የሄዋን አመጽ (ሄኖክ የሺጥላ)
ሄኖክ የሺጥላ
ለምን ባርያ ሆነን? ለምን ባንድ ቡድን ( ዘረኛ ቡድን ) የበላይነት ይህን ያህል ጊዜ መከራችንን አየን ፣ ለምን ለውጥ ማምጣት አቃተን የሚለውን ነገር ስብሰለሰልበት ነበር ። እንደ ትልቅ ምክንያት ሆኖ የገባኝ እና የተረዳሁት አንዱና ዋነኛ ምክንያት ” የህይወታችንን ብዙን ጊዜ ያለ ሥራ መንገድ ላይ ቆመን ስለሆነ የምናሳልፈው ፣ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ለማሰብ ፣ ለማንበብ ፣ ለመጠየቅ ጊዜው ሳይሆን ደንታው የሌለን ስለሆነ መሰለኝ ። ሕይወታችን በተሻለ እና ለተሻላ ሕይወት በመጣር እና በመታተር ላይ ያተኮረ ሳይሆን ፣ የአዙሪት () የሆነውና እና የተለመደውን ሕይወት በመደጋገም ላይ የተመረኮዘ ስለሆነ ። ሕይወታችን ባህልን ከእድገት ጋ በማምታታት ፣ ባህልን ከነጻነት ጋ በማምታታት ፣ ረብ ያለው ግንዛቤም ይሁን ፣ አቅል የገዛ እይታ ሳይኖረን ፣ እንዲሁ እንደ ወይፈን በጊዜያዊ ነገሮች ላይ እምቡር እንዳልን ፣ ለአንዱም ስሜታችን መልስ ሳናገኝ ፣ የውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ሕይወት ውስጥ የተጠመድን ይመስለኛል ።
ስለ መብት የምናስብበት መስተ-ሃልይ ስለ ሩጫ ከምናስብበት ጋ አንድ ነው ። ይህም ማለት ኃይሌ የኦሎምፒክ ሜዳይ እና የሆነ ሺ ዶላሮች ባገኘ ጊዜ ፣ መስቀል አደባባይን በሯጭ እና ሩጫ የምናጣብብ ፣ ምርጫ በመጣ ቁጥር ( ጊዜ ) በሰላማዊ ሰልፍና አንድ በመሆን ጊዜያችንን የምናጠፋ ፣ የጊዜው ሰዎች ሆን ። እንዳንዴ ” እንዴ ከምርጫ በፊት እና ከምርጫ በሁዋላ መብት የሚባለው ነገር የለም ? ” እላለሁ ። ነጻ ላለመሆናችን እንደ ትልቅ ችግር ያየሁት ፣ ትግሉን ለረጅም ዘመንም ይሁን ቀርጸን ለውጥ በሚያመጣ መልኩ መንቀሳቀስ አንችልም ። የዛሬ አስር ዓመት ይሄን በእርግጠኝነት ማድረግ እንችላለን ብለን አንነሳም ። ይልቅ ለጊዜያዊ ድልና መፍትሄ ነው የምንሮጠው ። ያ ደሞ ለተደጋጋሚ ውድቀት ፣ እና ውርደት ዳርጎናል ። ሩቅ አሳቢነታችን እና ቅርብ አዳሪነታችን ከዚህ ከሰነቅነው የተስፋ ግሽበት ጋ ይያያዝ ይመስለኛል ። አልም ግን ስታልም ማንም ያላለመውን አልም ። ወጥን ግን ስትወጥን ተራራ የሚገፋ ውጥን ይኑርህ ፣ ድልህን በጊዜ ሳይሆን በሚያመጣው ውጤት ለካው ።
እርግጥ ፈሪዎች አድርገውናል ፣ ይሄ በአምባ ገነን ስርዓት ውስጥ የሚኖር የማንኛውም አይነት ሕዝብ ባህር ነው ፣ ግን መፍራታችንን መተማመን አለብን። መፍራት ነውር አይደለም ፣ መፍራት የሚያሳፍር ነገር አይደልም ፣ ነውርና አሳፋሪው እንደፈሩ መኖሩ ነው ። እንደውም (Fear is a useful fiction to achieve the state of anger) ። ያልፈራ ሊደፍር አይችልም ፣ ያልፈራ ሊቆጭ አይችልም ፣ ያልፈራ ሊያምጽ አይችልም ።
ይህ በኛ ላይ የምናየው የፍርሃት ድባብ የኛ ብቻ በሃሪ አይደለም ፣ በጭቆና ውስጥ የነበሩ ሀገሮች ህዝቦች በሙሉ የቀመሱት ጽዋ ነው ። ግን ይህንን ተደጋጋሚ በደል እና ወጀበ- ወንጀል ለመረዳት አለመቻል እና መደንቆር ግን ያስፈራል (What we see in us is not unique to us but a state of mind to anyone who is in fear Our ability to sense patterns of a repeated sage and conspiracy is almost deafened by our inability to move forward and face it in a rational way!)
የምንኖረው በማህበረሰባዊ ዓለም ነው ፣ የኛ የመኖር ህልውና በሌላ ምድር ወይም ደሴት ላይ ከሚኖሩ ሰዎች የመኖር ህልውና በምንም የተለየ አይደለም ፣ እኛም የምንዋኝበት የህዝብ ቅይያኖስ ሌሎችም የሚጠልቁት ባህር ነውና ( We live in a social world, we swim to a see of people and our existence is no less and or different from those existed in another land or Iceland….) ። ስለዚህ በሰውነት እና በሰዋዊ ጥያቄዎች ፣ ሁላችንም የፍርሃታችንን ያህል እኩል ነን ። ያለ አግባብ ስበድሉን ለምን የምንል ፣ ፍርሃትን የምንዋጋ ፣ አዲስ ነገር የምያምረን ፣ ለውጥ የሚናፍቀን ብቻ ሳይሆን ለለውጥ የምንሰራ 9 ሕይወትን አሳልፎ እስከመስጠት ) መሆን አለበት ባይ ነኝ ። ነጻነት ከሰማይ የተሰጠ ጸጋ ነው ፣ ምድራዊያኖች ሲነጥክቁህ ፣ በነጠቁህ መንገድ ቀማቸው ! አለበለዚያ ግማሽ ሰው ሆኖ መኖር ካልገደደህ ፣ ዝም በል !
ፕ/ሰር መስፍን ወ/ማርያም ” የመጀመሪያውን አመጽ ያስተማራች ሴት ነች ይላሉ ። የሐሳባቸው መነሻ የሆነውም ” የገነት በለስ ” ናት ። ይሄን እንዴ ብያለሁ ። የሄዋን አመጽ በምድራዊ ክልከላዎች ላይ ይቀጣጠሉ ! ድሮም ደፋርና ጭስ ነው ነገሩ !!!!
Source: ሄኖክ የሺጥላ fb
The post የሄዋን አመጽ (ሄኖክ የሺጥላ) appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.