አንድነት መሰናክሉን ያልፋል – አቶ አለነ ለምርጫ ቦርድ መልስ ሲሰጡ ( መደመጥ ያለበት)
ምርጫ ቦርድ እያደረገ ባለው ኢ-ሕገመንግስታዊ ተግባራት ዙሪያ የአንድነት አመራር አባል የሆኑት አቶ አለነ ማጸንቱ ለኢሳት ማብራሪይ ሰጥተዋል።
አቶ አለነ፣ በጎጃም ክፍለ ሀገር አገው ምድር አውራጃ ሲሆን የተወለደው፣ የ28 አመት ወጣት ነው። በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1999 በሶሻል ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ በ2004 ደግሞ ሁለተኛውን ድግሬ ተቀብሏል።
በተለያዩ የግል ኮሌጆች ዲን እና አስተማሪ በመሆን እንዲሁም በግል ትምህርት ቤቶች ርዕሠ- መምህር በመሆን አገልግሏል። አሁን ደግሞ በሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒሥቴር የጥናትና ምርምር ቡድን አስተባባሪ በመሆን የተለያዩ መመሪያዎች፣ ፕሮግራሞች እና መርሀ ግብሮችን በማዘጋጀት ለተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች የአሠልጣኞች ሥልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።
በ1997 የመኢአድ(ቅንጅት) በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የወጣቶች አደራጅ፤ ከ2001 እስከ 2002 በአዊ ዞን የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ እና የህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ፣ ከ2003 እስከ 2005 በአንድነት ፓርቲ በጥናትና ምርምር ቋሚ ኮሚቴ የማህበራዊ ጉዳይ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ ከ2006 ወዲህ ደግሞ በአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ስራ አስፈጻሚ አባል እና የማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛል።
አቶ አለነ ከኢሳት ጋር ያደረገዉን ቃለ ምልልስ ያዳምጡ።