የቴሌኮሙኒኬሽን ሰራተኞች እና የዶክተር (በተገዛ ዲግሪ) ደብረጺሆን አለመግባባት ወደ ስድብ አመራ።

"..እንዲህ አይነት ጥያቂዎችን እነማን እንደሚጠይቁ እናውቃለን ደንቆሮ ዝቃጭ .." ደብረጺሆን
"በስልጠናው ላይ ሰራተኛው ለኢሕአዴግ ያለውን ጥላቻ በሰፊው አሳይቶበታል። " የካድሬዎች ሪፖርት
ይህን ሰሞን ለምርጫ የሚሆን ድጋፍ እና አዳዲስ አባላትን ለመመልመል የወያኔው ጁንታ የመንግስት ሰራተኞችን እና የዩንቨርስቲ ተማሪዎችን የመልካም ልማታዊ አስተዳደር በሚል ሽፋን ለፖለቲካ አጀንዳነት ሊጠቀምባቸው በማሰብ እያደረገ ያለው ስልጠና ከአለመግባባት አልፎ እስከ ስድብ መድረሱ ሰልጣኞችን አስቆጥቷል።

በዚሁ መሰረት የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኞች ለስልጠና የጠራው የወያኔ ቡድን ካድሪዎቹ የሰራተኛውን ጥያቄ መመለስ ስላቃታቸው ወደ ደብረጺሆን ያስተላለፉት ሲሆን ዶክተር (በተገዛ ዲግሪ ) ደብረጺሆን በከፍተኛ ቁጣ በተቀላቀለበት ሁኔታ ሲመልሱ ተስተውሏል። ሰራተኞቹ የሃይማኖት ነጻነት እና ሙስሊሞች ፣ ዞን 9 ፣ የኦሮሞ ተማሪዎች ፣ የኑሮ ውድነት ፣ የዘረኝነት መስፋፋት ፣ የሃገሪቱ ታሪክ ማበላሸት እና የሃገር ዳር ድንበር ፤ የሚታሰሩ ዜጎች እና የተቃዋሚዎች ሮሮ …. ፣ ወዘተ ያቀረቧቸው ጥያቂዎች ከደብረጺሆን ጋር ካለመግባባት በስድብ እና በቁጣ የታጀቡ እንደነበሩ ታውቋል።

በወያኔ ካድሬዎች ዘንድ ከፍተኛ መደናገጥ የታየበት ይህ የኢትዮ ቴሌኮም ስልጠና ዶክተር የሚባሉት ደብረጺሆን በከፍተኛ ቁጣ በሺዎች የሚቆጠረውን ሰልጣኝ የመንግስት ሰራተኛ …..ቁጣ በተቀላቀለበት አምባገነናዊ መንፈስ ድንጋጤን ተላብሰው ….. ደንቆሮ …..ደደብ … የዘቀጠ .. በሚሉ የስድብ አጀቦች ጥያቄዎቹ የነማን እንደሆኑ እናውቃለን .. በሚል ማስፈራሪያ ሰራተኛውን ማሰልታን ሳይሆን ማስጠንቀቅ በሚል እንዲሁም ለመጪው ጊዜ እርምጃ እንደሚወሰድ መል እክት በሚያስተላልፍ መልኩ ሲዝቱ ሲሳደቡ ተስተውሏል።

ዶክተር በሚባሉት ደብረጺሆን መልስ ሰራተኛው ከፍተኛ ቁጣ ይሰማ ሲሆን ከአሁን በኋላ በሚደረጉ የስልጣና ቀኖች ላይ ምንም ጥያቄ ላለመጠየቅ እና አስተያየት ላለመስጠት ሰራተኛው አድሞ ወደ ስልጠናው እንደገባ ሲታወቅ የወያኔ ካድሬዎች የሰራተኛውን ድፍርት እና በጥያቄዎች መግነን ተከትሎ ድንጋጤ የፈጠረባቸው ቢሆንም ከጀርባ ግን ሰራተኛውን ሲያበረታቱ ተስተውሏል።
ከስልጠናው መልስ ካድሪዎች ለአለቆቻቸው የሚያቀርቡት ሪፖርት እንደሚጠቁመው የመንግስት ሰራተኛውም ይሁን የዩንቨርስቲው ተማሪ ለኢሕአዴግ ያለውን ጥላቻ የሚያሳይ መሆኑን እንደሆነ ከፓርቲው ጽ/ቤት የተገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።ሚኒሊክሳልሳዊ