የኢሳት ጋዜጠኞች መሳይ መኮንን እና ፋሲል የኔዓለም አስመራ ገቡ፤
ኢሳት በሰበር ዜና እንዳቀረበው ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ከዋሽንግተን ዲሲ እንዲሁም ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ከሆላንድ ኤርትራ ገቡ።
ከኢሳት እንደተገኘው መረጃ ከሆነ ጋዜጠኞቹ አስመራ የገቡት ትናንት ሲሆን በኤርትራ ቆይታቸውም እዚያ ያለውን ሃይል እንደሚጎበኙና ዘገባም እንደሚያቀርቡ በተጨማሪም የኤርትራ ባለስልጣናትን እንደሚያነጋግሩ ይጠቁማል።
የቀድሞው የጀርመን ድምጽ ጋዜጠኛና የአሁኑ የኢሳት ራድዮ ከፍተኛ አዘጋጅ መሳይ መኮንን፣ እንዲሁም የቀድሞው የአዲስ ዜና ጋዜጣ ዋና አዘጋጅና የአሁኑ የኢሳት ቲቪ ኤዲተር ፋሲል የኔዓለም በአስመራ ለስንት ጊዜያት እንደሚቆዩ እስካሁን የተገኘ መረጃ የለም።