Tag: Ethiopians
ወንድ ሆኖ ሳለ የሴት ጾታ ነው ያለኝ በማለት ያጭበረበረው ወጣት በእስራትና በገንዘብ ተቀጣ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ወንድ ሆኖ ሳለ የሴት ጾታ ነው ያለኝ በማለት ሴት የሚያስመስለውን አልባሳትና መዋቢያዎች ተጠቅሞ በማታለል በርከት ያለ ገንዘብ ለመውሰድ ሲሞክር የተያዘው የ17 ዓመቱ ወጣት በጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ።
ሙሉቀን ተመስገን የተባለው ይህ ተከሳሽ ሴት ሊያስመስለው የሚችለውን ውጫዊ መለያዎችን በመጠቀምና ስሙን ቅድስት በማለት ነው ድርጊቱን የፈጸመው።
ተከሳሹ የግል ተበዳይ የሆነችውን ግለሰብ ከተዋወቀ በኋላ ነው ቤቷ በመመላለስ በርከት ያለ ገንዘብ ለመውሰድ የሞከረው።…
ኢትዮጵያዊያን አንዳርጋቸውን ሲያዩ የሚታያቸው ጽናት፣ አርበኝነትና አልበገር ባይነት ነው። ሲል ግንቦት 7 ለፍትህ፣ ለዲሞክራሲና ለነፃነት ንቅናቄ ገለጸ።
ግንቦት 7 <<ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌን እንሁን!!!>> በሚል ርእስ ዛሬ ታህሳስ 29 ቀን ባስነበበው ርእሰ-አንቀጽ፤በህወሓት ሙሉ ቁጥጥር ስር የሚገኘው የፌደራል ፖሊስ እሁድ እለት በቴሌቪዥን ፕሮግራሙ በግፍ እስር ላይ የሚገኘውን የግንቦት 7 ዋና ፀሐፊን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለ 10 ደቂቃ አቅርቦት እንደነበር በማውሳት፤ይህ የ10 ደቂቃዎች ምስል ለቁጥር በሚያታክት ሁኔታ ተቆራርጦ የተቀጣጠለ በመሆኑና አቶ አንዳርጋቸው በትክክል ምን እንዳለ […]
ታምራትና ስብሃት
ጠንቋይ ታምራት ገለታ ለእስር የበቃበት ምክንያት ተከታዩን እንደሚመስል የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ጠንቋይ ታምራት ሸራተን ጐራ ይላል፤ አካሄዱ ስብሃት ነጋን ለማግኘት ነበር። ሲያገኛቸው ትእቢት በተሞላበት አነጋገር « እርሶ ዘንድ የላኩኝ ባለስልጣናት ናቸው። ከበቂ በላይ ገንዘብ ያለኝ ሰው ነኝ። በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘቤን ኢንቨስት ማድረግ ስለምፈልግ መሬት እንዲሰጠኝ ትእዛዝ ያስተላልፉልኝ» ይላል። ስብሃትም « ምናልከኝ?» ይሉታል። ታምራት ደረቱን ለጥጦ […]
አሁን አንድነት ግልፅ ጦርነት የታወጀበት ይመስላል – አቶ ኪዳኔ አመነ – የመድረክ ወጣት አመራር
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በተመለከተ ብዙ እየሰማን ነው፡፡ ፓርቲው ራሱን የማፅዳት ሃላፊነት ከተወጣ በኋላ ገዢው ፓርቲ ጥርሱን የነከሰበት ይመስላል፡፡ ብዙ ፈተና እየገጠመው ነው፡፡ በምርጫ ቦርድ ጥያቄ መሰረት ጠቅላላ ጉባኤ በድጋሚ እስከማድረግም ደርሰዋል፡፡በኔ እምነት አንድነት ፓርቲ በበኩሉ ብዙ ርቀት የሄደ ይመስለኛል፡፡ ትእግስታቸው አደንቃለሁ፡፡ ፓርቲው በውስጡ ከጥቂቶች በቀር በዙዎቹ ቁምነገር የሚያስቡ የምናከብራቸውና የምንወዳቸው ጥሩ ሰዎች አሉት፡፡ ትርጉም […]
መታረም የሚገባዉ ማነዉ? ርዕዮት አለሙ ከቃሊቲ እስር ቤት
በግል የህትመት ዉጤቶች አማካኝነት በሀገሬ ዉስጥ የምመለከታቸዉን ችግሮች ለህዝብ ማቅረብና እንደዜጋም መፍትሔ ይሆናሉ ብዬ የማስባቸዉን ሀሳቦች መጠቆም ከጀመርኩ አምስት አመታት አለፉ፡፡ የመጀመሪያ ፅሑፌን ያዘጋጀሁት ” “ስህተቶችን” ለማረም የተፈፀሙ ስህተቶችና የስህተት ማረሚያ እርምጃዎች” በሚል ርዕስ እንደነበረ አስታዉሳለሁ፡፡ በዚህም ፅሑፍ የፕሬስ፣የፖለቲካፓርቲዎች ምዝገባና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የተመለከቱ አዋጆች የወጡበት ምክንያትና እንደሀገር የሚያሳድሩትን ተፅእኖ ለመዳሰስ ብሎም ኢህአዴግ ከስህተቶቹ እንዲታረም ለመምከር ሞክሬያለሁ፡፡
የኢህአዴግ ሰዎች በአንድ የገዢዉ ፓርቲ ልሳን በሆነ ድረገፅ አማካኝነት የማስጠንቀቂያ ይዘት ያለዉ ምላሽ መስጠት የጀመሩት ከላይ ከጠቀስኩት የመጀመሪያ ፅሁፌ ጀምሮ የነበረ ቢሆንም በአዲስፕሬስ ጋዜጣ ላይ በአዘጋጅነት ተቀጥሬ መስራት ስጀምር ግን ሁኔታዉ እየባሰ መጣ፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም አዳማ ላይ ከተለያዩ ሚዲያዎች ለተዉጣጣን ጋዜጠኞች የሰጠዉን ስልጠና ከተካፈልኩ በኋል ከስልጠናዉ ጋር በተያያዘ ለህትመት ያበቃሁት ፅሁፍ ኢህአዴጎችን በእጅጉ አስቆጣቸዉ፡፡ በመሆኑም ወደቢሮአችን ተደዉሎ ከኢህአዴግ ፅህፈት ቤት የተደወለ መሆኑ ከተገለፀ በኋላ ለጽሑፌ ምላሽ የላኩ በመሆኑ በፍጥነነት እንድናወጣዉ ቀጭን ትዕዛዝ ተሰጠን፡፡ ምላሻቸዉን ለማዉጣት የእነሱ መደወልም ሆነ ትዕዛዝ አስፈላጊ አልነበረም፡፡ የዝግጅት ክፍላችን አንድ ጽሑፍ የቀረበበት አካል ምላሹን በዚያዉ በተፃፈበት የህትመት ዉጤት ላይ ማስነበብ እንደሚችል በህግ የተደነገገ መሆኑን ከማወቁም በላይ የትኛዉንም አይነት ሀሳብ ለማስተናገድ ክፍት ነበርና ምላሻቸዉን በጋዜጣችን ላይ ታተመ፡፡ በዚህ ብቻ ግን አልተገቱም፤ በወቅቱ የገዢዉ ፓርቲን ሀሳብ በማቀንቀን ይታወቁ የነበሩት እንደ ዳጉ ኢትዮጵያና ሰነድ ያሉ ጋዜጦች ሀሳቦቼን በሃሳብ መምታት ባለመቻላቸዉ ይሁን ባለመፈለጋቸዉ ተራ ዘለፋዎችን ያወርዱብኝ ጀመር፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የገዢዉ ፓርቲ ደህንነቶች ስልክ በመደወል፣ በዝግጅት ክፍላችን አድራሻ በስሜ ደብዳቤ በመላክና በአካልም በማግኘት ጭምር መንግስትን የሚተቹ ፅሑፎችን እንዳልፅፍ ሊያስፈራሩኝ ሞከሩ፡፡ “ማስፈራራት የሚቻለዉ የሚፈራ ሲኖር ነዉ” እንዲሉ ሙከራቸዉ ዋጋ አልነበረዉም፡፡ ምክንያቱም የመጀመሪያ ፅሑፌን ለህትመት ከማብቃቴ በፊት ልከፍለዉ ስለምችለዉ መስዋዕትነት በሚገባ አስቤበታለሁ፡፡ የሀገሬን ጉዳይ በንቃት የምከታተል ዜጋ እንደመሆኔም ከገዢዉ ፓርቲ የተለየ ሀሳብ ያቀነቀኑ ሰዎች የደረሰባቸዉን በሚገባ አዉቃለሁ፡፡ በመሆኑም ከሁለት መጥፎ ምርጫዎች አንዱን ማለትም እነሱ የደረሰባቸዉን ግፍ እንዳይደርስብኝ የሀገሬን ጉዳይ በተመለከተ ፍዝ ተመልካች መሆንን ወይም በሙያዬ የምችለዉን አስተዋፅኦ አበርክቼ የሚመጣዉን መቀበል መምረጥ ነበረብኝ፡፡ ሁለተኛዉን የተሻለ መጥፎ ምርጫ ከመረጥኩ የሰነበትኩ በመሆኑም እየበረከቱ የመጡትን ማስፈራሪያዎች ከቁብ ሳልቆጥር የጋዜጠኝነት ስራዬን መቀጠል ቻልኩ፡፡ በዚሁ መሰረት ስራ ለመያዝ፣ የደረጃ እድገት ለማግኘትም ሆነ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከደህንነት ስጋት የፀዳ ኑሮ ለመኖር የኢህአዴግ አባል ካልሆነም ደጋፊ መሆን ከጊዜ ጊዜ ግድ እየሆነ መምጣቱን የሚያሳዩ፣ ገዢዉ ፓርቲ እንዳጎናፀፈን የሚገልፅልን ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በተጨባጭ አለመኖሩን የሚሞግቱ፣ የኢህአዴግን እንደሀገር የማሰብ ችሎታ ወይም ፍቃደኝነት አናሳ መሆን የሚተቹና ሌሎችም መንግስት ቀናነት ቢኖረዉ ኖሮ ሊታረምበት የሚያስችሉትን በርካታ ፅሑፎች አቀረብኩ፡፡ አንድ ቀን ጧት ግን አምባገነኑ መንግስታችን ከጀመርኩት ጉዞ ገታኝ፡፡ ሰኔ10/2003 በወቅቱ እሰራባት በነበረችዉ ተወዳጇ ፍትህ ጋዜጣ ላይ የቀድሞዉን ጠቅላይ ሚኒስትር በተመለከተ ፅሑፍ ለህዝብ ማቅረቤን ተከትሎ ሰኔ14/2003 ዓ.ም ለእስር ተዳረግሁ፡፡
ማዕከላዊና ቃሊቲ ምንና ምን ናቸዉ?
ዉድ አንባብያን፤ ፊዘኛዉ መንግስታችን በሽብርተኝነት እንደሚጠረጥረኝ ገልፆ በእጆቼ ካቴና በማጥለቅ በቁጥጥር ስር አዋለኝ ካዋለኝ ከዚያ ቀን ጀምሮ እስካሁን ድረስ ለቁጥር የሚያታክቱ የመብት ጥሰቶችን እየፈፀመብኝ ይገኛል፡፡ ለአብነት ያህል እጅግ በጣም ጥቂቶቹን እነሆ!
ከህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ነዉ የሚባልለት ህገመንግስት በጥበቃ ስር ያሉ ሰዎች በጠበቆቻቸዉ የመጎብኘት መብት እንዳላቸዉ ቢገልፅም እኔና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች ግን ይሄ መብታችን በማዕከላዊ አለቆች ተጥሷል፡፡ ጠበቃዬን ለማግኘት የተፈቀደልኝ ምርመራዉ ከተጠናቀቀና ቃል ከሰጠሁ በኋላ ወደቃሊቲ ለመዉረድ የአስርቀናት ዕድሜ ያህል ሲቀረኝ ነበር፡፡ በቤተሰብና በጓደኞቼ ለመጎብኘት የተፈቀደልኝም ሁለት ወር ከ3 ሳምንታት ክልከላ በኋላ ነበር፡፡ ከጠበቃዬ ጋር እንዳልገናኝ ተደርጎ የሚካሄደዉ ምርመራ የፃፍኳቸዉን ፅሑፎች ለምን እንደፃፍኩ፣ ከበስተኋላዬ ሆኖ የሚገፋኝ አካል ስለመኖር አለመኖሩና የመሳሰሉት ጥያቄዎች ላይ ያተኮረ ቢሆንም አልፎ አልፎ ደግሞ መልኩን ይቀይራል፡፡ አንዳንድ ቀን መርማሪዎቹ በማስተምርበት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በተካሄዱ ስብሰባዎች ላይ ያቀረብኳቸዉን ሀሳቦች እያነሱ ከመንግስት የደህንነት ሀይሎች የሚያመልጥ ምንም ነገር እንደሌለ በመግለፅ ቢጤ ያሰሙኝ እንደነበር ሳልጠቅስ ማለፍ አልፈልግም፡፡፡ እንዲህ አይነቱ ንግግራቸዉ አሰልቺዉን ምርመራ ዘና እልበት ዘንድ የሚረዳኝ የእፎይታ ጊዜ ሰጥቶኛል፡፡ በአደባባይ ስብሰባዎች ላይ የተናገርኩትንና ደህንነት ሊሰልለዉ የማያስፈልገዉን ግልፅ ነገር እንደ ትልቅ የደህንነቶች የስራ ዉጤት ተደርጎ ሲገለፅ ከመስማት በላይ ምን የሚያዝናና ነገር ይገኛል? የት/ቤት ርዕሰ መምህራኖች በሙሉ የኢህአዴግ አባል እንዲሆኑ የተደረገበት ምክንያት መንግስት እንደሚለዉ የትምህርት ፖሊሲዉን ለማስፈፀም ሳይሆን የመምህራንንና የተማሪዎችን የፖለቲካ አቋም ለማወቅና ይህንኑ ሪፖርት ለማድረግ መሆኑን የማይረዳ መምህር ይኖራል? ይህንን ለማድረግ ፍቃደኛ ያልሆኑ ርዕሰ መምህራኖች ሰበብ እየተፈለገላቸዉ ከቦታቸዉ እንዲነሱ ሲደረግስ ስንታዘብ አልኖርንም? “ሁሉን ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራል” አለ ያገሬ ሰዉ! ሆዴ ባዶ እንዳይቀር ሁሉን መተንፈሴን ትቼ የጀመርኩትን የማዕከላዊ ምርመራ ጉዳይ ልቀጥል፡፡
የምርመራዉ ይዘት ከጥቂት ሳምንታት በኋላ መልኩን እየቀየረ መጣ፡፡ በሪፖርተርነት እሰራበት የነበረዉ የኢትዮጵያ ሪቪዉ ድረገፅ አዘጋጅ ኤልያስ ክፍሌ የሽብር ተልዕኮ እንደሰጠኝ በሀሰት እንድናገርና ተከሳሽነቴ ቀርቶ ምስክር ሆኜ እንድፈታ ለማድረግ የተለያዩ ጫናዎቸው ይደርሱብኝ ጀመር፡፡ ለአምስት ደቂቃ ያህል ጧትና ማታ ወደመፀዳጃ ቤት ለመሄድ ከሚከፍቱልኝ በስተቀር ለአስራሶስት ቀናት ያህል ብቻዬን አንድ መጥፎ ሽታ ያለዉ ክፍል ዉስጥ ተዘግቶብኝ ከረምኩ፡፡ በዚህ ወቅት ጉዳዬን የያዘዉ ዐቃቤህግ ማዕከላዊ በመምጣት እያስጠራኝ ሀሳቤን የማልለዉጥ ከሆነ እድሜ ልክ ወይም ሞት እንደሚያስፈርድብኝ ይዝትብኝ ነበር፡፡ ሀሰን ሽፋ በበኩሉ በሀሳባቸዉ የማልስማማ ከሆነ የያዘኝን የወጣት ጀብደኝነት ማስተንፈስ ለነሱ ከባድ ስራ አለመሆኑን ነግሮኛል፡፡ በኔ በኩል ደግሞ ከተጠረጠርኩበት ወንጀል ንፁህ መሆኔ እንጂ ኤልያስ ላይ በሀሰት መመስከሬ ሊያስፈታኝ እንደማይገባ ስለማምን ይህንኑ በተደጋጋሚ አስታዉቄ ተከሳሽ መሆንን መረጥኩ፡፡ ኢህአዴግ እስካለ ድረስ የተሻለዉን መጥፎ እየመረጡ መኖር ዕጣፋንታችን ከሆነ ቆየ አይደል?
ማዕከላዊ እያለሁ ከተፈፀሙብኝ የመብት ረገጣዎች ዉስጥ አንዱ የሆነዉ በአንድ ፖሊስ የተሰጠኝ ጥፊና ከግድግዳ ጋር ማጋጨት በተለይ ወንድ የፖለቲካ እስረኞች ከሚፈፀምባቸዉ ለዘላቂ የአካል ጉዳት የሚዳርግ ከባድ ድብደባ አንፃር ሳስተያየዉ የማዕከላዊ መርማሪዎች እንደሚሉት “ቁንጥጫ” ተብሎ ከመግለፅ የሚያልፍ ባለመሆኑ ብዙ ልልበት አልፈልግም፡፡ በወቅቱ የነበርነዉ ሴት እስረኞች ላይ ያን ያህል የከፋ አካላዊ ድብደባ አልተፈፀመም ማለት ግን የማዕከላዊ መርማሪዎች ለሴቶች ይሳሳሉ ማለት አይደለም፡፡ ለማሳያነት እስካሁን ድረስ ማዕከላዊ በተፈፀመባት ከባድ ድብደባ የተነሳ በህመም የምትሰቃየዋን የፖለቲካ እስረኛ እማዋይሽ አለሙን መጥቀስ ይቻላል፡፡ አይ ማዕከላዊ! ማዕከላዊ ዘና ብለዉ የሚራመዱ ኩሩ የኢትዮጵያ ልጆች በገቡ ሳምንት በማይሞላ ጊዜ ዉስጥ በቃሬዛና በሰዎች ድጋፍ በሸክም ሲያሳልፉና የድረሱልኝ ዋይታ ሲያቀርቡ የሰማሁበት አሰቃቂ ቦታ ነዉ፡፡ ምስላቸዉ ከአይኔ ላይ፣ ጩኸታቸዉ ከጆሮዬ ተጣብቆ የሚኖረዉ እነዚህ ወገኖቼን እያሰብኩ መናደድ መቆጨት የዕለት ተዕለት የኑሮዬ አካል ሆኗል፡፡
የማዕከላዊዉን የመብት ረገጣ እዚህጋ ገታ ላድርገዉና በተለይ የፖለቲካ እስረኞችን ሰብአዊ መብት ከመጨፍለቅ አንፃር አምሳያዉ ወደ ሆነዉ የቃሊቲ እስር ቤት ልለፍ፡፡ ጳጉሜ3/2003 ዓ.ም ቃሊቲ እንደገባሁ በኋላ ላይ የጥበቃ ክፍል ሀላፊ እንደሆነች በተገነዘብኩት ሀላፊ አማካኝነት ጋዜጠኝነቴ ከታሰርኩ በኋላ የቀረ በመሆኑ ግቢዉ ዉስጥ በሚኖረኝ ቆይታ አርፌ መቀመጥ እንደሚኖርብኝ ተነገረኝ፡፡ አልጋ እስከሚለቀቅ ተብሎም እኔና በአንድ መዝገብ የተከሰስነዉ ወ/ሮ ሂሩት ክፍሌ ምንም እንኳን ሁለታችንም የሳይነስ በሽታ ያለብን ቢሆንም ሽንት ቤት አጠገብ መሬት ላይ ፍራሽ አንጥፈን እንድንተኛ ተደረገ፡፡ ዉድ አንባቢያን ስለቃሊቲ ስታስቡ ወደ አዕምሮአችሁ የሚመጡት ያማሩ ግንብ ቤቶችና የተዋቡ አልጋዎች ከሆኑ ኢቲቪ እንደሸወዳችሁ ልነግራችሁ እወዳለሁ፡፡ የፓስተር ዳንኤል ገ/ስላሴ ፕሪዝን ፌሎሽፕ የተባለ ድርጅት እንዳሰራቸዉ የሚናገሩት እነዚህ ያማሩ ግንብ ቤቶች ሁለት ክፍሎችና መፀዳጃ ቤት ብቻ ያሏቸዉ ሲሆኑ የተቀሩት በሴቶች ዞን ዉስጥ ያሉ ክፍሎች ከሁለት ያረጁ ግንብ ቤቶች በስተቀር በቆርቆሮ የተሰሩና እስረኞች በተጨናነቀ ሁኔታ የሚኖሩባቸዉ ናቸዉ፡፡ የቃሊቲ ምቾት አልባነት የሚሰማዉ አካልን ብቻ አይደለም፡፡ ቃሊቲ ከአካል በከፋ ሁኔታ ለነፍስና ለመንፈስ ይጎረብጣል፡፡ እንዴት ቢሉ እንዲህ እልዎታለሁ፡፡ የቃሊቲ የሴቶች ዞን ቤተመፃሕፍት ከጥቂት ወራት ጀምሮ በመፅሐፍቱ አይነትም ሆነ ቁጥር መሻሻልን ቢያሳይም እኔ ቃሊቲ ከገባሁ ጀምሮ እስከቅርብ ጊዜያት ድረስ ግን ከመኖር በማይቆጠር ደረጃ የሚገኝ ነበር፡፡ ይህንን ክፍተት ቤተሰብና ጓደኞቼ በሚያስገቡልኝ መፀሐፍት ለመሙላት ባስብም ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የሚመጡልኝ መፅሐፍት የቃሊቲን ሳንሱር እንደወደቁ ተገልፆ እኔጋ ሳይደርሱ ይመለሳሉ፡፡ ከነዚህ መፅሐፍት ዉስጥ አዲስአበባ ዩኒቨርስቲ የሚሳትማቸዉ የታሪክ መፅሐፍት ሳይቀር ይገኙበታል፡፡ ቃሊቲ ለመንፈስም አይመችም ያልኳችሁ በዚህ ብቻ አይደለም፡፡ በራሴ ወጪ ኢንድራ ጋኒዲ ናሽናል ኦፕን ዩኒቨርስቲ በርቀት ፖለቲካል ሳይንስ ለማጥናት ከብዙ ዉጣዉረድ በኋላ ተፈቅዶልኝ የተበዘገብኩ ቢሆንም የመማሪያ ሞጁሎቹን ለማስገባት ግን የቃሊቲ አለቆች ፍቃደኛ አልነበሩም፡፡ ከብዙ ደጅጥናት በኋላ ሞጁሎቹ ሲገቡ ደግሞ በትምህርቱ ዙሪያ ላነባቸዉ የሚገቡኝ አጋዥ መፅሐፍት ስለፖለቲካ የሚያወሩ በመሆናቸዉ በፍጹም ሊገቡ እንደማይችሉ የመፅሐፍት ገምጋሚዎቹ አረዱኝ፡፡ ይባስ ብሎ በዚያን ወቅት ከሌላዉ ጊዜ በተለየ ሁኔታ ምንም አይነት መፅሐፍት እንዳይገቡልኝ በመደረጉ ለጠቅላላ ዕዉቀት ያህል ሞጁሎቹን ማንበቤን ብቀጥልም ትምህርቱ ግን በዚህና በሌሎች ምክንያት ለማቋረጥ ተገደድኩ፡፡
በቃሊቲ የኔ ብቻ ሳይሆን ከእኔ ጋር የተቀራረቡ ወይም ደግሞ ሰላምታ ያቀረቡልኝ ሰዎች ሳይቀር መብታቸዉ ተጥሷል፡፡ ከሁለት አመታት በላይ የሚሆነዉን ጊዜ በርካታ እስረኞች በነበሩበት ክፍል ያሳለፍኩ ቢሆንም እኔን እንደሌላዉ እስረኛ ለመቅረብ የሞከሩ በሙሉ ስሜትን የሚጎዳ ወከባ፣ዘለፋና ለየት ያሉ ፍተሻዎችን አስተናግደዋል፡፡
በህክምና ጉዳይ የነበሩብኝን ችግሮች በተመለከተ ቤተሰቦቼ ደጋግመዉ የገለፁት መሠረታዊ ችግር በመሆኑ በዚህ ፅሑፍ ነካ አድርጌዉ ብቻ አልፋለሁ፡፡ ጡቴ ዉስጥ በበቀለዉ እጢ ምክንያት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የህክምና ክትትል በማደርግበት ወቅት በቀጠሮዬ ቀን ወደ ሆስፒታሉ ከምወሰድባቸዉ ይልቅ የማልወሰድባቸዉ ጊዜያት ይበዙ ነበር፡፡ የግራ ጡቴ ቀዶጥገና ከተደረገለት በኋላ በወቅቱ ክትትል ታደርግልኝ የነበረችዉ ዶክተር በሶስተኛ ቀን የቁስሉ ፕላስትር መቀየር እንዳለበትና በሳምንቱ ደግሞ ክሩ መዉጣት እንዳለበት ገለፀችልኝ፡፡ አብረዉኝ የሚሄዱት አጃቢ ፖሊሶች ከዶክተሬም ጋር ስነጋገር እዛዉ ነዉና የሚቆሙት እንዲህ አይነቱን ነገር ለማድረግ የሚችል ጤናጣቢያ ማረሚያቤቱ እንዳለዉ ተናገሩ፡፡ እኔም ቀጠሮ ቢሰጠኝ እንኳ በዚህ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ወደሆስፒታሉ ተመልሼ መሄድ አዳጋች መሆኑን ስለማዉቅ የተባሉት ነገሮች ቃሊቲ መፈፀማቸዉን አልጠላሁትም፡፡ በመሆኑም ለህክምና ክትትል የሶስት ወራት ቀጠሮ ተሰጠኝ፡፡ ክሩ መዉጣት ባለበት ቀን ስለጉዳዩ ለጥበቃ ክፍሉ አስታወቅኩ፡፡ እነሱም አሁን ደቡብ ሱዳን ከሚገኝዉ ጦር ጋር አብራ ከተጓዘች አንዲት የህወሐት ታጋይ የነበረች ነርስ ጋር አገናኙኝ፡፡ እሷም እዛዉ ጨርሼ መምጣት እንደነበረብኝና እዚህ ክሩን ማዉጣት እንደማይችሉ ነገረችኝ፡፡ የምታሳየኝ ጥላቻ በሷ እጅ የህክምና አገልግሎት ከማግኘት ቢቀር የሚሻል መሆኑን የሚጠቁም በመሆኑ ብዙም ልከራከራት አልፈለኩም፡፡ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የተባሉ ሌሎች ሀላፊዎች ወደጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እንዲወስዱኝ ብጠይቅም “ቀጠሮ የለሽም” በሚል ሰበብ ሳይወስዱብኝ ቀሩ፡፡ በአሁኑ ወቅት የቀኝ ጡቴም ተመሳሳይ እጢ ያለበት በመሆኑ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ወደ ምኒሊክ ሆስፒታል ቀዶጥገና አደርግ ዘንድ የላከኝ ቢሆንም (ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በእድሳት ላይ በመሆኑ)እጅግ የከፋ ህመም ካልታመምኩ በቀር ቃሊቲ ሆኜ ቀዶጥገና ማድረጉን አልፈለኩም፡፡ በመሆኑም አልፎ አልፎ የሚሰማኝን ህመም በህመም ማስታገሻ መድሀኒቶች በማቃለል የቃሊቲን አስቀያሚ ቀኖች በመግፋት ላይ እገኛለሁ፡፡
ሌላዉ የቃሊቲ ቆይታዬን በተመለከተ ልጠቅሰዉ የምፈልገዉ ጉዳይ ከመንግስት አካላትና ከተለጣፊዎቻቸዉ ጋር ካለፍላጎቴ እንድንገናኝ እየተደረገ የሚፈፀምብኝ የሰብአዊ መብት ረገጣ ነዉ፡፡ ለምሳሌ ያህልአንዱን ብቻ ልጥቀስ፡፡ አምና መጋቢት ወር ዉስጥ አምባሳደር ጥሩነህ ዜናን ጨምሮ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መምጣታቸዉን የገለፁ ሌሎች አስር ሰዎች ከአመት በፊት ወደገባሁበትና ከሌሎች ከአራት ሰዎች ጋር ብቻ ወደምኖርበት ክፍል መጡ፡፡ እኔም ኮሚሽኑ በተለይም ደግሞ አምባሳደሩ የሰብአዊ መብት አከባበርን አስመልክቶ የሚሰጧቸዉ ከእዉነት የራቁ መግለጫዎች የሚያሳዝኑኝ በመሆኑ ለመነጋገር ፍቃደኛ አለመሆኔን በማስታወቅ ከክፍሉ ወጥቼ በሩ ላይ ቆምኩ፡፡ ከሰዎች አንዱ የምኖርበትን ክፍልና አልጋዎቻችንን ፎቶ ሲያነሳ ተመለከትኩ፡፡ ገረመኝ፤ መሬት አንጥፌ ስተኛ፣በተደራራቢ አልጋ የላኛዉ ክፍል ላይ ከጡት ህመም ጋር እየታገልኩ ስተኛና በተፋፈገ ክፍል ዉስጥ ስኖር ለምን የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ፎቶ አላነሳም? ማረሚያ ቤቱ በጥሩ ሁኔታ እስረኞቹን የያዘ መሆኑን ማሳያ ለማድረግ እንደተፈለገ ገመትኩ፡፡ እዉነታዉ ግን ይቺ ያለሁባት በቆርቆሮ የተሰራች ክፍልና ጠባቧ ግቢ አምና መስከረም ላይ በጠያቂዎች የመጎብኘት መብቴ መጣሱን ተከትሎ በጥድፊያ የተዘጋጀች ማግለያ ቦታ መሆኗ ነዉ፡፡ ክፍሉን ብቻ ፎቶ አንስተዉ መሄዳቸዉ ያላረካቸዉ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰዎች በማግስቱ አራት ሆነዉ መጡ፡፡ ሁለቱ ወደግቢዉ ዉስጥ ሲገቡ ሌሎቹ ሁለቱ ደግሞ በሩጋ ቆሙ፡፡ ግቢዉ ዉስጥ ከገቡት አንዱ ትላንት ለምን ላናግራቸዉ እንዳልፈለኩ ጠይቆኝ በድጋሚ ከነሱ ጋር መነጋገር ያልፈለኩበትን ምክንያት እያስረዳኋቸዉ እያለ የግቢዉ በር ክፍት ስለነበር ግቢዉ በርጋ ከቆሙት አንዱ ፎቶ ሊያነሳኝ ሲሞክር ለመመልከት ቻልኩ፡፡ ምስሌን አንስቶ ቢሆንና ስለኔ አንዳች አይነት ዉሽት ሲናገሩ ብሰማ ጉዳዩን በዝምታ እነደማላልፈዉ ነገርኩትና ወደቤት ዉስጥ ገብቼ በሩን ዘጋሁት፡፡ ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ከክፍሉ ወጥቼ ኢህአዴግ ማሰሩ ሳይበቃዉ ሰብአዊ መብትን ለማስከበር እንዳቋቋማቸዉ በሚናገረዉ ተለጣፊ ድርጅቶቹ ሳይቀር ሰብአዊ መብቴን ለምን እንደሚጥስ ከሀላፊዎቹ አንዷን በማስጠራት ጥያቄ አቀረብኩላት እሷም ሰዎቹ ካሜራ መያዛቸዉን እንደማታዉቅ ነገረችኝ፡፡ በ2005ዓ.ም ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች የህዝብ ግኑኝነት ክፍል እኔን ለማናገር እንደመጣ የገለፀልኝ ሰዉ ኮቱ ዉስጥ ደብቆ በያዘዉ ሪከርደር ድምፄን ለመቅረፅ ሲሞክር ደርሼበት ይህንን ማድረግ የሚችለዉ የግል ፕሬስም ተገኝቶ ንግግራችንን የሚቀርፅ ከሆነ ብቻ መሆኑን ነግሬዉ ነበር፡፡ ይሄንን ያልኩበት ምክንያት የግል ፕሬሱ ባልተገኘበት ለመንግስት ሚዲያዎች ብቻ አስተያየታቸዉን የሰጡ ግለሰቦች ሀሳባቸዉ ተቆርጦና ተቀጥሎ ለማለት ያልፈለጉት ይዘት ይዞ እንደሚቀርብ አዉቅ ስለነበር ነዉ፡፡ የተናገርኩትን ሙሉዉን ነገር ቀርፀዉ ሊያወጡልኝ የሚችሉ አካላት በሌሉበት ለሰዉዬዉ አስተያየቴን መስጠት ያለፈለኩትም ይኸዉ እንዳይደርስብኝ በመስጋት ነበር፡፡ አስገራሚዉ ነገር ይቺ የኮሚሽኑ ሰዎች ካሜራ መያዛቸዉን እንደማይታወቅ የገለፀችልኝ ሀላፊ ያኔም የሰዉየዉን የድምፅ ሪከርደር መያዝ በተመለከተ ላቀረብኩላት ጥያቄ የሰጠችኝ ተመሳሳይ መልስ ነበር፡፡
የቃሊቲ ጉድ ማብቂያ ስለሌለዉ አንድ የመጨረሻ ጉዳይ ላንሳና የፅሁፌ መነሻ ወደሆነዉ የአመክሮ ጉዳይ አልፋለሁ፡፡ ዉድ አንባቢያን በሀገሪቱ ዉስጥ ያሉ የትኞቹንም እስረኞች አያያዝ የተመለከቱ ህጎችን፣ አዋጆችን፣ ደንቦችንም ሆኑ መመሪያዎችን በጣሰ ሁኔታ ከወላጆቼ በቀር ጠበቃን ጨምሮ በሌላ በማንም ሰዉ የመጎብኘት መብቴን ከተነጠቅኩ አመት ከኣራት ወራት አልፎኛል፡፡ አዛዉንት እናትና አባቴም ከእርጅና፣ ህመምና ድካም ጋር እየታገሉ የቃሊቲን ፈታኝ መንገድ መዉጣትና መዉረዳቸዉን ቀጥለዋል፡፡
ነገረ አመክሮ
ያለፈዉ አመት ነሐሴ ስምንት ቀን ከሰአት በኋላ ወደ ጠበቃ ክፍል ሃላፊዋ ቢሮ በአንዲት ፖሊስ ተጠርቼ ተወሰድኩ፡፡ እዚያም ከፌደራል ማረሚያ ቤቶች ዋናዉ መስሪያ ቤት የይቅርታና የአመክሮ ጉዳይ ክፍል እንደመጣና ኮማንደር አስቻላዉ እንደሚባል ከነገረኝ ሰዉ ጋር ተገናኘሁ፡፡ ኮማንደሩ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ያቀረበልኝ የመጀመሪያዉ ጥቃቄ “ይቅርታ ለምን አልጠየቅሽም? ይቅርታ በመጠየቅ ላይ ያለሽ ሀሳብስ አልተቀየረም ወይ?” የሚል ነበር፡፡ ይቅርታ ያልጠየኩት ስላላጠፋሁና የተፀፀትኩበት ጉዳይ ስለሌለ በመሆኑና አሁንም ምንም የተቀየረ አቋም እንደሌለኝ አስረዳሁተ፡፡ “ይሄ የፍርድቤት ጉዳይ ነዉ፡፡ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ እስካለሽ ድረስ ወደዚያ መመለስ አይኖርብንም” አለኝ፡፡ እኔም አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት እንዳሻዉ የሚያሽከረክረዉ ፍርድቤት በንፁሃን ላይ የጥፋተኝነት ዉሳኔና ፍርድ ማስተላለፉን አሜን ብዬ ይቅርታ የምጠይቅበት ምንም አይነት ምክንያት እንደሌለ ገለፅኩለት፡፡ ጥቂት ደቂቃዎች ያህል ስለጤንነቴና በጊቢዉ ዉስጥ ስለሚያጋጥሙኝ ችግሮች በተመለከተ ጥያዎችን ስያቀርብልኝ ቆየና ወደ መጣበት ሌላዉ ዋና ጉዳይ ተመለሰ፡፡
“ቅድም ይቅርታ የማልጠይቀዉ ስላልተፀፀትኩ ነዉ ብለሻል፡፡ አመክሮ እኮ የሚሰጠዉ ለተፀፀተ ሰዉ ነዉና እንዴት ልታደርጊ ነዉ?” በማለት ስለ በአመክሮ የመፈታት አካሄድ አንዳንድ የሚኒስተሮች ምክር ቤት ደንቦችን ጭምር በመጥቀስ ሊያብራራልኝ ሞከረ፡፡ “ታዲያ እንዲህ ከሆነ በይቅርታና በአመክሮ መሀል ምንም አይነት መሰረታዊ ልዩነት የለም ማለት ነዋ?” ለሚለዉ ጥያቄ ቀጥታ መልስ ሊሰጠኝ አልፈለገም ይልቁኑ ሁሉም ታራሚ 2/3ኛዉን የእስር ቅጣቱን ለመፈፀም ሁለት ወራት ገደማ ሲቀሩት እንደታረመና እንደተፀፀተ የሚገልፅ ፎርም መሙላት ስለሚኖርበት እኔም ለመፈታት ከፈለኩ ይህንኑ ማድረግ እንደሚጠበቅብኝ አስረግጦ ነገረኝ፡፡ የፃፍኩት የማምንበትንና መቼም ልቆምለት የምችለዉ እዉነት መሆኑን፣ በዚህ የተነሳ አሸባሪ መባሌ ደግሞ የበለጠ ኢህአዴግን እንድታገለዉ የሚየደርገኝ እንጂ የሚያፀፅተኝ ባለመሆኑ እንዲህ አይነቱን ከማንነቴ ጋር የሚቃረን ፎርም እንደማልሞላ አስረግጬ ነገርኩት፡፡ ኮማንደሩም ላልታረመና ለልተፀፀተ ሰዉ አመክሮ መስጠት ለእነሱም እንደሚከብዳቸዉ ከገለጸልኝ በኋላ “እኛ ፎርሙን ብንሞላልሽስ?” የሚል አስገራሚ ጥያቄ አቀረበልኝ፡፡ እኔ “ታርሜያለሁ” እንዳልኩ ተደርጎ ምንም አይነት ነገር ቢደረግ ሀሰት መሆኑን ከማጋለጥ ወደኋላ እንደማልል አስታወቅኩት፡፡ በዚህ አይነት ተመሳሳይ ሀሳቦች ላይ እየተሸከረከርን ጥቂት ጊዜ ከፈጀን በኋላ እንዳሰብበት አሳስቦኝ ተለያየን፡፡
ይህ ከሆነ ሀሁለት ወራት በኋላ የመፈቻዬ ቀን የነበረዉ ጥቅምት 14/2007 ማለፊን ተከትሎ “የአመክሮ ፎርሙን ለምን አትሞይም?” የሚል ጥያቄ ከተለያዩ ሀላፊዎች ይቀርብልኝ ጀመረ፡፡ ከህዳǑ
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ ደህንነቱ አደጋ ላይ መሆኑ ተገለፀ
በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶበት የሶስት ዓመት እስር የተበየነበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ደህንነቱ አደጋ ላይ መሆኑ የቅርብ ቤተሰቦቹ ገለፁ፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን፣ በዝዋይ ወህኒ ቤት ኮማንደር ቢኒያም ተብሎ በሚጠራው የወህኒ ቤቱ አስተዳዳሪ ጠዋትና ማታ ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰበት እንደሚገኝና በተጨማሪነትም በቀን ለአምስት ጊዜ ያህል ሌሊትን ጨምሮ በሰበብ አስባቡ ከክፍሉ እየተጠራ እንደሚወሰድ የቅርብ ቤተሰቦቹ አስታውቀዋል፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን፣ […]
ተዋሕዶ በተዐቅቦ
የአሸባሪዎች ጥቃት በፓሪስ
ፈረንሣይ መዲና ፓሪስ ውስጥ «ቻርሊ ኤብቶ» በተሰኘው፥ ምፀታዊ ምስሎችን በሚያወጣ ሣምንታዊ መፅሔት ዋና ጽ/ቤት ላይ በተጣለ ጥቃት 12 ሰዎች ተገደሉ። ፈረንሳይ ዛሬ የሃዘን ቀን አዉጃለች። በርካታ ተጠርጣሪዎችም እየተያዙ ነዉ።
ሻእቢያ ያገታቸውን ታጋዮቻችንን ለፕሮፓጋንዳ ሊጠቀምባቸው እያስገደዳቸው ነው ሲሉ የአማራ ንቅናቄ (አዲሃን)ምንጮች ገለጹ::
ሻእቢያ ያገታቸውን ታጋዮቻችንን ለፕሮፓጋንዳ ሊጠቀምባቸው እያስገደዳቸው ነው ሲሉ የአማራ ንቅናቄ (አዲሃን)ምንጮች ገለጹ::
Minilik Salsawi : የኤርትራ መንግስት በህገወጥ መንገድ ያገታቸውን እና የሰወራቸውን ታጋዮቻችንን በአስቸኳይ እንዲለቅ እንጠይቃለን በማለት በተደጋጋሚ መግለጫ ያወጣው የአማራ ንቅናቄ አይን ያወጣው ሻእቢያ ያገታቸውን አባሎቼን ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታው በማስገደድ ሊጠቀምባቸው ነው ማለቱን የንቅናቄው የውስጥ ምንጮች ከሰሜን ጎንደር ገልጸዋል::
ሕዝቦች ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብታቸው እየተገደበ ነው የሚሉት የንቅናቄው ምንጮች ከ70 በላይ የሚሆኑ የድርጅታችን አመራሮች እና ታጋዮቻችን በኤርትራ ወህኒ ቤቶች እየተሰቃኡ ከመሆኑም በላይ እንዲሁም በሺዎች የሚቆተሩ ኢትዮጵያውያን በእስር የማቀቁ ባሉበት ሁኔታ ሻእቢያ የነጻነት አባት በመምሰል በኢትዮጵያውያን ስም የሚሰጠውን ፕሮፓጋንዳ ምንም ተቀባይነት የሌለው ነው ሲሉ ንቅናቄውን ዋቢ በማድረግ ጠቁመዋል::
– የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ በተደጋጋሚ የሰጣቸውን መግለጫዎች ዚህ ሊንክ ላይ ያግኙታል::
– በድምጽ እዚህ ላይ ይጫኑት :
አስመራ የታገቱት የአማራ ንቅናቄ አባላት በሻእቢያ ከባድ እንግልት እየደረሰባቸው ነው::የሚለው ንቅናቄው በዚህ ዙሪያ መግለጫ ያወጣል ተብሎ የተጠበቀ ነው::

እዉነቱ እዚህ ምርጫ ቦርዱ የሚለፍፈው እዚያ ፣ እዉነቱን ይረዱ (መደመጥ ያለበት)
እዉነቱ እዚህ ምርጫ ቦርዱ የሚለፍፈው እዚያ ፣ እዉነቱን ይረዱ
=====================================
የምርጫ ቦርድ ምክትል ሃላፊ አቶ አዲሱ ገብረግዚአብሄር በፋና ራዲዮ እንዲሁም ሃላፊው ፕሮፌሰር መርጋ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፣ መኢአድ እና አንድነት ችግር እንዳለባቸው በመገልጽ በስድስት ቀናት ዉስጥ ፓርቲዎቹ “ችግሮቻቸውን” ካልፈቱ ሕጋዊ እርምጃ ይወሰደባቸዋል ሲል አስጠንቅቀዋል። ምርጫ ቦርድ የገዢው ፓርቲ አገልጋይ እንደሆነ ይነገርለታል።
የምርጫ ቦርድ ሃላፊዎች በሕጉ መሰረት የሚንቀሳቀሱ ሳይሆን የፖለቲካ ዉሳኔ የሚያስፈጸሙ እንደሆኑ በሚያደርጓቸው ኢሕገ መንግስታዊ እንቅስቃሴዎች እያሳዩ እንደሆነ የሚገልጹት የመኢአድ እና የአንድነት አመራር አባላት የተደቀነባቸውን እንቅፋት ከህዝብ ጋር ሆነው እንደሻገሩትን በሙሉ መተማመን እየገለጹ ናቸው።
የመኢአድ እና የአንድነት አመራሮች በአባላት ደረጃ እንደተዋሃዱ፣ አብረዉ እየተሳሩ፣ እየደሙ እንዳለ የገለጹት አመራር አባላቱ መኢአድ እና አንድነት አብረው እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። መኢአድ በ354 ወረዳዎች አንድነት ደግሞ ከ450 ወረዳዎች በላይ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ የገለጹት አመራሮቹ፣ አገዛዙ በምርጫ ቦርድ በኩል በድርጅቶቹ ላይ እየፈጸመ ያለው ነገር ፣ ድርጅቶቹ በሕዝብ ተቀባይነት እንዳላቸው በመረዳቱ ነው ሲሉ፣ ከህዝብ ጋር ሆነው የሚመጣውን ነገር ሁሉ ለመቋቋም ዝግጁ እንደሆኑ አረጋግጠዋል።
የመኢአድ ሊቀመንበር አቶ ማሙሸት አማረ ከኢሳት ጋር ያደረጉትን ያዳምጡ
https://www.youtube.com/watch?v=M0OfiIh … e=youtu.be
አንድነት መሰናክሉን ያልፋል – አቶ አለነ ለምርጫ ቦርድ መልስ ሲሰጡ ( መደመጥ ያለበት)
ምርጫ ቦርድ እያደረገ ባለው ኢ-ሕገመንግስታዊ ተግባራት ዙሪያ የአንድነት አመራር አባል የሆኑት አቶ አለነ ማጸንቱ ለኢሳት ማብራሪይ ሰጥተዋል።
አቶ አለነ፣ በጎጃም ክፍለ ሀገር አገው ምድር አውራጃ ሲሆን የተወለደው፣ የ28 አመት ወጣት ነው። በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1999 በሶሻል ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ በ2004 ደግሞ ሁለተኛውን ድግሬ ተቀብሏል።
በተለያዩ የግል ኮሌጆች ዲን እና አስተማሪ በመሆን እንዲሁም በግል ትምህርት ቤቶች ርዕሠ- መምህር በመሆን አገልግሏል። አሁን ደግሞ በሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒሥቴር የጥናትና ምርምር ቡድን አስተባባሪ በመሆን የተለያዩ መመሪያዎች፣ ፕሮግራሞች እና መርሀ ግብሮችን በማዘጋጀት ለተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች የአሠልጣኞች ሥልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።
በ1997 የመኢአድ(ቅንጅት) በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የወጣቶች አደራጅ፤ ከ2001 እስከ 2002 በአዊ ዞን የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ እና የህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ፣ ከ2003 እስከ 2005 በአንድነት ፓርቲ በጥናትና ምርምር ቋሚ ኮሚቴ የማህበራዊ ጉዳይ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ ከ2006 ወዲህ ደግሞ በአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ስራ አስፈጻሚ አባል እና የማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛል።
አቶ አለነ ከኢሳት ጋር ያደረገዉን ቃለ ምልልስ ያዳምጡ።
https://www.youtube.com/watch?v=x5DzqIK … e=youtu.be
አንድነት መሰናክሉን ያልፋል – አቶ አለነ ለምርጫ ቦርድ መልስ ሲሰጡ ( መደመጥ ያለበት)
ምርጫ ቦርድ እያደረገ ባለው ኢ-ሕገመንግስታዊ ተግባራት ዙሪያ የአንድነት አመራር አባል የሆኑት አቶ አለነ ማጸንቱ ለኢሳት ማብራሪይ ሰጥተዋል። አቶ አለነ፣ በጎጃም ክፍለ ሀገር አገው ምድር አውራጃ ሲሆን የተወለደው፣ የ28 አመት ወጣት ነው። በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1999 በሶሻል ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ በ2004 ደግሞ ሁለተኛውን ድግሬ ተቀብሏል። በተለያዩ የግል ኮሌጆች ዲን እና አስተማሪ በመሆን እንዲሁም በግል […]
እዉነቱ እዚህ ምርጫ ቦርዱ የሚለፍፈው እዚያ ፣ እዉነቱን ይረዱ ( መደመጥ ያለበት)
የምርጫ ቦርድ ምክትል ሃላፊ አቶ አዲሱ ገብረግዚአብሄር በፋና ራዲዮ እንዲሁም ሃላፊው ፕሮፌሰር መርጋ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፣ መኢአድ እና አንድነት ችግር እንዳለባቸው በመገልጽ በስድስት ቀናት ዉስጥ ፓርቲዎቹ “ችግሮቻቸውን” ካልፈቱ ሕጋዊ እርምጃ ይወሰደባቸዋል ሲል አስጠንቅቀዋል። ምርጫ ቦርድ የገዢው ፓርቲ አገልጋይ እንደሆነ ይነገርለታል። የምርጫ ቦርድ ሃላፊዎች በሕጉ መሰረት የሚንቀሳቀሱ ሳይሆን የፖለቲካ ዉሳኔ የሚያስፈጸሙ እንደሆኑ በሚያደርጓቸው ኢሕገ መንግስታዊ እንቅስቃሴዎች […]
የኢሳት ጋዜጠኞች መሳይ መኮንን እና ፋሲል የኔዓለም አስመራ ገቡ፤
ኢሳት በሰበር ዜና እንዳቀረበው ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ከዋሽንግተን ዲሲ እንዲሁም ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ከሆላንድ ኤርትራ ገቡ። ከኢሳት እንደተገኘው መረጃ ከሆነ ጋዜጠኞቹ አስመራ የገቡት ትናንት ሲሆን በኤርትራ ቆይታቸውም እዚያ ያለውን ሃይል እንደሚጎበኙና ዘገባም እንደሚያቀርቡ በተጨማሪም የኤርትራ ባለስልጣናትን እንደሚያነጋግሩ ይጠቁማል። የቀድሞው የጀርመን ድምጽ ጋዜጠኛና የአሁኑ የኢሳት ራድዮ ከፍተኛ አዘጋጅ መሳይ መኮንን፣ እንዲሁም የቀድሞው የአዲስ ዜና ጋዜጣ ዋና […]
እንኳን አደረሣችሁ ከአሜሪካ ድምፅ
በገና ምሽት በአሜሪካ ድምፅ የተላለፈውን ሙሉ ቅንብር ለማድመጥ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ይክፈቱ
የገና ምሽት መልዕክቶች በአሜሪካ ድምፅ – ረቡዕ፤ ታኅሣስ 29/2007 ዓ.ም – ጃንዩወሪ 08, 2015
Messages – Ethiopian X-Mas on VOA – Amharic
የቤተ ክርስቲያኒቱ የገቢ ማስገኛ ተቋማት ኪራይ የግለሰቦች መጠቀሚያ መኾናቸው ተጠቆመ
መሬት በካሬ በሺሕዎች ዋጋ እያወጣ የቤተ ክርስቲያን በ1.50/2.00 ተከራይቷል ሀብትና ጥቅሟን የሚያስጠብቅ የኪራይ ተመን ፖሊሲ ጥናት ተጀምሯል የጥቂት አድባራት ሓላፊዎች እንቅስቃሴ ጥናቱን እንዳያኮላሸው ተሰግቷል የአለቆች የመኪና ሽልማት የአማሳኞች ከለላና ለብልሹነት በር የሚከፍት ነው * * * የኪራይ ውሎችንና ሌሎች ሰነዶችን በመደበቅ በአግባቡ ያለማቅረብ፣ የጥናቱን ዓላማ በማጣመም ተቃውሞ ለማነሣሣት መሞከር፣ የልኡካንን ስም ማጥፋትና ሥራውን ማጥላላት ከቀንደኛ …![]()
ኢሕአፓ ወያኔ በቅርቡ በጎንደር ክፍለሀገር በሕዝብ ላይ ያደረገውን ጭፍጨፋ ያወግዛል!!!
ባለፈው ሳምንት የወያኔ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከባድ መሳሪያዎች በመታጀብ ጎንደር
አርማጭሆ ውስጥ ሶረቃ በሚባለው አካባቢው አርሶ አደሮችን በኃይልና በማን አለብኝነት
አስነስተው ቦታውን ወደ ትግራይ ክልል ለማጠቃለል ያደረጉት ጥረት ሕዝቡ ከዳር እስከዳር
በመንቀሳቀስና ውጊያ በመግጠም ያከሸፈው መሆኑ ታውቋል። በተደረገው ግጭትም ከሁለቱም
በኩል ጉዳት የደረሰ መሆኑ ከሥፍራው የሚገኙ ዜናዎች ያስረዳሉ። ሁኔታው እስካሁን ያልበረደ
ሲሆን ሕዝቡም ከዳር እስከ ዳር ተጠራርቶ መብቱን ለማስከበርና ንብረቱን ለማስጠበቅ
ባንድነት ለመታገል ወስኗል።
የወያኔ አገዛዝ ሥልጣን ላይ ለመቆየት አገሪቱን በጎሳና በቋንቋ እንዲሁም በሃይማኖት በመከፋፈል
በሕዝብና በሀገር ላይ ከፍተኛ በደል ከመፈጸሙ በተጨማሪ ለዓመታት በጎንደርና በወሎ
ክፍለሀገራት የነበሩትን ሰፊ አካባቢዎች ያለ ሕዝቡ ፈቃድና ስምምነት ቀምቶ በትእቢትና
በማናለብኝነት በትግራይ ክልል ውስጥ እንዲጠቃለሉ ያደረገ መሆኑ ይታወሳል። የወያኔ እኩይ
ተግባር ሕዝቡን ከፍተኛ ብሶት ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል። ይህ አልበቃ ብሏቸው የወያኔ ሆዳም
ባለሥልጣኖች ደኻውን ገበሬ ከእርሻ ቦታው ላይ አፈናቅለው መሬቱን ለመቀራመት የወሰዱት
እርምጃ በጽኑ የሚወገዝ ነው።
ጸረ ኢትዮጵያ የሆነው የወያኔ ቡድን በሥልጣን ኮርቻ ላይ ከተቆናጠጠ ጀምሮ የኢትዮጵያን
አንጡራ ሀብት ዘርፎና ለቡድኑ መጠቀሚያ አድርጎ በወሰን አካባቢ ያሉ ለም መሬቶችን
ተቃዋሚዎችን ለሚቆጣጠርለትና መስል አጽፋዊ ስጦታ ለሚያደርግለት ለሱዳን አስረክቦ፤ ሰፋፊ
ለም የእርሻ ቦታዎችን ለውጭ አገር ከበርቴዎች በሊዝ ሸጦ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ትውልድ ይቅር
የማይለው ከፍተኛ በደል ፈጽሟል።
ይህን ግፍና በደል ለማስቀረትና የሕዝቡን መብትና ጥቅም ለማስከበር ከቡድኑ ጥቅም በላይ
ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደንታ የሌለውን ዘረኛና አምባገነን ቡድን በሕዝባዊ ኃይል
ከማውረድ በስተቀር ሌላ አማራጭ የሌለ በመሆኑ ዛሬም ትግላችንን በሕብረት አጠናክረን ወደፊት
እንግፋ የሚለው ጥሪ ወቅታዊ ሆኖ የሚገኝ ነው።
ሕዝባዊ ትግሉን በኀብረት እናጠናክር !!
ፀረ ኢትዮጵያ የሆነው የወያኔ አገዛዝ ይወገዳል !!
የኤርትራው የተቃዋሚ ሃይሎች የውህደት ጉባዬ ተጀምሯል:: ኢሳቶች ተጉዘዋል::
MinilikSalsawi : በኤርትራ የሚንቀሳቀሱት የአርበኞች ግንባር እና የግንቦት ሰባት ውህደት የመጀመሪያው ዙር ጉባዬ በዛሬው እለት መጀመሩን የአስመራ ምንጮች ተናግረዋል:: ጉባዬውን በተመለከተ አስፈላጊውን መረጃዎች ዝርዝር እንደደረሰኝ አቀርባለሁ::
ኢሳት ሁለት ጋዜጠኞች ያለውን ሁኔታ እንዲዘግቡ ወደ ኤርትራ የላከ ሲሆን በዚህም መሰረት መሳይ መኮንን እና ፋሲል የኔአለም ወደ ኤርትራ ተጉዘዋል::በኤርትራ ቆይታቸው የውህደቱን ጉባኤ እና የተቃዋሚዎችን እንቅስቃሴ የሚቃኙ ሲሆን የሻእቢያን ባለስልጣናት ያናግራሉ ተብሎ ይጠበቃል::
ለማስታወስ ያህል::
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ጃንዩወሪ 07, 2015
የፕሮግራም መግለጫ
ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡
የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡
ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና
ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና
ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ
ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት
ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)
ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና
ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡
ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡
የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡
ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡
የገና በዓል አከባበር
የገና በዓል ልዩ ዝግጅት በተመለከተ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ የአውሮጳ ሃገራት የሚገኙ ወኪሎቻችን የላኩት ዘገባ በተለይ በአውሮጳ የሚገኙ ስደተኞች በዓሉን እንዴት እንዳከበሩት ያስቃኛል። ዘገባዎቹ ከኢትዮፕያ፣ ከፈረንሣይ፣ ከጀርመን እና ከጣሊያን የተላኩ ናቸው።
ኢትዮጵያዊያን አንዳርጋቸውን ሲያዩ የሚታያቸው ጽናት፣ አርበኝነትና አልበገር ባይነት ነው። >> ነው ሲል ግንቦት 7 ለፍትህ፣ ለዲሞክራሲና ለነፃነት ንቅናቄ ገለጸ።
ታኀሳስ ፳፱(ሃያ ዘጠኖ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግንቦት 7 <<ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌን እንሁን!!!>> በሚል ርእስ ዛሬ ታህሳስ 29 ቀን ባስነበበው ርእሰ-አንቀጽ፤በህወሓት ሙሉ ቁጥጥር ስር የሚገኘው የፌደራል ፖሊስ እሁድ እለት በቴሌቪዥን ፕሮግራሙ በግፍ እስር ላይ የሚገኘውን የግንቦት 7 ዋና ፀሐፊን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለ 10 ደቂቃ አቅርቦት እንደነበር በማውሳት፤ይህ የ10 ደቂቃዎች ምስል ለቁጥር በሚያታክት ሁኔታ …
በምርጫ ቦርድ እና በአንድነት ፓርቲ መካከል የተፈጠረው ውጥረት እየተካረረ ነው። የአንድነት አመራሮች ለአባሎቻቸው ጥሪ እያቀረቡ ነው።
ታኀሳስ ፳፱(ሃያ ዘጠኖ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የውጥረቱ መካረር ምክንያት የምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር አዲሱ ገብረ እግዚአብሔር ከቦርዱ ውሳኔ ቀድመው ወደ ድርጅት ሚዲያ በመሄድ ” አንድነትና መኢአድ የውስጥ ችግራቸውን ካልፈቱ በምርጫ ላይሳተፉ ይችላሉ” የሚል መግለጫ መስጠታቸው ነው። ዶክተር አዲሱ፤ ሁለቱ ፓርቲዎች በህገ- ደንባቸው መሰረት ውስጣዊ ችግራቸውን እንዲፈቱ በቦርዱ ቢነገራቸውም ችግራቸውን አለመፍታታቸውን በመጥቀስ፤ አሁን …
ከትናን በስቲያ ሰኞ ታህሳስ 27 ቀን 2007 ዓመተ ምህረት በአዲስ አበባ ወሎ ሰፈር የሚገኙ የውስጥ መንገዶች በግድግዳ ላይ ጽሁፎችና መፈክር በተጻፈባቸው ወረቀቶች አሸብርቀው ማደራቸውን ፍትህ ራዲዮ ዘገበ።
ታኀሳስ ፳፱(ሃያ ዘጠኖ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ራዲዮው ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የውሎ ሰፈር የውስጥ መንገዶች ግድግዳ ላይ የተጻፉት መፈክሮች-ህዝበ-ሙስሊሙ መብቱን ለማስከበር ያነሳቸውን ያቄዎች የሚያሰተጋቡና መብታቸውን በመጠየቃቸው የታሰሩት የሙስሊም መሪዎች እንዲፈቱ የሚጠይቁ ናቸው። ከተለጠፉት መፈክሮች መካከል፦”አዐባሪዎች አይደለንም፣ የታሰሩት ሙስሊሞች ይፈቱ!ኮሚቴው ይፈታ!የሂጃብ ገፈፋው ይቁም! ትግሉ ይቀጥላል! እና ፍትህ ናፈቀን!”የሚሉት ይገኙበታል። በግድግዳ ላይ ከተጻፉትና ከተለጠፉት ባሻገር ሙስሊሞች …
ብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስ ሁለተኛው ኢትዮጵያዊ ካርዲናል ሆኑ
ታኀሳስ ፳፱(ሃያ ዘጠኖ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳትና የኢትዮጵያ ጳጳሳት ጉባዔ ፕሬዚዳንት ብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስ ሱራፌል የካርዲናልነት ማዕረግ አገኙ፡፡ ብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስን ጨምሮ ለ15 ሊቃነ ጳጳሳት የካርዲናልነት ማዕረግና ለአምስት ሊቀ ጳጳሳትና ጳጳሳት ደግሞ ድምፅ አልባ የካርዲናልነት ሹመት ባለፈው እሑድ ረፋድ ላይ በቫቲካን በመስጠት ይፋ ያደረጉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ …
ዶ/ር መረራ ጡረታ እንዲወጡ እንደተጠየቁና ጥያቄውን እንዳልተቀበሉት ተናገሩ
ላለፉት 28 ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ያገለገሉት ዶ/ር መረራ ጉዲና ከኮንትራት ቅጥር አፈፃፀም ጋር በተያያዘ ከዩኒቨርሲቲው ጋር አለመስማማታቸው ታወቀ። ዶ/ር መረራ ስለጉዳዩ ከሰንደቅ ጋዜጣ ተጠይቀው ካለፈው ሐምሌ ወር 2006 ዓ.ም ጀምሮ ጡረታ እንዲወጡ እንደተጠየቁና ጥያቄውን እንዳልተቀበሉት ተናግረዋል። ለዚህም የሰጡት ምክንያት አንድ ለጡረታ የደረሰ ሰው ሦስት ዓመት እንዲራዘምለት መጠየቅ የሚችልበት የሕግ አግባብ ስላለ ነው ብለዋል። ከሐምሌ 2006 ዓ.ም ጀምሮ የዩኒቨርሲቲው የሶሻል ሳይንስ ኮሌጅ በኮንትራት እንዲሰሩ የቀጠራቸው መሆኑን አስታውሰው ሆኖም የዩኒቨርሲቲ ፐርሶኔል ክፍል ቅጥሩን አልቀበልም በማለቱ እስካሁን ጉዳዩ በእንጥልጥል ላይ መሆኑን ገልፀዋል። በዩኒቨርሲቲው የሴኔት ሕግ መሠረት ኮሌጆቹ የሚፈልጉትን መምህር የመቅጠር መብት እንዳላቸው በማስታወስ የፐርሶኔል ክፍሉ በማያገባው ገብቶ ቅጥሩን ከልክሏል ብለዋል። ከዚሁ አለመግባባት ጋርም ተያይዞ ላለፉት ስድስት ወራት ደመወዛቸው መቋረጡን ጠቅሰው፤ ከዩኒቨርሲቲው ጋር ያላቸውን ሁኔታ ተከታትለው መፍትሄ ከጠፋ መብታቸውን በሕግ ለማስከበር ማሰባቸውን ጨምረው ገልፀዋል። በጉዳዩ ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም። ዶ/ር መረራ ጉዲና ከዩኒቨርሲቲው መባረራቸውን ሰሞኑን በአንዳንድ ማኅበራዊ ድረገጾች መዘገቡም አይዘነጋም። ******* ምንጭ፡- ሰንደቅ፣ ታህሳስ 22-2007 More from Horn Affairs Amharicዶ/ር መረራ ጉዲና – ለ6 ወር ደሞዝ አልተከፈለኝም፣ ፕሮፌሰርነት እስካሁን ድረስ አልተሠጠኝምሰንደቅ ጋዜጣ:- ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ በሠነዘሩት አሉባልታ ሊከሰሱ ነውዶ/ር መረራ ጉዲና፡- ኢሳት ጠመንጃ የለውም፣ የትጥቅ ትግልም እያካሄደ አይደለምኢትዮ-ቴሌኮም በ75 የአዲስ አበባ አካባቢዎች የኔትወርክ ችግር ፈታሁ አለዓለማየሁ አቶምሳ – ኪራይ ሰብሳቢነትን አምርሮ የታገለና ያታገለየኢዴፓ መግለጫ – “በሽብርተኝነት ስም […]
ዶ/ር መረራ ጉዲና – ለ6 ወር ደሞዝ አልተከፈለኝም፣ ፕሮፌሰርነት እስካሁን ድረስ አልተሠጠኝም
(አለማየሁ አንበሴ) ባለፈው ሳምንት በማህበራዊ ድረ-ገጽ በተሰራጨ መረጃ፣የፖለቲካል ሣይንስ መምህርና የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና፤ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጡረታ እንደተባረሩ ቢነገርም መረጃው እውነት አለመሆኑን ከአንደበታቸው ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ሆኖም ከዩኒቨርሲቲው ጋር የተፈጠረ ችግር እንዳለ ይናገራሉ – ዶ/ር መረራ፡፡ ችግሩ ምን ይሆን? ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ፤ይሄንንና ሌሎች ከመምህርነት ሙያቸው ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ጠይቋቸው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ አዲስ አድማስ:- ከዩኒቨርሲቲው ጋር የተፈጠረው ችግር መነሻው ምንድን ነው? ዶ/ር መረራ ጉዲና:- ሁሉንም ሲያልቅ መናገር ይሻላል፡፡ ነገር ግን ለ6 ወር ያስተማርኩበት ደሞዝ አልተከፈለኝም፤ መነሻው ይሄ ነው፡፡ ፓርላማ በቆየሁባቸው ጊዜያትም ደሞዝ አይከፈለኝም ነበር፤ የዩኒቨርስቲው ይበቃሃል ተብዬ፡፡ እዚህም እንግዲህ ለ6 ወር በነፃ እያገለገልኩ ነበር ማለት ነው፡፡ አዲስ አድማስ:- ምክንያቱ ተነግርዎታል ? እርስዎስ አልጠየቁም ? ዶ/ር መረራ ጉዲና:- የቅርብ አለቆች እየተነጋገሩበት ነው የሚል ምላሽ ነው የተሰጠኝ፡፡ ግን ማስተማሬን አላቆምኩም፤ በነፃ እያገለገልኩ ነው ማለት ነው፡፡ ምናልባት መፍትሄ ካልተገኘ መብቴን ለማስከበር ወደ ፍ/ቤት ላመራ እችላለሁ፡፡ አዲስ አድማስ:- በዩኒቨርሲቲው ምን ያህል ጊዜ አስተማሩ? ዶ/ር መረራ ጉዲና:- እሱ የአደባባይ ሚስጥር ነው፤ ለ28 አመት ፖለቲካል ሣይንስ አስተምሬያለሁ፡፡ አዲስ አድማስ:- በዩኒቨርስቲው በሃላፊነት የመስራት እድል አጋጥሞት ያውቃል? ዶ/ር መረራ ጉዲና:- አዎ! በሦስት የተለያዩ ጊዜያት የፖለቲካል ሣይንስ ትምህርት ክፍል ተጠሪ ነበርኩ፡፡ ለምን ያህል ጊዜ እንደሆነ በትክክል ባላስታውስም ለመጨረሻ ጊዜ በኃላፊነት የሠራሁት ከሦስት ዓመት በፊት ነው፡፡ ኢህአዴግ ከገባ በኋላ ሦስት ጊዜ ሃላፊ ሆኜ ሰርቻለሁ፡፡ አዲስ አድማስ:- የተቃዋሚ ፓርቲ […]
ሪክ ለመስራት እንዘጋጅ – አቶ ተክሌ በቀለ የአንድነት ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበር
አንድነት ፓርቲ የኢህኣዴግን ምንነት ላላመኑ ወገኖች ለማጋለጥ በትጋትና በስሌት ሲሰራ ቆይቷል፡፡እየሰራም ነዉ፤እዚህ ደርሷል፡፡ “የሆደ ሰፊዉን ምርጫ ቦርድ” ሆድ በገሃድ አጋልጧል፡፡በነአሞራዉና ወዲ ቐሺ(በተጋሩ ሁሉ) ትግልና ሞት የሚቀልዱትን በህዝብ ፊት ወጥተዉ ዛሬም እንዲዋሹና ለኢትዮጵያችን የፖለቲካ ታሪክ እነማን ምን እንደሆኑ አንድነት ፓርቲ የበኩሉን ሚና ተጫዉቷል፡፡ ለኔ ከባድመ ዉሳኔና ልህዝቡ በወቅቱ ከተነገረዉ ጋር ይመሳሰላል፤ይጠጋጋል፡፡ኢህኣዴግ ምርጫዉን እንደማይፈልገዉ፤ከፈለገዉም ለተለመደዉ ቀልዱ ከነማን […]
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ባቀረበው ይግባኝ ላይ ክርክር አደረገ
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በጠበቃው በአቶ አምሐ መኮንን አማካይነት፣ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረበው ይግባኝ ላይ ክርክሩን አደረገ፡፡ ክርክሩን የተከታተለው የተወሰነበትን የሦስት ዓመታት የእስራት ቅጣት እየፈጸመ ባለበት በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ዝዋይ እስር ቤት ሆኖ በፕላዝማ ነው፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ቀርቦበት የነበረው ክስ፣ እሱ የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆኖ ሲሠራ […]
ጎበዝ ጠንከር ነው – ግርማ ሰይፉ የአንድነት ም/ሊቀመነበር
ምርጫ ቦርድ ማንም ይዘዘው ማንም ወይም በግል ተነሳሽነት እያደረገ ያለው ነገር የኢትዮጵያን የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ከምን ጊዜውም በለይ ወደኋላ ለመመለስ እንደሆነ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሊረዳው ይገባል፡፡ ምርጫ ቦርድ ምርጫ እንዲያሰተዳድር በተሰጠው ኃላፊነት የፓርቲዎች አስተዳደሪ ለመሆን እየቃጣው ያለ ተቋም ነው፡፡ ስናከብረው ለመከበር ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ለዚህ ተቋም መጠናክር የበኩላችንን መወጣት አለብን ብለን የተነሳን ፓርቲዎችን ጭምር እየገፉ አለቆቹን ለማስደሰት ደም ተግቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህን የሚያደርጉትን ሰዎች ደግሞ በህዝብ ፊት ለብይን እንዲቀርቡ በግልፅ ማጋለጥ ይኖርብናል፡፡
ትላንትና ዶ/ር አዲሱ በሚዲያ ቀርቦ የተናገረው በምንም መልኩ አንድነትን አይመጥንም፡፡ የተቀሩት የቦርድ አባላትም ይመጥነናል ካሉ ትዝብት ላይ ይወድቃሉ፡፡ የምርጫ ቦርድ አባላት ሳያገባቸው እንፈትፍት ሲሉ መፈተፍቱን ለእኛ ተዉልን ነው ያልናቸው፡፡ ዶ/ር አዲሱ በሚዲያ የቦረድ ውሳኔ ሊሆን ይችላል ብሎ ካቀረበ በኋላ ዛሬ ታህሳስ 28 2007 ቦርድ ተሰብስቦ ውሳኔ ሰጥቶዋል፡፡ ይህን ውሳኔ እንገራችሁ ብለው በስልክ ከጠሩን በኋላ የአንድነት ፓርቲ የወረዳ አባላት የሆኑትንም በተመሳሳይ መልክ ጠርተው ነበር፡፡ ለነገሩ ይህ አካሄድ አንድነትን ስለማይመጥን በፅሁፍ እንዲገልፁልን ነግረናቸው ተመልሰናል፡፡ ለማንኛውም ዶ/ር አዲሱ የሰጠው መግለጫ ይህ መግለጫ እንዲሰጥ የወሰኑትን ጨምሮ ለተቀሩት የቦርድ አባላት ያላቸውን ንቀት የሚያሳይ ነው፡፡ ቦርዱ ተሰብሰቦ ምንም ዓይነት ውሳኔ ከመወሰኑ በፊት ውሳኔውን ሚዛን የሚያሳጣ መግለጫ ለመስጠት ምን እንዳጣደፋቸው መገመት ቀላል ነው፡፡ በልባቸው የሚደግፉትን ፓርቲ ለማንገስ ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው፡፡
ልክ የዛሬ አምስት ዓመት አንድነት ላይ ተመሳሳይ ግብ ግብ ተፈጥሮ ነበር፡፡ የዚህ ተልዕኮ ፈፃሚዎች ዛሬ ላይ ሆነው ምን እንደተጠቀሙ ሲያሰላስሉ ምን እንደሚሰማቸው ባላውቅም ዛሬ በዚህ ተግባር ላይ የተሰለፉት አባላት ደግሞ ምን እንደሚያደርጉ መጠበቅ ነው፡፡ ለመማር ያልተፈጠረን ሁሉ ምንም ማድረግ ይቻላል? ማንም ተላላኪና ላኪ ሆኖ ቢያገለግልም ዛሬ የተሰማኝ ነገር አንድነት በምርጫ ለመሳተፍ ሲወስን እንደዚህ ዓይነት ተቋማት በምን ያህል ደረጃ ለመዋረድ ዝግጁ እንደሆኑ ለመረዳት የሚያስችል ነው፡፡ አሁንም ትግሉ መራራ፣ የሚያስከፍለው መስዋህትነትም ውድ ሊሆን እንኳን ቢችል የአንድነት አባላት በድል እንደሚወጡት ምንም ጥርጥር የለኝም፡፡ እሩቅ እንደሆነ አውቀን ለጀመርነው ትግል አቋራጭ እንደማንፈልግ መግለፅ ይኖርብናል፡፡
ውድ የአንድነት አባላት ለቀጣይ አንድነት ከምርጫ ቦርድ አሻጥር ለማላቀቅ ለምናደርገው ትግል ቀበቶ ጠበቅ ነው፡፡ ከሰማይ በታች አንድነት ለመፍታት የማይችለው ፈታኝ ነገር ምርጫ ቦርድም ሆነ በውሰጥችን ያሉት ዙንቢዎች ሊያቀርቡ አይችሉም፡፡ ጎበዝ ጠንከር ነው፡፡
አሁን አንድነት ግልፅ ጦርነት የታወጀበት ይመስላል – አቶ ኪዳኔ አመነ – የመድረክ ወጣት አመራር
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በተመለከተ ብዙ እየሰማን ነው፡፡ ፓርቲው ራሱን የማፅዳት ሃላፊነት ከተወጣ በኋላ ገዢው ፓርቲ ጥርሱን የነከሰበት ይመስላል፡፡ ብዙ ፈተና እየገጠመው ነው፡፡ በምርጫ ቦርድ ጥያቄ መሰረት ጠቅላላ ጉባኤ በድጋሚ እስከማድረግም ደርሰዋል፡፡በኔ እምነት አንድነት ፓርቲ በበኩሉ ብዙ ርቀት የሄደ ይመስለኛል፡፡ ትእግስታቸው አደንቃለሁ፡፡ ፓርቲው በውስጡ ከጥቂቶች በቀር በዙዎቹ ቁምነገር የሚያስቡ የምናከብራቸውና የምንወዳቸው ጥሩ ሰዎች አሉት፡፡ ትርጉም ያለው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ከሚያደርጉ ጥቂት ፓርቲዎች አንድነት አንዱ ነው፡፡ እናም በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ና እውነተኛ ፍትህ ለማምጣት የአንድነት መኖር ከፍተኛ ትርጉም አለው፡፡ ፓርቲው የአንድነት ፓርቲ አባላትና የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሣይሆን የራሳችን አቋምና መስመር ይዘን በሌላ ፓርቲ ያለን ሰዎች እንኳ አንድነት እንዲኖር አጥብቀን እንፈልጋለን፡፡ ወደፊት አንድነትም እኛም ቤታችን እያፅዳን መንገድ ላይ መገናኘት አለብን፡፡
ያኔ ብቻ ነው ኢትዮጵያን የምናድናት፡፡ እንዳንራመድ ቀይዶ የያዘን ገመድ እየበጣጠስን፤ ፀረ-ለውጥና አድሃሪ አቋምን እየመከትንና እያፀዳን የዴሞክራሲ እና የሉዓላዊነት ፍለጋው ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል፡፡
አሁን አንድነት ግልፅ ጦርነት የታወጀበት ይመስላል ፡፡ አንድነቶች አሁን ነው የፖለቲካ ፅናታቸው በጥበብ ማሳየት ያለባቸው፡፡ ወንድሞቻችን በርቱ!!!
ታሪክ ለመስራት እንዘጋጅ – አቶ ተክሌ በቀለ የአንድነት ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበር
አንድነት ፓርቲ የኢህኣዴግን ምንነት ላላመኑ ወገኖች ለማጋለጥ በትጋትና በስሌት ሲሰራ ቆይቷል፡፡እየሰራም ነዉ፤እዚህ ደርሷል፡፡ “የሆደ ሰፊዉን ምርጫ ቦርድ” ሆድ በገሃድ አጋልጧል፡፡በነአሞራዉና ወዲ ቐሺ(በተጋሩ ሁሉ) ትግልና ሞት የሚቀልዱትን በህዝብ ፊት ወጥተዉ ዛሬም እንዲዋሹና ለኢትዮጵያችን የፖለቲካ ታሪክ እነማን ምን እንደሆኑ አንድነት ፓርቲ የበኩሉን ሚና ተጫዉቷል፡፡ ለኔ ከባድመ ዉሳኔና ልህዝቡ በወቅቱ ከተነገረዉ ጋር ይመሳሰላል፤ይጠጋጋል፡፡ኢህኣዴግ ምርጫዉን እንደማይፈልገዉ፤ከፈለገዉም ለተለመደዉ ቀልዱ ከነማን ጋርና በምን ሁኔታ እንደሚፈልገዉ ፓርቲያችን ሶስተኛዉን (የአዉሮፓና አሜሪካ ታዛቢዎች የሌሉበት ምርጫ መሆኑን፤የህዝብ ታዛቢዎች የተበላሸ የምርጫ ሂደትና ፓርቲዎችን የማፈራረስ/የማዳከም ስራዎች) ነጥብ አስመዝግቧል፡፡
በዚህ ሂደት ላይ ሰፊ እዉነታ ለህዝብ ይቀርባል የሚል እምነት አለኝ፡፡ከምርጫዉ ቦርድ መጋረጃ ካሉት ወገኖች ጋር በሃሳብ እየተሸነፈ ግን ተሳትፎዉ ያለተቋረጠ አንድ ከፍተኛ አመራር እንዳለ እናዉቃለን፡፡ሁሉን ነገር በደንብና በመርህ የምንሰራዉ ለኢህኣዲግ/ምርጫ ቦርድ ካለን ፍርሃት ሳይሆን ለወደፊቱ ለምናስተዳድረዉ ህዝባችንና ለኢትዮጵያችን ፖለቲካ ክብር ስንል ነዉ፡፡እናም ከደንብ ወጥተን የሰራነዉ ክዋኔም በግፍ የገፋነዉ አመራርም፤አባልም የለም፡፡በመቻቻል መንፈስ ዲሰፒሊን ተጥሶም እንዲጓተት ተደርጓል፡፡ይህንንም የኢህኣዴግ ተባባሪነት ለታሪክ አስቀምጠነዋል፡፡
ምርጫ ቅንጦት ሆኖብን፤የተከበሩ እየተባሉ ለመጠራት ሳይሆን እፊታችን ላይ ያለ እድልና ስልትም ስለሆነ አንድነት ፓርቲ መጪዉን ምርጫ የምር እንዲሆን ወስኗል፡፡ ኢህኣዴግ ደግሞ ማበላሸቱን ተያያይዞትል፡፡ምርጫ በአምባገነን ቡድኖች ለሚገዙ አገራት ለለዉጥ እንዱ ስልት እንጂ ብቸኛዉ አለመሆኑ ይታመናል፡፡ፓርቲያችን ለለዉጥ ተደራጅም ይላል፡፡እዉነተኛ ፓርቲዎች ከምርጫዉ ባሻገር ላለዉ ግብ እንዲዋሃዱና እንዲተባበሩም ጥሪ አቅርቧል፤ስልቶችን ለማቀራረብም እየጣረም ነዉ፡፡የአንድነት ኣባላት በያለንበት ድርብ ሃላፊነት አለብን፡፡ለአንድነት ሃይሎች ስልቶቻችን ሁሉ በማቀራረብ የተጀመረዉ የስልጣን ሃይሎችን እያራገፉ ትግሉን በሰለጠነና አንድነቱን በጠበቀ መልኩ የማስቀጠልና ልዩነቶችን በማቻቻል ሰፊ መሰረት የማንበር ሃለፊነት አለብን፡፡ ታሪክ ለመስራት እንዘጋጅ፤ፊታችንን ወደ ዋናዉ ግብ እናድርግ፤ከሃዲዱ አንወርድም!
ታሪክ ለመስራት እንዘጋጅ – አቶ ተክሌ በቀለ የአንድነት ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበር
አንድነት ፓርቲ የኢህኣዴግን ምንነት ላላመኑ ወገኖች ለማጋለጥ በትጋትና በስሌት ሲሰራ ቆይቷል፡፡እየሰራም ነዉ፤እዚህ ደርሷል፡፡ “የሆደ ሰፊዉን ምርጫ ቦርድ” ሆድ በገሃድ አጋልጧል፡፡በነአሞራዉና ወዲ ቐሺ(በተጋሩ ሁሉ) ትግልና ሞት የሚቀልዱትን በህዝብ ፊት ወጥተዉ ዛሬም እንዲዋሹና ለኢትዮጵያችን የፖለቲካ ታሪክ እነማን ምን እንደሆኑ አንድነት ፓርቲ የበኩሉን ሚና ተጫዉቷል፡፡ ለኔ ከባድመ ዉሳኔና ልህዝቡ በወቅቱ ከተነገረዉ ጋር ይመሳሰላል፤ይጠጋጋል፡፡ ኢህኣዴግ ምርጫዉን እንደማይፈልገዉ፤ከፈለገዉም ለተለመደዉ ቀልዱ […]
አሁን አንድነት ግልፅ ጦርነት የታወጀበት ይመስላል – አቶ ኪዳኔ አመነ – የመድረክ ወጣት አመራር
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በተመለከተ ብዙ እየሰማን ነው፡፡ ፓርቲው ራሱን የማፅዳት ሃላፊነት ከተወጣ በኋላ ገዢው ፓርቲ ጥርሱን የነከሰበት ይመስላል፡፡ ብዙ ፈተና እየገጠመው ነው፡፡ በምርጫ ቦርድ ጥያቄ መሰረት ጠቅላላ ጉባኤ በድጋሚ እስከማድረግም ደርሰዋል፡፡ በኔ እምነት አንድነት ፓርቲ በበኩሉ ብዙ ርቀት የሄደ ይመስለኛል፡፡ ትእግስታቸው አደንቃለሁ፡፡ ፓርቲው በውስጡ ከጥቂቶች በቀር በዙዎቹ ቁምነገር የሚያስቡ የምናከብራቸውና የምንወዳቸው ጥሩ ሰዎች አሉት፡፡ […]
ጎበዝ ጠንከር ነው – ግርማ ሰይፉ የአንድነት ም/ሊቀመነበር
ምርጫ ቦርድ ማንም ይዘዘው ማንም ወይም በግል ተነሳሽነት እያደረገ ያለው ነገር የኢትዮጵያን የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ከምን ጊዜውም በለይ ወደኋላ ለመመለስ እንደሆነ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሊረዳው ይገባል፡፡ ምርጫ ቦርድ ምርጫ እንዲያሰተዳድር በተሰጠው ኃላፊነት የፓርቲዎች አስተዳደሪ ለመሆን እየቃጣው ያለ ተቋም ነው፡፡ ስናከብረው ለመከበር ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ለዚህ ተቋም መጠናክር የበኩላችንን መወጣት አለብን ብለን የተነሳን ፓርቲዎችን ጭምር እየገፉ አለቆቹን […]
ከአምስት የሚበልጡ የውጭ አገር ዜጎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተጠቆመ
ምክንያቱ በግልጽ ባይታወቅም ቁጥራቸው ከአምስት የሚበልጡ የውጭ አገር ዜጎች ታኅሳስ 27 ቀን 2007 ዓ.ም. ረፋዱ ላይ ቦሌ ቲኬ ሕንፃ አካባቢ በፖሊስ ተይዘው መወሰዳቸው ተጠቆመ፡፡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ቻይና አፍሪካ አደባባይ ፊት ለፊት በሚገኘው ቲኬ ሕንፃ ላይ በሚገኘው ሰንበርድ ካፌ አጠገብ ድንገት በተነሳ ግርግር በአካባቢው ለተወነሰ ጊዜ ውክቢያ ተፈጥሮ፣ አካባቢው በሰዎች ተሞልቶ እንደነበር በሥፍራው የነበሩ የዓይን […]
አቡነ ብርሃነየሱስ ሁለተኛው ኢትዮጵያዊ ካርዲናል ሆኑ
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳትና የኢትዮጵያ ጳጳሳት ጉባዔ ፕሬዚዳንት ብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስ ሱራፌል የካርዲናልነት ማዕረግ አገኙ፡፡ ብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስን ጨምሮ ለ15 ሊቃነ ጳጳሳት የካርዲናልነት ማዕረግና ለአምስት ሊቀ ጳጳሳትና ጳጳሳት ድምፅ አልባ (የመምረጥም ሆነ የመመረጥ መብት የሌላቸው) የካርዲናልነት ሹመት ባለፈው እሑድ ረፋድ ላይ በቫቲካን በመስጠት ይፋ ያደረጉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ናቸው፡፡ ቫቲካን ሬዲዮ ታኅሣሥ […]
የማለዳ ወግ … አፈ ጉባኤ አባ ዱላ …ግን ለምን አልሰሙንም? – ነቢዩ ሲራክ
* የኮንትራት ሰራተኛዋ አይነ ብርሃኗን ማጣትና የስም የለሿ ሟች እህት መጨረሻ ! * ሰሚ እስኪገኝ እንጮሃለን ! ታህሳስ 27 ቀን 2007 ዓም ሰኞ በማለዳው ያገኘኋቸው ሁለት መረጃዎች የወጡት በሁለቱ አንጋፋ የሳውዲ ጋዜጦች በአረብ ኒውስ Arab News እና በሳውዲ ጋዜት Saudi Gazette ነው። በአንዱን አይቸ ቢከፋኝ ፣ መፍትሔ ላይገኝ ይህን መርዶ ከንፈር ለማመስመጠጥ ብቻ መረጃ ብየ […]
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ጃንዩወሪ 06, 2015
የፕሮግራም መግለጫ
ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡
የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡
ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና
ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና
ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ
ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት
ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)
ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና
ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡
ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡
የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡
ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡
የቦስተን የቦምብ ጥቃት እና የሞት ፍርድ
በአሜሪካን የማሳቹሴትስ ግዛት የሞት ፍርድ ለመጨረሻ ጊዜ ተግባራዊ የተደረገው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1947 ዓ.ም. ነበር። በግዛቲቱ ፊሊፕ ቤሊኖ እና ኤድዋርድ ጌርትሰን ላይ ብያኔው ተግባራዊ ከሆነ በኋላ የሞት ፍርድ እንዲቀር ተድርጎ ቆይቷል።
የዩሮ መቀነስ ጠቃሚ ወይስ ጎጂ ነው?
ለአውሮፓ ገበያተኞች የዩሮ መቀነስ አስደሳች ዜና ሆኖ ሳለ ፤ አውሮፓ ተቀምጠው ከሌላው የአለማችን ክፍል ለሚሸምቱ ደግሞ ሁኔታው አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል። የዩሮ መቀነስ ጠቃሚ ወይስ ጎጂ ይሆን?
ፔጊዳና ተቃዋሚዎቹ
ፔጊዳ የተባለውን በአውሮፓ ፀረ እስልምና ንቅናቄን ዓላማ ና እንቅስቃሴ በመቃወም ትናንት ማምሻውን በበተለያዩ የጀርመን ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል ። በተመሳሳይ ጊዜ የንቅናቄው አባላትና ደጋፊዎቻቸውም በአንዳንድ የጀርመን ከተሞች አደባባይ ወጥተዋል ።
የቦኮ ሃራም መስፋፋት
በናይጀርያ የሚንቀሳቀሰዉ ቦኮሀራም የሚባለው እስልምና አክራሪ ቡድን ጥቃት በጎረቤት ሃገራት በመዛመቱ በምዕራብ አፍሪቃ ሃገራት ሥጋት ፈጥጥሯል። ቡድኑ ታኅሣሥ 26 ቀን፤ 20017 መጨረሻ በናይጀርያ የሚገኘዉን የአህጉሪቱን የጥምር ወታደራዊ ጦር ሰፈር በቁጥጥሩ ሥር ማድረጉ ይታወቃል።
የዓለም ዜና 060115
የዕለቱ ዜና
ምርጫ ቦርድ ፤አንድነትና መኢአድ በምርጫው ላይሳተፉ ይችላሉ አለ።
ታኀሳስ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድነት፤ ከምርጫው ከታገድኩ ውሳኔው ፖለቲካዊ ነው የሚሆነው አለ። አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት)እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የውስጥ ችግሮቻቸውን ካለፈቱ የምርጫውን ሂደት ላይሳተፉ ይችላሉ ሲል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስጠነቀቀ። የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር አዲሱ ገብረ እግዚአብሄር ፦ሁለቱ ፓርቲዎች በውስጥ ህገ ደንባቸው ሊሄዱ እንዳልቻሉ በመጥቀስ፤ ይህንንም …
ወሎ ውስጥ በኦሮሞዎች ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ ነው ተባለ
ታኀሳስ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ሊግ፤ ከአማራ ክልል ኦሮሚያ ዞን ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ ታስረው ከስምንት ወራት በላይ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ታሳሪዎችን ስም ዝርዝር ይፋ አደረገ። ሊጉ የ 26 እስረኞችን ስም ዝርዝር በማያያዝ ባወጣው መግለጫ፤ ከወራት በፊት የአዲስ አበባን አዲስ ማስተር ፕላን በመቃወም ተነስቶ ከነበረው ሰላማዊ ተቃውሞ …
አቶ መለስን የሸለመው”ያራ” ኩባንያ” ከባድ የሙስና ክስ ተመሰረተበት
ታኀሳስ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምርጫ 97 ወቅት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን የሸለመው “ያራ” የተሰኘ የኖርዌይ ድርጅት በሙስና ተከሰሰ ፤ ኢትዮጰያውያንም ተጨማሪ ክስ ያቀርባሉ። በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1997 ዓመተ ምህረት ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ 200 000 ዶላር የሸለመውና- ሽልማቱን ተከትሎ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የኢትዮጵያ ብቸኛ የማዳበሪያ አቅራቢ የሆነው የ”ያራ ኩባንያ”ዳይሬክተር ቶርሊፍ ኢንገር፤ …