በመጠጥ ውኃ ችግር ውስጥ ከሚገኙት ሦስት የትግራይ ክልል ከተሞች አንዷ ለሆነችው ታሪካዊቷ የአክሱም ከተማ ንፁህ የመጠጥ ውኃ ለማቅረብ 440 ሚሊዮን ብር ብድር ተገኘ፡፡

ለአክሱምና ለአካባቢዋ ንፁህ የመጠጥ ውኃ ለማቅረብ ለኢትዮጵያ ብድር የሰጠው የኩዌት መንግሥት ነው፡፡

የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አህመድ ሼዴና የኩዌት ፈንድ ለዓረብ ኢኮኖሚ ልማት ምክትል ዳይሬክተር ሚስተር ሀሜድ ኤስ አል ኦማር የብድር ስምምነቱን ሰኔ 9 ቀን 2007 ዓ.ም. ተፈራርመዋል፡፡

በዚህ ፕሮጀክት 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ማይጨው ወንዝ ላይ ግድብ በመገንባት፣ ለአክሱምና ለአካባቢው ንፁህ የመጠጥ ውኃ የማቅረብ ዓላማ የያዘ መሆኑን አቶ አህመድ ተናግረዋል፡፡

በዚህ ፕሮጀክት የውኃ ማጠራቀሚያ ጋኖች፣ የውኃ መሳቢያ ፓምፖች፣ ትራንስፎርመሮችና የማጣሪያ ጣቢያዎች ግንባታ ተካተዋል፡፡ 

ይህ ብድር በረዥም ጊዜ የሚከፈል ከመሆኑም በተጨማሪ፣ የኩዌት ፈንድ ለኢትዮጵያ የሚያደርገው ድጋፍ 110 ሚሊዮን ዶላር አድርሷል፡፡

በትግራይ ክልል በውኃ እጦት ችግር ውስጥ የሚገኙ ከተሞች ችግርን ለመፍታት፣ የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸው ከአካባቢው የሚመጡ መረጃዎች አስረድተዋል፡፡  

 

ፕሬዚዳንት አል በሽር ከደቡብ አፍሪካ እስኪወጡ በሱዳን የሚገኙ የደቡብ አፍሪካ ወታደሮች በጦር ኃይል ተከበው ነበር

የደቡብ አፍሪካ መንግሥት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለምን እንዳላከበረ ማብራሪያ ተጠየቀ 

ለአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ወደ ደቡብ አፍሪካ ፕሪቶርያ ያቀኑት የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሐሰን አል በሽር፣ የአገሪቱ ፍርድ ቤት በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ትዕዛዝ ቢሰጥም በሰላም ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡

የሱዳን ጦር ኃይል በበኩሉ የደቡብ አፍሪካ ሰላም አስከባሪ ኃይል አባላትን በቁጥጥር ሥር አውሎ እንደነበር ታወቀ፡፡

እ.ኤ.አ. በ2009 እና በ2010 በዳርፉር በተፈጸመው ጅምላ ጭፍጨፋ ምክንያት በዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት (አይሲሲ) የእስር ማዘዣ ዋራንት የተቆረጠባቸው የሱዳን ፕሬዚዳንት አል በሽር፣ ከአይሲሲ ውሳኔ በኋላ የደቡብ አፍሪካን ምድር ሲረግጡ ለመጀመርያ ጊዜ ነበር፡፡ 

የአይሲሲ ፈራሚ አገሮች አንድ የእስር ማዘዣ የተቆረጠበት ግለሰብ (መሪ) የመያዝና የማስረከብ ግዴታ ያለባቸው ሲሆን፣ ደቡብ አፍሪካም ከፈራሚዎቹ መካከል ነች፡፡ የኅብረቱን ስብሰባ ለመሳተፍ ወደ አካባቢው ያቀኑት ፕሬዚዳንቱ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ የደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቢሰጥም፣ የአገሪቱ መንግሥት ግን ፕሬዚዳንቱ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ በመፍቀድ አስመልጧቸዋል እየተባለ ነው፡፡ 

ተቀማጭነቱ ፕሪቶሪያ የሆነው አይዊትነስ ኒውስ የተባለ ሚዲያ እንደዘገበው ደግሞ፣ የደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አል በሽር በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ በዳርፉር አካባቢ የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ የደቡብ አፍሪካ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች የሚገኙባቸው ሦስት ካምፖች በሱዳን ጦር ኃይል ተከበው ነበር፡፡ የደቡብ አፍሪካ የመከላከያ ባለሥልጣናት እንዳረጋገጡት፣ የሱዳን ጦር ኃይል በቁጥጥር ሥር አውሏቸው የነበሩ ካምፖችን የለቀቀው ፕሬዚዳንት አል በሽር ከአገሪቱ መውጣታቸው በተረጋገጠ ጊዜ ነበር፡፡ 

የደቡብ አፍሪካ መከላከያ ኃይል ባለሥልጣናት በሱዳን የሚገኙት አባሎቻቸው ደኅንነትና የተባለውን ነገር እንዲጣራ፣ የአገሪቱን ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማን መጠየቃቸውን ዘገባው ያመለክታል፡፡  

ከፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ በኋላ የዓለም አቀፍ ሚዲያዎች አጀንዳ ሆነው የሰነበቱት ፕሬዚዳንት አል በሽር፣ ከፕሪቶሪያ ከተማ ወጣ ብሎ ከሚገኘው አንድ የአየር ኃይል ሠፈር ተነስተው ነበር ሰኞ ጠዋት በራሳቸው አውሮፕላን ወደ አገራቸው የበረሩት፡፡ በካርቱም ኤርፖርትም በደጋፊዎቻቸው ከፍተኛ አቀባበል እንደተደረገላቸው ዘጋርድያን ከአካባቢው ዘግቧል፡፡

ውሳኔ እስኪሰጥባቸው ድረስ ከደቡብ አፍሪካ ምድር እንዳይወጡ አስፈላጊው ዕርምጃ እንዲወሰድ ትዕዛዝ ያወጣው የአገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ለአይሲሲ ተላልፈው እንዲሰጡ ውሳኔ ያስተላለፈው ግን እሳቸው ወደ አገራቸው በመጓዝ ላይ ሳሉ ሰኞ ጠዋት ነበር፡፡ 

የአገሪቱ ፍርድ ቤት መንግሥት ትዕዛዙን በመጣስ ሕገ መንግሥቱን የሚጋፉ ተግባር መፈጸሙን ጠቅሶ፣ በአንድ ሳምንት ውስጥ የጽሑፍ ማብራርያ ይዞ እንዲቀርብ አዟል፡፡ ፕሬዚዳንቱ እንዲወጡ ያደረገበትን ምክንያት ማብራሪያ ይዞ እንዲቀርብ የተጠየቀው የደቡብ አፍሪካ መንግሥት፣ ለአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ የሚመጣ ማንኛውም የአገር መሪ ሙሉ ያለመከሰስ መብት (Immunity) የተሰጠው መሆኑን በመጥቀስ ራሱን እየተከላከለ ይገኛል፡፡ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ውድቅ ያደረገበትም ምክንያት ይኼው መብት እንደሆነ፣ ፕሬዚዳንት አል በሽር ወደ ደቡብ አፍሪካ የመጡት በመንግሥት ግብዣ መሆኑን የመንግሥት ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡ 

የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ፕሬዚዳንት የዚምባብዌ መሪ ሮበርት ሙጋቤ ስብሰባውን የመሩት ሲሆን፣ ቀደም ሲል የኅብረቱ አባላት ከአይሲሲ ፈራሚነት ራሳቸውን እንዲያገሉ ሲወተውቱ እንደነበር ይታወሳል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት አይሲሲ እየነጠለ የአፍሪካ መሪዎችን ፍርድ ቤት የሚያቀርብ ተቋም መሆኑን በመግለጽ ተቃውሞ በማሰማቱ፣ ላለፉት ጥቂት ዓመታት በኅብረቱና በፍርድ ቤቱ መካከል የነበረው ግንኙነት እየሻከረ መምጣቱ ይታወቃል፡፡ አሜሪካና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ግን ፕሬዚዳንቱን በቁጥጥር ሥር ባለማዋሉ የደቡብ አፍሪካ መንግሥትን እየወረፉ ይገኛሉ፡፡ 

የተመድ ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን በጀኔቭ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ‹‹አይሲሲ በፕሬዚዳንት አል በሽር ላይ ያወጣው የእስር ማዘዣ ትልቅ ትኩረት የምሰጠው ነው፡፡ የተቋሙ ትዕዛዝ መከበርና ተፈጻሚ መሆን ነበረበት፤›› ብለዋል፡፡ የደቡብ አፍሪካ ገዥ ፓርቲ ኤኤንሲ ግን የአይሲሲ ‹‹አግባብነትና ገለልተኝነት›› ወደፊት የሚከለስበት ሁኔታ እንዲፈጠር እንደሚፈልግ ገልጿል፡፡ 

 

ቋሚ ሲኖዶሱ የሀ/ስብከቱን የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት አመራር በማነጋገር ትእዛዝ ሰጥቷል መዋቅሩ ችግሮችን በየደረጃው የሚፈታበት ፍትሐዊነት እና ተአማኒነት መፈተሽ ይኖርበታል ከቤተ ክህነቱ በላይ የሚያሾሙና የሚያሽሩ አማሳኝ አለቆች እንዳሉ መግባባት ላይ ተደርሷል በፓትርያርኩ ዙሪያ ያሉትን ጨምሮ በፀረ ሙስና እየተመረመሩ በሕግ እንዲዳኙ ተጠይቋል *          *          * ዋ/ሥ/አስኪያጅ የማነ÷ ‹‹በፀረ ሙስና አብሬ እሠራለኹ፤ በፀረ ተሐድሶ …

ቱጃሩ ‘ሼክ’ መሐመድ አል አሙዲን፤ጋጠወጦቹ የወያኔ መንግስት ሹማምንቶች፦ የሃገሪቱ ፕሬዚደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፣ የፌደረሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ በረከት ስምዖን፣ እንዲሁም ታላላቅ ‘የተከበሩ’ እንግዶችና የአርቲስት ቤተሰቦች በተገኙበት፤ በትላንትናው እለት የትዝታው ንጉስ ጋሽ ማህሙድ አህመድ 50ኛ ዓመት የሙያ ጉዞ በማስመልከት የተዘጋጀ ዝግጅት ሲከበር፤ ከወጣቷ አክትረስ ማህደር አሰፋ ጋር ከትዳራቸው ውጭ ሲማግጡ ታይተዋል። ይህ […]

ሰኔ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃያዎቹ መጨረሻ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ዞን ጸሃፊ ሳሙኤል አወቀ ሰኔ 8/2007 ዓም ምሽት ላይ ሁለት ግለሰቦች ወደ ቤቱ ሲገባ ጠብቀው በፈጸሙበት ድብደባ ህይወቱ አልፎአል። የሳሙኤል ጓደኞችና የስራ ባልደረቦች ድርጊቱን የመንግስት ሃይሎች እንደፈጸሙት ምንም ጥርጣሬ እንደሌላቸው ተናግረዋል። ሳሙኤል ጀግና እና ለአገሩ የሚቆረቆር ጠንካራ …

ሰኔ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትውልድ ቦታው አሶሳ አከባቢ የሆነ የፌዴራል ፖሊስ አባል ሌሎች ሶስት የፌዴራል ፖሊስ አባላትን እና አንድ ቻይናዊን በምዕራብ ሀረርጌ ሚኤሶ ወረዳ ልዩ ስሙ ቦርደዴ በተባለ ቦታ በጥይት ተኩሶ ከገደላቸዉ በሃላ መሰወሩን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል:: የፌደራል ፖሊሶችና የኦሮምያ ፖሊስ ገዳዩን ለመያዝ በጭሮ፣ ሚኤሶ፣ በዴሳ፣ ገለምሶና አዋሽ ከተሞች ቤት ለቤት …

ሰኔ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጊምቦ ገዋታና በቦንጋ የተራዘመው ምርጫ ባለፈው ሳምንት ከተጠናቀቀ በሁዋላ፣ የግል ተወዳዳሪው ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የምርጫ ቀስቃሽና አደራጅ የሆነው ምትኩ ወልዴ ፣ ትናንት ከቀኑ 6 ሰአት ከ 30 ደቂቃ ላይ ፖሊሶች ከቤት አውጥተው የደበደቡት ሲሆን፣ ግለሰቡ በደረሰበት ከፍተኛ ድብደባ ቦንጋ ሆስታል ከገባ በሁዋላ፣ ወደ ጅማ ሪፈራል ሆስፒታል ተወስዷል። …

ሰኔ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን ተሻግረው በሽበርተኝነት የተፈረጀውን የግንቦት ሰባት ወታደራዊ ክንፍ ሊቀላቀሉ ሲሉ ማይካድራ ላይ በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር አውያቸዋለሁ ያላቸውን እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው ክስ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያቸውን አቅርበዋል። ዛሬ ሰኔ 9/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የቀረቡት በእነ ብርሃኑ ተክለያሬድ የክስ …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፀኃፊና በ2007 ዓ.ም ምርጫ የፓርቲው ዕጩ ተወዳዳሪ የነበረው ወጣት ሳሙኤል አወቀ ተገደለ፡፡ ወጣት ሳሙኤል አወቀ ትናንት ሰኔ 8/2007 ዓ.ም ምሽት ላይ ወደ ቤቱ እየገባ በነበረበት ወቅት በሁለት ግለሰቦች ከፍተኛ ድብዳባ ከተፈፀመበት በኋላ ሆስፒታል ውስጥ ነፍሱ አልፋለች፡፡ ወጣት ሳሙኤል ከቀድሞው አንድነት ጀምሮ ሲታገል የቆየ ሲሆን የሰማያዊ ፓርቲ መስራች አባል ነው፡፡ በአካባቢው […]

በሀ/ስብከቱ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የተጠራ ጉባኤ፣ የአንድ ወር እንቅስቃሴውን ገምግሟል ንቅናቄውን ከመሪ ዕቅዱ ቁልፍ ጉዳዮች ጋር አስተሳስሮ የሚመራ ራሱን የቻለ አካል ተቋቁሟል ከማኅበረ ካህናት እና ምእመናን፣ የማኅበረሰብ ተቋማት እና የፀረ ሙስና አካላት ጋር ይሠራል ዓላማውን ከቤተሰብ እስከ ኅብረተሰብ በማስተዋወቅ በስፋት ማነሣሣትና ማንቀሳቀስ ተግባሩ ነው የዕቅበተ እምነት የመልካም አስተዳደርና የፍትሕ ንቅናቄው በገዳማውያን አበው ጸሎት ይታገዛል *        …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ቅዳሜ በሰሜን ጎንደር ዞን በጭልጋ ከተማ የፌደራል ፖሊሶች በወዱት እርምጃ ከ5 እስከ 6 የሚደርሱ ወጣቶች መገደላቸውን፣ ከ10 ያላነሱ ወጣቶች ደግሞ መቁሳላቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል። የቅማንት ተወላጆች የራስ አስተዳደር መብት ይሰጠን በሚል ላቀረቡት ጥያቄ ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት “ጥያቄያቸው በክልሉ ውስጥ እንደሚገኙት እንደ ሌሎች ብሄረሰቦች ሊታይላቸው” …

ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በትሪፖሊ አካባቢ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንደተናገሩት ሰሞኑን እንደ አዲስ በተጀመረው አፈሳ ቁጥራቸው ከ90 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ተይዘው ታስረዋል። በአካባቢው በሚገኙ የተለያዩ እስር ቤቶች ከ500 ያላነሱ ኤርትራውያንና ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙም ገልጸዋል። ኢትዮጵያውያኑ የተያዙት በህወጥ አዘዋዋሪዎች ሲሆን፣ ገንዘብ ካላመጡ እንደማይለቀቁ እንደሚነገራቸው ገልጸዋል፡፡ አንድ ከእስር ቤት ያመለጠ ወጣት ሲናገር፣ በእስር ቤቱ ውስጥ …

ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ፣ ልደታ ምድብ ሰኔ 8/2007 ዓም በዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች ላይ በቀረበው የሽብረተኝነት ክስ ላይ ብይን ለመስጠት ለሐምሌ 13/2007 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ ጥቁር ለብሰው ፍርድ ቤት የተገኙ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱም ከዚህ ቀደም በቀረበለት የቪዲዮ ማስረጃ …

ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፕሮቪደንት ፈንድ ያላቸውን የግል ድርጅት ሠራተኞችን ገንዘብ በመውሰድ በጡረታ እንዲተዳደሩ ለማድረግ የተረቀቀው የግል ድርጅቶች ማህበራዊ ዋስትና አዋጅ ማሻሻያ በበርካታ ሰራተኞች ዘንድ ተቃውሞ ማስከተሉን ተከትሎ በተለይ ፕሮፌሽናል ባለሙያዎች የግል ድርጅቶችን በገፍ እየለቀቁና ለመልቀቅ የመልቀቂያ ደብዳቤ እያቀረቡ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት እየተሰራበት ያለው አዋጅ ቁጥር 715/2003 ለማሻሻል በምርጫው ማግስት …

በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ቀርቦባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች የቀረበባቸውን ክስ መከላከል ያስፈልጋቸዋል ወይስ በነጻ ይሰናበቱ የሚለው ላይ ብይን ለመስጠት ለሐምሌ 13/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ ዛሬ ሰኔ 8/2007 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ልደታ ምድብ የቀረቡት ጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ ጥቁር ለብሰው ችሎት ፊት ቀርበዋል፡፡ መዝገቡ ለዛሬ ተቀጥሮ […]

የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን: በልማት ስም ከጥቅመኛ ግለሰቦች ጋር በመመሳጠር የቤተ ክርስቲያንን ሀብት እና ንብረት ለግሉ በማካበት በሚታወቀው የቀድሞው አለቃ ኃይሌ ኣብርሃ፥ በግንባታ እንዲኹም የባለቤትነት እና የተጠቃሚነት መብቱን አሳልፈው በሚሰጡ የኪራይ ውሎች ከመመዝበሩም በላይ የሚልዮኖች የባንክ ባለዕዳ አድርጎት ያለተጠያቂነት ለመሰል ዘረፋ ወደ ሌላ ደብር ተዘዋውሯል፡፡ በእግሩ የተተኩት ግብታዊው እና ዐምባገነኑ መልአከ ብርሃን ዘመንፈስ […]

የአልበሽር ጉዳይ ሰሞኑን ፌስቡክን ተቆጣጠራት፡፡ ከተለያየ አቅጣጫ በርካታ አስተያየቶች ስለተሰጡ እኔ ብዙም የምጨምረው ላይኖር ይችላል፡፡ በጉዳዩ ላይ ሱዳናውያን ምን ይላሉ በሚለው ነጥብ ዙሪያ ብዙም የተወራ ስላልመሰለኝ ያንን ለመነካካት ነው ሃሳቤ፡፡ …..… ሁለት ሱዳናውያን ወዳጆች አሉኝ፡፡ አንደኛው በሐሰን ቱራቢ ዘመን በበጎ ፈቃድ ጅሃድ ለማካሄድ የዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን አቋርጦ ሁለት ጊዜ ወደ ደቡብ ሱዳን ዘምቷል፡፡ አሁን አሁን የኡመር […]

የቀድሞው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከዓመት በፊት ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ ሲያከናውን ከየክልሉ የመጡ ተሳታፊዎችን የማግኘትና በክለላቸው ስለሚያደርጓቸው እንቅስቃሰዎች፣ስለሚደርስባቸው እስራት፣ወከባ፣ድብደባና ስለሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዲያካፍሉን የፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ባልደረቦች እንወተውታቸው ነበር፡፡ አብርሃም ልጃለም ከጎንደር አካባቢ ወደ አዲስ አበባ ለጠቅላላ ጉባኤው የራሳቸውን የትራንስፖርት ወጪ ችለው ከመጡ የክልሉ የአንድነት አመራሮች አንዱ ነው፡፡ጎንደሮች አዲስ ሲመጡ ባዶ እጃቸውን አልመጡም፡፡ገበሬውን […]

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ሁለት የስኳር ፋብሪካዎች በስድስት ወራት ውስጥ የሙከራ ምርት እንደሚጀምሩ ይጠበቃል

ዳንጎቴ የምርት ማሸጊያ ፋብሪካ ለመገንባት ጠይቋል 

ሦስት የስኳር ፋብሪካዎች የሙከራ ምርት መጀመራቸውን በማስመልከት ለሪፖርተር ማብራረሪያ የሰጡት የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ አብተው፣ ከሰም ስኳር ፋብሪካ ሙሉ ለሙሉ የሙከራ ሥራ መጀመሩንና በቅርቡም ወደ ዋናው የምርት ሒደት እንደሚገባ ገለጹ፡፡ 

በከፊል የሙከራ ምርት ከጀመሩት ውስጥ የተንዳንሆና የኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎችም ከሦስት እስከ ስድስት ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ ሙከራ ተግባር ይገባሉ ብለዋል፡፡ የከሰም ስኳር ፋብሪካ በቀን እስከ 10,000 ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም እንዳለው የገለጹት አቶ አህመድ፣ ሆኖም በአሁኑ ወቅት 6,000 ቶን አገዳ በቀን በመፍጨት ሙከራ እንደሚጀምር አስታውቀዋል፡፡ እንደ ስኳር ኮርፖሬሽን መረጃ ከሆነ፣ የከሰም ስኳር ፋብሪካ በ20,000 ሔክታር መሬት ላይ የተንጣለለና በመስኖ ውኃ የሚለማ የአገዳ እርሻ አለው፡፡ 153 ሺሕ ቶን ስኳር፣ 12,500 ሜትር ኩብ ኤታኖል ሥራ በሚጀመርበት ወቅት እንደሚያመርት የሚጠበቅ ፕሮጀክት ነው፡፡ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር 260 ሺሕ ቶን ስኳርና 30,000 ሜትር ኩብ ኢታኖል፣ እንዲሁም 15 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል ተብሎ ይጠበቃል፡፡  

የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በሁለት ምዕራፍ ግንባታው እተካሄደ መሆኑን የገለጹት  አቶ አህመድ፣ በጠቅላላው 26 ሺሕ ቶን አገዳ በቀን የመፍጨት አቅም እንዳለውና በመጀመርያው ምዕራፍ 13,000 ቶን አገዳ በቀን ይፈጫል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ወደ ሙከራ እየገባ ያለው በስድስት ሺሕ ቶን አገዳ ይጀምራል ተብሏል፡፡ ይህ የሆነውም የተርባይንና የእንፋሎት ሥራዎች ስለሚቀሩ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ ከሦስት እስከ ስድስት ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ ለሙከራ የሚያበቃው ሥራ ተጠናቆ ምርት እንደሚጀምር ይጠበቃል፡፡

  ሆኖም ተንዳሆ የሚያመርተው 63 ሺሕ ሜትር ኩብ የኢታኖል ምርት ለኢንዱስትሪዎች ፍጆታ ሊውል መታሰቡን አቶ አህመድ ገልጸዋል፡፡ በኬሚካል አምራችነት የተሰማሩ የውጭ ኩባንያዎችና የከብት መኖ በማምረት ላይ የሚገኙ ፋብሪካዎች ኢታኖል እንዲቀርብላቸው በመጠየቃቸው የተንዳሆ ኢታኖል ምርት ለእነዚህ እንደሚውል አስታውቀዋል፡፡ 

በአገሪቱ እስካሁን እየተመረተ የሚገኘው ዓመታዊ የስኳር ምርት መጠን 300 ሺሕ ቶን እንደሆነ የሚገልጸው ስኳር ኮርፖሬሽን፣ ይህንን መጠን ወደ 2.25 ሚሊዮን ቶን ለማድረስ እየሠራ እንደሚገኝ፣ በአሁኑ ወቅት እየተመረተ የሚገኘውን 18 ሚሊዮን ሊትር ኢታኖል ወደ 44 ሚሊዮን ሜትር ኩብ የማሳደግ ዕቅድ መያዙን ሲገልጽ ቆይቷል፡፡ ሆኖም አገሪቱ ከ137 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ ኢታኖል የማምረት አቅም እንዳላት ይፋ አድርጓል፡፡ አምስት የስኳር ፋብሪካዎች ይኖሩታል የተባለውን የኩራዝ ፕሮጀክትን ጨምሮ፣ የወልቃይትና የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክቶች በግንባታ ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ 

በሌላ በኩል በስኳር ኢንዱስትሪው ውስጥ ይሳተፋሉ ከሚጠበቁ የአገር ውስጥና የውጭ ኩባንዎች እስካሁን ያልተሳካለቸው ሲኖሩ፣ በቅርቡ በሲሚንቶ ምርት ላይ በመሰማራት ሥራ የጀመረው ዳንጎቴ ግሩፕ በስኳር ልማት እንደሚሳተፍ ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡ አቶ አህመድ እንደሚሉት የናይጄሪያው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ፣ በስኳር ልማት ለመሰማራት የሚያስችላቸውን ጥናት እያካሄዱ ሲሆን፣ የምርት ማሸጊያ ፋብሪካ ለመገንባት በእንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡  

 

 

ድሬዳዋ ምድር ባቡር የቀድሞ ሠራተኞች እንዲለቁ የተደረገባቸውን ቤቶቻቸውን ተረከቡ

በድሬዳዋ ከተማ በቀድሞው ኢትዮ-ጂቡቲ ምድር ባቡር ጣቢያ ለረዥም ዓመታት ያገለገሉ ሠራተኞች በአገልግሎታቸው ወቅት ተሰጥተዋቸው ከነበሩት መኖሪያ ቤቶች እንዲለቁ ሲደረጉ፣ የከተማው ከንቲባ ጣልቃ በመግባት የተፈናቀሉት ሠራተኞች ቤቶቻቸውን መልሰው ማግኘታቸው ታወቀ፡፡

ከ2,000 በላይ ቤተሰቦችን እንደሚያስተዳድሩ የተነገረላቸው ቁጥራቸው 240 ገደማ የሚሆኑ የምድር ባቡር ሠራተኞች፣ ካለፈው ዓመት ጀምሮ በጣቢያው ኃላፊዎች ቤቶቹን ለድርጅቱ አስረክበው እንዲለቁ ታዘው ነበር፡፡ በተፈጠረው ውዝግብ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ሄዶ የድሬዳዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለድርጅቱ የፍርድ ውሳኔ ሲሰጥ፣ ሠራተኞች መበተናቸውንና ለችግር ተዳርገው እንደበር ሠራተኞቹ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ነገር ግን ተፈናቃዮቹ ያለመጠለያ መቅረታቸውን ያወቀው የከንቲባው ጽሕፈት ቤት፣ ከጣቢያው ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር ሠራተኞችን ወደ ቀድሞ ቤታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ጥረት አድርጎ እንደነበር የቀድሞ ሠራተኞች ጠቁመዋል፡፡ ሆኖም  የጽሕፈት ቤቱ ጥረት ውጤት ማስገኘት ባለመቻሉ የከተማው ከንቲባ ጉዳዩን ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትና ለጂቡቲ መንግሥት አቅርበው እንደነበር፣ የቀድሞ ሠራተኞች መሠረታዊ ማኅበር ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ሽመልስ እሸቱ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

በፌዴራል ደረጃ ያሉ ተቋማት በተለይም ከትራንስፖርት ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ምድር በቡር ኮርፖሬሽን፣ ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ ከፍትሕ ሚኒስቴር፣ ከፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ጋር ኮሚቴ አቋቁመዋል፡፡ በኮሚቴው አባላት በዝርዝር ምርመራ ከተደረገ በኋላ የተፈናቀሉ ሁሉም የቀድሞ ሠራተኞች የመኖሪያ ቤታቸውን እንዲያገኙ ተወስኗል፡፡ በውሳኔው ምክንያት ወደ መኖሪያ ቤታቸው መመለሳቸውንና ፍትሕ መገኘቱን አቶ ሽመልስ ተናግረዋል፡፡ 

‹‹በአገራችን እኛን ያጋጠሙን ዓይነት መሰል ችግሮች በተለያዩ ጊዜያት ይከሰታሉ፡፡ ከአንድ ተቋም ጋር በሚፈጠሩ ችግሮች ዜጎች በአብዛኛው ፍትሕ አጥተው ለችግር ሲጋለጡ ይስተዋላል፡፡ ለእኛ የተወሰነው ውሳኔ ለዜጎች ተቆርቋሪነትን ያሳየና ፍትሕ ወይም መልካም አስተዳዳርን ያስፈነ በመሆኑ፣ እንደ አርዓያ መታየት ያለበት ይመስለኛል፤›› ሲሉ አቶ ሽመልስ በከተማው ከንቲባ የተደረገላቸውን ፍትሐዊ ዕርዳታ አወድሰዋል፡፡

ችግሩ ሊያስከትል የሚችለውን ማኅበራዊ ቀውስ በመረዳት የተቻለውን ጥረት በማድረግ ዜጎችን ከችግር ለማዳን የተደረገው ጥረት ውጤት በማስገኘቱ፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተደደር የነዋሪዎችን ደስታ መካፈሉ እንዳስደሰተው የአስተዳደሩ የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ፍቃዱ በየነ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 03 ወይም ከዚራ በሚባለው አካባቢ የኢትዮና የጂቡቲ ምድር ባቡር ኩባንያ ከ30 ዓመታት በፊት ለሠራተኞቹ ቤቶቹን መገንባቱን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ነገር ግን በድርጅቱና በሠራተኞቹ መካከል በቤቶቹ ጉዳይ ውዝግቡ ከደርግ ዘመን ጀምሮ እንደነበረ፣ የሠራተኞቹ ጡረተኞች ማኅበር ሊቀመንበር አቶ አብዱሰላም ሁሴን ይናገራሉ፡፡ እሳቸውም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ላደረገላቸው እገዛ ምሥጋናቸውን ገልጸዋል፡፡

 

ባለሥልጣኑ ክሱን አልተቀበለውም

የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን እየተካሄደ ያለው የመንገድ ልማት ዘርፍ ለሙስና የተጋለጠ ነው አለ፡፡ ኮሚሽኑ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በሚያካሂዳቸው ሥራዎች ላይ ያካሄደውን ጥናት ባለፈው ሐሙስ ይፋ አድርጓል፡፡ 

ኮሚሽኑ ‹‹የመንገድ ልማትና የግንባታ ዘርፍ ለሙስናና ብልሹ አሠራር ያለው ተጋላጭነት›› በሚል ርዕስ ባቀረበው ጥናት፣ ተቋራጮች የተረከቡትን ሥራ ሳያጠናቅቁ ሌላ ሥራ ያገኛሉ ብሏል፡፡ 

ከዚህ በተጨማሪም የዲዛይን ሥራዎች በአግባቡ አለማከናወን፣ የጨረታ ሒደት ግልጽነት የጎደለው መሆኑ፣ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ አለመጠናቀቃቸው፣ በካሳ ክፍያ ወጥ የሆነ አሠራር አለመኖር ተጠቃሽ ችግሮች ሆነው ቀርበዋል፡፡ 

በዋናነት ጎልተው ከተነሱት ጉዳዮች መካከልም የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች በተደጋጋሚ ከተመሳሳይ አማካሪ ድርጅቶች ጋር እንዲሠሩ ተደርጓል የሚል ነው፡፡ 

ለዚህ እንደ አብነት የቀረቡት ሳትኮን ኮንስትራክሽን ኩባንያ ከቤዛ ኮንሰልት ጋር በሁለት ፕሮጀክቶች መገናኘታቸው፣ ገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ከኮኪር ኮንሰልት ጋር በተለያዩ ፕሮጀክቶች መሥራታቸው ነው፡፡ 

ነገር ግን ይህንን ጉዳይ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ኃላፊዎችም ሆኑ ስማቸው የተጠቀሰው ኩባንያዎች አልተቀበሉትም፡፡ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ኃላፊዎች እንዳሉት፣ ጨረታ ሲወጣ የብቃት ጉዳይ እንጂ እከሌ ተወዳዳር፣ ወይም አትወዳደር አይባልም፡፡ ኩባንያዎቹ ያካሄዷቸው ፕሮጀክቶች ሁሉ ጥሩ አፈጻጸም ያሳዩ ናቸው በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ 

ከዚህ በተጨማሪ በቀረበው ጥናታዊ ጽሑፍ ሳትኮን ኮንስትራክሽን 12 ፕሮጀክቶች ይዟል የተባለው ትክክል እንዳልሆነ፣ ኩባንያው በአሁኑ ወቅት በእጁ አምስት ፕሮጀክቶች ብቻ እንደሚገኙና የኩባንያው የሥራ አፈጻጸምም መልካም ነው የሚል ምላሽ ተሰጥቷል፡፡ ከሦስት ዓመታት ወዲህ ፕሮጀክት እንዳላገኘ ተገልጿል፡፡

ገምሹ በየነ ኮንስትራክሽንም እንዲሁ የሚያካሂደው ግንባታ መጠናቀቅ ካለበት ጊዜ ቀድሞ በማጠናቀቅ የሚያስረክብ ኮንትራክተር በመሆኑ፣ ወቀሳው ተቀባይነት እንደሌለው ተገልጿል፡፡ 

የፀረ ሙስና ኮሚሽን የሙስና መከላከል ዋና አማካሪ አቶ ፈለቀወርቅ ኃይሌ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ ከተነሱት ችግሮች በተጨማሪ፣ በትግራይ ክልል ከአዲ ረመጥ ጀምሮ እስከ ደጀናና ዳንሻ ድረስ የሚገነባው 97 ኪሎ ሜትር መንገድ በተያዘለት የጊዜ ገደብ አለመጠናቀቁ ነው፡፡ 

ሁናን ሁንዳ የተባለው የቻይና የሥራ ተቋራጭ የሚገነባው ይህ መንገድ በተያዘለት የጊዜ ገደብ ባለመጠናቀቁ ከተያዘለት በጀት 35 በመቶ ያህል የገንዘብ ጭማሪ እንዲደረግ ማስደዱ ተገልጿል፡፡ አቶ ፈለቀወርቅ እንደሚሉት፣ በቢሊዮኖች የሚቆጠር በጀት የሚመደብለት የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ብዛት ያላቸው አካላትን የሚያሳትፍ በመሆኑ ለሙስና ተጋላጭ ነው፡፡ 

‹‹በቅድመ ግንባታ ወቅት፣ ከዲዛይን ጀምሮ ጥራቱን ያልጠበቀ መንገድ ገንብቶ እስከ ማስረከብ ድረስ ሙስና ይፈጸማል፤›› በማለት አቶ ፈለቀወርቅ አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ኃላፊዎች የቀረበውን ጥናት ሙሉ በሙሉ አልተቀበሉትም፡፡ ነገር ግን የአሠራር ማሻሻያ ሊደረግባቸው የሚገቡ ጉዳዮች እንዳሉ አምነዋል፡፡ 

አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የባለሥልጣኑ የሥራ ኃላፊ በጥናቱ አቀራረብ ላይ ጥያቄ እንዳላቸው ይናገራሉ፡፡ ይኸውም ኮንትራክተርና ኮንሰልታንት በጨረታ ሒደት በሚገኝ ውጤት አብረው በተደጋጋሚ ሊሠሩ እንደሚችሉ፣ ዋናው ጉዳይ በፕሮጀክቶች ጥራት ላይ የሚፈጥሩት ተፅዕኖ ነው መገምገም ያለበት ይላሉ፡፡ ኮንትራክተርና ኮንሰልታንት ዛሬ ተዋውቀው ችግር መፍጠር እንደሚችሉ የጠቆሙት ኃላፊው፣ ጥናቱ በመንገዶች ግንባታ አፈጻጸም ላይ የታዩ ጉልህ የሚባሉ የጥራትና የመጓተት ችግሮች ላይ ቢያተኩር ጠቃሚ ነበር ብለዋል፡፡ 

የመንገድ ዘርፍ ልማት መርሐ ግብር ከተጀመረ የዛሬ 18 ዓመት ጀምሮ ከአንድ ሺሕ በላይ ኮንትራቶች መፈረማቸውን ገልጸው፣ ከእነዚህ መካከል እጅግ በጣም ጥቂት ምሳሌዎችን ነቅሶ በማውጣት ሙስና አለ ማለት ይከብዳል ሲሉ አስረድተዋል፡፡ ዋናው መተኮር ያለበት በመንገድ ዘርፍ አፈጻጸም ላይ የታዩ ዋነኛና መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ መሆኑን ገልጸው፣ ጉልህ የሆኑ ግድፈቶች ሲኖሩ ነቅሶ ማውጣትና በግልጽ መነጋር የሚያግባባ ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

 

 

የማዕድን ሚኒስቴር ስለኩባንያው ሽያጭና ዝውውር የቀረበልኝ ጥያቄ የለም ብሏል

ላለፉት ስድስት ዓመታት በኢትዮጵያ የፖታሽ ማዕድን ፍለጋና ማምረት ሥራ ይገባል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው አላና ፖታሽ ኩባንያ፣ እስራኤል ኬሚካልስ ለተባለ የእስራአል ኩባንያ በመሸጡ ምክንያት ሽያጭና ዝውውሩ ሰኞ ሰኔ 8 ቀን

2007 ዓ.ም. እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ፡፡ ማዕድን ሚኒስቴርን ስለኩባንያው ዝውውር እስካሁን በይፋ የደረሰኝ መረጃ የለም ብሏል፡፡

አላና ፖታሽ ለኩባንያው ሠራተኞች ባለፈው ሳምንት ባስተላለፈው መልዕክት፣  ለእስራኤሉ ኩባንያ ዝውውር ተፈጻሚ እንዲሆን ከሁሉም የአላና ፖታሽ ባለአክሲዮኖች ድጋፍ በማግኘቱ የኩባንያው ዝውውር በይፋ ይካሄዳል ብሏል፡፡ የእስራኤሉ ኩባንያ  ከሰኞ ጀምሮ በይፋ ሥራ የሚጀመር መሆኑን በማረጋገጥ፣ በኢትዮጵያ የሚገኙት የአላና ፖታሽ የማኔጅመንት አባላትና ሠራተኞች አብረውት እንዲሠሩም የተላለፈው መልዕክት አመልክቷል፡፡

የኩባንያው ዝውውር ለአላና ፖታሽ ስኬታማነትን የሚያረጋግጥና ለድርጅቱ ሠራተኞችም መልካም አጋጣሚዎችን የሚፈጥር መሆኑን የሚጠቁመው መልዕክት፣ እስካሁን ያሉት ሠራተኞች ከእስራኤሉ ኩባንያ ጋር የሚቀጥሉ መሆኑን አረጋግጦላቸዋል፡፡ አላና ፖታሽ 120 ያህል ሠራተኞች አሉት፡፡

የእስራኤሉ ኩባንያ አላና ፖታሽ ኩባንያ ያሉትን 300 ሚሊዮን አክሲዮኖች እያንዳንዳቸው በ0.50 የካናዳ ዶላር ዋጋ እንደገቸዛው ታውቋል፡፡ ይህም ከ150 ሚሊዮን የካናዳ ዶላር በላይ ይሆናል፡፡ አላና ፖታሽ የተሸጠበት ይህ ዋጋ አላና ፖታሽ እስካሁን ለፕሮጀክቱ ካወጣው ወጪ አንፃር ሲታይ አትራፊ የሆነበትን የሽያጭ ገቢ እንዳገኘ የሚያመላክት ነው ተብሏል፡፡ 

የአላና ፖታሽ በአፋር ክልል በዳሎል ጠቅላላ የኢንቨስትመንት ወጪው ከ750 እስከ 800 ሚሊዮን ዶላር ሊደርስ ይችላል ተብሎ ይገመት ነበር፡፡ ከእስራኤሉ ኩባንያ ጋር የሽያጭ ስምምነቱ እስከተፈጸመበት ጊዜ ድረስ አላና ፖታሽ ከ130 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ማድረጉን፣ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ነጅብ አባቢያ ለሪፖርተር መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ የእስራኤል ኩባንያ አላና ፖታሽን ሙሉ በሙሉ ከመግዛቱ ቀደም ብሎ፣ የ16 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ለመውሰድ የሚያስችለውን ከ85 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸውን አክሲዮኖች ግዥ ለመፈጸም ስምምነት ተደርሶ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ እስራኤል ኬሚካልስ ኩባንያ ከ85 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለአላና ፖታሽ ገቢ ሳያደርግ በመቆየቱ ስምምነታቸው ሳይፈርስ እንዳልቀረ ተነግሮ ነበር፡፡ በመሀል ግን አላና ፖታሽ ለፕሮጀክቱ ኢንቨስትመንት የሚውል ካፒታል ለማሰባሰብ በሽርክና ሊሠሩ የሚችሉ ሌሎች አማራጮችን ወደማፈላለግ ገብቶ፣ ከሦስት ኩባንያዎች ጋር ድርድር በማድረግ በመጨረሻ ከእስራኤሉ ኩባንያ ጋር ስምምነት ላይ በመደረስ ግዥውን ሊፈጽም ችሏል፡፡ ይህም ስምምነት መጋቢት 17 ቀን 2007 ዓ.ም. ተፈጽሟል፡፡

የማዕድን ሚኒስቴር ግን የአላና ፖታሽን ሽያጭና ዝውውር የሚመለከት ምንም ዓይነት ይፋዊ የሆነ መረጃ ያልደረሰው መሆኑን ይገልጻል፡፡ የሚኒስቴሩ አንድ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አላና ኩባንያውን ሸጫለሁ ስለማለቱ መረጃ ቢኖርም እስካሁን በሕጋዊ መንገድ ጥያቄ አለመቅረቡን ነው፡፡

‹‹እስካሁን ለእኛ የቀረበልን ነገር የለም፤›› ያሉት እኚሁ ኃላፊ፣ “አላና ፖታሽ ለእስራኤሉ ኩባንያ ሊተላለፍ መሆኑን የሚያመለክት ጥያቄ አላቀረበም፤” ብለዋል፡፡ በጆይንት ቬንቸር ለመሥራት ከሆነ በራሳቸው ስምምነት ሊፈራረሙ የሚችሉ ቢሆንም፣ ኩባንያውን ለሌላ ኩባንያ አስተላልፋለሁ ካለ ግን ጉዳዩ ለማዕድን ሚኒስቴር መቅረብ እንደሚኖርበት ገልጸዋል፡፡

የዝውውሩ ጥያቄም ተቀባይነት የሚኖረው መጀመሪያ አላና ፖታሽ ግዴታውን የተወጣ መሆኑ ከተረጋገጠ ነው፡፡ ኩባንያው የሚተላለፍለት ድርጅት ሕጋዊ፣ የቴክኒክና የፋይናንስ ብቃት ያለው መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ ነው ብለዋል፡፡ ኩባንያዎቹ በግላቸው የሚደርሱበት ስምምነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የኩባንያው ዝውውር የሚፈቀደው ማዕድን ሚኒስቴር ማረጋገጫ ሲሰጥ ብቻ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

አላና ፖታሽ ላከ በተባለው መልዕክት ላይ ኩባንያዎቹ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የሚደራደሩ መሆናቸው ጠቅሷል፡፡ የመጨረሻ የሽያጭ ርክክቡ በካናዳ ይካሄዳል የተባለ ሲሆን፣ መንግሥት የሚጠይቃቸውን ፎርማሊቲዎች ከርክክቡ በኋላ ሊከናውኑ ይችላሉ ተብሎ ተገምቷል፡፡ የእስራኤሉ ኩባንያ በዳሎል የሚገኘውን ፕሮጀክት ለረጅም ጊዜ እንደ ስትራቴጂካዊ ፕሮጀክት የሚመለከተው መሆኑን፣ በኢትዮጵያ ከሚገኘው የአላና ፖታሽ ቡድን ጋር በመሆን የፕሮጀክቱን ሥራ  እንደሚቀጥልም አስታውቋል፡፡

ባለፈው ሳምንት በኩባንያው ይፋ በሆነው መረጃ መሠረት የእስራኤሉ ኩባንያ አላና ፖታሽን ሙሉ ለሙሉ ለመግዛት የወሰነው በቀጣይ በአፍሪካ፣ በተለይም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ገበያ ግምት ውስጥ በማስገባት ነው  ተብሏል፡፡ ከኢትዮጵያ ለዓለም ገበያ የሚቀርበው የፖታሽ ማዕድን ምርት በዋነኝነት ለግብርና ማዳበሪያ ማምረቻ የሚጠቅም ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ለሚገነቡ የማዳበሪያ ፋብሪካዎች በአገር ውስጥ ጥሩ ገበያ አለው ተብሎ ስለሚታመን ጭምር ነው፡፡ ፕሮጀክቱ ማምረት ሲጀምር ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኝ መሆኑን የሚገልጸው በኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ፣ አሁን ባለው ገበያ በዓመት የፖታሽ ወጪ ንግድ ገቢው ከ400 እስከ 500 ሚሊዮን ዶላር እንደሚሆን ይጠቁማል፡፡

የአላና ፖታሽ ፕሮጀክት ሊያስገኝ የሚችለውን ጥቅም በመገንዘብ መንግሥት የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በተለይ የፖታሽ ምርትን በዓለም ገበያ ለማቅረብ ይረዳሉ የተባሉ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን እያካሄደ ነው፡፡ ከደንከል-ጂቡቲ ታጁራ ወደብ ድረስ በመገንባት ላይ ያለው መንገድ ይጠቀሳል፡፡  

ተቀማጭነቱን ካናዳ ያደረገው አላና ፖታሽ በኢትዮጵያ ውስጥ ፖታሽ ለማምረት በአፋር ክልል በደንከል ዝቅተኛ አካባቢ የፖታሽ ፍለጋውን በስኬት በማጠናቀቁ፣ ከማዕድን ሚኒስቴር የፖታሽ ማዕድን የማውጣት ፈቃድ አግኝቶ ነበር፡፡ የፖታሽ ምርቱንም በዚህ ዓመት አውጥቶ ለዓለም ገበያ ለማቅረብ ዕቅድ የነበረው ሲሆን፣ ይህንን ሳያሳካ ኢንቨስትመንቱን ሸጧል፡፡ አላና ፖታሽ ይዞት የነበረው ዕቅድ ሳያሳካ ወደ ሽያጭ የገባው ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ የሚያስፈልገውን ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ወጪ ማሟላት ባለመቻሉ ነው፡፡ በተለይ የእስራኤሉ ኩባንያ እገዛዋለሁ ላለው የ16 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ይከፍላል ተብሎ የነበረውን ገንዘብ በወቅቱ ባለመክፈሉ ሌላ አማራጭ ፍለጋ ሊገባ እንደቻለም ይነገራል፡፡ አላና ፖታሽ በበኩሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ የፖታሽ ዋጋ ማሽቆልቆል ኩባንያውን ለመሸጥ እንዳስገደደው ይገልጻል፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከዓመታት በፊት አንድ ቶን ፖታሽ ከ570 ዶላር በላይ ነበር፡፡ አሁን ግን ወደ 280 ዶላር ወርዷል፡፡ በካናዳ ባለው የፖታሽ ስቶክ ገበያም ከአራት ዓመት በፊት 2.8 ዶላር ይሸጥ የነበረው የአላና የአንድ አክሲዮን ዋጋ፣ አሁን ከ0.40 የካናዳ ዶላር በታች በመውረዱ አላና ፖታሽን ለመሸጥ ውሳኔ ላይ እንዲደርስ እንዳደረገው ተነግሯል፡፡ አቶ ነጅብ እንደገለጹት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የፖታሽ ዋጋ ዝቅ እያለ በመምጣቱ አላና ፖታሽ ሊሸጥ ችሏል፡፡ የእስራኤል ኩባንያ የሽያጩ ሒደት ስምምነት መፅደቁን ተከትሎ በፍጥነት ወደ ሥራ በመግባትና የቅድመ ግንባታ ጥናት በመጀመር፣ የፕሮጀክቱን የኢንጂነሪግ ዲዛይንና የቦታ መረጣ፣ የውኃ አቅርቦትና የትራንስፖርት ሎጂስቲክስ ሥራዎችን ተፈጻሚ ያደርጋል ተብሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ፕሮጀክቱ ተፈጻሚ የሚሆንበትን በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እንደሚመክርበት የኩባንያው መረጃ ያመላክታል፡፡ በኢትዮጵያ የሚገኘውን የአላና ፖታሽ የማኔጅመንት ቡድን የእስራኤሉ ኩባንያ  ሲረከብ ዓላማውንና የሥራ ድርሻውን በመግለጽ፣ ለአዲሱ ኩባንያ የሚያስረዳበትን ዝግጅት እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡

የእስራኤሉ ኩባንያ በንግድ ድርጅትነት በኒውዮርክ የአክሲዮን ገበያና በቴልአቪቭ አክሲዮን ገበያ የተመዘገበ ነው፡፡ የኩባንያውን የቅድመ ታሪክና ወቅታዊ አቋሙን በሚመለከት ባለፈው ሳምንት ለአላና ፖታሽ ሠራተኞች በተሠራጨው መልዕክት ላይ፣ እስራኤል ኬሚካልስ እ.ኤ.አ. በ2014 አጠቃላይ ገቢው ወደ 6.1 ቢሊዮን ዶላር መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ኩባንያው በዋናነት በምግብ፣ በምህንድስና መገልገያ መሣሪያዎች ምርትና ሥርጭት ላይ የተሰማራ ነው፡፡ ከዚህም ሌላ በቀዳሚነት በፖታሽ፣ በፎስፌትና በብሮሚን ምርቶች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ የሚገኝ ሲሆን፣ በመላው ዓለም ከ30 በላይ በሚሆኑ አገሮች ይንቀሳቀሳል፡፡ 12,500 ያህል ሠራተኞች አሉት፡፡ የኩባንያው ጠቅላላ ሀብትም 12 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ የፖታሽ ምርትን በዓለም ገበያ ለማቅረብ በቅድሚያ ተነሳሽነቱን ያሳዩት የአላና ፖታሽ መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ነጅብ አባቢያ፣ ወደ ኢንቨስትመንቱ ሲገቡ ተሰማርተው የነበሩት በወርቅ ማዕድን ፍላጋ ላይ ነበረ፡፡ ነገር ግን በመጨረሻ በአገሪቱ ያለውን የፖታሽ ማዕድን ዕምቅ ሀብት መኖሩን በጥናት በማረጋገጥ፣ ወደ ዘርፉ ፊታቸውን ሊያዞሩ መቻላቸውን መግለጻቸው አይዘነጋም፡፡ አቶ ነጅብ ኢትዮጵያ ውስጥ በጂኦተርሚል ኃይል ማመንጨት ኢንቨስትመንት ውስጥ ለመሥራት እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ይታወቃል፡፡

 

የዓለም ባንክ 150 ሚሊዮን ዶ

-ላር ሊያበድር ነው

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ለ2008 በጀት ዓመት፣ በታሪኩ ከፍተኛ የተባለውን የ12 ቢሊዮን ብር የበጀት ጥያቄ ሊያቀርብ እንደሆነ ተጠቆመ፡፡

ምንጮች እንደገለጹት፣ ባለሥልጣኑ ለ2008 በጀት ዓመት ለሚያከናወናቸው የመንገድ መሠረተ ልማት ግንባታዎች ያስፈልገኛል ያለውን የበጀት ጥያቄ፣ በሚቀጥለው ሳምንት ለከተማው የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ባለሥልጣኑ የጠየቀው በጀት እስካሁን ለከተማዋ የመንገድ መሠረተ ልማት ለአንድ የበጀት ዓመት ያስፈልገኛል ብሎ አቅርቧቸው ከነበሩ  የበጀት ጥያቄዎች ሁሉ ከፍተኛው እንደሆነ ታውቋል፡፡ 

ባለሥልጣኑ በ2007 በጀት ዓመት የ6.6 ቢሊዮን ብር በጀት ይዞ ሲንቀሳቀስ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ አስተዳደሩ የፈቀደለት በጀት 6.1 ቢሊዮን ብር ነበር፡፡ ቀሪውን ከመንገድ ፈንድና ከሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ያገኘው ነው፡፡ በ2006 ዓ.ም. ደግሞ 3.8 ቢሊዮን ብር በጀት ተፈቅዶለት እንደነበር ይታወሳል፡፡

ባለሥልጣኑ በመጪው ዓመት ለሚያስጀምራቸው በርካታ አዳዲስ መንገዶችና በግንባታ ላይ ለሚገኙ መንገዶች ማጠናቀቂያ፣ እንዲሁም ለአዳዲስ መንገዶች ዲዛይን ሥራዎች ይህንን ከፍተኛ የበጀት ጥያቄ ማቅረቡ ታውቋል፡፡

በአስተዳደሩ ሥር ካሉ ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ከፍተኛ የሚባለውን በጀት የሚያገኘው የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን፣ ለ2008 በጀት ዓመት   ያስፈልገኛል ብሎ የሚጠይቀውን 12 ቢሊዮን ብር አስተዳደሩ ሙሉ ለሙሉ ይደግፈዋል ተብሎ እንደማይገመት ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ ባለሥልጣኑ ከዚህ ቀደም ለ2008 በጀት ዓመት ያቀረበውን ያህል አይሁን እንጂ፣ ከፍተኛ የተባለ በጀት ጠይቆ ከጠየቀው በጀት ግማሽ ያህሉ የተፈቀደለት ጊዜ እንደነበር ያስታውሳሉ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዓለም ባንክ ለመንገድ መሠረተ ልማትና ለአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ማሻሻያ ፕሮግራም የሚውል የ150 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለመፍቀድ የተስማማ መሆኑ ታውቋል፡፡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደገለጹት፣ የዓለም ባንክ በመንገድና በትራንስፖርት ዘርፍ ለአስተዳደሩ ብድር ሲፈቅድ ለመጀመርያ ጊዜ ነው፡፡  ከዓለም ባንክ በሚገኘው ብድር በዋነኝነት የመንገድና የትራንስፖርት ዘርፍ አገልግሎቶችን ለማቀላጠፍ በሚያስችሉ መሠረተ ልማት ሥራዎች ላይ የሚውል ነው ተብሏል፡፡ ብድሩ ሙሉ በሙሉ ከመለቀቁ በፊት ብድሩ ለታቀደለት ዓላማ እንዲውል ለሥራዎች ማስጀመርያ 4.5 ሚሊዮን ዶላር የተሰጠ መሆኑም ታውቋል፡፡ ዋናው ብድር በሚቀጥለው ዓመት እንደሚለቀቅ ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

ከዓለም ባንክ ብድር በተጨማሪ በ2008 በጀት ዓመት ከውጭ የፋይናንስ ምንጮች በሚገኝ ብድር የሚተገበሩ ፕሮጀክቶችም አሉ ተብሏል፡፡ በተለይ ጃፓን ለአዲስ አበባ የመንገድ ጥገና ሥራና ለአሴት ማኔጅመንት የሚውል የሚውል ብድር መፍቀዷ ታውቋል፡፡ ፈረንሣይና ቻይናም ለአዲስ አበባ መንገድ መሠረተ ልማት የሚውል በተመሳሳይ ብድር ለመስጠት ስምምነት ላይ መድረሳቸው ይነገራል፡፡ ከእነዚህ የፋይናንስ ምንጮች የሚገኘው ገንዘብ በ2008 ዓ.ም. የአስተዳደሩ በጀት ውስጥ ተካቶ የሚቀርብ እንደሆነም መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ 

አስተዳደሩ ለመንገድ ዘርፍ ከውጭ የፋይናንስ ምንጮች ይህንን ያህል ገንዘብ አግኝቶ እንደማያውቅ፣ ከዚህ በኋላም እንደ ዓለም ባንክ ያሉ አበዳሪዎች ከአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ግንባታ የሚውል ብድር እንዲሰጡ የሚያስችል ፕሮጀክቶች እየተሠሩ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

ለኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ተሾመ

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የሱር ኮንስትራክሽን ኩባንያ የኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት ኃላፊ የነበሩትን ኢንጂነር አርዓያ ግርማይ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አድርጐ ሾመ፡፡ 

በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ፊርማ የወጣው ደብዳቤ፣ አቶ አርዓያ ከሰኔ 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን ይገልጻል፡፡ 

ኢንጂነር አርዓያ በዋና ዳይሬክተርነት መሾማቸውን ለሪፖርተር አረጋግጠው፣ መንግሥት በመንገድ ልማት ዘርፍ ያስቀመጠውን ግብ ለማሳካት እንደሚሠሩ ተናግረዋል፡፡ 

ኢንጂነር አርዓያ በ1987 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሲቪል ኢንጂነሪንግ ትምህርት መስክ ተመርቀዋል፡፡ ከትምህርት ዓለም በኋላ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ከጌዶ – ፊንጫ ድረስ ባካሄደው የመንገድ ግንባታ የፕሮጀክት ኃላፊ ሆነው መሥራታቸው ታውቋል፡፡

ኢንጂነር አርዓያ በ1999 ዓ.ም. በኤፈርት ሥር ተቋቁሞ በሥራ ላይ የሚገኘውን ሱር ኮንስትራክሽን ኩባንያ ተቀላቅለዋል፡፡ 

የሱር ኮንስትራክሽን ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ታደሰ የማነ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ኢንጂነር አርዓያ በ1999 ዓ.ም. ኩባንያውን እንደተቀላቀሉ በሰሜን ጎንደር ከሻውራ – ገለጎ ድረስ ለተገለነባው 147 ኪሎ ሜትር መንገድ የፕሮጀክት ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል፡፡ 

‹‹ይህ መንገድ እጅግ አስቸጋሪ የነበረ ሲሆን፣ ኢንጂነር አርዓያ ከፍተኛ ስኬት ያስመዘገበበት ነው፤›› በማለት ምስክርነታቸውን አቶ ታደሰ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በኋላም ከመነቤኛ – ለምለም በረሃ የተገነባውን መንገድ ጨምሮ አራት የመንገድ ፕሮጀክቶችን መርተው በስኬት ማጠናቀቃቸውን ኢንጂነር ታደሰ አስረድተዋል፡፡ 

ኢንጂነር አርዓያ የአሁኑ ሹመት እስኪሰጣቸው ድረስ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የሚያስገነባውን የዛሪማ ግድብ በኃላፊነት እየመሩ፣ ውጤታማ ሥራ መሥራታቸውን ኢንጂነር ታደሰ ገልጸዋል፡፡

‹‹ኢንጂነር አርዓያ ካሉን የፕሮጀክት ኃላፊዎች መካከል በውጤታማነታቸው ከሚታወቁት አንዱ በመሆኑ ወደ ዋናው መሥሪያ ቤት አምጥተን ለከፍተኛ ኃላፊነት አጭተነው ነበር፤›› በማለት የሚናገሩት ኢንጂነር ታደሰ፣ መንግሥት ለበለጠ ከፍተኛ ኃላፊነት ስለመረጣቸው ምንም ማድረግ አለመቻላቸውን የኢንጂነር አርዓያን ብቃት በማድነቅ ገልጸዋል፡፡ 

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ላለፉት አሥር ዓመታት የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉትን አቶ ዛይድ ወልደ ገብርኤልን፣ ከጥቅምት 30 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ማሰናበቱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ 

የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ በቀለ አቶ ዛይድን በመተካት የራሳቸውን ሥራ ጨምረው ላለፉት ስምንት ወራት በተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተርነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ በዚህ ሳምንት ኢንጂነር አርዓያ ሥራቸውን ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡   

 

በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ለማስቀረት አንድ ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል

በአዲስ አበባና በዙሪያዋ የሚገኙ 12 የኦሮሚያ ክልል ልዩ ዞን ከተሞች በየጊዜው የሚገጥማቸውን የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ለማስቀረት ማስተር ፕላን ተነደፈ፡፡ አዲሱን ማስተር ፕላን ተግባራዊ ለማድረግ አንድ ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል፡፡

‹‹አዲስ አበባና ዙሪያዋ የኤሌክትሪክ ዲስትሪቢውሽን ማስተር ፕላን ጥናት ፕሮጀክት›› በሚል ስያሜ የተነደፈው ማስተር ፕላን፣ በሚቀጥሉት 20 ዓመታት በአጭር፣ በመካከለኛና በረዥም ጊዜ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል፡፡ 

ባለፈው ሐሙስ ሰኔ 4 ቀን 2007 ዓ.ም. በማስተር ፕላኑ ላይ ውይይት በተደረገበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አዜብ አስናቀ እንደተናገሩት፣ እ.ኤ.አ. እስከ 2017 ድረስ ተግባራዊ በሚደረገው የአጭር ጊዜ ዕቅድ አሮጌ ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ይለወጣሉ፡፡ 

በአጠቃላይ ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ አንድ ቢሊዮን ዶላር በጀት መያዙ ተገልጿል፡፡ ከዚህ ውስጥ እ.ኤ.አ. እስከ 2017 ለሚተገበረው የአጭር ጊዜ ዕቅድ ማስፈጸሚያ 285 ሚሊዮን ዶላር፣ እ.ኤ.አ. ከ2018 እስከ 2022 ተግባራዊ ለሚሆነው መካከለኛ ዘመን ዕቅድ ማስፈጸሚያ 37 ሚሊዮን ዶላር፣ ለረዥም ጊዜ ዕቅድ ማስፈጸሚያ (እ.ኤ.አ. ከ2023 እስከ 2034) 745 ሚሊዮን ዶላር መበጀቱ ተገልጿል፡፡ 

በአጠቃላይ በአዲስ አበባና አካባቢው የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎትና ዕድገት ለማጣጣም የተያዘውን ዕቅድ ለማስፈጸም፣ 1,067 ቢሊዮን ዶላር ይፈጃል ተብሎ ተገምቷል፡፡ 

ፕሮጀክቱ ተግባራዊ የሚደረገው በአዲስ አበባ በሚገኙት አሥር ክፍላተ ከተሞችና በኦሮሚያ ልዩ ዞን በሚገኙት አዲስ ዓለም፣ ኢሉ፣ ወልመራ፣ ሙሎ፣ ሱሉልታ፣ በረህ፣ አሌልቱ፣ ጊምቢቹ፣ አደአ፣ አቃቂ፣ ዓለም ገና፣ ቀርሳና ማሊሞ ወረዳዎች ናቸው፡፡ 

አዲስ አበባና ዙሪያዋ አገሪቱ ከምታመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ 60 በመቶውን እንደሚጠቀሙ ኢንጂነር አዜብ ገልጸው፣ አካባቢዎቹ የሚያጋጥማቸውን የኤሌክትሪክ ኃይል ሥርጭት መቆራረጥ ለማስቀረት የፕሮጀክቱ ተግባራዊ መሆን ወሳኝ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ 

ይህንን ማስተር ፕላን ከአፍሪካ ልማት ባንክ በተገኘ 3.5 ሚሊዮን ዶላር ያጠናው የእንግሊዝ ኩባንያ የሆነው ፓርሳን ብሪንኤርሆፍ ሊሚትድ ነው፡፡ የኩባንያው ተወካይ ናንካ ብሩስ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት፣ አዲስ አበባ በፍጥነት እያደገች በመሆኑ እያጋጠማት ካለው የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ወጥታ፣ ለዕድገቷ የሚያስፈልጋትን ኃይል ለማግኘት ማስተር ፕላኑ ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡ 

ይህ ፕሮጀክት ተግባራዊ ሲሆን፣ በከተማው የሚገኙ አሮጌ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያዎች በአዲስ ይተካሉ፡፡ መሻሻል ያለባቸውም እንዲሻሻሉ ይደረጋል በማለት ኢንጂነር አዜብ ተናግረዋል፡፡ 

በቀጣይነት ይህ ፕሮጀክት በሐዋሳ፣ በመቐለ፣ በባህር ዳርና በሌሎች ትልልቅ የክልል ከተሞች ተግባራዊ እንደሚሆን ኢንጂነር አዜብ አስረድተዋል፡፡ 

በአዲስ አበባና በአካባቢው ለረጅም ጊዜ እያጋጠመ ያለው የኃይል መቆራረጥ፣ በዋናነት በኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያና ማሠራጫ ጣቢያዎች እርጅና ምክንያት ነው ሲባል ቆይቷል፡፡ ነገር ግን ከቅርብ ወራት ወዲህ ለኃይል መቆራረጡ የበልግ ዝናብ በተፈለገው መጠን ባለመዝነቡ ምክንያት፣ ግድቦች በቂ ውኃ ባለመያዛቸው እንደሆነ ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው፡፡ 

 

አውሮፓ ኅብረት ለኤርትራ ቃል የገባው የ312 ሚሊዮን ዩሮ ዕርዳታ እንዲታገድ ጀርመን ጠየቀች

በቅርቡ አውሮፓ ኅብረት ለኤርትራ በዕርዳታ መልክ ሊሰጠው የወሰነው 312 ሚሊዮን ዩሮ ዕርዳታ እንዲታገድ፣ የጀርመን ፓርላማ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡

ሰኔ 4 ቀን 2007 ዓ.ም. የጀርመን የፓርላማ አባላት ባደረጉት ስብሰባ፣ ሰሞኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የኤርትራ ሰብዓዊ መብት አጣሪ ኮሚሽን ያወጣውን ባለ 484 ገጾች ሪፖርት ይዘት አስመልክቶ ከተወያዩ በኋላ፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በአስመራ መንግሥት ላይ ጠንካራ ዕርምጃ እንዲወስድ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

ፓርላማው በኤርትራ ላይ የወጣውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሪፖርት ዝርዝር ለአንድ ሰዓት ያህል ከተወያየበት በኋላ፣ በተለይ ጀርመን ዋነኛ አስኳል የሆነችበት የአውሮፓ ኅብረት ከጥቂት ወራት በፊት ለኤርትራ እ.ኤ.አ. እስከ 2020 በዕርዳታ ሊሰጠው ያቀደው የልማት ድጋፍ እንዲታገድ በፅኑ ጠይቋል፡፡

የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን የኤርትራን ልማት ለመደገፍ በሚቀጥሉት አምስት ዓመት ውስጥ ለመስጠት ቃል የገባው ዕርዳታ 312 ሚሊዮን ዩሮ ነው፡፡ ሒውማን ራይትስ ዎች፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ማኅበር፣ ‹‹የአስመራ መንግሥትን መርዳት በኤርትራ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲቀጥል ማድረግ ነው፤›› በማለት በተመሳሳይ አቋም መቃወማቸው ይታወሳል፡፡

 በኤርትራ ያለውን ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ያጋለጠው የተመድ የሰብዓዊ መብት አጣሪ ኮሚሽን ሪፖርት ከመውጣቱ ቀደም ብሎ፣ ከ20 በላይ የኤርትራ የሚዲያ ተቋማት፣ የሲቪል ማኅበረሰቦችና ተቃዋሚዎች ይህንን የአውሮፓ ኅብረትን ውሳኔ ተቃውመዋል፡፡ የድጋፍ ድምፅ ፊርማ በማሰባሰብ ለተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ማቅረባቸውም ይታወሳል፡፡

ስዊድን ቀደም ሲል በኤርትራ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠያቂ ያለቻቸውን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ጨምሮ፣ የተለያዩ የሲቪልና የወታደራዊ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት እንዲያዙ መወሰኗ አይዘነጋም፡፡

የተመድ የሰብዓዊ መብት አጣሪ ኮሚሽን በ484 ገጾች ባወጣው ሪፖርት፣ የኤርትራ መንግሥት በዜጎች ላይ የሚፈጽማቸው የሰብዓዊ መብት ጥቃቶች ሆን ተብለውና ታስቦባቸው የሚፈጸሙ ናቸው ብሏል፡፡ ድርጊቱም በሰብዓዊ ፍጡር ላይ የሚፈጸም ወንጀል ነው በማለት ያትታል፡፡ 

‹‹የኤርትራ መንግሥት ሕዝቡ ውስጥ በርካታ ሰላዮችን በማስረግ ዜጎችን ይሰልላል፡፡ በሕገወጥ መንገድ ዜጎችን በማሰር የፈለገውን ዕርምጃ ይወስዳል፡፡ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት በመደፍጠጥ ነፃነት እንዳይሰማቸው ያደርጋል፡፡ ተቃውሞ ያስነሳሉ ወይም የተለየ አስተሳሰብ ያንፀባርቃሉ ተብሉ የሚጠረጠሩ ግለሰቦች ለእስር ይዳረጋሉ፡፡ አንዳንዶቹ የት እንደደረሱ ሳይታወቅ ይሰወራሉ…›› ይላል፡፡

 በኤርትራ ወታደራዊ አገልግሎት ከባርነት እንደማይተናነስና ሴቶች ለወሲብ ባርነት እንደሚዳረጉ ሪፖርቱ አመልክቶ፣ ሕዝቡ በፍርኃትና በድንጋጤ ውስጥ ነው የሚኖረው ብሏል፡፡ የኤርትራ መንግሥት ግን ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ የአጣሪ ኮሚሽኑን ሪፖርት መሠረተ ቢስ በማለት አጣጥሎታል፡፡

 

 

የኢትዮጵያ የግብፅና የሱዳን የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ካይሮ ሊገናኙ ነው

የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን መንግሥታት የታላቁ የህዳሴ ግድብን ለመገምገም የቋቋሙት የቴክኒክ ኮሚቴ ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓ.ም. በካይሮ እንደሚገናኙ ተሰማ፡፡

የቴክኒክ ኮሚቴው ከእያንዳንዱ አገር አራት ባለሙያዎች የተወከሉበት ሲሆን፣ ዓላማውም ከዚህ ቀደም ግድቡን የገመገመው ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ሦስቱ አገሮች በጋራ እንዲተገብሯቸው ያቀረቧቸውን ሁለት ምክረ ሐሳቦች ዕውን ማድረግ ነው፡፡ ሁለቱን ምክረ ሐሳቦች ተግባራዊ ለማድረግ በወጣው ዓለም አቀፍ ጨረታ ከተወዳደሩት አምስት ኩባንያዎች መካከል፣ ሁለት ኩባንያዎች ማለትም የፈረንሣዩን ቢአርኤል ግሩፕና የኔዘርላንዱ ዴልታሪዝ በመጨረሻ መቅረታቸው ይታወሳል፡፡

በሚያዝያ ወር በአዲስ አበባ የተገናኙት የሦስቱ አገሮች የኮሚቴ አባላት ሁለት ቀናት የፈጀ ውይይት በማድረግ የፈረንሣዩ ቢኤርኤል ግሩፕ አጠቃላይ ጥናቶችን በበላይነት እንዲያከናውን፣ የኔዘርላንዱ ዴልታሪዝ ደግሞ ከፈረንሣዩ ኩባንያ የተወሰኑ ሥራዎች እንዲሰጠው ተስማምተዋል፡፡

በዚህ ውሳኔ መሠረት ሁለቱ ኩባንያዎች ውሳኔውን እንዲያውቁት ከተደረገ በኋላ፣ ረዥም ቀናት ፈጅተው በግንቦት ወር የቴክኒክ ሰነድ ለኮሚቴው አስረክበዋል፡፡

ይኼ ሰነድ ምን እንደሚያትት ባይታወቅም፣ የሦስቱ አገሮች የኮሚቴ አባላት በዚሁ የቴክኒክ ሰነድ ላይ ከሰኞ ጀምሮ እንዲሚወያዩ ታውቋል፡፡

የዓለም አቀፍ አጥኚዎች ቡድን ቀደም ሲል የሰጠው ምክረ ሐሳብ የግድቡ ኃይድሮ ሲሙሌሸን ሞዴል ማለትም ግድቡ ውኃ የሚይዝበትና የሚለቅበት በተለያዩ የዝናብ ወቅቶች ምን መሆን አለበት የሚለው አንዱ ሲሆን፣ የግድቡ ግንባታ በሦስቱ አገሮች ላይ ሊፈጥረው የሚችለውን የአካባቢያዊና የማኅበራዊ ጥናት ተፅዕኖ ግምገማ ደግሞ ሁለተኛው ምክረ ሐሳብ ነው፡፡

 

ሕልመኛው አውሮፕላን ሠሪ

ከ19 ወራት ያላነሰ ጊዜ የፈጀችውና በሰንዳፋ ዳቢ ጊዮርጊስ ሜዳ ላይ ተንደርድራ ልትበር የነበረችው አነስተኛ አውሮፕላን ባጋጠማት ብልሽት ሳትበር ቀረች፡፡ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ለበረራ ዝግጁ ትሆናለች ተብሏል፡፡ 

ትውልዱ ትግራይ ክልል ዋጅራት አካባቢ ነው፡፡ ያደገው ሐዋሳ ሲሆን የተማረው በአለማያ (ሐሮማያ) ዩኒቨርሲቲ የጤና መኮንንነት ነበር፡፡ ይህን የተማረው አማራጭ ስላጣ እንጂ የልጅነት ሕልሙ አውሮፕላን አብራሪ መሆን እንደነበረ ይናገራል፡፡ 

የ35 ዓመቱ አስመላሽ ዘፈሩ ከ14 ዓመታት በፊት የጤና መኮንን ለመሆን ያስገደደውን አጋጣሚ ለሪፖርተር የገለጸው፣ ለመሥራት አንድ ዓመት ከሰባት ወራት የፈጀችበትን አውሮፕላን ለማብረር እየተዘጋጀ በነበረበት ወቅት ነበር፡፡ አስመላሽ  አውሮፕላን ለማብረር ከልጅነቱ ጀምሮ ሲመኝ ኖሯል፡፡ በትምህርቱ አጥጋቢ ውጤት አምጥቶ ዩኒቨርሲቲ ቢገባም፣ በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ የበረራ ትምህርት የማይሰጥ በመሆኑ የጤና መኮንንነትን ለማጥናት ተገዷል፡፡ ይህም ሆኖ በድሬዳዋ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአብራሪዎች ምልመላ ሲያካሂድ ተመዝገቦ ቢቀርብም፣ ቁመትህ በሚፈለገው ልክ አይደለም ተብሎ ሳይመረጥ መቅረቱን ይናገራል፡፡ 

‹‹ቁመትህ አንድ ሳንቲ ሜትር አጥሯል ተብዬ የአብራሪነት ሕልሜ ሳይሳካ ቀረ፤›› የሚለው አስመላሽ፣ ከ21 ዓመት ዕድሜው ጀምሮ የራሱን አውሮፕላን ሠርቶ የማብረር ፍላጎት እንዳደረበት ተናግሯል፡፡ በዚህ አኳኋን ከጤና መኮንንነት ሙያው ባሻገር የምህንድስና ትምህርት በማታው ክፍለ ጊዜ በመከታተልና ስለአውሮፕላን አሠራር በማጥናት በመጨረሻም ‹‹K-570A›› የሚል ስያሜ የሰጣትንና ሁለት ሰው ማሳፈር የምትችል የድሮ ሞዴል አውሮፕላን ሠርቶ ለማብረር ተቃርቦ ነበር፡፡ ከእናቱ ወይዘሮ ኪሮስ ስም የመጀመርያ የእንግሊዝኛ ፊደል በመውሰድና አውሮፕላኑን ለመሥራት የፈጁበትን 570 ቀናት፣ እንዲሁም ‹‹ኤርክራፍት›› ከሚለው ፊደል የመጀርያውን ተጠቅሞ ለአውሮፕላኑ ስያሜ ሰጥቷል፡፡ 

ባለፈው ሐሙስ ሰኔ 4 ቀን 2007 ዓ.ም. አውሮፕላኗን ከአዲስ አበባ በ40 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ሰንዳፋ ከተማ፣ ዳቢ ጊዮርጊስ በተባለ ሜዳ ላይ አንደርድሮ ለማብረር ዝግጅት በማድረግ ላይ ሳለ፣ ሁለት ጊዜ በተሰበሩበት የአየር መቅዘፊያዎች ምክንያት በረራውን ሳያካሄድ ቀርቷል፡፡ አየር መቅዘፊያውን በጥቂት ቀናት ውስጥ በመሥራት ለሞት አደጋ ሊያጋልጠው የሚችለውን አስፈሪ በረራ በድጋሚ ለመሞከር መወሰኑን አስታውቋል፡፡ 

የመትረፍ ዕድሉ ግማሽ በግማሽ እንደሆነ የሚገልጸው አስመላሽ፣ እስካሁን እልህ አስጨራሽ ጉዞ ማድረጉንና ያለውን ነገር ሁሉ አሟጦ በአቅሙ መሥራት የቻለውን አውሮፕላን ዕውን ማድረጉን በመግለጽ ከማብረር እንደማይመለስ ይፋ አድርጓል፡፡ ለሠራው አውሮፕላን 160 ሺሕ ብር ማውጣቱን፣ ከዚህ አውሮፕላን ውጪ ምንም ነገር እንደሌለው፣ ሙሉ ጊዜውን አውሮፕላን ለመሥራት ሲል ከሥራ ገበታው ራሱን ማግለሉን አስመላሽ ይናገራል፡፡ ከወዳደቁ ቁሳቁሶች፣ 40 የፈረስ ጉልበት ካለው የቮልስ ዋገን ሞተር፣ ከእንጨት፣ ከብረት፣ ከሱዙኪ ሞተር ብስክሌት ጎማዎች፣ ከአልሙኒየምና ከመሳሰሉት ቁሳቁሶች የሠራት አውሮፕላን አንዴ ከበረረች በኋላ ዳግመኛ ስለማትበር ሙዚየም የምትገባ መሆኗን ገልጿል፡፡ የቅርብ ጊዜ ህልሙ ናይጄሪያዊው ወጣት ከውድቅዳቂዎች የሠራትንና በአራት ሜትር ከፍታ ላይ ያበረራትን አውሮፕላን በመብለጥ፣ ተጨማሪ ሜትሮችን ወደ ሰማይ በመንሳፈፍ ለማብረር አቅዷል፡፡ 

እጁን ካፍታታባትና ሙሉ በሙሉ ሜካኒካል በሆነ መንገድ ከምትሠራው አውሮፕላን በተጨማሪ፣ ዲጂታል የሆነና አራት ሰዎችን ማሳፈር የሚችል ዘመናዊ አውሮፕላን የመሥራት ሕልም የሰነቀው አስመላሽ፣ በሰንዳፋ የሠራትን አውሮፕላን ለማበረር ሲሰናዳ የሕይወት አድን ጃኬትም ሆነ ከአየር መዝለያ ፓራሹት አልታጠቀም ነበር፡፡ የሞተር ብስክሌት ሔልሜት በአናቱ ላይ ከማጥለቁ በቀር ለአውሮፕላን አብራሪ የሚመጥን ምንም ዓይነት ቅድመ ዝግጅት አይታይበትም፡፡ ይህ ሁሉ አቅም ስለሌለው እንጂ ሳያስፈልገው ቀርቶ እንዳልሆነ ይገልጻል፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ የሠራት አውሮፕላን በርካታ ማሟላት የሚገባት መሠረታዊ ነገሮች እንደሚቀረም ያምናል፡፡ ይህም ሆኖ አሥር ሜትር ያህል አብርሮ ለማሳረፍ የሚያስችል ዝግጅት ተደርጎባት ነበር፡፡ 

የአስመላሽ አባት አቶ ዘፈሩ፣ ከ90 ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸውና የ11 ልጆች አባት ሲሆኑ፣ አሥረኛው ልጃቸው አስመላሽ ራሱ በሠራው አውሮፕላን እየሩሳሌም እንደሚወስዳቸው ከልጅነቱ ጀምሮ ይነግራቸው እንደነበር ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ አስመላሽን ጨምሮ አብዛኞቹ ልጆቻቸው በሰማይ ላይ መብረርን አጥብቀው የሚመኙ፣ የራሳቸውን መኪና ለመሥራት ሲጥሩ የነበሩ መሆናቸውን ገልጸው፣ አንድ ቀን እየሩሳሌምን የመጎብኘት ሕልማቸው በልጃቸው እንደሚሳካ ተስፋቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ልጃቸው በሠራት አውሮፕላንም ከመደሰት በላይ ለአገሩ የሚያኮራ ሥራ መሥራቱን እንደሚያምኑም ገልጸዋል፡፡ 

  

 

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

በሰላማዊ ትግል ውስጥ ሁለት አብይት የትግል ስልቶች አሉ፡፡ አንደኛው ገለልተኛ የዴሞክራሲ ተቋማትና ህግጋት ባሉበት ነባራዊ ሁኔታ የሚደረግ ህዝብን ያሳተፈ ምርጫ ነው፡፡ ምርጫ ሲባል ዝም ተብሎ ለማስመሰልና የአምባገነኖችን የስልጣን እድሜ ለማራዘሚያነት የሚደረገውን አይጨምርም፡፡ ምርጫ ሲባል ዓለም አቀፍ መመዘኛዎች ያሉት ነው፤ መመዘኛዎችን ባሟላ መልኩ የሚደረግ ምርጫ፣ ምርጫ ሊባል ይችላል፡፡ አምባገነን ስርዓቶች ምርጫ ሲያደርጉ አስተውለናል፤ ግን የይስሙላ ነው፡፡ […]

የገዥው የኢህአዴግ መንግስት በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ ህዝቦችን የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ የተቃዋሚ ድርጂቶች ዲሞክራሲያዊ ናቸው ብላችኋል በማለት ንፁሃን ዜጎችን እያሰረ መሆኑን ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን አስረድተዋል። በአዲስ አበባ ከተማ ጀሞ በተባለው አካባቢ ግንቦት 7 እና ሌሎችም የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ ድርጂቶች ዲሞክራሲያዊ ናቸው የሚል በራሪ ወረቀት መበተኑን ተከትሎ ለጊዜው ስሙ ያልታወቀ የጀሞ አካባቢ ነዋሪ ግንቦት 22 ቀን […]

በጥያቄአቸው፣ በአስተዳደር ይኹን በልማት ሥራ ምንም ችግር የለም ብለዋል፤ በሌለ ልማት! ምእመናኑንም ‹‹ምንም ዓይነት ድርሻ የሌላቸውና ማንነታቸው የማይታወቅ›› ሲሉ ገልጸዋቸዋል የታሰሩት ምእመናን በፖሊስ ጣቢያ ‹‹ማዕተባችኹን በጥሱ መስቀላችኹን አውልቁ›› ተብለዋል የቀድሞው የደብሩ አለቃ ዘካርያስ ሓዲስና ኃይሌ ኣብርሃ ከውዝግቡ ለማትረፍ እያሰሉ ነው የቤተ ክርስቲያን ይዞታ ከቤተ ክርስቲያን አቋም ጋር በሚስማማ እና ሀብቷን በሚያስጠብቅ አኳኋን እንዲለማ በመጠየቅ በቅንጅት …

ኢሳት ዜና (ሰኔ 4 2007 ዓም) የኢትዮጵያ መንግስት በሀገሪቱ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ማፈኑን ተከትሎ የተቃዋሚ ፓርቲዎች “ ቅድሚያ ለነጻነት ” ወደሚል ትግል ማዘንበላቸውን የእንግሊዝ ዘ-ጋርዲያን ጋዜጣ ሐሙስ ለንባብ ባበቃው እትሙ ዘገበ። ገዢው የኢሃዴግ መንግስት በቅርቡ በተካሄደው ብሄራዊ ምርጫ በብቸኝነት ለድል መብቃቱም በመንግስት ላይ ጥያቄ ያላቸው አካላት ሌሎች አማራጮችን እንዲመለከቱ ማስገደዱንም ጋዜጣው በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ …

ጃሚዮ በተባለ መንደር የሚኖሩ ነዋሪዎች በሁለቱ ሃይሎች መካከል ከፍተኛ ጦርነት መካሄዱንና ከባድ የጦር መሳሪያዎች ሲተኮሱ መስማታቸውን ተናግረዋል።አልሸባብ አገኘሁት ያለውን ድል በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል የተበባለ ነገር የለም። ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ሆርሲድ ሚዲያ እንደዘገበው ደግሞ የአልሸባብ ተዋጊዎች የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን የጫኑ ወታደሮችን አድፍጠው በመጠበቅ ጥቃት ፈጽመዋል።ለ12 ሰአታት ያክል የቆየ በከባድ መሳሪያዎች የታጀበ ጦርነት መካሄዱን ነዋሪዎች ገልጸዋል። አልሸባብ […]

ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ እንደዘገበው በማእከላዊ ሶማሊያ በተደረገው ጦርነት ታጣቂ ሃይሉ 30 የኢትዮጵያ ወታደሮችን መግደሉን አስታውቋል። ጃሚዮ በተባለ መንደር የሚኖሩ ነዋሪዎች በሁለቱ ሃይሎች መካከል ከፍተኛ ጦርነት መካሄዱንና ከባድ የጦር መሳሪያዎች ሲተኮሱ መስማታቸውን ተናግረዋል። አልሸባብ አገኘሁት ያለውን ድል በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል የተበባለ ነገር የለም። ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ሆርሲድ ሚዲያ እንደዘገበው …

በደቡብ አፍሪካ የሚደረገዉን የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ለመካፈል ወደዚያዉ ያመራዉ የወያነኔ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቴድሮስ አድሐኖም በጆሐንስበርግና በፕሪቶሪያ ዙሪያ እንዳይዘዋወሩ ጥብቅ መልእክት ከወያኔ መረጃ ቢሮ በፕሪቶሪያ ለሚገኘዉ የወያኔ ኢንባሲ መተላለፉን ከዉስጥ የወጣ መረጃ አመለከተ፤ ተላላኪዉ ቴድሮስ አድሐኖም በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ የወያኔ ደጋፊዎችን ሰብስቦ ሊያነጋግር በሞባይል ስልክ መልክት (text)እያደረገ ሳንድተን ሪክሬሽን ሴንተር ቀጠሮ እያስያዘ መሆኑን የደረሱበት በደቡብ […]

ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል የሥነምግባርና የጸረ ሙስና ኮምሽን የመንግስት ተሿሚዎችን፣ ተመራጮችንና የመንግስት ሠራተኞች ሃብት የመመዝገብ ሥራዎችን ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ እያከናወነ ቢሆንም ባሉበት ጫናዎች ምክንያት መረጃውን ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ አለመቻሉን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቆሙ፡፡ ኮምሽኑ የባለስልጣናትን ሀብት እንዲመዘግብ ስልጣን ሲሰጠው በመንግስትና በሕዝብ መካከል መተማመን ይፈጥራል ተብሎ ነው፣ ይሁን እንጅ ኮምሽኑ …

ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ለ3 ቀናት በደብረ ዘይት ከተማ በተካሄደው ግምገማ ባለስልጣኖቹ እርስ በርስ ሲወነጃጀሉ እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የመገምገሚያ ነጥቦቹ “አመራሮቹ በየምርጫ ምደባቸው የነበራቸው ውጤታማነትና ውስጣዊ ስኬት፤ በተቋማቸው የነበረው የኪራይ ሰብሳቢነት ትግልና የተመዘገበ ውጤት፣ እንዲሁም ግለሰባዊ ድክመታቸው ” የሚሉ ሲሆኑ፣ በግምገማውም ባለስልጣኖቹ ከኤ እስከ ዲ ያሉ ውጤቶችን …

ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት15 ምርጫ ከመካሄዱ 2 ሳምንት በፊት መንግስት ዋና ዋና የሚባሉ የምግብ ሸቀጦች ዋጋ እንዲቀንስ ቢያደርግም ፣ ከምርጫው በሁዋላ ተመልሶ መውጣቱን ዘጋቢያችን ገልጿል። ምስር በኪሎ ከ50 ብር በላይ፣ በርበሬ ከ120 ብር በመሸጥ ላይ መሆኑን የገለጸው ዘጋቢያችን፣ ዘይትና ስኳር ተመልሰው ከገበያ መጥፋታቸውን የስጋና የወተት ምርቶች እንዲሁም በሁሉም የእህል ዘሮች …

ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ረቡዕ 200 ኢትዮጵያውያንን የጫኑ 2 ጀልባዎች ከ24 ሰአታት የባህር ላይ ጉዞ በሁዋላ ጅቡቲ በሰላም ደርሰዋል።ኢትዮጵያውያኑ የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ወደ አዲስ አበባ ይጓጓዛሉ። በየመን አሁንም በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ። በአገሮቱ ከሚኖሩት ከ80 ሺ በላይ ስደተኞች መካከል ወደ አገራቸው ለመመለስ ፍላጎት ያሳዩት ከ2 …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)