በአርሲ ዞን አኖሌ አካባቢ የተሰራዉ ሃዉልት ቂም ቀስቃሽ ነዉ ተበለ፥ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በበኩሉ የተፈጸሙ ድርጊቶች እንዳይደገሙ ለማስታወስ ነዉ ሲል አስተባበለ።
በአርሲ ዞን ሂጦሳ ወረዳ እየተገነባዉና በቅርቡ የሚመቀ የአኖሌ ሃዉልት አብሮት የተገነባዉን ቤተመዘክር ጨምሮ ሃያ ሚሊዮን ብር የወጣበት መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መረጃ ያመለክታል።
የተቆረጠ ጡት በተቆረ ጡት በተቆረጠ እጅ ላይ የሚያሳየዉ ሃዉልት ከተቃዋሚዉ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት አሉታዊ አስተያዬት ቀርቦበታል።
የመኢአድ ፕሬዚደንት አቶ አበባዉ መሃሪ “አጼ ሚኒሊክ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ ታላቅ ስራ የሰሩ መሪ መሆናቸዉን ወደ ጎን ትተዉ መጥፎ ስም በመስጠት ያልተደረገዉን ተደረገ በማለትመኮንኑ ተገቢ አይመስለኝም። የኦሮሞ ሕዝብ ታላቅ ታሪክ ያለዉ ሕዝብ ነዉ፥ አጼ ሚኒልክ በኦሮሞ ላይ ይህን አድገዋል፤” ብሎ መናገር ሕዝቡን ማሳነስ ነዉ ሲሉ አስተያየታቸዉን አክለዋል። “ታሪኩ አልተፈጸመምና የኦሮሞ ተወላጆች የሃዉልቱ መቆም ስህተት…