለው አካባቢነው፡፡ በልጅነቷ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በተለምዶ አስራ ሥምንት ማዞሪያ የሚባለው አካባቢ አደገች ፡ ፡ ገና በለጋ እድሜዋ እሷ ሳታስበው የኪነጥበብ ፍቅሩ ቀድሞ በሯን አንኳኳ፡፡ የመጀመሪያ ስራዋ ብዙም ነፍስ ባላወቀችበት ጊዜ የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ሆና የሎተሪ ማስታወቂያ እንድትሰራ…

ቁም ነገር መፅሄት 196

ሰሞኑን በማህበራዊ ድረገፆች እና አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ላይ ስሟ በተደጋጋሚ የሚነሳው አርቲስት አስቴር በዳኔ የሀገራችን ‹ታዋቂ› አርቲስቶችን ባሳተፈውና ህወሃት የተመሰረተበትን 40ኛ ዓመት ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው የጉብኝት ፕሮግራም በጠየቀቻቸው ጥያቄዎች መነጋገሪያ አጀንዳ ሆና ሰንብታለች፡፡ አስቴር ለመከላከያ ሚኒስትር ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ለሆኑት…

ቁም ነገር መፅሄት 196

መቼም የሀገራችን የመጀመሪያው እንደሆነ ስለሚነገርለት ቴአትር ቤት አላውቅም አትለኝም፡፡ አንጋፋው ቴአትር ቤት ሀገር ፍቅር በጠላት ፋሽስት ወረራ ወቅት ተቋቁሞ የተለያዩ አርበኝነትን የሚያበረታቱ ዜማችንንና ድራማዎችን ያቀርብ እንደነበር መቼም ታውቃለህ አይደል?
እናስ? አንጋፋው ቴአትር ቤት ምን ሆነ? ምንም…

ለምን ባርያ ሆነን? ለምን ባንድ ቡድን ( ዘረኛ ቡድን ) የበላይነት ይህን ያህል ጊዜ መከራችንን አየን ፣ ለምን ለውጥ ማምጣት አቃተን የሚለውን ነገር ስብሰለሰልበት ነበር ። እንደ ትልቅ ምክንያት ሆኖ የገባኝ እና የተረዳሁት አንዱና ዋነኛ ምክንያት ” የህይወታችንን ብዙን ጊዜ ያለ ሥራ መንገድ ላይ ቆመን ስለሆነ የምናሳልፈው ፣ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ለማሰብ ፣ ለማንበብ ፣ […]

The post የሄዋን አመጽ (ሄኖክ የሺጥላ) appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

ጥር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራና በትግራይ ክልሎች መካከል የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ፣ ህዝቡን አስተባብረዋል የተባሉ ሰዎች እየታሰሩ ሲሆን፣ ሌሎች አመራሮችም እየታደኑ ነው። የኢሳት የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በአካባቢው ለተፈጠረው ውጥረት ተጠያቂ ናቸው ተብለው ከተጠረጠሩት መካከል አቶ አዋጁ አቦሃይ ቅዳሜ ጥር 23 ቀን 2007 ዓም በ8 የፌደራል ፖሊሶች መሳሪያቸውን ተቀምተው ታስረዋል። ሶረቃ ውስጥ …

ጥር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቦርድ ያወጣው ረቂቅ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ውድድር የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሰዓት አጠቃቀም ድልድል ፍትሃዊና በእኩልነት ላይ የተመሰረተ አለመሆኑን አስታውቋል። ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው ጥር 25 ቀን 2007 ዓ.ም የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሀገር አቀፍ ፓርቲዎችን በረቂቅ የሰዓት ድልድሉ ላይ ጊዮን ሆቴል ጋብዞ ውይይት አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ …

ጥር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ፣ ሰሜን ወሎና ባቲ አካባቢዎች የሚኖሩ ከስደት ተመላሽ ወጣቶች ባሰሙት ቅሬታ፤ ከአረብ ሃገር ወደ ሃገራችሁ ግቡ የሚለውን የገዢው መንግስት ቅስቀሳ በመስማት ስራቸውን ጥለው ወደ ሃገር ቤት ቢመጡም፣  ከስደት በፊት ጥረው ግረው ያለሙትን ቦታ በኢንቨስትመንት ስም ለባለሃብቶች ተሰጥቶ በማግኘታችው አብዛኛው ወጣቶች ተመልሰው ሲሄዱ ሌሎች ደግሞ ለችግር ተዳርገዋል። 1 …

ጥር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባሳለፍነው ሳምንት በሲዳማ ዞን በአለታ ጩኮ ወረዳ በጩኮ 02 ቀበሌ በቡድን የተደራጁ ሰዎች የአንድን ነጋዴ ቤት  በመዝረፍ ግምቱ 9 መቶ ሺህ ብር የሚያወጣ ንብረት ዘርፈውና ድብደባ ፈጽመው ከተሰወሩ በሁዋላ፣ ድርጊቱን የተቃወሙ  የአለታ ጩኮ ጤና አጠባበቅ ጣብያ ሃላፊ አቶ ሰለሞን ጤና እንዲያዝ የእስር ትዕዛዝ ወጥቶበታል ። ዝርፍያው የተፈፀመው …

ጥር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶስት ተከፍሎ ከሚካሄደው የአዲስአበባ ቀላል ባቡር ግንባታ መካከል ከቃሊቲ እስከ ለገሃር ያለው መስመር ሙሉ በሙሉ ሳይጠናቀቅ በጥድፊያ ባለፈው እሁድ እንዲመረቅ መደረጉና የሙከራ ስራው ለቀጣይ ሶስት ወራት እንደሚቀጥል መታወቁ እያነጋገረ ነው። የባቡሩ ግንባታ የኤሌክትሮ መካኒካል ስራዎችና የመንገደኞች ተርሚናሎች እንዲሁም ከሀያት ወደ ጦር ሃይሎች እና ከፒያሳ የሚነሳው መስመር ግንባታው አልተጠናቀቀም። …

 

በአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ለግማሽ ፍፃሜ ያለፉ አራት ቡድኖች ታወቁ። እነርሡም – አስተናጋጅ ኢኳቶሪያል ጊኒ፥ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ፥ ጋና እና አይቮሪኮስት ናቸው። 

  አራቱ ብሄራዊ ቡድኖች የፊታችን ረቡዕና ሐሙስ በወሳኙ የጥሎ ማለፍ ፍልሚያ ይጫወቱና አሸናፊዎች ዕሁድ ለዋንጫ ተሸናፊዎች ደግሞ ቅዳሜ ለደረጃ ይጋጠማሉ።

በዚህ ዝግጅት፥ የእስካሁን ውድድሮችን አዲስ አበባ በቴሌቪዥን የሚከታተለው ባልደረባችን ገዛ̎ኸኝ ጽዮንመስቀል ግምገማና የአድማጮች አስተያየት ተካቷል።

በሥፍራው የሚገኙት አቶ ፍቅሩ ኪዳኔም በቱኒዝያና ኢኳቶሪያል ጊኒ መካከል በተካሄደውና ዳኛው ስለሰጡት አነታሪኪ የፍፁም ቅጣት ምት የሚሉት…

የፕሮግራም መግለጫ

ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡

የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡

ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡