ነሃሴ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምእራብ አርማጭሆ ዞን በአብርሃ ጅራ ከተማ ነዋሪ የሆነው የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወጣት አባይ ዘውዱ ዛሬ ሰኞ ጠዋት በአካባቢው ከሚገኘው የመከላከያ ካምፕ በመጡ መቶአለቃ ተስፋየ ስዩምና መቶ አለቃ ቅባቱ  ተዋጅ በተባሉ የመከላከያ  የመረጃ እና የደህንነት ሰራተኞች ከታሰረ በሁዋላ የአካባቢው ህዝብ ባደረገው ጫና ለመፈታት ችሎአል። ወጣት አባይ በኤርትራ …

ነሃሴ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመኢአድ የሰሜን ጎንደር የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ የሆኑት አቶ ዘመነ ምህረት ለኢሳት እንደገለጹት የደቡብ ጎንደር ዋና ጸሃፊ አቶ ጥላሁን አድማሴ ባለፈው ቅዳሜ 8 ሰአት ላይ በ6 ፌደራል ፖሊሶች ታፍኖ መወሰዱን ገልጸዋል። ፖሊሶቹ መሳሪያ አለው በሚል ፍትሻ አድርገው የነበረ ቢሆንም ምንም አለመገኘታቸውንና አቶ ጥላሁንን ወዳልታወቀ ቦታ መውሰዳቸውን  አቶ ዘመኑ ገልጸዋል። …

ነሃሴ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሁሉም የኦሮምያ ክልሎች  በሚገኙ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች፣ የግብርና ዋና እና ምክትል ሃላፊዎች፣ የሴቶች ጽ/ቤት ፣ መሬት ጥበቃ ፣ ሲቪል ሰርቪስ እና መልካም አስተዳደር ፣ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ፣ ውሃና ማእድን፣ ገጠር መንገድ ፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ጽ/ቤት ፣ ገንዘብና ኢኮኖሚ ፣  ትምህርት/ጽ/ቤት፣ እና  የወጣቶችና ስፖርት ሃላፊዎች ከነገ ጀምሮ ለአስቸኳይ …

ነሃሴ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኮንዶምኒየም ቤቶች በወቅቱ ዕጣ ወጥቶ ለሕብረሰቡ ማስተላለፍ ካለመቻሉ ጋር ተያይዞ ቆጣቢዎች በመሰላቸትና ተስፋ በመቁረጥ ከፕሮግራሙ ራሳቸውን እያገለሉ መሆኑ ተሰምቷል። የአዲስአበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ዋና ስራአስኪያጅ አቶ መስፍን መንግሥቱ ሰዎች በተለያየ ምክንያት እየለቀቁ መሆኑን አምነው ነገር ግን ከተስፋ መቀረጥ ጋር እንደማይገናኝ ለመንግሥት መገናኝ ብዙሃን አረጋግጠዋል፡፡ እንደእሳቸው ገለጻ በድጋሚ ከተመዘገቡ …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በሶማሊያ የአፍሪቃ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ AMISOM ከሁለት ዓመታት በኋላ ወታደሮቹን ከሶማሊያ ለማዉጣት እቅድ እንዳለዉ ተነገረ። በተመድ የጸጥታዉ ምክር ቤት መርሃግብር መሠረት AMISOM በሶማሊያ የሚኖረዉ የሰላም ማስከበር ኃላፊነት በተጠቀሰዉ ዓመት ያበቃል።

የኤቦላ ወረርሽኝ የመነጋገሪያ ርዕስ በሆነባት ናይጄሪያ ፤ ከበሽታው ሌላ ህዝቧን ያሳሰበው ሌላም ነገር አለ። ይህም በሀገሪቱ ስር የሰደደው አማፂው እስላማዊ ቡድን ቦኮ ሀራም ነው። አማፂያኑ በተቆጣጠሩት ሰሜን ናይጄሪያ እስላማዊ ካሊፋት መመሥረታቸውን በገለፁበት በአሁኑ ወቅት በሌላ በኩል ታግተው የተወሰዱትን ሴት ተማሪዎች ለማስመለስ ትግል ተይዟል።

ሊቢያ የስድስት ሚሊን የሚገመተዉ ሕዝቧ የነብስ ወከፍ ገቢ ከአስራ-አራት ሺሕ ዶላር በላይ ነበር።ከዘጠና በመቶ የሚበልጥ ሕዝቧ የተማረ ነበር። በነዳጅ ላይ የተመሠረተዉ ምጣኔ ሐብቷ በአመት በአማካይ 10,5 ከመቶ ያድግ ነበር።ዛሬ ሐብት ንብረት-የሕዝቧ ቅምጥል ኑሮ አይደለም አንድ ሐገርነቷም ያዉ ነበር ነዉ።

በመጪው ዓመት በታህሳስ ወር ሥራውን እንደሚጀምር የተነገረው «የምስራቅ አፍሪቃ ፈጣን ጣልቃ ገብ ጦር » ሰላም እና መረጋጋት በራቃቸው የምስራቅ አፍሪቃ ሃገራት ወታደሮችን እያሰማራ አፋጣኝ ርዳታ ለመስጠት አቅዷል።

ብርቱ ወዳጀ እስከዳር Esky አንች የብርቱም ብርቱ ሰው መሆንሽን አውቃለሁ ። ከባህሬኑ የስደት ኑሮ ግብግብ ፣ ለወገን ድጋፍ ማድረግና ባህልን ከማስተዋወቅ አልፈሽ ተርፈሽ ” የጥቁር እንግዳን” ፊልም ለዛሬ ያበቃሽ ድንቅ እህታችን ነሽ ። ፊልሙን በቡድን ከማዘጋጀት እስከመተወን ባደረግሽው ድንቅ ጥረት በባህሬን ምድር የክብር ቀይ የክብር ምንጣፍ አስነጥፈሽ ስማችን በረከሰበት የአረብ ሃገር ፊልምሽን ስታስመርቂ የኮራሁት ኩራት […]

(አጭር ልብወለድ)

 ማትያስ ከተማ (ወለላዬ ከስዊድን)

እግሬ እንደተነፋች ዶሮ ጢል ብሎ አብጧል። ጫማዬን ወጥሮት ማቆም እያቃተኝ ነው። ይኼን አሳዛኝ ሁኔታ ኃላፊው ማወቅ አለበት። ሄድኹኝ ምንም ሳልናገር ጫማዬን አውልቄ አሳየሁት። እሱም ምንም ሳይናገር ወደ ጓዳ ገብቶ ተመለሰ። የፕላስቲክ ነጠላ ጫማ አንጠልጥሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ኢትዮጵያ ዉስጥ ግን አደጋ የሚያስከትሉ መድሐኒቶች ሳይቀሩ በየመድሐኒት መደብሩ እንደልብ መሸጣቸዉ በሠፊዉ እየተነገረ ነዉ።በተለይ አስቸኳይ የፅንስ መከላከያ እንክብል (Emergency Ccontraceptive pill)ን ካንድ ጊዜ በላይ ከሐኪም ትዕዛዝ ዉጪ መዉሰድ በተጠቃሚዎቹ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያስከትል ባለሙያዎች እየመከሩ ነዉ።

ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
—–

“ዐጀም” በዐረብኛ “ባዕድ የሆነ” ማለት ነው፡፡ ይህም በጥንተ ማንነቱ ዐረባዊ ያልሆነ ህዝብና ሀገር ለማለት ነው፡፡ ይሁንና “ዐጀም” የሚለው ቃል በዐረብኛ ስነ-ጽሑፍ ውስጥ በስፋት የሚያገለግለው ዐረብ ያልሆኑ ሙስሊሞችን ለማመልከት ነው፡፡ በዚህም መሰረት ኢራን፣ ቱርክ፣ ኢንዶኔዚያ፣ ማሌዥያ፣ ፓኪስታን፣ ባንግላዲሽ ወዘተ…. ዐጀም ናቸው ማለት ነው፡፡ 

   ወደ ሀገራችን ስንመጣ ግን “ዐጀም” ሌላ ተልዕኮ ያለው ቃል ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ይህም የሀገራችን ቋንቋዎች በዐረብኛ ሆሄያት የሚጻፉበትን ስርዓተ-ፊደላት ነው የሚያመለክተው፡፡ ኦሮምኛ፣ አማርኛ፣ አፋርኛና ሶማሊኛ በዚህ ስርዓተ ጽሑፍ ይጻፉ ነበር፡፡ ዛሬም በርካታ የእስልምና ሊቃውንት በዐጀም አጻጻፍ ስርዓት ይጠቀማሉ፡፡ ታዲያ እነዚህ ሁሉ ቋንቋዎች የሚጻፉበት “ስርዓተ ፊደላት” በወል “ዐጀም” ተብለው ቢጠሩም በሚይዟቸው የሆሄያት ብዛት ይለያያሉ፡፡ ይህም ከቋንቋዎቹ የስነ-ድምጽ ባህሪ ጋር በቀጥታ ይዛመዳል፡፡ ለምሳሌ ኦሮምኛ የሚጻፍበት የ“ዐጀም” ስርዓት ሶማሊኛ በሚጻፍበት “ዐጀም” ውስጥ የሌሉ (“ጨ”፣ “ኘ”፣ ጰ የተሰኙትን ድምጾች የሚወክሉ) ሶሰት ፊደላት አሉት፡፡ የአማርኛው ዐጀምም በኦሮምኛው “ዐጀም” ውስጥ የሌሉ ሁለት ፊደላት (“ዠ” እና “ጸ”) አሉት፡፡

    ለመሆኑ የዐጀም አጻጻፍ ስርዓት ሲሰራበት የነበረው እንዴት ነው?….. ትምህርቱስ እንዴት ነበር የሚሰጠው? በልጅነቴ የተማርኩትን የኦሮምኛውን “ዐጀም” እንደምሳሌ ልውሰድና ለማስረዳት ልሞክር፡፡

 *****

   በምስራቁ የኢትዮጵያ ክልል ለረጅም ዘመናት ፊደል የማስጠናት ተግባር ሲፈጽሙ የኖሩት “ቁርኣን ጌይ” የሚባሉ የትምህርት ማዕከላት ናቸው፡፡ በነዚህ ማዕከላት የሚሰጠው ትምህርት ዋነኛ ዓላማ ህጻናት ቅዱስ ቁርኣንን በራሳቸው ብቻ ( ያለምንም ረዳት) የማንበብ ችሎታ እንዲኖራቸው ማድረግ ነው፡፡ በመሆኑም ወደ ቁርኣን ጌይ ለትምህርት የመጣ ተማሪ በቅድሚያ የዐረብኛ ፊደላትን እንዲለይ እና የተማራቸውን ፊደላት መልሶ እንዲጽፍ ይደረጋል፡፡ ከዚያም ወደ ቁርኣን ምንባብ ትምህርት ይሸጋገራል፡፡

   ታዲያ የቁርኣን ጌይ ተማሪ የሚማረው የቁርአን ምንባብ ትምህርትን ብቻ አይደለም፡፡ ከቁርኣን ትምህርት በተጨማሪ የዐቂዳ (ስነ-መለኮት)፣ የፊቂህ (እስላማዊ ድንጋጌ)፣ የሂሳብ እና የኸጥ (የዐረብኛ ፊደላት አጣጣል) ትምህርቶችም ይሰጣሉ፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን በትምህርታቸው ጎበዝ የሆኑ ልጆች እየተመረጡ የ“ዐጀም” ስርዓተ ጽሕፈትን እንዲማሩ ይደረጋል፡፡ የዚህ ስርዓተ ጽሕፈት ዓላማ ተማሪው የአፍ መፍቻ ቋንቋው የሆነውን ኦሮምኛን በዐረብኛ ፊደላት መጻፍ እንዲችል ማድረግ ነው፡፡

    የዐጀም ስርዓተ ፊደላት መነሻ የዐረብኛው የፊደል ገበታ ነው፡፡ በዐረብኛው የፊደል ገበታ ላይ ያሉት ሀያ ስምንት ፊደላት በሙሉ የኦሮምኛው “ዐጀም” አካላት ናቸው፡፡ በተጨማሪም በዐረብኛ ውስጥ የማይገኙ ስድስት የኦሮምኛ ድምጾችን  የሚወክሉ “ውልድ” ፊደላት ተቀርጸው የስርዓተ ጽሑፉ አካላት ተደርገዋል፡፡ በዐረብኛ ውስጥ የሌሉት ስድስት የኦሮምኛ ድምጾች ከዐረብኛ ሆሄያት በተራቡ “ውልድ” ፊደላት ሲወከሉ የሚከተለውን ይመስላሉ፡፡

ዸ/Dh= ڎ

ገ/G= ݞ

ጨ/C= ڟ

ጰ/Ph= ٻ

ኘ/Ny= ٿ

ቸ/Ch= ݜ

  እነዚህ ውልድ ፊደላት የተቀረጹት በድምጽ የሚቀርቧቸውን የዐረብኛ ፊደላት መነሻ በማድረግ ነው፡፡ ለምሳሌ “ገ” በድምጹ ለዐረብኛው “” ይቀርባል፡፡ በመሆኑም በዚሁ ፊደል ላይ ሁለት ነጥቦች ተጨምረው የ“ገ” ወኪል ሆኖ የሚያገለግል ڠ  የሚባል ውልድ ፊደል ተፈጥሯል፡፡

   ከላይ እንደጠቆምኩት የኦሮምኛው የ“ዐጀም” ስርዓተ ፊደላት በዐረብኛው የፊደል ገበታ ላይ የሌሉትንና “ዸገ”፣ “ጨ”፣ “ጰ”፣ “ኘ” እና “ቸ” የተሰኙ ስድስት የኦሮምኛ ድምጾችን የሚወክሉ ውልድ ፊደላትን በመቅረጽ የተፈጠረ ነው፡፡ ታዲያ ተማሪዎች እነዚህን ፊደላት በቀላሉ እንዲያስታውሷቸው ለመርዳት ሲባል የሀረርጌ ዑለማ “ዸጋ ጨጳ ኛቹ” የሚል ዐረፍተ ነገር ፈጥረዋል፡፡ በአማርኛ “የተሰበረ ድንጋይ መብላት” እንደማለት ነው፡፡ በዚህ ዐረፍተ ነገር ውስጥ ያሉት ድምጾች በሙሉ በዐረብኛ ውስጥ የሉም (በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቆይታዬ “ሁሉንም የእንግሊዝኛ ፊደላት የያዘው ዐረፍተ ነገር የትኛው ነው” እየተባልን ስንጠየቅ ከነበረው ፎርሙላ በፊት “ዸጋ ጨጳ ኛቹ”ን ነው የማውቀው)፡፡

     የኦሮምኛው የዐጀም ስርዓተ ፊደላት የኦሮምኛ ተናጋሪ ሙስሊሞች መኖሪያ በሆኑት ሀረርጌ፣ ባሌ፣ አርሲ፣ ጅማ፣ ደቡብ ወሎ (ከሚሴ ዙሪያ) ወዘተ… ይታወቃል፡፡ አንዳንድ ምንጮች “የአሮምኛው ዐጀም አጻጻፍ የተፈጠረው በሀረርጌ ምድር ነው” ይላሉ፡፡ ለዚህም በ19ኛው ክፍለ ዘመን የተጻፉ ልዩ ልዩ ድርሳናትን እንደ ማስረጃ ይጠቅሳሉ፡፡ አንዳንዶች ግን “ዐጀም በወሎ ክፍለ ሀገር ውስጥ ባለው የ“ደዌ” ወረዳ (ከሚሴ) የተፈጠረ ነው፤ በደዌ የተማሩ ቀደምት ዑለማ ናቸው ወደ ሀረርጌ ያመጡት” የሚል ሐሳብ አላቸው፡፡ አንዳንዶች ደግሞ “በባሌው የሼኽ ሁሴን መስጊድ ዙሪያ የሚያስተምሩ ዑለማ ያስገኙት ነው” የሚል ክርክር ያቀርባሉ፡፡ በዚህ ረገድ የተጨበጠ ማስረጃ የለኝም፡፡ ስለዚህ ጥናትና ምርምር ያሻዋል፡፡

*****

ከመግቢያዬ እንደገለጽኩት የዐጀም ስርዓተ ፊደላት በሌሎች የሀገራችን ቋንቋዎችም ልዩ ልዩ ጽሑፎችን ለመጻፍ አገልግሏል፡፡ በዚህ ረገድ በቀዳሚነት የሚጠቀሱት ሀረሪና አማርኛ ናቸው፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የሀረሪ ቋንቋ በዐጀም አጻጻፍ መጻፍ የጀመረው በመካከለኛው ዘመን ነው፡፡ በመሆኑም የሀረሪ የዐጀም አጻጻፍ በሌሎች ቋንቋዎች ከምናውቃቸው የዐጀም ስነ-ጽሑፎች በሙሉ ይቀድማል ማለት ነው፡፡ ለዚህ ማስረጃ የሚሻ ሰው በዶ/ር ኤንሪኮ ቼሩሊ የታተሙ የጥንት ድርሳናትን መመልከት ይችላል፤ ከ1648-1875 በቆየው የሀረር አሚሬት ዘመን የተመዘገቡ ድርሳናትን መመልከት ይቻላል፤ ሌላው ቀርቶ ሰር ሪቻርድ በርተን በ1854 ሀረርን በጎበኘበት ጊዜም የሀረሪ ቋንቋ በዐጀም አጻጻፍ ሲጻፍ እንደተመለከተ የተናገረውን መነሻ ብናደርግ የሀረሪ ቋንቋ ከብዙ ቋንቋዎች በፊት በዐጀም ይጻፍ እንደነበረ በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡ 

   አማርኛ በዐጀም መጻፍ የጀመረበትን ዘመን በትክክል ማመልከት ባይቻልም ጅምሩ በወሎ ክፍለ ሀገር እንደተጸነሰ በድፍረት መናገር ይቻላል፡፡ ይህ የአማርኛው የዐጀም አጻጻፍ በስፋት ጥቅም ላይ ሲውል የነበረውም በወሎ ነው፡፡ እነ ሼኽ ዑመር ቡሽራን የመሳሰሉ የወሎ ታዋቂ ዑለማ የገጠሟቸው የመንዙማ ግጥሞች ሙሉ በሙሉ በዐጀም የተጻፉ ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የሼኽ ሑሴን ጂብሪል ትንቢታዊ ግጥሞች በቅድሚያ የተጻፉት በዐጀም አጻጻፍ ነው ይባላል፡፡

*****

  ኢትዮጵያችን በዐጀም ስርዓተ ጽሕፈት የተጻፉ የበርካታ ድርሳናት ባለቤት ናት፡፡ የጥንቱ ሙስሊም ዑለማ የመንዙማ ግጥሞችን ከመጻፍና የዕለት ተዕለት ሁኔታን ከመመዝገብ በተጨማሪ በታሪክ፣ በቋንቋ፣ በግብርና፣ በአስትሮኖሚ፣ በህክምና፣ በስነ-ማዕድንና በሌሎችም የህይወት ዘርፎች ላይ ያተኮሩ ድርሳናትን በዐጀም የአጻጻፍ ስርዓት ጽፈዋል፡፡ ይሁንና ከነዚህ ድርሳናት መካከል በጣም የሚበዙት ተሰብስበው በህዝብ ሀብትነት አልተመዘገቡም፡፡ በርካቶቹ በግለሰቦች እጅ ተይዘው ብልና ምስጥ እየበላቸው ነው፡፡

    የ“ዐጀም” አጻጻፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየደከመ መምጣቱ ደግሞ ሌላው ጉዳት ነው፡፡ ድርሳናቱ በጥቂቱ ተሰብሰበው ባሉበት አካባቢዎች የዐጀም አጻጻፍ እየተረሳ ነው፡፡ ድርሳናቱን ማንበብ የሚቻልበት ስርዓት ተጠብቆ ካልቆየ ቀጣዩ ትውልድ እነርሱን አንብቦ መረዳት ሊያቅተው ይችላል፡፡ ስለዚህ ሁለቱም ጉዳዮች ሊተኮርባቸው ይገባል፡፡ አንደኛ የዐጀም ድርሳናት ተሰብስበው የተሻለ እንክብካቤ በሚያገኙባቸው ስፍራዎች መቀመጥ አለባቸው፤ ሁለተኛ የዐጀም አጻጻፍ ስርዓታችን ተመዝግቦ ለትውልድ መተላለፍ አለበት፡፡ በዚህ ረገድ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስር ያለው የፊሎሎጂ ዲፓርትመንት ቀዳሚ ሆኖ መንቀሳቀስ ይኖርበታል እላለሁ፡፡

—-

አፈንዲ ሙተቂ

ሀምሌ-2006

——-

የኢጣሊያ የባህር ኃይል ዛሬ እንዳስታወቀው በላምፔዱዛ የባህር መዳረሻ 18 አስክሬኖችን ሰብስቧል። የጀልባው ሞተር ላይ ጉዳት በመድረሱ ስደተኞቹ አደጋ እንደገጠማቸው ያስታወቀው የባህር ኃይል አክሎም «ሲሮ» የተባለው የባህር ኃይል መርከብ 73 ሰዎችን ከባህር ማትረፉን ገልጿል።

የገዥው ፓርቲ ቅድመ ምርጫ የጽዳት ዘመቻ
(ከላይ ከግራ ወደቀኝ) ቶማስ አያሌው፣ ዳንኤል ድርሻ እና ግዛው ታዬ፣ (ከታች) ሰናይ አባተ እና አስናቀ ልባዊ (Top, left to right) Thomas Ayalew, Daniel Dirsha and Gizawe Taye. (Bottom, left to right) Senay Abate and Asnake Lebawi

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ነሐሴ 17 ቀን 2006 ዓ.ም. August 23, 2014)፦ በአምስት ሣምንታዊ መጽሔቶችና አንድ ጋዜጣ ላይ የተመሰረተውን ክስ ተከትሎ አስራ አንድ ጋዜጠኞች ለስደት ተዳረጉ። አስራ አንዱ ጋዜጠኞች የተሰደዱት በፍትህ ሚኒስቴር ሐምሌ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. “የዐመጸ ቅስቀሳና የሐሰት ወሬዎችን በመንዛት ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመናድ ጥረት አድርገዋል” በተመሰረተባቸው ክስ መሆኑን ለኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ የደረሰን መረጃ ያስረዳል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በምዕራብ አፍሪቃ ኤቦላ ተኀዋሲ አብዝቶ ጉዳት እያደረሰ ካለባቸው ሀገራት ውስጥ ላይቤርያ ናት። ከ15 የላይቤርያ ግዛቶች መካከል በስምንቱ የአስቸኳዩ ጊዜ ታውጆዋል። ስለበሽታው በቂ መረጃ የሌለው እና በሰበቡም ስጋት ያደረበባቸው የሀገሪቱ ነዋሪዎቹ በመንግሥታቸው ላይ እምነት አጥተዋል።

ዛሬ ወደ ኪይቭ የተጓዙት የጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ፔትሮ ፕሮሼንኮ ጋር ተገናኝተው ተወያዩ። ይህ በእንዲህ እንዳለ የርዳታ ቁሳቁስ የጫኑት የሩስያ ከባድ ተሽከርካሪዎች በሙሉ ከምስራቅ ዩክሬይን መዉጣታቸዉ ተነገረ።

«ራሱን ግንቦት 7 ብሎ ከሚጠራ ድርጅት ጋር እና ከድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በመገናኘት ፤ እንዲሁም ከባንክ በትዕዛዝ ብር በመቀበል የግንቦት 7 ተልዕኮና አላማ ለመፈፀም፤ ቁጥራቸው ከ60 በላይ የሆኑ ግለሰቦችን ለዚህ ጥፋት እንዲሰማሩ በማድረግ» የሚል ክስ ነው በወዲ ሃዉዜን/ትግራይ በሆነው አንጋፋ ፖለቲከኛ እና ብሎገር ላይ ክስ የቀረበው። ሌላው አንጋፋና አንደበተ ርትኡ፣ የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ ግብረ ኃይል ሰብሳቢ፣ […]

አንዱዓለም ተፈራ (እስከመቼ) 

“ ኢትዮጵያዊነት ማለት፤ ኢትዮጵያዊያንን መውደድ፣ ኢትዮጵያን ማፍቀር፤ የኢትዮጵያን መንግሥት በተገቢው መንገድ መደገፍና፤ ይህ መንግሥት የተሳሳተ መንገድ ሲይዝ መቃወም ማለት ነው። በሥልጣን ላይ ያለው ክፍል ፀረ-ኢትዮጵያዊያንና ፀረ-ኢትዮጵያ ሲሆን፤ ያንን ክፍል በማንኛውም መንገድ ማስወገድ፤ የያንዳንዱ ኢትዮጵያዊና የያንዳንዷ ኢትዮጵያዊት፤ ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው።”

ሙሉውን አስነብበኝ …

ኤፍሬም ማዴቦ

ባለፈው ሰሞን ቻይና አፍሪካ ውስጥ ሰላሳ አመት በማይሞላ ግዜ ውስጥ ያደረገችው የኤኮኖሚና የፖለቲካ መስፋፋት ያሳሰባቸው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ምነው ምን አድረግናችሁና ነው ፊታችሁን ያዞራችሁብን ብለው ለመጠየቅ በርከት ያሉ የአፍሪካ መሪዎችን ቤተ መንግስታቸው ድረስ ጋብዘዋቸው ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ጋባዥነት በቅርቡ ከተካሄደው የዋሽንግተኑን የአፍሪካ ፕሬዝዳንቶች ጉባኤ ትይዩ የሲቪል ማኅበረሰብ ተቋማትና ተጋባዥ እንግዶች የተሳተፉባቸው ስብሰባዎች ተካሂደዋል።

በእነኚህ ስብሰባዎችም በዋናው የፕሬዝዳንቶቹ ጉባኤ ትኩረት ሊደረግባቸው ይገባ ነበር ያሏቸውን አሳሳቢ የማኅበረሰብ ልማትና ብልጽግና፥ መልካም አስተዳደርና ዲሞክራሲ የተመለከቱ በርካታ ርእሰ ጉዳዮች አንስተዋል።

ከስብሰባዎቹ ተሳታፊዎች አንዷ የሆኑት የቀድሞዋ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ሊቀመንበር ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በውይይቶቹ የተነሱትን ጭብጦች መነሻ በማድረግ ባቀረቡት ጽሁፍ ይዘት ዙሪያ አነጋግረናቸዋል።

“..እንዲህ አይነት ጥያቂዎችን እነማን እንደሚጠይቁ እናውቃለን ደንቆሮ ዝቃጭ ..” ደብረጺሆን
“በስልጠናው ላይ ሰራተኛው ለኢሕአዴግ ያለውን ጥላቻ በሰፊው አሳይቶበታል። ” የካድሬዎች ሪፖርት
ይህን ሰሞን ለምርጫ የሚሆን ድጋፍ እና አዳዲስ አባላትን ለመመልመል የወያኔው ጁንታ የመንግስት ሰራተኞችን እና የዩንቨርስቲ ተማሪዎችን የመልካም ልማታዊ አስተዳደር በሚል ሽፋን ለፖለቲካ አጀንዳነት ሊጠቀምባቸው በማሰብ እያደረገ ያለው ስልጠና ከአለመግባባት አልፎ እስከ ስድብ መድረሱ ሰልጣኞችን አስቆጥቷል።

በዚሁ መሰረት የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኞች ለስልጠና የጠራው የወያኔ ቡድን ካድሪዎቹ የሰራተኛውን ጥያቄ መመለስ ስላቃታቸው ወደ ደብረጺሆን ያስተላለፉት ሲሆን ዶክተር (በተገዛ ዲግሪ ) ደብረጺሆን በከፍተኛ ቁጣ በተቀላቀለበት ሁኔታ ሲመልሱ ተስተውሏል። ሰራተኞቹ የሃይማኖት ነጻነት እና ሙስሊሞች ፣ ዞን 9 ፣ የኦሮሞ ተማሪዎች ፣ የኑሮ ውድነት ፣ የዘረኝነት መስፋፋት ፣ የሃገሪቱ ታሪክ ማበላሸት እና የሃገር ዳር ድንበር ፤ የሚታሰሩ ዜጎች እና የተቃዋሚዎች ሮሮ …. ፣ ወዘተ ያቀረቧቸው ጥያቂዎች ከደብረጺሆን ጋር ካለመግባባት በስድብ እና በቁጣ የታጀቡ እንደነበሩ ታውቋል።

በወያኔ ካድሬዎች ዘንድ ከፍተኛ መደናገጥ የታየበት ይህ የኢትዮ ቴሌኮም ስልጠና ዶክተር የሚባሉት ደብረጺሆን በከፍተኛ ቁጣ በሺዎች የሚቆጠረውን ሰልጣኝ የመንግስት ሰራተኛ …..ቁጣ በተቀላቀለበት አምባገነናዊ መንፈስ ድንጋጤን ተላብሰው ….. ደንቆሮ …..ደደብ … የዘቀጠ .. በሚሉ የስድብ አጀቦች ጥያቄዎቹ የነማን እንደሆኑ እናውቃለን .. በሚል ማስፈራሪያ ሰራተኛውን ማሰልታን ሳይሆን ማስጠንቀቅ በሚል እንዲሁም ለመጪው ጊዜ እርምጃ እንደሚወሰድ መል እክት በሚያስተላልፍ መልኩ ሲዝቱ ሲሳደቡ ተስተውሏል።

ዶክተር በሚባሉት ደብረጺሆን መልስ ሰራተኛው ከፍተኛ ቁጣ ይሰማ ሲሆን ከአሁን በኋላ በሚደረጉ የስልጣና ቀኖች ላይ ምንም ጥያቄ ላለመጠየቅ እና አስተያየት ላለመስጠት ሰራተኛው አድሞ ወደ ስልጠናው እንደገባ ሲታወቅ የወያኔ ካድሬዎች የሰራተኛውን ድፍርት እና በጥያቄዎች መግነን ተከትሎ ድንጋጤ የፈጠረባቸው ቢሆንም ከጀርባ ግን ሰራተኛውን ሲያበረታቱ ተስተውሏል።
ከስልጠናው መልስ ካድሪዎች ለአለቆቻቸው የሚያቀርቡት ሪፖርት እንደሚጠቁመው የመንግስት ሰራተኛውም ይሁን የዩንቨርስቲው ተማሪ ለኢሕአዴግ ያለውን ጥላቻ የሚያሳይ መሆኑን እንደሆነ ከፓርቲው ጽ/ቤት የተገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።ሚኒሊክሳልሳዊ

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

ላለፉት 23 ዓመታት ህወሓት/ኢህአዴግ ስራዬ ብሎ ካዳከማቸውና ጉዳዬ ከማይላቸው ዘርፎች ውስጥ የሚመደበው የትምህርት ስርዓቱ ሲሆን ይህም ከኢህአዴግ ስህተቶች ሁሉ ዋነኛው እና አሳፋሪ ተግባሩ ነው፡፡ ለሁለት አስርት አመታት ትውልዱን በማምከን በሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ ከገፉት ጉዳዮችም ግንባር ቀደሙ የህወሓት/ኢህአዴግ የተምታታበት የትምህርት ፖሊሲ መሆኑም ይታወቃል፡፡ ትምህርት ለአንድ ሀገር እድገት የጀርባ አጥንት መሆኑ እየታመነ የትምህርት ስርዓቱ ሆን ተብሎ በንቀት እና በዝርክር አሰራር እንዳያድግና ጥራት እንዳይኖረው ኢህአዴግ እየተጋ አሁን ድረስ ዘልቋል፡፡

በዚህ አይነቱ አጥፊ አካሄድ ምክንያትም ሀገራችን በዓለም ደሃ ሀገራት ተርታ ቀዳሚዋ ሆናለች፡፡ የተማረ እየተገፋ በስራ አጥነት ሲንከራተት እና ለስደት ሲዳረግ በካድሬነት የስርዓቱ አገልጋይ መሆን ደግሞ በተቃራኒው ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል፡፡ በተለይም ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው የገዢው ፓርቲ አባል እንዲሆኑ ሲገደዱ መቆየታቸውና የኢህአዲግ አባል ካልሆኑም ስራ ሊያገኙ እንደማይችሉ እየተነገራቸው በፍራቻ ለአባልነት የተመዘገቡ ብዙዎች እንደሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ በዚህ ሳያበቃ አሁን አሁን ደግሞ የገዢውን ፓርቲ ያረጀና ያፈጀ ኋላቀር አስተሳሰብና ርዕዮተ-ዓለም በተማሪዎች ላይ ለመጫን በየዓመቱ መጀመሪያ ‹ስልጠና› በሚል ፈሊጥ በጀት በጅቶ በግድ ሊግታቸው እየሞከረ ይገኛል፡፡

በዚሁ በያዝነው ወርም በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎች እንዲሰበሰቡና ስልጠና እንዲወስዱ ጥሪ የተላለፈ ሲሆን ስልጠናውን ያልተከታተለም መደበኛ ትምህርቱን እንደማይቀጥል ማስፈራሪያ አይሉት ማሳሰቢያ በገዢው ፓርቲ በኩል ተላልፏል፡፡ ሌላው አስገራሚ ዜና ደግሞ ተማሪዎቹ በግድ ስልጠናውን እንዲወስዱ መገደዳቸው ሳያንስ ወደ ግቢ ከገቡ በኋላ ተመልሰው መውጣት እንደማይችሉ መሰማቱ ነው፡፡ ይህም ኢህአዴግ ካድሬዎቹን የሚያሰለጥንበት ዝግ የስብሰባ ስልት መሆኑ ጉዳዩን የበለጠ አስገራሚ ያደርገዋል፡፡

ህወሓት/ኢህአዴግ ይህንን ስልጠና ሲያካሂድም፡-

1. ህግን በጣሰ መልኩ የትምህርት ማዕከላትን የፖለቲካ ማራመጃ እና የአንድ ፓርቲ ርዕዮተ-ዓለም ማስፈፀሚያ አድርጓል፡፡

2. ይህን ፋይዳ ቢስ ስልጠና በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎችና ከ800.000 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች በሚሰጥበት ወቅት ከፍተኛ የህዝብ ሀብት እያባከነ ይገኛል፡፡

3. ተማሪዎች የእረፍት ጊዜያቸውን በነፃነት ማሳለፍ ሳይችሉ በአስቸኳይ ወደ ዩኒቨርስቲዎች እንዲመለሱ ተገድደዋል፡፡

4. በሚሰጠው ስልጠናም ላይ በአክራሪነት በብሔርተኝነትና በመሳሰሉት ጉዳዩች ሽፋን በተማሪዎች ዘንድ መርዛማ ጥላቻን እየረጨ ይገኛል፡፡

5. በአጠቃላይ በስልጠናው ወቅት ርካሽ የፕሮፖጋንዳ ስልትን በመጠቀም መጪውን ምርጫ በማምታታት ለማለፍ እየሞከረ ሲሆን ይህም በአምባገነንነቱ ቀጥሎ ህብረተሰቡን አማራጭ ለማሳጣትና ሀገሪቷን ወዳልተፈለገ አለመረጋጋት ሊወስድ እየሞከረ መሆኑን ያሳያል፡፡

በመሆኑም ሰማያዊ ፓርቲ ይህን የገዢው ፓርቲ ህገ ወጥ አድራጎት አጥብቆ እያወገዘ ጉዳዩን እየተከታተለም አቋሙን ይፋ የሚያደርግ መሆኑንን ይገልፃል፡፡ ተማሪዎችም በዚህ ህገ ወጥ ተግባር ሳይደናገጡ ያለምንም ፍርሃት ህጋዊ በሆነ መንገድ ይህን ካድሬያዊ ስልጠና በማውገዝ፣ የገዢውን ፓርቲ ድብቅ ሴራ በማጋለጥ እና ለህወሓት/ኢህአዴግ የተለመደ አጥፊ ፕሮፖጋንዳ ባለመታለል ተማሪዎች በአንድነት እንዲቆሙ ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ነሀሴ 15/2006 ዓ.ም ሰማያዊ ፓርቲ

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ከኢትዮጵያ ሀገሬ የደቀቀ ኢኮኖሚ ላይ በማን አህሎኝነት ወጪ ተደርጎ፣ ቅጥ ባጣ መልኩ በመላ አገሪቱ እየተከበረ ስላለው የቀድሞ አምባገነን ጠ/ሚኒስትር ሁለተኛ ሙት ዓመት ዝክርም ሆነ ሰውየውን ዛሬም በአፀደ-ህይወት ያለ ለማስመሰል እየሞከሩ ላሉት ጓዶቹ አንዲት ምክር ብጤ ጣል ማድረጉ ተገቢ ነው ብዬ ስለማስብ በአዲስ መስመር እንዲህ እላለሁ፡-

አብዮታዊው ገዥ-ግንባር ግንቦት ሃያ፣ የህወሓት ምስረታ፣ የብአዴን አፈጣጠር፣ የኦህዴድና የደኢህዴን ውልደት፣ የብሔር ብሔረሰቦች በዓል፣ የባንዲራ ቀን፣ የመከላከያ ሳምንት፣ የፍትሕ ሳምንት፣ የሕዳሴ ግድብ መሰረት ድንጋይ የተጣለበት… ጅኒ-ቁልቋል እያለ ዓመቱን ሙሉ በማይጨበጥ ተራ ፕሮፓጋንዳ ማሰልቸትን መንግስታዊ ኃላፊነት አድርጎታል፡፡ ይህ እንግዲህ ለቁጥር የሚያታክቱ፣ በነጭ ውሸት የታጨቁ እና በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ቅኝት የተንሸዋረሩ ‹ዶክመንተሪ ፊልሞቹ›ን ረስተንለት ነው፡፡

ይህ ሁሉ ያልበቃው ‹‹ጀግናው›› ኢህአዴግ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህልፈት ወዲህ፣ ወርሃ-ነሐሴንም እንደ ግንቦት ሃያው ሁሉ የሟቹን ታጋይነትና አብዮታዊነት፤ ሕዝባዊነትና አርቆ አስተዋይነት፤ የርዕዮተ-ዓለም ተራቃቂነትና የአየር ንብረት ተካራካሪነት፤ በፖለቲካ ቢሉ በኢኮኖሚ ቁጥር አንድ ጠቢብነትና ባለራዕይነት፤ ፍፁም ፃድቅነትና ሰማዕትነት…. የሚተረክበት ሲያደርገው ቅንጣት ታህል ሀፍረት አልተሰማውም፡፡ ሰሞኑን በ‹‹ኢትዮጵያ›› ቴሌቪዥን ግድ ሆኖብን ተመልክተንና ሰምተን በትዝብት ካሳለፍናቸው ‹‹መለስ፣ መለስ›› ከሚሉ የከንቱ ውዳሴ አደንቋሪ ድምፆች በተጨማሪ፣ የኦሮሞን ባሕላዊ ልብስ ሲያለብሱት፣ ሐረሪዎች ጋቢ ሲደርቡለት፤ በደቡብ የሚገኙ ብሔሮች የየራሳቸውን ባሕል የሚወክሉ አልባሳት ሲሸልሙት፣ ስለወላይታነቱ ሲመሰክሩለት… ደጋግመን ለመመልከት ተገደናል፤ ይሁንና ድርጅቱ ስለ ቀድሞ ሊቀ-መንበሩ አልፋና ኦሜጋነት ለመስበክ ዙሪያ ጥምዝ ከዳከረለት ከእንዲህ አይነቱ የተንዛዛ ፕሮፓጋንዳ ይልቅ፣ በዚሁ የቴሌቪዥን መስኮት የቀረበ አንድ ጎልማሳ ‹‹መለስ ሁሉም ማለት ነው›› ሲል የሰጠው አስተያየት፣ ቅልብጭ አድርጎ ይገልፅለት ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡ የዚህ አይነቱ ምጥን አስተያየትም በጥራዝ ነጠቅነት ዘላብዶ የኋላ ኋላ በሀፍረት ከማቀርቀር ያድናል፡፡ ለምሳሌ እናንተ የግንባሩ ካድሬዎች ስለመለስ ምሁርነት ለመናገር ስትዳዱ ሁሌ የምትደጋግሙት፣ ያንኑ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ አርቃቂነቱ እና የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ኀልዮት አዋቃሪነቱ ነው፡፡ ግና፣ ይህ ‹‹ንድፈ-ሃሳብ›› ተብዬ ራሱ በርዕዮተ-ዓለምነት ለመጠራት የማይበቃ የተውሸለሸለ ጭብጥ ስለመሆኑ በርካታ ምሁራን በጥናቶቻቸው ከማስረገጣቸው ባሻገር፣ አገሪቷን ለከባድ ኢኮኖሚያዊ ድቀት፣ ሕዝቧን ደግሞ ለጥልቅ ድህነት መዳረጉን ብቻ ማስታወሱ በቂ ይሆናል፡፡ ስለልማታዊ መንግስት አዋጭነት በብቸኝነት እንደተከራከረ ተደርጎ የሚለፈፈውን እንኳን ንቆ መተው ሳይሻል አይቀርም፡፡ ከታንዲካ ማካንደዋሬና መሰል የፅንሰ-ሃሳቡ አበጂዎች የዘረፋቸውን መከራከሪያዎች ማን ዘርዝሮ ይዘልቀውና፡፡ ‹መለስን ቅበሩት› የምለውም፣ እንዲህ ያሉ አስነዋሪ ማንነቶቹን ማስታወስ ስለሚያም ነው፡፡

እናም እውነት እውነት እላችኋለሁ፡- ስለሰውዬው የምትነግሩን እና የምታስቀጥሉት ‹ሌጋሲ›ም ሆነ የምትተገብሩት ረብ ያለው አንድም ራዕይ የለምና ዝም፣ ፀጥ ብላችሁ የምራችሁን ቅበሩት፡፡ እስቲ! ኦጋዴንን ተመልከቱ፤ ካሻችሁም ወደ አኝዋኮች ተሻገሩ፤ ያን ጊዜ እናንተ በአርያም የሰቀላችሁት ሰው፣ ለነዚህ ሁለት ብሔሮች የቀትር ደም የጠማው ጨካኝ መሪ እንደነበር፣ በክፋት ትዕዛዞቹ ጥፋት ከተረፈ ጠባሳ ትረዱታላችሁ፡፡ ለአቅመ-ሔዋን ያልደረሱ ህፃናት በሰልፍ የሚደፈሩባት፣ ወጣቶች እንጀራ ፍለጋ በተስፋ-ቢስነት ጥልቁን ውቅያኖስ ሰንጥቀው ለመሰደድ የማያመነቱባት፣ የጤና ኬላ ማግኘት ተስኗቸው በልምሻ የሚባትቱ ብላቴኖችን በአቅም-የለሽነትና በቁጭት የምናስተውልባት ደካማ አገር አስረክቦን እንዳለፈ ከወዴት ተሰወረባችሁ? ከቀዬዎቻቸው በጉልበት ለተፈናቀሉ ወገኖች በመቆርቆር ‹‹ሕግ ይከበር!›› ባሉ በየጉራንጉሩ ወድቀው እንዲቀሩ የተፈረደባቸው ጎበዛዝትን ሬሳ እንድንቆጠር ያደረገን ደመ-ቀዝቃዛ ‹መሪ› እንደነበረስ ስንት ጊዜ እያስታወስን እንቆዝም? ቀደምት አባቶች ወራሪውን ፋሽስት ለማንበርከክ የተዋደቁባቸው ጢሻና ኮረብቶች በዚህ ዘመን የዜጎች ወደሞት አገራት መሸጋገሪያ ጽልማሞቶች የሆኑት በማን ሆነና ነው? ከሕግ ተጠያቂነት ቢያመልጥ፣ ከታሪክ ተወቃሽነት ልትታደጉት የምትችሉ ይመስላችኋልን?

…ይልቅ እመኑኝ! ፀጥ ብላችሁ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ጥልቅ ጉድጓድ ቆፍራችሁ ቅበሩት! ላይመለስ በመሄዱም እንደ ግልግል ቆጥራችሁት እርሱት!! መቼም በገዛ ራሱ ሕዝብ ላይ ትውልዶች ይቅር ሊሉት የሚሳናቸውን ይህን መሰሉ መከራ ላዘነበ ሰው በአፀደ-ስጋ ሳለም ሆነ በበድን የሙት መንፈሱ ስር በየዓመቱ ለአምላኪነት መንበርከክ፣ የናንተን አልቦ ማንነት እንጂ ሌላ አንዳች የሚነገረን ቁም ነገር ጠብ ሊለው አይችልም፡፡ ይህም ሆኖ ለመለስ አምልኮ እጅ መስጠት አሳፋሪነቱ፣ ለካዳሚዎቹ ብቻ መሆኑን መስክሮ ማለፉ የቀሪዎቻችን ዕዳ እንደሆነ መገንዘብ አለብን፡፡

Image

በሆዳችን አንገዛም !!!!! የተማሪው የዛሪው መሪ መፈክር
“እየተቃውመ የሚሰለጥን እያጉረመረመ የሚበላ ትውልድ ……… ከሰልጣኞቹ ይልቅ አሰልጣኞቹ ጥያቄ የሚያጭር ንግግር እያደረጉ ተቃውሞውን ያባብሱታል ” ከወያኔ ካድሬዎች አንዱ በስካይፒ

ምንሊክ የዘመናዊ ኢትዮጵያ አባት ነው ።……… ኢትዮጵያዊነት በስር መሰረት ሲተላለፍ የመጣ ስለሆነ በዘረኝነት አይናድም።….. አናካሽ እና ከፋፍለህ ግዛ የሚለውን ሰነዳችሁን አቃጥሉት ።… ስልጠናው ይቁም ።….
የተትረፈረፈ ምግብ አምጥታችሁ በሆዳችን ልትገዙን ከሆነ አትሞኙ ። ምግቦች ከመትረፍረፍ የተነሳ እየተደፉ ነው ለምን ለጎዳና ተዳዳሪዎች አይሰጡም።……. ለምን ስንበላ በፖሊስ እንታጀባለን ? ………
የህዝብ ገንዘብ የገዢውን ፓርቲ ፕሮፓጋንዳ ለመርጨት ያላግባብ እየተጠቀማችሁበት ነው።፣…………..
ሕዝብን እየተሳደባችሁ እድሜያችሁ የሚረዝም እንዳይመስላችሁ …. 2007 ምርጫ ድጋፍ ለማግኘት ትባዝናላችሁ ……የሃገር ሃብት ለናንተ ፖለቲካ አጀንዳ እየዋለ እናንተ በቻይና ብድር ታራውጡናላችሁ። ………….ለሕዝብ ጥቅም የዋለ የሃገር ሃብት የለም። …የሚያሳዝነው ሕዝቡ መሮታል የሚመራው አጥቶ ነው እንጂ ….ሰበብ እየፈጠራችሁ ንጹሃንን እያሰራችሁ ተቃዋሚዎችን ወህኒ እየከተታችሁ ሌላውን እያሳደዳችሁ ምርጫ የሚኖር ይመስላቹሃል? …. ከ እናንተ ጋር የሚወዳደር ያለ ይመስላችኋል።
Image

ሰልጣኝ ተማሪዎች ስልጠናው ግጭትን የሚያስነሳ በመሆኑ እንዲቆም ጠየቁ ።ሰልጣኞቹ ፌስ ቡክ እንዳይጠቀሙ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) VIA ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia
ከነሀሴ 9 ጀምሮ በደብረማርቆስ ከተማ በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣ ተክለኃይማኖት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ቤተ መንግስት፣ መምህራን ኮሎጅና የደብረ ማረቆስ መሰናዶ ትምህርት ቤት ተከፋፍለው በአራት የሥልጠና ቦታዎች እንዲሁም 45 የውይይት ቡድኖች ስልጠና እየወሰዱ የሚገኙት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስልጠናው ከፋፋይና ለትውልዱ ጎጅ በመሆኑ ሊቆም እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ሰልጣኞቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡

ተማሪዎቹ በተለይም ‹‹የኢትዮጵያ ህዝቦች ትግልና የአገራችን ህዳሴ›› በሚል ህዝብን ከህዝብ ያጋጫል ያሉትን ያሉት ሰነድ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ እንዳሰሙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ተማሪዎች ‹‹እስር በእስር ለማናከስ የተዘጋጀ ሰነድ ነው፡፡ በመሆኑም ሰነዱ ሊቃጠል ይገባዋል፡፡ በቀጣይ ወደ ዩኒቨርሲቲ ስንገባ የሚያጋጨን ስለሆነ ስልጠናው በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል፡፡ የኦሮሚያ ተማሪዎችን አመጽ የቀሰቀሰው በዚህ የኢህአዴግ ከፋፍለህ ግዛ ሴራ ነው፡፡ ሰነዱ እንደሚለው ኢትዮጵያ ከታናሽንት ወደ ታላቅነት ሳይሆን ከታላቅነት ወደታናሽነት ነው የወረደችው፡፡ ለዚህ ከፋፋይ ሰነድ በርካታ ወጭ ወጥቶ እርስ በእርሳችን ለማናከስ ከሚጣር በገንዘቡ በየጎዳናው የወደቁ ኢትዮጵያውያንን ከርሃብ መታደግ ይችል ነበር፡፡›› በሚል ጠንካራ ተቃውሞ ማሰማታቸውን ገልጸውልናል፡፡

ተማሪዎቹ አክለውም ‹‹አጼ ምኒልክ በጊዜያቸው መልካም ስራ ሰርተዋል፡፡ ስህተት ሰሩ እንኳ ቢባል የዘመኑ ወጣቶች ያ ስህተት ላይ ተሳታፊዎች ባለመሆናችን የእኛም ስህተት ተደርጎ ከሌሎቹ ጋር ለማናከሻነት መዋል የለበትም፡፡ በዚህ ዘመን ህወሓት፣ ብአዴንና ሌሎቹ የኢህአዴግ አባላት እንጅ ህዝብ ነፍጠኛ ሊባል አይገባም፡፡ ብአዴን አማርኛ ተናጋሪውን አይወክልም፡፡›› ማለታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተለይ ኢህአዴግ ስኬታማ እንደሆነ በሚገልጸው የሰነዱ ክፍል ላይ ካድሬዎች በየ እምነት ተቋማት ጣልቃ እየገቡ በመሆኑ የእምነት ነጻነት እንደሌለ፣ ጋዜጠኞች እየሰደዱ መሆንንና ሚዲያዎች በመዘጋታቸው ሀሳብን በነጻነት መግለጽ እንዳልተቻለ፣ የመድብ ፓርቲ እንደሌለና የኢህአዴግ አፋኝ መሆኑን በመግለጽ ሰነዱ ላይ የተጠቀሱት ስኬቶች በተግባር እንደሌሉ ተከራክረዋል፡፡

ትምህርትን በተመለከተ ሰነዱም ሆነ ኢህአዴግ በየጊዜው ያብጠለጥላቸዋል ያሏቸውን አጼ ምኒልክ ‹‹እኔ ቤት እንጀራ የለም፡፡ እንጀራ ያለው ትምህርት ቤት ነው ፡፡›› ብለው እንደነበር በማውሳት ከመቶ አመት በፊት ከነበረው ስርዓትም ያነሰ መሆኑን የተከራከሩ መኖራቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም የትምህርት ስርዓት ከመቼውም ጊዜ በባሰ መውደቁ፣ ተማሪዎች ተመርቀው በተማሩት ዘርፍ ሳይሆን ኮብልስቶንን ጨምሮ ያልተማሩትን እንዲሰሩ መገደዳቸውንና ስራ አጥ መሆናቸውን በመግለጽ የትምህርት ስርዓቱን ውድቀት አስረድተዋል ተብሏል፡፡ በስልጠናው ወቅት ከኢህአዴግ ስኬት በስተጀርባ ዋናው ተዋናኝ ሆነው የቀረቡት አቶ መለስ ዋነኛ የመወያያ ርዕስ እንደነበሩና ተማሪዎችም ‹‹አማርኛ ተናጋሪውን አቶ መለስ አከርካሪውን መትተነዋል ብለዋል፡፡ አከርካሪውን ከተመታ አሁን ሌላ ከፋፍለህ ግዛን የሚያሰፍን ስልጠና ለምን አስፈለገ? የመለስን ራዕይ አሳካለሁ የሚለው ብአዴን አማርኛ ተናጋሪውን አይወክልም፣ ህዝቡን የሚሳደቡ ባለስልጣናት ምንም አይነት እርምጃ የማይወሰድባቸው ስርዓት ለህዝብ ንቀት ስላለው ነው፣ ኢህአዴግ ራሱ ዘረኛ ነው፡፡›› በሚል ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡

ስልጠናው ወጣቱ ኢህአዴግ የያዘውን የተሳሳተ መስመር ለማስያዝ የሚጥርና የማይጠቅም በመሆኑ ሊቆም እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ በውይይቱ ወቅት ዝምታን የመረጡ ተማሪዎችም እንደ ወጣት ማንም አውቅልሃለሁ ሳይላቸውና ሳይፈሩ ስህተቱን እንዲቃወሙ ማሳሰባቸው ታውቋል፡፡ በስልጠናው ወቅት አሰልጣኞች ተማሪዎች ፌስ ቡክ ውሸት በመሆኑ እንዳይጠቀሙ፣ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ፌስ ቡክን በመጠቀማቸውና በፌስ ቡክ አማካኝነት በሚነሳ ብጥብጥና ሌሎች ችግሮች ምክንያት መንግስት በሚወስደው እርምጃ ተጎጅ እንደሚሆኑ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላት ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ተማሪዎች በስልጠናው እንዳይሳተፉ ጥረት ተደርጓል ያሉት ሰልጣኞቹ ‹‹አክራሪና አሸባሪ የሚባሉ አካላት መሳሪያ እንዳትሆኑ፣ ለእነዚህ አካላት መሳሪያ በመሆናችሁ የእርምጃው ሰለባ ትሆናላችሁ፡፡ መንግስት ተጠያቂ አይሆንም፡፡›› የሚል ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል፡፡

በስልጠናው ወቅትም ተቃዋሚዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ፌስ ቡከኞች፣ መንግስት በእምነታቸው እንዳይገባ ኢትዮጵያውያን በአጥፊነት መፈረጃቸውንና ተማሪዎች ከእነዚህ አካላት መራቅ እንዳለባቸው ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት መተላላፉን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ተማሪዎች በበኩላቸው ‹‹በአሁኑ ወቅት ኢህአዴግ ሚዲያውን እያፈነ ነው፣ ተቃዋሚዎችን እያሰረ ነው፣ በእምነት ጉዳይ ጣልቃ እየገባ ነው፣ የሚቀጥለውን ምርጫ ወቅት የእነዚህ ሁሉ ጭቆና ወደ አመጽ ቢያመራ ተጠያቂው ማን ነው? ለምን እንደ ሻዕቢያ በግልጽ አምባገነን መሆናችሁን አታውጁም? ህዝቦችን በየ አካባቢው እያፈናቀላችሁ ለምን ምኒልክን ትከሳላችሁ? ብሄራዊ እርቅን ለምን ትፈራላችሁ? የስልጠናው በጀት ይነገረን? ትራንስፎርሜሽኑ አልተሳካም፣ አባይ ግድብ የኢህአዴግ ፕሮጀክት ነው እና ሌሎችንም ጥያቄዎችና አስተያየቶች ማንሳታቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በደብረማርቆስ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአሰልጣኝነት ከተመደቡት መካከል አብዛኛዎቹ የገዥው ፓርቲ የካቢኔ አባላት እንደሆኑና በተለይ ታሪክ ላይ ያተኮረው የስልጠናው አካል በብአዴን አባላት ጭምር ቅሬታ እንዳስነሳ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ነሃሴ 9 የጀመረው ስልጠና በሁለት ዙር ለ15 ቀናት የሚሰጥ ሲሆን በዋናነት የኢትዮጵያ ህዝቦች ትግልና የአገራችን ህዳሴ፣ የታድሶ መስመርና የኢትዮጵያ ህዳሴ፣ ልማታዊ ዴሞክራሲ ስርዓትና ፈተናው እንዲሁም ህገ መገንስታዊ መርህና የሰላማዉ ትግል ስልት የተሰኙ አራት ጥራዞችን ያካተተ እንደሆነ ታውቋል፡፡ በቀጣይ ቀናት ከሰልጣኞቹ የተላኩትን የስልጠኛ ሰነዶችና መረጃዎች እየተከታተልን ለአንባቢያን የምናደርስ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

‹‹ይድረስ ላንቺ››

ተፃፈ ከስድስተኛ ተከሳሽ በዘላለም ክብረት

ወዳጄ ልቤ ከቶ እንደምንድን ነሽ? እውን እኔና አንቺ በአለም ስንኖር ሌላ የመገናኛ ዘዴ አጥተን ወደ snail mail እንመላለሳለን ብለሽ አስበሽ ታውቂያለሽ? ለማንኛውም እንዲህ ሆነ፡፡ ጥጋበኛ ሰው ያስቀናኝ ጀምሮልሻል፣ ጥጋበኛ እንዲህ የሚለው ትዝ አለኝ፡፡

‹‹ ….ደብዳቤ ቢጽፉት እንደ ቃል አይሆንም፣

እንገናኝ እና ልንገርሽ ሁሉንም….››

የደላው! ቢያሻው በደብዳቤ፣ ሲፈልግ በአካል እያማረጠ እኮ ነው፡፡ ለእኔ አሁን ባለሁበት ሁኔታ ሁለቱም ቅንጦት ነው (ወይ ደብዳቤው አይደርስሽም ወይም አንቺን ማየቴ ሊገደብ ይችላል)፡፡ቆይ ትንሽ የጎን ወሬ ላዋራሽና ምክንያቱን እነግርሻለሁ፡፡ ‹‹አንቺ›› ተብለሽ በዚህ ደብዳቤ ስለተጠቀስሽው ‹‹አንቺ››ና ይሄን ደብዳቤ ለሚያነቡ ወዳጆች የዕምነት ክህደት ቃሌን በትንሹ ላስፍር፡፡

እመቤት ሲልቪያ ፓንክረስት የኢትዮጵያ ፍቅረኛ (Ethiopian by choice) ዱቼ ሞሶሎኒ እትዮጵያን በወረረ ጊዜ፤ ወራሪው ሃይል በመላው ኢትዮጵያ ‹‹ የኢትዮጵያን ስም እያነሱ መፃፍ ክልክል ነው›› የሚል ያልተፃፈ አዋጅ አውጆ እንደነበር ይነግሩናል፡፡ በዚህም ምክንያት ፀሀፍቱና አዝማሪያኑ ስውር መጠሪያ መጠቀም ስላስፈለጋቸው እስከ ዛሬ ድረስ ተወዳጁ ሕዝባዊ ዘፈን አንቺ ልጅ አንቺ ልጅ እንደ ስውር የፍቅር ዘፈን ተበርክቷል፡፡ በዘፈኑ ‹‹አንቺ ልጅ ›› የተባለችውም ኢትዮጵያ ናት፡፡ እኔስ በዚህ ዘመን ‹ይድረስ ለባለ ታሪኩ›፣ ‹ይድረስ ለባለ ንብረቱ›… እንደሱ የሀዘን ደብዳቤ ርእስ ‹ይድረስ ለኢትዮጵያ › በማለት ፋንታ ‹ይድረስ ለአንቺ› ለማለት ስውር መጠሪያ ተጠቅሜያለሁ? ፤ በፍፁም! ጌቶች እንደሚሉት ሕገ መንግስቱ የመናገር ነፃነቴን ሙሉ ለሙሉ አስከብሮልኛልናi

ቧልቱ ይቆየንና በዚህ ደብዳቤ ርዕስ ዙሪያ ያለማንም አስገዳጅነት የእምነት ክህደት ቃሌን ላስፍር አንቺ የተባለችው ኢትዮጵያ አይደለችም፡፡ ‹አንቺ› የኔዋ ሀቢቢ ግን ባለሽበት ይድረስሽ፡፡ ውዴ እንግዲህ በዚህ ደብዳቤ ያለፈውን እያነሳሁ እነግርሻለሁ፡፡ወይ ትስቂያለሽ (ሳቅሽ እንዴት ያምራል?) ወይ ደግሞ ታዝኛለሽ (እኔን!)

ይህንን ደብዳቤ የመፃፍ መብት

እነሆ ላንቺ ስለሆነው ሁሉ ላጫውትሽ ስጀምር፤ በመነሻው ያሰብኩት ነገር ይሄን ደብዳቤ የመፃፍ ሕጋዊ መብት አለኝን? የሚለውን ጥያቄ ነው፡፡ ለዚህም መነሻዬ አሁን ያለሁበት ሁኔታ ነው፡፡ በመጀመሪያ “ሕገ-መንግስታዊ ስርአቱንና ሕገ-መንግስቱን በሀይል ፣በዛቻና በአድማ ለመናድ በመምከር/ በመናድ” ወንጀል ተጠርጥሬ የታሰርኩ ቢሆንም፤ በታሰርኩ በ23ኛው ቀን ወንጀል ወንጀልን፤ ጥርጣሬ ሌላ ጥርጣሬን እየወለደ የተለያዩ የሽብር ተግባራትን ለመፈፀም ለማሴርና ለማነሳሳት ወንጀል ተጨማሪ ጥርጣሬ በፓሊስ ዘንድ በማሳደሬ የክፋት ልኬ ከፍ ያለ ሲሆን፤ በመጨረሻም ሕገ-መንግስቱን እንደ እያሪኮ ግንብ ለመናድ በመሞከር፤ ሕብረተሰቡን ደግሞ ከሚተነፍሱት የሰላም አየር ለማቆራረጥ ከማሰብ የተለያዩ የሽብር ተግባራትን ለመፈፀም ሲንቀሳቀስ ተይዟል በሚል ወንጀሎች ተከስሼ በማረፊያ ቤት እገኛለሁ፡፡ ይሄን ሁሉ የምነግርሽ ‹ለ አንቺ› አዲስ ነገር ነው በማለት አይደለም፡፡ ይልቁንስ ያለሁበት የእስር ሁኔታ ደብዳቤ ካንቺ ጋር እንዳልፃፃፍ ይከለክለኛልን? የሚለውን ለማስረዳት በማሰብ ነው፡፡

መቼም አሁን ያለሁበት ሁኔታ ተገቢ ነው ብዬ ባላምንም ‹ ዋስ ጠበቃዬ ነውና› ስለመብቴ ስናገር ያን የፈረደበት ህግ መጥቀሴ አልቀረም፡፡ ታዲያስ በእስር ላይ ያለ ሰው ከወዳጁና በሕይወቱ ጋር ደብዳቤ ሊፃፃፍ ምን ገደብ አለበት? ይላል ስል፤ ስለፌደራል ታራሚዎች አያያዝ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 138/1999 በአንቀፅ 18 ላይ “ታራሚዎች (ተጠርጣሪዎች) ከማረሚያ ቤቱ (ከማረፊያ ቤቱ) ውጭ ካሉ ሰዎች ጋር መፃፃፍ ይፈቀድላቸዋል፡፡ ሆኖም ለጥበቃ ስራ ተቃራኒ የሆነ ተግባር እንዳይፈፀም በፅሁፎቹ ላይ ቁጥጥር ይደረጋል” በማለት የኔና አንቺ ደብዳቤ መፃፃፍ በሕግ የተፈቀደ ነገር እንደሆነ ደንግጎልናል፡፡ አሜን! (እንዲያው ይሄ ልጅ አሁንስ ተስፋዬ.. ማነው ? ሕጉ አይደለምን… የሚል የጅል ዘፈኑን አላቆምም እንዴ ብለሽ እንደማታሾፊብኝ እምነቴ ነው) ጓድ ሌኒን በዛች የፒተርስበርግ እስር ቤት ውስጥ ደብዳቤ መፃፃፍ አትችልም ተብሎ ተከለከለ እርሱ ግን የ Russia Social Democratic Party ን ፕሮግራም መፅሀፍ ውስጥ በየመስመሮቹ መሀል በ Invisible Ink በመፃፍ ታሪክ ስራ፡፡ እነሆ እኔ ግን በትናንት ሌኒኒስቶች (ፋና)፤ በዛሬ አሳሪዎቻችን መልካም ፈቃድ ደብዳቤ የመፃፃፍ ሕጋዊ መብቴ ተከብሮልኝ ይሔው በነጩ ወረቀት ላይ እንደ ሕዳሴው ባቡር እፈነጭበታለሁ፡፡

እንዲህ ሆነልሽ

አበባዬ- አፄ ሀይለስላሴ ከማንኛውም ባለስልጣን በሕይወት ዘመናቸው የበለጠ የቀረቧቸው የነበሩት ከ1934-1948 ድረስ ለ14 ዓመታት በፅህፈት ሚንስትርነት ያገለገሏቸውን ፀሀፊ ትዕዛዝ ወልደ ጊዎርጊስ ወልደ ዮሀንስን እንደ ነበር ነግሬሻለሁ? ወዳጅነትና ፍቅር ያልፋልና ሀይለስላሴና ወልደ ጊዎርጊስ ተጣሉ፡፡ የአፄ ሀይለስላሴ መንግስት መፅሀፍ ፀሀፊ አቶ ዘውዴ ረታ የወልደጊዎርጊስን መጨረሻ ሲተርኩ፡፡

‹‹ ፀሃያማው ሚያዚያ 17/1948 ቀን ለ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሀንስ እንደ ሌሎቹ ቀናት ብሩህ ሁና ነበር የነጋችው፡፡ ብሩህ ሁና እንደምታመሽም አልተጠራጠሩም ነበር፡፡ ምን ያደርጋል! ያች ክፉ ሰኞ የወልደጊዎርጊስ ከፍተኛ ስልጣን መጨረሻ ሆነች፡፡ በእኩለ ቀን ገደማ ቤተ መንግስት ተጠርተው ከፅህፈት ሚንስተርነታቸው ተነስተው የአሪሲ ጠቅላይግዛት ደረሳቸው››

(መፅሀፉ አጠገቤ ስለሌለ ቃል በቃል አልጠቀስኩም)

ወልደጊዮርጊስ ተሽረው ከቤተ-መንግስት እንዲርቁ የተደረገበት ምክንያት የሀይለስላሴን ወንበር በሰዒረ መንግስት ለመገልበጥ አስበዋል በሚል ምክንያት ነበር፡፡ወልደጊዎርጊስን እዚህ ጋር ማንሳቴ የሚያዚያ 17 ስለት እኔም ጋር በመድረሷ ነው፡፡ ውዴ! የእኔዋን ሚያዚያ 17/2006 ዓ.ም ውሎ እንደ ዘውዴ ረታ ስተርክልሽ ይሔን መሳይ ይሆናል፡፡

‹‹ ፀሃያማዋ ዓርብ ሜያዚያ 17/2006 ዓ.ም አጀማመር እንደ ወትሮው አልነበረም፡፡የጠዋት ትምህርት ክፍለ ጊዜ እንዳይረፍድብኝ እየተቻኮልኩ ወደማስተምርበት (የመጨረሻ ክላስ ነበር) አምቦ ዩንቨርሲቲ ስሄድ፤ ተማሪዎች አዲስ የተዘጋጀውን የአዲስ አበባ ከተማ መሪ እቅድ ‹ሕገ-መንግስታዊ አይደለም በሚል መነሻ የተለያዩ መፈክሮችን እያሰሙ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው ነበር፡፡ ሰልፉ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተካሂዶ እንደተጠናቀቀ በሰልፍ ምክንያት የቀረውን የመጨረሻ ክላስ ሚያዚያ 18/2006 ዓ.ም ለማካሄድ ተማሪዎቼ ጋር ቀጠሮ ይዤ ብለይም ‹ሰው ያቅዳል ፣ እግዜር ይስቃል› እንደሚባለው ሆነና በዛች ሚያዚያ 17/2006 ዓ.ም ማምሻ ላይ እንደ ወልደጊዎርጊስ ወልደ ዮሃንስ ‹የመንግስትን ዙፋን በሕዝባዊ አመፅ ልትነጥቅ አሲረሀል› በሚል ክስ በቁጥጥር ስር እንደዋልኩ የደህንነት ግሪሳዎች (8 ወይም 9 የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አባላት ) አበሰሩኝ፡፡

) ነገ ጠዋት 3 ሰዓት እንዲገኙ ብለው በስልክ ቢጠሩኝ ‹እሺ ነገ ሶስት ሰአት ላይ ክላስ አለኝ ከክላስ ወደ 9 ሰዓት አካባቢ አመጣለሁ › ብዬ የምቀርበውን ሰው ይሔን ሁሉ ሀይል ከሁለት መኪና ጋር በመመደብ ላከበረኝ መንግስቴ ‹ጉዳት› ባሰብኩ ግዜ ነው፡፡ ላክባሪዬ ውለታ መላሽ ያርገኝ i

ዓለሜ- ደብዳቤዬን እያነበብሽው እንደሆነ ተስፋ አለኝ፡፡ በቁጥጥር ስር ውሏል የምትለው ሀረግ ድሮም ትንሽ ፈገግ ታደርገኝ ነበር፤ አሁን ደሞ እኔን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከአዲስ አበባ የመጣው የደህንነት ቡድን መሪ የመሰለኝ እድሜው ትንሽ ገፋ ያለ ሰው አንድ ሶስቴ ስልክ እየደወለ (ለማን ይሆን) ‹በቁጥጥር ስር አውለነዋል› እያለ መልክት ሲያስተላልፍ ስሰማ ፈገግ ማለቴ አልቀረም፡፡ ሀሳቤ ልቤ ፣ ይሄውልሽ ከስራ ቦታዬ ‹ሀገር ሰላም› ሕዝባዊ አመፅ ለመቀስቀስ አስበሃል በሚል ጥርጣሬ በቁጥጥር ስር የዋልኩት እንዲህ እንደገለፅኩት ነበር፡፡ ከሚያዚያ 17/2006 -ሀምሌ 11/2006 ዓ.ም ያሉት 84 ቀናት የተደጋገሙና ሕይወት አልባ በመሆናቸው እንዲሁ ከማሰለችሽ 5 ሁነቶችን ልፃፍልሽና ዘና በይ፡፡ ከሁነቶቹ በፊት ግን ስለ 84 ቀናቱ አጭር መግለጫ ልስጥሽ፡፡

የመጀመሪያዎቹን 75 ቀናት በፌደራል ወንጀል ምርመራ ዘርፍ (ማዕከላዊ) ጥብቅ ጥበቃ ክፍል (Siberia) ውስጥ 5 ቁጥር የተባለ 4 ሜትር በ5 ሜትር የሆነችና 5 ፍራሾችን በምትይዝ ክፍል ውስጥ ከረምኩ፡፡ ክፍሉ የተፈጥሮ ብርሀን በምንም አይነት መንገድ (ቀንን ጨምሮ) የማይገባበት ሲሆን፣ ለ24 ሰዓታት የመብራት ብርሀን ይበራበታል፣ መብራት ሲጠፋ በጄኔሬተር ሀይል ይተካል፡፡ ጄኔሬተሩ ነዳጅ ሲጨርስ ደግሞ ቀንም ሆነ ማታ ጨለማ ነው ባትሪ፣ ሻማ፣ ማንኛውንም አይነት ሰዓት መያዝ አይቻልም፡፡ ጠዋት 12 ላይ ለ10 ደቂቃ ፤ ማታ ከ10 ሰዓት አስከ 12 ሰዓት ለ 10 ደቂቃ ሽንት ቤት ለመጠቀም የክፍላችን በር የሚከፈት ሲሆን፤ በቀን ውስጥ ከ15 – 20 ደቂቃ ለሚሆን ጊዜ ደግሞ ከክፍላችን በየተራ ወጥተን ነፋስ/ፀሀይ እናየለን፡፡ ከዛ ውጭ በቀን ውስጥ ከ23 ለሚበልጠው ሰዓት የክፍሉ በር ዝግ ሲሆን ጮክ ብሎ ማውራትና መዝፈንም ቅጣት ያስከትላል፡፡

ወዳጄ በነዚህ 75 ቀናት ስንት ‹አሸባሪ› ወዳጆችን አፈራሁ መሰለሽ፡፡ መንግስቴ የ 15 እና የ14 ዓመት ልጆችን በአሸባሪነት ጠርጥሮ እንደሚያስርም ለመረዳት ችያለሁ፡፡ አብረውኝ በእስር የነበሩት ወዳጆቼ ጥርጣሬ አጅግ የተለየ ነው፡፡ ከአል-ሸባብ አስከ ኦብነግ እስከ ኦነግ እስከ የቤኒሻንጉል ጉምዝ ሕዝቦች ነፃ እውጭ ግንባር እስከ አቂዳ(አዲስ የሽብር ቡድን)… ስቃይን መማር ጥሩ ነውና ሁለት ለሚሆኑ ቀናት ብቻዬን በመታሰሬም solitary confinement ን experience ለማድረግ ‹ታድያለሁ›፡፡ በርግጥ ብቻዬን ታስሬ ነበር ከምል ካንቺ ሀሳብ ጋር ታሰርኩ ብል ይቀለኛል፡፡

አምስቱን ሁነቶች ዘንግቼ ስለ ስቃዬ ተንዛዛሁብሽ ይሆን? ለዚህ ተግባሬ በእስረኛ ቋንቋ ‹ተፀፅቻለሁ›፡፡ በቃ ወደ ጉዳዮቹ፡፡ ከዚህ በታች የምገልፃቸው ሁነቶች የ84 ቀናቱ የእስር ወቅት (የምርመራ) ጊዜ ምን እንደሚመስል እንደነበር ያስረዱሻል ብዬ አስባለሁ፡፡ (ሁሉም በእውነት እኔ ላይ የደረሱ ጉዳዮች ናቸው)፡

1.

ሚያዝያ 17/2006 ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ ከምኖርበት አምቦ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ከደህንነቶች ጋር በቤት አውቶሞቢል እየተጓዝኩ ነው፡፡ አንድ ልጅ እግር ደህንነት ጠየቀኝ

‹‹ዘላለም የህግ መምሕር ነህ አይደል..››

እኔ

ማለትህ እጅግ ያሳዝናል፡፡ ለማንኛውም እንኳን ተማሪዎቹን ሳታበላሻቸው በጊዜ በቁጥጥር ስር ዋልክ፡፡ ኧረ ለመሆኑ ከውጭ ስንት ሽህ ደላዮችን አግኝተሻል? Any way በልማታችን ቀልድ የለም” አለኝ፡፡ (እኔም ባስተማርኩባቸው 4 አመታት ስንት ተማሪዎችን ‹እንዳበላሸሁ › እያሰብኩና ልማታችን በወለደው የአስፋልት መንገድ ፏ ብዬ ከምሽቱ 3፡50 ላይ ማዕከላዊ ከቸች፡፡

2.

እመቤቴ – መንግስት ሕዝባዊ አመፅ ለመቀስቀስ አሲራችኋል፤ ለዚህም በቂ ማስረጃ አለኝ በማለት ያሰረን ቢሆንም መንግስት ሀሳቡ እውነት ይሆንለት ዘንድ የእኛን ‹አዎ አሲረናል› የሚል መልስ በማባበልና በሀይል ለማግኘት ከመሞከር ውጭ ሌላ ያቀረበው አንዳችም ማስረጃም ሆነ መረጃ(በጠ/ሚንስትሮች ቋንቋ) አልነበረም/የለምም፡፡ ለዚህም ይመስላል በማእከላዊ የቆየሁባቸው ቀናት ምርመራው በሙሉ ‹አላማችሁ ምንድን ነው በሚል ሕይወት አልባና አሰልቺ ጥያቄ የተሞላው፡፡ እኔም የዚህ ጥያቄ ሰለባ ሁኜ ከረምኩልሽ፡፡ እንዲህ ላጫውትሽ፣

መርማሪ ፖሊስ (በተደጋጋሚ) – እንደ ዞን 9 አላማችሁ ምንድን ነው?

እኔ

መርማሪ ፖሊስ፡ እሱ ሽፋን ነው፤ እውነተኛ ዓላማችሁን ተናገር?

እኔ

መርማሪ ፖሊሱ እንድንመልስለት የሚፈልገው ‹ከበላይ አካል› ይዞ እንዲመጣ የታዘዘውን መልስ፤ “አላማችን እንደ ጭቃ ተረግጦ፤ እንደ ገል ተቀጥቅጦ የሚገኘውን ጭቁን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከተጫነበት ቀንበር ነፃ ማውጣት ነው፡፡ ለዚህም መሳካት ሕዝባዊ አመፅ ማደራጀትን እንደ ዋነኛ ዓላማ አድርገን ነው የተቋቋምነው፡፡”

ሲሆን ይህ ደግሞ ከአላማችን ጋር የማይገናኝ መንግስታዊ ፍላጎት በመሆኑ እንዲህ አይነት መልስ ከእኔ ማግኘት እንደማይችል የተረዳው መርማሪ በተደጋጋሚ አስብበት በማለት ይሰናበተኝ ነበር፡

3.

የእኔ ፅጌሬዳ አላማችን እንደ ቡድን ባይጠይቁኝ ኑሮና የግል ዓላማዬን ቢጠይቁኝ አላማዬ ‹አንቺ› እንደሆንሽ ከመናገር ወደኋላ እንደማልል ታውቂያለሽ አይደል? የሆንሽ ‹አሸባሪ› ነገር፡፡ Any way ምርመራዬ ቀጥሎልኛል፡፡ ሁለት መርማሪዎች እየተፈራረቁ ገራሚ ገራሚ ጥያቄዎችን እየጠየቁኝ ነው፡፡ እነሆ ፡

መርማሪ ፖሊስ፡ ከአለም መሪዎች ማን ማንን አግኝተህ ታውቃለህ?

እኔ

መርማሪ ፖሊስ፡ እኛ እኮ ያለመረጃ አይደለም እየጠየቅን ያለነው፡፡ ጉድ ሳይመጣብህ ብትናገር ይሻላል፡፡

እኔ፡ እስኪ አስታውሱኝና ምን እንደተነጋገርን ልናገር፡፡ በርግጥ ባለፈው የኔልሰን ማንዴላ ማስታወሻ ፕሮግራም በ አፍሪካ ህብረት በተከበረበት ወቅት ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ አግኝቻቸዋለሁ፡፡ ሌላ የማስታውሰው የለም፡፡

መርማሪ ፖሊስ፡ ህም! እሺ ዘንድሮ ኦባማ ፊት ንግግር ለማድረግ ከተመረጡ 3 ኢትዮጵያውያን አንዱ አንተ አይደለህም?

እኔ፡ ‹‹እንዴ ኦባማ ፊት ንግግር ነው ያልከኝ? ድንገት ከታሰርኩ በኋላ ተመርጬ (በማሾፍ ድምፀት) ከሆነ አላውቅም፡፡ወይ በስም መመሳሰል ሊሆን ይችላል፡፡ አሜሪካ በአፍሪካ ጉዳይ ምን አግብቷት ነው? ላልከኝ ግን ወጣቶችን Empower ማድረግ ችግር ያለው አይመስለኝም ፤ ደግሞ በረሀቡም በድርቁም ጊዜ ርዳታ የምታደርገው እኮ አሜሪካ ነች፡፡ ምን አግብቷት ነው የምትረዳው አይባልም መቼም?!››

መርማሪ ፖሊስ፡ አሁን ዘመኑ የልማት ነው፤የምን ረሀብ ነው የምታወራው? በል ተወው፡፡

(‹ፈሪ ውሃ ውስጥ ያልበዋል› ሰምተሻል ውቤ? መንግስቴ ብቻውን እየሮጠም ፍርሃቱና ስጋቱ ብዛቱ፡፡ የሚቆጨኝ ነገር ከዓለም መሪዎች ማን ማንን አግኝተሃል? ‹ስባል› ከሲሪላንካ ፕሬዜዳንት ጋር ተገናኝቼ ወደ ደቡብ አሜሪካ ፔሩ በመጓዝ ማቹፒቹን ጎብኝቻለሁ ብዬ ብናገር ኑሮ፤ ክሳችን ላይ ‹ከሲሪላንካ መንግስት ባገኘው የገንዘብና የመሳሪያ ድጋፍ ወደ ፔሩ በመጓዝ ሕገ-መንግስት እንዴት እንደሚናድ በማቹፒቹ ኮረብታ ስልጠና ወስዶ ተመልሷል፡፡ ለዚህ እንደ ማስረጃ ይሆን ዘንድ ላፕቶፔ ውስጥ የተገኙት ከ300 በላይ የቼጉቬራ ምስሎችና Machu Pichu: The Mecca of Hippies” የሚል ባለ 22 ገጽ ‹ሰነድ› አብሮ ይያዝልኝ ነበር፡፡ ሲያበሳጭ

4.

ፍቅር አደከምኩሽ አይደል?! ልጨርስ ስለሆነ ትንሽ ታገሺኝ፡ በዛውም ‹ፍቅር ታጋሽ ነው› የሚለውን Paulian ወንዴነት፤ ‹ፍቅር ታጋሽ ናት› በሚል ማስተካከያ እንድናርመው፡፡ የዚህ የምርመራ ነገር እኮ አላልቅልኝ አለ፡፡ በእስሬ ወቅት ሌላው በተደጋጋሚ እንዳስረዳ ስጨቀጨቅበት የነበረው ጉዳይ ‹ኒዮ-ሊብራልነቴና ልማትና ዲሞክራሲ ጎን ለጎን አብረው ይሄዳሉ ማለቴ ነበር፡፡

መርማሪ ፖሊሶቹ እየተቀያየሩ ስለኢህአዴግ የፖሊሲ ትክክለኛነት ‹ያስረዱኝ› ነበር፡፡ “አንተ ምን ጎደለብኝ ብለህ ነው ነጭ አምላኪ የሆንከው ? ትንሽ የተስፋ ጭላንጭል ስናይ አንተና ጓደኞችህ አይናችሁ ለምን እንደሚቀላ እስኪ ንገረን ? ይህች አባቶቻችን ‹በደምና በጾም› ያቆዩልንን አገር አንተና ያንተ ትውልድ ግን ውበቷ እና ድንቅነቷ ላስጎመጃቸው ነጮች ለመሸጥ መደራደር ጀመራችሁ….” እያሉ ‹በባንዳነት› ሲከሱኝ ከረሙ፡፡ የሀገሪቱ ውበትና የነጮች በውበቷ መጎምጀት ነገር ሲነሳ ጊዜ ‹አንቺ› ትስቂ ዘንድ የሚከተለውን አንቀፅ አሻግሬ ታደሰ የተባሉ ፀሐፊ ከ 50 ዓመት በፊት ‹እኔና አንተ› ካሉት ጽሁፋቸው ላይ እጠቅስልሻለሁ

“ኢትዮጵያ እጅግ ያማረች፤ የተዋበች ፤የተደነቀች፤ላያት ሁሉ የምታማልል፤የምታዘናጋ…….ናት፡፡ ዓይኗ የብር አሎሎ መለሎ ከአጥቢያ ኮከብ የተፎካከረ….. ነው፤ አገራችን ኢትዮጵያ ፅጌረዳ መስላ የሰኔን ቡቃያ ትመስላለች፡፡ የመስከረም አበባ ሆና በሩቅ ትስባለች፤የመስህቧ ኃይል ማግኔት ምስጋን ይንሳው፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ ጥርሷ እንደ በረዶ ሆና ለፈገግታ ያህል ትንሽ ከንፈሯን ስትገልፀው እንኳንስ ለሰው ግብዙ መልዓክ ያብዳል፡፡ ኢትዮጵያ ፀጉሯ የሀር ነዶ ነው፤ኢትዮጵያ አጠረች ፤ረዘመች፤ወፈረች፤ብሎ ስለአካሏ መናገር አይቻልም፡፡ እንዲያው ዝም ይሻላል፡፡ በጠቅላላው ኢትዮጵያ ውበቷ ሰነፉን ይገድላል፡፡ ብርቱውን አነሁልሎ ያሳብዳል፡፡ እግዚአብሔር፤ኢትዮጵያን ሲፈጥር በብዙ ተራቋል፤ተጠቧል፤ ውበቷ በሩቅ ይስባል፤ አጥንትም ይሰብራል፤አዕምሮን ይሰውራል፡፡ ይገርማል!” ይላሉ፡፡

ምንም እንኳን ውበት እንደተመልካቹ ነው ቢባልም፤ መርማሪዎቹ በዚህ ዓይነት Vulgar Natioanlism ሰክረው እኔና የእኔ ትውልድ ሀገሪቱን ‹በውበቷ ለሰከሩ› ነጮች ልንሸጣት እንደተዋዋልን እየነገሩኝ ነው፡፡ ይገርማል! ዲሞክራሲን ከልማት እኩል ማስኬድ ነውር የለበትም፤ ተገቢም ነው ማለት እንደ አገር ሽያጭ ውል የሚቆጠርበት ብሎም ‹ሩቅ አስባ ሩቅ ለማደር እየተጋች ያለችን አገር› መንገድ ላይ በጠረባ ለመጣል የተደረገ ሙከራ ተደርጎ የሚወለድባትና ‹አሸባሪ› የምንሰኝባት፣ ‹ለፈገግታ ያህል ትንሽ ከንፈሯን ስትገልጠው እንኳን ሰውን ግብዙን መልዓክ የምታሳብደው ኢትዮጵያ!

ሊቁ ገብረሕይወት ባይከዳኝ ‹ልማትን ሲተች› “እውቀት በሌለው ሕዝብ አገር መንገድና የምድር ባቡር ቢሰራ ሕዝቡ እንዲደኸይ ያፋጥናል እንጂ አይጠቅመውም፡፡ ጥቅሙ ከርሱ ጋር የሚገበያዩ አዋቂ ሕዝቦች ነው” በማለት ‹ልማት ብቻውን ዋጋ የለውም› ሲል ይበይናል፡፡ ገብረሕይወት የእኛው ትውልድ አባል ቢሆን ኖሮ “የኢኮኖሚ እድገቱን በመካድ፤ ሕዝቡ በአዕምሮ መናወጥ ምክንያት የዘረጋነውን የባቡር ሀዲድ ፈነቃቅሎ እንዲጥልና ሌሎች የሽብር ተግባራትን እንዲፈፀም በማነሳሳት ‹ወንጀል›” መመርመሩና መከሰሱ አይቀሬ ነበር፡፡

ውዴ! ያን ‹አሸባሪ› ሳቅሽን ሳስብ በፀረ-ሽብር ሕጉ መሠረት ጉዳይሽ ሊታይ ይችላል የሚል ስጋቴ የበዛ ነው፡

5.

እንዲያው ለዚህ 84 ቀናት ውስጥ የሆንኩትን ሁሉ እንዳልፅፍልሽ እንዳትሰለችብኝ ፈራሁ፡፡ እያንዳንዱን ሁነት በ Diary መልክ ከትቤ እንዳልክልሽ በነዛ ቀናት ውስጥ ብዕርም ሆነ ነጭ ወረቀት ይዞ መገኘት ‹ከፍ ብሎ አንገትን፣ ዝቅ ብሎ ባትን› ባያስቆርጥም ዛቻና ዱላን ማስከተሉ አይቀርም ነበርና ልከትብ አልቻልኩም፡፡ እንዲሁ በደፈናው ግን አንዳንድ ጉዳዮችን ብዘረዝርልሽ፡

በነዛ ክፉ ቀናት ከምሽቱ 12 ሰዓት እንቅልፍ መተኛትን ለመድኩ፡፡ ይሔም ነገር መልካም እንደሆነ አየሁ፡፡ ምክንያቱም ሌሊት ከእንቅልፍ ተቀስቅሰው ራቁታቸውን ሲደበደቡ አድረው ከ 3 እና 4 ሰዓታት ቆይታ በኋላ በነፍስ ወደ መኝታ ክፍላችን የሚመጡ የእስር ጓደኞቼን (Cellmates) ስቃይና ሰቆቃ ላለመስማት፡፡በ2004 ዓ.ም የፌዴራል ፖሊስ ‘Cyber crime Laboratory’ ተቋቁሟል መባሉን ሰምቼ ‹እንግዲህ cyber criminal ሁሉ የት ትገቢ? አለቀልሽ!› ብዬ ነበር፡፡ በጊዜ ቀጠሮ ጊዜ እንደተረዳሁት ደግሞ ‹ያለችን አንዲት ኮምፒውተር ናት የእነዚህ ልጆች ዳታ በአንድ ኮምፒውተር መርምረን መጨረስ ስላልቻልን የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠን› ሲባል ነው፡፡ አረ እንዲያውም ‹እስኪ Anti-virus ካለህ ኮምፒውተሬ ላይ ጫንልኝ› ተብዩ ሁሉ ነበር፡፡ ‹ለሽብር ተግባራት› መመርመሪያ ያልሆነ ‘Cyber crime laboratory’ ለመች ሊሆን ነው?

– ‹አንተ ከየት ነው የመጣኸው?› (አንድ ተማሪ ወዳጄን)

– ‹ከሀሮማያ ዩኒቨርስቲ›

– ‹አሀ እናንተ ናችኋ…..›

****

– ‹አንተኛውስ ከየት ነው የመጣኸው?!›

– ‹ከወለጋ ዩኒቨርስቲ›

– ‹አሁን ኦሮሚያ ብትለማ ምን የሚያስከፋ ነገር አለው?!….›

*****

– ‹አንተስ ከየት ነው የመጣኸው› (እኔን ነው)

– ‹ከአምቦ ዩኒቨርስቲ›

– ‹ሕዝቡን እርስ በርስ አጋጭታችሁ ከተማዋን በደም ያጠባችኋት እናንተ….›

– ‹አረ እኔ ከግጭቱ በፊት ነው የታሰርኩት›

– ‹በእውነት ነው የምልክ እድለኛ ነህ፡፡ የኦሮሚያን ልማት ተቃወመ ተብለህ በታሪክ አለመስፈርህ በጣም እድለኛ አድርጎሀል፡፡›

(ለመሳቅ ሁላችንም የጎልማሳውን ከክፍል መውጣት እየተጠባበቅን እኮ ነው ውዴ) – ሁሉ ቧልት የሆነበት ሀገር!

በነዚህ ሁሉ የጉድ ቀናት ለምን እንደታሰርኩ ትክክለኛውን ምክንያት የሚነግረኝ አካል ፍለጋ ሁሌም አስብ ነበር፡፡ መታሰሬ ግን አያስገርመኝም፤ አያስከፋኝም! ደስታን በሔድኩበት ሁሉ እፈልጋለሁ፤ የእድል ነገር ሆኖ ደስታም ከእኔ አይርቅም፡፡ ፍቅሬ ለረጅም ዘመናት ‹የሰው የመኖር አላማ ማወቅ ነው› የሚለውን Aristotlian (አሪስቶትሊያን) አስተምህሮ በልቤ ይዤ እኖር ነበር፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ‹የመኖር ዓላማ መደሰት ነው› የሚለው አስተምህሮ በአርስቶትሉ ‹የማወቅ ዓላማ› ደባልቄ ይሔው እየተደሰትኩልሽና እያወቅሁልሽ እገኛለሁ፡፡ ‹አንች› የደስታዬ ምንጭ፡

‘‘Thanks to you….For you exist’

Clézio

ስለክሴና ስለተስፋዬ ሌላ ደብዳቤ እፅፍልሻለሁ፡፡

P.S አሳሪዬ ሆይ ልብ ይስጥህ!

ያንችው ዘላለም

ከብዙ ፍቅር ጋር!

እኛ ኢትዮጵያውያን የዚያ ብሔር ወይም የዚያ ጎሣ አባል ሆነን የተፈጠርነው የሆነ ቅጽ ሞልተን ወይም ዕጣ ተጣጥለን አይደለም፡፡ ተፈጥሮ ነው፡፡ በባለጠበንጆቹ ወያኔዎች የተነጠቅነውን መብትና ግዴታን በማስከበር፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን መገንባት የምንችለው ግን እንደ ብሔር ወይም ብሔረሰብ አባል ብቻ ታስረንና ጠበን ሳይሆን፣ እንደ አንድ አገርና ሕዝብ በጋራ ስንቆምና እጅ ለእጅ ስንያያዝ ነው፡፡

ኢትዮጵያዊነት እንዳያብብ የሃገር መልካም ታሪክ እንዳይወራ ጠንክረው የሚሰሩት ወያኔዎችን የማሳፈር እቅዳቸውን የማደባየት ግዴታው የኛ የኢትዮጵያውያን ነው:: የዓለም፣ የአኅጉራዊና የአገራዊ ፈተናው እየከበደ በሄደ ቁጥር የኢትዮጵያዊነት መለኪያና የጥንካሬው ማረጋገጫ እየጨመረና እየከበደም መጥቷል፡፡ እስካሁን ድረስ ያለው ኢትዮጵያዊነታችን ጠንካራ አይደለም ወይ? የሚል ጥያቄ ሊነሳና አነጋጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ በግልጽ እንነጋገር ከተባለ ግን ኢትዮጵያዊነታችን ደካማ ነው አንልም እንጂ፣ ካለው የኢትዮጵያዊነት ስሜት በላይ እጥፍ ድርብ ጠንካራ የሆነ ኢትዮጵያዊነት ያስፈልገናል ብለን ግን በድፍረትና በእምነት እንናገራለን፡፡

አንድነት እና ጥንካሬ በዜጎች መሃል እንዳይሰርጽ በወያኔ የሚሰራውን ደባ የማክሸፍ ሃገራዊ ግዴታ አለብን:: ኢትዮጵያዊ ሚናችንን በአግባቡ ለመወጣት እንኳ ጠንካራ አንድነትና ኢትዮጵያዊነት ያስፈልገናል፡፡ ይህ ጠንካራ ኢትየጵያዊነት ነው ሚና እንድንጫወት ዋስትና የሚሆነው፡፡

ልድገመው !!!
እኛ ኢትዮጵያውያን የዚያ ብሔር ወይም የዚያ ጎሣ አባል ሆነን የተፈጠርነው የሆነ ቅጽ ሞልተን ወይም ዕጣ ተጣጥለን አይደለም፡፡ ተፈጥሮ ነው፡፡ ይህ እንዳለ ተቀብለን የብሔራችንን ባህልና ቋንቋ እናከብራለን፤ እናሳድጋለን፤ ይህንን ማድረግ ማንንም አይጐዳም፡፡ ሁላችንን ግን ይጠቅማል፡፡ ይህን እያከናወንን ግን ከድህነት በመላቀቅ፣ በመበልፀግ፣ ሰላምና መረጋጋትን እውን በማድረግ፣ መብትና ግዴታን በማስከበር፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን መገንባት የምንችለው ግን እንደ ብሔር ወይም ብሔረሰብ አባል ብቻ ታስረንና ጠበን ሳይሆን፣ እንደ አንድ አገርና ሕዝብ በጋራ ስንቆምና እጅ ለእጅ ስንያያዝ ነው፡፡

ከዚህ ውጪ ሌላ መንገድ ወይም አማራጭ የለም፡፡
https://www.facebook.com/minilik.salsawi

ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ኢህአዴግ ምንጮች እንደገለጹት በሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሙሃመድ ኡመር እና በክልሉ የካቢኔ አባሎች መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ተከትሎ በጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ጽ/ቤት በተካሄደው አስቸኳይ ግምገማ ፣ ፕሬዚዳንቱ ፈጸሟቸው የተባሉ በርካታ ወንጀሎች ተዘርዝረው ቀርበዋል። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በሰብሳቢነት በመሩት ግምገማ ላይ ም/ል ጠ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የጠ/ሚኒስትሩ የጸጥታ ዘርፍ …

ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በባቲ ወረዳ ልዩ ስሙ ቡርቃ በተባለ ቀበሌ አካባቢ የሚኖሩ የሁለቱ አጎራባች ክልሎች ነዋሪዎች በተለያዩ ጊዜያት በተኩስ እየተጋጩ በሁለቱም ወገን ሰዎች እየሞቱ ቢሆንም ፤የሁለቱ ክልል መሪዎች ጉዳዩን ለመፍታት ምንም ዓይነት ጥረት አለማድረጋቸው እንዳሳዘናቸው የባቲ ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ በቡርቃ  ቀበሌ  የተቀበረ ወርቅ አለ ተብሎ መነገሩ ለግጭቱ መባባስ ምክንያት መሆኑን የሚናገሩት …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሐምሌ ወር ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ደመወዝ ጭማሪ መደረጉ ከተነገረ  በኃላ ይበልጥ የተባባሰውንየዋጋንረትለማስታገስመንግሥትእየወሰዳቸውያሉትየሃይልእርምጃዎችውጤትባለማምጣታቸውከፍተኛአመራሩውጥረትውስጥ ከመወደቁጋርተያይዞአምራች፣አስመጪናአከፋፋይነጋዴዎችዋጋአለመጨመራቸውንለሕዝብእንዲናገሩ እየተገደዱ ነው። በሰኔ ወር አጋማሽ የሲቪል ሰርቪስ ቀን ሲከበር ከአንድ ዓመት በላይ ተጠንቶ የዋጋ ንረት በማያስከትል መልኩ የደመወዝ ጭማሪ መደረጉ በጠ/ሚኒስትርኃ/ማርያምደሳለኝከተነገረበሃላበዋናነትበሸቀጦች፣በምግብናበቤትኪራይዋጋላይከፍተኛንረትመከሰቱየመንግሥትን ጭማሪ ዋጋቢስነት ያሳየ ከመሆኑም በላይተ አማኒነቱንም ጎድቶአል፡፡ በተለይየጭማሪውመጠንእጅግዘግይቶሲነገርገዥውፓርቲበራሱአባሎችናደጋፊዎችጭምርእየተተቸመምጣቱከፍተኛአመራሩንአደናግጦአል፡፡በዚህም መደናገጥ በየመንደሩየሚገኙተራሱቆችንከማሸግናነጋዴዎችን ከማሰርጀምሮበራዲዮናበቴሌቪዥንነጋዴውንየማጥላላትናየማስፈራራትስራዎችንሲያከናውንየቆየቢሆንም የዋጋንረቱአሁንምቢሆንሊረጋጋአልቻለም። የንግድ ሚኒስቴር ከደመወዝ …

ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብአዴን ከፍተኛ ሹሞች ከከተማው ህዝብ ተወካዮች፣ ከኢህአዴግ አባላትና ከተለያዩ የመስሪያ ቤት ሃላፊዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ነዋሪዎች የተለያዩ ችግሮችን አንስተዋል። አንድ አስተያየት ሰጪ የጤና ተቋማት መድሃኒት በማጣታቸው አግልግሎት እየሰጡ አለመሆኑን ተናግረዋል ሌላ አስተያየት ሰጪ ደግሞ የመብራት ችግር የከተማው ችግር መሆኑን ገልጸዋል ኮብልስቶን ለይስሙላ ተብሎ የሚሰራ በመሆኑ ለህዝቡ ችግር እየፈጠረ …

ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በባህርዳር ከተማ ነዋሪ የሆኑት የአቶ መለስ ዜናዊ የቅርብ ዘመድ አቶ ወልዱ ወልደአረጋይ በ7 አመትፅኑ እስራት መቀጣታቸውን የክልሉ ዘጋቢያችን ገልጻለች። መንግስት ማግኘ ትየነበረባትን ከ900 መቶ ሺህ ብር በላይ እንዳያገኝ ያደረገ ታክሰ በማጭበርበር ወንጀል የተከሰሰው ወልዱና ቤተሰቡ ኃላፊነት የተወሰነየግል ማህበርበእስራትናበገንዘብእንዲቀጣየምዕራ ጎጃም ዞንየባህርዳርምድብችሎትውሳኔማስተላለፉንየአማራክልልጠቅላይፍርድቤትየውሳኔመዛግብትዋቢ በማድረግ ገልጻለች። የምዕራብጎጃምፍርድቤትባህርዳርምድብችሎት  ወልዱናቤተሰቡሀላፊነቱየተወሰነየግልማህበር፣ አቶ ወልዱወልደአረጋይ እና አቶብስራትወልዱወልዳረጋይየተጨማሪእሴትታክስሰብስቦያለማሳወቅናያለመክፈልእንዲሁምየተጨማሪእሴትታክስባልሆነደረሰኝግብይትበማካሔድወንጀል በአመትስድስትነጥብሶስትሚልዩንብርመሰብሰባቸው …

የኢትዮጵያ መንግስት ያስረናል ወይም ሌላ ጠንካራ እርምጃ ይወስድብናል ብለው የሚሰጉ የግል ጋዜጠኞች ሃገሪቱን ጥለው መሰደዳቸውን እንደ ቀጠሉ ነው።ከሳምንት በፊት ለግል መገናኛ ዘዴዎች ይሰሩ የነበሩ ሶስት ጋዜጠኞች ከሃገር ተሰደዋል።በያዝንው ሳምንት ደግሞ ሌሎች ሰባት ጋዜጠኞች ወደ ውጭ ሃገር ተሰደዋል።

ወደ ደቡብ ሱዳን በብዛት የሚገባው የጦር መሳሪያ ጦርነቱ እንዳይቆም እያደረገ ነው ሲሉ የጦር መሣሪያዎች ዝውውር ተቆጣጣሪዎች ያሳስባሉ ።አንዳንድ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ደግሞ በደቡብ ሱዳን ላይ የጦር መሣሪያ ሽያጭ ማዕቀብ እንዲጣል እየጠየቁ ነው ።

የኢትዮጵያ መንግስት ያስረናል ወይም ሌላ ጠንካራ እርምጃ ይወስድብናል ብለው የሚሰጉ የግል ጋዜጠኞች ሃገሪቱን ጥለው መሰደዳቸውን እንደ ቀጠሉ ነው።ከሳምንት በፊት ለግል መገናኛ ዘዴዎች ይሰሩ የነበሩ ሶስት ጋዜጠኞች ከሃገር ተሰደዋል።በያዝንው ሳምንት ደግሞ ሌሎች ሰባት ጋዜጠኞች ወደ ውጭ ሃገር ተሰደዋል።

በ ዩ ኤስ አሜሪካ የእርዳታ ድርጅት (USAID)አስተባባሪነት፣ በተለያዩ የግብርና ዘርፎች ላይ ያተኮረ ተመራማሪዎችንና ባለሙያዎችን ያሰባሰበ ዐውደ ጥናት አዲስ አበባ ውስጥ በመካሄድ ላይ ነው። ከአፈር ማዳበሪያ አጠቃቀም አንስቶ የጥራጥሬ እኽልንና

በምሥራቅ ዩክሬን ለተባባሰዉ ዉጊያ መፍትሄ ለመፈለግ ሁለት እንቅስቃሴዎች በተከታታይ ተይዘዋል። በመጪዉ ሳምንት የዩክሬን ፕሬዝደንት ፔትሮ ፕሮሼንኮና በሀገራቸዉ በተፈጠረዉ ብጥብጥ እጇን ከታለች በማለት የሚከሷት የሩሲያ አቻቸዉ ቭላድሚር ፑቲን ቤላሩስ ላይ ተገናኝተዉ እንደሚነጋገሩ ተገልጿል።