በያቤሎ የአውቶቡስ አደጋ አሥራ ሦስት ሰው ሞተ – VOA

በደቡብ ኦሮምያ፤ ቦረና ዞን ውስጥ ትናንት፣ ዓርብ ምሽት ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ ቢያንስ የ13 ሰው ሕይወት መጥፋቱን የሆስፒታል ምንጮች አስታወቁ፡፡

አደጋው የደረሰው አንድ መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከልክ በላይ አሳፍሮ ሜጋ ወረዳ ውስጥ ካለችው የዓርብ ገበያ ከሚቆምባት ዱቡሉቂ ከተማ ወደ ጎብሶ የገጠር ቀበሌ ሲያመራ ቀርሳ ቦሩ ላይ በመገልበጡ መሆኑን የአባባቢው ምንጮች ለቪኦኤ ገልፀዋል።

በአደጋው ጉዳት የደረሰበት ብዙ ሰው ወደ ያቤሎ ሆስፒታልና በአካባቢው ወዳሉ የጤና ተቋማት መወሰዳቸው ተገልጿል።