የቦምብ ጥቃት በሶማሊያ DW Amharic February 27, 2014 Tagged with Amharic, amharic news, Ethiopia, ethiopian news in amharic, Ethiopians, News in Amharic ሶማሊያ ዋና ከተማ መቅዲሾ ውስጥ ዛሬ በደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃት ከ10 የሚበልጡ ሰዎች ህይወት ጠፋ ። ሰባት ሰዎች ደግሞ ቆሰሉ ። በሶማሊያ ብሔራዊ የፀጥታ ዋና መስሪያ ቤት አቅራቢያ በደረሰው በዚሁ ጥቃት ከተገደሉት መካከል ሰላማዊ ሰዎችና የደህንነት ኃይሎችም ይገኙበታል ። ለጥቃቱ አሸባብ ሃላፊነቱን ወስዷል ።