ይገረም አለሙ

አቶ ግርማ ሠይፉ ማሩ / Girma Seifu Maru

ከ2002 ዓ.ም. እስከ እስከ 2007 ዓ.ም. ድረስ የፓርላማ አባል የነበሩት አቶ ግርማ ሰይፉ “ለዴሞክራሲ ሥርዓት ምን ዓይነት ፓርቲ ያስፈልገናል?” በሚል ርዕስ ያቀረቡትን ጽሁፍ ለማንበብ የጓጓሁት የአንድነት ም/ሊቀመንበር ነበሩና ከተግባር ተሞክሮአቸው በመነሳት ድክመት ጥንካሬን መለስ ብለው ቃኝተው መሆን ያለበትን ያመላክታሉ በሚል ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ (በግራ) ዶ/ር መረራ ጉዲና (በቀኝ) / Prof. Beyene Petros (Left) & Dr. Merera Gudina (Right). (AP Photo/Mulugeta Ayene)ግርማ ሠይፉ ማሩ

በሀገራችን የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪል ማኅበራት እንዲሁም የሚዲያ ተሳትፎ እጅግ ወሳኝ እንደሆነ ሁሉም ይረዳዋል ማለት ባይቻልም፤ በተለይ የፖለቲካ ፓርቲ አባል አመራር የሆኑ ሰዎች ይጠፋቸዋል ብሎ የሚገምት ላይኖር ይችላል። እውነቱ ግን ከዚህ የተለየ ነው። በአሁኑ ጊዜ የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ ሰዎች የሚሳተፉት በዋነኝነት በሀገራችን የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያላቸውን መዋጮ በማስላት ሳይሆን፤ ገዢውን ፓርቲ በማስወገድ ላይ ብቻ ያጠነጠነ ይመስላል። ይህንንም ማድረግ የሚፈልጉት ደግሞ በትርፍ ጊዜያቸው ከሥራ መልስ ወይም በጡረታ ጊዚያቸው ነው። ይህን ሲያደርጉ ደግሞ የብዙ ወጣቶች ጊዜና ጉልበት መስመር ባልያዘ አቅጣጫ እንደሚመሩ አይረዱም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የአፍሪካ ቀንድ ተስፋ ሊኖረው ይችላልን? Horn of Africaፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2014 “ለአፍሪካ ተስፋ ሊኖረው ይችላልን?“ በሚል ርዕስ አንድ ትችት ጽፌ ነበር። ያንን ትችት የጻፍኩት ባለፉት ጥቂት አስርት ዓመታት ውስጥ ተንሰራፍቶ በሚገኘው እና ማቆሚያ በሌለው በአፍሪካ ሰው ሰራሽ ቀውስ ምክንያት ምንም ዓይነት ተስፋ የሌለኝ በመሆኑ ነበር። እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2014 የመካከለኛው አፍሪካ ሬፐብሊክ (መአሬ) አውዳሚ በሆነ የጎሳ-ኃይማኖት የዘር ማጥፋት ዘመቻ እልቂት ውስጥ ተዘፍቃ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ግርማ ካሳ

ሰሞኑን በሰሜኑ የሀገራችን ግዛት ጦርነት ተቀስቅሷል። አስመራም፣ አዲስ አበባም ያሉ ገዢዎች ጦርነት መደረጉን ማመን ብቻ ሳይሆን “ይሄን ደመሰስን፣ ይሄን ያህል ገደልን” እያሉ በመማጸደቅ ላይ ናቸው። ዓለም የትናየት ደርሳለች፣ ትላንናት እኛ እየረዳናቸው ነጻ የወጡ የአፍሪካ ሀገራት እንኳን የትናየት ደርሰዋል፣ እኛ አሁንም መግደልን እንደ ጀብዱ አድርገን እናወራለን።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሲኖዶስ ብየ ስል “የትኛውን?” የሚል አይጠፋም፡፡ በአንድ ሀገር ቤተክርስቲያን ውስጥ ሊኖር የሚችለው አንድ ሲኖዶስ ነው ሁለት ሲኖዶስ የለም፡፡ ሲኖዶስ ይሰደዳል ወይ?፣ እዚህ ሀገር ቤት ያሉትም ሲኖዶስ ነን ይላሉና የትኛው ነው ትክክለኛና እግዚአብሔር የሚቀበለው? ፣ ፓትርያርኩና ጳጳሳቱ መሰደድ ነበረባቸው ወይ? ስደታቸው ከወንጌልና ከሕገ ቤተክርስቲያን አኳያ ትክክልና የሚገባ ነው ወይ? ለሚሉ ጥያቄዎች ከተፈጠሩ ነባራዊ ሁኔታዎች አኳያ ወንጌልንና […]

(ተረፈ ወርቁ):- “… እንደው እነዚህ በአሜሪካ የሚገኙት አባቶች እንደምንም ብለው ተጠናክረው በአገራችን በኢትዮጵያ በእነርሱ በሚመራው በአሜሪካው “ሲኖዶስ” ሥር ያለ/የሚመራ አንድ እንኳን ቤተ ክርስቲያን መመሥረት ቢችሉ በየቦታው ተበታትኖ ያለውን የተሃድሶ እንቅስቃሴ አንድ ማድረግ መምራት ይቻል ነበር እኮ …።”

ይህ ቁጭት፣ ምሬት አዘል ቃል በአንድ  ወቅት የኢትዮጵያን ቤ/ን እናድሳለን ብለው ከተነሡ ሰዎች መካከል ማህበር አቋቁሞና ከአንዳንድ ስለ ሃይማኖታቸው በቂ የሆነ መሠረት ከሌላቸውና የእውነት ዕውቀትን በፍቅር ካልተቀበሉና እንደ “ዘመነ መሳፍንቱ” – የባላባቶች ዘመን “አወዳሽና አንጋሽ” ፈላጊ በሆኑ ባለ ጠጋዎች፣ ወይዛዝርት፣ ነጋዴዎች ምጽዋትና እንዲሁም ከውጭ አገር በሚላክለት ዶላር (በተለይ ከዱባይና ከአሜሪካ) በዐሥር ሺዎች የሚገመት ዘመናዊ ቤት/አዳራሽ ተከራይቶ የተሐድሶን እንቅስቃሴ ለማስፋፋት ላለፉት 20 ዓመታት እየደከመ ያለ ሰው የተናገረው ምሬት ያዘለ ቃል ነው። ለነገሩ ይህ ማህበር በነጋ ጠባ ራሳቸውን በሾሙ በጎበዝ አለቆች የሥልጣን ይገባኛልና በጥቅም ግጭት ሲፈርስ ሲሠራ የኖረ፣ እንዳሰቡትና እንዳለሙት እንኳን የኢትዮጵያን ቤ/ን ሊወርሱ ቀርቶ የሕልም ዳቦቸውን እየገመጡ በቀቢፀ ተስፋ ተውጠው ነው ያሉት።

ይህን የተሐድሶ አራማጆች፣ “ተጠሪነቱ  ለአሜሪካው “ሲኖዶስ” የሆነ ቤ/ን በአገር ቤት ቢያቋቁሙ” የሚለው የጥፋት፣ የክፋት ሐሳብ/የሕልም ዓለም ምኞታቸውን ያነሳሁት አለምክንያት አይደለም። በአሜሪካ የሚገኙት ራሳቸውን “ሕጋዊው የኢትዮጵያ ቤ/ን “ሲኖዶስ”/ስደተኛው “ሲኖዶስ” በሚል የሚጠሩ አንዳንድ አባቶችና አገልጋዮች በቤተ ክርስቲያኒቱ ዶግማና ቀኖና ያላቸው የተዛባ ምልከታ፣ አፍቃሪ-ፕሮቴንስታዊ/Pro-Protestant አስተምህሮአቸው የተነሳ የተሃድሶ አራማጅ ነን ከሚሉ ሰዎች ጋር “የጡት ልጅን” ያህል በጥብቅ ተዛምደዋል፤ ተጣብተዋል። ይህ ደግሞ አለምክንያት የሆነ አይደለም።

እስቲ እነዚህ የተሃድሶ አራማጅ ነን ባዮችን ዓይናቸውን ወደ ምዕራቡ ዓለም/አሜሪካ እንዲያነሡ ያደረጋቸውንና በአሜሪካ ያለው “ሲኖዶስ”ም – “እልል በቅምጤ” እንዲሉ እነዚህን ሰዎች በደስታ እጃቸውን ዘርግተው እንዲቀበሉ ያደረጋቸውን ምክንያቶቹን በጣም በጥቂቱ ለማየት እንሞክር።

ለረጅም ዓመታት በኖሩበት የምዕራቡ ዓለም የዘቀጠ ባህል ተፅዕኖ ስር የወደቁ የአሜሪካው ስደተኛ “ሲኖዶስ” አንዳንድ “Liberal” ነን ባይ አባቶችና አገልጋዮች በፕሮቴስንታታዊ አስተምህሮአቸውና ሥርዓት አልበኝነታቸው በአገር ቤት የተለዩ ሰዎች መጠለያና መሸሸጊያ መሆናቸው ነገር መቼም ፀሐይ የሞቀው የአደባባይ ምስጢር ነው።

“ወንድሜን ሥጋ መብላት የሚያሰናክለው ከሆነ ለዘላለሙ ሥጋን አልበላ።” የሚሉ ቅዱሳን አባቶችና ሐዋርያት ባለፉባት ቤ/ን ስለ “አሳማ ሥጋ” እና ስለ “ኦርጋን መሳሪያ” ክርክር እያስነሡ ምእመናንን የሚያለያዩ ትምህርትን የሚያስተምሩ አባቶችንና አገልጋዮችን የታዘብነው በዚሁ በአሜሪካው “ሲኖዶስ” ነው።

ቁሳዊነት/Materialism፣ ደስታን የማሳደድ የሕይወት ዘይቤ/Hedonism፣ ግላዊነት/Individualism፣ ዘመናዊነት/Modernism …ወዘተ በገነነበት ዓለም የሚኖሩ እነዚህ አንዳንድ አባቶችና አገልጋዮች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ የምዕራቡን ዓለም መንፈሳዊ ተቋማት ከመገዳደር አልፈው እያፈራረሷቸው የሚገኙትን እነዚህን ዓለማዊ የሆኑ አስተሳሰቦችንና የኑሮ ዜይቤዎችን በዘመናዊነት ካባ ወደ ቤ/ን ለማስገባት እየተጣጣሩ ነው።

በዛን ሰሞን በአሜሪካው “ሲኖዶስ” የሚገኙ አባቶችና አገልጋዮች፣ “በኦርጋን መዘመር አለበት!” በሚል መግለጫ እስከማውጣት የዘለቁበት አካሔዳቸው – የአገራቸው/የማንነታቸው መግለጫ፣ የባህል መሳሪያዎቻችን ከሆኑት ከእነ በገና፣ ማሲንቆ፣ ክራር፣ እምቢልታና መለከት …ወዘተ ተለያይተው ምን ያህል በምዕራቡ ዓለም ባህል ተጠልፈውና ተጠላልፈው እንደወደቁ አንድ ትልቅ ማሳያ ነው።

እነዚህ ሰዎች አውቀውትም ሆነ ሳያውቁት ለሺ ዘመናት የትናንትና  ታሪካችን፣ የሥልጣኔያችንና የማንነታችን መገለጫና መታወቂያ ከሆነና የቅዱስ ወንጌል መሠረት ካለው ክርስቲያናዊ ባህላችንና ትውፊታችን፣ ወግና ሥርዓታችን ትውልዱን በማናወጥ የማንነት ቀውስ/Identity Crisis ውስጥ እንዲገባ የማድረግ ዘመቻ ውስጥ እየተዘፈቁ ነው።

ሌላኛዉ ምክንያት የአሜሪካው ሲኖዶስ የአባላቱን ቁጥር ከፍ በማድረግ ሀያልነቱን ለማሳየት ሲባል ወደ እነርሱ የሚመጡትን ሰዎች/አገልጋዮች ብዙም ጥያቄ ሳያበዙ ነው የሚቀበሏቸው። ለነገሩ ይህን ለማድረግም ጠንካራ የሆነ እንደ ሊቃውንት ጉባኤ ያለ መንፈሳዊ ተቋም አለመኖሩም ሌላኛው ጉዳት ነው። ስለዚህም ይህ ጥብቅነት የሌለው ብዛትን እንጂ ጥራትን ከቁጥር ውስጥ ያልሰገባው አሠራር አንዳንዶችን የራሳቸውን አስተምህሮ እንደፈለጋቸው ለመዝራት እንዲችሉ አስችሎአቸዋል።

እዚህ ጋር አባላትን ከማብዛት አንፃር በደቡብ አፍሪካ የሆነ አንድ ታሪክ ላንሳ። እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ቤ/ን በጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ሕዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ታሪክ ውስጥ ያላት ስም ትልቅና የከበረ ነው። ደቡብ አፍሪካውያን ለኢትዮጵያ ቤ/ን ያላቸው ይህ ፍቅርና ክብር ከመቶ በላይ ዓመት ያስቆጠረው ለነፃነት ያበቃቸው ANC ፓርቲያቸው የተመሠረተው ቄስ ጆን ዱቤ በተባሉ የቤተ ክርስቲያናችን አባልና ተከታዮቻቸው ነው።

ይህ ታሪክ እውነታ የኢትዮጵያን ቤ/ን በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ጠንካራ መሠረት እንዲኖራት አድርጓል። እናም ቤተ ክርስቲያናችን በደቡብ አፍሪካ ምድር ከአምስት የሚልቁ ቤ/ን፣ በማህሌታዊው ቅዱስ ያሬድ ስም የተመሰረተ አንድ ገዳምና ከሃያ በላይ መንፈሳዊ ጉባኤያት አሉ። ታዲያ ከእነዚህ ጉባኤያት መካከል ማፊኬኔ በተባለ ከተማ ያለ አንድ ጉባኤ በወያኔ በሚመራ ሲኖዶስ እንዴት ትመራላችሁ በሚል የፖለቲከኞች ስብከት፣ መንፈሳዊ፣ አስተዳደራዊ ጥያቄና ብሶት ምክንያት ራሳቸውን ለይተው ግንኙነታቸውን በአሜሪካው ሲኖዶስ ስር በሚመራው ቤ/ን ስር ሆነው ነበር።

ይሁን እንጂ በአሜሪካው ሲኖዶስ ስር ያሉ አባቶችና አገልጋዮች መንፈሳዊ አገልግሎታቸው በዋና ከተማው በጆሃንስበርግ፣ በፕሪቶሪያና በአካባቢው ብቻ የተወሰነ በመሆኑ እነዚህ ከጆሃንስበርግ በብዙ ኪሎ ሜትር ርቀው የሚገኙት የማፊኬኔ ጉባኤ የ”እኛ አባል ናቸው” ከሚል ንግግር ባለፈ ተገቢውን መንፈሳዊ አገልግሎትና አስተዳደራዊ መመሪያ ለመስጠት የሚችሉበት ሁኔታ ላይ አልነበሩም። በሂደትም የጉባኤው አባላት እንዳሰቡት መንፈሳዊ አገልግሎት ባለማግኘታቸው፣ በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ቤ/ን በደቡብ አፍሪካውያን መካከል እየተስፋፋች መምጣቷ ያሳደረባቸው ባይተዋርነት የተነሳ በመጨረሻ ይቅርታ ጠይቀው ወደ ኢትዮጵያ ቤ/ን የተመለሱበትን ታሪክ አስታውሳለሁ።

በመጨረሻም ለማንሳት የምፈልገው ምክንያት፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ አስተዳደር ውስጥ እጃቸውን የሚያስረዝሙ ፖለቲከኞቻችን የፈጠሩት ክፍተት፣ በዘመነ ኢሕአዴግ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ባሉ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች መካከል የተለያዩበትን አሳዛኝ የታሪክ አጋጣሚ ለመጋፈጥ ተገደናል።  ከዚሁ ጋር ተያይዞም  ለአብነትም በአሜሪካ በስደት ላይ የሚገኙ አባቶቻችን በግንቦቱ ሲኖዶስ ስብሰባቸው ያወጡትን ባለ 15 ነጥብ የአቋም መግለጫ መመልከት በቂ ነው። የቤተ ክርስቲያን ሳይሆን የአንድ የመንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲ ያወጣው ሊያውም ስሜት አልባና አደናጋሪ የአቋም መግለጫ ነው የሚመስለው።

ሌላው በጣሙን የገረመኝ ነገር ደግሞ የአሜሪካው ሲኖዶስ በዚሁ መግለጫቸው ከወያኔ መንግሥት ጋር ተባብሮ የሚሠሩትንም ሰዎችን ሁሉ አውገዘናል የሚለው ዐርፍተ ነገር ደግሞ ይበልጥኑ አስገረመኝ፣ አሳዘነኝም። ይሄ ማውገዝ፣ መወጋገዝ በቃ ባህል ሆነ ማለት ነው?!

ከጥቂት ዓመታት በፊትም የአሜሪካው ሲኖዶስ አንድ ሊቀ ጳጳስ የሆኑ አባት፣ “በወንጌል እመኑ፣ ንስሓ ግቡ።” ከሚለው እጅግ በከከበረው የዐዲስ ኪዳን የጌታችንና የመድሀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል አገልግሎት ወርደው፣ “በኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳትጓዙ፣ የወያኔ ሽርኮች የሚያስመጡትን በርበሬና ሽሮ እንዳትገዙ … ወዘተ በማለት በየቦታው ሲቀሰቅሱ ብናያቸው በጣሙን አፈርንም፣ ተሳቀቅንም።

የባለፈው ሰሞንም በአሜሪካ ያሉ አባቶች በኦርጋን ይዘመር ዘመቻም የዚህችን ጥንታዊት፣ ባለ ታላቅ ታሪክና የገናና ሥልጣኔ ባለቤት የሆነች የአገራችንና የቤተ ክርስቲያናችንን ታሪክና ቅርስ፣ ማንነትና ባህል፣ ሥርዓትና ትውፊት ለማጥፋት፣ ለመናድ ከሚደረግና እንዲሁም በዘመናዊነትና በሥልጣኔ ስም የምዕራቡን ዓለም ባህል ለመጫን/ለማራገፍ ከሚደረግ እኩይ ዘመቻ/ሴራ ተለይቶ የሚታይ እንዳልሆነ ነው የታዘብኩት።

ወደ ሲኖዶሱ መግለጫ ስመለስም በእውነት ያሳፍራል፣ ያሳቅቃልም። ይህ መግለጫ የጥላቻና የፅንፈኝነት መንፈስ ከሚነዳቸው፣ ዕድሜ ዘመናቸውን ከደምና ከቂም በቀል ትርክት መውጣት ካልቻሉት የ60ዎቹ ትውልድ የፓርቲ ስብስብ ማብቂያ የሌለው፣ የነጋ ጠባ የፖለቲካ መግለጫቸው እምብዛም የተለየ ሆኖ አላገኘሁትም።

ለመሆኑ የተሸከምነው ወንጌል የፍቅር፣ የሰላም መልዕክት እንጂ የጥላቻና የመለያየት ወንጌል ነው እንዴ …?! ሌላው የሲኖዶሱ መግለጫ ከበርካታ የፊደል ግድፈቶቹ፣ እዚህም እዛም የተደነገሩት ትርጉም የለሽ ቃላቶች በላይ ደግሞ የቤተ ክርስቲያናችንን/የግእዙን ቋንቋ አጻጻፍ ሥርዓት የተከተለ አይደለም። ለአብነትም በሐመሩ “ሐ” መጻፍ ያለበት በሀሌታው “ሀ” ተጽፏል፣ ለአልፋው “አ” መጻፍ ያለበት በዓይኑ “ዐ”፣ ሌላም ሌላም የማይጠበቁ ስህተቶች ያሉበት መግለጫ ነው።

እንግዲህ በዚህ ሁሉ ውዝግብ ውስጥ – ፖለቲካው፣ ዘረኝነቱ፣ የአስተምህሮ ችግሩ፣ መለያየቱ፣ መከፋፈሉ … ወዘተ ገና ይሄ ነው የሚባል መፍትሔ ሳይበጅለት በአሜሪካ የሚገኙ አባቶች ኤጲስ ቆጶሳት ሹመቱን ተያይዘውታል። ሊያውም ደግሞ በአስተምህሮአቸውና በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ጥያቄ የሚነሳባቸውን ሰዎች ሳይቀር ለዚህ ታላቅ ለሆነ መንፈሳዊ ሓላፊነት ሹሞአቸዋል። ይህ ከመንፈሳዊ ቅናት ይልቅ የእልክ የሚመስል የአባቶቻችን ጉዞ ፍጻሜው ምን ሊሆን እንደሚችል የምናየው ነው የሚሆነው።

አንድ ስለምታደርግ ሥጋውና ደሙ እግዚአብሔር በይቅርታው አንድ ያደርገን ዘንድ ሰላምን እንማልዳለን።
እስከ ፍጻሜያችን ድረስ እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ አንድነት ይጠብቀን ዘንድ ስለ አንድነታችን እንማልዳለን። የሚለው ዘወትር በሥርዓተ ቅዳሴያችን የምንጸልየው ጸሎት ትርጓሜው ምን ማለት ይሆን ግን …?!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!    

Deje Selam is a venue of news, views and opinions about or related to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. [email protected]

ማስተዋል በለጠ (ከአዲስ አበባ)

የወያኔ ውድቀት የአደባባይ ምሥጢር መሆኑን የሚያመላክት አጋጣሚ

ከደቂቃዎች በፊት ከአንዱ የመሥሪያ ቤቴ ቅርንጫፍ ወደ ዋናው መ/ቤት ስመጣ እንዲህ ሆነ። መኪናዋ ውስጥ በተላላኪነት የምትሠራ አንዲት ወጣት፣ ሹፌራችንና እኔ ብቻ ነን የነበርነው። የዛሬው ቀን የከተማችን ወሬ የሆነውን የማትሪክ ፈተና መሰረቅ አነሳሁና የተለጎመውን የሦስታችንንም አንደበት በጋራ የሀገር ጉዳይ ከፈትኩት። በዚህን ዓይነት ሁኔታ እኔ ብዙውን ጊዜ ነገር እለኩስና ዋና ሥራየ ማዳመጥ፣ ማዳነቅና ማውጣጣት ነው። ቀዳሚው ሥራየ ግን የማዋራቸው ሰዎች በኔ ላይ እምነት እንዲኖራቸው ጥረት ማድረግ ነው፤ ሰው ከተጠራጠረህ የልቡን አይናገርም። ዝም ሊል ወይም ሊዋሽህና ሊያታልልህም ይችላል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይገረም አለሙ

Ginbot 20, 25th anv. ግንቦት 20፣ 25ኛ ዓመት

በእርስ በርስ ጦርነት ከሁለቱም ወገን የሚሞተው የአንድ ሀገር ልጅ ነው። አባትና ልጅ፤ ወንድምና ወንድም ከዛና ከዚህ ተሰልፈው የሚገዳደሉበት አጋጣሚም ይኖራል። ይህም በ17 ዓመቱ የርስ በርስ ጦርነት በግልጽ ታይቷል። ወያኔዎች ለድል የበቁት የኢትዮጵያን ሠራዊት ብቻ ሳይሆን ደርግን ተቃውመው ብረት ያነሱ፤ ነገር ግን ከዋሉ ካደሩ ለህወሓት ህልውና አስጊ ይሆናሉ ያሉዋቸውን ድርጅቶች ጭምር (ለምሳሌም ኢህአፓ፣ ኢዲዩ፣ …) ተዋግተው፤ ከዚህም አልፎ በህወሓትም ውስጥ የተለየ አስተሳሰብ ያራመዱ ወይንም ለሥልጣን ያሰጋሉ የተባሉትን እያሰቃዩና እየገደሉ በመሆኑ፤ መገዳደሉ በአንድ ሀገር ልጆች መካከል ከመሆን አልፎ በቤተሰብ መካከል ጭምር እንደነበር አሌ አይባልም። ለዚህ ደግሞ ሩቅ መሄድ ሳያስፈልግ በኢህአፓነቱ በወያኔ እንደተገደለ የሚነገረውን የአቶ በረከት ስምኦን ወንድም መጥቀስ ይቻላል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሄኖክ የሺጥላ

ስደት

ወዳጄ እና ጓደኛዬ በቅርቡ በሱዳን አሳብሮ፣ በሊቢያ በረሃ አቋርጦ፣ በባህር አሳልጦ ጣሊያን፣ ከጣሊያን ደሞ ጀርመን እንደደረሰ አጫወተኝ። እርግጥ የተጓዘው መንገድ፣ ያየው መከራ፣ የቀመሰው ችግር እንዲህ በሁለት መስመር በሱዳን አድርጎ በሊቢያ አቋርጦ ጣሊያን ደረሰ ብሎ እንደማለት ቀላል አይደለም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ግንቦት 20 እንዲህ መቀለጃ ሆና ትቅር?ታዛቢ (ከአዲስ አበባ)

ሥራየ መምህርነት ነው። በአንድ የመንግሥት የ2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት ውስጥ አስተምራለሁ። ሰሞኑን ታዲያ የግንቦት 20 የኢትዮጵያ የነፃነት ቀን እንደመሆኑ የበዓሉን መቃረብ አስታክኬ በየምገባባቸው በርካታ ክፍሎች ትምህርቱን ከመጀመሬ በፊት “እንኳን አደረሳችሁ” እላለሁ። ይሀንን የምለው ኢህአዲግ መራሹ ዴሞክራሲያዊው መንግሥታችን ጨቋኙን የደርግ መንግሥት ደምስሶ ህዝባዊ መሠረት የተላበሰና በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የቆመ የዴሞክራሲ ሥርዓት በመትከሉ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Ethiopiaይገረም ዓለሙ

በ1982 ዓ.ም. ኢትዮጵያ ወዴት እየሄደች እንደሆነ አይደለም የት ላይ እንዳለች አንኳን መናገር በማይቻልበት ወቅት፤ ከአንድ ባልንጀራየ ጋር እየሄድን፤ እኔ ከማላውቀው የእርሱ ጓደኛ ጋር መንገድ አገናኘን። እናም ሠላምታ ተለዋውጠው፤ ታዲያስ እንዴት ነህ፣ እንዴት ናችሁ ሲለው፤ ምን እባክህ ሰውም አለን ሰውም የለንም ሲል መለሰለት።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ከረጅም ዓመታት በፊት በፖለቲካ ምክንያት በሶማሊያ መኖር እንዳልቻሉ በመግለጽ በኖርዌይ ያቀረቡት የጥገኝነት ጥያቄ ተቀባይንት አግኝቶ ፤ የመኖሪያ ፈቃድ እና ዜግነንት ተሰጥቷቸው የነበሩ ወደ አንድ መቶ የሚጠጉ ሶማሌያውያን የኖርዌይ ዜግነታቸውን ተነጠቁ። ለዚህ ሁሉ የዳረጋቸው ደግሞ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ስለራሳቸው የሚያወጡት መረጃ …

በፌስቡክ ምክንያት በርካታ ሶማሌያውያን የኖርዌይ ዜግነታቸውን ተነጠቁ – VOA Read more »

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቤቶችና የከተማ ልማት ሚኒስቴር የሥራ አፈፃፀም ዝርዝር ዘገባ ባደመጠበት ወቅት ጠፉ እየተባለ ስለሚነገርላቸዉ የኮንደሚኒየም ቤቶች የሚኒስቴር መሥርያ ቤቱ አጣርቶ እንዲያቀርብ መጠየቁ ተሰምቷል። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ታቅደዉ ያልተሠሩ መኖራቸዉን ለምክር ቤቱ ቢጠቁምም፤ ጠፋ የተባሎት የኮንደሚኒየም ቤቶች ጉዳይ …

ኮንደሚኒየሞቹ የት ተሰወሩ? – ዶይቸ ቬለ Read more »

በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ስፖርት ክለብ ውስጥ በመካከለኛ ርቀት 800 ሜትር ተወዳዳሪ የነበረችውና በብሔራዊ ቡድን ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ተመራጭ በመሆን የምትታወቀው የ19 አመትዋ አትሌት ኩለኒ ገልቻ ከወንድ ጓደኛዋ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት በአትሌት ጓደኛዋ እጅ ህይወቷ በስለት ማለፉን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የፌዴራል …

አትሌት ኩለኒ ገልቻ በወንድ ጓደኛዋ ተወግታ ተገደለች – VOA Read more »

ሰሞኑን በደቡብ ኢትዮጵያ ጥቃት ያደረስኩት እኔ ነኝ ሲል አርበኞች ግንቦት ሰባት ኃላፊነቱን ወስዷል። የድርጅቱ ሊቀ መንበር ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ከዝግጅት ክፍላችን ጋር ባደረጉት አጭር ቆይታ፥ ”ትግላችንን የምናካሂደው እዚያው ኢትዮጵያ ውስጥ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ሆነን ነው” ብለዋል። ያዳምጡ → listen

ነገረ ኢትዮጵያ የተሰኘዉ ጋዜጣ አዘጋጅ ጌታቸዉ ሽፈራዉ ክስ ሳይመሰረትበት ከአራት ወራት በላይ መታሠሩን ጠበቃዉ አስታወቁ። ጠበቃ አመሐ መኮንንን ዛሬ እንዳስታወቁት የሐገሪቱ የፀረ-ሽብር አዋጅ በሚያዘዉ መሠረት ፖሊስ በደንበኛቸዉ ላይ በአራት ወራት ዉስጥ ክስ መመሥረት አለያም እስረኛዉን መልቀቅ ነበረበት። ፖሊስ በተደጋጋሚ የጊዜ …

ያለፍርድ የታሠረዉ ጋዜጠኛ – ዶይቸ ቬለ Read more »

ግርማ ካሳ

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር (ኦዴግ). Oromo Democratic Front (ODF)

አንዳንድ በተለይም በውጭ ያሉ የኦሮሞ ብሔረተኞች፣ የአክራሪውን እና የብዙ ወገኖች ደም በእጁ ያለበትን የኦነግን ባንዲራ እያውለበለቡ፣ የጭቁን ኦሮሞ ወገኖቻችንን ተቃውሞ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም እና እንቅስቃሴውን ሃይጃክ በማድረግ፣ የኦሮሚያ ሪፑብሊክን ለመመስረት ያላቸውን ሕልም ለመተግበር ደፋ ቀና እያሉ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በፍቅር ለይኩን*

Ethiopian patriots. ጀግኖች አርበኞቻችን

“… When he saw a poster, Mussolini Invades Ethiopia, he was immediately seized by a violent emotion. At the moment, he writes, it was almost as if the whole of London had suddenly declared war on me personally. For the next few minutes I could do nothing but glare at each impassive faces, wondering if these people could realize that wickedness of colonialism, and praying that the day might come when I could play my part in bringing about the downfall of such a system. … I was ready to go through hell itself, if need be, in order to achieve my object.”

ዕውቁ ፓን አፍሪካኒስትና የ”ጋና የነጻነት አባት” በሚል ቅጽል የሚጠራው ዶ/ር ክዋሜ ንኩርማ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ አሜሪካ በሚያደርገው ጉዞው በለንደን ከተማ ባደረገው አጭር ጊዜ ቆይታ ያስተዋለው፣ ለአፍሪካና ለመላው ጥቁር ሕዝብ የነጻነት ምልክት፣ የጥቁር ሕዝብ ታሪክ፣ ሥልጣኔ፣ ቅርስና ማንነት መገለጫ፣ የነጻነት የተስፋ ምድር- ከነዓን ተደርጋ የምትቆጠረው ኢትዮጵያ በፋሽስት ኢጣሊያ በግፍ የመወረር አስደንጋጭ ዜና፣ መርዶ በውስጡ ያሳደረበትን ስሜትና ቁጭት “ጋና” በሚል ርዕስ በጻፈው የሕይወት ታሪኩ መጽሐፍ ያሰፈረውን በጥቂቱ የቀነጨብኩት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይሄይስ አእምሮ

Tigrinya. ትግርኛ

መምህር ልዑለቃል አካሉ የተባሉ ኢትዮጵያዊ በቅርቡ በኦሮምኛ ቋንቋ የላቲን ፊደል አጠቃቀም ዙሪያ የጻፉትን መጣጥፍ ቆየት ብዬም ቢሆን ዛሬ አነበብኩት፤ ግሩም ነው። እሳቸው የሚሉት “ለኦሮምኛው ከላቲን ይልቅ የግዕዙ ፊደል አይቀርብም ወይ?” ነው። ይሄን ያህል ለምን ሩቅ ተሄደ ነው ጥያቄያቸው። ላቲኑን ለመጠቀም ለምን ያን ያህል ሩቅ መንገድ መጓዝ እንዳስፈለገም መልሱ በመጣጥፉ ውስጥ አለ – ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች በወያኔ በመታገዝ ሀገሪቱን ለመበታተን ከሸረቡት ሤራ አንዱ መሆኑ በስፋት ተጠቅሷል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ከኢትዮጵያዊ ማንነት አንጻር ለውይይት መነሻ እንዲሆን የቀረበ ጽሁፍ

መምህር ልዑለቃል አካሉ (ሲያትል፣ ዋሽንግተን)

መግቢያ

ሰሞኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መጽሐፈ ቅዳሴዋን ወደ ኦሮምኛ ቋንቋ ተርጕማ አሳትማለች። መሆን ያለበትና መደረግም የነበረበት ነው። በምርቃቱ መርሐ ግብርም የቀድሞውን ፕሬዝደንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስን ጨምሮ ብዙ እንግዶች ተገኝተው እንደ ነበር ታውቋል። ይሁን እንጂ ከግርማ ወልደ ጊዮርጊስ በቀር የላቲንን ፊደል በቅዳሴው ላይ መጠቀሟ ትክክል አለመሆኑን ያስታወሰ እና ለወደፊትም ቤተ ክርስቲያን እንድታስብበት የጠየቀ የለም ተብሎአል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

• ከስም ማጥፋት ወንጀል በተጨማሪ የ100 ሺሕ ብር የፍትሐ ብሔር ክሥ አቤቱታም ቀርቧል • ግንቦት 17 እና 26 ቀን በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቂርቆስ ምድብ ችሎት ይቀርባል • የሕግ አገልግሎት መመሪያው የጉዳዩ አያያዝ እና የክሡ አቀራረብ ጥያቄ አሥነስቷል • ጽሑፉ፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ተቋማዊ አሠራር ጥላሸት የሚቀባ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ፓትርያርኩን ስም የሚያጠፋ …

ሄኖክ የሺጥላ

የሀገራችን ፖለቲካ፣ ትችት እና ዘለፋ እንደ ርችት እያብረቀረቀ የሚዘንብበት የነገር ሸራተን ነው። ትናንት ወዳጅህ የነበረ፣ ዛሬ እንደ አማዞን እባብ ቆዳውን ሸልቅቆ ሙልጭ አድርጎ ሊሰድብህ ይችላል፤ ሃሳብህን ሳይሆን ሱሪህን ሊያወልቅ ይፈልጋል። እሱ ራሱ የወጣለት ጠንጋራ ብሔርተኛ ሆኖ፣ ዓይኑን በጨው አጥቦ «ለምን ስለ አንድነት አትሰብክም» ይልሃል፤ የሌሎችን ቁመና ሲያፍረጠርጥ ከርሞ፣ የሱ ቁመና ሲነካ፣ አደለም ቁመናዬን እዳሪዬን እንኳ መተቸት (መንካት) መብትህ አይደለም ሲል አያፍርም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

እነሆ በሀገራችን አዲስ ጎሳ መፈጠሩ ተሰማ፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ ሰዎች የጎሳ ማንነታቸውን ለማስከበር፣ ባህላቸውንና ታሪካቸውን ለመግለጥ ሲታገሉ ነበር የምናየው፡፡ ታሪክ የማያልቅባት ኢትዮጵያ የነባር ጎሳዎችን መብት ማስከበር ብቻ ሳይሆን አዳዲስ ጎሳዎችንም መመሥረት አለብኝ ብላለች፡፡ በርግጥ በሕገ መንግሥቱ ላይ ነባር ጎሳዎችን በተመለከተ …

‹ፌስዳቢ› – ዳንኤል ክብረት Read more »

በደቡብ ኦሮምያ፤ ቦረና ዞን ውስጥ ትናንት፣ ዓርብ ምሽት ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ ቢያንስ የ13 ሰው ሕይወት መጥፋቱን የሆስፒታል ምንጮች አስታወቁ፡፡ አደጋው የደረሰው አንድ መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከልክ በላይ አሳፍሮ ሜጋ ወረዳ ውስጥ ካለችው የዓርብ ገበያ ከሚቆምባት ዱቡሉቂ ከተማ ወደ …

በያቤሎ የአውቶቡስ አደጋ አሥራ ሦስት ሰው ሞተ – VOA Read more »

በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ከተማ ውስጥ ባለፈው ዕሁድ ሌሊት ከፖሊስ ድብደባ ጋር በተያያዘ አንድ ተማሪ መሞቱን የከተማዋ ነዋሪዎች ለኦሮምኛ ፕሮግራም ክፍል ባልደረባ ለጃለኔ ገመዳ ተናግረዋል። የነጆ ከተማ አስተዳደር ግን ተማሪው የሞተው በሕመም ምክንያት መሆኑን ሐኪም አረጋግጧል ይላል። ​በሌላ በኩል፥ ቤተሰብ …

በምዕራብ ወለጋ ዞን ከፖሊስ ድብደባ ጋር በተያያዘ አንድ ተማሪ መሞቱን የከተማዋ ነዋሪዎች ይገልጻሉ – VOA Read more »

ፍርዱ ዘገዬ

Mega books plc. ቋንቋን በጄኔቲክ ከአባትህ አትወርሰውም

ዳዊት በመዝሙሩ፣ “አቤቱ ጌታ ሆይ ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴም ወዳንተ ይድረስ፣ በመከራየም ቀን ፊትህን ከኔ አታዙር” ሲል ፈጣሪውን ተማጽኗል። እኛስ? ከልበ ድንጋዮቹ ወንድሞቻችን ግፍና በደል የሚታደገንን ሙሤ እንዲልክልን እንደዳዊት እየጮኽን ነው ወይንስ እንደኖኅና እንደሎጥ የቅጣት ዘመናት በአሥረሽ ምቺው የኃጢኣት ባሕር ከተዘፈቁት ጋር አብረን ፈጣሪን ረስተናል?

ሙሉውን አስነብበኝ …

Bekele Gerba. በቀለ ገርባፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)

በአሜሪካ የሕግ አፈ ታሪክ የስኮፐስ የዝንጀሮ (የይስሙላ) ፍርድ ቤት ነበር

እ.ኤ.አ በ1925 ጆን ስኮፐስ ተብሎ የሚጠራ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር በቴኔሲ ግዛት ድንጋጌን በመጣስ በአንድ የሕዝብ ትምህርት ቤት ውስጥ ስለሰው ልጆች ዘገምተኛ ለውጥ/human evolution ሲያስተምር ተገኝቶ እንደወንጀለኛ ተቆጥሮ ለፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር። የስኮፐስ የፍርድ ሂደት ጉዳይ ልጆቻቸው በዘመናዊ ትምህርት እንዲታነጹ በማይፈልጉ ምንም በማያውቁ ደንቆሮዎች እና ሌሎች ደግሞ ዘመናዊውን የአሜሪካ የሳይንስ ትምህርት እንዲገበዩላቸው በሚፈልጉ ሰዎች መካከል የሚደረግ ትግል ስለነበር የፍርድ ሂደቱ በመላው ዩኤስ አሜሪካ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ሲታይ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ለይኩን እሸቱ. Leyikun Eshetu(ኢ.ኤም.ኤፍ) ከሚኖርበት ሆላንድ ወደ ትውልድ ሀገሩ ኢትዮጵያ የገባው ወጣት ለይኩን እሸቱ፤ በፋሲካ በዓል ዋዜማ ስምንት ቦታ በስለት ወግተው የገደሉት ወንጀለኞች እስካሁን አልተያዙም። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ገዳዮቹ ባለጊዜዎች ስለሆኑ ሟች ደመ ከልብ ሆኖ ቀርቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Ethiopian Airlines. የኢትዮጵያ አየር መንገድይሄይስ አእምሮ

የ2008ን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ አንድ የኢትዮጵያ ይሁን የትግራይ ውሉ ባልታወቀ አየር መንገድ ውስጥ የሚሠራ ሰው በቤቱ ምሣ ጋበዘኝ። ተራ ጎረቤቱ እንጂ የሰማሁትን በሆዴ የማላሳድር ወሬ አራጋቢ መሆኔን አያውቅም። በሀገር ተቆርቋሪነት ስሜት በቀድሞው አጠራር ስለኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ደግሞ ስለ”ትግራይ አየር መንገድ” እየተንገፈገፈ ሲናገር እንደማንኛውም ተጋባዥ አደመጥኩ። የምፈልገውን ወሬ ከጨበጥኩ በኋላ የተከፈተልኝን ቢራ እንኳን በቅጡ ሳልጨርስ ወደቤቴ አመራሁ – እንደልማዴ ልጫጭር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በጥቂት ቀናት ልዩነቶች ውስጥ የደረሱትን እነዚህን ጥቃቶች መንግሥት ፈጥኖ መከላከል አለመቻሉ ደግሞ እያስወቀሰው ነው ። ከግጭቱ በኋላም ስለተወሰዱ እርምጃዎች ግልፅ መረጃ ባለመስጠትም እየተተቸ ነው ።

“በኢትዮጵያ ያለው የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት ምን ይመስላል?” ስትል ጽዮን ግርማ የሂዩማን ራይትስ ዎች የጥናት ባለሞያ ፍሊክስ ሆርንና የደህንነት ጥናት ተቋም የጥናትና ምርምር ባለሞያ ሃሌሉያ ሉሌን ጠይቃለች። ሁለቱም ባለሞያዎች በኢትዮያ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት እጦት ተባብሷል ይላሉ። ሙሉ ዘገባውን ያዳምጡ → listen

ገጣሚ ናቸዉ። ፀሐፌ ተዉነትም። ከብዙ የግጥምና የተዉኔት ድርሰቶቻቸዉ መሐል ጣልቃ የገባች አንዲት የታሪክ መፅሐፍ አለቻቸዉ። መፅሐፏ በ19ኛዉ መቶ ክፍለ-ዘመን በሥነ-ፅሑፉ መድረክ ዓለም አቀፍ ክብርና ሞገሥ ያተረፈዉ የሩሲያዊዉ ባለቅኔ የአሌክሳንደር ሰርግዬቪች ፑሽኪን ታሪክን ነዉ የምትወሳዉ። በእሳቸዉ አገላለፅ «ሕዝባዊ» የሚሉት ለገበሬዉና ለዝቅተኛዉ …

ባለቅኔ እና ፀሐፌ-ተዉኔት አያልነህ ሙላቱ – ዶይቸ ቬለ Read more »

የኢትዮጵያው ፌዴራል ዐቃቤ ህግ 33 ሰዎችን በአገር ውስጥ የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን (የኦነግን) ድርጅታዊ ህዋስ በመመሥረት፣ በመምራትና አባላት በመሆን የሽብር ወንጀል ፈጽመዋል ሲል በፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ክስ መሠረተባቸው። ፍርድ ቤቱም፣ ተከሳሾቹ መልስ እንዲሰጡ በማለት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ …

33 ሰዎች የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን ድርጅታዊ ህዋስ በመመሥረትና በአሸባሪነት ተከሰሱ – VOA Read more »

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከፍተኛ የአመራር አባል አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 22 በሽብር የተጠረጠሩ ተከሳሾች ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀረቡ። እነ አቶ በቀለ በማረሚያ ቤት ስድብ ማስፈራራትና ሌሎችም ከፍተኛ ተጽኖዎች እንደተፈጸመባቸው ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ …

የኦፌኮ ከፍተኛ የአመራር አባላት በማረሚያ ቤት ከፍተኛ በደል ይደርስብናል አሉ – VOA Read more »

የኢትዮጵያን ቋንቋ፣ ታሪክና ባህል ለበርካታ ትውልደ ኢትዮጵያውያን አዳጊ ህፃናትንና ወጣቶችን በማስተማር ላይ ከሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት መካከል በሜሪላንድ የሚገኘው የደብረ ገነት መድሃኒያለም ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን አንዱ ነው። በዚሁ ቤተክርስቲያን በምክትል አስተዳዳሪነትና በቅዳሴ በማገልገል ላይ የሚገኙት መልአከ ምህረት ቆሞስ አባ ገብረወልድ አገዝ ወደ …

የቆሎ ተማሪ በአሜሪካ – VOA Read more »

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ የወንጀል ችሎት በሽብር ተግባር በተከሰሱ ሰባት ተከሳሾች ላይ ዛሬ ከሰባት እስከ ዘጠኝ ዓመት ፅኑ የእስራት ቅጣት በየነ። በብይኑ መሰረት፣ የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ኦኬሎ ኦኳይ

·         የ2008 ዓ.ም በዓለ ስቅለት በእመቤታችን ቀን ውሏል። እናም ይሰገዳል? ወይስ አይሰገድም?
·         ይኸው ገጠመኝ በ1913 ዓ.ም ተከስቶ በነበረበት ወቅት አበው ጉዳዩን እንዴት ፈቱት?
(መምህር ጳውሎስ መልክአ ሥላሴ):- በተወሰኑ ዓመታት መካከል የስቅለት ዕለት በየጊዜው ዘንድሮ እንደሆነው ሲገጥም ክርክር ይነሳል። አስታውሳለሁ የመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪ ሳለሁ እንዲሁ ስግደት በእመቤታችን ዕለት በመዋሉ ምክንያት በተለያዩ አድባራት ተበታትነን በዓሉን የምናሳልፍ ተማሪዎች እንደየደብሩ አለቃ ስሜት ወይም ግንዛቤ አሳልፈን ተመልሰናል። ማለትም አንዱ ጋር ይሰገዳል አንዱ ጋር አይሰገድም። ይህ ክርክር ዘንድሮም ቀጥሏል። ቅዱስ ሲኖዶስ የማያዳግም ምላሽ ቢሰጥበት መልካም ነው። በቅድሚያ ጾሙን በጥሩ ሁኔታ የቻላችሁትን ያክል በትጋት ላሳለፋችሁ ሁሉ እግዚአብሔር ድካም ባለው ተጋድሎዋችሁ ቸርነቱን አክሎበት የልባችሁን መሻት ይስጥልኝ። የጾምና ጸሎታችሁም በረከት ይድረሰን ለብርሃነ ትንሳኤውም በሰላም ያድርሰን እላለሁ።
ወደ ተነሳሁበት ጉዳይ ስመለስ ዘንድሮ ስቅለት በእመቤታችን ቀን ውሏል። እናም ይሰገዳል? ወይስ አይሰገድም? በሕማማት ውስጥ ከትንሳኤ በፊት ያለችው ቅዳሜ የተሻረች ሰንበት ትባላለች (ቀዳሚት ስዑር) ሃይማኖተ አበው እንደሚያዝዘን በቅዳሜ ቀን መጾም ክልክል ነው። ከቀዳሚት ስዑር በቀር ይላል ስለተሻረች የሕማማትን ቅዳሜ እንጾማታለን በሕማማት ውላለችና። ልክ እንደዚሁ በሕማማት ማንኛውም በዓል ቢውል አይከበርም።
የእመቤታችን በዓል ስለሆነ ስግደት የለም ካልንና ካልሰገድን ቅዳሴ ሊኖር ይገባ ነበር። ቅዳሴ ሳይቀደስ የሚከበር የእመቤታችን በዓል የለንምና ስለዚህ የነገው አርብ ይሰገዳል። ይህ የኔ አሳብ አይደለም የአባቶቼ ትምህርት እንጂ። እስቲ የዛሬ ዘጠና አምስት ዓመት ገደማ ስቅለት እንደዛሬ ውሎ የተፈጸመውን ክስተት ላቅርብላችሁ። የታሪኩ ጸሐፊ ክቡር ብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደቂርቆስ ናቸው። ዓመተ ምህረቱም ሚያዝያ ፳፩ ቀን ፲፱፻፲፫ ዓ.ም( ሚያዝያ 21/ 1913 ዓ.ም ነው)። ምንም ያልተጨመረበትና ያልተቀነሰለት ታሪኩ እንዲህ ይላል።

“የስቅለት በዓል በዚህ ዘመን ሚያዝያ ፳፩ ቀን ላይ ውሎ ነበር። የአዲስ አበባ አድባራት ሊቃውንትም እኩሌቶቹ በማርያም በዓል ምክንያት ስግደት መስገድ አይገባም ሲሉ እኩሌቶቹ መስገድ ይገባል ብለው ነበርና የአሳብ ልዩነት ተፈጥሮ ዋለ።
ግርማዊት ንግሥትና ልዑል አልጋወራሽ በሚገኙበት ቤተ ክርስቲያን በሥዕል ቤት ኪዳነ ምህረት (በዓታ ያለችውን ኪዳነ ምህረት ነው) ባንድ ወገን መምህር ደስታ “መስገድ አይገባም ሲሉ” ግማሹ ሕዝብ እሳቸውን ተከትሎ አንገቱን ብቻ ጎንበስ እያደረገ ጸሎቱን ያደርስ ጀመር። እሳቸው ለማስረጃ ያቀረቡትም “መቅድመ ተአምር የማርያምን በዓላት እንደ እሁድ ሰንበት አድርጋችሁ አክብሩ ይላልና በእሁድ ቀን ምን ጊዜም ስግደት ስለሌለ ዛሬ መስገድ አይገባም” የሚል ቃል ነው።
በሁለተኛው ወገንም አለቃ ገብረ መድኅን “ስግደት መስገድ ይገባል” ስላሉ ግማሹ ሕዝብ እሳቸውን ተከትሎ ይሰግድ ጀመር። ለማስረጃም ያቀረቡት “የዛሬው በዓል በስግደት የሚከበር በዓል ነው። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታ በተሰቀለበት ቀን በመስቀሉ ስር ቆማ እያለቀሰች እና እየተጨነቀች በብዙ ድካም የዋለችበት ቀን ነው። ከዚህም በላይ ከእመቤታችን በዓል ይልቅ የክርስቶስ በዓል ይበልጣልና እንደ አበው ሥርዓት በዓሉ በስግደት ሊከበር ይገባል” የሚል ነበር። ይህ የአለቃ ገ/መድኅን አሳብ በትልቁ መምህር በአለቃ ወልደማርያም የጊቢ ገብርኤል አለቃ ሲደገፍ
የመምህር ደስታም አሳብ በሌሎች አለቆች ተደገፈ።
ከዚህም በኋላ ግርማዊት ንግሥትና ልዑል አልጋወራሽ ይህን የሊቃውንቱን ልዩነት ለማስቀረት እና አንድ ነገር ለማስወሰን ስለፈለጉ ወደ አቡነ ማቴዎስ ሁለት መልእክተኞችን ላኩ። እነርሱም የንግሥት መምህረ ንስሐ መላከ ገነት ተድላና የልዑል አልጋወራሽ መምህረ ንስሐ አባ ወልደማርያም ናቸው። እኔ ራሴ አባ ወልደማርያምን ተከትዬ ሄጄ ነበርና የሆነውን ሁሉ በቅርብ ተከታትዬዋለሁ።
መልክተኞቹ ከሊቀ ጳጳሱ ፊት ቀርበው የነገሩን አኳኋን ካስረዱ በኋላ በዛሬው ቀን ይሰገድ እንደሆነ ወይም አይሰገድ እንደሆነ ለመጠየቅ እና ውሳኔዎን ለመቀበል መጥተናል ብለው ተናገሩ። አቡነ ማቴዎስም ያለምንም ማመንታት ለአልጋወራሽ አሳወቋቸውና ይሰገድ ጀመረ።
የሆነው ሆኖ አብዛኛው ሰዓት በክርክርና በጥያቄ ምክንያት ባክኖ ነበር። እኔም ይህን ታሪክ መጻፌ ወደፊት የዚህ ዓይነት ነገር ቢያጋጥም ማስታወሻ እንዲሆን በማሰብ ነው።”
ምንጭ።- መርስዔ ኀዘን ወልደቂርቆስ “የሃያኛው ክ.ዘ. መባቻ የዘመን ታሪክ ትዝታዬ ካየሁትና ከሰማሁት” (1896-1923 ገጽ 237/38።)
++++++
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን
Deje Selam is a venue of news, views and opinions about or related to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. [email protected]

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ዛሬ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የብሔራዊ ቡድኑ የአሰልጣኞች እና ብሔራዊ ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በሙሉ ከስራቸው እንዲሰናበቱ መወሠኑን አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሪሽን ዛሬ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ የሆኑትን ኢንስትራክተር ዮሀንስ ሣህሌ ፣ ምክትል አሰልጣኝ የነበረው ፋሲል… Continue Reading →

ባለፈዉ ሐሙስ በጋምቤላ ክልል በጄዊ የስድተኞች መጠለያ ካምፕ አከባቢ ንብረትነቱ /ACF/ የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት የሆነ አንድ ተሽከርካሪ ባደረሰው አደጋ ሁለት የስደተኞች ልጆች ከሞቱ በኋላ ስደተኞቹ 21 የአካባቢውን ነዋሪዎች ሲገድሉ፣ ከ10 በላይ መቁሰለቸዉን ዘገባዎች ያሳያሉ።

ይገርምሃል ወንድሜ በሕይወትህ ድል አድርገህ ዋንጫ ወሰድክ ማለት እዚያው የልዕልና ማማ ላይ እንደተሰቀልክ ትቀራለህ ማለት አይደለም፡፡ አታየውም ቸልሲን መከራውን ሲቀበል፡፡ አምና እርሱ ዋንጫ ሲበላ ያየ ሰው ዘንድሮ መከራውን ይበላል ብሎ ማን ገመተ? ብዙዎችኮ ሲወጡ መውረድን ይረሱታል፡፡ ለሚወጣ ሰው ግን መውረድ …

ሕይወት – ሌስተርና ቼልሲ (ዳንኤል ክብረት) Read more »

በትግራይ ክልል የእምባስነይቲ ህዝብ ቀድሞ የነበረውን ወረዳ እንዲመለስለት ከ20 ዓመታት በላይ ጠይቆ አወንታዊ መልስ ባለማግኘቱ ምክንያት የተሰማውን ቅሬታ ትላንት በሰላማዊ ሰልፍ ገልጿል።

መንግስት የቆየውን ወረዳችን የማይመልስልን ከሆነ ከወረዳ እስከ ተወካዮች ምክር ቤት የወከልናቸውን ሰዎች ከዛሬ ጀምሮ ውክልናችን ማንሳታችን እንገልፃለን ብሏል ህዝቡ።

ከ500 ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዕለተ ስቅለትን እንዴት ታከብር እንደነበር በመጠኑ ሊያሳዩን ከሚችሉ መዛግብት አንዱ ‹ዜና ደብረ ሊባኖስ› የተሰኘው መዝገብ ነው፡፡ ዜና ደብረ ሊባኖስ በ1586 ዓም የተጻፈ መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ አምስት ነገሮችን ይዟል፡፡ የደብረ ሊባኖስን ታሪክ ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት …

ሥርዓተ ዕለተ ስቅለት ዘደብረ ሊባኖስ – ዳንኤል ክብረት Read more »

“ጠዋት ቂሊንጦ ስንሄድ አራቱ ሰዎች የሉም። ያሉበትን የሚነግረን አላገኘንም።” ወ/ሮ ዓይናለም ደበሎ፤ ላለፉት አራት ወራት በማዕከላዊ እሥር ቤት የነበሩትና ካለፈው አርብ አንስቶ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተዛውረዋል፤ ከተባሉት የኦሮሞ ፌድራሊስት አመራር አባላት ቤተሰብ አባላት አንዷ ናቸው። ዝርዝር ዘገባውን ያዳምጡ → …

እስር ላይ የሚገኙትን አራት የኦፌኮ አመራር አባላት መጠየቅ እንዳልቻሉ ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ – VOA Read more »

በበፍቃዱ ኃይሉ

ዓይን የሚፈታተን ደብዛዛ ብርሃን ያለበት ክፍል ውስጥ አስገብተው ከኋላዬ ወፍራሙን የብረት በር፣ ልብ በሚያደባልቅ ጓጓታ ድብልቅ አድርገው ዘጉት፡፡ ወደመታሰሪያ ክፍል የገባሁት እንዲህ ነበር፡፡ ሰዓቱ ከምሽቱ 3፡00 ወይም 4፡00 ሰዐት ገደማ ነው፣ ሚያዝያ 17፣ 2006፡፡ ከውስጥ መሬት ላይ የተኙ ሰዎች ይታዩኛል፡፡ በእጄ ያንጠለጠልኩትን ፌስታል እንደያዝኩ ተራ በተራ አየኋቸው፡፡ አንደኛው ከተኛበት ተነስቶ ቁጢጥ አለ፡፡ ‹ካቦው ይሄንኛው ነው ማለት ነው› አልኩ በልቤ፡፡ ‹የሻማ ሲጠይቁኝ ኪሴ ውስጥ ያለውን ሁሉ ሰጥቼ ለመገላገል ፈልጌያለሁ› እነርሱ ግን የሻማ አልጠየቁኝም፡፡ ‹አረፍ በል› አሉኝ፡፡ ጠርዝ ላይ ተቀመጥኩ፡፡ ‹ራት በልተሃል?› አሉኝ፤ ‹አዎ በልቻለሁ›፡፡

‹ምን አድርገህ ነው?›
‹ጸሐፊ ነኝ፡፡›
‹አሃ፣ ጋዜጠኛ ነህ?›
‹አይ፣ ኢንተርኔት ላይ ነው የምጽፈው፡፡›
‹ሙስሊም ነህ?›
‹አይ አይደለሁም፡፡›

የሚያስፈራ ዝምታ ሰፈነ፡፡ ‹እናንተስ?› አልኳቸው፤ ዝምታውን ለመስበር፡፡

ቁጢጥ ያለው፣ ‹እኔ እና እሱ› አለ ወደ አንደኛው ልጅ እየጠቆሙ ‹በሙስሊሞች ጉዳይ ነው፤ እነሱ› አለኝ ወደሌሎች ሦስት ልጆች እየጠቆመ ‹ከጋምቤላ ነው የመጡት፤ እኚህ ከሶማሊ ክልል ነው የመጡት፡፡ ያኛው› ወደጥግ ወዳለው እየጠቆመ ‹በግንቦት ሰባት ነው የተጠረጠረው› አለኝ፡፡ ሰባት ነበሩ፡፡ እኔ ስምንተኛ ሆንኩላቸው፡፡ በሳይቤሪያ የዘጠኝ ቁጥር እስረኛ ሆኜ ተቀላቀልኳቸው፡፡ ማብራሪያውን የሰጠኝ ረደላ ሸፋ ነበር፡፡ ሦስቱ አኙዋኮች ኡማን ኝኬው፣ ኡጁሉ ቻም እና ኝጎ ኩምቻሬ ነበሩ፡፡ ሶማሌው፣ እኔ በገባሁ በሁለተኛው ቀን ስለተፈታ ዘነጋሁት፡፡ የረደላ አባሪ ሐሰን ነው፡፡ ጥግ ላይ የነበረውና በክፍላችን ብቸኛው የግንቦት ሰባት ወታደርነት ተጠርጣሪ የነበረው አበበ ካሴ ነበር፡፡

ኒጎ ኩምቻሬ እሱ ተኝቶባት የነበረውን ፍራሽ ለቆልኝ እስከመጨረሻ ድረስ የቆየሁባትን ጥግ ላይ ያለች ምቹ ቦታ አወረሰኝ፡፡ ‹በቃ፣ አሁን ተኛ እና ነገ እናወራለን› አሉኝ፡፡ እሺ አልኳቸው፡፡ እነርሱ ተኙ፡፡

አበበ ካሴ እኔ በገባሁበት ሰዐት ምርመራ ጨርሶ ነበር፡፡ ነገር ግን በአስፈሪ ዝምታ የተዋጠ ሰው ነበር፡፡ ተሰብስበን ኮንከር (ካርታ) ስንጫወት ብቻ፣ እየዳኘ በተራው ይጫወታል፡፡ እየቆየን ስንመጣ ግን ቀስ በቀስ ያዋራኝ ጀመር፡፡ ጠርጣራ ስለነበር፣ ድምፁን በጣም ዝቅ አድርጎ በእርጋታ ነበር የሚያዋራኝ፡፡ ምርመራ አምሽቼ ስመጣ፣ እልሄን የምወጣው እነሱ ጋር ነበር፡፡ ያሉኝን ብስጭቶችና ብሶቶች ሁሉ እነርሱ ላይ እዘረግፈዋለሁ፡፡ እነርሱም፣ አብዛኞቹ ምርመራቸውን ጨርሰው ክስ የሚጠባበቁ ስለነበሩ፣ እኔን ከበው ማፅናናት ብቻ ሆነ ሥራቸው፡፡ አበበ አንድ ቀን ማታ መጥቼ እንደለመድኩት ‹ሊገሉኝ ነው፤ ካልገደሉኝ አይለቁኝም› እያልኩ ሳማርር፡፡

‹አሁን ይቺን ተመታሁ ብለህ ነው?› አለኝ፡፡

በአባባሉ ተናድጄ መልስ ከመስጠቴ በፊት የእጆቹን አይበሉባ አሳየኝ፡፡ ‹ጥፍሮቼን እያቸው› አለኝ፡፡ ጥፍሮቹ ጣቶቹ ላይ የሉም፡፡ ‹እኔ እንኳን እንዲህ አድርገውኝ ዋጥ ነው ያደረግኳት፡፡ ወንድ ልጅ ቻል ነው ማድረግ ያለበት፡፡ ወንድ አደለህ እንዴ?› እኔ የወንድነት ጀብድ የምመኝበት ጊዜ ላይ አልነበርኩም፡፡ ይልቁንም እሱ እኔን ለመምከሪያ ያሳየኝ ጣቶቹ ማስፈራሪያ ሆነው አረፉት፡፡ እኔም ባለተራ ነኝ ብዬ አሰብኩ፡፡

አበበ ካሴ ቀድሞ የመከላከያ ሠራዊት አባል የነበረ፣ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት የተዋጋ፣ ከዚያ በኋላ ግን ለቅቆ ግንቦት ሰባትን የተቀላቀለ ወታደር ነበር፡፡ ሲራመድ ያነክሳል፡፡ ‹ምን አርገውህ ነው?› ስለው ‹ምኑን አውቄ› አለኝ፡፡ ሲደበደብ ራሱን ይስት ነበር፡፡ አበበ ካሴ ከኤርትራ ጎንደር የዘመዱን ሠርግ ለመታደም መጥቶ ነው የተያዘው፡፡ በምርመራ ወቅት የግንቦት ሰባት ወታደር መሆኑን በፍፁም አላመነም ነበር፡፡ ያደገበት እና የኖረበት ኩራት በዱላ ፊት መንበርከክ አልፈቀደለትም፡፡ ክስ ከተመሠረተበት በኋላ ግን ለፍርድ ቤቱ “አዎ፣ የግንቦት ሰባት ወታደር ነኝ፤ የሆንኩትም አምኜበት ነው” ብሏል፡፡

አበበ ካሴ ከኔ ክፍል ተቀይሮ ተስፋለም ታስሮበት ወደነበረው 4 ቁጥር የተዛወረው ከአጭር ቀናት በኋላ ነበር፡፡ ነገር ግን መልሰን ቂሊንጦ ዞን ሁለት ተገናኘን፡፡ አበበ መጀመሪያ የተከሰሰው በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ በአንቀጽ 4 ቢሆንም፣ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ከተደመጡ በኋላ ተቀይሮለት 7/1 ሆኖለታል፡፡ የዛኔ ‹እንኳን ደስ አለህ› ልለው ክፍሉ ሄጄ ነበር፡፡ ሳቀብኝ፡፡ ‹ታስሬ እያለሁ ቁጥር ተቀነሰልኝ ብዬ የምደሰት ይመስልሃል?› ስሜቱን አላጣሁትም፡፡

እንደአበበ ካሴ በቂሊንጦ አስተዳደር የሚጠላ የፖለቲካ እስረኛ አልገጠመኝም፡፡ አበበ ሕክምና ተከልክሎ እግሩ ከጊዜ ወደጊዜ እየተሸመቀቀ አጥሮ ግቢ ውስጥ በምርኩዝ ነው የሚንቀሳቀሰው፡፡ ብልቱ ላይ በምርመራ ወቅት በደረሰበት ጉዳት የሚያዥ ነገር ተከስቶበት ሕክምና ሲጠይቅ ተከልክሏል፡፡ በጥቅሉ የሰው ልጅ ላይ የሰው ልጅ ሊያደርስበት የሚችለው በደል ሁሉ እየደረሰበት ነው፡፡
አበበ ካሴ አሁን 7 ዓመት ከዘጠኝ ወር ፅኑ እስራት ተፈርዶበት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ገብቷል፡፡

እንደ አበበ ሁሉ አዱኛ እና መገርሳም በየቀኑ ሐሳቤ ናቸው፡፡ ማዕከላዊ ሳይቤሪያ የሚባለው ወንዶች ክፍል፤ ዘጠኝ ቁጥር ውስጥ ሁለት ሳምንት ከቆየሁ በኋላ ከክፍላችን የሚወጡ ሰዎች በዙ፡፡ ከሦስቱ የአኙዋ ልጆች አንዱ – ኝጎ ኩምቻሬ – ጓደኞቹ ላይ ሊመሰክር ተስማምቶ ወደጣውላ ክፍል ተዛወረ፡፡ ኡማን እና ኡጁሉ ክስ እስኪመሠረትባቸው ድረስ ወደሚቆዩበት ሸራተን ተዛወሩ፡፡ የሶማሊ ክልሉ ሰው ተፈታ፡፡ በምትካቸው ግን ብዙ ሰዎች መጡ፡፡

የአዳማ ዩንቨርስቲው አዱኛ ኬሶ መጣ፡፡ ገብረሚካኤል እና ሌላ ሥሙን የዘነጋሁት ሰው ከትግራይ ክልል መጡ፡፡ ሌላም ሰውዬ ከሶማሊ ክልል መጡ፡፡ አጀሌ ከቤንሻንጉል/ጉምዝ መጣ፡፡ ሁሉም የተጠረጠሩት በሽብርተኝነት ወንጀል ነው፡፡

ከሁሉም ሳቂታና ተጫዋች የነበረው አዱኛ ኬሶ ነበር፡፡ አዱኛ ከተያዘ 19 ቀናት እንደሆነው ነገረን፡፡ ‹የት ቆየህ?› አያውቀውም፡፡ ምክንያቱም፣ ወደቆየበት ቦታ ሲሄድም ሆነ ወደእኛ ሲመጣ ዓይኖቹ በጨርቅ ተሸፍነው ነበር፡፡ ሌላው ቀርቶ ወደሽንት ቤት ሲወሰድ እና ሲመለስ ዓይኖቹ በጨርቅ ይሸፈኑ ነበር፡፡ አዱኛ ወደኔ ክፍል ሲመጣ ግራ ዓይኑ ስር የበለዘ ነገር ነበረው፡፡ ‹ምንድን ነው?› ብዬ ስጠይቀው፣ ‹ሲይዙኝ በቡጢ የነረቱኝ ነው› አለኝ፡፡ አሁን ድረስ ያ የቡጢ አሻራ ጠባሳ ሁኖ ቀርቷል፡፡

ከጥቂት ቀናት በኋላ በፖሊስ ተደግፎ መጥቶ፣ በፖሊስ ተደግፎ 8 ቁጥር (የብቻ ጨለማ ቤት) ሲወጣና ሲገባ የቆየው መገርሳ ወደእኛ ክፍል ገባ፡፡ መገርሳ ወርቁ የሐሮማያ ዩንቨርስቲ ተማሪ ነበር፡፡ መገርሳ መጀመሪያ የተያዘው ሐረማያ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ላይ በተወረወረ ቦምብ ተሳትፈሃል በሚል ተጠርጥሮ ነበር፡፡ መገርሳን ሐሮማያ ከተማ ተደብድቧል፡፡ ድብደባው እርቃን ነበር፡፡ እጆቹ በገመድ ተጠፍረው ጉልበቱን ያቅፍና በእጆቹ መታጠፊያ እና በቋንጃው መካከል እንጨት ያልፍና ይሰቀላል – ወፌ ይላላ፡፡ ከዚያ ይደበደባል፡፡ መገርሳ ይህንን ይነግረኝ የነበረው፣ እግሮቹ መታጠፊያ ላይ የቀረውን ሰምበር የመሰለ ነገር እያሳየኝ ነው፡፡ ‹ተንጠልጥዬ እየተሰቃየሁ ብልቴን ይጎትቱታል› ብሎኛል ሲነግረኝ፡፡ በመሐሉ ራሱን ይስታል፡፡ ‹ከዚያ ቅዝቅዝ ሲለኝ እነቃለሁ፤ ስነቃ አውርደውኝ አገኛለሁ፡፡ አሁንስ ታምናለህ አታምንም ይሉኛል፡፡ የማምነው ነገር እንደሌለ ሲያውቁ መልሰው ይሰቅሉኛል፡፡› አለ፡፡ በመጨረሻ ግን መገርሳ ተረታ፡፡
‹ሳስበው ከምሞት፣ ዕድሜ ልክ ተፈርዶብኝ በሕይወት ብኖር ይሻለኛል ብዬ አሰብኩ› አለ፡፡ ‹አዎ፣ እኔ ነኝ ቦንቡን የወረወርኩት› አላቸው፡፡ መርማሪዎቹ ተደሰቱ፡፡ ራቁቱን የሆነ ክፍል ውስጥ መሬት ላይ አጋድመውት ሄዱ፡፡ ከዚያ ‹በሕይወቴ የማይዘነጋኝ ዘግናኝ ነገር ተከሰተ› ብሎ የሚከተለውን አጫወተኝ፡፡ ቤቱ ውስጥ የዶሮ ጫጩቶች ነበሩ (የአንዱ የደህንነት ሰራተኛ መኖሪያ ቤት ውስጥ ይመስለዋል ያለው)፡፡ ጫጩቶቹ መጥተው እየተራመዱ እላዩ ላይ ይወጡበታል፡፡ መገርሳ እነርሱን “እሽ” ብሎ የሚያባርርበት አቅም አልነበረውም፡፡ እግራቸው ይበላዋል፡፡ ሲነግረኝ ‹ጫጩቶቹን ጠላኋቸው› ነበር ያለኝ፡፡ ግን ምንም ሊያደርጋቸው አልቻለም፡፡

በማግስቱ በካሜራ ፊት ሐረማያ ዩንቨርስቲ ግቢ ውስጥ የፈነዳውን ቦምብ ያፈነዳው እሱ እንደሆነ አመነ፡፡ እሱ በወቅቱ ዩንቨርስቲው ግቢ ውስጥ አልነበረም፡፡ እንዲያውም የታቀደ ረብሻ እንዳለ መረጃው ቀድሞ ደርሶት ለዩንቨርስቲ ግቢው የኦሕዴድ ጽ/ቤት ደውሎ ማስጠንቀቁን ነግሮኛል፡፡ ያ ሁሉ አልፎ አዲስ አበባ ማዕከላዊ ተላልፎ ተሰጠ፡፡ ነገር ግን፣ እሱ ወደአዲስ አበባ እየመጣ እያለ ፖሊስ የእውነትም ቦንቡን ወርውሮታል ብሎ ያመነበትን ሰው ያዝኩኝ አለ፡፡ ነገር ግን ካፈርኩ አይመልሰኝ ባይ መንግሥት መገርሳን ከመክሰስ አልተመለሰም፡፡ ጽፈኸዋል በተባለው ግጥም ክስ ተመስርቶበት ‹ተከላከል› ተብሎ፣ መከላከያ ምስክሮቹን አስደምጦ ‹የነጻ› ወይም ‹ጥፋተኛ› ብይን እየተጠባበቀ ነው፡፡ አዱኛ ኬሶም በተመሳሳይ መዝገብ ‹በቄሮ አባልነት› ተከላከል ተብሎ መከላከያ ምስክሮቹን እያስደመጠ ነው፡፡

ታስሮ መፈታት ቅጣት ነው፡፡ ሰቅጣጭ በደል በሚፈፀምባት ከተማ፣ አገር ሠላም ብሎ ከሚኖር ሰው ጋር ምንም እንዳላየ፣ ምንም እንዳልሰሙ መስለው የመኖር ቅጣት፡፡

ማዕከላዊ ምርመራ ወጥቼ ስገባ፣ መታሸት ሲያስፈልገኝ ሲያሸኝ፣ ጨዋታ ሲያመምረኝ ሲያጫውተኝ የነበረው ረደላ ሸፋ እና አባሪው ሀሰን ሁለቱም ‹ነጻ ለመውጣት ወይም ጥፋተኛ ለመባል ተከላከሉ› ተብለው መከላከያ ምስክሮቻቸውን ለማስደመጥ ቀጠሮ ይዘዋል፡፡ የቤንሻንጉሉ አጄላ አራት ዓመት ተፈርዶበት ሸዋ ሮቢት ማረሚያ ቤት ተወስዷል፡፡ አቦይ ገብረሚካኤል ‹ተከላከሉ› ተብለው መከላከያ ምስክር እያስደመጡ ነው፡፡ ኡማን እና ኡጁሉም ‹ጥፋተኛ› ተብለው ፍርዳቸውን ለመመቀበል ቀጠሮ ተይዞላቸዋል፡፡

እስረኞች ይመጣሉ፣ ከሰሜን ይመጣሉ፣ ከደቡብ ይመጣሉ፣ ከምሥራቅ ይመጣሉ፣ ከምዕራብ ይመጣሉ፡፡ በሕዝብ ጥቅም ሥም ጦር መዝዞ ሥልጣን የተቆጣጠረው መንግሥት ዛሬም የፖለቲካ እስረኞች የሉኝም ይላል፡፡

ከአራት መቶ በላይ የሚሆኑ አሶሳ አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች በፌደራል ትምሕርት ሚኒስቴርና በቤንሻጉል ክልል ምክር ቤት ላይ የፍትሐቤር ክስ መመስረታቸው ታወቀ። ለክክልሉ ምክር ቤት መጥሪያ ሊሰጡ የሄዱት የአርሶ አደሮቹ ተወካይ ተይዘው መታሰራቸውም ይሰማል። የክልሉን ምክትል አስተዳዳሪ እና የቤንሻንጉል ጉምዝ ሕዝቦች …

ከ400 በላይ የሚሆኑ አሶሳ አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች ክስ መመስረታቸው ታወቀ – VOA Read more »

በናትናኤል ፈለቀ

ሚያዝያ 17 ቀን 2006 ከምሽቱ 3፡30 አካባቢ ከቤት የሸከፍኩትን ጋቢ እና ቅያሪ ልብስ እንደያዝኩ ማዕከላዊ በተለምዶ ሳይቤሪያ በመባል የሚታወቀው የእስረኞች ማጎሪያ ሕንፃ 7 ቁጥር ገባሁ፡፡ ውስጥ 7 ሰዎች ነበሩ፡፡ እኔ 8ኛ ሆኜ ነው የተቀላቀልኳቸው፡፡ ምንም ሳልናገር ቆሜ ክፍሉን አየሁት፡፡ ሰዎቹን አየኋቸው፡፡
አንድም ቃል ሳንለዋወጥ አንደኛው “ኢትዮጵያ” ብሎ በሀዘኔታ ጭንቅላቱን ነቀነቀ፡፡
ኦቻን ኦፕዮ የአኝዋክ ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ በ1996 በጋምቤላ የተቀሰቀሰውን ግጭት ሸሽተው ወደአሁኗ ደቡብ ሱዳን ከተሰደዱት ኢትዮጵያውያን መካከል ነበር፡፡ በወቅቱ የተከሰተውን ችግር ተከትሎ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ይፈፅም የነበረውን ግድያ በመሸሽ ለቀናት ጫካ ውስጥ ተደብቆ ከቆየ በኋላ ነበር ቀናትን የፈጀ የእግር ጉዞ አድርጎ ደቡብ ሱዳን የገባው፡፡ ከጁባ አቅራቢያ የአለ የስደተኞች ጣቢያ ውስጥ ከ8 ዓመት በላይ የቆየው ኦቻን ቤተሰብ መሥርቶ፣ ሁለት ልጆችን ወልዶ በጁባ የተረጋጋ ሕይወት መኖር ጀምሮ ነበር፡፡
የ1996ቱ የጋምቤላ ቀውስ በተቀሰቀሰበት ወቅት ክልሉን በርዕሰ ብሔርነት ይመሩ የነበሩት አቶ ኦኬሎ ኦኳይ በደቡብ ሱዳን መንግሥት ተይዘው ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፈው ሲሰጡ ከጁባ አብረዋቸው የታሰሩት የአኝዋክ ተወላጆች መካከል ኦቻን ኦፕዮ ነበር፡፡
ወደደቡብ ሱዳን ሲሸሽ ጫካ ውስጥ እሾሃማ የዛፍ ቅርንጫፍ የቀኝ ዓይኑን መቶት የማየት ችሎታውን ቢጋርድበትም የቀረችውን የማየት ችሎታውን በአኝዋክኛ የተተረጎመውን መጽሐፍ ቅዱስ እያነበበ የእስር ግዜውን ያሳልፋል፡፡ (በነገራችን ላይ መጽሐፍ ቅዱስን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደአኝዋ የተረጎሙት ኡመድ አግዋ በአሁኑ ወቅት በሽብር ወንጀል ተከሰው ቂሊንጦ ይገኛሉ፡፡)
ኦቻን ሲበዛ ሠላማዊ ሰው ነው፡፡ የሁለት ልጆቹ ነገር አብዝቶ ያሳሰበው ቀን ግን ከሰው ጋር መነጋገር አይፈልግም፡፡ አንድ ቀን ድንገት ብቻውን ስቅስቅ ብሎ ያለቅስ ጀመር፡፡ ሰባት ቁጥር በግዜው የቀረነው እሱ፣ እኔና ዘግየት ብሎ የተቀላቀለን ቢልሱማ የሚባል የሐሮማያ ዩንቨርስቲ ተማሪ ነበርን፡፡ ሁለታችን በጣም ተደናግጠን ምን እንደሆነ ጠይቀነው ሊነግረን ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ቆይቶ ሲረጋጋ ልጆቹ እንደናፈቁት እና ምን አጥፍቶ እንዲህ ያለ ፈተና እንደገጠመው እንዳልገባው እያማረረ አጫወተኝ፡፡
በነኦኬሎ ኦኳይ መዝገብ 3ኛ ተከሳሽ ሆኖ ቀድሞ ቂሊንጦ የወረደው ኦቻን ነበር፡፡ ከጥቂት ግዜያት በኋላ እኔም በነሶልያና ሽመልስ መዝገብ 3ኛ ተከሳሽ ሆኜ ቂሊንጦ ስወርድ ኦቻንን ዞን3 አገኘሁት፡፡ እንደመጀመሪያው ሁሉ ተንከባክቦ ግቢውን አላመደኝ፡፡
ኦቻን የአኝዋ አስተማሪዬም ነበር፡፡ ለቤት የመጀመሪያ ልጅ መሆኔን ስለሚያውቅ በአኝዋ ባሕል እንደሚደረገው ኡመድ እያለ ነው የሚጠራኝ፡፡ ትንሽ የማይባሉ የአኝዋ ቃላትንም አስተምሮኛል፡፡
የአኙዋኩ ጓደኛዬ የተከፈተበት የሽብር ክስ የአገር ግዛት አንድነትን ለማፍረስ ሞክሯል በሚል ተቀይሮለት ጥፋተኛ ተብሎ ቂሊንጦ ፍርዱን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ እስር ስገባ ያስተዋልኩት በሐዘን ተሞልቶ “ኢትዮጵያ!” ሲል ያማረረው ፊቱ እስከ ሕይወቴ ፍፃሜ አብሮኝ ይዘልቃል፡፡ ይህችን አጭር ጦማር ያለህበት ድረስ መንፈስ ይዞት ይመጣ እንደሆን ይነ ፑዋ! ኦሎ ቦንጎ! ብዬሃለሁ፣ ኦቻን ኦፒዮ፡፡

«የሽምብራው ጥርጥር የዛፎቹ ፍሬ የትም የትም ዞሬ ትዝ አለኝ ሀገሬ» የዛሬ ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩን «የመሰንቆው ሊቅ» ጌታመሳይ አበበ ዘመን ተሻጋሪ ከሆኑ የባህል ሙዚቃ ጨዋታዎች በግንባር ቀደምትነቱ የሚታወቀዉ ነዉ። ሁለ ገቡ ከያኒ ጌታመሳይ አበበ «የጥበብ ገበሪም » በመባል ይታወቃሉ። …

«የመሰንቆው ሊቅ» ጌታመሳይ አበበ – ዶይቸ ቬለ Read more »