የኢንተርኔት አገልግሎትና ተማሪዎች
እስቲ የተወሰኑ አመታት መለስ ብለን እናስብ፤ የኢንተርኔት አገልግሎት ባልነበረበት ጊዜ። ማንኛውንም መልዕክት ይሁን መረጃ ለማግኘት ከባድ እና ጊዜን የሚወስድ ነበር። የኢንተርኔት አገልግሎት ለትምህርት፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር ለመገናኘትም ይሁን ዜና እና መረጃን ለማግኘት ምን ያህል ጠቅሞናል? ጉዳቱስ እንዴት ይገለፃል?
እስቲ የተወሰኑ አመታት መለስ ብለን እናስብ፤ የኢንተርኔት አገልግሎት ባልነበረበት ጊዜ። ማንኛውንም መልዕክት ይሁን መረጃ ለማግኘት ከባድ እና ጊዜን የሚወስድ ነበር። የኢንተርኔት አገልግሎት ለትምህርት፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር ለመገናኘትም ይሁን ዜና እና መረጃን ለማግኘት ምን ያህል ጠቅሞናል? ጉዳቱስ እንዴት ይገለፃል?
ዩጋንዳ በቅርቡ ያፀደቀችው ግብረ ሰዶማዊነትን የሚቃወም ህግ ዓለም ዓቀፍ ትችት አስከትሏል ። አንዳንድ ምዕራባውያን ሃገራት ለዩጋንዳ የሚሰጡትን እርዳታ እያገዱ ነው ። የጀርመን የልማት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በበኩሉ የበርሊን መንግሥት ፣ የልማት እርዳታ ቅነሳ ከማድረጉ በፊት ጥንቃቄ የተሞላበት ክትትል እንደሚያደርግ አስታውቋል ።
ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት (HRW) ደቡብ ሱዳን ውስጥ ሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች የጦር ወንጀል በመፈጸም ላይ ናቸው ሲል አጋለጠ። በፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በሚመራው የደቡብ ሱዳን መንግሥት ወታደሮችና ፣ የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ሪኤክ
የዕለቱ ዜና
በዘገባዉ መሠረት ኢትዮጵያ ዉስጥ ሐሳብን የመግለፅ፥ የፕረስና የሃይማኖት ነፃነት ክፉኛ ተደፍልቋል። ኤርትራ ዉስጥም የሠብአዊ መብት ሙሉ በሙሉ መገደቡን ዘገባዉ አዉስቷል።
ትላንት የጥላቻ ንግግርን የተመለከተ ጥናት ማሟያ ውይይት ላይ ተሳትፌ ነበር። በርዕሰ ጉዳዩ ላይ በሰፊው የምመለስበት ቢሆንም፥ ቀብዱን ግን እነሆ፦
ርዕሱ በኢሕአዴግ እና በደጋፊዎቹ አተረጓጎም “የጥላቻ ንግግር” ተብሎ ሊመደብ ይችላል። አንድ የዴሞክራሲ ሕልመኛ ርዕሱ ላይ የተጠቀሰውን ዓ/ነገር ቢናገር ኢ-ዴሞክራሲያዊም ሆነ ጥላቻ ሰባኪ አያሰኘውም ባይ ነኝ እኔ ግን። እኔ ራሴ ርዕሱ ላይ የተጻፈውን ያለምንም ጥላቻ ከውስጥ ፍላጎቴ ነው ያፈለቅኩት።
ከዴሞክራሲ ዐብይ ባሕርያት አንዱ ገዢ ፓርቲዎች ወርደው የሕዝብ ምርጫ በሆኑ ተቃዋሚዎች መተካት የሚችሉበት እና ገዢ የነበሩ ተቃዋሚ ሆነው የሚሮጡበት ስርዓት ማመቻቸት ነው። ስለዚህ ለኔ ኢትዮጵያ ለዴሞክራሲያዊነት መፍጨርጨሯ ሐቀኛ ነው ልል የምችለው ኢሕአዴግ ወርዶ ተቃዋሚ ሆኖ ሳየው ነው።
የጥላቻ እና የፍቅር ንግግሮች የሉም ማለት አልችልም። ነገር ግን የጥላቻም ይሁን የፍቅር ንግግሮች ዋጋቸው ከአንድ ክበብ አያልፍም። ለምሳሌ ኢትዮጵያ ነክ የአገር ውስጥ እና የውጭ ሚዲያዎች በባሕሪያቸው መድባቸው ብባል በሦስት እመድባቸዋለሁ፦
1ኛ) አፍቃሬ-ኢሕአዴግ፣
2ኛ) ኢሕአዴግን-አያሳየኝ እና
3ኛ) I-don’t-know-what-to-doዎች በማለት።
የመጀመሪያዎቹ [አፍቃሬ-ኢሕአዴግ]ዎቹ ዋነኛ ሥራቸው በማንኛውም መንገድ ኢሕአዴግን ማንቆለጳጰስ እና ከተቃዋሚዎች ክፉ ዓይን መጠበቅ ናቸው። አዳም ሲፈጠር ጀምሮ “በስም መስጠት ነው (naming)” ነው ሥራውን የጀመረው እንዲሉ እኔም በዚህ ምድብ የምፈርጃቸውን ጥቂቶች ልዘርዝር፤ ኢቴቪ፣ ዛሚ ኤፍኤም፣ ኢትዮ-ቻናል፣ ትግራይ ኦንላይን እና ወዘተ ናቸው።
ሁለተኛው ምድብ ውስጥ የሚገኙት [ኢሕአዴግን-አያሳየኝ]ዎች ደግሞ የሚደግፉት (የሚያፈቅሩት) የተለየ የተቃዋሚ ቡድን የላቸውም፣ የሚራሩለት እንጂ። ነገር ግን ያለምንም ጥርጥር ኢሕአዴግን አይወዱም። ስለዚህ ሥራቸው ኢሕአዴግን መተቸት ነው። እነዚህ ውስጥ ኢሳት፣ ፋክት፣ ኢትዮጵያን ሪቪው እና ወዘተ ይገኛሉ።
ሦስተኛው ምድብ [I-don’t-know-what-to-do]ዎች ውስጥ ያሉት ደግሞ በመሐል ቤት ይዋልላሉ። ለዚህ ቡድን አሪፍ ምሳሌ የሚሆኑት ደግሞ አዲስ አድማስ ጋዜጣ እና ሸገር ኤፍ ኤም ናቸው። በተረፈ ጥቂቶች ብቻ ለመፈረጅ የማይመች የሚዲያ ሥራ እና ሊረዱት የሚከብድ የአቋምና አቀራረብ ልዩነት ያሳያሉ።
ለምን እነዚህን ፍረጃዎች እና ስየማዎች ማድረግ አስፈለገኝ? ምክንያቱም የጥላቻ ንግግሮች በማን፣ እንዴት እንደሚተረጎም ቀላል ማስረጃ ስለሚሆነኝ ነው። ምድብ አንድ ውስጥ ለሚገኙ ማንኛውንም ዓይነት ኢሕአዴግ ላይ የተሰነዘረ ትችት የጥላቻ ንግግር ነው።
ምድብ ሁለት ውስጥ ለሚገኙትም ከኢሕአዴግ አፍ የሚወጣ ሁሉ ክፉ ነገር ነው። ሦስተኛው ምድብ ከቻለ ሁሉንም ለማስደሰት ካልቻለ ሁሉንም ላለማስከፋት ይፈጨረጨራል። በመሐል ቤት እውነት ማደሪያ ታጣለች። ሁሉም ለዓላማው እጇን ይጠመዝዛታል።
በአገራችን የጥላቻ ንግግር የሚባሉት ሁሌም ከጥላቻ የመነጩ ላይሆኑ ይችላሉ። በባሕላችን የሰውን ስህተት ፊት ለፊቱ መንገርን እንደአለመከባበር የሚያስቆጥር ስህተት ነው። ስለዚህ የአንድን ሰው ጉልህ እንከን እንዲህ ነህ ብሎ መንገር በጣም አስደንጋጭ ነው የሚሆነው። እንዲያውም በጠብ ወቅት ብቻ የሚከሰት ነገር ነው። ስለዚህ በትልቁ (በፓርቲና በፖለቲካዊ አመለካከት ላይ) ሲሰነዘር የእርምት አስተያየት መሆን ቀርቶ የትችት ማዕረግ እንኳን አያገኝም። የጥላቻ ይመስላል (ይባላል)።
ነገር ግን፤ ድክመትን እየሸሸጉ ብርታትን እንደመንገር ያለ አደገኛ ንግግር (dangerous speech) አይቼም ሰምቼም አላውቅም። ለግለሰብም ይሁን ለቡድን ግብዝነት ይዳርጋል። ድክመት ሲነገረው እልል ብሎ በፈገግታ ተጉመጥምጦ የሚውጥ ግለሰብም ይሁን ቡድን ገጥሞኝ አያውቅም፤ ከትችቱ አለመማር ግን እየሰሙ አይቻልም፤ ከስህተት ላለመማር መፍትሔው እንደኢሕአዴግ ተቺውን ማፈን ብቻ ነው። ትችት ካደመጡት ግን ምናልባት ለመዋጥ ጊዜ ይወስድ ይሆናል እንጂ ዘልቆ መቆጥቆጡ አይቀሬ ነው።
ይሄ ሁሉ ግን ስለጠሉ ብቻ የሚተቹ፣ ስለወደዱ ብቻ የማይሞገሰውን የሚያወድሱ የሉም ማለት አይደለም። ጥላቻና ፍቅርም ምክንያታዊ አይሆኑም ማለት ይከብዳል። ነገር ግን ክርር ያሉት የሥነ ልቦና ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል።
የጥላቻ ንግግርን መብት ከሐሳብን የመግለጽ መብት ለይቶ ለማስቀረት ሁነኛው መፍትሔ የማንፈልገውን ብቻ ሳይሆን የምንፈልገውንም ጭምር ማወቅ አለብን፤ አራማጅ ተራማጅነታችንም በመርሕ እንዲመራ ማድረግ መድኃኒቱ ነው።
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል 34 አምቡላንሶችን ለክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች አስረከበ። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር 34 24.7 ሚሊዮን ብር ያወጣባቸው 34 አምቡላንሶችን ለክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አስረከበ። ከ300 ሺህ በላይለሚሆኑ ዜጎች አገልግሎት እየሰጠ ያለው ማኅበር፣ አሁን ደግሞ አቅሙ ከፍ ሊል እንደሚችል አስታውቋል።
በአዲስ አበባ የሚያስገነባው የገቢ ማስገኛ ሥራም መጀመሩን፣ ዋና ጸሓፊው ገልጸዋል። ዝርዝሩን መለስካቸው አምኃ ከላከዉ ዘገባ ያድምጡ።
የምስራቅ አፍሪቃ የልማት በየነ መንግስታት ድርጅት ኢጋድ የደቡብ ሱዳን መንግስትና ተቃዋሚዎቹን የማደራደር ጥረት ቀጥሏል። ኢትዮጵያ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ከደቡብሱዳን የሰላም ድርድር ጋር የተያያዘና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ሃይለማራምደሳለኘ የተላከ ልዩ መልዕክት ለፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር አድርሰው ተመልሰዋል።
ልዩ የተባለው መልዕክት ይዘት ግን አልተብራራም። የቀሪዎቹ አራት የሱዳን መንግስት ተቃዋሚ ባለሥልጣናት ከእስር አለመፈታት ፣ ለሰላም ድርድሩ መሳካት እንቅፋት ከሆኑ ነጥቦች አንደኛው እንደሆነ ይነገራል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቶ ዲና ሙፍቲ ለአገር ዉስጥ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የህዳሴ ግድብ ግንባታጋር በተያዘ የግብጽ መንግስት ላይ ሂስ ሰንዝረዋል። አቶ ዲና የግብጽባለስልጣናት የግድቡን ግንባታ…
© Masresha Mammo
የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሞራል መሠረት እና ብቃት በሌላቸው ፖለቲከኞች እጅ ከወደቀ ሰንብቷል። ይህ የሰነበተ እውነታ በአሁን ሰዓት ከዝቅጠትም በታች እየኾነ ነው። ለኢትዮጵያ የሚያዋጣት ብሔርን መሠረት ያደረገ ፖለቲካዊ ርዕዮት ነው የሚለው የፖሊቲካል ኢኮኖሚ ስትራቴጂ ሁሉን አቀፍ ፍትህ የተንሰራፋበት ቢኾን ምናልባት አዋጪ ሊኾን ይችላል የሚል ግምት ማስቀመጥ ይቻል ነበር። ነገር ገን ስትራቴጂው ወረቀት ላይ ሌላ መልክ የያዘ፤ ምድር ላይ ደሞ ሌላ ትርክት የዋጠው ነው። ከጅምሩ ፍትሃዊነቱ አጠራጣሪ ስለኾነ ስትራቴጂው ለማፋጀት ያለመና እርስ በርስ በጥርጣሬ ከመተያየት የማያመልጡ የብሄር ፖለቲከኞችን እየፈለፈለ ይገኛል። ለዚህም ነው ከሁለት ዐሥርተ ዓመታት በፊት “በትምክህት” ፍረጃ የተጸነሰው ሕዝብን የማቃለል ጅምር ወደ ለሃጭ ተዋስዖ ያደገው።
የብአዴን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አለምነው መኮንን ይህን የለሃጭ ተዋስዖ ከየት አመጡት? የሚለው ጥያቄ በእኔ እምነት ወሳኝ ጥያቄ ነው። ብዙዎች እንደሚያምኑት ብአዴን እንደ ፓርቲ የራሱ የኾነ ነጻነት እና እምነት ያለው ፓርቲ አይደለም፤ አሻንጉሊት እና አስፈጻሚ፤ ከሕወሃት የሚወርድለትን ትዕዛዝ እና ፖለቲካዊ ትንተና ለማስተላለፍ የሚያገልግል “ትቦ/ቧንቧ ፓርቲ” ነው። ከአራቱ የኢሕአዴግ ፓርቲዎች ውስጥ ራሱን ሥልጣን እንደሚጋራና 22 ሚልዮን ሕዝብ እንደሚወክል ድርጅት ፖለቲካዊ ስሌት ውስጥ አስገብቶ የሚንቀሳቀስ ፓርቲም አይደለም። “የአማራውን” ሕዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚያስችል ምንም ዐይነት ተነሳሽነትም የለውም። ይህን እውነታ በግልጽ ለመረዳት የፓርቲውን ቁልፍ ሰዎች ማንነት ማየት ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ። አንድ የብሔር ፓርቲ የአባልነት መመዘኛ መስፈርቱ ምንድነው? የሚለውን ጥያቄ ቀድመን እናንሳ። በደም እና በዘር ከዚያ ብሔር የተገኘ ሰው ብቻ ነው የፓርቲው አባል መኾን ያለበት? ወይስ በምርጫም የዚያ ብሔር አባል ነኝ ማለትን ያካትታል?
የሚያካትት ከኾነ በብሔር የመደራጀት ትርጉም ለምን ያስፈልጋል የሚለውን ጥያቄ ማንሳታችን አይቀርም። ይህን ጉዳይ ማንሳት የፈለግኹት የመንግሥት ቁልፍ ሰው ናቸው ተብለው የሚነግርላቸውን አቶ በረከትን እንደምሳሌ ለመመልከት ነው። አቶ በረከት በደም ከአማራው ጋራ የሚያስተሳስራቸው አንዳችም ነገር የለም። ነገር ግን የአማራው ጉዳይ የእኔ ነው ብሎ በተቀመጠው ፓርቲ ላይ ቁልፍ ቦታ አላቸው። የብአዴን አመራሮችም ኾኑ አባላት አቶ በረከት ከዚህ ፓርቲ ራሳቸውን እንዲያወጡ መጠየቅ አለባቸው፤ ቡግና ውስጥ ተወልዶ ማደግ አማራነትን ያቀዳጃልና እኔም አማራ ነኝ የሚል አቋም ካላቸው፤ ቀድመህ ለተገኘህበት የብሔር ማንነት ቅድሚያ ስጥ ከሚለው የራሳቸውና የተከታይ ካድሬዎቻቸው ትንተና ጋራ ስለሚጋጭ የሚያዋጣ አካሄድ አይኾንም። እንደ በረከት ዐይነት “የአማራነት ልብስን ቀደው ያሰፉ” ሰዎች ለአማራው ሕዝብ ቆመናል ብለው ከሚያስቡ ሰዎች ጋራ በአንድ ጠረጴዛ ላይ መቀመጣቸው መዘዙ ብዙ ነው። በዋነኛነት ሌሎችን ነጻነት ያሳጣቸዋል። ነጻነት የሌለው ሰው ደግሞ ከራሱ የሚናገረው ነገር የለውም።
አቶ በረከት ከጫካ ጀምረው የሕወሓት ዋነኛ ሐሳብ አስተግባሪ ናቸው። አማራ ትምክህተኛ እና ነፍጠኛ ነው የሚል የፖለቲካ መሣርያ ይዘው መሥራት የጀመሩት ዛሬ አይደለም። አማራው እንደ ሕዝብ ትምክህት አለበት ወይ የሚለው ሐሳብ በራሱ ሕዝብን በአንድ ቅርጫት ውስጥ አስገብቶ እንደመፍረድ ስለሚቆጠር ሐልዮቱ በራሱ ወኃ የሚያነሳ ጭብጥ የለውም። የአማራውን ልሂቅ ስህተት እና ተግባር ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋራ ጭቆናን ሲካፈል ለኖረ ሕዝብ ማሸከምም የወጣለት ኢ-ፍትሃዊነት ነው። የትኛውም አማራ፤ የትኛውም ትግሬ፣ የትኛውም ኦሮሞ፣ የትኛውም ጉራጌ፣ የትኛውም ወላይታ . . .እና ሌሎችም ብሔሮች የጨቋኝ አገዛዝ ሰለባዎች ነበሩ፤ እንደ ሕዝብ። አሁንም ናቸው። አማራ እንደ ሕዝብ የተለየ ያገኘው ጥቅም አለ ብዬ አላስብም። ስለዚህ አማራውም እንደ ሕዝብ በብሔር መብቱን ያስጠብቅ የሚል መነሻ ይዘን ከመጣን ስድብን ተሸክሞ የሚዘልቅበት ምንም ዐይነት ምድራዊ ምክንያት ሊኖር አይችልም።
የህወሓት ከፍተኛ ባለሥልጣናት አማራውን ወክለናል ብለው በሚንቀሳቀሱ አመራሮች ላይ ለምን “ትምክህተኛ”፣ “ነፍጠኛ” እና “ለሃጫም” የሚሉ ቃላቶችን በአፋቸው ላይ ማስቀመጥ መረጡ? በኦሮሞው ላይ “ጠባብ” እና “ሁሉም ሲፋቅ ኦነግ ነው” የሚለውን ፍረጃ እና ስድብ ማሸከምስ ፈለጉ? ይህን ፍረጃ እና ስድብ የመረጡበት ምክንያት አንድና አንድ ብቻ ነው። የሁለቱ ብሔሮች ጥንካሬ የሥልጣን መሠረታቸውን ስለሚያናጋ ነው። ራሳቸው ቀይደው ባመጡት የብሔር ፖለቲካ አደረጃጀት ኦሮሞው እና አማራው ባላቸው የሕዝብ ብዛት ብቻ የሥልጣን ተቀናቃኝ በመኾን ወደፊት የሥልጣን ርካብ ላይ እንደ ሕወሓት ያለው ድርጅት እንዳይወጣ እንደሚያደርገው ጠንቅቀው ያውቃሉ። ስለዚህም “እኔ ትምክህተኛም፤ ጠባብም አይደለሁም” የሚለውን ፍረጃ መልስ እስኪሰጡበት ድረስ ሥልጣናቸውን ማራዘም ይፈልጋሉ። ሕወሃት ለሌሎቹ የኢትዮጵያ ብሔሮች ቀርቶ ሕዝባዊ መሠረት አለኝ ለሚለው የትግራይ ማኅበረሰብም የማይገደው መኾኑን በተደጋጋሚ አሳይቷል። (ለዚህ የአብርሃ ደስታን ሪፖርቶች መከታተል ብቻ በቂ ነው)።
ብዙ የነቁ የትግራይ ልጆች እና ራሳቸውን ከአረና ጎን አሰልፈው የሕወሃትን አምባገነናዊ አስተዳደር ለሚታገሉ ሰዎች የሚያወጣላቸው ስም አማራውን እና ኦሮሞውን ከፈረጁበት ጋራ ተመሳሳይ ነው። አሁንም አዲሱ “የትምክህት ለሃጭ” ተዋስዖ በገዛ ልጁ አባቱን ማሰደብ ዐይነት ነው። ይህ አዲስ ነገር አይደለም። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ ይህንኑ ተመሳሳይ ድርጊት ፈጽመዋል። ይህ ሕዝብን የማቃለል እና በእሳት ላይ ቤንዚን የማርከፍከፍ ተግባር ተጸንሶ የሚያድገው በሕውሓት ሴል ውስጥ አይደለም ብሎ ማንም አይጠረጥርም።
በ97 ምርጫ ገዢው ፓርቲ ከተቃዋሚ ፓርቲ በኩል ያለው ጫና እየበረታበት ሲመጣ እና በፖሊሲ ክርክሮች ላይ ሕዝቡ የበለጠ ድምጹን ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ሊሰጥ ወደሚችልበት ኹኔታ ባዘነበለበት ወቀት “ኢንተርሃምዌይ” የምትለዋን ቃል ከአለቃቸው ተቀብለው በቴሌቪዥን መስኮት መጥተው የነገሩን አማራውን እወክላለሁ ብለው የተቀመጡት አቶ አዲሱ ለገሰ ነበሩ። ከራሱ አፍልቆ ያመነበትን ነገር በራሱ ቋንቋ የሚናገር አንድም ባለሥልጣን እንደሌለን እናውቃለን። አቶ መለስ ቃላቶችን ይፈበርካሉ፤ እነዚያን የተፈበረኩ ቃላት በዙሪያቸው ኅሊና እና ሆዳቸውን የሸጡ ባለሥልጣናት እንደ ዐየር ባየር ነጋዴ አውጥተው እንደ በቀቀን ሲጮኹብን ይውላሉ።
እጅግ በጣም አስገራሚው ነገር ኢሕአዴግ ውስጥ ካሉት አራት ድርጅቶች መካከል በአመራር ደረጃ ለወከሉት ሕዝብ ባለመቆርቆር ብአዴኖችን የሚተካከላቸው አለመገኘቱ ነው። በታምራት ላይኔ ተጀምሮ፣ በአዲሱ ለገሰ ተባብሶ፣ በአለምነው መኮንን የዝቅጠት ደረጃ ላይ ደርሷል። ምንም እንኳ “የዘር ምርጥ፤ ወይም ንጹህ ዘር” የሚባል ጽንሰ ሐሳብ በዚህ ዓለም ላይ ባይኖርም፤ (አለ ብለው የሚያስቡ ካሉ፤ እንደ ሂትለር ዐይነት በሽታ የተጠናወጣቸው ይመስለኛል) አንዳንዶች የእነሱን ዘር ከሌላው ዘር የተለየ እና የተሻለ አድርገው ለማሳየት ሲታትሩ እየተመለከትን ነው። እያንዳንዱ የሰው ልጅ ሲፈጠር እኩል ነው የሚለውን ዋናና መሠረታዊ ጉዳይ ኾነ ብለው ለመሸሽ ፖለቲካዊ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ “ማንነት እንዲህ ነው፤ እንዲያ ነው” በሚል ጉንጭ አልፋ ክርክር ውስጥ የሚገቡ ሰዎችም ሞልተዋል። እነዚህ በፖሊቲካ መጫዎች ሜዳው ታስቦ እና ተሰልቶ ከተቀመጠላቸው ተዋስዖ ውጪ አዲስ ተዋስዖ መፍጠር ያቃታቸው ናቸው። ቀጣይቱ ኢትዮጵያ አዲስ ተዋስዖ ያስፈልጋታል። ሁሉም የሰው ልጆች በመጀመርያ እኩል ናቸው በሚል መሠረታዊ ኀልዮት ላይ የሚያጠነጥን ተዋስዖ።
የለሃጭ ተዋስዖው በሁለት ወገን ራሳቸውን የቀየዱ ልጋጋም ተፋላሚዎችን እያሳየን ነው። “ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል” ወደሚል መፈክረኛነት መሻገር አርቆ አሳቢነትን የሚያሳይ እንዳልኾነ ግልጽ ነው። ምክንያታዊ ከኾኑ ምልከታዎች ወጥተን የስድብ ጅራፍ የምናጮህ ትውልዶች መኾናችንም አሳዛኝ እውነታችን ኾኗል። አማራው እንደ ሕዝብ እየተሰደበ ነው የሚለው ነገር የሚያስቆጣን እና የሚያንገበግበን ከአማራ ስለተወለድን ብቻ ከኾነ ፍትሃዊ የመኾን ዕድላችን ይመነምናል። ይህ ማለት ግን መሰደብን አሜን ብላችሁ ተቀበሉ እና እለፉት ከሚል እሳቤ ጋራ ፈጽሞ አይገናኝም። ግለሰቦችም ኾኑ ብሔሮች በማንኛውም ኹኔታ መሰደባቸውን መቃወም እና መታገል ነው ዋናው እና ትልቁ ቁም ነገር።
በሌላ በኩል ሌላው ብሔር ሲሰደብ ወገባቸውን ታጥቀው የሚመጡ ሰዎች አማራውም እንደ ሕዝብ ሊሰደብ አይገባውም ብለው ከጎኑ ካልቆሙ፤ ለብሔር እንቆረቆራለን የሚሉት ጊዜያዊ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ትርፋቸውን ለማስጠበቅ ብቻ እንደኾነ ያሳብቅባቸዋል። ይህ ደግሞ እንደ አገርም ኾነ እንደ ማሕበረሰብ ዘላቂ የኾን ትርፍ የምናካብትበት ጉዳይ አይኾንም።
ለብሔር/ለጎሳ ፖለቲካ ቅድሚያ ሰጥተው የክርክር ሰይፋቸውን የሚመዙ ሰዎች አሁን አማራ በሚባለው ብሔር ላይ የተቃጣውን ስድብ ሲቃወሙት ካላየን፤ የሚከተሉት ፖለቲካዊ ርዕዮት ሚዛን የሚደፋ ነው ብለን እንድናስብ አያደርጉንም።
በእኔ እምነት አቶ አለምነው መኮንን የፈጸሙት ነገር ወንጀል ነው። ያውም ትልቅ ወንጀል። ጉዳዩ በግምገማ ወይም ከሥራ ኀላፊነታቸው ዝቅ በማድረግ ብቻ የሚታለፍም አይደለም። የሚመራውን ሕዝብ በዚህ ደረጃ አሳንሶ እና አዋርዶ የሚመለከት መሪ ፓርቲውንም ኾነ አገሩን አይጠቅምም። የፌዴራል መንግሥቱ የክልል መንግሥታት እና ባለ ሥልጣናት የህዝብን ክብር እና ስም የሚያጎድፍ ተግባር ሲፈጽሙ ነገሩን የሚዳኝበት የራሱ የኾነ ሕገ መንግሥታዊ ማዕቀፍ አለው። በዚህ ጉዳይ ላይ መንግሥት ርምጃ የመውሰድ የሞራል ብቃትም ኾነ መሠረት የለውም የሚል መከራከርያ ሊነሳ እንደሚችል እገምታለሁ። ይህ መከራከርያ እና ግምት ትክክል ነው ብዬም አምናለሁ። ይህ ዐይነቱ በሕዝብ ላይ ቁጣ ሊያስነሳ የሚችል ድርጊት ከወዲሁ በራሱ በፌዴራል መንግሥቱ መልስ የማያገኝ ከኾነ፤ ራሱን በጊዜ ሂደት ከስሩ መንግሎ ሊጥለው እንደማይችል ምንም ማረጋገጫ አይሰጠንም። ይህ ሐሳብ ራሳቸውን በተቃዋሚ ጎራ ላሰለፉ ዜጎች ‘የዋህና የኢትዮጵያን መንግሥት ተፈጥሯዊ ማንነት ካለማወቅ የመነጨ’ ሊመስላቸው ይችላል። ለጊዜው መልሴ ይምሰላችው ግድ የለም የሚል ይኾናል። ነገር ግን በበሰበሰ አሠራሩም ቢኾን ይህን ጉዳይ ችላ ማለት አያዋጣውም ባይ ነኝ። ባለሥልጣናቴ ሙስና ሲሠሩ አገኘኋቸው ብሎ ዘብጥያ ካወረደ፤ አቶ አለምነህን የማያወርድበት ምንም ምክንያት ሊኖር አይችልም ከሚል መነሻም ነው።
በመጨረሻ፦ የአቶ አለምነው ንግግር ማንንም ሰው የኾነ ሰው ሁሉ ምን ያህል ሊያስቆጣ እንደሚችል ለማሳየት ንግግሩን በሌሎች ብሔሮች ገልብጬ ማየት ፈለግሁ። ይህን ማድረግ የፈለግኹት ለብሔር ማንነት ቅድሚያ የሚሰጡ ሰዎች ዝምታ ምን ያህል አግባብ እንዳልነበረ ለማሳየት ነው።
አቶ አለምነው እንዲህ ነበር ያሉት። “አማራው በባዶ እግሩ እየሄደ፤ ነገሩ መርዝ ነው፤ ይህንን የትምክህት ለሃጩን ካላራገፈ በአንድነት አብሮ መኖር አይችልም!”
ይህንኑ ንግግር የሕወሃት ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲህ ብለው አቀረቡት ብለን እናስብ “ትግሬ በሰቆጣ እየሄደ፤ ነገሩ መርዝ ነው፤ የእብሪት ለሃጩን ካላራገፈ በአንድነት አብሮ መኖር አይችልም!”
እንደገና ይህንኑ ንግግር የኦህዴዱ ምክትል ፕሬዝዳንት ሲያቀርቡት “ኦሮሞ በቦት ጫማ እየሄደ ነገሩ መርዝ ነው፤ የመገንጠል ለሃጩን ካላራገፈ በአንድነት አብሮ መኖር አይችልም!” ቢሉ ምላሾቻችን ምንድን ነው የሚኾኑት? የለሃጭ ተዋስዖ ምናልባትም ልጋግ ኾኖ ሁላችንንም ጠራርጎ እንዳያጠፋን ያሰጋል። ሁላችንም ከጊዜያዊ ጥቅማችን በላይ ለሰው ልጆች እኩልነት እኩል እንቁም።
News, Cultural Mosaic, Kebele Lives and Environment or Tech
ሶማሊያ ዋና ከተማ መቅዲሾ ውስጥ ዛሬ በደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃት ከ10 የሚበልጡ ሰዎች ህይወት ጠፋ ። ሰባት ሰዎች ደግሞ ቆሰሉ ። በሶማሊያ ብሔራዊ የፀጥታ ዋና መስሪያ ቤት አቅራቢያ በደረሰው በዚሁ ጥቃት ከተገደሉት መካከል ሰላማዊ ሰዎችና የደህንነት ኃይሎችም ይገኙበታል ። ለጥቃቱ አሸባብ ሃላፊነቱን ወስዷል ።
በጀርመን በየካቲት ወር አጋማሽ ላይ ለሳምንት የሚዘልቀዉ የካርኔቫል ድግስ ዛሪ በድምቀት ተጀምሮአል። ጀርመናዉያን የሚያከብሩት ብዙ ባህላዊና ልማዳዊ በዓላት አልዋቸዉ። ትልቅና ተወዳጅ ከሆኑት በዓላት መካከል ፤ የገና፣ የዘመን መለወጫ እንዲሁም የፋሲካ በዓል ሲሆን፤ ከሃይማኖት ጋር ግንኙነት የሌለዉ የካርኔቫል ድግስም
የባሮሶ እና የአቻዎቻቸዉ ንግግር ከአቡጃ ሲንቆረቆር የሰሜን ምሥራቅ ናጄሪያ ግዛት የአዳማዋ መንደሮች ጥይትና ቦምብ ይዘንብባቸዉ ነበር።አስራ-ሰወስት ሰዎች ተገደሉ።አንድ የክርስቲያን መንፈሳዊ ትምሕርት ቤት ጋየናይጄሪያ የዛሬዉ ሰሜናዊና ደቡባዊ ግዛትዋ
………………..ቴወድሮስ ከጎንደርና ከአሁኑ አማራ ይልቅ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ከዚያም አልፎ እየሩሳሌም ነጻ ለማውጣት እቅድ እንደነበረው ይነገራል፡፡አጼ ዮሃንስም እራሱን የትግራይ ሳይሆን የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ነበር፡፡ አሉላ አባነጋ ቀይ ባህር ድረስ ይዋትት የነበረው ለተንቤን አሊያም ለትግራይ አልነበረም፡፡
አጤ ምኒልክ የአንኮበር ወይንም የሸዋ ንጉስ ብቻ አልነበሩም፡፡ ምኒልክና ጀኔራሎቹ አድዋ ድረስ የዘመቱት የአሁኑ ዘመን መሪዎች እንደሚሉት ‹‹ነፍጠኛውን›› ብቻ ወክለው አልነበረም፡፡ ንጉስ ጦና እና ሌሎችም የትግራይን ተራራዎች የወጡ የወረዱት ለእናት ሃገራቸው ኢትዮጵያ ነው።
እንደ በላይ ዘለቀ ያሉ ጀግና የኢትዮጵያ አርበኞች በአምስት አመቱ የትግል ወቅት የጣሊያን ፋሺስትን የተዋጉት ተጋድሎ ያደረጉት ለኢትዮጵያ ሃገራቸው ነው ። በደርግ ዘመን በሶማሊያ እና በኤርትራ ተራሮች ወንበደዎችን የተዋጉት ወታደሮች የእናት ሃገራቸው አንድነት …. በባድመ የተሰዉት ወጣት ወገኖቻችን የእናት አገራቸው አንድነት አነሳስቷቸው ነው። ምንሊክ ሳልሳዊ
አንድነት/መኢአድ እና ትብብር፣ በጋራ የአድዋ ድልን ለማክበር ከአንድነት ጽ/ቤት ጀመሮ እስከ ጊዮርጊስ የእግር ጉዞ እንደሚያደርጉ፣ በሚኒሊክ ሃዉልት ሥርም አበባ እንደሚያስቀምጡ በመግለጽ ፣ በሕጉ መሰረት ፖሊስ አስፈላጊዉን ትብብር እንዲያደርግ ቢያሳዉቁም፣ ኢሕአዴግ በሚቆጣጠረዉ የአዲስ አበበ አስተዳደር አማካኝነት «በዓሉ በብሄራዊ ደረጃ ስለሚከበር ማስተናገድ አንችልም» የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ሕዝቡን ባሳተፈ መልኩ በብሄራዊ ደረጃ የአድዋ በዓል፣ በኢሕአዴግ ዘመን፣ ከዚህ በፊት […]
የአንድነት ፓርቲ ከሰባ እስከ ሰማኒያ የሚሆን ሕዝብ ድምጹን ለማሰማት መዉጣቱ ገልጾ፣ ለባህር ዳር ሕዝብ ያለዉን አክብሮኢትና አድናቆት የካቲት 20 ቀን 2006 ባወጣዉ መግለጫ ገለጸ። ፓርቲ የባህር ዳሩ አይነት እንቅስቅሴ በሌሎች የአገሪቷ ክፍሎችን እንደሚደረጉ ያሳወቀ ሲሆን በአገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ሁሉ ከጎኑ እንዲቆሙ፣ ድጋፍ እንዲሰጡና ትግሉን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል። UDJ Press release on Bahir […]

በሕወሓት የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት/ኦህዴድ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ የድርጅቱን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር ተመደበ።
በዚሁ መሰረት ምክትል ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ሙክታር ከድር የድርጅቱ ሊቀመንበር ሆነው ተመድበዋል። የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት ወይዘሮ አስቴር ማሞ ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመድበዋል።
የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት/ኦህዴድ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር በሕወሓት የተመደቡት ሕወሓት በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ ነው።ተመዳቢዎቹ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት የሚወጡ መሆናቸው ታምኖባቸዋል።
በሕወሓት በወረደው ትእዛዝ የኦሕደድ ማዕከላዊ ኮሚቴው የተባለው ምድብ በቅርቡ ባካሄደው ስብሰባ የድርጅቱ ሊቀመንበር የነበሩት የሕክምና ውጪያቸው ከክልሉ በጀት እኩል ስለሆነ ባለመፈለጋቸው አቶ አለማየሁ አቶምሳ በህመም ምክንያት ተብሎ ከስልጣናቸው የተሰናበቱ ሲሆን በቦታው ላይ ከተመደቡ ጀምሮ ምንም አይነት ስራ አልሰሩም ሲል ሕወሓት አማሯል።

(ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)
ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራ በረዳትነት የሚያበረውን ቦይንግ 767 አውሮፕላን አቅጣጫ ቀይሮ ስዊዘርላንድ የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ ካሳረፈ ወዲህ የዓለም አቀፍ የብዙኃን መገናኛውን ትኩረት ይዞ ቆይቷል፡፡ ከዚህ ድርጊት በኋላም በሁለቱም ጎራ ያሉ አካላት ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራን በተመለከተ የተለያየ መላምት ትችትና ነቀፋ ሲሰነዝሩበትና ሲሰናዘሩበት ሰንብተዋል፡፡ የሕዝብ ወገን የሆነው ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራን ጀግና ነው አርበኛ ነው ሲለው “መንግሥት” እና ደጋፊዎቹ ደግሞ ከሀዲ ነው ብለውታል፡፡
እነኝህ ሁለቱም አካላት ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራን በየበኩላቸው ያሉትን ለመሆኑ የየራሳቸውን ማስረጃ የሚሏቸውን ነገሮች በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡ የሕዝብ ወገን የሆነው ክፍል ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን ጀግና ነው የሚሉበትን ምክንያት ሲጠቅሱ በአገዛዙ ተማሮ የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቁን፣ ይሄንን ድርጊት ከመፈጸሙ በፊትም ለወያኔ ባለመመቸቱ አሜን ወዴት ባለማለቱ እኅቱ በፌስ ቡክ (በመጽሐፈ ገጽ) በሰጠችው ገለጻ መሠረት ስልኬን ጠልፈውብኛል ይል እንደነበር፣ “መንግሥት” በተለያየ ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶች እየተከሰሰ እንዳለው የተለያዩ ግለሰቦችን በኮምፒውተራቸው (በመቀምራቸው) መሰለያ በመጫን እየሰለለ እንደሆነ እንደሚነገረው ሁሉ ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅንንም የግል ኮምፒውተሩን (መቀምሩን) ካሜራ (በመቅረጸ ምስል) በመጠቀም እያንዳንዱን እንቅስቃሴየን ይከታተሉኛል ይል እንደነበር ኮንፒውተሩን (መቀምሩን) ሲጠቀም ካሜራውን (መቅረጸ ምስሉን) ለመሸፈን ይገደድ እንደነበር፣ መኖሪያ ቤቱንም በሌለሁበት እየገቡ ይፈትሹብኛል ይል እንደነበር፣ የሚያስፈራሩት አካላት እንደነበሩ፣ አልፎም ለቤተሰቦቹ እንደሚሠጋ ባጠቃላይ ደኅንነቱ በሚያሳዝን ሁኔታ አደጋ ላይ የወደቀ እንደነበር፣ ይህ ሁሉ ውክቢያና ማስፈራሪያ እየደረሰበትም ለእነሱ ቡድናዊ የፖለቲካ (እምነተ አሥተዳደር) ፍላጎት ባለመንበርከኩ ባለማደሩ ባለመገዛቱ እንደነበር ይህ ሁኔታ ደግሞ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ችግር መሆኑንና አዲስ ነገር አለመሆኑን በሁሉም ዜጎች ላይ እንደሚደርስ አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው የጋራ ችግር መሆኑን ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን ግን እንደ ብዙዎቻችን ሁሉ በእነዚህ ግፎች ሁሉ ተንበርክኮ ባለመሸነፉና አሻፈረኝ ብሎ እራሱን ነጻ በማውጣቱ ለዚህ ለደረሰበት ሰላም ለሚነሳ ውክቢያ እጅ አለመስጠቱን በመጥቀስ ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን ጀግና እንደሆነ ያረጋግጣሉ፡፡
“መንግሥት” እና ደጋፊዎቹ ደግሞ ምንም እንኳን እስከአሁን ከቦታው በተገኘው መረጃ መሠረት ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን የፖለቲካ ጥገኝነት እንዳቀረበ በግልጽ የታወቀ ጉዳይ ሆኖ ያለ ጉዳይ ቢሆንም በማኅበራዊው የብዙኃን መገናኛው የ“መንግሥት” ደጋፊዎች የሆኑቱ የረዳት አብራሪውን የኃይለ መድኅንን ጉዳይ ኢሳትን በመሳሰሉ የብዙኃን መገናኛዎች ፖለቲካዊ ገጽታ ተሰጥቶት በማየታቸው ስሕተት መሆኑን በመኮነን ሲናገሩ ተስተውለዋል፡፡ ማስተዋል ካለመቻላቸው ይሁን የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቅ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ካለማወቃቸው ሊገባኝ አልቻለም፡፡
ጥቂቶት የመንግሥት ደጋፊዎች እና “መንግሥት” ግን ይህ ጉዳይ ምን ማለት እንደሆነ በሚገባ ገብቷቸዋል፡፡ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድም የሠጉት ትርጉም እንዳይወሰድና ስማቸው አሁን ካለበት ደረጃ ይብስ እንዳይጠፋ ያደረጉ መስሏቸው ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን ይህንን እርምጃ በወሰደበት ወቅት በደኅና በትክክለኛ (normal) የአእምሮ ጤና ላይ እንዳልነበረና ሱሰኛም እንደሆነ በዚህም ምክንያት ድርጊቱን እንደፈጸመ በማስረዳት ለመከላከል እየሞከሩ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን ይህ ድርጊታቸው ከድጡ ወደ ማጡ መሆኑን አልተረዱም አልተገነዘቡም፡፡ ድርጊታቸው ፈጽሞ ኃላፊነት የጎደለውና አርቆ ማሰብ የተሳነው፣ አየር መንገዱንም ለከፍተኛ ኪሳራ የሚዳርግ የደነቆረ ማስተባበያ ነው፡፡ ምክንያቱም ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን እንዲህ እንዳሉት ዓይነት ሱሰኛና ሥራውን በትክክል ለመሥራት በማያስችል የመንፈስ ጭንቀትም ሆነ የሥነ ልቡና መታወክ እንዳለበት እየታወቀ ሥራ ላይ በማሠማራት በመቶዎች የሚቆጠሩ ደንበኞቹን ደኅንነት ለአደጋ አጋልጧል የሚል ትርጉም እንደሚያሰጠውና አየር መንገዱ ለደንበኞቹ ደኅንነት የማያስብ የማይገደው የማይጠነቀቅ ኃላፊነት የማይሰማው እንደሆነ ተቆጥሮ ለዘመናት በብዙ ድካም የገነባውን መልካም ስም እንደሚያጠፋው ደንበኞቹንም እንዲያጣ እንደሚያደርገው ያልተረዱና መረዳት የማይችሉ ሰዎች የደነቆረ አርቆ ማሰብ የተሳነው ስም ማጥፋት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ሥራየ ብለው ይህንን ስም ማጥፋት ያደረጉትና እያደረጉም ያሉት ደናቁርት አየር መንገዱ ለሚደርስበት ጉዳትና ኪሳራ ኃላፊነቱን የሚወስዱ ይሆናሉ፡፡
በሌላ በኩል በእርግጥም እንደተባለው ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን የአውሮፕላኑን አቅጣጫ መቀየር ሳያስፈልገው በራሱ በግሉ በፈለገው ሀገር ላይ በሔደበት ጥገኝነት ጠይቆ መቅረት የሚችል ሰው ነበር፡፡ እንደኔ ግምት ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን ይህንን ያደረገበት ምክንያት ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች አሉት፡፡ የአውሮፕላኑን አቅጣጫ ከሮም ወደ ስዊዘርላንድ ማድረጉና ጥገኝነቱን እዚያ መጠየቁ ሲጠይቅም አውሮፕላኑን መያዙ መውሰዱ ምክንያቱ አንደኛው ሽንት ቤት ሲገባ የቆለፈበት ዋናው አብራሪ ጣሊያናዊ በመሆኑ ለሚያቀርበው የፖለቲካ ጥገኝነት በቂም ምክንያት እንቅፋት እንዳይሆነው በመሥጋቱ ሲሆን ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን በሄደበት ቀርቶ ብቻውን መጠየቅ ሲችል ይሄንን ያላገረገበት ምክንያት ጉዳዩ የሱ የግሉ ጉዳይ ሆኖ እንዲቀር ስላልፈለገ፣ ይህ እሱን ያሰቀቀውና ያንገላታው ችግር የሱ ችግር ብቻ አይደለምና አውሮፕላኑን በመውሰድ የኢትዮጵያን ሕዝብ አቤቱታ በአደባባይ አጉልቶ በማሰማት እንዲያቀርብ አድርጎታል፡፡
ይህ ሰው እንደሌሎቻችን ሁሉ ሆዳም ቢሆን ኖሮ የያዘው የሙያና የኑሮ ደረጃ አይደለም በኢትዮጵያ በየትኛውም ሀገር ቢሆን ተንደላቆ ተንቀባሮ መኖር የሚያስችለው ደረጃ ነበረው፡፡ ነገር ግን ልጁ ሰው ነውና፣ ባለ ሕሊና ነውና፣ ጭንቅላት ያለው ዜጋ ነውና፣ አስተዋይ ነውና ሕዝቡ ወገኑ በችጋርና በሰብአዊ መብቶች እጦት እየተሰቃየ እያየ የሚበላውና የሚጠጣው ሊዋጥለት አልችል አለው፡፡ ምቾቱ ሊደላው አልቻለም፡፡ በአፍንጫየ ይውጣ አለ፡፡ አለና ድሎት ያለውን ሕይዎቱን መሥዋዕት አድርጎ በአስደናቂ ብቃትና አፈጻጸም የሕዝብን አቤቱታ በተገቢው ቦታና ሁኔታ ለዓለም ሕዝብ አቀረበ አሰማ፡፡
አዎ ይሄም እውነት ነው ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራ ከሀዲ ነው፡፡ ግፈኛ አገዛዝን አላገለግልም ብሎ የግፍ አገዛዙን ክዷልና፡፡ ይህ አሁን እሱ ያደረገው ሥራ የሰላማዊ ትግል መሐንዲስ የሆነው ጋንዲ ለስኬት የበቃበት የሰላማዊ ትግል አንዱ ዓይነት እርምጃ ነው፡፡ ከተጠቀምንበትና ሁላችንም ከተባበርን የረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅንን አርአያነት ከወሰድን፡፡ ወያኔን በጣት በሚቆጠሩ ቀናት ውስጥ ብቻ እጅ እንዲሰጥ ማድረግ አቅሙን ጨካኝ ጉልበቱን ማሽመድመድ ይቻላል፡፡ እስከመቸ ነው እሽሩሩው? እስከመቸ ነው ትዕግሥቱ? እስከመቸ ነው መቻሉ? መጨረሻ የለውም እንዴ? ልክ የለውም እንዴ? በዚህ ሁኔታ ትውልድ እያለፈ ትውልድ መተካት አለበት እንዴ? ሁሉም ነገር ቢሆን እኮ ልክና መጨረሻ ገደብም አለው፡፡ ትዕግሥታችን እሽሩሩአችን መቻላችን መጨረሻ ገደብና ልክ ካለው ጊዜው አሁን ነው ጊዜው ዛሬ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ የምንጨምራቸው ጊዜያት የሚባክኑ ብቻ ሳይሆኑ ህልውናችንን የሚያስከፍሉ የሚበሉ የሚያጠፉ የጥፋት የመዓት ቀናት ጊዜያት ዘመናት ናቸው፡፡
በተናጠል የሚወሰዱ እርምጃዎች የትም አያደርሱንም፡፡ የዚህን ጀግና እርምጃ ዐይተን አድንቀን መቀመጡ ምንም አይጠቅመንም እሱ ትልቁን እርምጃ ተራምዶ ጀምሮልናል የግድ መከተል ይኖርብና፡፡ ይሄኔ ሀገርን ሕዝብን እራሳችንን ነጻ እናወጣለን፡፡ ነጻ ነጻ ነጻ እንሆናለን እኛም ወግ ይደርሰንና ለሥልጣኔ ሽምጥ እንጋልባለን፡፡ የነጻነት ፍሬዎችን ልማትን፣ ሰላምን፣ አስተማማኝ ደኅንነትን፣ ምቾትን፣ ጤናን፣ ፍቅርን እናጣጥማለን እንኮመኩማለን፡፡ ሥጋትን፣ ፍርሐትን፣ ጭቆናን፣ እንግልትን፣ አፈናን፣ እረገጣን፣ መብት መነፈግን፣ ረሀብን፣ ችጋርን፣ ጉስቁልናን፣ አንገት አስደፊውን አዋራጁን ድህነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ቶሎ እናሰናብታለን እንቀብራለን፡፡ ይህች ሀገር ከራሷ አልፋ ለስንት የሚበቃ ሲሳይ በረከት አላት፡፡ ሕዝብ የተቸገረው የተራበው የሚጠማው ስለሌለን አይደለም፡፡ በጨካኝና አንባገነን አገዛዙ ተዘግቶብን፣ ተይዞብን፣ ተቆልፎብን፣ ተከልክለን፣ ተነፍገን ነው እንጂ፡፡ እውነት እንዳይመስላቹህ ድሆች አይደለንም በፍጹም ምንም የሚቸግረን ነገር አልነበረም፡፡
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!\
http://www.goolgule.com/hailemedhin-and … re.me_aL1F
አንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ!!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)
================================
በባህር ዳር ከተማ የታየው ህዝባዊ ተቃውሞበሌሎች የሀገራችን ክፍሎችም ተጠናክሮ ይቀጥላል! ===========================
ከአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ!!!
=========================================
ከጊዜ ወደ ጊዜ አምባገነናዊ የአፈና መዋቅሩን በማጠናከር ለመድብለ ፓርቲ የፖለቲካ ሥርዓት በር መዝጋቱን አጠናክሮ ለብቻው አውራ ፓርቲ ለመሆን እየታተረ ያለው የኢህአዴግ መንግሥት ደርግ በውድቀቱ ዋዜማ ወደ ተላበሰው ባህሪ እየተሸጋገረ እንደሆነ ተስተውሏል፡፡
የዚሁን ድርጅታዊ ባህሪ ውርስ በዋነኛነት ከሚያስፈጽሙት የግምባሩ አባል ድርጅቶች አንዱ የሆነው ብአዴን ኢህአዴግ በአማራው ህዝብ ላይ እየፈፀመው ያለው የንቀት እና የማጥላላት ዘመቻም አብይ ተደርገው ሊወሰዱ ከሚችሉ የግንባሩ አፍራሽ ተግባራት በዋነኝነት ሊጠቀስ የሚችል ነው፡፡
የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የብአዴን ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን የክልሉን ህዝብ የናቀ እና ያዋረደ አስነዋሪ ንግግር ካደረጉ በኋላ ከጥፋታቸው ከመታረም ይልቅ በክልሉ ቴሌቭዥን ያንኑ አምባገነናዊ ባህሪያቸውን እንደያዙ የግሌ ብቻ ሳይሆን የድርጅቴ አቋም ነው ሲሉ መመለሳቸውም መላውን የሀገሪቷን ህዝብ ያስቆጣ ተግባር ነው፡፡
ይህንን አስነዋሪ ተግባር የፈጸመውን ብአዴንን ከ70 እስከ 80 ሺህ የሚደርሱ የባህር ዳር ከተማና የአካባቢው ነዋሪዎች ከፓርቲያችን ጎን በመሰለፍ እሁድ የካቲት 16 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም የባህር ዳርን ጎዳና እና አደባባዮች በህዝባዊ ማዕበል ሲያስጨንቁ መዋላቸውም ሰላማዊ ትግሉ የደረሰበትን ሁኔታ በግልፅ የሚያስገነዝብ ነው ማለት ይቻላል፡፡ የኢህአዴግ መንግሥት በአንፃሩ ዛሬም ከስህተቱ ለመማር ያልተዘጋጀ በመሆኑ ይህን የሰፊ ህዝብ ቁጣ በማጣጣል አፋኝ እና ተሳደቢ መሪዎቹን ከጉያው ላለመነጠል እየሞከረ እንደሆነም አስተውለናል፡፡ ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ አንድነት የባህር ዳር እና አካባቢው ነዋሪዎች ላደረጉት ህዝባዊ ትገል ከፍተኛ ክብር እና አድናቆት አለው፡፡ ይህንን ህዝባዊ መሠረታችንን ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር በሁሉም የሀገራችን ክልሎች ተቃውሞው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ልናረጋግጥ እንወዳለን፡፡
የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ይህንን የህዝብ ጥያቄ አለመቀበሉን እየገፋበት በመሆኑም በባህርዳር የታየው ህዝባዊ ተቃውሞ ቤሎች የሀገራችን ክልሎች ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን አቶ አለምነው መኮንን በፍርድ አደባባይ ለማቆም በአጭር ጊዜ ውስጥ ክስ መስርተን ለህዝብ ይፋ እንደምናደርግ እናረጋግጣለን፡፡
በመጨረሻም በዚህ ፈታኝ የትግል ምዕራፍ ፡-
1ኛ. መላው የኢትዮጵያ ህዝብ
2ኛ. በውጭ ሀገር የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን፤ የፓርቲያችን አባላት እና ደጋፊዎች ከጎናችን በመሆን ትግላችንን እንድትደግፉ ጥሪ እናቀርባለን !!!!
———————————-
በባህርዳር የታየው ህዛባዊ መነቃቃትና የትግል ስሜት በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች ይደገማል !!!
—————————–
ድል የህዝብ ነው !!!
የካቲት 20 ቀን 2006 ዓ.ም

ሰማያዊ ከድሬዳዋ ከተማ ህዝብ ጋር ተወያየ
*‹‹ወደ ድሬዳዋ መጥታችሁ ስላነጋገራችሁን ደስ ብሎናል›› የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች፤
ድሬዳዋ፡- ሰማያዊ ፓርቲ (ሰማያዊ) በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችና በፓርቲው የትግል አቅጣጫ ዙሪያ ከድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ጋር የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም በከተማዋ ተገኝቶ ባደረገው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ተወያየ፡፡
በስብሰባው ላይ ፓርቲው እስካሁን ያደረጋቸውን ህዝባዊ ትግሎችና ያስገኛቸውን ዋና ዋና ውጤቶች በድርጅት ጉዳይ ኃላፊው አቶ ጌታነህ ባልቻ በኩል ለነዋሪዎች ገለጻ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም በፓርቲው ሀገራዊ አላማና የፖለቲካ ፕሮግራም ዙሪያ ለከተማዋ ነዋሪዎቹ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡
‹‹ወደ ድሬዳዋ ከተማ መጥታችሁ ስላነጋገራችሁን ደስ ብሎናል›› ያሉት የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ‹‹ምርጫ ሲደርስ ብቻ ወደ እኛ የመምጣቱን የቆየ ልምድ ሰብራችሁ ከአሁኑ ራሳችሁን ስላስተዋወቃችሁንና የትግል አጋራችሁ እንድንሆን ስለፈቀዳችሁ እናመሰግናለን›› ብለዋል፡፡ በስብሰባው ላይ የተገኙ አንድ አስተያየት ሰጭ በድሬዳዋ ከተማ ስላለው ወቅታዊና የፖለቲካ ሁኔታ አንስተው፣ በኢህአዴግ አገዛዝ የድሬዳዋ ነዋሪዎች እየደረሰባቸው ያለውን በደል አጋልጠዋል፡፡
‹‹ኢህአዴግ የማይገባበት ነገር የለም፤ ወዳጅ መስሎ በመሐላችን እየገባ ያጣላናል፡፡ ኢህአዴግ ክፉ መንግስት ነው፡፡ እንኳን መጣችሁልን እንጂ አብረናችሁ እንታገላለን፤ ለነጻነታችን ለመታገል ሞትን አንፈራም›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
በድሬዳዋው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ከህዝቡ በርካታ ጥያቄና አስተያየቶች የተሰነዘሩ ሲሆን በፓርቲው ከፍተኛ አመራሮችም ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡ የድሬዳዋ ነዋሪዎች መሬትን፣ ብሄር ብሄረሰብን፣ ሰንደቅ አላማን፣ የታሰሩ ጋዜጠኞችንና ፖለቲከኞችን፣ ምርጫ-2007ን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የውህደት አጀንዳን እና ሌሎች በርካታ አንኳር ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡
የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በተለይ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት በተመለከተ ‹‹በኢትዮጵያ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዳሉ እንገነዘባለን፡፡ ነገር ግን ፓርቲያችን በግለሰብ ነጻነትና መብት ያምናል፡፡ ምክንያቱም የግለሰብ መብት ከተከበረ የቡድን መብትም አብሮ እንደሚከበር እናውቃለን፡፡ እስኪ ለአብነት የግለሰብ መብት ተከብሮ የቡድን መብት የማይከበርበት ሁኔታ ካለ እናንሳ…የለም፡፡ ስለዚህ ትኩረታችን በግለሰብ መብት መከበር ከሆነ የቡድን የሚባሉ መብቶችም አብረው መከበራቸው እሙን ነው›› በማለት አስረድተዋል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ ‹ሞደሬት ሊብራሊዝም› አይዶሎጅን እንደሚያራምድ የተናገሩት ሊቀመንበሩ፣ የመሬትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ከዚህ መነሻነት የተቃኙ እንደሚሆኑ ጠቅሰዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ‹‹ሰማያዊ አብሮ በመስራትና በትብብር ያምናል፡፡ ነገር ግን ሁሌም ምርጫ ሲደርስ እንደሚደረገው በሩጫ ወደ ውህደት ለመግባት አንፈልግም፡፡ ካለፉት የሌሎች ተሞክሮዎች ብዙ ተምረናል፡፡›› ብለዋል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ ድሬዳዋ በነበረው ቆይታ በዚያው የከፈተውን ቢሮና የአካባቢውን መዋቅር የማስተዋወቅና የማጠናከር ስራም ሰርቷል፡፡ ፓርቲው በሌሎች ከተሞችም ተመሳሳይ ስራ መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል፡፡
ትግሉን ይቀላቀሉ ኪሚሊዮኖች አንዱ ይሁኑ ! እንዴት ካሉ የሚከተለዉን ያንብቡ
======================================
የባህር ዳር ሰልፍ በአስደናቂ ሁኔታ በሰላም ተጠናቋል። ሕዝቡ ከፍተኛ አፈናን ተቋቁሞ፣ ፍርሃትን አዉልቆ የነጻነትን ደዉል አውጇል። ሕዝብ በባህር ዳር ተናግሯል። በዚህ በባህር ዳር ሰልፍ፣ መኢአድ እና አንድነት ሰላማዊ ሰልፍ ስለጠሩ ብቻ አይደለም ሕዝብ የተሰባሰበው። ዉስጥ ዉስጡን ከፍተኛ ድርጅታዊ ሥራ ስለተሰራ፣ ሕዝቡን በወረዳና በቀበሌ ደረጃ ማንቀሳቀስ ስለተቻለ ነው። ድርጅቶች (መኢአድ፣ አድንነት እና ትብብር) በተናጥል ሳይሆን በትብብርና አብሮ በመስራት ስለመሩት ነዉ።
ይህ የባህር ዳር ሰልፍ በየቤታችን ትልቅ ደስታን እንደፈጠረ ይገባናል። ዜጎች በድፍረትና በነጻነት ድምጻቸዉን ሲያሰሙ የመሰለ ደስታ የለም። ሁላችንም ተደስተናል፣ በባህር ዳር ሕዝብም ኮርተናል።
የባህር ዳሩ ሰልፍ ግን ጅማሬ እንጂ ፍጻሜ መሆን የለበትም። ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች እየተደጋገሙ፣ በጥራትና በብቃት፣ በመቀሌ፣ በአዋሳ፣ በድሬደዋ፣ በጂማ፣ በጎንደር፣ በአዲስ አበባ በመሳሰሉ ሌሎች ከተሞች መደረግ አለባቸው። የነጻነት፣ የሰላም፣ የኢትዮጵያዊነት እሳት መቀጣጠል አለበት።
አንድነት/መኢአድ በፊታቸው ከፍተኛ ሥራ አለባቸው። ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። በባህር ዳር የታየዉን አይነት ሥራ ለመስራት ትልቅ ወጭ አለው። ኢትዮጵያዊ ሁሉ ቀበቶዉን እንዲታጠቅ፣ ትግሉን እንዲቀላቀል፣ የድርሻዉን እንዲወጣ ያስፈልጋል። ከአሁን በኋላ ወደ ኃላ መመለስ የለም። ሰላማዊ በሆነ መንገድ፣ በባህር ዳር እንደተደረገዉ፣ በአገራችን ግዛቶች ሁሉ ሕዝቡን ማደራጀትና ማንቀሳቀስ ያስፈልጋል፤ የግድ ነው። ይቻላልምም።
በባህር ዳር ሁኔታዎች ስለተመቻቹ አልነበረም። የፖለቲካ ምህዳሩ ስለተከፈተ አልነበረም። የመኢአድ እና አንድነት አባላት፣ ደጋፊዎች፣ ታስረዋል፣ ተዋክበዋል ከሥራ ተባረዋል፣ የግድያ ዛቻ ደርሶባቸዋል። ትልቅ ዋጋ ከፍለዋል፤ እየከፈሉም ነዉ። ነገር ግን የተዘጋዉን በር በትግላቸው አስከፍተው ነዉ በባህር ዳር እንዳየነው ሕዝቡን ያንቀሳቀሱት።
በአገር ቤት ያለን ምሁራን፣ ተማሪዎች፣ ሴቶች ፣ ወንዶች ፣ ወጣቶች አረጋዉያን፣ ክርስቲያኑ ፣ ሙስሊሙ፣ ትግሬው፣ አማራዉ፣ ኦሮሞዉ፣ ቅልቅሉ … ሁሉን ኢትዮጵያዊ ከአንድነት ጎን እንዲሰለፍ እንጠይቃለን። አንድነት ጠመንጃ እንደ ሌሎች ጠመንጃ የለውም። አንድነት የፈረንጆችን ጥቅም እንደሚያስጠብቁት እንደ ሌሎች የዉጭ መንግስታት ድጋፍ የለዉም። የአንድነት ኃይልና መተማመኛ ሕዝብ ብቻ ነው።
እንግዲህ
1. አገር ቤት ያለን በአካባቢያችን ወዳሉ የአንድነት ጽ/ቤቶች፣ በዉጭ ደግሞ ያለን የአንድነት ድጋፍ ድርጅቶች በመሄድ እንዴት መርዳትና መተባበር እንዳለብን እንጠይቅ።
2. http://www.andinet.org/ በመሄድ በክሬዲት ካርድ ወይንም ፔይ ፓል የገንዘብ ድጋፍ እናድርግ።
3. የሚሊየነም ድምጽ ለነጻነት ፌስ ቡክ እና የፍኖተ ነጻነት ገጽ ላይክ በማድረግ እየተሰሩ ያሉትን እንከታተል። መልእክቶችን በማስተላለፍ የቅስቀሳቅዎች አካል እንሁን::
https://www.facebook.com/FinoteNestanet https://www.facebook.com/MillionsOfVoicesForFreedomUdj
4. አገር ዉስጥ ላለን በአካባቢያችን የአንድነት መዋቅር ከሌለ፣ በዉጭ ደግሞ የድጋፍ ድርጅት ከሌሉ፣ ሁለት ሶስት ፣ ሆነን እራሳችንን አደራጅተን፣ ፓርቲዉን ፓርቲዉን በማሳወቅ ትግሉን እንቀላቀል። የድጋፍ ድርጅቶች ከሌሉ፣ የአገር ቤቱን ትግሉ የሚደገፉ ሌሎች የሲቪክ ድርጅቶች ሊኖሩ ስለሚችሉ፣ በነርሱ በኩል ድጋፍ ማድረግ ይቻላል።
5. በግለሰብ ደረጃም በጽሁፍ፣ በሃሳብ መርዳት ከፈለግን [email protected] በሚለው ኢሜል አድራሻ ያሳውቁን።
ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ አንድ ወቅት እንዳለችዉ፣ ፀሐይ ለኢትዮጵያ ወጥቶላታል። ከአሁን በኋላ አይጨልምም::


አደዋ ደረሰ ጎጠኞች ከፋቸው
ኢትዮጵያዊነት ሊተረክባቸው ።
የአድዋ ድል ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የማንነታችን መሰረትና የህልውናችንም መገለጫ ነው፡፡ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ብቻም ሳይሆን ለመላው የጥቁር ህዝብ የነፃነት ተምሳሌትና የአርነት መስታዎትም ጭምር ነው፡፡ የሰው ልጅ በቆዳው ቀለም ምክንያት መዋረድም ሆነ ማነስ እንደሌለበት፣ ጥቁር ህዝብ በአፈጣጠሩም ሆነ በአስተሳሰቡ ‘ልዩና ድንቅ ነን’ ብለው ከሚኮፈሱት ነጮች ያላነሰ ማንነት እንዳለው፣ ካልነኩት ተንኮል የማይሸርብ ሲነካ ግን በማንነቱ ላይ የማይደራደር ድንቅ ፍጥረት መሆኑ የታየበት ድል ነው የአድዋ ድል፡፡
ዛሬ አለም አብዝታ ስለሰው ልጆች እኩልነት እየሰበከችና በዚህም ስም አያሌ መድረኮችን እያዘጋጀች ቢሆንም ገና ብዙ ያልተፈቱ ተያያዥ ችግሮች እያየን መሆኑ የሚካድ ሃቅ አይደለም፡፡ የአድዋ ድል ግን ገና ያኔ ስልጣኔ ባላደገበት፣ የሰው ልጅ አስተሳሰቡ ባልጎለመሰበት፣ እንኳን ነጮች ጥቁሮች ራሳቸው ባርነት የመፈጠራቸው ዕጣ ፈንታ፣ የአርባ ቀን እድላቸው እንደሆነ አስበው ባርነታቸውን ከእንባቸው ጋር እያጣጣሙ በነበሩበት በዚያ ዘመን… የጥቁርነት ትርጉሙን ፣ የሃገርና ህዝብን ሉአላዊ ክብርን ለመላው አለም በወሬ ሳይሆን በተግባር ያሳየ ዘመን አይሽሬ የመመኪያችን መድረክ ነው የአድዋ ድል፡፡

እነ እስከማውቀው ድረስ የትዊተር አካውንታቸው አልተጠለፈም። ምንሊክ ሳልሳዊ
ሰሞኑን በብአደን ውስጥ የተነሳውን የአቶ አለምነህ እና ተያያዥ የለውጥ ጉዳይ እና የአይሮፕላን ጠለፋ/ እገታ በኢሕአደግ አባላት የተነሱትን እና ሕዝቡ የሚያሰማውን ጉምጉምታ አቅጣጫ ለመቀየር የተደረገ ወያነያዊ የማዘናጊያ ስልት ነው።
ኢትዮጵያውያን ባህላችንን እና የወንጀለኛ መቅጫ ህጋችንን ከድሮም ስለምናውቀው ወይዘሮዋ የተነፈሱ አሊያም የጻፉት ራሳቸው መሆናቸውን በቂ ማረጋገጫዎች ከመኖራቸውም በላይ እነው ራሰ በትዊተር ገጻቸው ላይ መልስ ከመስጠት አንስቶ በግል በመልእክት ሳናግረቸው ያመኑበት መሆኑን አረጋግጠው ሳለ የወያነ መንግስት የሳቸውን ጉዳይ መነጋገሪያ አድርጎ የሰሞኑን ህዝባዊ ጥያቀዎችን በመሸፋፈን ለማዘናጊያነት የተጠቀሙበት ስልት ነው። የትዊተር ገጻቸውን ራሳቸው ዘጉት እንጂ አልተጠለፈም ሃሰት ነው።
ፌስቡክ እና ትዊተር በፍጹም ሊጠለፉ የማይችሉ ሶሻል ኔትወርኮች ናቸው ፣ ያልተማረውን ሰው ያታሉት …https (Hypertext Transfer Protocol Secure ደዲኬቲቭ ሰርቨር የሚባለው ሰርቨር ያላቸው ሲሆን በማይክሮ ሰከን ሁሉንም መረጃዎች ገልብጦ ለማውጣት ፈጣን የሆነ ቅልጥፍና ያለው እና ጠላፊዎች ሲመጡ ለሰኩሪቲ ሲስተም ፕሮቶኮል ኢንጂኒየር የሚጠቁም ኢለመንት ወይንም ኮድ አላቸው ስለዚህ ምንም ነገር ሊደረግ የማይችል ነገር ነው ፣…….. እንደ እኛ አይነት ዌብ ሳይት ያላቸው ሰዎች ቢሉ ይቻላል :: ምክንያቱም የምንጠቀመው የተከራየ ሰርቨር ሲሆን የፈለገ ደዲኬቲቭ ሰርቨር ብንጠቀም በአንድ ሰርቨር ውስጥ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ዌብ ሳይቶች ስለሚሞሉበት ለማመልከት ይቸግረዋል …የነ ትውተር እና ፌስቡክ ግን እራሱን የቻለ ሰርቨር ያላቸው ትልቅ ድርጅት ነው ፣እንደዚያማ ቢሆን ኖሮ እንደ እነ ቢቢሲ እና ሲኤን ኤን ያሉ የመረጃ ድርጅቶች ኤፍቢአይን ጨምሮ ትውተር ባልተጠቀሙ ነበር !
አይሮፕላን ተጠለፈ የአቶ አለምነህ ድምጽ ተጠለፈ የወይዘሮ ዘነቡ አካውንት ተጠለፈ ….. አሁን የቀረው ማነው…? ? ? ምንሊክ ሳልሳዊ

ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ በእያንዳንዱ የሕወሓት የልደት በዓል ማለትም የካቲት 11 በዋነኝነት ከሚከበርበት የትግራይ ርዕሰ ከተማ መቐለ ተገኝተው በሚያደርጉት ንግግር በዓሉን ሁሌም ድምቀት ይሰጡት ነበር፡፡
ሥልጣን ላይ ያለው ኢሕአዴግ ዋነኛ መሥራች የሆነውን ሕወሓት የረጅም ጊዜ ጠንካራ ሊቀመንበሩን ያጣው ባለፈው ዓመት በዓሉን ከማክበሩ ስድስት ወራት በፊት ነበር፡፡
አቶ መለስ ለመጀመርያ ጊዜ ያልተገኙበት 38ኛው በዓል ግን እሳቸውን በመዘከር በሐዘን ድባብ ነበር ያለፈው፡፡ ተተኪያቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝም በወቅቱ በበዓሉ ላይ ቢገኙም፣ በአቶ መለስ መሪነት እዚህ ደርሷል ያሉት ሥርዓት ከፍተኛውን መስዋዕትነት ከፍሎበታል ካሉት ከትግራይ ሕዝብ ጋር እጅና ጓንት በመሆን እንደሚሠሩ፣ ‹‹የማፅናኛ›› ንግግር አድርገው ነበር የተመለሱት፡፡
ዘንድሮ የተከበረው 39ኛው የሕወሓት በዓል ግን ባለፈው ዓመት በሐዘን ድባብ ያለፈውን በዓል ያካካሰ በሚመስል ሁኔታ እጅግ ደማቅ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ላለፉት 22 ዓመታት ሥልጣን ላይ የቆየው ኢሕአዴግ ዋነኛ አካል የሆነው ሕወሓት፣ በሚቀጥለው አርባኛ የልደት ዓመቱ በበለጠ በደመቀ ሁኔታ ያከብራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የዘንድሮው ግን ከተገመተው በላይ ደማቅ ሆኖ ተከብሯል፡፡
የሕወሓት በዓል እጅግ እንዲደምቅ ምክንያት የሆነው ባለፉት ሁለት ዓመታት የተለየ የሠራው ነገር ኖሮ አይመስልም፡፡ እንዲያውም ድርጅቱ ጠንካራ መሪውን በሞት ካጣ በኋላ መረጋጋት ተስኖት በውስጥ መከፋፈልና እርስ በርስ በመወነጃጀል ማሳለፉ ይነገራል፡፡ የድርጅቱ ሌሎች አንጋፋ መሪዎችም ያላግባብ ከአመራር መሸኘቱ ከፍተኛ ትችት ያስተናገደበት ዓመት ነበር፡፡ በሌሎች ዓመታት እንደተለመደው የድርጅቱን የትጥቅ ትግል ታሪክ በሚያወሱ ዘጋቢ ፊልሞች፣ የጦር ውሎዎችና ሥልጣን ላይ በቆየባቸው ጊዜያት ያስመዘገበው ልማት በመንግሥት ሚዲያ ታጅቦ ነው በዓሉ የተከበረው፡፡
ይህ ጽሑፍ ዋና ዓላማው የሕወሓትን የልደት በዓል ወይም የድርጅቱን የትጥቅ ትግልና መስዋዕትነት ለመተረክ አይደለም፡፡ የዘንድሮው የድርጅቱ የልደት በዓል እንዲደምቅ ምክንያት የሆነው የተለየ አንድ ውጫዊ የሆነን አጋጣሚ መነሻ በማድረግ አገራዊ አንድምታውን መዳሰስ ነው፡፡
‹‹ሴሲና›› ታሪካዊው አውሮፕላን
ወጣት ተስፋሁን አምባቸው በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ካፌ ውስጥ ሻይ ቡና እያለ በኢቲቪ በቀጥታ ሲተላለፍ የዋለውን የድርጅቱን በዓል ሲመለከት ነበር፡፡ የድርጅቱ ሊቀመንበርም ሆኑ ሌሎች አመራሮች ያደረጓቸው ንግግሮች ምን እንደሚሉ ቀድሞ እንደሚያውቅ ሰው ለመስማት እምብዛም የጓጓ አልነበረም፡፡ የተስፋሁንን ቀልብ መሳብ የጀመረው የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሐሰን አል በሽር መኖራቸውን ሲመለከት ነው፡፡ ለረጅም ጊዜ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የቅርብ ወዳጅ እንደበሩ የሚነገርላቸው ፕሬዚዳንት አል በሽር፣ በዚህ የሕወሓት በዓል መገኘታቸው ብቻ አይደለም የተስፋሁንን ቀልብ የሳበው፡፡
የተስፋሁንና የጓደኞቹ ወሬ የሚያጠነጥነው በሕወሓት የልደት በዓል ላይ አልነበረም፡፡ ፕሬዚዳንት አል በሽር ኢትዮጵያ መጥተው በሕወሓት በዓል ላይ ሲገኙ ለመጀመርያ ጊዜ ነው፡፡ የግሉ ሚዲያ እምብዛም ትኩረት የሰጠው ባይመስልም፣ የመንግሥትን ሚዲያ ለተከታተሉ አብዛኛዎቹ ሰዎች አነጋጋሪ የሆነው የእነተስፋሁን ጓደኞችንም ቀልብ የሳበው የፕሬዚዳንቱ መገኘት ነው፡፡ የብዙ ኢትዮጵያውያን ዜጐችን ቀልብ የሳበው ግን የፕሬዚዳንቱ መገኘት ብቻ በራሱ አይመስልም፡፡ በግንቦት 1983 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር መለስና አቶ ሥዩም መስፍን፣ አቶ ተፈራ ዋልዋና ሌሎች የሕወሓት ኢሕአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ድርጅቱ ባካሄደው ጦርነት ደርግን አሸንፎ ወደ አራት ኪሎ ታላቁ ቤተ መንግሥት ሲገባ በአንድ አውሮፕላን ነበር የመጡት፡፡ ከሱዳን ካርቱም ወደ አዲስ አበባ የመጡበት አውሮፕላን አብራሪ የነበሩት ቀድሞ በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር ጄኔራል አልፋታህ በበዓሉ ላይ ተገኝተዋል፡፡ በወቅቱ በጉዞ ላይ እያሉ የዚህ ታሪካዊ አውሮፕላን አንደኛው ሞተር ከሥራ ውጪ በመሆኑ፣ አደጋ አፋፍ ላይ ሆነው በወቅቱ ታጋይ ሥዩም መስፍን ከአብራሪውና ከድርጅቱ ሊቀመንበር ታጋይ መለስ ዜናዊ የተለዋወጡዋቸው ‹‹ኑዛዜ›› የሚመስሉ ምልልሶች ነበሩ፡፡ በተለይ አቶ ሥዩም፣ ‹‹ይኼ ሕዝብ ዕድለኛ አይደለም ማለት ነው፣ እኔ ነኝ ጉድ ያደረጉኩህ፡፡ ጓዶች በመኪና እንድንመጣ አስጠንቅቀውን ሳለ በፕሌን እንድንመጣ በማድረጌ አዝናለሁ፤›› ሲሉ፣ ታጋይ መለስ በበኩላቸው በፈገግታ፣ ‹‹አንተ ባስክብንኮ›› ማለታቸውን አቶ ሥዩም አውስተዋል፡፡ በወቅቱ በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር የነበሩት አብራሪው ጄኔራል አልፋታህም ከታጋዮች ጋር የቅርብ ወዳጅ የነበሩ በመሆናቸው ትውስታቸውን እንዲህ በማለት ነበር የገለጹት፡፡
‹‹አንድ የማስታውሰው ነገር ቢኖር የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ፣ አል በሽርና እኔ ተቀምጠን እየተወያየን ነበር፡፡ ለብዙ ጊዜያት የሕወሓት የትግሉ አካል መሆኔን ተመልክቶ አምባሳደር እንድሆን ሲጠይቀኝ እኔም አምባሳደር ሆንኩኝ፡፡ እኔ የአውሮፕላን አብራሪ ብቻ ሳልሆን ደርግንም የምታገል አካል ነበርኩ፡፡ የዚህ ታላቅ ታሪክ አካል መሆኔ እጅግ ያስደስታል፤›› ነበር ያሉት፡፡
‹‹ሴሲና›› በመባል የሚታወቀውና ከአስፈሪው አደጋ ያመለጠው ይህ ታሪካዊ አውሮፕላን ለኢትዮጵያ በስጦታ የተበረከተ ሲሆን፣ በመቐለው የሰማዕታት ሙዚየም ውስጥ እንዲቀመጥ ተወስኗል፡፡
የፕሬዚዳንት ሐሰን አል በሽር ንግግርም ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስና ሕወሓት ጋር የነበራቸው የቀረበ ወዳጅነት፣ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን መልካም ግንኙነት በተመለከተ ነው፡፡ በበዓሉ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ለታዳሚዎቻቸው ከፍ ባለ ድምፀት ያለው ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ ድርጅታቸው በኢትዮጵያ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገቡን፣ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ጠንሳሽነት የተመሠረተው ድርጅት ራዕይ ተግባራዊ መሆኑን ነበር የተናገሩት፡፡ ‹‹የሰማዕታት ደም ሊካስ የሚችለው ሰማዕታት የወደቁባቸው ተራሮች፣ ሜዳውና ሸንተረሩ በልማት ሲሸፈኑ ነው፤›› ብለዋል፡፡ የሕወሓት ሊቀመንበር አቶ ዓባይ ወልዱም ንግግር አድርገዋል፡፡
ከጉርብትናም በላይ ወዳጅነት
የፕሬዚዳንት አል በሽርና በኢትዮጵያ የቀድሞ አምባሳደር ጄኔራል አልፋታህ በዚሁ የሕወሓት በዓል መገኘታቸው ትልቅ ቀልብ የሳበበት ምክንያት የሁለቱ አገሮች መልካም ጉርብትና ብቻም አይደለም፡፡
በቅርቡ ኢትዮጵያውያንና ግብፃውያንን እያጨቃጨቀ ያለው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ከጉብኝቱ ጀርባ ያለ ይመስላል፡፡ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ የተነሳውን አለመግባባት ለመፍታት ሱዳንን ጨምሮ ላለፈው አንድ ዓመት የተካሄደው የሦስትዮሽ ውይይት ትልቅ ሥፍራ የተሰጠው ነበር፡፡ በሦስተኛው ውይይት ሒደቱ ያለውጤት ቢበተንም፣ የግብፅ ታሪካዊ ወዳጅ የሆነችው ሱዳን በድርድር ሒደት ውስጥ ፊቷን ወደ ኢትዮጵያ ማዞሯ ለኢትዮጵያ ትልቅ ስጦታ ነበር፡፡
ቀደም ሲል ግብፅና ሱዳን በዓባይ ላይ የተዋዋሉዋቸው አግላይ ስምምነቶች (1929 እና 1959) የውኃውን ክፍፍል ለሁለቱም አገሮች ማድረጋቸውና ሁሌም የሱዳን አቋም ከግብፅ ጋር የተገናኘ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሁለቱም አገሮች ከተፋሰስ አባል አገሮች በስድስቱ የተፈረመውን የአሥር ዓመት የውይይት ውጤት በሆነው የዓባይ ፍትሐዊ የውኃ አጠቃቀም ማዕቀፍ (CFA) በእንቢተኝነት ፀንተው ነበር፡፡ ከዚያም በተጨማሪ አንዳንድ የአሜሪካ የስለላ መረጃዎች እንዳጋለጡት፣ በግብፅና በሱዳን ባለሥልጣናት መካከል በተደረጉ ሚስጥራዊ ግንኙነቶች፣ ግብፅ ግድቡን ለማውደም የሱዳንን ግዛት ለመጠቀም ዕቅድ ነበራት፡፡ የአሁኑ የሱዳን አቋም መለወጥ ግን በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል የነበረው የኃይልና የዲፕሎማሲ ሚዛን እንዲቀለበስ ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ፡፡
በአሁኑ ወቅት የግብፅና የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት አንዳንድ የተካረሩ ቃላት እየተለዋወጡ ሲሆን፣ ከፕሬዚዳንት አል በሽር ጋር በጋራ በመቐለ በሕወሓት በዓል ታዳሚ የነበሩት የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የግብፅን አካሄድ በመቃወም ግልጽ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አሊ ካርቲ ለሱዳን ትልቁ ሚዲያ ሱዳን ትሪቢዩን እንደተናገሩት፣ የግብፅ ባለሥልጣናት በሚዲያ እየሰጡዋቸው ያሉት ተንኳሽ መግለጫዎች ሁኔታውን የሚያባብሱ ናቸው፡፡ ‹‹የሱዳን አቋም ግልጽ ነው፡፡ በግብፅ ባለሥልጣናት በቀውሱ ላይ ሱዳን በምትጫወተው አወንታዊ ሚና እንዲጠቀሙ ነግረናቸዋል፡፡ የቀድሞ ገዥዎቻቸው ግትርነት አላሠራ ብሏቸዋል፤›› ብለዋል፡፡ ራሳቸው ፕሬዚዳንት አል በሽርም ቀደም ሲል በግልጽ ቋንቋ የታላቁን ዓባይ ግድብ መገንባት እንደሚደግፉ ተናግረው ነበር፡፡
ሱዳን የአቋም ለውጥ ለምን አደረገች?
የዓባይን ውዝግብ በተመለከተ ቀደም ሲል በሱዳንና በግብፅ መካከል የነበረው ግንኙነት መዳሰስ የዛሬውን ለመገንዘብ ይረዳል፡፡ በተለይ በቅኝ ግዛት ዘመን የተፈረሙትን ሁለቱን ስምምነቶች መመልከቱ ተገቢ ነው፡፡ እ.ኤ.አ. በ1929 በታላቋ ብሪታንያና በግብፅ መካከል የተደረገ ነው፡፡ ለሱዳን የተሰጠ የውኃ መጠን አራት ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ሲሆን፣ የተቀረው 48 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ ደግሞ ለግብፅ ነበር፡፡ በስምምነቱ መሠረት ግብፅ በፈለገችው ጊዜ በወንዙ ላይ ግድብ የመሥራትና የመጠቀም ሥልጣን ያላት በመሆኑ፣ ሱዳን ይህንን ለማድረግ የግብፅን ፈቃድ እንደትጠይቅ ትገደዳለች፡፡
ሁለተኛው ስምምነት፣ እ.ኤ.አ. በ1959 የተፈጸመ ነው፡፡ ይህ በሱዳንና በግብፅ መካከል የተደረገ ስምምነት ነበር፡፡ በቀድሞው የውኃ ስምምነት ያልታወቀ የውኃ መጠን በመገኘቱ በዚህ ስምምነት የሱዳንን ድርሻ ወደ 18.5 መቶኛ ኪዩቢክ ሜትር ከፍ እንዲል የተደረገ ቢሆንም፣ ሱዳኖች ውኃውን የመጠቀም መብታቸው በግብፅ በጎ ፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ መረዌ የተባለው ግድብ ከአራት ዓመታት በፊት ተገንብቶ የተጠናቀቀ ቢሆንም፣ በውኃ ለመሙላት እስካሁን ሱዳኖች ፈቃድ አላገኙም፡፡ ሮዜሬስ የተባለውን ግድብ የውኃ መጠኑን ከፍ ለማድረግ ጠይቀውም እስካሁን አልተፈቀደላቸውም፡፡
የውኃው ዋነኛ ምንጭ የሆነችው ኢትዮጵያን ጨምሮ የላይኛው ተፋሰስ አገሮችን ያገለሉ እነዚህ ስምምነቶች ውኃውን በግብፅና በሱዳን መካከል የሚከፋፍሉ ቢሆንም፣ ሱዳን በስምምነቱ ተጠቃሚ እንዳልሆነች ትገነዘባለች፡፡ ግብፆች በሱዳኖች ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሕይወት ውስጥ ያላቸው ተፅዕኖ ከፍተኛ ነበረ ቢሆንም፣ ዛሬ ዛሬ እየቀነሰ መጥቷል፡፡ በሚኒስትሮች ደረጃ ሳይቀር እጃቸው ረዘም ያለ እንደነበረ ቢታወቅም፣ በአሁኑ ወቅት ጫናው እየተሸረሸረ መጥቷል፡፡
በመስኖና የውኃ ሚኒስትር የወሰንና የወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈቅአህመድ ነጋሽ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ሱዳኖች በዓባይ ውኃ ጥቅማቸው የሚጠበቅላቸው ከግብፆች ጋር በማበራቸው ሳይሆን ከላይኛው ተፋሰስ አገሮች ጋር በመተባበራው መሆኑን በተግባር ታዝበዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የተከዜ ግድብ በመገደቡ ምክንያት ባልተለመደ ሁኔታ በርካታ ገበሬዎች በመስኖ ከፍተኛ ልማት እያከናወኑ መሆናቸው ይነገራል፡፡ ቀደም ሲል በጎርፍ ይጥለቀለቁ እንደነበር፣ አሁን ከዚህ ችግር መገላገላቸውና በደለል ይሞላ የነበረው ወንዛቸው አሁን ከዚህ ችግር ወጥቶ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ሲሰጥ ማየታቸው ለሱዳኖች አቋም መለወጥ ዋና ምክንየት መሆኑን ኃላፊው ይናገራሉ፡፡
ዶ/ር ያሲር መሐመድ በሱዳን የውኃ ጥናት ተቋም ዳይሬክተር ናቸው፡፡ በኔዘርላንድስ ደግሞ የዩኔስኮ የውኃ ትምህርት ተቋም የውኃ ሀብት ተጋባዥ መምህር ናቸው፡፡ ከሦስት ወራት በፊት በመቐለ በተካሄደው አንድ የውኃ ኤክስፖርቶች ቴክኒካዊ ምክክር ላይ ተሳታፊ ነበሩ፡፡ በወቅቱ በአጋጣሚ አግኝተናቸው ስለጉዳዩ አጭር ቆይታ አድርገን ነበር፡፡ እሳቸው እንደሚሉት፣ የግብፅ ሥጋት ኢትዮጵያ በምትገነባው ግድብ የውኃው መጠን እንዳይቀንስ አይደለም፡፡ የዓባይ ወንዝ ተፋሰስ አገሮች በወንዙ ሊለማ የሚችል መሬት ተደምሮ አንድ ላይ የሱዳንን ያህል አይሆንም፡፡ እስካሁን ግን ሱዳን በከፍተኛ ደረጃ የመስኖ ልማት እምብዛም ተጠቃሚ አይደለችም፡፡ የወደፊት ዕቅዷ ግን ይኼንን ውኃ ጥቅም ላይ በማዋል ዓለም አቀፍ ኢንቨስተሮችን መሳብ ነው፡፡ እንደሳቸው እምነት፣ ግብፅ የምትጎዳው እዚህ ላይ ነው፡፡ የውኃውም መጠን የሚቀንሰው ሱዳን ውኃውን ለመስኖ መጠቀም የጀመረች ቀን ነው፡፡
ዶ/ር ያሲር መሐመድ እንደሚሉት፣ ግብፆች ግልጽ ባያወጡትም በኢትዮጵያ ላይ የሚያሳዩት ተቃውሞ በተዘዋዋሪ በዋናነት በሱዳን ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ ‹‹የውክልና ጦርነት ነው፡፡ እውነተኛ ችግራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ሳይሆን ከሱዳን ጋር ነው፡፡ ውዝግቡን ግን ለፖለቲካ ፍጆታ ሲሉ ከኢትዮጵያ ጋር እንዲሆን ይመርጣሉ፤›› ብለዋል፡፡
የታላቁ የዓባይ ግድብ መገንባትን የሚደግፉት የውኃ ተመራማሪው እንደሚሉት፣ የሱዳን መንግሥት ሰፊ ለም መሬቱን ተጠቅሞ በመስኖ ማልማት የሚችለው ኢትዮጵያ እንዲህ ዓይነት ግድቦችን ከሠራች ብቻ ነው፡፡ ‹‹ግብፆችም ሱዳኖችም ይህንን ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ብዙ ኢትዮጵያውያን ግን ይህንን የሚገነዘቡ አይመስለኝም፤›› ብለዋል፡፡ እንደ እሳቸው እምነት፣ ሱዳንና ኢትዮጵያ በወንዙ ላይ ስትራቴጂካዊ የሆነ ትብብር ማድረግ አለባቸው፡፡
የሱዳኑ የውኃ ምሁር አስተያየት ማረጋገጫ የሚመስል አንድ መረጃ ተገኝቷል፡፡ የተከዜ ግድብ ከተሠራ በኋላ የደለል መሙላት በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ ሲሆን፣ የሱዳኑ አትባራ ወንዝ የውኃ መጠን በአሥር እጥፍ መጨመሩ የሱዳን መንግሥት ይፋ አድርጓል፡፡
ሱዳኖች ያሳዩት የአቋም ለውጥ ከራሳቸው ተጨባጭ ጥቅም በመነሳት መሆኑን ለሪፖርተር የገለጹት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ የሱዳን ፕሬዚዳንት በበዓሉ ላይ መገኘት ጥልቅ የሆነ ወዳጅነት መመሥረቱ አመላካች ነው ብለዋል፡፡ ‹‹መምጣታቸውም ለአገራችንና ለሕዝባችን ያላቸውን ጥልቅ ድጋፍና ከበሬታ የሚያሳይ ነው፤›› ይላሉ፡፡ የሁለቱም አገሮች ወዳጅነት ምን ደረጃ እንደደረሰ አመላካች መሆኑን በማስረዳት፡፡
ሱዳንና ኢትዮጵያ ትናንትና
የሱዳንና ኢትዮጵያ ግንኙነት ታሪክ ከሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች የተለየ አይመስልም፡፡ አንዱ የሌላውን አማፂ ቡድን የመደገፍ አዝማሚያዎች ያሳዩ ነበር፡፡ በደርግ ጊዜ ኢትዮጵያ በቅርቡ ነፃነታቸውን ላገኙት የደቡብ ሱዳን ኃይሎች (SPLM) እና በተቀረው የሰሜን ሱዳን አካባቢ የሚንቀሳቀሱ አማፂዎችን ትደግፍ ነበር፡፡ ሱዳን በበኩሏ፣ አሁን ሥልጣን ላይ ላለው ሕወሓት፣ ለኤርትራ ነፃ አውጪ ድርጅትና በሕወሓት አሸናፊነት ለተበታተነው ለኢዲዩ ከፍተኛ ወታደራዊና የትጥቅ ድጋፍ ታደርግ እንደነበር ይታወቃል፡፡
የሁለቱም አገሮች ጐርባጣ ግንኙነት የተቀየረው ኢሕአዴግ ወደ ሥልጣን ሲመጣ ነበር፡፡ ባለፉት ቅርብ ዓመታትከ ኢትዮጵያ ጋር ያላት መልካም ጉርብትና በቀዳሚነት የሚነሳ ነው፡፡ የሱዳን ገዢ ፓርቲ ብሔራዊ እስላማዊ ግንባር (National Islamic Front – NIF) እና የሱዳኑ ፕሬዚዳንት አል በሽር ከኤርትራ እስላማዊ ኃይሎችና ከኤርትራ መንግሥት በተለይ ደግሞ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ያላቸው አንዴ ሞቅ ሌላ ጊዜ ቀዝቀዝ የሚለው ግንኙነት፣ የኢትዮ ሱዳን ትብብር ዘላቂነትን ሁሌም ጥርጣሬ ላይ የሚጥለው ነበር፡፡
በሁለቱም አገሮች ከፍተኛ የጋራ የድንበር ኮሚሽን አማካይነት በቅርቡ የድንበር መካለል ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ መንግሥት ትችቶችን ባይቀበልም፣ የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን እየተሰጠ ነው በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ ሲሰማ ሰንብቷል፡፡ ያም ሆኖ ግን ላለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት ሁለቱም አገሮች በመልካም ጉርብትና ላይ የተመሠረተ ግንኙነት አላቸው፡፡ ለዚህም ኢትዮጵያ በሁለቱም ሱዳኖች መካከል በተከሰተው የድንበር ጦርነት ዋና ገለልተኛ ሸምጋይ ሆና የተገኘች ሲሆን፣ በተመድ ጥላ ሥርም ቢሆን አቢዬ ላይ ከሠፈረው ሰላም አስከባሪ ኃይል አብዛኞቹ ከኢትዮጵያ የተውጣጡ ወታደሮች ይገኙበታል፡፡
ደቡብ ሱዳኖች ነፃነታቸውን በሕዝበ ውሳኔ ከማግኘታቸው ትንሽ ቀደም ብሎ፣ በዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት የክስ ዋራንት ተቆርጦባቸው የነበረው ፕሬዚዳንት አል በሽር የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ድጋፍ ያስፈልጋቸው ነበር፡፡ በወቅቱ አኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተሰሚነታቸው ከፍ ብሎ የነበረው አቶ መለስ፣ ፕሬዚዳንት አል በሽርን ከዚህ ክስ ነፃ እንዲሆኑ በአፍሪካ ኅብረት አማካይነት ያደረጉት የተሳካ ጥረት ለሱዳን ፕሬዚዳንትና መንግሥት ትልቅ እፎይታ የሰጠ ነበር፡፡
ከግርማ አንድሪያስ (ኔዘርላንድ -ኣምስተርዳም)
”…ልብ በሉ ልጆች የምነግራችሁን ኣድምጡ። ችሎታችሁ ምንም ጥርጥር የለውም። መሮጥ ከጀመራችሁ – ካልጨረሳችሁ አንደማታቆሙ ኣውቃለሁ። የምትሮጡት አንደባለፈው ጃፓን -ቶኪዮ ላይ ኣይደለም። ኣይደለም። የኣሁኑውድድራችሁ ጣሊያን ጣሊያን ጣሊያን ጣሊያን ሮም ነው። ነው። ነው። ጣሊያኖች ችሎታችሁን ስለማይችሉት ሊተኖኮሎኣችሁ ይችላሉ። በውድድር ላይ ሆናችሁ ቢመቱዋችሁ አንኩዋን መልስ ኣትስጡ። ለማዘናጋት ለማሰናከልና ስህተት አንድትሰሩ ስለሚፈልጉ የሚጠቀሙበት ተንኮላችው ተንኮላችው ተንኮላችው ተንኮላችው ተንኮላችው ነውና ነውና ነውና ኣደራ ኣደራ ኣደራ !… ይድነቃቸው ተሰማ ነበሩ። ነበሩ። አነ ኣበበ ቢቂላን ወደ ሮም ለሩጫ ከመውሰዳቸው በፊት በዝግጅት ላይ የተናገሩት። (ድሮ መጽሔት ላይ ቃል በቃል ባይሆንም በግርድፉያስታወስኩትን ያሰፈርኩት ነው።)
ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)
‹‹…የውሳኔ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት ተጠናቀቀ፡፡ የባሕር መዝገቡም ተዘጋ፡፡ …ቀፋፊ ምሽት ነበር፡፡ በእያንዳንዳችንም ፊት ፈገግታ አይታይም፡፡ ከአዳራሹ ሳንርቅ ከራሳችን ጋር ብቻ እየተነጋገርን በሃሳብም ርቀን እየሄድን አመሸን፡፡ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ወደ አዳራሹ እንድንገባ ተነገረን፡፡ በፍጥነት ገብተን ቦታችንን ያዝን፡፡ ሊቀ-መናብርቱም ቦታቸውን ያዙ፡፡ ‹ዛሬ ስለወሰድነው እርምጃ ለጦር አዛዦች ማሳወቁ ይበጃል በማለት ጠርተናቸው እዚሁ ይገኛሉ› ብለው ወደ አጃቢዎቻቸው ፊታቸውን ዘወር አድርገው ‹አስገቧቸው!› የሚል ትዕዛዝ ሻለቃ መንግስቱ ሰጡ፡፡ ጄነራል ጃጋማ ኬሎ፣ ጄነራል ግዛው በላይነህ፣ ጄነራል ታደሰ ገብሬ፣ ጄነራል ወርቁ መኮንን ተከታትለው ገቡ…››
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ወደ ትዝታ ዓለም ወደ ትዝታ ጊዜ በትዝታ ሰረገላ ልወስዳችሁ ነው። እኔ እንኳ በአጻጻፌ አበባዊ ቋንቋ አልወድድም። ለማንኛውም ግን አብረን እንድንነጉድ እጋብዛችኋለሁ። ወደ እንግሊዝ አገር! 1953 እ.አ.አ ወደ አንድ የለንደን ስብሰባ አዳራሽ እንገባለን። እንግዶች የነፃነት ታጋዮች ወደ አዳራሹ ከመግባታቸው በፊት የዌስት ኢንዲስ ተወላጅና የዓለም አቀፍ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ንቅናቄ መሪ የሆነው ጆርጅ ፓድሞን በአዳራሹ ውስጥ ፕሪዚደሙን […]
በአርሲ ዞን ሂጦሳ ወረዳ እየተገነባዉና በቅርቡ የሚመቀ የአኖሌ ሃዉልት አብሮት የተገነባዉን ቤተመዘክር ጨምሮ ሃያ ሚሊዮን ብር የወጣበት መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መረጃ ያመለክታል።
የተቆረጠ ጡት በተቆረ ጡት በተቆረጠ እጅ ላይ የሚያሳየዉ ሃዉልት ከተቃዋሚዉ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት አሉታዊ አስተያዬት ቀርቦበታል።
የመኢአድ ፕሬዚደንት አቶ አበባዉ መሃሪ “አጼ ሚኒሊክ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ ታላቅ ስራ የሰሩ መሪ መሆናቸዉን ወደ ጎን ትተዉ መጥፎ ስም በመስጠት ያልተደረገዉን ተደረገ በማለትመኮንኑ ተገቢ አይመስለኝም። የኦሮሞ ሕዝብ ታላቅ ታሪክ ያለዉ ሕዝብ ነዉ፥ አጼ ሚኒልክ በኦሮሞ ላይ ይህን አድገዋል፤” ብሎ መናገር ሕዝቡን ማሳነስ ነዉ ሲሉ አስተያየታቸዉን አክለዋል። “ታሪኩ አልተፈጸመምና የኦሮሞ ተወላጆች የሃዉልቱ መቆም ስህተት…
የአንድነት ፓርቲ ከመኢአድ እና ትብብር ተብሎ ከሚታወቀዉ የአሥር ድርጅቶ ስብስብ ጋር በመሆን የ118 ኛውን የአድዋ ድል መታሰቦያ እንደሚያከብሩ፣ የአንድምነት ልሳን ፍኖት ነጻነት ገለጸ። በአሉ የሚከበረዉ ወደ 3.7 ኪሎሜትር ከቀበና የአንድነት ጽ/ቤት እስከ ጊዮርጊስ የሚኒሊክ አደባባይ በመጓዝ ሲሆን፣ በይነቱ የመጀመሪያዉ አከባበር ሊሆን እንደሚችል ይጠበቃል። የፍኖትን ዘገባ እንደሚከተለው ያንብቡ ፍኖት – 118ኛውን የአድዋ ድል በዓል 3 ፓርቲዎች […]
ካለፈዉ ወር ወር ጀምሮ አስራ አምስት ሺህ የሚሆኑ ደቡብ ሱዳናዉያን የእርስ በርስ ጦርነት ሸሽተተዉ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ሲሆን በከባድ ረዥም ጉዞ ምክንያት በረሃብና በዉሃ ጥም በእጅጉ የተጎዱ መሆናቸዉን ዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ መስርሪያ ቤት ታዉቋል።
የድርጅቱ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ከፍተኛ የስራ ሃላፊ Gabriel Okeitoi እንዳብራሩት ጀልባና ተሽከርካሪ በመጠቀም ወደ አንድ መቶ አስራ ሰባት ኪሎ ሜትሮች ወይንም ስልሳ ሰባት ማይሎች ርቀት ሰደተኞቹን ልክቾር ወደሚባለዉ አዲስ የስደተኞች ካምፕ አጓጉዟል።
ብዙዎቹ ከደቡብ ሱዳን ማላካል ተነስተዉ እስከ አኮቦና ፓጋግ ድረስ ረጅም ርቀት ለአያሌ ቀናት በእግራቸዉ በሚያደርጉት ጉዞ የተጠሙ የተራቡ ሰለሆኑ ከፍተኛ የሰዉነት ፈሳሽ መቀነሰም እንደሚታይባቸዉ የተናገሩት…
News, Ethiopians in America, Americana, Democracy and Women and Family
ባለንበት ምዕተ ዓመት የምድራችን የሙቀት መጠን ከ 2 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ እንዳያሻቅብ ሥጋት መኖሩ ቢታወቅም፤ ባንዳንድ የተፈጥሮ ክሥተቶች ሳቢያ ክፍተት ሊፈጠር ሚችልበትን ፤ ባጭሩ የሙቀቱ መጠን የሚቀነስበትን ሁኔታ ፣ አነስተኛ የእሳተ ገሞራ
የዩክሬይን ሁኔታ ገና አልሰከነም፤ በሀገሪቱ ደቡብ ምስራቃዊ ከፊል በክሩሚያ ልሣነ-ምድር ፤ በሩሲያ ተጻራሪና ደጋፊ ዩክሬናውያን ዘንድ ግጭት እንደነበረ ተነግሯል። በኪቭ፤ ከሥልጣን የተወገዱትን ፕሬዚዳንት ቪክቶር ያኑኮቪችን የተካው አዲስ አስተዳደር፤ በእርሳቸው የአስተዳደር ወቅት የነበሩ የተቋሞችን መርኆዎች በመሻር ላይ ነው።
ዘረኝነትንና ያለመቻቻል ስሜትን ፣ ጀርመን መታገል እንደሚኖርባት የአውሮፓ ም/ቤት ፀረ ዘረኝነት ኮሚሽን አሳሰበ። ኮሚሽኑ ትናንት ይፋ ባደረገው ዘገባ፤ በተለይ ወንጀለኞችን በመያዝና ጥፋተኞችን ተከታትሎ ተገቢውን ቅጣት በመስጠት ረገድ ድክመት ይታያል
ባለፈው ቅዳሜ በነፃ የተለቀቁት የቀድሞዋ የዩክሬን ጠቅላይ ሚኒስትር ዩልያ ቲሞሼንኮ ለፕሬዝዳንትነት የመወዳደር እቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል ። ከእስር እንደተለቀቁ ወደ ክየቩ የነፃነት አደባባይ በመሄድ ደስታቸውን እዚያ ከተሰበበሰው ከ100 ሺህ ከሚበልጥ ህዝብ ጋር የተጋሩት ቲሞሼንኮ በውዝግቡ የተገደሉት ሰዎች ጉዳይ እንዲጣራም ጠይቀዋል ።
በርዋንዳ የጎሣ ጭፍጨፋ ወቅት የግድያ ትዕዛዝ ሰጥተዋል ተብለው የተጠረጠሩት የቀድሞው የወንጌላዊቷ ጴንጠቆስጤ ቤተ ክርስትያን ቄስ ዣን ቦስኮ ዊኪንዴ ችሎት ዛሬ በመዲናይቱ ኪጋሊ ተጀመረ።
ከሚከናወኑት የልማት ሥራዎች መካከል በአፋር ክልል የሰመራ ከተማና አካባቢው እንዲሁም በሎግያ የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት እና የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ግንባታ ይገኙበታል ።
የባህር ዳር ሰልፍ በአስደናቂ ሁኔታ በሰላም ተጠናቋል። ሕዝቡ ከፍተኛ አፈናን ተቋቁሞ፣ ፍርሃትን አዉልቆ የነጻነትን ደዉል አውጇል። ሕዝብ በባህር ዳር ተናግሯል። በዚህ በባህር ዳር ሰልፍ፣ መኢአድ እና አንድነት ሰላማዊ ሰልፍ ስለጠሩ ብቻ አይደለም ሕዝብ የተሰባሰበው። ዉስጥ ዉስጡን ከፍተኛ ድርጅታዊ ሥራ ስለተሰራ፣ ሕዝቡን በወረዳና በቀበሌ ደረጃ ማንቀሳቀስ ስለተቻለ ነው። ድርጅቶች (መኢአድ፣ አድንነት እና ትብብር) በተናጥል ሳይሆን በትብብርና […]
‹‹መላዋ አፍሪካ በአውሮጳ መንግሥታት ቅርምት የምትጠናቀቅበት ቀን ቀርቧል፤ አውሮጳውያኑ በአሜሪካ ያሳኩትን የዘር የበላይነት በአፍሪካ ለመድገም ተዘጋጅተዋል፡፡ በአሜሪካ ቀይ ሕንዶችን በማስወገድ ለራሳቸው ዝርያ መኖሪያ መፍጠር የቻሉበትን ብቃት በአፍሪካ ለመድገም የጥቁር አፍሪካ ዝርያዎችን በቅርቡ ማጥፋት ይጀምራሉ፡፡››
![]() |
| ከብርሃኔ ንጉሤ ትዊተር ገጽ የተወሰደ |
‹‹ድሉ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የአፍሪካን መፃኢ ዕድል የወሰነ ነበር፡፡ በዚህም የአድዋ ጦርነት የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካም ጭምር ነው፡፡ ምክንያቱም በቀጣይ መቶ ዓመታት የአውሮፓ የበላይነት እና አገዛዝ በአፍሪካ አክትሟል፡፡ የዘመናዊት አፍሪካ የሉዓላዊነት መሠረት ድንጋይ የጣለው አድዋ ላይ ነበር፡፡››
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከጥቂት ዓመታት በፊት ተራራው ላይ ይቆማል ተብሎ የነበረውን ግዙፍ ‹ላንድማርክ› በተመለከተ ምን ደረጃ ደርሶ እንደነበር ያሬድ ሹመቴን ጠይቄው ነበር፡፡ ቢዘገይ እንኳን፣እስከ120ኛው በዓል ድረስ እንደሚጠናቀቅ ያለውን መረጃ አጣቅሶ ተስፋ ሰጥቶኛል፡፡
ባህር ዳር እና አዲስ አበባ የከተመውን ሕወሓት መራሹ የብአዴን ስብሰባ ውጥረት ነግሶበታል።በቅርቡ ከፍተኛ የብኣዲን አመራሮች የፖለቲካ ጉዳዮች ሰለባ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል::
ምንሊክ ሳልሳዊ:- የአቶ አለምነህ መኮንን ንግግር አጣብቂኝ ውስጥ የከተተው ብኣዴን ለሕወሓት ግን አዳዲስ ታማኝ አሽከሮችን ለመሾም በሩን ወለል አድርጎ ከፍቶላታል::ከአዲስ አበባ እና ከባህር ዳር የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚያመላክቱት የብኣዲን አመራሮች የፖለቲካ ጉዳዮች ሰለባ እንደሚሆኑ እና እነሱንም በአዳዲስ የሕወሓት ታማኞች ለመተካት መታሰቡን ተጠቁሟል:: የአቶ አለምነህን መኮንን ንግግርን ተከትሎ እና የተቃዋሚዎችን እንቅስቃሴና ጫና አያይዞ እንዲሁም ስለ ሙስና እና የፖለቲክ መዳከም ያነሳው የብኣዴን ስብሰባ በከፍተኛ መፈራራት እና የራስን መብት እስከመጠራጠር በሚያደርስ መልኩ እንደተካሄደ ተሰምቷል::
ውስጣዊ የፖለቲካ አፈና እንዳለ የጠቆመው ይህ የብኣዴን ስብሰባ እንዲሁም በከፍተኛ ፍራቻ እና ውጥረት የተደረገ ሲሆን የአለመተማመን ስሜቶች የመጠራጠር ሁኔታዎች እንደነበሩበት ከአመራሮቹ የመጣ መረጃ ይጠቁማል::በስፋት ሂስ እና ግለሂስ ይሰጥበታል ቢባልም ከዚህ ቀደም አቶ መላኩ እንዳሉት የሕወሓት ስውር እጆች እንዳይዘረጉ የሚል ፍራቻ በአመራሮቹ መካከል አለመተማመን ነግሶ ታይቷል::በአቶ አለምነህ ንግግር ዙሪያ ሕወሓት የራሱን እርምጃ ካልወሰደ አመራሮች በዚህ ጉዳይ ላይ ቢናገሩ ሁኔታዎች ተዘናግተው ወደ ሙስና ተለውጠው ወደ ፖለቲካዊ አፈና ስለሚያመሩ መጠንቀቅ ይበጃል የሚሉ የውስጥ አስተያየቶች በግል እንደነበሩ በምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ተጠቁሟል::
በአመራሮቹ መካከል ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ከታች ካድሬዎች የተሰበሰቡ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ዙሪያ ውይይት መደረጉን ተጠቁሟል::ከአቶ አለምነህ ንግግር ጀምሮ እስከ የፖለቲካ የበላይነት ….አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ተጠይቀዋል:: የድርጅታችን አሰራር ኢዲሞክራሲያዊ ነው በውጪ የሚሰበከው ፕሮፓጋንዳ እና በገህድ የምንየው የተለይየ ነው:: የአቶ አለምነህ ንግግር የኢሕኣዴግ የበላይ ሹማምንቶች ለአማራው ብሄር ያላቸው ጥላቻ ውጤት ነው:: ብኣዼን ከሕወሓት እኩል ታግሏል ማንም ከማንም የነሰ መስዋትነት አልነበረውም ሁሉም ለነጻነት በሚል እኩል መስእዋት ነው የሆነው ቁልፍ የበላይነት ያለው በአንድ ብሄር ስር ነው አማራ ላይ ጫናው በርትቷል የሚሉ እና ተመሳሳይ ጥያቄዎች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን አቶ አለምነህ የተናገሩት ንግግርን ተከትሎ በብኣዴን አመራሮች እና ካድሬዎች መካከል ከፍተኛ የጥርስ መነካከስ ብሶበት የታየ ስብሰባ ነበር::ድርጅቱን የማይፈልጉ አባላት ራሳቸውን ሊይሰንብቱ ይችላሉ ሁኔታዎችን በሂደት እንፈታዋለን ሲሉ አቶ በረከት ተደምጠዋል::ስብሰባው የቀጠለ ሲሆን አስተይየቶች እና ጠንካራ ውይይቶች በቀጣይነት ይካሄዳሉ መፍራቱ እና መጠራጠሩ ለማቆም እንሞክራለን ሲሉ መረጃውን የሰጡ አባላት ተናግረዋል::
ከአቶ አለምነህ ጉዳይ ጎን ለጎን በጥብቅ የቀረበው ጉዳይ እና ምናልባት የብኣዴኝ መኮንኖች አቀረቡት የተባለው ተብሎ የሚጠረጠረው የብኣዴን አባላት በሙሰኞች ላይ የተጀመረውን ዘመቻ ተከትሎ በወታደራዊው ክፍል ፓርቲን እና መንግስትን ደንብን እና ህግን መደበቂያ በማድረግ ከፍተኛ ህገወጥነት እና ሙሰኝነት ይፈጸማል የሚል አቤቱታ ለድርጅታቸው ጥቆማ ቢያቀርቡን ተሰሚነት ሊያገኙ አለመቻላቸው እያበሳጫቸው መሆኑን ገልጸዋል:: የሙስናውን ክፍል በግንባር ቀደምትነት የሚመሩት የሕወሓት ጄኔራሎች ናቸው ስለዚህ በእነሱ ላይ ምርመራ ሰፋ ያለ ምርመራ ይደረግ የሚሉ ጥቆማዎች አበርትተን ብናቀርብም ምንም አይነት መልስ ልናገኝ አልቻልንም ይልቅ የሕወሓት ስውር እጆች የፖለቲካ ባላንጣዎቻቸውን በማፈን ላይ መሆናቸውን እና በቅርቡም ከፍተኛ የብኣዴን አመራሮች ወደ ፍርድ ቤት በሙሰኝነት ስም እንደሚቀርቡ ተናግረዋል::ይህ በእንዲህ እንዳለም አስቸኳይ ስብሰባ በባህር ዳር ሲጠራ በአዲስ አበባ ደግሞ የብኣዼን (አማራ)የጦር መኮንኖችን የሰበሰበ እና ለመጪው ግምገማ መንገድ ይጠርጋል የሚል ምስጢርዊ ግምገም እንደተካሄደ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ጠቁመዋል::ይህ የአማራ መኮንኖችን ብቻ ለይቶ የሰበሰበው ጉዳይ በብኣዴን ውስጥ የተፈጠረን አጣብቂኝ ያስደነገጣቸው እና የአማራው የጦር መኮንኖች ውስጥዊ ችግሮች እንዳይፈጥሩ ለማስፈራራት እና ሽብር ለመፍጠር እርስ በእርስ እንዳይተማመኑ ለማድረግ የታቀደ ሴራ ነው ሲሉ መረጃውን ያቀበሉ መኮንኖች ተደምጠውል:: በቡድን በቡድን ተከፋፍለን የምንወያይበት ጉዳይ ይኖራል የተባለ ቢሆንም ስብሰባው እንደጀመረ በአማራው መኮንኖች ላይ ጫና የሚፈጥሩ እና የሚያሸብሩ መልእክቶች ተደምጠዋል:: በተለያዩ ምክንያቶች ሰራዊቱን እንድትለቁ ማድረግ ይቻላል እስከማለት የደረሰ ዛቻ እንደተደሰኮረ ተመልክቷል::የመከላከያ ሰርዊት ውስጥ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ዝርዝሩን እመለስበታለሁ ::ምንሊክ ሳልሳዊ