ያለፍርድ የታሠረዉ ጋዜጠኛ – ዶይቸ ቬለ

ነገረ ኢትዮጵያ የተሰኘዉ ጋዜጣ አዘጋጅ ጌታቸዉ ሽፈራዉ ክስ ሳይመሰረትበት ከአራት ወራት በላይ መታሠሩን ጠበቃዉ አስታወቁ። ጠበቃ አመሐ መኮንንን ዛሬ እንዳስታወቁት የሐገሪቱ የፀረ-ሽብር አዋጅ በሚያዘዉ መሠረት ፖሊስ በደንበኛቸዉ ላይ በአራት ወራት ዉስጥ ክስ መመሥረት አለያም እስረኛዉን መልቀቅ ነበረበት። ፖሊስ በተደጋጋሚ የጊዜ ቀጠሮ ቢጠይቅም እስካሁን በይፋ ክስ አልመሰረተም። ጋዜጠኛ ጌታቸዉን አለቀቀምም። ዝርዝር ዘገባውን ያዳምጡ → listen